Wednesday, March 6, 2013

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ

fisherman
 የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው
 
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።
ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።

ኡሞት ኡዶል (ፎቶ: ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ)
አቶ ኡሞት በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነትም አላቸው። ኢህአዴግ ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ በክልሉ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ አጥብቀው በግልጽ የሚቃወሙ ሰው መሆናቸውን የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አቶ ኡሞት ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ህዝብን የሚያስተባብሩና ለዓመጽ የሚያነሳሱ ናቸው በሚል ኢህአዴግ ቢወነጅላቸውም ውንጀላውን በማስረጃ ማቅረብ እንደማይችል እነዚሁ ክፍሎች ይገልጻሉ

ባለፈው አመት የአሳሳ ግርግር የታሰሩ ከ45 በላይ ሙስሊሞች ተፈረደባቸው፡፡

ፍርዱ ከሁለት አመት እስከ አስራ አንድ አመት ይዘልቃል፡፡
ባለፈው ዓመት በኦሮሚያዋ አርሲ ዞን አሳሳ ከተማ ፖሊስ በመስጊድ ውስጥ ባስነሳው ግርግር ታስረው የነበሩ ወደ 48 የሚደርሱ የከተማዋ ሙስሊሞች ከፍተኛ ፍርድ ተፈረደባቸው፡፡ ውሳኔው የመንግስትን ጸረ ሙስሊም እንቅስቃሴ ገላጭ ተብሎለታል፡፡ በወቅቱ በተነሳው ግርግር የአራት ንጹሀን ሰዎች ሕይወት በፖሊስ ጥይት መጥፋቱ የሚታወስ ሲሆን በግርግሩ ሰበብም የታሰሩ ሴቶችን ጨምሮ ወደ 53 የሚጠጉ ሙስሊሞችም በሻሸመኔ ወህኒ ቤት የይስሙላውን ፍ/ቤት ጉዳይ ሲከታተሉ ቆተው ዛሬ የመጨረሻ ፍርድ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከ53 ታሳሪዎች 2 ሴት እና 3 ወንዶች በጥቅሉ 5 ሰዎች ከአንድ አመት እስር በኋላ በነጻ ሲሰናበቱ የጠቀሩት 48 ሙስሊሞች ከሁለት አመት እስከ አስራ አንድ አመት በሚዘልቅ እስር ብይን ተሰጥቶባቸዋል፡፡በባለፈው አመት የአሳሳ ግርግር የታሰሩ ከ45 በላይ ሙስሊሞች ተፈረደባቸው፡፡
ፖሊስ ግርግሩ እንዲነሳ ምክንያት አድርጎ የጠቀሳቸውና የህጻናት የቁርአን አስተማሪ የሆኑት ሼኸ ስኡድ ይህ ነው በማይባል ማስረጃ አስራ አንድ አመት ከሦስት ወር የተፈረደባቸው ሲሆን፣ ሼኸ አብደላ ኪኒሶ ሶስት አመት ከስድስት ወር፣ ሼኸ ሁሴን ሶስት አመት ከስድስት ወር የተፈረደባቸው ሲሆን የተቀሩት 45 ሙስሊሞች እያንዳንዳቸው የሁለት አመት ከሶስት ወር እስር ተበይኖባቸዋል፡፡ የዛሬውን ችሎት ለመታደም በሻሸመኔና ዙሪያዋ የሚገኙ በርካታ ሰዎች የተገኙ ሲሆን የፍ/ቤቱ ውሳኔ ሲሰማም በአካባቢው ከፍተኛ የሀዘን ድባብ ተፈጥሮ እንደነበር ተሰምቷል፡፡
በፎቶው ላይ የሚታዩት በዛሬው እለት ብይን የተሰጠባቸው የአሳሳ ሙስሊሞች ናቸው፡፡
አላሁ አክበር!

