Sunday, April 14, 2013

ዘር ማጥራትን ያህል ወንጀል ፈጽሞ ይቅርታ መጠየቅ ፌዝ ካልሆነ ድራማ ነው!

ግርማ ሞገስ (girma.moges@yahoo.com)
ቅዳሜ ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት (Saturday, April 14, 2013)

Amhara Ethnic group members Ethiopiaበፌዴራል ስም የተሸፈኑ ህውሃት/ኢህአዴጎች እና በአቶ መለስ ራዕይ የተጠመቁ የክልል ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ የዘር ማጥራት (Ethnic Cleansing) ወንጀል ስለመፈጸማቸው መዘገብ ከጀመረ ውሎ አድሯል። ይኽ ዜና በኢትዮጵያ ወዳጆች ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ዜጎች ዘንድ ስጋት ፈጥሯል። ኢትዮጵያ እንድትበተን የሚፈልጉ ግን አፍና እጃቸውን አስተባብረው ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከመንገዳቸው ላይ ተወግዳ ህልማቸው ወደሆኑት የቃል-ኪዳን አገሮቻቸው (Promised-land) ለመድረስ የጀመሩትን ጉዞ ፍጥነት እና ግልጽነት ሳያመቻቸው ዝቅ ሲያመቻቸው ደግሞ ከፍ ያደርጋሉ እንጂ አያቆሙም። የህውሃት ሕገ መንግስት (አንቀጽ 39) ግፉ በርቱ ይላል። ስለዚህ የቤንሻንጉል ጉምዝ አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ናስር ቀደም ብሎ በቪኦኤ አማርኛ ፕሮግራም ሲጠየቅ አፉን ሞልቶ ሞቅ ባለ ስሜት አማርኛ ተናጋሪውን ያፈናቀልነው መሬቱን ለልማት ስለፈለግነው ነው እንዳላለ ሁሉ ድንገት ተነስቶ ሰሞኑን ይቅርታ መጠየቁ ማጭበርበሪያ ድራማ እንጂ ሃቅ አይደለም። ይኽ ይቅርታ ከራዕይ እና ከፖሊሲ ለውጥ የመነጨ ሳይሆን የተለመደው የህውሃት ማዘናጊያ እና አቅጣጫ ማስቀሪያ ፕሮፖጋንዳ ነው። ለአንድ ደቂቃ እንኳን መዘናጋት የለብንም። ላብራራ።
በውጭ እና በአገር ቤት ያለው ኢትዮጵያዊ በአንድነት የዲፕሎማሲ ትግሉን ሙቀት ከፍ በማድረጉ ህውሃት ትኩሳቱ ሲፈጀው በተለየም የለጋሽ አገሮች የገንዘብ እርዳታ ሊቋረጥበት እንደሚችል ወለል ብሎ ሲታየው ስለተደናገጠ ቀውስ ለመቆጣጠር የተፈጸመ ትዕይንት ነው ይቅርታው። አለም አቀፍ የዘር ማጥራት ወንጀል እንዲፈጽም ያግባቡት ጌቶቹ ህውሃቶች እራሳቸውን ነፃ ለማውጣት አቶ አህመድ ናስር አደባባይ ወጥቶ ወንጀሉን ወደ ራሱ እና ወደ ወረዳ ሹሞቹ እንዲያስተላልፍ፣ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ የተፈናቀሉት ወደ ቀድሞ ስፍራቸው ይመለሱ ብሎ እንዲናገር አዘዙት። በጌቶቹ የታዘዘውን አቶ አህመድ ናስር ፈጸመ። በቅድሚያ እንደታዘዘው የፌዴራል ባለስጣኖች ከወንጀል ነፃ ለማድረግ ሞከረ። በሁለተኛ ደረጃ እራሱን እና ከወረዳ በላይ ያሉ የክልል ሹሞቹን