Monday, September 29, 2014

Ethiopian-American Council Endorses Congressman Mike Honda for Reelection


Ethiopian American Council (EAC)San Jose, California, September 29 – Citing his past service and his concern for the rights and general welfare of all Americans – with a keen eye on immigrant and ethnic communities – the Ethiopian-American Council of North America (EAC) has decided to endorse the reelection of Michael M. Honda as Representative of the 17th Congressional District in the State of California.
Congressman Mike Honda
Congressman Mike Honda
The EAC is a grassroots policy advocacy organization, based in San Jose, California, that operates on the behalf of Ethiopian ethnic and immigrant communities across North America.
In a letter of endorsement to Mr. Honda, EAC cited the time in his youth that he had spent in an internment camp during World War II. EAC expressed hope that with people such as himself in office – those who have experienced prejudice and a consequent loss of rights – that something as egregiously wrong as the Japanese internment will never again happen to any immigrant or ethnic community in the United States of America.
The Ethiopian diaspora and the resultant ethnic and immigrant Ethiopian communities in North America are a result of actions similar to the Japanese internment, and others far more heinous – including the jailing and murder of free-press journalists and political activists – promulgated by the corrupt regime presently ruling Ethiopia.
The EAC partially based their endorsement of Mr. Honda’s reelection on answers to a questionnaire we had sent to his office. After considering his answers, and after some discussion, the EAC decided to lend as much financial and social support as they deem appropriate to ensure that Ethiopian-American voters, and any other citizens they are able to encourage, will go to the polls for Mr. Honda.
Many issues were raised in the questionnaire and Mr. Honda’s answers regarding those issues convinced EAC to endorse him as the one who will most likely help strengthen the Ethiopian community, and the 17th Congressional District in California at large, politically, socially, and economically. The points raised generally include:
• His advocacy for social justice and giving a voice to those who do not have one.
• His being a founder of the Congressional Ethiopia and Ethiopian-American Caucus while
continuing to fight for human rights everywhere.
• His support of H.R.2003 – Ethiopia Democracy and Accountability Act of 2007, a bill that
would have directed the President to provide support for human rights in Ethiopia.
• His securing of a legislative provision that promoted freedom of expression – specifically one
that objects to government harassment and restrictions on a free press in Ethiopia.
• His desire to provide a meaningful path to citizenship for law-abiding undocumented
immigrants currently in the United States.
• His awareness that a family-based system of immigration is key to ensuring that admission is
not based solely on education, wealth, or U.S. economic benefit.
• His belief that immigrants have strengthened our nation’s social and economic fabric and that
it is unconstitutional and wrong to create a class of secondary citizens who have no right to
vote and no access to health care.
• His commitment to engaging communities in civic service by providing leadership and
internship opportunities for interested individuals of all ethnicities.
• His recognition of the need for leaders who have experienced and overcome injustice – who
understand what it means to have basic rights infringed upon solely because of status as a
minority.
EAC and other members of the Ethiopian-American community in the 17th Congressional District perceive they have a forward-thinking friend in Mr. Honda. EAC is interested in preserving Ethiopian heritage in America. EAC wants Ethiopian youngsters and other community members to be politically wise and socially responsible as they involve themselves in the processes of the United States. EAC sees the need for an entrepreneurially friendly environment to put the business acumen of many of its community members to the best and fullest use.
EAC has decided to put its trust in Mr. Honda by endorsing and working for his reelection to the House of Representatives in hopes of realizing these and other important community goals.
The Ethiopian Americans Council of North America (EAC) is a grassroots policy advocacy organization serving Ethiopian ethnic and immigrant communities across North America.
The Ethiopian American Council

የታጋይ አንደርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በአውሮፓ ህብረት ምክርቤት ኮሚሽን ውይይት ተደረገበት፤ በአስቸኮይ እንዲፈታም ጠይቀዋል።