Human Rights Watch World Report 2013 – Ethiopia




     ETHIOPIA

   Source: Human Rights Watch World Report 2013, pp 114-120
The sudden death in August 2012 of Ethiopia’s long-serving and powerful prime minister, Meles Zenawi, provoked uncertainty over the country’s political transition, both domestically and among Ethiopia’s international partners. Ethiopia’s human rights record has sharply deteriorated, especially over the past few years, and although a new prime minister, Hailemariam Desalegn, took office in September, it remains to be seen whether the government under his leadership will undertake human rights reforms.
Ethiopian authorities continued to severely restrict basic rights of freedom of expression, association, and assembly in 2012. Thirty journalists and opposition members were convicted under the country’s vague Anti-Terrorism Proclamation of 2009.The security forces responded to protests by the Muslim community in Oromia and Addis Ababa, the capital, with arbitrary arrests, detentions, and beatings.
The Ethiopian government continues to implement its “villagization” program: the resettlement of 1.5 million rural villagers in five regions of Ethiopia ostensibly to increase their access to basic services. Many villagers in Gambella region have been forcibly displaced, causing considerable hardship. The government is also forcibly displacing indigenous pastoral communities in Ethiopia’s Lower Omo Valley to make way for state-run sugar plantations.
Freedom of Expression, Association, and Assembly
Since the promulgation in 2009 of the Charities and Societies Proclamation (CSO Law), which regulates nongovernmental organizations, and the AntiTerrorism Proclamation, freedom of expression, assembly, and association have been increasingly restricted in Ethiopia. The effect of these two laws, coupled with the government’s widespread and persistent harassment, threats, and intimidation of civil society activists, journalists, and others who comment on sensitive issues or express views critical of government policy, has been severe. Ethiopia’s most important human rights groups have been compelled to dramatically scale-down operations or remove human rights activities from their man dates, and an unknown number of organizations have closed entirely. Several of the country’s most experienced and reputable human rights activists have fled the country due to threats. The environment is equally hostile for independent media: more journalists have fled Ethiopia than any other country in the world due to threats and intimidation in the last decade—at least 79, according to the Committee to Protect Journalists (CPJ).
The Anti-Terrorism Proclamation is being used to target perceived opponents, stifle dissent, and silence journalists. In 2012, 30 political activists, opposition party members, and journalists were convicted on vaguely defined terrorism offenses. Eleven journalists have been convicted under the law since 2011.
On January 26, a court in Addis Ababa sentenced both deputy editor Woubshet Taye and columnist Reeyot Alemu of the now-defunct weekly Awramaba Times to 14 years in prison. Reeyot’s sentence was later reduced to five years upon
appeal and most of the charges were dropped.
On July 13, veteran journalist and blogger Eskinder Nega, who won the prestigious PEN America Freedom to Write Award in April, was sentenced to 18 years in prison along with other journalists, opposition party members, and political
activists. Exiled journalists Abiye Teklemariam and Mesfin Negash were sentenced to eight years each in absentia under a provision of the Anti-Terrorism Law that has so far only been used against journalists. Andualem Arage, a member of the registered opposition party Unity for Democracy and Justice (UDJ), was sentenced to life for espionage, “disrupting the constitutional order,” and recruitment and training to commit terrorist acts.
In September, the Ethiopian Federal High Court ordered the property of Eskinder Nega, exiled journalist Abebe Belew, and opposition member Andualem Arage to be confiscated.
On July 20, after the government claimed that reports by the newspaper Feteh on Muslim protests and the prime minister’s health would endanger national security, it seized the entire print run of the paper. On August 24, Feteh’s editor, Temesghen Desalegn was arrested and denied bail. He was released on August 28, and all the charges were withdrawn pending further investigation.
Police on July 20 raided the home of journalist Yesuf Getachew, editor-in-chief of the popular Muslim magazine Yemuslimoche Guday (Muslim Affairs), and arrested him that night. The magazine has not been published since, and at this writing, Yesuf remained in detention.
On December 27, 2011, two Swedish journalists, Martin Schibbye and Johan Persson, were found guilty of supporting a terrorist organization after being arrested while traveling in eastern Ethiopia with the Ogaden National Liberation Front (ONLF), an outlawed armed insurgent group. They were also convicted of entering the country illegally. The court sentenced them to 11 years in prison. On September 10, they were pardoned and released along with more than 1,950 other prisoners as part of Ethiopia’s annual tradition of amnesty to celebrate the Ethiopian New Year.
On several occasions in July, federal police used excessive force, including beatings, to disperse largely Muslim protesters opposing the government’s interference with the country’s Supreme Council of Islamic Affairs. On July 13, police forcibly entered the Awalia mosque in Addis Ababa, smashing windows and firing tear gas inside the mosque. On July 21, they forcibly broke up a sit-in at the mosque. From July 19 to 21, dozens of people were rounded up

ከኬኒያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ምን እንማራለን?

