Wednesday, April 9, 2014

Ethiopia inflation rises to 8.8 pct in March


ADDIS ABABA (Reuters) – Ethiopia’s inflation rate quickened to 8.8 percent in the year to March from 7.9 percent the previous month, owing to a rise in both food and non-food items, official data showed on Tuesday.Ethiopia inflation rises
The Central Statistics Agency (CSA) said food prices rose 6.1 percent in March over the 12-month period from 4.7 percent in February, driven by price increases of bread and cereal.
Non-food prices edged up to 11.8 percent in the year to March from 11.4 percent in February, owing largely to price increases of khat, a leafy plant chewed as a stimulant in the Horn of Africa and the Arabian peninsula.

ነገረ-ኢትዮጵያ፣ ቅጽ 1 ቁጥር 7 ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ ወጥታለች


Click here for PDF

Negere Ethiopia, Semayawi party newspaper
  • የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሃዊ ምርጫ፣
  • የ2007 ምርጫ ከወዲሁ ትኩረት ይሻል!
  • የማዕድኑ ሙስና በኢትዮጵያ፣ የመምህራን ፍዳ፣
  • ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ በስተጀርባ፣
  • የሂውማን ራይትስ ዎች የቴሌኮም እና ኢንተርኔት ቁጥጥር በኢትዮጵያ ሪፖርት፣
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ብርሃኑ ዳምጤ – ደቡር፣ አባ መላ፣ ዘ-አገምጃ


