Thursday, March 7, 2013

ጋምቤላ አሁንም በወያኔ ወራሪ ሠራዊት እየታመሰች መሆኗ ተሰማ

 

በ1996 ዓም ከ400 በላይ አኝዋኮችን በግፍ የጨፈጨፈዉ የወያኔ ወራሪ ሠራዊትና ልዩ ኃይል ከሰሞኑ በብዛት ወደ ጋምቤላ በመዝመት ሠላማዊ ዜጎችን በተለይ የአካባቢዉን አርሶ አደሮች እየያዘ ማሰርና መግደል መጀመሩን ከአካባቢዉን እየሸሹ ጫካ የገቡ ዜጎች ለኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን ስልክ እየደወሉ በሚልኩት ዜና ገለጹ። በተለይ ካለፈዉ አርብ ጀምሮ ፌዴራል ፖሊስ፤ መከላከያ ሠራዊትና የደህንነት ልዩ ሀይሎች ተቀናጅተዉ በጋራ በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ ተቃዋሚዎችን ይረዳሉ ወይም ታጣቂዎችን ሊቀላቀሉ ይችላሉ ብለዉ የጠረጠሯቸዉን ሠላማዊ ዜጎች ማሰራቸዉንና እራሳቸዉን ለማዳን የሞከሩ ሰዎችን ተኩሰዉ መግደላቸዉን ከአካባባዉ የደረሰን ዜና ጨምሮ ያስረዳል። በአሁኑ ወቅት የወያኔ ወራሪ ሠራዊት በብዛት ወደ ጋምቤላና አካባቢዉ እየዘመተ ሲሆን የአካባቢዉ ህዝብም እራሱን ለማዳን ጫካ እየገባ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የወያኔ ወራሪ ሠራዊት ካለፈዉ ዐርብ ጀምሮ በወሰደዉ የማጥቃት አርምጃ ከአስራ ሁለት በላይ ሠላማዊ ዜጎችን የገደለ ሲሆን ከሟቾቹ ዉስጥ አንድ የአካባቢዉ ተወላጅ የሆነ የአሜሪካ ዜጋ ይገኝበታል። የግንቦት ሰባት ድምጽ ዝግጅት ክፍል የወያኔ ጦር በአካባቢዉ ያደረገዉ ጭፍጨፋ እንደተሰማ በክልሉ የሚገኙ አንዳንድ ባለስልጣናትን ሰልክ ደዉሎ ሁኔታዉን ለማጣራት ሞክሮ ነበር ፤ ሆኖም የዝግጅት ክፍላችን ያናገረዉ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣን በአካባቢዉ ምንም አይነት ግጭት የለም በማለት በአለም ዙሪያ የተሰራጨዉን እዉነት ለመካድ ሞክሯል። በሌላ በኩል አዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣኖች የጸጥታ ሀይሎች ጋምቤላ አካባቢ የአማጽያንን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በሚል በወሰዱት እርምጃ አንድ የአሜሪካ ዜግነት ያለዉ ሰዉ መገደሉን ለአሜሪካ ኤምባሲ ተናግረዋል።
የአዲስቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ የሆኑት አቶ አባንግ ሜቶ ከኢሳት ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በጋምቤላና በአካባቢዉ ያለዉን ወታደራዊ ዉጥረት ድርጅታቸዉ በቅርብ እንደሚከታተለዉ ተናግረዉ ከሰሞኑ በወያኔ ወታደሮች ተገደለ ስለተባለዉ የአሜሪካ ዜጋ አስፈለገዉን የክትትል መረጃዎች ለአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መስጠጣቸዉን ተናግዋል። ዜጎችዋ በዉጭ አገር በሚደረጉ ወታደራዊ ግጭቶችና አመጾች ሲገደሉ ወይም ደብዛቸዉ ሲጠፋ ክፍተኛ ክትትል የምታደርገዉ ዩ ኤስ አሜሪካ አሁንም ጋምቤላ ዉስጥ በወያኔ ወታደሮች ተገደለ የተባለዉን ዜጋዋን ጉዳይ መከታተል መጀመሯን ለማወቅ ተችሏል። በቅርቡ የኦባማ አስተዳደር ከአሸባሪዎች ጎን ተሰልፈዉ በሚዋጉ የአሜሪካ ዜጎች ላይ የሚወስደዉን አርምጃ በተመለከት ሾልኮ የወጣዉ መረጃ ኮንግሬሱን ጨምሮ አያሌ አሜሪካኖችን እንዳስቆጣ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህ ከሰሞኑ ጋምቤላ ዉስጥ የተገደለዉ አሜሪካዊ ጉዳይ ይበልጥ በተሰማና በታወቀ ቁጥር ወያኔ ላይ መዘዝ ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ።
 


ጥቃት በየተራ እስከመቼ?