           ታምሩ ገዳ
ህዝባዊ ምርጫዎች በመጡ ቁጥር ስልጣኑን እነማን ይርከባሉ? ምርጫው ምን አዲስ ነገር ይፈጥርልን ይሆን? ምርጫው ሰላም ወይም አለመረጋጋት ... ወዘተ ይቀሰቀስ ይሆን? የሚሉ መሰል ጥያቄዎች በበርካታ መራጮች አይምሮ ውስጥ መመላለሱ የተለመደ ነው።

ከአምስት አመት (2007/2008 እ.ኤ.አ.) በፊት ተካሄዶ በነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሳቢያ ከ1300 በላይ ዜጎቿን ያጣች፣ ከ600 ሺህ በላይ ዜጎቿ የተፈናቀሉባት እና በቤሊዮኖች የአሜሪካ ዶላሮች የሚገመቱ ንብረቶች የወደሙባት ጎረቤት አገር ኬኒያ በያዝነው የፈረንጆቹ መጋቢት 4 2013 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አድርጋለች። ከአንድ ሳምንት በፊት በጋዜጠኞች አዘጋጅነት ስምንት እጩ ፕሬዝዳንታዊ ተመራጮች ባደረጉት 3 ሰአት የፈጀ የመጀመሪያው ዙር ክርክር በ34 ራዲዮኖች እና ስምንት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች በቀጥታ ተተላልፋል። ይህ ከትምህርት ፖሊሲ አንስቶ እስከ የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ድረስ ያካተተው ክርክር ከ40 ሚሊዮን በላይ የሚገመተው የኬኒያ ህዝብን ቀልብ ከመሳብ አልፎ አለማቀፋዊ ትኩርትን መሳቡ አልቀረም።

በዚህ የጦፈ ክርክር ላይ እጩ ፕሬዝዳንታዊ ተመራጮቹ ከተሰጣቸው ጊዜ ሲያልፉ ወይም ለጥያቄው ተገቢ ምላሽ ሲያጡ ተናጋሪዎቹን በማቋረጥ ተከታታይ ጥያቄዎችን ያለ ፍርሃት በመደርደር (እንደ አስፈላጊነቱ ) በማድረጋቸው አወያዮቹ (ሞደሬተሮቹ) ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። የወዳጆች መገናኛ ብዙሃናት የሆኑት አነ ፌስ ቡክ እና ቲዊተርም ቢሆኑ በአስተያየት ሰጬዎች ተጨናንቀው ነበር የሰነበቱት። የበርካታ ኬኒያዊያን አንገት ያስደፋው እና ቁስሉ እስከ ዛሬ ድረስ ያልደረቀው የድህረ 2007/2008 እ.ኤ.አ. ምርጫ መዘዝ በሰሞኑ የምረጡኝ ዘመቻ ክርክር ላይ መነሳቱ አልቀረም። በአይነ ቁራኛ የሚተያዩት እና በሰሞኑ ምርጫ ላይ የአሸናፊነቱ እድል እንዳላቸው ሰፊ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት ጠ/ሚ/ር ሪያላ ኦዲንጋ እና የኬኒያ መሰራች እና የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆሞ ኬኔያታ ወንድ ልጅ የሆኑት ኡሁሩ ኬኔያታ ያለፈው ቅራኔያቸውን እና ልዩነታቸውን ወደጎን በማድረግ፣ ከጥላቻ እና ከከፋፋይነት አመለካከት ይልቅ በአገር ጉዳይ አብሮ መስራት ጠቀሜታ እንዳለው በተለያዩ መድረኮች ላይ የተናገሩ ሲሆን ያለፈውን ቁርቋሶ በተመለከተ እጃቸው አለበት ተብልው እስከ አሁን ድረስ ከተከሰሱት 14 ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት እጩ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኔያታ "ፕሬዝዳንት ሆነው ቢመረጡ በሆላንዷ ዘ-ሔግ ከተማ በተሰየመው የአለማቀፉ የወንጀለኞች ችሎት (ICC) የቀረበቦትን የዘር ማጥፋት ውንጀላን እንዴት ያደረጋሉ?" ለሚለው የሞደሬተሩ (አወያዩ) ጥያቄ ሲመልሱ "የኬኒያ ህዝብ እንዳገለግለው ከመረጠኝ በዘ-ሔግ ላይ የቀረበብኝ ውንጀላን በተመለከተ ተሟግቼ እራሴን ነጻ አደርጋለሁ" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በምረጡኝ ክርክሩ ላይ የተሳተፉት ጠ/ሚ/ር ኦዲንጋ ለጥቅ አድርገው "ዘ-ሔግ ላይ ሆኖ አገርን በስካይፕ (ኢንተርኔት አማካኝነት) መምራት ከባድ ይመስለኛል። ተቃዋሚ ነን የሚሉ ወገኖች ካግበሰበሱት ሰፋፊ መሬት ጥቂቱን እንኳን ለደሃው ህዝብ ቢያካፍሉ? በማለት ታዋቂው ፎርቢስ መጽሄት በቅርቡ የኬኔያው ቁጥር አንድ ቱጃር ሲል የሰየማቸው ኡሁሩ ኬኔያታን በነገር ወረፍ አድርገዋቸዋል። በነገራችን ላይ ኡሁሩ ኬኔያታ እና የጥምረት አጋራቸው የሆኑት ዊሌየም ሩቶ በዘ-ሔግ ላይ የተረመሰረተባቸው ክስ አነርሱን ከፖለቲካው መድረክ ለማባረረ በስልጣን ላይ ባለው ገዤ መንግስት እና በምእራባዊያን የተወጠነባቸው ሴራ አንደሆነ ይናገራሉ።