መስፍን ቀጮ/ወፍ
የሚቀጥለውን ትረካ ለመጻፍ ብዙ ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነበር፡፡ ብጽፈውስ ምን ዋጋ አለው የሚል ስሜትም ተጭኖኝ ነበር፡፡ ሆኖም ‹ጅብ በማያውቁት ሀገር ቁርበት አንጥፋልኝ› እንዲሉ ከላይ የተጠቀሰው ብርሃኑ ደቡር አባ መላ በአዲሶቹ አለቆቹ የተረቀቁለትን ቃለ መጠይቆች ሲያነበንብ መስማቱ ስለሰለቸኝ ‹ማን ያውጋ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ› በማለት የልጅነት ጓደኛዬን ሳልወድ ለማጋለጥ ወሰንኩ፡፡Berhanu Damte Ethiopian regime supporter
እኔና ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ማዕድ እየበላን በሰፈር ወንዝ እየተራጨን እየተንቦራጨቅን ብይና አርቦሽ እየተጫወትን ሌላም ሌላም ነገር እየሰራን ያደግን ልጆች ነበርን፡፡ ብርሃኑና እኔ ት/ቤት ስንገናኝ እንዲሁ ጓደኛሞች ሆነን እኔ ከእሱ በዕድሜ አራት ዓመት አንስ ስለነበር ትምህርት የጀመርኩት ከሱ በኋላ ነበር፡፡ አንደኛ ክፍል ስገባ እሱ ወደሶስተኛ ተዛውሯል፡፡ ከሱ በእድሜ ከማነሴ በላይ ደቃቃ በመሆኔ ‹ቀጮ› የሚል ቅፅል ስም ወጥቶልኝ ነበር፡፡ ብርሃኑ በዚያን ጊዜ ከክፍል ልጆች በዕድሜ ይበልጥ ነበር፡፡ በትምህርቱ ደካማ ስለነበር ክፍል ስለሚደግም ታናናሾቹ ይደርሱበትም ይቀድሙትም ነበር፡፡ ለዚህም ነው እኔና እሱ ስድስተኛ ክፍል ላይ የተገናኘነው ብርሃኑ በጣም ወፍራምና ለፍላፊ ነበር፡፡
ሲለፈልፍ በፍንጭቱ ይረጨው የነበረው ምራቅ ከውፍረቱ ጋር ሆኖ ትርክርክነቱን ያጎላው ነበር፡፡ አንድ የጠቅላይ ግዛት ልጅ ‹የድሃ መሃቻ› (ሊጥ ማቡኪያ) ብሎ ጠራው፡፡ ከዚያ በኋላ የድብቅ መጠሪያ ስሙ ሆነ፡፡ ብርሃኑ ምግብ በተለይ ጥሬ ሥጋና እንቅልፍ ከሁሉም በላይ አብልጦ የሚወድ ልጅ ነበር፡፡
ከስድስተኛ ክፍል በኋላ እኔና ብርሃኑ በጣም ጥብቅ ጓደኛሞች ሆንን ብርሃኑን የተጠጋሁት የሰፈር ጉልቤዎች በሚተናኮሉኝ ጊዜ ይከላከልልኝ ስለነበር እሱ የወደደኝ ደግሞ ክፍል ውስጥ የቤት ስራም ሆነ ፈተና ስለማስገለብጠው ከዚያም አልፎ ከትምህርት ቤት በኋላ እቤቴ ሸኝቶኝ ምግብ በልቶ ስለሚሄድ ነበር፡፡ በወላጆቼ በኩል ከቀልደኝነቱ ባሻገር አንድ ልጃቸው በመሆኔ እንደ አይነ ብሌናቸው ያዩኝ ስለነበር ወንድም በማግኘቴ ደስ ብሏቸው ይወዱት ነበር፡፡
የስድስተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈትነን ውጤት ሳንሰማ በክረምት ወር አባቴ በመስሪያ ቤቱ ትዕዛዝ ወደ ጠቅላይ ግዛት በመዛወሩ እኔም አብሬ ተጓዝኩ፡፡ በሶስተኛ ዓመት ክረምት ላይ ለዕረፍት አዲስ አበባ መጥቼ ስለነበር ጓደኛዬን ለማግኘት ሰፈር ስሄድ አያቶቹን ሊጠይቅ አገምጃ ጉራጌና ኦሮሞ አገር መሄዱ ተነገረኝ፡፡ በነገራችን ላይ ብርሃኑ በአባቱ መንዜ ሲሆን በእናቱ ደግሞ የአገምጃ ጉራጌና ኦሮሞ ነው፡፡ ሳላገኘው በመመለሴ እያዘንኩ ወደ ጠቅላይ ግዛት ተመለስኩ፡፡ በዓመቱ አባቴ እንደገና ወደ አዲስ አበባ በመዛወሩ ተመልሼ አዲስ አበባ መጣሁ ብርሃኑንም ወዲያው አገኘሁት፡፡
ብዙ ገጠመኞቻችንን እየተለዋወጥን እንደቀድሟችን አብረን መጫወትና መዋል ቀጠልን፡፡ ታዲያ መስከረም ጠባና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችንን ስንጀምር እኔ ከአስረኛ ክፍል ልጆች ጋር ስሰለፍ ጓደኛዬ ከዘጠነኞች ጋር ተሰልፎ አየሁት፡፡ ሚኒስትሪ በመውደቁ አንድ ዓመት ደግሟል፡፡ አልገረመኝም ጓደኛዬን ስለማውቀው!
ከስልሳዎቹ መጀመሪያ የኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚያንቀሳቅሱት የመንግስት ተቃውሞና አመጽ እየበረታ  በሄደበት ወቅት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ቀልብ ስቦ የእንቅስቃሴው አጋርና ደጀን አድርጓቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ስድስትና አራት ኪሎ በተነቃነቁ ቁጥር መላው የአዲስ አበባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ወረቀት ይበተናል፣ የከተማ አውቶቢስ ይሰባበራል፡፡ ሌላም ብዙ ሌላ ነገር ይደረጋል፡፡ በዚያን ወቅት የመርካቶን ተማሪዎች የምናስተባብረው ብርሃኑ፣ እኔ፣ ተስፋዬ የማነና ሌሎም ነበርን፡፡ ተስፋዬ የማነ ችኩል ቅብጥብጥ ግብታዊና ደፋር ነበር፡፡ ይህን ስለምናውቅ አደገኛ ሁኔታዎችን እንዲፈጽም እናደርገው ነበር፡፡ አንድ የማልረሳውና እስከ አሁን ድረስ የሚፀጽተኝ ነገር ላውራችሁ፡፡ ከሰፈር ወጥተን ልክ ጠቅላይ ቢሮ ስንደርስ ሹፌሩ ብቻ ያለበት አንድ አውቶቢስ ቆሞ እናያለን፡፡ አውቶቢሱ ብቻ ለምን እንሰብራለን ሹፌሩም መመታት አለበት አለ ብርሃኑ ችኩልና ቅብጥብጡ ተስፋዬ ዕብድ በሚያክል ድንጋይ የሾፌሩን አናት ተረከከው፡፡ ምስኪኑ ሹፌር
የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የየካቲትን አመጽ አስከተለ፡፡ አመጹ በመካሄዱ ላይ እንዳለ ከውጪ የመጡ ምሁራንና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየፊናቸው ሕቡዕ ጥናት ክበቦችን በማቋቋም ወጣቱን መመልመል ተያያዙት፡፡ በዚህም መሰረት ኢህአፓና መኢሶን ወጣቱን እየተቀራመቱ በየጎራቸው ኮለኮሉት ታዲያ ብርሃኑ፤ ተስፋዬና እኔ የኢህአፓ ሰለባዎች ሆንን፡፡ እንደማንኛውም ወጣት የድርጅቱ ተገዢና ደጀን ለመሆን በሙሉ ልብ ተሰናዳን፡፡ ከብዙ ፈተናና ምስጢራዊ ግምገማ በኋላ ታማኝነታችን በመረጋገጡ ከበላይ አካል የሚሰጠንን ሚሽኑ (ግዳጅ መፈጸም ጀመርን) በዚህ ወቅት ነበር፡፡ ብርሃኑ ዳምጤ ‹‹ደቡር›› የተሰኘውን የኮድ ስም የተጎናጸፈው እኔም ከቀጮ ወደ ‹‹ወፍ›› ተቀየርኩ፡፡ የተስፋዬን ረሳሁት፡፡ በድርጅቱ መዋቅር መሠረት እኔ በቅርብ እንዳውቃቸው የተደረጉት ተስፋዬና ብርሃኑ ደቡር ብቻ ነበሩ፡፡ በደቡር በኩል እየተነገረኝ ከበላይ የሚፈሰውን መመሪያና ግዳጅ መፈጸም የቀን ተቀን ተግባራችን ሆነ፡፡
ከትዝታዎቹ አንድ ቀን ደቡር ግዳጃችንን ነገረን ይኸውም ምዕራብ ሆቴል ጀርባ አንድ ሀብታም ነጋዴ የቀን ገቢውን ማታ ማታ ቤቱ ይዞ ስለሚሄድ መኪናው አካባቢ በመቆየት ገንዘቡን ተረክቦ መሄድ ስለሚሆን ሁለት የታጠቁ ጓዶች በአካባቢው እንደሚገኙና ወፍ የተቀዳደደ ልብስ ለብሰህ ማዘናጋት ትጀምራለህ ተባልኩ፡፡ ወዲያውም ጓዶቹ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳሉ፡፡ ሰውየውን ገና ስጠጋው ጓዶቹ ከመቅጽበት መጥተው ገንዘብ ተረክበው ይባስ ብለው የሰውየውን ፔጆ መኪና ቁልፍ ነጥቀው አስነስተው ፈረጠጡ ወደ መደበቂያችን ቦታ ሄድኩ፡፡ ደቡርና ተስፋዬ ቤቱን አሟሙቀው ጫት እየቃሙ ደረስኩ፡፡ በምርቃና የተለያዩ እቅዶችን ስናወጣና ስናወርድ ቆይተን ወደ ጨብሲ ተዘዋወርን፡፡ ብዙ ስንገነባና ስናፈርስ አድረን፡፡ የበላይ አካልን ትዕዛዝ እንጠብቃለን፡፡ ራሳችን በግብታዊነት፣ በጠላት ስም ሰዎችን እረሽነናል፡፡ ሚሽን ከሌለን ሥጋ መጠጥና ጫት አስገዝተን ለሌላ ግድያ እንዘጋጃለን፡፡ ቀልቤሳ በቀበሌ የኛ ግፍና ጭካኔ ደግሞ ከሱ ቢበልጥ እንጂ አያንስም፤ ምን ዋጋ አለው ለአንባቢያን ማቅረቡ እኔን ራሴን ስለሚዘገንነኝ ዝም ብዮ እዘጋዋለሁ፡፡ ባለፈረሱ ብርሃኑ ደቡርስ ምን ይሰማው ይሆን? እንደ አርበኞችና ጀግኖች እሱም ባለፈረስ ሆነ አባነብሱ፣ አባዳኜ፣ አባጠቅል፣ ሲባል ሰምቶ ብኩን አረመኔ!
ትግሉ እየጋለ በሄደ ቁጥር የመኢሶንና የኢህአፓ ጦርነት እየተፋፋመ ሄደ፡፡ በዚህም ጊዜ ራስን ለማዳን ወይም ለአላማ ብዙ ጓዶች ተገድለዋል፡፡ እኛም ብዙ ረፍርፈናል፡፡ ብዙ ሀብታሞችን አስገብረናል፡፡ የንጹህ ሰዎችንም ደም በከንቱ አፍሰናል፡፡ ቤት ይቁጠረው፡፡ ከአሜሪካን ግቢ ጀምሮ አደሬ ሰፈርን ሰባተኛን ኮልፌን አካሎ በአሸባሪነትና በገዳይነት የታወቀው ስም ደቡር የዛሬው አባመላ ከነህዋሱ ነበር፡፡ ሁኔታዎች እየከፉ ሄደው በቀበሌና በደርግ ፖሊሶች ኢህአፓ፣ መመታት ጀመረ፡፡ ይባስ ብሎም ኢህአፓ ለሁለት ተከፈለ፡፡ በመሆኑም የኢህአፓ መዋቅር ውዝምብር ውስጥ በመግባቱ ግማሹ ወደ አሲንባ፣ ሸዋና ወሎ ገጠር ውስጥ ሲገባ ግማሹ ደግሞ ከተሞች ውስጥ መፍጨርጨር ጀመረ፡፡ እኔ አዲስ አበባ ስቀር ደቡርና ተስፋዬ ወደ አጋምጃ ሸፈቱ፡፡ ሩቅ ሳይሄዱ አንዲት ትንሽ ሆቴል አልቤርጎ ውስጥ ተማርከው ወደ አዲስ አበባ ተወሰዱ፡፡ ወሬውን ስሰማ በጣም አዘንኩ፣ ተደናገጥኩ፡፡ ተደብቆ መኖርንም ተያያዝኩት፡፡ ከጥቂት ወራቶች በኋላ ተስፋዬን አገኘሁት፡፡ እንደኔው ተጨናንቆና ተደናግጦ ነበር፡፡ ከእስር እንዴት እንደተፈታ አላጫወተኝም፡፡ የመጨረሻ መተያየት ሆነ፡፡ ሰንብቼ ስጠይቅ ተስፋዬ የማነን እህቶቹ ወደ አሜሪካ እንደወሰዱት ሰማሁ፡፡ አይ ቅብጥብጡ ተስፋዬ አሁንስ ሰክኖ ይሆን?
