Wednesday, April 24, 2013

የኢትዮዽያ ውስጥ ያለውን ጓንታናሞ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ምርመራ ሊያደርግበት ይገባል!

    
By: Meranu Habibty
ከባራክ ኦባማ ቀደም ብሎ አሜሪካንን ለ8 አመታት የገዛው ጦረኛው ጆርጅ ዊሊያም ቡሽ ከሂትለር የሚሻለው በጥቂቱ ነው፡፡ ሂትለር ኦሺዊትዝ የሚባል ካምፕ ገንብቶ በርካታ ሚሊዮን አይሁዶችን ከነነፍሳቸው እቶን እሳት ውስጥ እያስገባ ሲጨርሳቸው አለም በአንድ ግንባር ተነስቶ የሂትለርን ርእዮትና አስተዳደር ከገምድረ ገፅ ለማጥፋት ግራና ቀኝ ማየት አላስፈለገውም ነበር፡፡ አሁን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ሌላኛው ጦረኛ ጆርጅ ዊሊያም ቡሽ በአፍጋኒስታን “ባግራም” የተባለ ማሰቃያ ካምፕ፣ በኢራቅ “የአቡ ግሬብ”እስር ቤትን ና ሌላኛውን ደግሞ በኩባ ጓታናሞ የተባለውን አሰቃቂ እስር ቤት ገንብቶ በርካታ ሰዎችን በሚዘገንን ሁኔታ ሲያሰቃይ ይህን የሚያውቁ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ጆርጅ ቡሽ ከላይ በተለያዩ ሃገራት በገነባው ማሳቃያ እስር ቤቶች ውስጥ እስረኞች በሚጠብቋቸው ወታደሮች ከሚያደርሱባቸው አሰቃቂ ድብደባና ግርፊያ በተጨማሪ በቀጥታ ከጆርጅ ቡሽ አስተዳደር በሚታዘዙ መርማሪዎች አማካኝነት ጥፍር ግሽለጣ፣ ሰውነትን በኤሌክትሪክ ሾክ በማድረግ፣ የሚያናዝዝ መርፌ በመውጋት፣ሰብአዊ ክብርን በመድፈርና(ወታደሮቹ እስርኞቹ ላይ ነውር በሆነ ሁኔታ ወሲብ እንዲፈፀምባቸው በማድረግ፣ በአደገኛና ተናካሽ በሆኑ ውሾቻቸው ማስነከስ ወዘተ ) አይነቶች ማሰቃያ ዘዴዎች በመጠቀም ከሂትለር ቀጥሎ ይቅር የማይባሉ “ወንጀለኞች” የሚያስብላቸውን ድርጊት ሲፈፅሙ ቆይተዋል፡፡ ምስጋና ለቴክኖሎጂ ይሁንና ይህን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእስረኞችን አያያዝ በሚመለከት ያወጣውን ህግ በሚጥስ መልኩ የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር በጓንታናሞ፣ በባግራምና በአቡ ግሬብ እስር ቤቶች ሲፈፅሙት የነበረው ህገወጥ ድርጊት በራሳቸው ወታደሮች ሞባይሎች ተቀርፀው በYoutube ፣goole ፣Face book እና Twitter ድረ ገፆች ላይ ለአደባባይ በመብቃታቸው፣ እንዲሁም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ነገሩን ተቀባብለው በመዘገባቸው አለም ጆርጅ ቡሽን ስለሰብአዊ መብት አያያዝ የመናገር ምንም አይነት ሞራል እንደሌለውና ቢናገርም አዳማጭ እንደሌለው አስረግጠው ነግረውታል፡፡ ከሁሉም በላይ የአሜሪካንን ክብርና ተሰሚነትም አውርዶት እንደነበር የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበውት ነበር፡፡ በተለይ በጓንታናሞ እስር ቤት የሚፈፀሙት ህገወጥ ምርመራዎችና ሌሎች አሰቃቂ የሰብአዊ ጥሰቶችን የሚያሳዩ በድብቅ የተቀረፁ ቪዲዮዎች በየድረገፁ ይፋ መደረጋቸውና ይህን ተከትሎ አለማቀፍ ጫናዎች በመብዛታቸው አሜሪካ ጓንታናሞ የሚባለውን እስር ቤት ለመዝጋት የወሰነችበትን አጋጣሚን ፈጥሯል፡፡
ወደሃገራችን ስንመጣም ከሚኒሊክ አደባባይ ወደ ሰሜን ሆቴል በሚወስደው አስፋልት ግማሽ ኪሎ ሜትር የማይሞላ መንገድ እንደተጓዙ በተለምዶ ማእከላዊ የሚባል እስር ቤት ያገኛሉ፡፡ ይህ እስር ቤት ከባባድ ወንጀል የፈፀሙ እስረኞች ግዜያዊ ማረፊያ በሚል የዳቦ ስም ቢሰጠውም በከባድ ወንጀል ስም የሚገቡ እስረኞችን የሚበላና የጓንታናሞ አይነት ማሰቃያ መጋዘኖች ያሉበት የምድር ጀሃነም(ገሃነም) አይነት ነው፡፡ ይህን መንግስት የሚተቹ የሃይማኖት አባቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና ግለሰቦች የትም ሳይሆን እዚህ ቦታ ተወስደው በፊልም ላይ ያዩትን ማሰቃያ ሁላ ያገኙታል፡፡ ሰው መሆን እስኪያስጠላዎት ድረስና በሃገሪቱ ህግ የሌለ እስኪመስልዎት ድረስ ሰውነትዎ ላይ የማያርፍ የማሰቃያ አይነት የለም፡፡ ከኤሌክትሪክ ሾክ ማድረጊያ እስከ ደም የጠማው ድቡልቡል ዱላ ድረስ፡፡ በሽተኛ መሆንዎ ከታወቀማ አበቃ!ህመምተኛ የሆኑበት ቦታ ተፈልጎ ይቀጠቀጣል፡፡ በአፍዎ ውስጥ አሮጌ ቆሻሻ ጨርቅ ይወተፍብዎትና ያለገላጋይ ተገልብጠው ይታሻሉ፡፡ አፍዎ ውስጥ የተወተፈው አሮጌ ጨርቅ 20 አመት ሙሉ በማእከላዊ እስር ቤት የገቡ ሁሉ የተጠቀሙበት ነው፡፡ አንዱ በማእከላዊ እስር ቤት የነበረ እስረኛ ከታሰረ 2 አመት በኋላ ተመልሶ ሲገባ ያንኑ አፍ ውስጥ የሚወትፉትን ማፈኛ መልሰው እንደወተፉበት በአንድ መፅሄት ላይ የፃፈውን ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ አሁን ሰውየው ከሃገር ስለወጣ ምናልባት ድጋሚ ያ ጨርቅ ለ3ኛ ግዜ የሚወተፍበት አይመስለኝም፡፡ እሱ ውስጥ ተወትፎ የነበረው ቆሻሻ ጨርቅ ግን በሌላው ባለ ተራ አፍ ውስጥ ይወተፍበታል፡፡ ደብዳቢዎቹና እንዲደበድቡ ያዘዛቸው አካል የሚፈልጉትን እስኪያገኙ ድረስ ምግብ ሳይሆን ኢሰብአዊ ድርጊት ነው የሚመግብዎት፡፡ በጨለማ ክፍል ተዘግቶብዎት ሰውም አይጎበኝዎ፣ ፀሃይም አይሞቁ፡፡ ሌላው ቢቀር ቀኑ ማን እንደሆነና ሰዐቱ ስንት እንድሆነ እንኳ አያውቁትም፡፡ ቀኑ ማን እንደሆነና ሰዐት ስንት እንደሆነ ማወቅ የቅንጦት ያህል ነው፡፡ የሚገርመው ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ለምርመራ መስልዎት ከሆነ ተሳስተዋል፡፡ ሲጀመር የተያዙት ያለ ወንጀል እንደሆነ የያዘዎት አካል ድብን አድርጎ ያውቀዋል፡፡ የሚደበደቡበት ዋናው ጉዳይ የያዘዎት አካል ዝም ብሎ ያዘ እንዳይባል መንግስትን በሃይል ለመገልበጥ ሳሴር ነው የተያዝኩት ብለህ እመን ነው ያ ሁላ ውርጅብኝ፡፡ በማእከላዊ 3 አይነት ደረጃ እንዳለው አንብቤያለሁ፡፡ 1ኛው ደረጃ ሲቀጠቀጡ ያድሩና ሲነጋ ከማንም ጋር የማየገናኙበት ጨለማ ክፍል ያሉባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ እስረኛ ጋር አይገናኙም፡፡ 2ኛው ደረጃ ስቃዩ በከፊል አለ ሆኖም አብረው ሌሎች ተገራፊዎችን በአንድ ክፍል ያገኛሉ፡፡ 3ኛው ደረጃ ደግሞ ደብዳቢዎ አካል ወይ የሚፈልገውን አግኝቶ፣ ወይም ደግሞ በርስዎ ጥንካሬ ተስፋ ቆርጦ ወይም አለማቀፉ ማህበረሰብ ሲጮህበት ፀሃይ የሚሞቁበት፣ ጨለማ ያልሆነ ክፍል፣ከሌሎች እስረኞች ጋር እንድልብ የሚያወሩበት ቦታዎች ናቸው፡፡ በማእከላዊ (ይቅርታ ጓንታናሞው ማለቴ ነው) አንዳንዴ እንኳን ተገርፈው ተገልምጠውም ያላደረጉትን ይለፈልፋሉ፡፡ከዚህ በፊት በ97 ላይ እኔ ነኝ ያለ የተቃዋሚዎቹ ወሬ ነጋሪ የነበረ አንድ ግለሰብ (ፕሮፖጋንዳ ሃላፊ የነበረ ልበለው ይሆን?) በጣም ገልምጠውት ነው መሰለኝ ተልፈስፍሶ ከዱላው በፊት በአንድ ተራ ግልምጫ ብቻ ያላደረገውንና ያላሰበውን ሁሉ አድርጊያለሁ ብሎ በማግስቱ በኢቲቪ አኬልዳማ ፊልም ላይ አጠገቡ ማኪያቶ ቀርቦለት ከደህንነቶችቹ ጋር እየተሳሳቀ በውጭ ያሉ ተቃዋሚ ጓደኞቹን ሁላ ስም እየጠራ ሲሳደብ አይቼ ትንሽ ገርሞኝ ነበር፡፡ ነገሩ የገባኝ አሁን ነው፡፡ በሱም አልፈርድም፡፡ ማእከላዊ ገቡ ማለት ህግ ሳይሆን የሚያናግርዎት ሌላ ስለሆነ የማያውቁትን ስም እየጠሩ እሱ ልኮኝ፣አዞኝ፣ ቦንብ አፈንድቼ፣ ቦንም ቀምሜ፣ አውሮፕላን ላጋይ ስል፣ በቤተ መንግሱ የኋላ በር ገብቼ ጠቅላይ ሚስትሩን ልጠልፍ ስል፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መስኮት በኩል ገብቼ የህገ መንግስቱን ዋናውን መፅሃፍ ሰርቄ ለዲያስፖራ ልሸጥ ስል ነው የተያዝኩት እያሉ መለፍለፍዎ አይቀርም፡፡
እንግዲህ የኛዎቹ(የኢትዮፕያውያኖቹ ) የእድሜ ልክ ጀግኖች የሆኑት ኮሚቴዎቻችንም በዚህ የነጓንታናሞ ጓደኛ ከሆነው እስር ቤት ገብተው ኢሰብአዊና አሰቃቂ ድርጊት ሲፈፀምባቸው ከነበሩት ዜጎች መካከል ናቸው፡፡ ለወራት ያህል ሊነገር እንኳ የሚያሰቅቅ ማሰቃያና ግርፊያ ሲደረግባቸው ነበር የቆየው፡፡ በግለሰቦቹ ታላቅ ሰብእናና ጥንካሬ እንዲሁም አላህ ረድቷቸው የያዛቸው አካል ከነሱ የሚፈልገውን ሳያገኝ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ቢዘዋወሩም ድርጊት ግን ዝም የሚያስብል አይደለም፡፡ ኢትዮፕያዊያን በሙሉና አለም አቀፍ ማህበረሰቡ ማእከላዊ እንዲዘጋ ወይም አያያዙን