የታጋይ አንደርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በአውሮፓ ህብረት ምክርቤት ኮሚሽን ውይይት ተደረገበት፤ በአስቸኮይ እንዲፈታም ጠይቀዋል።

የታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በአውሮፓ ህብረት ምክርቤት ኮሚሽን ውይይት ተደረገበት፤ በአስቸኮይ እንዲፈታም ጠይቀዋል።

Sept 28, 2014
ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በአምባገነኑ ወያኔ እጅ ወድቆ መሰቃየት ከጀመረ 3 ወራት አልፈዋል። ባለፉት ቀናት የአውሮፓ ህብረት የሰበአዊ መብት ም/ቤት በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ውይይት አደርገዋል ። አንዳርጋቸው የፖለቲካ እስረኛ እና ለዲሞክራሲ፣ ለነጻነት፣ ለመልካም አስተዳደር እና ሰበአዊ መብት መከበር የሚታገል የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ሲሆን ባስቸኮይ ተለቆ ወደ እንግሊዝ እንዲመለስ ኮሚሸነር ተናግረዋል፡፡

የተከበሩ አና ጎሜዝ አንዳርጋቸው ብቻ አይደለም በርካታ ኢትዮጵያኖች ታስረዋል ብሎግ ዘጠኝ፣ ጋዜጠኞች፤ ፖለቲከኞች ሁሉም ካለ ምንም ምክንያት መፈታት አለባቸው። የኢትዮጵያን ፓርላማ ባለፈው ሂጄ አይቸዋለሁ በጣም የሚገርም ነው የፖለቲካ እስረኛ ሳይሆን ሽብርተኞች ናቸው ያሉን ሲሉ ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ ነው። እስክንድር ነጋ ሽብርተኛ ሳይሆን አለም አቀፍ የብእር ተሸላሚ ነው። ብሎግ 9 ጸሃፊያን፣ ጦማሪያን ናቸው። አንዳርጋቸው ጽጌ የፍትህ ታጋይ ነው። ታዲያ እንዴት ነው የኢትዮጵያ መንግስት ህግን የሚተረጉመው ሲሉ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በሁለት ወር ውስጥ ይህን ጉዳይና የኢትዮጵያን ሰበአዊ መብት በተመለከተ እና የአንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ የሚመለከት ኮሚቴ እንዲሰየም እና እንደገና እንደሚወያዩበት የወሰኑ ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸውን በተመለከተ አሳሳቢ በመሆኑ ከእንግሊዝ መንግስት ጋር በመሆኑ ለብቻ በሚቀጥሉት እናየዋለን ሲሉ ዘግተዋል።
በዚሁ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ቀርበው አሁንም የተለመደ ማስተባበያ ሰጥተዋል። እኛ ምንም አይነት ህግ አልጣስንም ብለዋል።