ከኢህአፓ መሰነጣጠቅ በኋላ ብዙ ጓዶች ለደርግ እጃቸውን ሰጡ ይቅርታ እየጠየቁ፡፡ አንድ ምሽት በተደበቁበት ቦታ ከብርሃኑ ደቡር የኮድ መልዕክት ደረሰኝ፡፡ በጣም በመገረም ወደ ቀጠሮው ቦታ ሄድኩ፡፡ በኮድ መሠረት ወደተባለችው ላንድክሩዘር ተጠጋሁ፡፡ ደቡር ጋር አይን ለአይን ተያየን፡፡ መኪናው ውስጥ ገባህ ተሳሳምን፡፡ መኪናዋ መንቀሳቀስ ጀመረች፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ መኪናውን ከሚሾፍረው ሰው ጋር አስተዋወቀኝ፡፡ ቀጥሎም መጠነኛ የፖለቲካ ትንታኔ ካደረገልኝ በኋላ ግራ የሚያጋባ ሚሽን (ግዳጅ) እንዳለን ገለጸልኝ፡፡ ይኸውም ጓዳችን የሆነው ጩልሌ (መላኩ) መመታት እንዳለበት በበላይ አካል መወሰኑን ነገረኝ፡፡ ጥርጣሬ ላይ ወደቅሁ፡፡ በማን? በደርግ? ወይስ ከሁለቱ የኢህአፓ አንጃዎች ባንዱ? ግራ ገባኝ፡፡ ብርሃኑ ደቡርና ሰውየው ጉንጫቸው በጫት ተወጥሮ ነበር፡፡ ጨብሲ እናድርግ ብለው ሰንጋ ተራ አካባቢ መኪናዋን አቆሙ፤ አንዲት ትንሽ መጠጥ ቤት ገብተን ቢራዎች መጠጣት ጀመርን፡፡ ከሁለት ሰዓት ቆይታ በኋላ ከቤቷ ወጥተን ወደ ተክለሃይማኖት አቀናን ጎላ ሰፈርን እንዳለፍን የተዋወቅኩት ሾፌር መኪናዋን አቁሞ ወረደ፤ ከመንገዱ ዳር ካለች የተዘጋች ኪዩስክ ጠጋ ብሎ ከአንድ ህፃን ጋር ተነጋግሮ ወደ መኪናው ተመለሰ፡፡ ወዲያውኑ ደቡር ክላሽንኮቭን ከመኪናው ወለል አንስቶ የመኪናውን የጎን መስታዋት አወረደ፡፡ ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ጩልሌ (መላኩ) ከመንገዱ ዳር ሲደርስ ብርሃኑ ደቡር የያዘውን ክላሽ አቅንቶ ጥይቱን አርከፈከፈበት፡፡ በሰኮንዶች ጊዜ ብትንትኑ ወጥቶ መሬት ላይ ተዘረረ፡፡ መኪናዋም በሀይለኛ ፍጥነት እየበረረች ሰፈሩን ለቀቅን፡፡ ብዙ ግድያዎች ላይ ተሳትፌአለሁ፡፡ እንደዛች ቀን ግን ደንግጨና ፈርቼ አላውቅም፡፡ እስከዛሬ ህሊናዬን የሚያስጨንቀኝ ነገር ቢኖር ጩልሌን ለምን? ነበር፡፡
ደቡርስ አሁን ምን መልስ ይሰጠን ይሆን ወይስ እንደጲላጦስ እጁን ታጥቧል፡፡ ጉዞዋችንን በመቀጠል ፒያሳን ካቋረጥን በኋላ በራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ እንደገና አንድ ቡና ቤት ውስጥ ገባን፡፡ እኔ እየተርበተበትኩ ነው፡፡ እነሱ ግን በጫቱና በጨብሲው ምክንያት የደፈረሱትንና ቦታ የጠበባቸውን አይኖቻቸውን እያጉረጠረጡ እንደገና አልኮል መገልበጥ ጀመሩ፡፡\ከትንሽ ጊዜ በኋላ ብርሃኑ ወሬውን ቅደድ ጀመረ፡፡ የኢህአፓን ከንቱነትና መፈረካከስ አመራሩን እየኮነነ ከዘላበደ በኋላ በሱ እምነት ደርግ ጋር ተጠግቶ በኢህአፓ ላይ ቀይ ሽብር ማፋፋም የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ገለጸልኝ፡፡ አያይዞም የጩልሌ እምቢታ ምን እንዳመጣበት አበክሮ አሳሰበኝ፡፡ ላብ በላብ ሆኜ እየተብረከረኩ እምቢታዬን ገለጽኩለት፡፡ ብዙ ሊያግባባኝ ሞከረ፡፡ ምንም እንኳ በሁኔታው ብደናገጥና ብፈራም ፍንክች አላልኩለትም ነበር፡፡ በግልጽም ነገረኝ፡፡ በጨካኙ የደርግ ምርመራ ሹም በሻለቃ ብርሃኑ ከበደ ሥር እንደሚሰራና ብዙ የኢህአፓ ጓዶችን ወደ ደርግና ወደአብዮቱ እንዲመለስና እምቢተኞችም እንዳስመታ ገለጸልኝ፡፡ አሁን ተደናገጥኩ ፍርሃቴም ቀጠለ፡፡ ብርክ ያዘኝ ከህሊናየ ጋር እየተሟከትኩ ቡና ቤቱን ለቀቅን፡፡ መኪናዋ ወደ አራት ኪሎ አመራች፡፡ በመካከላችን ፀጥታ ሸፍኗል በመጨረሻም ሰተት ብላ ሚኒልክ ግቢ ገባች፡፡ ከመኪና ወረድን በእግራችን ትንሽ ከሄድን በኋላ አንድ በጩኸትና በለቅሶ የተሞላ ቤት በረንዳ ላይ አስቀመጡኝ፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ አንድ የሰከረ መርማሪ በጥፊ እያዳፉ አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ አስገብቶ አግዳሚ እንጨት ላይ ገልብጦኝ፡፡ ወዲያውኑ አንዲት በደም የተጨማለቀች ኳስ ቢጤ አንስቶ ወደ አፌ ሊወትፍ ሲል ብርሃኑ ደቡር ብቅ አለና ስሙን ጠርቶ ቆይ አለው፡፡ በቅጽበታዊ ገለል ብሎ ቆመ፡፡ ከሁኔታው ደቡር አለቃው መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ‹‹እሱን ለኔ ተወው›› በማለት ከመጀመሪያው ጥፊ በቀር ተገልብጦ አዳነኝ፡፡ ብርሃኑ ደቡር ጓደኛዬን ማመን አቃተኝ የአብሮ አደግነት ቆሌ ከሰባተኛ ተነስታ መርካቶን ፒያሳን  ቤተመንግስት ገብታ አዳነችኝ፡፡ ክብር ምስጋና ይግባትና ከዚያ በኋላ አንድ በእስረኞች የተጣበበች ግማት በግማት ክፍል ውስጥ አጎሮኝ ተሰወረ፡፡ እዚያች ጠባብ ግም ክፍል ውጥ የሚዘገንኑ ትርኢቶች አጋጠመኝ አንድ ሁለቱ አዲስ ግርፎች ስለነበሩ ነባር እስረኞች ቁስላቸውን በቆሻሻ  ጨርቅ ሲጠርጉና ሲሸፍኑላቸው ተመለከትኩ፡፡ ቁስለኞቹም የስቃይ ድምጽና ለቅሶ ሲያሰሙ ታዘብኩ፡፡ በአጠቃላይ ሀያ ከሚሆኑ እስረኞች መሀል ሳልገረፍ የገባሁት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ አይ! የመርካቶዋ አድባር ቆሌ! ሺህ አድባር ውለታሽን ይክፈሉሽ አልኩ በልቤ፡፡ እዚያች ክፍል ውስጥ ሳለሁ ከተመለከትኩት አዲስ ቁስለኛ ሲመጣ የከረመው ወደ ሌላ ቦታ ይወሰዳል፡፡ ማገገሚያ ጣቢያ አይነት ነበረችና አንዳንዴም ባሳቻ ሰዓት የተወሰኑ ሰዎች ይወስዳሉ፡፡ ዕጣ ፋንታየ ምን እንደሆነ ሳላውቅ ይኸው አስር ቀን ሆነኝ፡፡ በአስራ አንደኛው ቀን ሰባት የምንሆን እስረኞች ስማችን እየተጠራ እንድንወጣ ተደረገ፡፡ ምን ይሆን እያልኩ ስጨነቅ ከሌላ ቦታ ከመጡ አምሳ ከሚሆኑ እስረኞች ጋር በአንድ አዳራሽ ውስጥ ተደባለቅን ከጥቂት ጊዜ በኋላ የስብሰባው አስተናባሪ የዕለቱን አንቂና ተናጋሪ በአንዲት በር በኩል አስከትሎት ገባ፡፡ ሌሎች ይወቁት አይወቁት እንጃ እኔ ግን ጓደኛየን ደቡርን ሳየው ስላላስገረፈኝ ከልቤ እያመስገንኩ የሚለውን ለመስማት በጉጉት መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ከንግግሩ ምንም የተለየ ነገር አልሰማሁም ያው እንደለመደው ኢህአፓን አጥብቆ አወገዘ ወደ አብዮቱ ካምፕ መመለስን አበክሮ ከአስገነዘበ በኋላ ምርምራችን ተጣርቶ ንጹህነታችን ስለተረጋገጠ ምህረት እንደተደረገልንና ከአሁን በኋላ ሰላማዊ ኑሮ እንድንጀምር አበክሮ ከአሳሰበን በኋላ ወዲያውኑ በተነን፡፡ ከደስታ ብዛት ግማሹ ያለቅሳል ሌላው ይስቃል አንዳንዱ ደግሞ የድጋፍ መፈክር ያሰማል ሳይጠየቅ ታዲያ ሌላ ምን ያድርግ? አይ የነፍስ ነገር የሆነው ሆኖ ከአዳራሹ ስንወጣ ደቡር ወደ ቢሮው ወሰደኝና ጥቂት ምክር ከሰጠኝ በኋላ ለታክሲና ለምግብ የሚሆን አስር ብር ሰጥቶኝ እንድሰወር ነገረኝ፡፡ አይ አብሮ ማደግ እያልኩ አመስግኘው ተለያየን፡፡
ህቡዕ በነበርኩበት ጊዜ ሁሉን ነገር በሬዲዮና በጋዜጣ እከታተል ነበር፡፡ በተለይም በ1968 እና በ1969 ኢህአፓ በከተማ ውስጥ በመደምሰሱ መኢሶንም ፍርጠጣውን ተያይዞት ስለነበር፤ ደርግ በነበረበት ፍልሚያ የውስጥ ተቀናቃኞችን መደምሰስና ማስወገድ ነበር፡፡ ባልታሰበ ሁኔታ ሰናይ ልኬና ኮሌኔል ዳንኤል አስፋው በሻለቃ ዩሃንስ እንደተገደሉ የወዝ ሊግ መዋቅር ከመቅጽበት ፍርስርሱ ወጣ፡፡ በወቅቱ በተራ ካድሬዎች ቀርቶ በራሳቸው በደርግ አባላት የሚፈራው ሻለቃ ብርሃኑ ከበደ የብርሃኑ ደቡርና የሌሎቹ መርማሪ ነፍስ ገዳዮች አለቃ ከወዝ አደር ሊግ መፈራረስ በኋላ ባንዲራው በመውደቁ ያ ጨካኝ አውሬ ነፍስ በላ በደርግ የመረሸን ፅዋ ደረሰው፡፡
በሁኔታው የተደናገጡት የወዝ ሊግ አመራር አባላት ይቅርታ እየጠየቁ ለመንግስቱ ሀይለማርያም ገበሩ በተዋረዱም ብርሃኑ ደቡርና መሰል ጓደኞቹ አለቃቸውን ሻለቃ ብርሃኑ ከበደን እየኮነኑና እያወገዙ ነጻ ሆኑ የዛን ጊዜዎቹ ጲላጦሶች! ደቡር ለተወሰነ ጊዜ ድምፁ ጠፋ፡፡ እንደ እኔ ህቡዕ ገባ ወይስ ከአገር ወጣ እያልኩ አብሰለስል ነበር፡፡
ከወራቶች በኋላ የዳምጤ ልጅ ደቡር የሰደን ካባ ለብሶ ከፍተኛ ካድሬነት መከሰቱ ሰማሁ፡፡ ‹‹ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል›› እንዲሉ ብዙ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሚካሄድበት ፒያሳ አካባቢ ነበር የተመደበው፡፡ እሳቱ ደቡር በስልጣኑ በመመካትና በማስፈራራት ብዙ ገንዘብ ዘርፏል፡፡ በነፃ ከሚጠጣውና ከሚመገበው ባሻገር በጣም የሚያሳዝነው እሱና ግብረ አበሮቹ በፀረ አብዮት ሰበብ ብዙ ወጣት ልጃገረዶችን እያሰሩ ደፍረዋል፣ አበላሽተዋል፡፡ በርብርቦሽ አባት አልባ ልጆችን አስወልደዋል፡፡ የርብርቦሽ ዲቃላዎች ማሳደግ አቅቷቸዋል፡፡ ብርሃኑ ደቡር በየሆቴሉ እየገባ በነፃ መብላትና መጠጣት መብቱ አድርጎት ነበር፡፡ ካስቴሊ በነፃ ይመግበውና ያጠጣው ነበር፡፡ ከምግብ ሁሉ ጥሬ ሥጋ አብልጦ ስለሚወድ በአራዳ ልኳንዳ ቤቶች በነፃ ትኩስ ብልቶች መብላት ሥራው ነበር፡፡ ሆዳም! ይህም ድርጊቱ የአደባባይ ምስጢር እየሆነ በመምጣቱ በቀንደኛው ደርግ አባልና የሰደድ የበላይ አካል በጋሻው አታላይ ክትትል እንዲደረግበት ታዘዘ፡፡ ክትትሉ ውጤት አስገኘ ኮንትኔንታል ቡና ቤት አጠገብ ወደ እርይ በከንቱ መውረጃ ላይ ፒዜሪያ የምትባል የጣሊያን ምግብ ቤት አለች፡፡ ጣልያናዊው ባለቤት ከለውጡ በኋላ ለላብ አደሮቹ መርቆ አገር ለቆ ሄደ፡፡ ላብአደሮቹ ለጥቂት ጊዜ አብረው ከሠሩ በኋላ በስምምነት ኤርትራዊ ላብአደር ምግብ ቤቱን ጠቅልለው ይህ ሰው በአካባቢው ቀበሌ ተመራጮች በፈለጉት ጊዜ መጥተው በነፃ ይመገቡ ጀመር፡፡ በተጨማሪም ገንዘብ ያስገብሩት ነበር፡፡ ችግሩን መሸከም ሲያቅተው በሰዎች ምክር አቤቱታውን ለከፍተኛው ካድሬ አሰማ፡፡ ደቡር አጋጣሚውን በጣም ወደደው፡፡ ቀበሌዎችን አስፈራርቶ ዘረፋውን አስቆመ፡፡ በምትኩ ቀበሌዎቹን ተክቶ በተራው ምግብ መጠጥና ገንዘብ መብላትና መጠጣት መዝረፍ ጀመረ፡፡