እንዲያስተካክል፣ እንዲሁም በዚያ ገሃነም እስር ቤት ውስጥ ድብደባ ሲፈፅሙና ሲያስፈፅሙ የነበሩት ሁላ ለፍርድ የሚቀርቡበትን ሁኔታ ማጤን አለባቸው፡፡ አለማቀፉ ማህበረሰብም በኢትዮፕያ ህዝብ ስም የሚሰጡትን ብድሮች የራሱን ሃገር ዜጎች የሚያሰቃይበትን ካምፖች መገንቢያና ለአሰቃዮችም ጡንቻ ማፈርጠሚያ ላይ እንደማይውል ማረጋገጥ አለበት፡፡ አለበለዚያ በዚህ ከቀጠለ ሃገሪቱ ሌላኛዋ በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ የትርምስ ሃገር እንዳትሆን ያሰጋል፡፡ ሁል ጊዜ ማንም እንደበሬ እየተጎተተ የሚታረድ የለምና፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ ለሃገሪቱም ሆነ ስትራቴጂክክ ወዳጅ ለሆኑ ሃገራት የሚፈለግ አይደምና፡፡ አላህ ሀገራችንን ከአምባገነኖች ነፃ ያድርግልን፡፡ ኮሚቴዎቻችንን ጨምሮ ያለ ወንጀል የታሰሩትን ኢትዮፕያውያን ነፃ ያውጣልን፡፡ ድልም ገኛ ጋር ይሁን፡፡ አሚን፡፡

Tuesday, April 23, 2013

ነጻነትን ከነጻ አውጭዎች የምንጠብቅበት ጊዜ ላይ አይደለንም!

Untitled g7
Untitled g7
ነጻነት እኛ ሰዎች በልደት ወደዚህ አለም ስንመጣ አብሮን የሚመጣ የተፈጥሮ ፀጋ ነዉ። ነጻነት ከሌሎች የምንጠብቀዉ ወይም ማንንም ስጠን ብለን የማንጠይቀዉ ፈጣሪ ለእያንዳንዳችን ያደለንን፤ በዚህ አለም ቆይታችን ለደቂቃም ቢሆን እንዲለየን መፍቀድ የሌለብን ኃብት ነዉ። ነጻነታችን እጃችን ላይ ሲኖር በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበት፤ እንዳንቀማ በጋራ የምንጠብቀዉና እንደወያኔ አይነቱ ፀረ ህዝብ ኃይል ሲቀማን ደግሞ በጋራ ታግለን ማስመለስ የሚገባን የግልና የጋራ ኃብት ነዉ። ዛሬ ከ21 የወያኔ አመታት በኋላ እኛ ኢትዮጵያዉያን በድህነትና በረሀብ የምንጠቃዉ፤ በዘረኝነት አለንጋ የምንገረፈዉ፤ የምንሰደደዉ፤ የምንታሰረዉና የምንገደለዉ ይህንን ፈጣሪ ያደለንን ነጻነት የሚባል ኃብት ወያኔ አንድ፤ ሁለትና ሦስት እያለ ሲቀማን አፋችንን ዘግተንና እጃችንን አጥፈን ስለተመለከትን ነዉ። መፈናቀላችን፤ ስደታችን፤ ዉርደታችንና በገዛ አገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖራችን እንዲያበቃ ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ ሌሎች መጥተዉ ነጻ ያወጡናል ከሚለዉ አመለካከት ተላቅቀን ነጻነታችንን ለማስመለስ ህዝባዊ ትግሉን መቀላቀል ብቻ ነዉ።