የታጋዮች ስቃይና የመስዋእትነት ፍሬ

                          
አዘጋጅ ናትናኤል አባተ
By Nathnael Abate (Norway)
            በሰዉ ልጅ ታርክ ዉስጥ ነጻነት ከመንግስታት ወይንም  ከገዥዎች ለተገዥዎ ች የሚቸር ስጦታ ሳይሆን ተጨቋኝ ተገዥዎች በደም ጠብታቸዉና ጩሄታቸዉ ከብዙ ትግል በሁዋላ  የሚቀዳጁት የመስዋእትነት ፍሬ ነዉ፣፣ ስለዝህ የነጻነት ታርክ ህዝባዊ እምቢተኝነትና  የመስዋእትነት ታርክ ነዉ፣፣የነጻነት ትግል በሚደረግበት ወቅት አንዳንድ ትግሉን የሚመሩና ለነጻነት የሚታገሉ የነጻነት ጀግናዎች ይሞታሉ፣ ይታሰራሉ፣ይሰቃያሉ፣፣ ከእነዝህ የነጻነት አርበኞች የሚፈሰዉ የደም  ጠብታዎ ች ትልቁ የነጻነት ዛፍ ሆኖ  ያድጋል፣፣ ለነጻነት ብለዉ በአምባገነኖች እጅ ስሰቃዩ  የነበሩ የሞት ጥላ ሸለቆ  አልፎ በመጨረሻ  አምባገነኖችን አሸንፈዉ የነጻነት ተራራ አናት ይደርሳሉ፣፣ ይህ ሁሉ መስዋእትነት የተከፈለበት ነጻነት፣ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ በደም የማይተላለፍ በመሆኑ ፣ካልተንከባከቡትና የነጻነትን ባህል ካልተከሉ፣ አንድ ትዉልድ ሲያልፍ ወይንም ያንድ ገዥ ዘመን ሲያልቅ ሊከስም  ይችላል፣፣ ስለዝህም አንድነትና ነጻነትን በህይወት እንድቀጥል  ለነጻነት የተጋደለዉ ትዉልድ ለተተኪዉ ትዉልድ ስለነጻነት ማስተማር እንድሁም የነጻነት ባህልን ማስረከብ አለበት፣፣ ባሃገራችን ለነጻነትና ፍትህ በተለያዪ ዘመናት የተለያዪ አይነት ትግሎ ች ተደርጉዋሉ፣፣ በንጉሱ ዘመን  የጎጃም፣የባለ፣የወሎ፣የተማሪዎ ች መሬት ላራሹ ጥያቄ ትግሎችና ሌሎች ዘዉዳዊ አገዛዝን ለመገርሰስ የተደረጉ ትግሎች ይጠቀሳሉ፣፣ ንጉሳዊዉ ስርአት ተገርስሶ  ወታደራዊዉ ስርአት በተተካ ጊዜም ቢሆ ን የተለያዩ ግለሰቦች ድርድችና ቡድኖ ች ለነጻነት ታግሉዋሉ፣ ተጋድለዋሉ ታስረዋሉ፣የተለያዩ  አይነት ስቃዮች ደርሶባቸዋል፣፣ ከላይ ያስቀመጥኳቸዉ ሁለቱም   ትግሎ ች ባሃገራዊ ማንነትና ብሄራዊ አንድነት ላይ ተመርኩዘው የሚደረጉ ስለሆኑ ወጠታቸዉ አመርቂ ነበር፣፣ወታደራዊዉ አገዛዝ ብሄራዊ አንድነትን የስርአቱ መሰረት ቢያደርም በህዝቦች ላይ የሚያደርሰዉ ግፍና ጭቆና በስልጣን  እንዳይቆይ እንዳደረገዉ የአደባባይ ምስጥር ነዉ፣፣ ወታደራዊዉን ስርአት የተካዉና አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ ከጫካ የመጣ የትግራይ ነጻ አዉጨ ቡድን ሲሆ ን ይህ የወበዴዎች ቡድን ሃገርቱን ለመዝረፍ በአክስዮን የተደራጀ እንድሁም ሃገር ለማፍረስና ህዝብ ለማጥፋት የታጠቀ  ነዉ፣፣ይህ የወንጀለኞች ቡድን በአስተዳደራዊ መዋቅሩ፣በሃገሪቱ ማህበራዊ ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ጉዳዮችም ከዘዉዳዊዉ አገዛዝና