ይህ ሲሆን የቀበሌ ተመራጮቹ አልተኙለትም ነበር፡፡ ብዙ ጭብጥ መረጃዎች አጠናቅረው ለበጋሻው አታላዩ አቀረቡለት፡፡ የዳምጤ ልጅ እንደለመደው ፒዜሪያ ገብቶ ሰዎች ጋብዞ እየበላና እየጠጣ ተዝናንቶ ሲወጣ እጅ ወደላይ ተብሎ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ በማግስቱ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ሆዳሙ ካድሬ ብርሃኑ ዳምጤ በሚል መግለጫ ግፉና ድርጊቱ ተነበበ፡፡ ከጥቂት ወራቶች እስር በኋላ በምህረት ተፈታ እስሩን አላከረሩበትም፡፡ ሁሉም ካድሬዎች የሱ አይነት ድርጊት  ይፈጽሙ ስለነበር፡፡ ከተፈታ በኋላ በአንዳንድ ጓደኞቹ እርዳታ ግብርና ሚኒስቴር ተቀጥሮ አጋርፋ እርሻ ማዕከል ተመደበ፡፡ እዚያ እየሰራ ሳለ እንደገና ታሰረ ምክንያቱን አላውቅም፡፡ በብዙ አማላጅና በሚኒስትሩ በዶክተር ገረመው ደበሌ ግፊት በእስር ተፈትቶ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ፡፡ በወቅቱ ደርግ በመላው ምስራቅ አውሮፓ ኮሚኒስት አገሮች የፖለቲካ ስልጠና እንዲገኙ ካድሬዎችን ይልክ ነበር፡፡ ታዲያ ቀልጣፋው ብርሃኑ ደቡር ተሰባብሮ ከአንድ ቡድን ጋር ወደሶቭየት ዩኒየን ለአስር ወራቶች የፖለቲካ ትምህር ተላከ፡፡ ከትምህርት መልስ ግብርና ሚኒስትር ተመለሰ፡፡ ሥራውን ጀመረ፡፡ ትንሽ ሰንበት ብሎ ወደ ዋናው ግብርና ሚኒስቴር ዕቃ ግዢ ክፍል ተመድበ፡፡ በመሆኑም ለሆዳሙ ጓደኛዬ ደቡር ሌላ አመቺ የዝርፊያ ሁኔታ ፈጠረለት፡፡ ከነጋዴዎች ጋር በመስማማት ገንዘብ ማካበት ጀመረ፡፡ ምርጥ ምርጥ ልብሶችና ጫማዎች መቀያየር ጀመረ፡፡ ቀን በቀን በውስኪ መታጠብ ጀመረ፡፡ በ247 ብር ደሞዝ ደርግ ድንብርብር ባለበት ዘመን ብዙ ፕሮግራሞ ያወጣ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት የኢሠፓን ካድሬዎች ለልማትና ለመንደር ምስረታ በሚል በየክፍለሀገሩ በተበተነበት ጊዜ ብርሃኑ ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ዘመተ፡፡ ተልዕኮውን ጨርሶ ሲመለስ አጅሬ ደቡር ‹‹ምን ይገደው›› ተገለባብጦ የኢሰፓ የአባልነት ቀይ ደብተር እጁ ውስጥ አስገባ፡፡ በዚህም ቀይ ደብተር ብዙ ነገደበት፡፡ ዘረፈበት ሌላም ሌላም ብዙ አደረገበት፡፡ ትዝ ከሚሉኝ አንዱ የግርማ ቢራቱ ነገር ነበር፡፡ ግርማ ቢራቱ የአባቱን ንግድ መርካቶ ውስጥ ያካሂዱ ነበር፡፡ ደስተኛ፣ ተጫዋች ሴት አሳዳጁና መጠጥ ወዳጁ ግርማ በጊዜው ተገጥሞለት ነበር
‹‹ከሰው ግርማ ቢራቱ
ከመኪና ቶዮታ ማርክ ቱ››
የዘመኑ የመርካቶና የአራዳ ልጆች ያስታውሱታል ብዮ አምናለሁ፡፡ ሞቷል ነፍሱን ይማረውና ታዲያ የብርሃኑ የገንዘብ ምንጭ ሆኖ ነበር፡፡ ወዶ ሳይሆን በመፍራት ሌሎች የሰፈራችን ነጋዴዎችና የቡና ቤት ሴት ባለቤቶች ገንዘብና ሩካቤ ስጋ ይለግሱት ነበር፡፡ ሳይወዱ በፍርሃት የደቡር ጉዞ ሁሌ እንደቀጠለ ነው፡፡ በተለመደው ‹‹አፍዝ አደንግዝ›› በነያሬድና በነአሳየ ብርሃኑ አማካይነት ደስ አለኝ ቤዛን ገልብጦ የግብርና ሚኒስቴር ቋሚ ካድሬ ሆነ፡፡ ደሞዙን ከ247 ብር ወደ 710 ተወረወረ ‹‹የባለ ማስትሬት›› ደሞዝ!!! ዶ/ር ገረመውን እያጫወተና እያሳቀ እንዳያፈናቅለው አደረገ፡፡ ይህም ሽፋን በዶክተሩ ስም እየነገደ ጉቦ መቀበል እንዲችል ረዳው፡፡ የግብርና ሚኒስቴርን የፋይናንስ መምሪያ ሃላፊዎች ብዙ ያልተወራረደ ገንዘብ እንዳለበት ተረጋግጦ እያለ እንዲመልስ አልተጠየቀም ካላበደ በቀር ማን ደፍሮ ሊጠይቅ! የብርሃኑ ዝርፊያ ብዙ አይነት ነበር፡፡ በብዙ መቶዎች የሚያስተናግደውን የሰራተኞች ክበብ መሪዎቹን አባሮ ክበቡን በቁጥጥሩ ሥራ ካደረገ በኋላ ከመርካቶ (ከሰፈሩ ሰባተኛ) ጩልሌ ልጆች ቀጥሮ የክበቡን ገቢ እየሰነጠቀ ሙልጭ አርጎ በልቷል፡፡ ሲሾም ያልበላ አይነት! ለምንስ አይዘርፍ ማን ሊጠይቀው! እንደገና ደርግ ሊወድቅ በሚንገዳገድበት ጊዜ የሞት የሽረቱን የኢትዮጵያን ወጣቶች እያስገደደ ለብሄራዊ ውትድርና ይመለምል ነበር፡፡ ካድሬዎች በየቀጠናው ኢሰፓ አንደኛ ፀሐፊዎች አመራር በኮሚቴ ምልመላውን ተያይዘውት ነበር፡፡ ብርሃኑ ደርቡም የአንዱ ቀጠና ኮሚቴ አባል ነበር፡፡ በወቅቱም ሀብታሞች ልጆቻቸው እንዳይዘምቱባቸው ለአንድ ልጅ እስከ 2000 ብር ይከፍሉ ነበር፡፡ እያንዳንዳቸው ቀጠናም የተወሰነ ኮታ መምታት ስለነበረበት ጉቦውን ከበሉ በኋላ በምትካቸው የድሃ ልጆችንና የጎዳና ተዳዳሪዎችን እያፈሱ ኮታቸውን ያሟሉ ነበር፡፡ ደቡርና መሰል ጓደኞቹ!
ብርሃኑ ደቦር የዳምጤ ልጅ ይሁን አባ መላ ምን ያላደረገው ነገር አለ፡፡ በስልጣኑ በመጠቀም መሬት ተመርቶ ጉለሌ ጳውሎስ ሆስፒታል ጀርባ ቪላ ቤት መሥራት ጀመረ፡፡ ቤቱም በሚያስደንቅ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገባደደ፡፡ አያስገርምም፡፡ ጥሬ እቃዎቹ በሙሉ የተበረከቱት በልዩ ልዩ ነጋዴዎች ሲሆን መሃንዲዎቹና እንጨት ማገሩን የግብርና ሚኒስቴር ነበሩ፡፡ በነገራችን ላይ አምፑል እንኳን ከኪሱ አውጥቶ አልገዛም፡፡ ምላጩ ደቡር አባመላ በዚህ አላበቃም ቤት መሸጥ መለወጥ በተከለከለበት ዘመን አንድ ቀን እንኳ ያላደረበት ቤት ጠግሮ ዶላሩን አጥቁሮ ማንም ሳይሰማ ሽል ብሎ አሜሪካ ገባ፡፡
ያ ተበድሮ ያላወራረደው ገንዘብ በግብርና ሚኒስቴር የፋይናንስ ሰራተኞች ደመወዝ እየተቆረጠ ለመስሪያ ቤት ገቢ ተደረገ ‹‹አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ›› አይነት!
ከላይ የብርሃኑ የዘር አመጣጥ የጠቀስኩት ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡ ብርሃኑ የቀንደኛው ወያኔ ግልገል የግርማ ብሩ የአክስት ልጅ ነው፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለግርማ ብሩ አጎቱ ነው፡፡ በግርማ ወልደጊዮርጊስ ልጀምር ይቅርታ በአክብሮት ባለመጥራቴ አክብሮት አይገባውምና! ይህ ሰው ሁለት ዘመን እያምታታና እያጭበረበረ የኖረ ሲሆን አሁን በሶስተኛው መንግስት ፕሬዚዳንት ሆነ፡፡ በንጉሱ ዘመን የፓርላማ አባልነቱን ወደ ኋላ ትቼ በደርግ ጊዜ የፈፀማቸውን ድርጊቶች ላውሳ፡፡ የኤርትራ ክፍለ ሀገር ሲቪልአቪየሽን ሀላፊ ሆኖ ተሾመ፡፡ ከጥቂት አገልግሎት በኋላ በይዘቱም ይሁን በቅርፁ ከርሳሙ መቶ አለቃ ግርማ ተስባብሮ የኤርትራ የትራንስፖርት አላፊ ለመሆን በቃ ቦታውን የፈለገው ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡ ‹‹ቦታው የወርቅ ማዕድን ነበርና›› በወቅቱ በደርግ አሰቃቂ ግፍ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ንብረታቸውን እየተው ሀገራቸውን ጥለው ወደ ውጪ ሀገር ወይም ወደበረሃ የሚጠፋበት ጊዜ ነበር፡፡ ምስኪኖች ሞትን ፈርተው! ‹‹ቀልጣፋው›› መቶ አለቃ ግርማ የየብሱና የባህሩ ትራንስፖርት ሀላፊው በመሆኑ የኤርትራውያኑን ምርጥ ምርጥ መኪናዎች ከምጽዋ አሰብ እየላከ በልጁ በሰለሞን ግርማ አማካኝነት አዲስ አበባ መሃል አገር እየቸበቸበ ብዙ ገንዘብ ካዝናው ውስጥ አስገብቷል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በልጁ ስም አንድ የንግድ ድርጅት አቋቁሞ ከሩቅ ምስራቅ የተዋጊ አውሮፕላኖችን መለዋወጫ የአውሮፕላን ቦንቦችና ሌላም ነገሮች መንግስት በማቅረብ ከፍተኛ ገንዘብ በኮሚሽን አግኝቷል፡፡ ‹‹ወያኔ እንደገባ በመገናኛ አውታሮች ሰለሞን ግርማ በወንጀል እንደሚፈለግ የለፈፈውን ያጤኗል እንደ አባት እንደልጅ እንዲሉ›› ሰለሞን ተቀለጣጥፎ ሩቅ ምስራቅ ኮበለለ፡፡ አሁን የት እንዳለ አላውቅም፡፡ መቶ አለቃ ግርማ ይበልጥ የሚታወቀው በስነ ምግባር ብልሹነቱና በሴሰኝነቱ ሲሆን የአስራ አራትና የአስራ አምስት እድሜ ያላቸውን ወጣቶች በሌሊት ሶስትና አራቱን እያበላሸ ያድር እንደነበር ይታወቃል፡፡
ለምሳሌ ያህል ከሁለት ወጣት እህትማማቾች ልጆች ማስወለዱም ይታወቃል፡፡ አብረኸት የተሰኘችውን የ12ኛ ክፍል ውሽማውን የምጽዋ ትራንስፖርት ሃላፊ በማድረግ የምሁራን ሠራተኞችን ሞራል አዳሽቋል ከርሳሙ መቶ አለቃ ግርማ የአሁኑ ፕሬዚዳንት! ያች ልጅ ‹‹Suger Dady›› ብላ የፃፈቸውን ያጤኗል፡፡
ግርማ ብሩን በተመለከተ ጎበዝ የቀለም ተማሪና በጣም ቀዝቃዛ ሰው ነበር፡፡ ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ በኢህአፓነት ተጠርጥሮ ደብረዘይት ከተማ ታስሮ ሲያበቃ የተፈታ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲውን ከጨረሰ በኋላ አንገቱን ደፍቶ በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ወንበር ያሞቅ ነበር፡፡ ወያኔ ከገባ በኋላ ከአጎቱ ከግርማ (መቶ አለቃ) ጋር በመሆን የሶዶ ጅዳ ተወካይ በመሆን ተሽሎክልኮ ባልዋለበት የኦህዴድ አባል በመሆን እስከ ሚኒስቴርነት ደረሰ፡፡ ይህ የድንጋይ ስር እባብ ምን ያህል ጨቋኝ አድርባይ ስለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነውና ብዙ አልዘበዝብም፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሶስት ዘመዳም ጉዶች አጋምጃን ይወክላሉ? የባልቻ አባ ነፍሶ አገር እነዚህን ጎዶች ታብቅል? ባልቻ አባ ነፍሶስ ምን ይሰማው ይሆን መልሱን ለአባ  ነፍሶ አፅም ትቸዋለሁ፡፡
በቸር ይግጠመን
መስፍን ቀጮ/ወፍ
ከጠቅላይ ቢሮ
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ ያልጠሩ ፓርቲዎችን አስጠነቀቀ

                   

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በፓርቲያቸው የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት በወቅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ያላደረጉ ፓርቲዎችን አስጠነቀቀ።
ቦርዱ ሰሞኑን ለፓርቲዎቹ አመራሮች ደብረዘይት በሚገኘው የስራ አመራር ኢንስቲትዩት ውስጥ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከሰጣቸው በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠሩ የሚያሳስብ ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል።
ቦርዱ በፓርቲዎቹ በበተነው ደብዳቤ እስካሁን በውስጥ ደንባቸው መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያሳለፉ ፓርቲዎች ጉባኤያቸውን በማካሄድ ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ቦርዱ ጉባኤ አልጠሩም ላላቸው ፓርቲዎች የላከው ደብዳቤ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ሪፖርት እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ነው።
ቦርዱ ለፓርቲዎቹ እስከ ሚያዚያ 30 ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠሩ ቢያዝም አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ከአቅም ማነስ ጋር በተያያዘ ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት እንደሚቸገሩ በመግለፅ ላይ ናቸው። አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች አንዴ ከተመሠረቱ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ አመራር መምረጥ እንዳልቻሉ ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ፓርቲዎቹ በሚመሩበት ሕገ-ደንብ መሠረት ጉባኤ በማካሄድ አመራር ከመመረጥ ይልቅ ልዩነት ሲፈጠር ብቻ ጉባኤ እንዲጠራ ቦርዱን እንደሚጠይቁ የታወቀ ሲሆን፤ ቀላል የማይባሉ ፓርቲዎች መሪዎቻቸውና የፓርቲዎቹ አድራሻ እንኳ የማይታወቅበት አጋጣሚ እንዳለም ለቦርዱ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይገልፃሉ።
ባለፈው ዓመት በወቅቱ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራትና አግባብ ያለው የሂሳብ ሪፖርት ላቀረቡ 13 ለሚሆኑ ፓርቲዎች ቦርዱ የምስጋና ደብዳቤ መፃፉ ይታወሳል። ቦርዱ ጉባኤ ያልጠሩ ፓርቲዎችን በአግባቡ ለመቆጣጠር የሕግ ክፍተት መኖሩን አንዳንድ የፓርቲ አመራሮች ተናግረዋል። ፓርቲዎቹ ሲመሰረቱ ብቻ እውቅና ለመጠየቅ ወደ ቦርዱ ከመሄድ ውጪ አንድ ጊዜ እውቅና ካገኙ በኋላ አድራሻቸው የሚጠፋበት አጋጣሚ እንዳለም እየተነገረ ነው። በአሁኑ ወቅት ጉባኤ ጠርተው አመራራቸውን ላላሳወቁ ፓርቲዎች ቦርዱ የፃፈው ደብዳቤ ከማሳሰብ ባለፈ ጥርስ እንደሌለው የሚገልፁ አሉ።
በአሁኑ ወቅት 79 ፓርቲዎች ሲኖሩ፤ 54 የሚሆኑ በክልል የተደራጁ ቀሪዎቹ 24 የሚሆኑ ደግሞ ሀገር አቀፍ መሆናቸው ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ቦርዱ ለፓርቲዎቹ ስለፃፈው ደብዳቤ ተጨማሪ ማብራሪያ የተጠየቀ ሲሆን፤ ማሳሰቢያው ለፓርቲዎቹ በማስታወቂያ እየተገለፀ መሆኑን በመግለፅ ወደፊት ከፓርቲዎቹ ጋር በመመካከር ምን ያህል ፓርቲዎች ጉባኤ እንዳልጠሩና እነማን እንደሆኑም ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የኦሮሚያ ልዩ ዞኖችን በሚያጠቃልለው ማስተር ፕላን ላይ መግባባት አልተቻለም

 