ለማትረፍ ሞከረ። በቃ ይኼው ነው። ለህውሃት ጠቃሚ ከሆነ ድራማ ያለፈ ምንም ፋይዳ ያለው ነገር አተደረገም። ወንጀል ለተፈጸመበት ህዝብ ካሳ አልተከፈለም። ስህተት ተፈጽሟል ቢባልም የደረሰውን ኪሳራ ተፈናቃዩ ህዝብ እንዲወርስ ነው የተደረገው። ኢትዮጵያ ደሃ አገር በመሆኗ ወደቀድሞ ቦታችሁ ተመለሱ የተባሉት አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከመፈናቀላቸው በፊት የነበሩዋቸውን የቤት እንሰሳት እና ሌሎች ቅርሶች ግማሽ ያህሉን እንኳን መልሰው ሳያፈሩ በድህነት እና በበሽታ ይሞታሉ። የቀሩትም ከስጋት ሳይላቀቁ የቀረ ዘመናቸውን ይጨርሳሉ። በተጨማሪ በቤንሻንጉል ጉምዝም ሆነ በሌሎች ክልሎች ዜናው ላስደነገጣቸው ሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዋስትና የሚሰጥ ህግ የፌዴራል መንግስት አላወጀም።
ካለአንዳች ሃፍረት አቶ መለስም ከመሞቱ በፊት አማርኛ ተናጋሪው ከጉራፈርዳ ወደ አገሩ እንዲመለስ የተደረገው አማርኛ ተናጋሪ በመሆኑ ሳይሆን ጫካ እየመነጠረ በማንደዱ ነው ብሏል። አቶ መለስ አማርኛ ተናጋሪው ወደ አገሩ እንዲመለስ ተደረገ ሲል በጭንቅላቱ ውስጥ ጉራፈርዳ ኢትዮጵያ መሆኗ አብቅቷል ማለት ነውን? ደቡብ ህዝቦች ለይስሙላ ካልሆነ በስተቀር የመገንጠል ሂደቱን ፈጽሟል ማለት ነውን? በሌላ ጊዜም በፓርላማ ብቸኛ ተቃዋሚ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ከጅጅጋ፣ ከደቡብ ህዝቦች እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው ህዝብ መፈናቀል ጥያቄን በማርላማ ሲያነሱ አቶ መለስ ተፈናቃዮችን ወንጀለኞች የሚያደርግ እንጂ እራሳቸውን (የፌዴራል ባለስልጣኖች) እና የክልል ባለስልጣኖችን ስተተኞች ወይንም ወንጀለኛ የሚያደርግ መልስ እንዳልሰጠ የቪዲዮ መረጃ ማቅረብ ይቻላል። ያም ሆነ ይህ በደቡብ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አቶ አህመድ ናስር፣ ከፈዴደራል አቶ መለስ ዜናዊ እና ምትኩ አቶ ኃለማሪያም ዘር የማጥራት ወንጀል ፈጽመዋል።
በተጨማሪ የጤና ምኒስትር ሳለ ከእንግሊዘኛ ተናጋሪ ለጋሽ አገሮች ጋር ቅርርብ ስለነበረው አቶ መለስ እንደሞተ አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም ቀደም ሲል አቶ ስዩም መስፍን ሲያደርግ እንደነበረው የኢትዮጵያን ሳይሆን የህውሃትን ጥቅም የሚያስቀድም የውጭ ጉዳይ ምንስትር ሆኖ በኢትዮጵያ ላይ መተከሉን እናውቃለን። ይኽ ግለሰብ ዛሬ ኢትዮጵያን ወክሎ በሚሄድባቸው ለጋሽ አገሮች በደቡብ ኢትዮጵያ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ስለተፈጸመው ዘር የማጥፋት ወንጀል ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ህውሃትን ከወንጀለኛነት ለማትረፍ በኢትዮጵያ የዘር-ማጥፋት ወንጀል አልተፈጸመም ማለት ከጀመረ ውሎ አድሯል።