ሰሞኑን የተሰበሰቡ ቅድመ የህዝብ የምርጫ አስተያየቶች እንዳመለከቱት ምርጫው ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ቢካሄድ ኖሮ ኡሁሩ ኬኔያታ ጠ/ሚ/ር ኦዲንጋን በ740 ሺህ ድምጽ አንደሚያሸንፋቸው የምርጫ ተንታኞች ተንበየው ነበር። ያለፈውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ተከትሎ ኬኔያ በደረሰባት የፖለቲካዊ፣ የኤኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ሳቢያ አለማቀፉ ማህበረሰብ በተለይ ደግሞ የቀድሞው የተመድ ዋና ጸሃፊ የሆኑት ጋናዊው ኮፌ አናን አማካኝነት የተካሄደው የሸምጋይነት ጥረት የተነሳ በጡረታ ተሰናባቹ በፕሬዝዳንት ማዋዬ ኬባኬ እና በተቀናቃኛቸው የአሁኑ ጠ/ሚ/ር ኦዲንጋ መካከል ጥምር መንግስት ለማቋቋም የተገደደችው ጎረቤት አገር ኬኔያ ህገመን ግስቷን በአዲስ መልክ በማሻሻል፡የፍትህ ስርአቷ ገለልተኛ እንዲሆን ጥርት በማድረግ በኩል እና ዜጎቿን ለብቀላ የሚጋብዙ ቃላትን እና ብሄርን በብሄር ላይ ለአመጻ የሚያነሳሱ አስተያየቶችን ከመጠቀም የሚያግድ የቁጥጥር ኮሚሽን በማቋቋም የሰሞኑ ምርጫ 2013 እ.ኤ.አ. የተሻለ ምርጫ ለማድረግ ውስጣዊ ጥረቶችን ብታደርግም ምርጫ ይሳካ ዘንድ ያለፈውን ደህረ ምርጫ ይመሰለ ዘግናኝ፡ የብቀላ እና ኤ-ዲሞክራሲያዊ እርምጃ እንዳይደገም እና የናይሮቤ መንግስት ዜጎቹን እንዲታደግ የአለማቀፉ ማህበረሰብ ከማሰጠንቀቀ አልቦዘንም። በወላጅ አባታቸው በኩል ኬኔያዊ ዝርያ ያላቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሰሞኑን ለኬኔያ ህዝብ በላኩት የቬዲዮ መልእክት ኬኔያዊያን ነጻ ፡ዴሞክራሲያዊ እና የሰከነ ምርጫ እንዲያካሄዱ ተማጽነዋል። የኬኔያ ቀኝ ገዢ የነበረችው እንግሊዝም በበኩሏ በምረጫ ስም ስርአተ አልበኝነት እንዲከሰት እንደማትሻ ገልጻለች።

(ለውጥ ፈላጊ ኬንያዊያን መራጮች ደምጽ ለመሰጠት ተራቸውን ሲጠባበቁ)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውሳኔ ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው ተባለ

በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረን ግጭት ተከትሎ 10 የኦሮሞ ተወላጆች ከትምህርታቸው እንዲታገዱ መደረጋቸውን የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብዓዊ መብት ሊግ አጥብቆ ያወገዘው ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ውሳኔም ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው ብሎታል።
የሰብዓዊ መብት ሊጉ ከትምርታቸው የታገዱትን ተማሪዎች ፎቶ አስደግፎ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው የታገዱት የመጀመሪያ ሴሚስተር ፈተናቸውን አጠናቅቀው የሁለት ሳምንት እረፍት ወስደው ከተመለሱ በሁዋላ ነው ብሏል።
ሊጉ ከውስጥ የደረሱትን መረጃዎች ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው ይህ በግልጽ ፖለቲካዊ የሆነውና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረው ውሳኔ የተላለፈው “ዲሲፕሊን ኮሚቴ” ተብሎ በሚጠራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አካል ሲሆን፤ኮሚቴው ለዚህ ውሳኔ ምክንያት የሆነውም ባለፈው ጥር ወር በኦሮሞና በትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ነው።
በሁለቱ ብሔረሰብ ተወላጆች መካከል ግጭቱ ሊፈጠር የቻለውም ጥቂት የትግራይ ተወላጆች የኦሮሞ ብሄረሰብን አስመልክቶ ተገቢ ያልሆነና ቆስቋሽ ጽሁፍ ጽፈው በመለጠፋቸው ምክንያት እንደሆነ ማረጋገጡን ሊጉ አውስቷል።
ይህን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ በግጭቱ ሳቢያ ከ10 በሚበልጡ ተማሪዎች ላይ የ እስራት፣የግርፋትና የድብደባ እርምጃ መወሰዱን፤ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ የ ኦሮሞ ተወላጆች እንደሆኑ ይፋ ማድረጉንም ሊጉ አስታውሷል።
በግጭቱ ምክንያት ከትምህርታቸው እንዲታገዱ የተደረጉት አስሩም ተማሪዎች ኦሮሞዎች መሆናቸውን እና ከመካከላቸው አንዷ ሴት መሆኗን ያመለከተው ሊጉ፤ ሁሉም ለአንድ ወር ያህል ታስረው በዋስ ከተለቀቁ በሁዋላ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው እንደነበር ጠቅሷል።
ከትምህርታቸው የታገዱት የኦሮሞ ተማሪዎች ከወለጋ ነቀምት የመጣው የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ታደለ ታረቀኝ፣ ከደቡብ ሸዋ ኦሮሚያ የመጣው የ3ኛ ዓመት ተማሪ አበጀ ቱጂ ጫላ፣ የ4ኛ ዓመቱ ተማሪ ገመቹ ደለቶ ዳፎ፣ የ 4ኛ ዓመት ተማሪ መልካሙ ሙሉጌታ፣ የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ፈቃዱ መሰራ፣ የ4ኛ ዓመቷ ሴት ተማሪ አዲስ ጋቴራ ያደሳ፣የ 4ኛ ዓመቱ ተማሪ በቃሉ ስዩም ተሻለ፣ የ3ኛ ዓመቱ ተማሪ ቀጀላ አድማሱ ደሬሳ፣የ 2ኛ ኣመት ተማሪው ኢሳያስ ኢታና እና የ 4ኛ ዓመት ተማሪው አራርሳ ዋቅቶላ ኦልጅራ መሆናቸው ይታወሳል።
ግጭቱን ከቀሰቀሱትም ሆነ በግጭቱ ከተሳተፉት የትግራይ ተወላጆች አንድም ተማሪ ላይ እርምጃ አለመወሰዱ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተብየውን ውሳኔ በግልጽ ፖለቲካዊና ዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ያሳያል ሲል የሰብዓዊ መብት ሊጉ አመልክቷል።
ይህ ውሳኔ ከሰብዓዊ መብት ሊጉ ባሻገር ብዙዎችን ያስገረመ እና ጥቂት በማይባሉም ታዛቢዎች ዘንድ፦ “በ እርግጥም ይህች አገር የማናት?” የሚልን ጥያቄ ያጫረ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝብንና አገርን የሚጠቅም ስራ መስራት እንደማይቻል የጀርመን ፋውንዴሽን ዳይሬክተር ተናገሩ

