Sunday, February 17, 2013

ግፍ ሲበዛ ማስፈራት፤ እስርም ሲበዛ ማሸማቀቁ ይቀራል


የወያኔ ልብ ወለድ “ደራሲዎች” ተደራሲ በሌለበት አለም ሆነው የገሃዱን አለም ነጸብራቅ ያልሆነውን የቀን ቅዠታቸውን በመርዛማና በዶለደመ መቃቸው ዛሬም እንደትላንቱ በቆሸሸው ኢቲቪ አማካይነት የጥጋብ ግሳታቸውን ማግሳት ቀጥለዋል፡፡ እኛም ግሳታቸውን በተራበ አንጀት እነሆ ለ21 አመት እየተጋትነው አለን።
የወያኔ ዘረኞች ቀደም ሲል በግንቦት 7 እና በሌሎቸም ደርጅቶች ላያ ያነጣጠሩ አኬልዳማን የመሰሰሉ የዉሸት ድራማዎችን በማቀነባበርና ሀአዲስ አበባን እንደ ባግዳድ የእልቂት ቀጠና ሊያደርጓት ነዉ የሚል የሞት ዜና ለህዝብ በማሰማት የታጋዮችን ቅስም ለመስበርና የህዝብን የተነሳሳ የትግል ስሜት ለማቀዝቀዝ ከፍተኛ ሙከራ አድርገዋል።
እነዚህ ዘረኞች በባህላችንም ሆነ በሀይማኖታችን እንዲሁም በኢትየጵያዊ ትውፊቶቻችን ላይ ሲያላግጡ ገና ከመጀመርያው በቃቸሁ በለመባላቸው ዛሬም እንደትናንቱ “የምን ትሆናላችሁ” ንቀታቸዉንና ለህዝብና ለአገር ያላቸዉን ጥላቻ ትውፊቶች ያላቸውን ጥላቻና ንቀጅሃዳዊ ሃረካት፡ በሚል የዘግናኝ ፈልም እያሳዩንነው ። ጅሃዳዊ ሃረካትን ከአኬልዳማ የሚለየዉ ነገር ቢኖር፤ ጅሃዳዊ ሃረካት፡ ለዘመናት ተከባብረው በኖሩት የሀገራችንን የእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ነው፤ ይህ የወያኔ ጭፍን ተግባር የሚያሳየን ወያኔ ስልጣኑን እስካራዘመለት ድረስ ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ተከባብሮ የኖረን ህዝብን፣ እምነትንና አገራችንንም ጭምር ለማጥፋት እንደማይመለስ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ እውነታውን ወይም ሀቁን ለይቶ የሚረዳና የሚያገናዝብ ህዝብ በመሆኑ እንጅ የወያኔ ቆሻሻ መልቀቂያ በሆነው በኢቲቪ የሚተላለፉትን ድራማዎች ወይም ውሸቶች፣ ከንቱ ትረካዎችና አንድን ህዝብ በሌላው ላይ እንዲሁም አንዱ ሃይማኖት በሌላው ሃይማኖት ላይ እንዲነሳ ለማድረግ ያደረጋቸዉ ሙከራዎች አገራችን ኢትዮጵያን የት ሊያደርሳት ይችል ነበር ብለን ስንገምት በኢትዮጵያ ህዝብ ጽናትና አርቆ አስተዋይነት ህዝብ እንድንኮራና እንድንተማመን ያደርገናል፡፡
በተቃራኒው ወያኔ እራሱ አገር ምድሩን እያሸበረ ሌሎች ለመብታቸው የሚታገሉ ወገኖቻችንንችን በተለይም የአስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችንን ሽብርተኞች ናችሁ እያለ በማሰሩ አፍረንበታል።
ወያኔ ይህንን የሚደርገው የታጋዮችን ቅስም ለመስበር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወጣቶች የታጋዮችን አርአያ ተከትለው ትግሉን እንዳይቀላቀሉና የስልጣን እድሜውን እንደያሳጥሩበት ለመቀጣጫ እንዲሆንና ወጣቱን ከትግሉ መንደር ለማራቅ ቢሆንም እውነታው ግን የሚያሳየው የተገላቢጦሽ ነው፡፡ ግፍ ሲበዛ ማስፈራቱ፣ እስርም ሲበዛም ማሸማቀቁ ይቀራል፡፡ በዛሬዬቱ ኢትዮጵያ እስርም ሆነ ግርፋት የማይፈራበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። ዛሬ የኢትዮጵያ ወጣቶች እኔ አቡበከር ነኝ እኔ አንዷለም ነኝ እያሉ ተነስተዋል፤ ይህም የወያኔ መውደቀያ ቀን አብይ ምልክት ነው