እነዚህ ስማቸው የተጠቀሱት እና ሌሎች ወንጀለኞች በአለም አቀፍ እና ወደፊት የህዝብ መንግስት ሲመሰረት በአገር ቤት ከሚመሰረትባቸው ክስ በተጨማሪ ለጉብኝትም ሆነ ለስራ ጉዳይ ወደ አሜሪካ የሚያስገባ ቪዛ እንዳያገኙ እና በውጭ ያስቀመጡት ሃብት እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ትግል ከግብ እስኪደርስ ድረስ ተጠናክሮ ሽቅብ እንዲጓዝ መደረግ አለበት። ከመረጃ እጥረት ይልቅ የመረጃ መብዛት ስለሚመረጥ መረጃ የማሰባሰብ ጥረትም እንደዚያው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይኽን ጉዳይ አስመልክቶ በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በአውሮፓ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ቁልፍ ናቸው። የሰላማዊ ሰልፈኛው ቁጥር ከፍ ማለት ደግሞ ተደማጭነትን እና ተጽዕኖን ከፍ ያደርጋል።
በአንድ አገር በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ዘር የማጽዳት ወንጀል (Ethnic Cleansing) መፈጸም ከተጀመረ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪም መጪ እጣ ምን እንደሆነ በየግድግዳው ላይ ተጽፎለታል ማለት ነው። በየግድግዳው ላይ የተጻፈለትን ማንበብ የቻለ ፈጠን ብሎ አካባቢውን መልቀቅ ማሰቡ አይቀርም። ምናልባትም ተወልዶ ያደገበትን ወይንም ለረጅም ጊዜ የኖረበትን የሚወደውን ቀየውን ለቆ ወደ ቀድሞ ዘመዶቹ ትውልድ ስፍራ መሄድን አሊያም ሌሎች እንዳደረጉት ወደ አረብ አገሮች ወይንም ወደ ምዕራቡ ዓለም ለመሰደድ ማውጣት ማውረድ ይጀምራል። የቀረው ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ደግሞ ጊዜው ሲደርስ (ለህውሃት ሁኔታው የተሟላ ሲመስለው ማለት ነው) ቀደም ሲል በሌላ ላይ የተፈጸመው የዘር-ማጥራት ወንጀል ይፈጸምበታል። ያም ሆነ ይኽ በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ የተጀመረው የዘር ማጥራት ወንጀል የዜጎችን ኑሮ ቀጣይነት ያናጋል። ዜጎች እንደቀድሞው ባሉበት አካባቢ ተስፋ አይኖራቸውም። ልማት እና እድገትን ይቆማል። ለምሳሌ በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በጎረቤቱ አማራ ህዝብ መካከል መቃቃር እየፈጠርክ እንዴት አድርገህ ነው በህዝብ ትብብር የአባይን ግድብ በቤንሻንጉል እየገነባሁ ነው የምትለኝ!? ባጭሩ የአቶ መለስ ራዕይ አብሮት እንዲቀበር ካልተደረገ በኢትዮጵያ ሁሉም በያለበት በተራ የዘር-ማጽዳት ወንጀልን እንደጽዋ መጎንጨቱ አይቀሬ

እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው?

ገብረመድህን አርአያ
ፐርዝ፤ አውስትራሊያ

ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በትግል በረሃ በነበርንበት ወቅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት.) በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ላይ ሲከተል የነበረውን አቋሙን
Gebremedhin Araya former TPLF
አቶ ገብረመድህን እርአያ
ተቀብሮ ከነበረበት ጉድጓድ አውጥቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነማን ናቸው የሚለውን ታሪካቸውን እና የተፈጸመውን ጸረ-እምነት ግፍ በአጭሩ ለማሳወቅ ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት. ገና ሲፈጠርና ተ.ሓ.ህ.ት. ተብሎ እንደተመሰረተ ሙልጭ ያለ ጸረ-ዲሞክራሲ ድርጅት ነው። በጸረ-ኢትዮጵያነትና በጸረ- ሕዝብነት የተሰማራ ቅጥረኛ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ በጽሑፍና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናግሬአለሁ። የአሁኑ ጽሑፌ ህ.ወ.ሓ.ት. በሃይማኖት ላይ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲ ገና ከመጀመሪያ ትግሉ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የነበረውን ጸረ- ሃይማኖት ተግባራቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ አውቆታል። እኔ ደግሞ የራሴን ልበል።
በ1969 መጀመሪያ ጀምሮ “ወይን” በሚለው የድርጅቱ ልሳን መጽሔት ላይ በተደጋጋሚ “የክርስትና ሃይማኖትና አማራው” በሚል ርእስ ተጽፎ የሚወጣው ጽሑፍ፣ “የክርስትና ሃይማኖት የአማራው ዋና መሳሪያና የግዛቱን ህልውና ማስጠበቂያ ነው፣ በመሆኑም የትግላችን ጠላት አማራውና መሳሪያው የተዋህዶ ክርስትና ስለሆኑ አብረው እንዲጠፉ ማድረግ አለብን” እያለ ያትት ነበር። ይህንን መጽሔት በሰፊው ለታጋዩና ለአባላቱ በማሰራጨት ሰፊ ቅስቀሳ አካሂዶበታል። በነሐሴ 1969 “ወይን” መጽሔት አማርኛ ቋንቋም አብሮ መጥፋት እንዳለበት ሃተታ ይዞ ወጥቷል።
“ወይን” የምትለውን መጽሔት የሚያዘጋጁት ከፍተኛ የአመራር አባላት በፕሮፓጋንዳ ቢሮ ሆነው ለዚሁ ተግባር የተዘጋጁ ጽሑፎችን በስፋት የሚያሰራጩት፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና መለስ ዜናዊ ነበሩ። እነዚህ ሶስቱ የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር አባላት እብዶችና በጸረ- ሃይማኖት፣ ጸረ-አማራ ባህሪያቸውና አቋማቸው በሰላማዊው ህብረተሰብና ታግዩም ጭምር በግልጽ የሚታወቁ ናቸው።
የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ የሚመራውም በነዚህ ሶስት እብድ አመራሮች ነበር። ከዚህ በመነሳት መስከረም 1970 በጸረ-ሃይማኖት፣ በተለይም በተዋህዶ ኦርቶዶክስ ላይ ቅስቀሳውን በስፋት ለማካሄድ በማሰብ፣ ሕዝብ ያሳምናሉ ተብለው የሚታመንባቸውን ታጋዮች መርጠው እገላ ወረዳ መሬቶ ተብላ በምትጠራ ቁሽት ውስጥ ተሰብስበው ቦታ ተዘጋጅቶ ከላይ በተጠቀሱት ሶስቱ አመራር ሴሚናር ተዘጋጀ። በሴሚናሩ ላይ የሚከተሉት ታጋዮች ተካፍለው ነበር፤
1. መርሳ ረዳ 9. ጉእሽ ጓእዳን
2. ሃለቃ ፀጋይ በርሄ 10. ቢተው በላይ
3. ቴዎድሮስ ሃጎስ 11. ሃድሽ ገዛኸኝ
4. አባይ ወልዱ 12. ሮማን ገ/ሥላሴ
5. ሃዳስ ዓለሙ 13. አፈራ ተክለሃይማኖት
6. ኃ/ሥላሴ ገ/ኪዳን 14. ወልደገብርኤል ሞደርን
7. ሃሪያ ሰባጋድስ 15. አዲስዓለም ባሌማ
8. ቅዱሳን ነጋ