 


ባለፉት 21 የወያኔ የግዛት አመታት አይነቱና መጠኑ ይለያይ እንደሆነ እንጅ ጥቃት፣ ግፍ፣ በደልና እብሪታዊ የመብት ገፈፋ ያልደረሰበት ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ክፍል የለም። ገበሬው፣ የመንግስት ሰራተኛው፣ የፋብሪካ ሰራተኛና በየዘርፉ የእለት ጉርሱን አሳዶ የሚኖረው ሁሉ የወያኔን የሰቆቃ ግፍ በትር በየተራ አይቶታል፣ እያየውም ይገኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት አንጀቱ ለፍቶ ያቋቋማቸው ተቋሞቹ እየፈራረሱ ለወያኔ አገዛዝ እንዲመቹ ሆነው ሲጨፈላለቁም አይተናል።
ወያኔ ይህን ሁሉ ያደረገው “አንዱን በአንዴ” በሚል ስልት ነው። መምህራንን ሲያጠቃ የፋብሪካውን ሰራተኛ ተመልካች ያደርገዋል፤ ገበሬውን ሲያጠቃ ከተሜውን ዝም ይለዋል፤ ከተሜው ላይ ሲዘምት ገበሬው ተመልካች ይሆናል፤ ቤተክርሰቲያን ላይ ሲዘምት ቤተ ሙስሊሙ ይመለከተዋል፤ የቤተ ሙስሊሙ የበደል ተራ ጊዜ ቤተክርስቲያን ተመልካች ትሆናለች። ይህ ወያኔን እስከዛሬ ያደረሰው ስልት ነው።
አራዊታዊው የወያኔ አገዛዝ በተመቸውና ይጠቅመኛል ብሎ በአሰበ ሰአት ሁሉ የውብ ህዝብነት ምልክታችን የሆነውን የባህልና የቋንቋ ስብጥርነታችንን እርስ በርስ ለማናከሻነት ሊጠቀምበትም ሞክሯል፤ በተወሰነ ደረጃ አልሰራላቸውም ማለት ያስቸግራል፡፡
ወያኔዎች ከፋፍሎ መግዛትንና በየተራ ማጥቃትን በኪነ ጥበብ ደረጃ አሳድገነዋል ብለው ያምናሉ። በህዝብ ወገን ያለነውም የዲሞክራሲና የነጻነት ሃይሎች ለዚህ አልተመቸንም ማለት ያስቸግራል፡፡ ይህንን ከፋፍሎ የማጥቃት ግፍ በጋራ ለመመከት ያደረግነው ጥረት ህዝባችን ላይ እየደረሰ ካለው ጥቃት ጋር ቢያንስ የሚመጣጠን አይደለም።
የወያኔ መሪዎች ዛሬ ስልታቸውን በማሻሻል አደገኛ ጭዋታ በቤተ እምነቶቻችን ዙሪያ መጫዎት ጀምረዋል። የቤተክርስቲያን እና የአቢያተ መስጊዶችን አስተዳደር በካድሬዎቻቸው ለመቆጣጠር ከሚያደርጉት ሳይጣናዊ ተግባር በተጨማሪ ህዝቡ ሃይማኖት ለይቶ እንዲባላ ለማድረግ በእጅጉ የሚቀፍ ፕሮፖጋንዳ እያካሄዱ ነው። ፍጹም ምሳሌያዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሲቪል መብት ጥያቄ እንደባዕድ መሳሪያነትና እንደ ሽብርተኝነት ለማሳየት እየሞከረ ይገኛል። በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሙሉ እጁን በማስገባት የተጀመረውን እርቀ ሰላም በማፍረስ የራሱን እንደራሴ ሰይሟል። ይህም አልበቃ ብሎት ለዘመናት በመከባበር የኖረውን ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን እርስ በርስ ለማጋጨት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል።
ዛሬ ከመቸውም በበለጠ ሀገራችን ወደማትወጣው አደጋ እየተገፋች ነው። ይህንን ወያኔ ያዘጋጀልንን የክፍፍልና ግጭት ድግስ ለመመከት ይበልጥ በአንድነት የምንቆምበት እና የምንታገልበት ግዜ ዛሬ ነው፡፡
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለወያኔ የ”ከፋፍለህ በየተራ ቀጥቀጥ” ፖሊሲ መድሃኒቱ አንድ ሆኖ በአንድነት አሻፈረኝ ብሎ መነሳት መሆኑን ያምናል፡፡ ወያኔ ጉልበቱ የኛ መከፋፈልና ለክፍፍሉ መመቸት መሆኑን ያምናል፡፡ እኛ ስንተባበርና ልዩነታችንን ለመጠቀም የሚያደረገውን ሙከራ ስናከሽፍና አንዱ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የሁላችንም ነው ብለን የተነሳን እለት ወያኔ የለም።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ወያኔ በፈቃዱ የማይታረም ፋሺስታዊ አምባገነን መሆኑን ከተረዳ ሰንብቷል። በመሆኑም ወያኔን በማስገደድ ወይም በማስወገድ ነጻነታችንን መቀዳጀትና ነጻ ሀገር እንዲኖረን ማድረግ አለብን ብለን እናምናለን። ለዚህ ትግልም ማንኛውንም መሰዋእትነት ለመክፈል ተነስተናል። ነጻነትና ኮርተህ በነጻነት የምትኖርባት ሀገር እንድትኖርህ የምትወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተቀላቀለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ESAT Daily News Amsterdam 07 March 2013 Ethiopia