ነጻነታችንን የቀሙን የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን እንደቀሙን ለረጂም አመታት ለመግዛት እንዲመቻቸዉ በዘር፤ በቋንቋ፤ በክልልና በሐይማኖት ከፋፍለዉን ከሃያ አንድ በፊት በኢትዮጵያ ሀዝብ ላይ ጀመሩትን እስራት፤ ስደት፤ ግድያና ዝርፍያ አሁንም እንደቀጠሉ ነዉ። የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን ቀምተዉ እየገዙን ቢሆንምገዛናቸዉ ብለዉ እጃቸዉን አጣጥፈዉ አልተቀመጡም። ዜጎች ነጻነታቸዉንና መብታቸዉን እንዳይጠይቁ አፋቸዉን ያዘጋሉ፤ አንዱ ለሌላዉ አንዳይቆም አገር፤ ባንዲራና ኢትዮጵያዊነት የሚባሉ ትላልቁቹን የጋራ እሴቶቻችንን በየቀኑ ያፈርሳሉ። ይህ የሚያሳየን ዜጎች ትልቅተስፋይዘዉ፤ ቤተሰብ መስርተዉ ለራሳቸዉና ለአገራቸዉ የሚኖሩበት ግዜ እየጠፋ ተስፋ መቁረጥ፤ ስደትና የመከራ ኑሮ ዘመን እየከበበን መምጣቱን ነዉ። ይህ ከሆነ የነገዋንየነጻነት፣ የፍትህ፣ የዴሞክራሲባለጸጋ ኢትዮጵያንለማየትእያንዳንዱዜጋበቻለው አቅሙሁሉጠንክሮበመታገል እና ከራሱባለፈሌላውዜጋ የነጻነት ትግሉንጎራእንዲቀላቀል ብሎም የዚህትግልባለቤት እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡የሀገራችን ህዝብ የነጻነት ችቦ አቀጣጣይ የትግሉአካልበመሆንመስራት እንጅ፣ ከቶ ሌላ አካል፣ ሌላ ሃይል መጦ ነጻ ያወጣኛል በሚል በባርነት እየተገዛ መጠበቅ የለበትም። ነጻነትናዴሞክራሲ በችሮታ አሊያም ከሰማይ እንደሚወርድ መና የሚጠበቅ ስጦታ አይደለም። ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል። አለበለዚያ “ላምአለኝበሰማይወተትዋንምአላይ” እንዳይሆን ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ የዘር በትር አለንጋ የሚደርስበት ግርፋት፣ ስቃይ፣ ርሃብ፣ ስደት፣ እንግልት በራሱ በህዝቡ ላይ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ራሱ ለራሱ ነጻነት፣ በእምቢ አልገዛም ባይነት የሚነሳበት ጊዜው አሁን ነው። ነጻነትን ከነጻ አውጭዎች በመጠበቅ እስከመቼ የወያኔ የጥይት ሰለባዎች እንሆናለን?
ወገንሁሉለራሱ ነጻነት፣ ህልውና ሲል የለውጡ እንቅስቃሴ ታጋይ የመሆን ኢትዮጵያዊግዴታውንእንዲፈጽምጥሪ እናደርጋለን፡፡ለአገሩ፣ ለማንነነቱ መሰዋእትነት ለመሆንእንደሚኮራሁሉአገሩም በሱ ትኮራለች ፡፡
በርግጥ ነው በህወሃት/ኢህአዴግ የአሰቃቂ ዘመናት ስለአገራችንየፖለቲካጉዳይማሰብና መናገር ወንጀልና ሽብርተኛ አስደርጎበጠራራፀሐይ የሚታሰሩበትናበግፍየሚገደሉበትጊዜነው።ይህንንአድርገሃልተብሎሳይሆንይህንንሳታስብአትቀርምተብሎያለምንምህጋዊናበቂምክንያትወጣቶች፣ አረጋውያንያለጊዜያቸው፣ያለዕድሜያቸውበከንቱአልቀዋል።በቅርቡም ደግሞ በአማራው ተናጋሪ የተጀመረው ዘርን የማጥፋት ዘመቻ አንዱ ነው። ስለዚህ እስከ መቼ ነው ለራሳችን ነጻነት ሌላ አካል ነጻ እስኪያወጣን የምንጠብቀው? ከዚህ በላይ ምን ስቃይ አለ? ሀገር የጠፋች እለት ምን ሊውጠን ይችላል።