ታምሩ ጽጌ
740px-Oromia_in_Ethiopia.svg-በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማስተር ፕላኑን ተቃወሙ
-ከአዲስ አበባ አዳማ በአዲሱ መንገድ ግራና ቀኝ መሬት መሸጥ ቁጥጥር ሊደረግበት ነው
አዲስ አበባ ከተማና በዙሪያዋ የሚገኙትን አምስት ልዩ የአሮሚያ ዞን ከተሞች ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሱሉልታ፣ ለገጣፎና ገላን አጠቃሎ በተሠራው ማስተር ፕላን ላይ መግባባት ባለመቻሉ ግምገማዊ ውይይት በማድረግ የመግባቢያ ፊርማ ለማድረግ የተጀመረው ስብሰባ ሳይጠናቀቅ መቋረጡን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም. የልዩ ዞኑና የአዲስ አበባ ከተማ ተወካዮች በማስተር ፕላኑ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የተሰበሰቡ ቢሆንም፣ በተሠራው ማስተር ፕላን ላይ አንድ ዓይነት አቋም ሊይዙ አለመቻላቸው ታውቋል፡፡ ከአንዳንድ ተሳታፊዎች መግባባቱን ወደኋላ ሊመልሱ የሚችሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በመነሳታቸው፣ በዕለቱ ይካሄዳል ተብሎ በነበረው የጋራ ውይይት ላይ ልዩነት መፈጠሩን ምንጮች አስረድተዋል፡፡
በአዳማ በተደረገው ውይይት በልዩ ዞኖቹ በኩል የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድና አዲስ አበባን በመወከል ከንቲባ ድሪባ ኩማ በጋራ ውይይቱን የመሩት ቢሆንም፣ በውይይቱ የተሳተፉ የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎችና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባነሱዋቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምክንያት በዕለቱ ሊቋጭ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው ግምገማዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን መሠረት ያደረገ የጋራ ማስተር ፕላን አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት፣ የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቁሞ፣ ከስምንት ዓመታት በላይ ጥናትና ውይይት ከተደረገበት በኋላ፣ ማስተር ፕላኑ ተሠርቶ መጠናቀቁንና በመጪው ግንቦት ወር ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡
ፕሮጀክቱ በ1996 ዓ.ም. በቀድሞው ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ መጠንሰሱን የሚናገሩት ምንጮች፣ ለፕሮጀክቱ መጠንሰስ ዋና ምክንያት የሆነው በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙት የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ታሳቢ ያደረገ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
በተሠራው ማስተር ፕላን ላይ ሁለቱ ወገኖች ተወያይተውና ተፈራርመው ለመለያየት በአዳማ ያደረጉት ስብሰባ በተለይ በአንዳንዶቹ የውይይቱ ተሳታፊዎች ያልተጠበቀ ጥያቄና አስተያየት ግራ የተጋቡት አቶ ድሪባ፣ ስብሰባውን ለመገናኛ ብዙኃን ዝግ በማድረግ ውይይቱን መቀጠላቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡
ጥያቄዎቹና አስተያየቶቹ የተነሱት ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ባሉ ግለሰቦች በመሆኑ፣ ምናልባት ስለማስተር ፕላኑ በቂ ግንዛቤ እንዳልተፈጠረ በመገንዘብ እንደገና ግንዛቤ ለማስያዝ ስብሰባው በዝግ እንዲካሄድ ሳይደረግ እንዳልቀረ ምንጮች ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡
ማስተር ፕላኑን በሚመለከት መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም. አዳማ ላይ ተደርጎ የነበረው ግምገማዊ ውይይትና ይፈጸማል ተብሎ የነበረው የስምምነት ፊርማ ለምን እንደተቋረጠ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳዊት ንጉሴ፣ ስብሰባው ተደርጎ እንደነበር አረጋግጠው፣ በወቅቱ መፈራረሙ የቀረው ስምምነት ጠፍቶ ሳይሆን፣ ለሁለት ቀናት ይደረጋል የተባለው ግምገማዊ ውይይት በአንድ ቀን እንዲያልቅ በመደረጉና ጊዜ ባለመብቃቱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ማስተር ፕላኑ አዲስ በመሆኑ መረጃ የሚፈልጉ ወገኖች እንደነበሩና ጥያቄ ማንሳታቸውን የገለጹት አቶ ዳዊት፣ አንዳንድ ግለሰቦች፣ ‹‹አዲስ አበባ ኦሮሚያን አስፋፍታ ልትይዝ ነው፣ ወደ ኦሮሚያ ምድር ልትስፋፋ ነው፤›› የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ መያዛቸው፣ ለጥያቄያቸው በቂ ምላሽ እንደተሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በበላይ አመራሮችና በቦርድ የሚመራ በመሆኑ፣ በሁሉም ነገሮች ላይ ስምምነት ላይ ተደርሶ ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሆነና ምንም ዓይነት ችግርና አለመግባባት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡
ልዩ ዞኖቹን ያጠቃለለውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች ተቃውመዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ‹‹ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆኗ በሕገ መንግሥታችን ተደንግጎ እያለና በሕገ መንግሥት አንቀጽ 49(5) ላይ በጉልህ ኦሮሚያ ከፊንፊኔ አስተዳደር ልዩ ጥቅም ይከበርላታል በሚል ቢደነገግም፣ መንግሥት በተገላቢጦሽ በፊንፊኔ ዙሪያ ያሉትን ከተሞች በልማት ሰበብ በፊንፊኔ ሥር ለማዋል የሚያደርገው የረቀቀ ተንኮል ሕገ መንግሥቱን የሚስ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የኦሮሞ ሕዝብ ሳይወያይበት፣ ሳይመክርበትና ምክንያቱን ሳይረዳ በሁለቱ ወገኖች ውሳኔ ብቻ መደረግ ስለሌለበት ድርጊቱ በአስቸኳይ እንዲቆምም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል፡፡
በማስተር ፕላኑ 85 በመቶ የሚሆነው መሬት ለግብርና የሚውል ሲሆን፣ 15 በመቶ የሚሆነው ለመኖርያ ቤት ግንባታ የሚውል ነው፡፡ በአጠቃላይ በማስተር ፕላኑ ክልል ውስጥ 13 ሚሊዮን ሕዝብ ይኖራል ተብሎ ሲገመት፣ ስምንት ሚሊዮኑ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እንደሚኖሩ፣ በነበረው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እስከ 55 ፎቅ ብቻ መገንባት ይቻላል የሚለው ተነስቶ ከዚያም በላይ መገንባት እንደሚቻል ታውቋል፡፡
ማስተር ፕላኑ የሚያቅፋቸውን ልዩ ዞኖች በተለይም ከአዲስ አበባ አዳማ በተሠራውና በቀጣይም በሚሠራው ዋና መንገድ (ኤክስፕረስ ዌይ) ግራና ቀኝ ያሉ መሬቶች በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ሕገወጥ በሆነ መንገድ እየተቸበቸቡ መሆኑን ተከትሎ፣ ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ መወሰኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድ ትዕዛዝ ምንም ዓይነት የመሬት ሽያጭ በሕገወጥ መንገድ እንዳይካሄድ ለማድረግ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉ ተገልጿል፡፡

ከምዕራብ ሸዋ ተፈናቅለው በፌዴሬሽኑ አፈ ጉባዔ አግባቢነት የተመለሱት ዜጎች መሬታቸውን በሃይል ተነጠቁ

 

geberewoch ethiopia
ከዳዊት ሰለሞን
ከሰላሳ የማያንሱ የምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ ባጅላ ዳሌ ቀበሌ ገ/ማህበር ነዋሪዎች ‹‹ ወደ ክልላችሁ ተመለሱ ›› ተብለው መሬታቸውን ለመነጠቅ መቃረባቸውን ለማመልከት አዲስ አበባ በመምጣት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተ/ብርሃንን ካናገሩ በኋላ አፈ ጉባኤው ‹‹ወደ ቀዬአችሁ ተመለሱ እኔ ችግሩ እንዲፈታላችሁ አደርጋለሁ››በማለታቸው ገበሬዎቹ ወደ አምቦ መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡
ወደ አምቦ የተመለሱትን ገበሬዎች የዞኑ ሃላፊዎችና የኦህዴድ ካድሬዎች ‹‹አዲስ አበባ በመሄድ ገመናችንን አጋለጣችሁ››በማለት ሲዝቱባቸው መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ከትናንት ጀምሮም የታጠቁ ሚሊሻዎችን በማስከተል የቀበሌ ገ/ማህበሩ አመራሮች‹‹መሬታችንን ለቃችሁ ወደ መጣችሁበት ክልል ተመለሱ ››በማለታቸውና ገበሬዎቹ ‹‹ አንለቅም ከዚህ ውጪ አገር የለንም›› ቢሉም በመሳሪያ በማስፈራራት ከአካባቢው እንዲርቁ በማድረግ መሬቱን ለሚፈልጓቸው ሰዎች ማከፋፈላቸውንና ሊደበድቡንና ሊገድሉን ይችላሉ ብለው የሰጉ ገበሬዎችም ልጆቻቸውንና ባለቤቶቻቸውን በመያዝ ጫካ መደበቃቸውን በስልክ ከስፍራው ያናገርኳቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡ገበሬዎቹ ከዛሬ ሀያ ዓመት በፊት ከጎንደር አካባቢ ተፈናቅለው አሁን ለስደት በተዳረጉበት አካባቢ የሰፈሩ ነበሩ፡፡
ገበሬዎቹ ለአቤቱታ አዲስ አበባ መጥተው በነበረበት ወቅት ለምን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር ሄዳችሁ ተብለው መታሰራቸው አይዘነጋም፡፡

ኦሮሞ ነኝ የሚለው ብዙው ሕዝብ በታላቁ ኢትዮጵያዊ ሚንሊክ ላይ ያለው ጥላቻ ከምን የመጣ ነው?

የታላቋ ቀን ልጅ
ሚያዝያ 1 2006 ዓ.ም.