ከላይ የተጠቀሱት ታጋዮች በተካሄደው ሴሚናር በጸረ-ክርስትና እና በጸረ-እስልምና አስተሳሰብ በሶስት ቀን ውስጥ ተጠምቀው ጨረሱ። እንደጨርሱም በሶስት ሪጅን ተመደቡ፤ አመዳደባቸውም፤ ሪጅን 1 መርሳ ረዳ፤ ሪጅን 2 ሃለቃ ጸጋይ በርሄ፤ ሪጅን 3 አዲስዓለም ባሌማ በሃላፊነት እንዲመሩት ተመረጡ። ቀሪዎቹም በእነዚህ የበላይ ተጠሪዎች ስር ተደለደሉ።
ሪጅን 1 ሪጅን 2 ሪጅን 3
መርሳ ረዳ ተጠሪ ጸጋይ በርሄ ተጠሪ አዲስዓለም ባሌማ ተጠሪ
1-ጉእሽ ጓእዳድ 1-ቅዱሳን ነጋ 1-ቴዎድሮስ ሃጎስ
2-አባይ ወልዱ 2-ሃዳስ ዓለሙ 2-ወ/ገብርኤል ሞደርን
3-ኃ/ሥላሴ ገ/ኪዳን 3-ቢተው በላይ 3-አፈራ ተ/ሃይማኖት
4-ሃርያ ሰባገድል 4-ሃድሽ ገዛኸኝ
5-ሮማን ገብረሥላሴ
በዚህ መልክ ተደራጅተው በየሪጅኑ ተሰማሩ። ድጋፍ ሰጪ የሕዝብ ግንኙነት ካድሬዎችም በየድርጅቱ በስፋት ተሰማሩ። እነዚህም በተጠናከረ ሃይል ጸረ-ክርስትና፣ ጸረ-አማራ፣ ጸረ-እስልምና ቅስቀሳቸውን ቀጠሉበት። በተዋህዶ ክርስትና ላይ ሙሉ ሃይላቸውን በመጠቀም በስፋት ጸረ-ክርስትና ቅስቀሳውን በተከታታይ እሁድና ሌሎች በዓላት እንዳይከበሩና የሥራ ቀን መሆናቸውን በማወጅ በህብረተሰቡ ላይ ካባድ ተጽእኖ አሳደሩበት። ቀሳውስትና ዲያቆናት በማንኛውም በዓላት ቤተ ክርስቲያን ከፍተው ሲቀድሱ ቢገኙ ከባድ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠነቀቁ። አልፎ አልፎ ተቃውሞ ይገጥማቸው ስለነበር በበላይ አመራሩ ለእነ ስብሃት ነጋ ምን እናድርግ እያሉ ሪፖርት ያቀርቡ ነበር። ከአመራሩ የተሰጠው ምላሽ፣ ማንም ያንገራገረ ቄስ፣ ባህታዊ፣ ዲያቆን ወይም ሌላ እዛው ባለበት በሕዝቡ ፊት ግደሉት የሚል መመሪያ ተሰጣቸው። በዚህ መሰረት አድዋ አውራጃ እንዳባጻህማ ወረዳ የሚገኘው እንዳሥላሴ ተብሎ የሚታወቀው ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን መሪ አባ ሃይለሥላሴ የሚባሉ ቄስ፣ “ሃይማኖታችንን አታርክሱት፣ የተቀደሰ ሃይማኖት ነው” ብለው ስላሉ በቦታው የነበረ ጸጋይ በርሄ የሚባል ታጋይ በያዘው አጭር ጓንዴ ተኩሶ ጭንቅላታቸው ላይ በመምታት በሕዝብ ፊት ገደላቸው። ቀሪው ምእመናን ተደናግጦና በርግጎ ተበታተነ። ሃለቃ ጸጋይ በርሄ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የነበረውን ንብረትና ሃብት ጠራርጎ ወሰደው። በተመሳሳይ፣ ዛና ወረዳ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን መሪ የነበሩት አባ ቄስ አርአያ ከአንድ የ90 ዓመት አዛውንት ባህታዊ ጋር ሆነው፣ “እባካችሁ ሃይማኖታችንን አታርክሱብን” በማለታቸው ከቢተው በላይ ጋር ተደራቢ ሆኖ የሄድው አርከበ እቁባይ ሁለቱን ንጹሃን ዜጎች በሕዝቡ ፊት ገደላቸው። በስብሃት ነጋ፤ አባይ ፀሃየና መለስ ዜናዊ የሚመራው ጸረ-ክርስትና ሃይማኖት ከላይ የተጠቀሱትን 15 ታጋዮች የተግባሩ ፋጻሚዎች በማድረግ በርካታ ቤተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል። ከአድዋ፣ አክሱምና ተምቤን አውራጃዎች ብዙ ቀሳውስትና ባህታውያን እንዲሁም ዲያቆናት ሌሊትና ቀን እየታፈኑ ተውስደው የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።
የእስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ፤ እስልምና ተከታይ ኢትዮጵያውያን ጸሎት ለመድረግ በሚሰበሰቡበት ጊዜ እየጠበቁ ጸረ-እስልምና ሰበካዎችን ለማራመድ በየመንገዱ ቅዱሱን ነብዩ መሃመድን እና ቅዱስ ቁርአንን ማብጠልጠልና ማራከስ በጀመሩበት ወቅት፤ ከሪጅን 1-3 በሚገኘው የእስልምና ተከታይ ሰፊ ተቃውሞ ገጠማቸው። በተለይ በሪጅን 3 አፋሮች የእስልምና ተከታዮች ስለሆኑ ጸረ-ወያኔ ተቃውሞ በማሰማት ለእምነታችን እንሞታለን፤ እንዋደቃለን በማለት ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ። በሪጅኑ