እማማ ኢትዮጵያ ለልጆቿ ህልውናዋን ከመፍረስ አደጋ እንዲጠብቋት፣ ከወያኔ የዘርና ዘረኝነት አደጋ እንዲታደጓት ስትማጸን፤ ልጆቿ ደግሞ አንዳች ሃይል መጥቶ ነጻነታቸውን ያጎናጽፋቸው ዘንድ የኢትዮጵያ አምላክ እያሉ ሲጠባበቁ እስከ መቼ? ስለዚህ ወጣት ጎልማሳ አዛውንት ሽማግሌ ዘር ጾታ ሳይለይ የዛሬ የነጻነትህ ትግል ጅማሮ እጅህ ላይ ነው። ሀገራችንየዛሬውንየወያኔን ጨለማሸኝታ የነገውንየነጻነት ብርሃንእየጠበቀችብቻሳይሆንእየናፈቀችአለች።ያንንድቅድቅጨለማሰንጥቆየሚወጣ የወጣት ጀግኖች ልጆቿንብርኃንትናፍቃለች።እናም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የብርሃኑመታያችቦ ሆኖ ታሪክ ይሰራ ዘንድ ለነጻነቱ የሚታገልበትና ትግሉን የሚቀላቀልበት ሰአት እየፈጠነ፣ እየቆጠረ፣ እየቀረበ ነውና ተነስ ባለህበት ያለህን አንሳና ወርውር፣ አቀብል።
ቋንቋችን አንድ ነው ለነጻነትህ ታገል! በማንነትህ በብሄር ምክንያት በተወለድክበት ሀገር፣ ቀዪ አትሰደድ! በሀገርህ ምድር እንደ ሁለተኛ ዜጋ የመኖሪያ ፈቃድ ጠያቂ አትሁን! ወንድምህ፣ እህትህ፣ አባትህ እናትህ ባልሰሩት ወንጀል ወደ እስር ቤት ሲታጎሩ፣ ሲገደሉ ዝም ብለህ አትይ! በሀገርህ ስብእና ክብርህ ተዋርዶ አትመልከት! ተነስና መብራቱን አብራ! ጀግኖች መከታ ሊሆኑህ ከጎንህ ተሰልፈዋል።
በአሁኑወቅትአያሌኢትዮጵያዉያንወያኔንለመታገልመሳሪያካነሱከነጻነት ታጋዮችጋርበየቀኑእየተቀላቀሉቢሆንም፤ ሀገር ውስጥ ያላችሁ እለታዊ ኑሮን ለማሸነፍ ስትሉ በየፋብሪካው በመንግስት ሴክተሩ እና ሌሎች ተቋማት የምትገኙ ሁሉ በድጋሜ ግንቦት 7 እንደሁሌው ሁሉ የውስጥ አርበኛ ሆናችሁ የነጻነት ትግሉን መቀላቀል፣ ራሳችሁንና ሀገራችሁ ከወያኔ የዘረኛ ማዳፍ እጅ ነጻ ትወጣ ዘንድ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ትግሉን ቀጥሉበት። ፍርሃታችሁን በጥሳችሁ በመደራጀትና መረጃ በማስተላለፍ ግዴታችሁን ተወጡ። ለሀገራችሁ ቅርብ ሁኑ! ለነጻነት ትግሉ፤ የትግልስልትናየተለየየትግልቦታሳትመርጡወያኔንያስወግዳልበምትሉትስልትናይመቸናልበሚሉትቦታሁሉእስከመጨረሻው ትታገሉ ዘንድ አደራችን ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬም ቢሆን የህዝባችን ሰበአዊ መብትና ነጻነትንገፈውሕግንያፈረሱ ህገ አራዊት የሆኑትን ወያኔዎች ከሀገራችን ምድር ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ በማስወገድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖርባትን ሀገር ለመመስረት የሚያደርገውን የትግል ጉዞ ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!