The Paradox We Need to Deal with Seriously and Honestly

                         March 07, 2013
                                                by T.Goshu
1) As an introduction
U.S. Ally Ethiopia is One of the Worst Human Rights AbusersLet me start by saying that as numerous researches conducted by many psychologists, sociologists, and other social scientist have shown , there is no any human or social interaction that is absolutely free from paradoxical attitudes and behaviors . Hearing and watching people making contradiction between what they say and what they actually do is not uncommon. And I do not have any illusion to make the case of the people of Ethiopia an exception to this very general fact of human attitude and behavior.
There is no doubt that with all unfortunately ugly sides of history, the people of Ethiopia have a very great place in the history of mankind. The kings/emperors, empresses, princes, great patriotic forefathers and mothers again with all challenges they had and mistakes they made, they had made a great history in the passing over of the country as we know it from generation to generation. They had to pay ultimate sacrifices which emanated from a deeply powerful conviction of selflessness. They had paid priceless sacrifices because they truly believed that preserving a homeland that is independent and sovereign could be unthinkable let alone possible without making aspirations and actions the two inseparable and indispensable factors of living with freedom and dignity as well as being the beneficiaries of all natural resources. Needless to say that our forefathers and mothers had selflessly paid huge sacrifices with a great belief that preserving the homeland was their glorious mission not only for few generations but for all generations to come.
When it comes to the role of religious institutions and their leaders, with all the problems they had, they not only preached/and taught about the values of national pride and human dignity but they also had paid their sacred and ultimate sacrifices. Although the Ethiopian Orthodox Christian Church by virtue of being the exercised earlier and being favored by most of the rulers, Muslim Ethiopians and all Ethiopians who belong to other domains of Christianity had a great role as far as preserving our homeland we call it Ethiopia is concerned. I am not here disregarding some terrible events that took place in the course of our political history. One way or another or gravely serious or less serious, it has to be admitted that mistakes had been made and those mistakes have to be put in the right perspective of history and taken as teachable lessons.
Let me add one more perspective of our recent political discourse. Yes, with all the ugly faces of our engagement in the struggle for better political life and socio-economic justice, hundreds of thousands of Ethiopians particularly the youth have paid another ultimate sacrifice. This part of our political chapter is characterized by the coming into being of opposition political parties in a real sense of modern politics. I am talking specifically about political activities since the 1960s.
2) Some encouraging moves despite being in the midst of a serious paradox
  • Before I proceed to the next and main points of view of mine, I want to say that there is a need to recognize and encourage those genuinely citizens or Ethiopian –origin who are trying the best they can for the struggle to succeed.
  • Moreover, the very movements by our Muslim compatriots, opposition political parties such as the walking of Medrek to move a step forward (front) and efforts of coming and acting together by the 33 opposition groups are remarkably encouraging.

ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አንድ ሆኖ መውጣት ተስኖታል ተባለ

                                                                              የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የውስጥ ሽኩቻ መበራከት የተነሳ ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አንድ ሆኖ መውጣት እንደተሳነው የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው።
በህወሀት ውስጥ ሁለት ቡድኖች ድርጅቱን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ መጀመራቸው ከተዘገባ ከወራት በሁዋላ ችግሩ ከመቃለል ይልቅ እየጨመረ መምጣቱን አንድ የቀድሞ የህወሀት ነባር ታጋይ ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸዋል።
ነባር ታጋዩ፤ በአቶ ስብሀት ነጋ በኩል ባሉ ሰዎች ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቦላቸው እንደነበር ጠቅሰው፤ እርሳቸው ግን አሻፈረኝ ማለታቸውን ገልጸዋል።
በድርጅቱ ውስጥ የሚታየው ክፍተት ለአደባባይ ባይበቃም፣ ህዝቡ የሚያየውና እየተነጋገረበት ያለ ጉዳይ መሆኑን ነባር ታጋዩ ገልጸዋል።
በኦህዴድ በኩል ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ የታየው ክፍተትም እየሰፋ እንጅ እየጠበበ ሲሄድ አለመታየቱ ነው የተገለጸው።
ከአንድ ወር በፊት የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት በድርጅቱ ውስጥ የሚታየው ሙስና እና ጎሳዊነት እንደጨመረና ድርጅቱንም አደጋ ላይ እንደጣለ አንዳንድ የምክር ቤቱ ተወካዮች ቢናገሩም፣ ምክር ቤቱ በስፋት እንዳይወያይበት መደረጉን በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል።
በተለይም በከፍተኛ ህመም የሚሰቃዩትን ፕሬዚዳንቱን አቶ አለማየሁ አቶምሳን ለመተካት ቢፈለግም፣ በእርሳቸውና በአፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሌላ ፕሬዚዳንት ለመሾም ሳይቻል በመቅረቱ አቶ አለማየሁ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ተደርጓል።
በኦህአዴድ ስራ አስፈጻሚዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተባብሶ በዞን ደረጃ ያሉ ስራ አስፈጻሚዎች ሳይቀሩ እንደተከፋፈሉና አጠቃላይ ድርጅቱ ወደ ሞት እያመራ እንደሆነ መዘገባችን አይዘነጋም።
ሪፖርተር ዛሬ ባወጣው ዘገባ ደግሞ ኦህዴድ የካቲት 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔውን ለማድረግ የተሰበሰበ ቢሆንም ፤ያልተጠበቁ አጀንዳዎች በመቅረባቸው ፤ ለኢሕአዴግ በሚቀርበው የሁለት ዓመታት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ብቻ በመወያየት ጉባዔውን ለሚቀጥለው ሳምንት አስተላልፎአል።
የ ኦህዴድ አባላት፤ ድርጅታቸው የተለያዩ ችግሮች ስላሉበት ጉዳዩ በአጀንዳ ተይዞ ውይይት እንዲደረግበት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፣ የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በድጋሚ ሌላ ስብሰባ እንደሚደረግና በዚያ ስብሰባ ላይ <<አሉ>> የተባሉ ችግሮችን በማንሳት መወያየትና መፍታት እንደሚቻል ቢናገሩም፣ ስምምነት ላይ አልተደረሰም ብሎአል- ጋዜጣው።
አባለቱ፤ ችግሩ የሕልውና ጉዳይ መሆኑን ደጋግመው በመግለጽ ራሱን የቻለ አጀንዳ ተይዞለት ውይይት እንዲደረግበት ቢጠይቁም፣ እንዲሁም የተወሰኑ አባላት ድርጅቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ ባከናወናቸው ሪፖርት ውስጥ የተነሳው ጥያቄ ተካቶ አንድ ላይ እንዲታይ ሐሳብ ቢያቀርቡም ፤ስምምነት ላይ ስላልተደረሰ ነው ጉባዔው እንዲተላለፍ የተደረገው።