Meles Zenawi Foundation

by Teklu Abate
Meles Zenawi foundations play a crucial role in advancing social and economic development.The government of Ethiopia organized a congress that founded the Meles Zenawi Foundation (MZF) on the 6th of April 2013 at the AU Hall in Addis Ababa. The foundation is set to establish a library, a research center, a fellowship programme, and a public park, and will also recognize great achievements. Present at the occasion were Meles family; senior government officials; Presidents of the Sudan, Uganda, and Djibouti; former President of Nigeria Olusegun Obasanjo; Commissioner of the African Union (AU) Commission Nkosazana Dlamini-Zuma; and other invited guests.
Foundations play a crucial role in advancing social and economic development, science and technology, equality, democracy, and the rule of law worldwide. Taking this context, it is required to acknowledge and support the MZF, as Ethiopia needs more and more such independent voices as foundations, think tanks, professional associations, and NGOs.
Unfortunately, the MZF seems to lack, from the very outset, such qualities as independence, diversity, innovation, and ambition expected of all foundations. I could argue that the MZF looks a quazi-government ministry that is intended to give to the works of the late PM eternity. I could further conclude that the foundation would not significantly contribute to the betterment of democratic culture and governance, freedom, and the rule of law in Ethiopia. It is rather intended to scale up and sustain the status quo. The following points ground this conclusion.
Aim of the Foundation
The rationale behind the formation of the MZF is to preserve the “legacy” of the late Meles. According to the AU website, “The Meles Zenawi Foundation aims to pursue the developmental democracy and socioeconomic renaissance initiated by the patriotic and pan-Africanist late Leader”. And the Ethiopian Radio and Television Agency has it that “The Meles Zenawi Foundation is dedicated to preserving and advancing the legacy of the Great Leader Meles Zenawi in his lifelong commitment to peace, justice, economic development, good governance, and democracy for the Ethiopian and African peoples”. Similarly, Walta Info wrote “The Foundation would serve as a living center of ideas and programs to further advance the works and legacy of the great leader Meles Zenawi”.
All these tell us just one thing: the foundation would not entertain ideas that deviate from the golden standard, Meles’ views and policies. Studies, scholarships, libraries, publications, and recognitions all must clearly reflect and advance the late PM’s convictions. We know that Meles did not care for democratic governance, individual freedom, free and fair election, national assets and cultures such as our flag and our borders, corruption, and generally the rule of law. The foundation is unfortunately poised to repeat the same failures. Nothing new is going to happen- it’s all about old wine in new bottle. This conclusion is consolidated further if one considers the governing bodies of the foundation.

Demonstration in Oslo: Against ethnic cleansing in Ethiopia


Ethnic cleansing of Amharic speaking Ethiopians
Demonstration in Oslo: The recent forceful eviction of members of the Amhara ethnic from Benishangul-Gumuz area was an obvious case of ethnic cleansing which is a serious crime.

The dilemma of adopting ethnic federal system in Africa in light of the perspectives from Ethiopian experience

Semahagn Gashu Abebe
Faculty of Law, University of Goettingen, Germany. E-mail: semahagn@gmail.com
Journal of African Studies and Development
Click here for full Article
This article aims to analyse the major challenges of adopting ethnic federal system in Africa with special focus on the context of Ethiopia’s ethnic federal system. It is argued that though the adoption of ethnic federal system in Ethiopia has created the opportunity for minority groups to exercise their cultural and linguistic rights, the ethnic federal experiment has faced enormous challenges. The challenges include problems of legitimacy, unprecedented emphasis on ethnicity and lack of genuine democratization process. The article argues for concrete measures to be undertaken on political accommodation of various political groupings, realization of genuine democracy and establishing efficient political institutions as well as the need to accommodate minority rights in a manner that fosters social cohesion and national unity in the country.
NTRODUCTION
The post-Second World War international development in human rights has been largely based on the assumption of a nation-state which is understood to refer to the convergence of the territory of a state with a nation, whose members are united by ties of history and culture and commitment to a common future (Ghai and Cottrell, 2008). The principal basis of rights and obligations in a nation-state is citizenship based on equality before the law and enjoying the same rights. The sovereignty of the people is expressed through the state, which provides a common regime of laws, the machinery for justice, democratic rights of franchise and candidacy in elections, and the protection of other rights of individuals (Ghai and Cottrell, 2008). In such systems, a citizen’s linguistic, religious, and cultural affiliations are largely ignored or undermined. In fact, there has been considerable consensus among many Marxist and non-Marxist scholars that ethnicity is reflection of isolation of communities and lack of efficient communications and blame ethno-cultural conflicts on temporary factors that would disappear through time (Karmis and Norman, 2005; Kymilcka and Opalski, 2001). It has been expected that industrialization, urbanization and the spread of modern education would reduce ethnic tendencies in the process. Marxists were also certain that socialism would mean the end of the ethnic tension and consciousness that existed in pre-socialist societies (Spiro, 2007). Assimilation of minorities into a large integrated whole was viewed as the inevitable future (Jalali and Lipset, 1992). Read more…