ወታደራዊዉ ስርአት ይልቅ እጅግ የከፋ ነዉ፣፣ ባለፉት በሁለቱም ስርዓቶች የነጻነት ጉድለት ብኖርም የብሄራዊ ማንነት ዉድቀትና የሃገር ሃብት ዝርፍያ አልተፈጸመብንም፣፣  ህወሃት መራሹ መንግስት ህዝብን ከመጨቆን፣ ከማዋረድ፣ከማሰር ፣ሃብት ንብረታቸዉን ቀን በጠራራ ጸሃይ  ከመዝረፍ አልፎ ይህንን እኩይ ተግባራቸዉን  የሚቃወምና የሚያጋልጥ ሰዉ እያሳደዱ መግደል ማሰርና ማፈን  ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፣፣  በወያኔ መንግስት እጅ የታሰሩ ፣የታፈኑና  ሽብርተኛ የተባሉ ሁሉ  የስርዓቱን እኩይ ተግባር ያወገዙ፣ ሃገር ለምን ታፈርሳላችሁ ያሉዋቸዉ፣ያገር ሃብት መዘረፍን የተቃወሙ፣ፍትህ ነጻነት፣እኩልነት ስጐድል አይቶ ዝም ያላሉና ለሆ ዳቸዉ አናድርም ብለዉ ለእዉነት የቆሙ ናቸዉ ፣፣ የወያነ  መንግስት የሃገርቱን፣ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት፣የደህንነት ሃይሎችን ለራሳቸዉ በሚያመች መልኩ የቀረጹዋቸዉ በመሆኑ የነጻነትን የሚጠይቁንና እነሱን  የሚቃወሙትን  ለማፈንና ለአሳድዶ ለመያዝ ሁነታዎችን ቀላል አድርጎላቸዋል ፣፣ ሆኖም የወያነ የነጻነት አፈና ሃይሎች ቁጭትና ቢሶት የወለደዉን ህዝባዊ ትግል ለማምከን አንዳችም አቅም የላቸዉም፣፣ ጭቆናና ግፍ የፈጠረዉ  ህዝባዊ ብሶት ባሃገራችን ዉስጥ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ባሁኑ ወቅት እጅግ የጎላ በመሆኑ ከላይ የቆመ የሚመስል ግን ከስሩ የበሰበሰ አራዊታዊን ስርአት ባስቸኳይ ለመጣል ትልቅ አጋጣሚ ይሆናል፣፣ በርግጥ እንድህ ሲባል የትግል ጉዞዉ ቀላል ነው ማለት አይደለም፣፣ምክንያቱም ወያነ ስርአት ለስልጣኑ ያሰጋኛል ብሎ ያሰበዉን ሁሉ እንደተራበ ጅብ ከመብላት፣ የፈራቸዉን ደሞ እንዳበደ ዉሻ ከመናከስና ከማጥፋት ወደኋላ የማይሉ በመሆናቸዉ እያንዳንዱ ትግላችን  በጥንቃቀ የተሞላና ዉጤት ተኮር መሆን አለበት፣፣ ዛሬ  እዝህ የተሰበሰብን  የነጻነት ሰባኪያኒና  የአንድነት ሃዋሪያት የሃገራችን ጉዳይ ስለሚያሳስበንና ለዉጥ ስለምንፈልግ ነዉ፣፣ ባሃገራችን  የፍትህ  የነጻነት፣የእኩልነትና አንድነት ክስረት ከደረሰብን ፣ የንጹሃን ደም በየአደባባዩ እንደጎርፍ መፍሰስ ከጀመረ፣ ብሄራዊ ማንነታችን ከተዋረደ  23 አመታት አለፉ፣፣ 24 አመታት፣ ፣ ለዝሁ ክስረታችንና ለወያነ ባርነታችን ትልቁ መንስኤ የአንድነታችን መናጋት መሆኑ ገሃድ ነዉ፣፣ አንድነት ከለለ፣ ሰላም የለም፣፣ ሰላም ከለለ ቤተሰብና ማህበረሰብ አይኖም፣፣ ማህበረሰብ ከለለ ደግሞ  ሃገር አይኖርም ፣፣ ምክያቱም  ቤተሰብ ማህበረሰብን ይገነባል፣ማህበረሰብ ደግሞ  ሃገር ይገነባል፣፣ ሃገር ማለት በአንድ አከባቢ የሚኖር የማህበረሰብ ድምር ነዉ፣፣ ስለዝህ ለሃገራዊ ህሊዉና ብቻ ሳይሆን