ሥራ አስፈጻሚው፤ ለኢሕአዴግ በሚያቀርበው የሁለት ዓመታት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ሲወያይ በዋናነት ያነሳቸው ችግሮች፣ በድርጅቱ ውስጥ የአመራር ችግር መኖሩን፣ እንደ ድርጅቱ ሳይሆን በግል የመጠቃቀም ሁኔታ መባባሱን፣ ለሥልጣን መሯሯጥ መስተዋሉን፣ ድርጅት ሳይመክርበት የፍርድ ቤት ሹማምንት ከኃላፊነት እንደሚነሱ መደረጋቸውን እና የግለሰቦች አምባገነንነት መንገሱን የሚመለከቱ ናቸው።
አባላቱ በችግሮቹ ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ፣ የተፈፀሙት ድርጊቶች ተገቢ እንዳልሆኑ መተማመናቸውን ጋዜጣው አክሎ ዘግቧል።
ከዚህም ባሻገር የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ከድርጅት ተባረው አገር ጥለው መጥፋታቸው እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት የሚከተለውን ፖሊሲ መቃወም መጀመራቸው በኦህዴድ ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግም ውስጥ ትልቅ ራስ ምታት ፈጥሯል ተብሏል።
ለኢሳት ቅርበት ያላቸው የኢህአዴግ ሰዎች እንደገለጡት፣ በርካታ የኢህአዴግ በተለይም የኦህዴድ አባላት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የጀመሩትን እንቅስቃሴ ከመደገፍ አልፈው በተለያዩ መንገዶች አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።
በኢህአዴግ ውስጥ የሚታየው ልዩነት ያሳሰበው ሪፖርተር ጋዜጣ ዛሬ በርእሰ አንቀጹ ድርጅቱ በመጪው ጉባኤ አንድ ሆኖ በመውጣት ለአገሪቱ የተጠናከረ አመራር እንዲሰጥ ተማጽኗል።
ጋዜጣው ” ሁኔታዎች እየከበዱና እየተካበዱ ናቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃም በአገር ደረጃም የኢኮኖሚው ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ ነው፡፡ ምንም እንኳ አሁንም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ዕድገት ለማስመዝገብ የሚያስችል አመቺ ሁኔታ ቢኖርም፤የውጭ ምንዛሪ እጥረትን፣ ግሽበትንና የኑሮ ውድነት ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም፤ ለተጀመሩና ለታቀዱ ዓበይት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ አግኝቶ መተግበር ትልቅ ፈተና ነው” ብሏል።
የመልካም አስተዳደር መጥፋት፣ የአቤቱታ ብዛትና የሰሚ እጦት እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱንም አልሸሸገም።
ጋዜጣው አያይዞም፦ ” መጪው የኢህአዴግ ጉባኤ ጠንካራ ኢሕአዴግና ጠንካራ መንግሥት ፈጥሮ፤ ጠንካራ መፍትሔ በመስጠት እንደ አንድ ኩሩ ሕዝብ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቀጥል ማድረግ ይጠበቅበታል ፣ህዝብም ጠንካራ ኢሕአዴግ ከጉባዔው እውን እንዲሆን ይጠብቃል” ብሎአል።
በሌላ በኩል ደግሞ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች የኢህአዴግን መዳከም በመጠቀም ወደ አንድነት ጎዳና በማምራት ለለውጥ መስራት እንዳለባቸው ከተለያዩ ወገኖች ጥሪ እየቀረበ ነው።
በቅርቡ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች በተካሄደ የኢሳት ገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ኢሳት ሁሉንም ተቃዋሚዎች በአንድ ጉባኤ በመጥራት አብረው እንዲሰሩ ግፊት እንዲያደርግ ተማጽነዋል።