 ባለፈዉ አመት መጨረሻ አካባቢ የወያኔ አገዛዝ አላሰራ ብሎት ኢትዮጵያን ለቅቆ የወጣዉ ሄንሪክ ቦል ፋዉንዴሺን የተበላዉ የጀርመን ምግባረ ሰናይ ድርጀት ዋና ዳይረክተር ኢትዮጵያ ዉስጥ ምንም አይነት የህዝብን ኑሮ የሚለዉጥ ስራ መስራት አይቻልም ሲሉ የወያኔን አገዛዝ ደንቃራነት አወገዙ። ሚስትር ፓትሪክ በርግ የተባሉ የምግባረ ሰናዩ ድርጅት ዋና ዳይረክተር ይህንን የተናገሩት ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ የለቀቀበትን ምክንያት ብሉምበርግ ለተባለዉ የዜና ማሰራጫ ተቋም ባስረዱበት ወቅት ነዉ። እንደ ዳይረክተሩ አባባል ኢትዮጵያ ዉስጥ ሌላ ቀርቶ የጥበብ ስራ እንኳን በአሁኑ ጊዜ በጥርጣሬ የሚታይ ነው፣ እኛ የምንሰራዉ ስራ ደግሞ ከሰብዓዊ መብቶች መከበር ጋር በቀጥታ የተያያዘ ስለሆነ አገዛዙ በፍጹም አልወደደዉም ካሉ በሁዋላ ይህንን ከመብት ጋር የተያያዘውን ስራችን አቁሙ በመባላችን ኢትዮጵያን ለቅቀን ወጥተናል” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከጾታ እኩልነትና ከሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጋር የምንሰራዉን ስራ ለመግታት እራሱ ከጻፈዉ ህገመንግስት ጋር የሚጻረር ህግ አዉጥቷል ያሉት ሚስተር ፓትሪክ በርግ አገዛዙ ነገሮችን የሚያየዉ ህዝብን ይጠቃማል ወይስ ይጎዳል ብሎ ሳይሆን ከራሱ የስልጣን ዘመን ጋር እያስተያየ ስለሆነ ከዚህ አይነት አገዛዝ ጋር ምንም አይነት ህዝብንና አገርን የሚጠቅም ስራ መስራት አይቻልም ብለዋል።
ድርጀቱን ወክሎ ከሚስትር ፓትሪክ በርግ ጋር የተወያየዉ የብሉምበርጉ ሚስትር ዊልያም ዳቪሰን ደግሞ የሲቪክ ሶሳይቲና ቻርቲ ህግ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ውርስ መሆኑን ተናግሮ ህጉ የወጣዉ ከመንግስት የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ተቃዋሚዎችና ምግባረ ሰናይ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ነዉ በማለት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን በመጥቀስ ተናግሯል።
በሌላ በኩል ደግሞ የሂውማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል በቀለ ፣ መንግስት ያወጣው የሲቪክ ሶሳይቲና ቻሪቲ ህግ ዋና ግቡ በአገር ውስጥ ካለው ፖለቲካና ሲቪክ ሶሳይቲ ስራ ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ የሆነዉ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ህጉ በሙስና የተዘፈቁ የሲቪክ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ተብሎ የተረቀቀ መሆኑን በመግለጽ፣ የወያኔን አቋም አንጸባርቋል።

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም


ኢሳት ዜና:- 
                  የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ሰራዊቱ እና የሶማሊ ልዩ ምልሻ በጋራ ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ የውሀ ጉድጓዶችን ተቆጣጥረው ህዝቡን ገንዘብ በማስከፈል እያሰቃዩት ነው። ድርጅቱ ለአለማቀፍ ድርጅቶች ባሰማው የድረሱልን ጥሪ ሰራዊቱ በአንድ ሰው እና በእንስሳ ቁጥር ልክ ገንዘብ እያስከፈለ ነው።
አንድ ቤተሰብ ወደ ውሀ በወሰዳቸው ግመሎች፣ ፍየሎችና በጎች ልክ ለውሀው እንደሚከፍል የገለጠው መግለጫው በአማካኝ አንድ ቤተሰብ እስከ 12 ሺ ብር በወር የመክፈል ግዴታ ጠጥሎበታል ሲል አስታውቋል።
ከፍተኛ ድርቅ በተስፋፋበት ኦጋዴን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መውሰድ በህዝቡ ላይ የሚፈጸም የዘር ማጥፋት እርምጃ በመሆኑ መንግስት ተጠያቂ መሆን እንዳለበት ድርጅቱ ገልጿል።
በተለይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ እንዲታደግ ድርጅቱ ጥሪ አቅርቧል።
በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት የሰጠው አስተያየት ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካልንም። የኦጋዴን አካካቢ አሁንም ከፍተኛ የጤር ቀጠና መሆኑ ይታወቃል።