minilik
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሚንሊክ
እጅግ ክፉና ማንነትን ከሚያዋርዱ ነገሮች አንዱ አእምሮን ከእውነትና ማስተዋል አስርቦ መነሻው ምን እንደሆነ ብዙዎች በማያውቁት ስሜተኝነት መነዳት ነው፡፡ ይን የሰው ልጆችን በስሜተኝነት የመጥለፍ አጋጣሚን ለመፍጠርና በተፈጠረውም አጋጣሚ ራሳቸውን አግዝፈው የሚኖሩ ግን በተፈጥሮ ብስለታቸው የወረዱ ሌሎችንም በእነሱ ደረጃ ከእነሱም ባነሰ ሊያዋርዱ ሌሊት ከቀን እንቅልፉ የሌላቸው ከዚያም በላይ በዕርኩሳን መናፍስት የሚታገዙ ሰብዐዊ ፍጡሮች በዙሪያችን እንደሚያንዣብቡ ብዙዎቻችን አንረዳም፡፡ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች አእምሮአቸው በጎ እንዳያስብ የነጠፈና  በምትኩ ክፋትን ከቀን ወደቀን በማሳደግ ራሱን ሰይጣንን የሚተካ ባሕሪን ያዳበሩ ናቸው፡፡  በዚህ አደገኛን በመረቀዘ አእምሮአቸው ሌሎችን የመርዛሉ ያጠፋሉ፡፡ እነዚህ ሰው የሚመስሉ ግን በአካል የሚንቀሳቀሱ ሰይጣኖች ከሚበዙባቸው ቦታዎች ደግሞ ሕዝብ ትላልቅና የተከበሩ ብሎ በሚያስብባቸው ከፍተኛ አመኔታ በሚሰጣቸው ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የፖለቲካ የሥልጣን መዋቅሮችና የሐይማኖት ተቋሞች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ መዋቅሮች ባሉ መሪዎች ላይ ሰዎች ከፍተኛ አመኔታን ይሰጣሉ፡፡ ግን ብዙ ጊዜ ለአመኔታቸው አጸፋው መልካም ነገር ላይሆን ይችላል፡፡ ብዙም ጊዜ ወድቀትና ወርደት ይሆናል፡፡ ሁለቱም መዋቅሮች እጅግ የበሰለ አእምሮን፣ ቅንነትን፣ የሕዝብ እንደራሴ መሆንን የሚጠይቁ ቢሆም በብዙ የታሪክ ገጠመኞች ግን ተቃራኒው ሲሆን ይስተዋላል፡፡ በአሁን ዘመን ደግሞ ከመቼውም የከፋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እነዚህ ከላይ የተጣለውን ሰይጣን የሚወክሉ ሰብዓዊ ፍጥረቶች በቅንነትና በበሰለ አእምሮ ለሕዝብና ለአገር ክብር የነበሩ ሰዎች ታሪካቸው እንዳይታወቅ፣ ከታወቀም ራሳቸው በፈጠሩት ሌላ ታሪክ የእነዚህን ባለታሪኮች ታሪክ በማጉደፍና የቀደመ ታሪክን የማያውቅ ሌላ እነሱን የመሰለ ትውልድ ተክቶ የታላላቅ ባለራዕዮችን ታሪክ ጨርሶ እንዲጠፋ በማድረግ የእነሱን ኑሮ ማደላደል አንዱ መገለጫቸው ነው፡፡
እኔ የምናገረው ከስሜተኝነት የተነሳ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ግን የተረዳሁትን ያህል እናገራለሁ፡፡ ባለማወቅ ግን ልሳሳት እችላለሁ እኔ የተረዳሁት ስህተት ሊሆን ስለሚችል፡፡ የሚያርመኝ ካለም እቀበላለሁ፡፡ ደግሜ እናገራለሁ ከሥሜት የተነሳ አላወራሁም፡፡
በእኔ ግንዛቤና መረዳት በአለፉት አምስተ መቶና ምንአልባትም ከዚያም በላይ እንደ ኢትዮጵያዊው መሪ ሚንሊክ ያለ መሪ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካም ብቻ ሳይየሆን በአለም ላይ ነበረ የሚለኝን የታሪክ ምሁር ትንተና እሻለሁ፡፡ እኔ በአለፉት አምስት መቶ ከዚያም በላይ በሚሆን ዘመን እንደ ኢትዮጵያዊው ሚንሊክ ያለ ታላቅ መሪ እንዳልነበረ አስባለሁ፡፡ በእኛው ዘነድ ስለሚንሊክ ያለን ግንዛቤ ወይም ከላይ በጠቀስኳቸው የወረዱ አእምሮዎች የጎደፈ ወይም በእጅ የያዙት ወርቅ አይነት ብዙም ትኩረት ያልሰጠነው ይመስለኛል፡፡
ዛሬ በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚንሊክ ታሪክ እንኳንስ የማንነታችን መገለጫ አድርገን የምንኮራበት በአንደበታችንም ለመናገር የሚቀፈን ሆኗል፡፡ ብዙዎቻችንም በመርዝ በተለወሰ ሌላ ታሪክ አእምሮአችን የታላቁን ሰው ታሪክ የሚያጎድፍ፡፡ በተለይም  በኢትርዮጵያ ትልቅ ቁጥር አለው ተብሎ በሚታመንለት ኦሮሞ እየተባለ በሚጠራው አብዛኛው ሕዝብ ዘንድ ዛሬ የሚንሊክ ጉዳይ ሲነሳ ያስበረግገዋል፤ እጅግ ያስቆጣዋል፤ ሥሙን አታንሱብኝ ይህን ሥም ከታሪክ ደምስሱት ጩኸት ያሰማል፡፡ ምክነያት ተብሎ ሲጠየቅ በዋነኝነት ብዙ ጊዜ የሚነሱት በሐረር የጨለንቆ ጦርነትና በአርሲ በሚንሊክ ዘመቻ ተፈጸሟል ተብሎ በዘበናውያን ታሪክ አዋቂዎች ነን ባሉ የተሰበከው የጡትና እጅ መቁረጥ (ሀርካ ሙራ ሐርማ ሙራ) ግፍ ነው፡፡
ሚንሊክን ታላቅ ከሚያሰኛቸው ታሪክ አንዱ ዛሬ ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራትን አገር አንድ በማድረጋቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያን አንድ ያደረጉበት ሂደት ደግሞ አልጋ በአልጋ የነበረ ሳይሆን ከብዙ በየስፍራው በነበሩ መሳፍንቶች ጋር ተዋግተው ነው፡፡ በወቅቱ እንደአሁን ዘመን ዲፕሎማሳዊ ሂደት ብዙም የሚያስኬድ አልነበረም፡፡ ሆኖም ሚንሊክ እርግጥም ከዘመኑ በፊት የተፈጠሩ ታላቅ ሰው ስለነበሩ ዲፕሎማሳዊው ሂደት ሁል ጊዜም ቅድሚያ የሰጡት ነበር፡፡ አንድም መስፍን (የአካባቢ መሪ) የሚንሊክን ታላቅ ራዕይ ሳይቃወም ጦርነት የከፈቱበት የለም፡፡ በወቅቱ ግን በነበረው የመሳፍንቶች ኋላ ቀር አስተሳሰብ ከሚንሊክ የቀደመ አስተሳሰብ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ የሚንሊክን አገርን የመገንባት ሂደት የሚተባበር አልነበረም፡፡ የእነዚያ ኋላ ቀር የአካባቢ መሪ ተብዬዎች ሕልም ለራሳቸው ከርስ የሚሞላ ሕዝብን ከመግዛት ያለፈ የዕድገትና ብልፅግና ሕልም ከቶውንም አልነበራቸውም፡፡ ይህ ደግሞ የሕዝብና የአገር ውርደትና ኋላ ቀርነት እንደ እሳት ለአንገበገበው ሚንሊክ እንቅፋት ነበር፡፡ በመሆኑም ሚንሊክ የወደደውን በውድ ያልወደደውን በግድ ማሳመን ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ከብዙ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ካላቸው የአካባባ መሳፍንት ጋር ጦርነት ገጥመዋል፡፡ በጦርነቶቹ ሁሉ የባለራዕዩ የበላይነት የግድ ቢሆንም ጦርነት ጦርነት ነውና ብዙ ጥፋቶች ጠፍተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የሰዎች ልጆች አልቀዋል፣ ተሰቃይተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ግን የሚንሊክ ፍላጎት ሳይሆን የመሳፍነቶቹ ምርጫ ነበር፡፡
በሀረር ጨለንቆና አርሲ የተከሰቱ ጦርነቶች ሚንሊክ አገርን ለመገንባት ካደረጓቸው ሁለቱ ናቸው፡፡ የጨለንቆው ጦርነት በአስከፊነቱ ብዙ ሕዝብ ያለቀበት ቢሆንም በጦርነት ከሚከሰቱ የተለመዱ ጥፋቶች ሌላ ለየት ያለ የታሪክ ጠባሳ ያቆየ አልመሰለኝም፡፡ የአርሲው ጦርነት ግን እስከዛሬም ድረስ እንዲረሳ አጋጣሚን ለመጠቀም በሚፈልጉ መርዘኞች እንደ መሣሪያነት እያገለገለ ነው፡፡
ሀርካ ሙራ ሐርማ ሙራ! በአማርኛ እጅ መቁረጥ ጡት መቁረጥ ማለት ነው፡፡ ይህ አሳቃቂ ግፍ በአርሲው የሚንሊክ ዘመቻ ተከስቷል እየተባለ ዛሬ ባለው ትውልድ ልዩ ስፍራ የተሰጠው አልፎም ሐውልት የቆመለት ጉዳይ ሆኗል፡፡ እኔ እንዲህ ያሉ ግፎች በዚያ ዘመን በነበሩ ጦርነቶች ሊከሰቱ ከሚችሉ አሳቃቂ ክስተቶች አንዱ ሊሆኑ እንደሚችሉ አምናለሁ፡፡ ሆኖም በአርሲ ተከሰተ የተባለው እንዲህ ያለ ግፍ የታላቁ ሰው ሚንሊክ ትዕዛዝና ይሁንታ አለበት ብዬ አላምንም፡፡ በብዙ ጦርነቶች እንደሚከሰተው፣ ይልቁንም በዚያ የጠበቀ የጦርነት የመምራት አቅምና ቅንጅት በሌለበት ዘመን ከተዋጊዎች አንዱ ወይም ከዚያም በላይ እንዲህ ያለውን ጥፋት ፈፅመውት ይሆናል፡፡ ሚንሊክ ግን እንዲህ ያደረጉትን ወታደሮች ማንነት ቢያውቁ የሚሸልሟቸው እንዳልሆኑ አምናለሁ፡፡ ይልቁንም በሞት ሳይቀር ሊቀጧቸው እንደሚችሉ አምናለሁ፡፡ ይህ የሚንሊክ እውነተኛው ልብ ነው! ሚንሊክ እውነተኛ ጀግና የሚባል ባሕሪ ያላቸው ናቸው፡፡ ጀግና ደግሞ ጨካኝ አይደለም! ጀግና ጠላቶቹ የማይቋቋሙት እንጂ! እነኳንስ በሴቶችና አቅም በሌላቸው ላይ ሊያጠፋቸው የመጣን ጠላት እንኳን ከመግደል ይልቅ ከእነነፍሱ ይዘው ምህረትን ሊያደርጉለት የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ጠላታቸውን እንኳን ገድለው በሬሳው ላይ የሚጨፍሩ አይደሉም፡፡ ይልቁንም አስቸጋሪና የተቋቋማቸው ጠላታቸውን ሲጥሉት ለአስከሬኑ ሳይቀር ክብርን የሚሰጡ ናቸው፡፡ እንዲህ ያለው ተቃራኒ ጠላት የሆነ ግን ጀግና አስከሬን ለውሻና ለአውሬ የሚሰጡ ሳይሆን በክብር የሚቀብሩ ውጊያውን የአላማ እንጂ የተፈጥሮ ጠላትነት እንዳልሆነ የሚያስቡ ናቸው፡፡ ሰውን በሰበዐዊነቱ የሚያከብሩ ልዩ አመለካከት ያላቸው ናቸው፡፡ ይህ የእውነተኞቹ ጀግኖች ልዩ መገለጫ ነው፡፡ ሚንሊክ ይህ ባሕሪ ልዩ መገለጫቸው ከሆኑ አንዱ ነበሩ! በነዚህ መስፈርቶች መሠረት ግን ብዙዎች በኢትዮጵያ ጀግኖች እየተባሉ የተወደሱትን ማንነት ቴዎድሮስን ጨምሮ እጠራጠራለሁ፡፡ ይልቁንስ በቅርብ ታሪክ የምናውቀው ሕወሐት አባል የነበረው ኃያሎም አረአያ እነዚህ የጀግኖች ልዩ መገለጫ ያልኳቸው ባህሪያት እንደነበሩት ብዙ የሰማቸው ገድሎቹ ይናገራሉ፡፡
እንግዲህ በስሜትና በጥላቻ በመረቀዙ አእምሮዎች ሳይሆን እውነትን ለመጋፈጥ በሚደፍሩ አእምሮዎች እኔ የተረዳሁትን የሚንሊክን ማንነት አይደለም የሚል ካለ ለማደመጥ እወዳለሁ፡፡ ሚንሊክ ሩሩህና ይቅር ባይነታቸው ባደረቸው ጦርነቶች ሁሉ በደረሱ እልቂቶችና ጥፋቶች እጅግ ይጸጸቱ ነበር፡፡ ችግሩ አማራጭ ብቻ በማጣታቸው ጦርነቱ ግድ ሆኖማቸው እንጂ፡፡ በደረሰው ጥፋት ካዘኑባቸው ጦርነቶች አንዱ ደግሞ የአርሲው ጦርነት ነው፡፡ በጦርነቱ አሸንፈው አገሩን ከተቆጣጠሩት በኋላም ወታደሮቻቸውን ሕዝቡ ባለማወቁ ምክነያት የደረሰበትን እልቂት አሳዝኗቸው ወታደሮቻቸውን አሸንፌያለሁ በሚል በሕዝቡ ላይ ሌላ በደል እነዳያደርጉበት አዋጅ አውጥተው ሁሉ ነበር፡፡ ለወታደሮቻቸውም የአርሲን ሕዝብ ሲገልጹት ወንድምህ የአርሲ ሕዝብ እያሉ ነበር እንጂ እንደ ጠላት አልነበረም፡፡ ይህን እውነታ የታሪክ አዋቂ ነን የሚሉት ለምን ለሕዝብ ለማሳወቅ አልፈለጉም፡፡ ይልቁንስ የሚንልክ ትዛዛዊ ግፍ ለመሆኑ አጠራጣሪ ስለሆነው ሀርካሙራና ሀርማ ሙራ ማግዘፍን ለምን ፈለጉ፡፡ ሌላው የሚንሊክ ማንነት የተገለጸበት ጦርነት የወላይታው ከንጉስ ጦና ጋር የነበራቸው ጦርነት ነው፡፡ ንጉስ ጦናን አሸንፈው በእጃቸው ካገቡና አላማቸውን ከአሳመኗቸው በኋላ ንግሰናቸውን አጽድቀው እንደሾሟቸው ይነገራል፡፡ ከዚያም በላይ ጦና በጦርነቱ በመቁሰላቸው ምክነያት ሌላውን ሰው ባለማመን ሚንሊክ ራሳቸው እየተከታተሉ እንዲታከሙ ማድረጋቸው ይነገራል፡፡ ሌሎችም አያሌ የሚንሊክን ሕይወት የሚናገሩ መዛግብቶች ሩሩሕና የጅግና ሰው ልዩ መገለጫ የሆኑትን ባሕሪያቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ሚንሊክ ጋር በቀል የለም ጭጋኔም የለም የአላማ ጽኑነትና ታላቅነት እንጂ፡፡ ዘረኝነትም የለም ሰበዐዊነት እንጂ፡፡ በሚንሊክ አስተዳደር ወቅት ኢትዮጵያ ዘመናዊ በሚመስል ፌደራሊዝም ትተዳደር እንደነበር ስነቶቻችን እናውቃለን? አንዳንድ የሚንሊክን አላማ ለመረዳት እመቢ ባሉ መሳፍንት በቀር ከጦርነት በኋላ ሳይቀር ለእነዚያው የተዋጓቸው መሳፍንት ስልጣንን በሰጠት የራሳቸውን አካባቢ እንዲያስተዳድሩ ያደርጉ ነበር፡፡ በወቅቱ የተሸለ ግንዛቤ የነበራቸው እንደነ አባ ጅፋር የጅማው ያሉ የሚንሊክን አላማና ራዕይ ለመረዳት ስላልተቸገሩ በሠላም በአገር አንድ ማድረጉ ሂደት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የሚንሊክ እውነተኛው ታሪክ ዛሬ ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራትን አገር የፈጠሩ፣ አለም ላይ በእሳቸው ዘመን ኡሉ የተባሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ወደ አገር ያስገቡ እነዚህም ስልክ፣ ኤሌክትሪክ፣ መኪና፣ ባቡር፣ ሌሎችም፣ አገርን በዘበናዊ አስተዳደር እንድትመራ የዋቀሩ (ሚኒስቴር መሠረት ያደረገ) ሌሎች ብዙ በአንድ ሰው እድሜ ሊሰሩ የሚችሉ የማይመሰሉ ብዙ ራዕዮችን በተግባር ያስጀመሩ ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ ማድረጋቸው ሳያንስ ሚንሊክን ከቅርብ ወዳጅ እስከ ሩቅ ባላአንጣዎቻቸው እጅግ ፈታኝ መነቆዎች ነበሩባቸው፡፡ በወቅቱ ባለው ኋላቀር አመለካከት ምክነያት ብዙ የቅርብ የተባሉ የቤተመንግስቱና የቤተክህነቱ ሰዎች እንቀፋቶች እንጂ ለሚንሊክ አጋዥ አልነበሩም፡፡ በሚንሊክ የአገር አንድ የማድረግም ሆነ አገርን ወደ ዘመናዊነት መቀየር ሂደት በተሻለ ወሳኝ ሚና የነበራቸው የውጭ አገር ሰዎችና አንዳንድ የቅርብ አባሮቻቸው ናቸው፡፡ ከቅር አባሮቻቸው ደግሞ በተለይም አገርን አንድ በማድረጉ ሂደት የሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝቦች ከየትኛውም የኢትዮጵ የሕብረተሰብ ክፍል ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ የሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪ በታሪካዊው የአድዋው የሚንሊክ ድልም እንደዛው ከሌሎች በተለየ ነበር፡፡
ዛሬ ላለው አብዛኛው የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ግን የሚንሊክም ታሪክ እነዛ የሚንሊክ የቀኝ ክንድ የነበሩት ኦሮምኛ ተናጋሪ ሸዌዎችም የሚታየው በበጎ ሳይሆን በጥላቻ ነው፡፡ ምክነያቱ ደግሞ የታላቅ ባለራዕዮች ሕልም የማይገባቸው፣ በተንኮል የነወረ አእምሮ ይዘው ታሪክን በማጉደፍ ትውልድን በእነሱ በተመረዘ አእምሮ ለመበከል ያሰራጩት መርዝ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ለአሁኑ ትውልድ የበለጠ የታሪክ ትውስታና ክፉውም ደጉም ከሞላ ጎደል ከሚታወቀው የደርግና የኃ/ሥላሴ ዘመን ስህተቶች ይልቅ የሚንሊክ ዘመን ስህተትን አቅርቦና አግዝፎ ለማሳየት የተመረዙ አእምሮዎች የሚፈጥሯቸው ሀተታዎች ብዙ ናቸው፡፡ ምክነያቱ ግልጽ ነው አሁን ያለው ትውልድ የሚንሊክን ዘመን እውነተኛ ነገሮች በአካል የሚመሰክርለት የለውም ስለዚህ ምስክር በሌለበት በመሰሪዎቹ አእምሮው ሊመረዝ የሚችለው በቆየው ታሪክ እንጅ በአካል ያሉ መስካሪዎች ባሉበት ታሪክን ለመዋሸት ስለማይመች ነው፡፡ ሌላው ሚንሊክ የሠሩትን ታላላቅ ሥራዎች በበጎነቱ ማንሳቱ ራስን የሚያሶቅስ አደጋ ስላለው ነው፡፡ ዛሬ ላለው ትውልድ የሚንሊክ ዘመን ራዕይ ባለዕዳ አደርጎታልና ነው፡፡ በሚንሊክ ዘመን ራዕይ ይህች አገር ቀጥላ ቢሆን የት በደረሰች ነበር፡፡ ሌላው የሚንሊክ ራዕይ የአገር አንድነትና ብልፅግና ልዩ መሠረት ሥለነበር ይህንን መሠረት ሳያፈርሱ ስለዘረኝነት፣ ቀበሌ ዝቅ ብሎም ስለ ጎጥ እንዲያስብ ሕዝብን ማምከን አይቻልም፡፡