ህወሃት አሸባሪ ድርጅት ነው። ህወሃት የማህበረሰባችን የእምነት ነጻነት፤ ክብርና መብት የሚገፍ፣ የሚያዋርድ፣ የሚያፈናቅል ጤነኛ ያልሆነ ስርአት በመሆኑ መብታችንና ነጻነታችንን ለማስከበር ማናቸውንም አይነት የትግል ስልት ተጠቅመን ወያኔን በመፋለም ህዝባችንን ከእርስበርስ ግጭት፤ አመጽና ትርምስ የማዳን ግዜው አሁን ወይም ዛሬ ነው ይላል ግንቦት 7።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነት የዲሞክራሲ ንቅናቄ ትላንት እንዳልነው ዛሬም ለመብታቸው ሲሉ በወያኔ እጅ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ያለንን ጥልቅ አክብሮት ይገልጻል፡የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ፣ ለማንነቱ፣ ለእምነቱ፣ የሚያደርገው መራራ ትግል ይቀጥላል። የህወሃት መርዘኛ አፈ ሙዞች ወይም የጅል ፕሮፖጋንዳ ድራማዎች ትግሉን ለደቂቃም ቢሆን አይገቱትም ያጠናክሩታል እንጂ፡፡ ወያኔ የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ጠያቂዎቹን በሀሰት የሚወነጅል ጀሃዳዊ ሀረካት ብሎ ያረበዉን ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያወግዛል፡፡
የድራማው ሌላኛው መልእክት በኢትዮጵያ ውስጥ የፍትህ ስርአት ሞቶ የተቀበረና የማይነሳ መሆኑን ቀባሪው ወያኔ የቀብሩን ስነስርአት በቲቪ መስኮት እነ አኬልዳማን፣ ጀሃዳዊ ሀረካትን ካለ ከልካይ እርሱ የሚጮኸው ጩኸት ትክክል መሆኑን ያሳየናል፣ ደጋግሞም ይነግረናል። ልብ ይበሉ የአሻንጉሊቱ የፍርድ ቤት ዳኞች የተባሉት በዚህ የቀብር ስነስርአት በየትኛው የአስለቃሽ ቦታ ላይ መሆናቸውን ግን ድራማው አያሳየንም።
ህግ የሚወጣው መንግስት የዜጎችን መብት ለመጠበቅ ነው፤ በወያኔ ግን “ህግ” ማለት የመንግስት መሳሪያ ዜጎችን መጨፍለቂያ ስልጣንን ማሰንበቻ ነው። በሀገራችን የመናገር መብት ተገፎ እያለ የማምለክ መብት ሊፋፋ አይችልም፤ ወይም ደግሞ ፍትሃዊ ዳኝነት የማግኘት መብት ተጥሶ እያለ የማምለክ መብትን የሚያስከብር ተቋም ሊኖር አይችልም።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የዛሬ ሁለት አመት ወያኔዎች አኬልዳማ የተሰነውን አማተርና ደካማ ድራማቸውን እንደፈለጉ በሚቆጣጠሩትና በሚያዙት የውሸት መፈብረኪያ ቴሌቪዥናቸው ሲያሰራጩ እንዲህ አይነቱን ንቀትና ውርደት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆምና የዘረኛ አምባገነኖችን ትእቢት ለማስተንፈስ ትግሉን አጠናክሮ በመቀጠል ወያኔን ለማስገደድና ለማስወገድ ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ ይገኛል። ስለዚህም ሙስሊሙ ወገናችንም ሆነ ህዝበክርስትያኑ ሰብአዊ መብቶች ሳይከበሩ የሃይማኖት ነጻነት ብቻውን ሊከበር የማይችል መሆኑን ተረድቶ ህውአትን ለማስወገድ በምናደርገው መራራ ትግል ግንቦት 7ን እንዲቀላቀል አለያም ከጎናችን እንዲቆም ወገናዊ ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!