ዛሬ ከየትኛውም ክልል ትልልቅ ከሚባሉ ክልሎች በሚያሳዝን ሁኔታ የኦሮምያ ክልል በልማቱም ሆነ በመልካም አስተዳደሩ ወደ ኋላ መቅረቱ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ መሠረታዊ ምክነያቱ ሕዝቡን ከሌሎች ጋርም ሆነ እርስ በእርስ ትብብር እንዳይኖረው የጥላቻን ዘፈን እየዘፈኑለት የራሳቸውን ኑሮ በተፈጠረላቸው አጋጣሚ እንደ ልባቸው የሚኖሩ ኦሮሞ ነን ባይዮች አደገኛ ዜጎች ናቸው፡፡ ይህንን ከሚያክል ትልቅ ክልልና ሕዝብ አይደለም ኢትዮጵያን ሊመራ የሚችል ክልሉን ሊመራ የሚችል ሰው ታጥቷል፡፡ ኦሮሞ ነኝ የሚለው አብዛኛው የዛሬው ትውልድ ትልቁ እርካታው የሌሎች መውደቅ በተለይም ነፍጠኛ እያሉ የሚጠሩት የአማራውና አሁን በስልጣን ላይ በብዛት እንደተወከለ የሚነገርለት የትግራይ ሕዝብ ውድቀት እንጂ የራሱ ብልጽግና አይደለም፡፡ ለኦምኛ ተናጋሪው ክልል በልማትና በአስተዳደር ወደ ኋላ መቅረት ቁጭት ተሰምቶት ሊሰራ ከሚሞክር መሪና ትውልድ ይልቅ ከብዙ አመታት በፊት የተፈጠሩ የታሪክ ስሕተቶች ደግሞደጋግሞ በማላዘን ሌላ መርዛማና በጥላቻ የተበከለ ትውልድ ለማዘጋጀት ተግቶ የሚሰራው በዝቷል፡፡
ዛሬ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሆኖ ያለው ሕዝብ በዘር (በደም) አንድ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ በደም ግንድ ከሆነ የወለጋና ሐረር ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ከሚቀራረበው በላይ የጎጃ አማርኛ ተናጋሪውና የወለጋ ኦሮምኛ ተናጋሪው ይቀራረባሉ፡፡ የባሌና ሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ከሚቀራረቡት በላይ የሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪና የሸዋ አማርኛ ተናጋሪ የበለጠ የደም ትስስር አላቸው፡፡  በባህልም ቢሆን እንደዚያው ነው፡፡ ዛሬ ዘረኝነትንና የቀበሌ አስተሳሰብን የሚሰብኩ ግን ቋንቋን ተመርኩዘው ግዙፉን ሕዝብ በአንድ ከአጨቁትና ከሌሎች ጋር ሕብረት እንዳይኖረው ከአወሩት በኋላ ወደታች ደግሞ በጎሳና፣ ቀበሌ፣ ዝቅ ብለው በጎጥ ይሸነሽኑታል፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ከሌሎች በአካባቢው የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ያልተጋጨው የለም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነበር፡፡ ሕዝቡ ለሌሎች ጥላቻ እንዲኖረው ስለሚሰበክ ነው፡፡ አልፎም ይሄው መለያየትን የሚሰብከው መዝሙር እርስ በእርስ ሳይቀር ጥላቻንና ግጭትን አስነስቶ አይተናል፡  እንደወንድማማች የሚተያዩት ጉጂና ቦረናን ሳይቀር ለከፍተኛ ደም መፋሰስ ዳርጓል፡፡
ይሄው ሃያ ምናምን አመት ሙሉ ስለቀድሙት ገዥዎች ጭቆናና በደል ሲነግሩን፡፡ የቀደሙትስ ጨቋኝና ጨካኝ ሆነው የኦሮሞን ሕዝብ ሲበድሉት ኖሩ ተብሎ ይታሰብ ዛሬስ የዚያን ዘመን በደል ሊያስረሳ የሚችል መሪ እንዴት ከዚህ ትልቅ ሕዝብ መካከል ጠፋ፡፡ እውነታው የቀደሙት ጨካኝና በደል አድርሰውም ከሆን ለኦሮምኛ ተናጋሪው የተለየ አልነበረም፡፡ ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ አማርኛ ተናጋሪ ከነበረው ይልቁንም የነገስታቱ ወገን ነው ተብሎ ከሚታመነው የሸዋ አማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ በቀድሞ ነገስታት የተሻለ ተጠቃሚ እንደነበር እናውቃለን፡፡ ሌላው ቀርቶ የነገስታቱ የቅርብ አጋር እየተባለ ዛሬም ድረስ በሌላው የኦሮምኛ ተናጋሪ በጥሩ አይን የማይታየው የሸዋው ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ በነገስታቱ ዘመን አንዳች ተጠቃሚ እንዳልነበረ አእምሮ ካለን እናስተውላለን፡፡ ለእነዚህ ሕዝቦች ከሌላው በተሻለ የቀረላቸው ሀብት ቢኖር ሌላውን በጥላቻ አለመመልከት ለአገር አንድነትም ልዩ ፍቅር መኖር ነው፡፡
ሌሎች ክልሎች በአቅማቸው ልማታቸውንና የአስተዳደርም ችግራቸውን በፍታት ልዩ መንገድን እየሄዱ ይገኛሉ፡፡ በተለይም የቀድሞው ገዥና ጨቋኝ ተብለው የተፈረደባቸው የአማርኛው ተናጋሪ ሕዝብ ክልል  በቁጭት በሚመስል ሁኔታ እያደገ ለመሆኑ ግልጽ እየሆነና ልዩነቱንም ከሌሎች እያሰፋ መሆኑን እያሳየን ይገኛል፡፡ ትግራይ የገዥውን መንግስት ድጋፍ እያገኝ ስለሆነ ነው እየተባለ ቢታማም እውነታው የእድገት ጥማት ባላቸው መሪዎች ምክነያት እንጂ የማዕከላዊው መንግስት ተፅዕኖ ብቻ እንዳልሆነ እናያየለን፡፡ ደቡብና ሌሎች አናሳ እይተባሉ የሚጠሩ ክልሎች ሳይቀር ከኦሮምያ በተሻለ ዕድገት እያሳዩ ናቸው፡፡ በማዕከላዊውም መንግስት ያላቸው ተሳትፎ ከኦሮምያ ይልቅ የደቡብ የተሻለ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ምክነያቱ ግልጽ ነው ኦሮምያ ኢትዮጵያን በሚወክል አመለካከት ይቅርና ክልሉን እንኳን በሚወክል አመለካከት የተገነባ ሰው ታጥቶበታል፡፡ በደቡብ ብዙ ሕዝቦች ኢትዮጵያዊ መሠረትን በደንብ ያደበሩ ናቸው፡፡ በኦሮምያ  ሌሎችን በመጥላት የተጀመረው ሂደት ዛሬ ወርዶ ቀበሌ ደርሷል፡፡ ወለጋው ወለጋውን፣ አርሲው አርሲውን፣ ታች ወርዶ ደግሞ ሻንቡ ሀረቶ ምናምን እያለ የሚከፋፍል ነው፡፡ ይህ አይነቱ ባሕሪ በሌሎች ክልሎች አይንጸባረቅም ሳይሆን በንጸባረቅም ሌሎች ሌሎችን ጨምረው በሚያማክሉ ከፍተኛ ባለአእምሮዎች ይመክንና ቀበሌ ከሆነ ቀበሌ፣ ከፍ ብሎ በክልልም ከሆን ክልሉን ሳያልፍ ይመክናል፡፡ ኦሮምያ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የወረደውን የጎጠኝነት ስሜትና አመለካከት የሚያመክን ጠፍቶ ትውልዱ በአብዛኛው በወረደው ጎጠኝነት ስሜት መክኗል፡፡
አሳዛኙ ነገር ተማርን የተሸለ የሕወት ልምድ አልን በሚሉት ይህ የአመለካከት ወርደት በርትቷል፡፡ በተለይም ደግሞ በተለያዩ መንገድ ወደ ውጭ ሄዶ በሚኖረው የኦሮምኛ ተናጋሪው ለሌሎች ያለው ጥላቻ እጅግ የከፋ ነው፡፡ አማራ ወይም ትግሬ የሚባለውን በመጥላት ሌሎችን ይጋብዛል፡፡ ሌሎችንም ወንድም እንደሆነ ሊሰብክ ይሞክራል፡፡ ይህ ጥላቻን ያዘለው ስብከት ከትልቋ ኢትዮጵያ እስከ ታች ተራ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ በቅርቡ በቴዲ አፍሮ ምክነያት የበደሌን ቢራ ላለመጠጣት የተደረገው አድማ አንዱ ሕዝቡ እንዴትና በምን አይነት አመለካከቶች እንደሚመራ በሌላውም ላይ ያለው ጥላቻ ምን ያህል እንደሆነ ያመላከተ ነበር፡፡  ይህን ለሚያሕል አደማ ደግሞ ያደረሰው በሌሎች ከፍተኛ አደናቆትን ያተረፈው የቴዲ አፍሮ  ጥቁር ሰው የሚለው ዘፈኑ እንደነበር ግልፅ ነው፡፡ የቴዲው ጥቁር ሰው ሚንሊክ ግን ለአፍሪካ ሳይቀር ኩራት እንጂ የሚያሳፍር አልነበረም፡፡ በጥላቻ የተመረዘው የእኛው ኦሮምኛ ተናጋሪ ግን ያንን የጥቁር ሕዝብ ሁሉ ክብር የሆነውን ታሪክ ለመስማት አለመፈለግ ብቻም ሳይሆን ያንን ታሪክ የሚያነሱትን በሚያገኘው አጋጣሚ ሊበቀል እንዳለው አየን፡፡ አሁን ያለው እንዲህ የተመረዘው የኦሮምኛ ተናጋሪ ትውልድ ግን ስለሚንሊክም ሆነ በዘመኑ ስለነበሩ ክስተቶች በውል የሚያውቀው ነገር የለም መርዛማና የራሳቸውን ልዩ ፍላጎት በሕዝቡ ሊያሳኩ የሚያሴሩትን ስብከት ተቀበለ እንጂ፡፡
በቅርቡ የሀረካ ሙራ ሐርማ ሙራ መታሰቢያ በሚል አንድ ሐውልት ተመርቋል፡፡ እኔ እውነትም ይህ ክስተት በየትኛውም ስህተት ቢሆን ተከስቶ ከነበረ መታሰቢያ መቆሙ ክፋት አለው ብዬ አላምንም፡፡ ሆኖም ክስተቱ ተፈጠረ ከተባለ ከስንት ዘመን በኋላ ዛሬ ሀውልት ለማቆም የታሰበበት አላማ ያንን ክስተት ለማስታወስ የተደረገ ሳይሆን ይልቁንም ጥላቻን ለማጠናከር እንዲህ ያደረገሕ ሕዝብ ነበር ለማለት የቆመ ሀውልት ሆኖ ነው የተሰማኝ፡፡ አሁን አሁን እንደውም ያ አሳቃዊ ክስትት ሆን ተብሎ የተፈጠረ ታሪክ ነውም ብዬ እየተጠራጠርኩ ነው ከሌሎች ጋር ጥላቻ እንዲፈጠር የሚደረገው ሴራ ብዙ ነውና፡፡  ይህ ሀውልት በተመረቀበት በዚህ ሰሞን የሩዋንዳውም እልቂት ሃያኛ ዓመት የሚታሰበበት ነበር፡፡ ሲታሰብ ግን ልዩ መልዕክት የነበረው የተፈጠረውን ክስተት የሚያስረሳ ሰላምንና የአገር ብልጽግናን በዚያች አገር የማምጣት ራዕን ነው፡፡ ሐውልት እነኳን ለእነዚያ ዜጎች መታሰቢያ ማቆም ቢያስፈልግ ዳግም እንደዚያ ያለ አረመኔነት በዚያች አገር እንዳይከሰት ለትውልድ ማስተማሪያነት እንጂ ቂም በቀለኝነትን ለማቆየት አይሆንም፡፡ የኦሮምያው የሀርካ ሙራ ሐርማ ሙራ ሐውልት ግን ግልጽ መልዕክቱ ሌሎችን በመጥላት የተመረዘውን ብዙ የኦሮምኛ ሕዝብ የበለጠ ጥላቻ እንዲያድርበት ሌሎችም ሌሎችን በመጥላት ተሳትፎ እንዲያደርጉ የታለመ ነው ብዬ አመንኩ፡፡
ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ የወደፊት ብሩሕ ራዕይ ደስተኛ አይደለም፡፡ እነዚህ የሕዝቡ አካላት የኢትዮጵያን ውድቀት እጅግ የሚመኙ ናቸው፡፡ ሌላ ቀርቶ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ወይም እነሱ በጣም ከሚጠሉት አማራ ወይም ትግሬ ከሚባለው ሕዝብ ጋር የተያያዘ የራሳቸው ነገር እንኳን እርም ነው፡፡ የአባይ ወንዝን እንደምሳሌ ላንሳው፡፡ የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ ብዙ ይነሳል፡፡ መነሻው ደግሞ ጎጃም የጮቄ ተራራ ነው፡፡ ሆኖም አባይን በውል የምታውቁት ካላችሁ አባይን አባይ ያደረገው የጮቄ ተራራ ወይም ከጣና የቀዘፈው ውሀ ሳይሆን ከኦሮምያ የሚነሱ ታላላቅ ወንዞች ናቸው፡፡ በተለይም ደዴሳና ዳቡስ፡፡ ይሄንን ለማስተዋል አሁን ግድብ እየተሰራበት ያለውን ቦታ የሚፈሰውን ውሃና ወደጎጃም ስትሻገሩ የምታዩትን ውሃ አስተውሉ፡፡ ግብጾቹም ይሁኑ ሌሎች እንቅልፍ የሚነሳቸው ጎጃም ያያችሁት አባይ አይደለም ደቡስና ዴዴሳ የደለቡት አባይ እንጂ፡፡ የአባይ ሥም ሲነሳ ግን ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ጥሩ ስሜት የለውም፡፡ ግድቡን ጨምሮ ሌሎች ለኢትዮጵያ ብልጽግናም ትልቅ ድርሻ ያላቸው ልማቶችም እንዲሁ በብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ በመልክም አይታዩም፡፡ ግን ለምን? የሚንሊክን ታሪክና ዘመን እንዲህ በጥላቻ የሚያስመለክትስ በእውን የተጨበጠ ይቅር የማያሰኝ ስህተት አለ? ካለስ ይህ ትውልድ እነዴትና በምን ምክነያት እነዚያ ስህተቶች እንደተከሰቱ ምን ያህል ተረድቶ ነው እንዲህ በጥላቻ የተመረዘው?! ነው ወይስ አሁንም እያየን እንዳለንው የኢትዮጵያ ነገር ስለማያደስተው ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተቆራኘውን የአገሪቱን መስራች ሚንሊክን በስሜት ብቻ መጥላት ይሆን?
ኦሮምያ ውስጥ ባለፉት ሃያ ምናምን አመት ከተከሰተው ግፍ በላይ በቀደሙ የታሪክ ጊዜያት ለመከሰቱ ጥያቄ እያጫረብኝ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ጥያቄዎች አሉ! ኦሮምያ የሚባለውም ክልል ይሁን ኦሮምኛ ተናጋሪ የተባለው ሕዝብ ግልጽ በሚታይ ሁኔታ እየተቀደመ እንደሆነ ይረዳ፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ይህ ልዩነት ጎልቶ ሲታይ ይህችን መልዕክቴን ያነበቡ ያስታውሱ ይሆናል፡፡  ግን ለምን???!!
የታላቋ ቀን ልጅ ሚያዝያ 1 2006 ዓ.ም.

ሰበር ዜና፡- ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ተሾሙ

ሪፖርተር  ጋዜጣ

ወ/ሮ አስቴር ማሞ
ወ/ሮ አስቴር ማሞ
በቅርብ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በተመረጡት አቶ ሙክታር ከድር ምትክ፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ተሾሙ፡፡
ማክሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. በፓርላማ ሹመቱ የፀደቀላቸው ወ/ሮ አስቴር በተጨማሪ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት በፓርላማው ሹመታቸው የፀደቀው ወ/ሮ አስቴር የመጀመርያዋ ከፍተኛ ተሿሚ ናቸው፡፡
‹‹ሴት ተሿሚ ለዚህ ከፍተኛ ሹመት በማቅረቤ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል፤›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው አባላት ስሜታቸውን ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አስቴር ሹመታቸው ከፀደቀ በኋላ ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡
በተለያዩ ከፍተኛ የፓርቲና የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ የቆዩት ወ/ሮ አስቴር፣ በፓርላማው የመንግሥት ተጠሪ የነበሩ ሲሆን እስከ ሹመታቸው ድረስ በምክትል ፕሬዝዳነት ማዕረግ የ ኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አማካሪ ነበሩ፡፡