ለቤተሰባዊ ህልዉናና ደህንነት ሃገራዊ አንድነት መሰረት ነዉ ማለት ነዉ፣፣  ነጻነት፣ እኩልነት፣  ዲሞክራሲ፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግናዎች ሁሉ ከአንድነት በኋላ የሚመጡ በመሆናቸዉ ከሁሉም አስቀድመን አንድነት እንድጎ ለብት መታገል አለብን፣፣ ከልዩ ነታችን ይልቅ አንድነታችንን ማጎልበትት አለብን ምክንያቱም ሁላችንም በአንደነት መኖር ካልቻልን ባንድነት እንጠፋለን፣፣ አንዳችን ከለላዉ ተለይተን ወደፍት መንቀሳቀስኧንችልም፣፣ ሁላችንም ወደፍት መሄድ የሚንችለዉ ባንድነታችን ብቻ ነው፣፣ ለዚህም  ምክንያቱ ማንነታችን አንድነታችን ሲሆን አንድነታችንም  ኢትዮጵያዊነችን  ነዉ፣፣  ስለዚህ ማንነታችን አትዮጵያዊነታች ነው፣፣ ስለዝህም የአማራ ኢትዮጵያ የለም፣ የኦሮም ኢትዮጵያ የለም ፣የወላይታ ፣የትግረ፣ የስዳማ ፣የአርጎባ፣የሃረር የለሎችም ኢትዮጵያ የለም፣፣  ያለዉ አንድ ኢትዮጵያ ሲሆን እኛም ኢትዮጵያዉያን ነን፣፣ ኢትዮጵያዊያንን በመሆናችን ሁላችንም አንድ አካሎች ነን፣፣ አንድ አካሎች ነን ስንል ከስጋዊ አካላዊነት ያለፈ መንፈሳዊ አካላዊነትንና ማንነትን አንድነት እያወራን ስለሆነ እጅግ ረቂቅ  ነዉ፣፣ ያ መንፈሳዊ አንድነት ነበር ባአባቶቻችን ዉስጥ የነበረዉ፣፣ ያ መንፈሳዊነት ነበር ጠላቶቻቸዉን አንከትክተዉ ከመረት ስር እንድቀብሩ የረዳቸዉ፣፣ እንግድህ የአባቶ ቻችን ታርክ የሚያስተምረን  ልይነቶቻችንን አጥፍተን አንድነታችንን ማጎልበት እንዳለብን የሚያሳይ ሲሆን ይህም ዛሬ የጋራ ጠላታችን የሆነ ወያነ ከሚያደርስብን ሃገራዊ፣ህዝባዊ፣ማህበረሰባዊ፣ቤተሰባዊና  ከግለሰባዊ ጥፋቶች ያድነናል፣፣ በገዛ ሃገራችን እንደሁለተኛ ዜጋ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ በደሎች እየፈጸሙብን፣ ስያሻቸዉ የሚያስሩን ፣የሚገርፉን፣ከቦታችን የሚያፈናቅሉንና ሃገር ጥለን እንድጠፋ የሚያደርጉን  ሃገር አልባ ሰዎ ች አድርገዉናል፣በወያኔ መንግስትና በአጫፋሪዎቹ ያልተበደለ፣ግፍ ያልደረሰበት ኢትዮጵያዊ የለም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣
 ለነጻነት ስታገሉ ብዙ ወንድሞቻችንና፣እህቶቻችን  በወያነ  ዲያብሎሳዊ ወጥመድ ስር ወድቋሉ፣፣ ለለሎች ነጻነት ብለዉ የራሳቸዉን ነጻነት ካጡ ከብዙዋች መሃከል መሪያችንና የነጻነት አባት የሆነዉ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በብእራቸዉ ጫፍ የወያነን ዙፋን ያናጉ፣ ርእዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ እና  ጦማሪያንና፣እነ በቀለ ገርባ ዉብሸት ታየና ለሎች ጠቅሰን የማንጨርሳቸዉ ይገኛሉ፣፣ እነዝህ እንቁ የሃገራችን ልጆች በዲያቢሎሱና ጨቋኙ ወያነ  ማጎርያ ጣቢያዎች ከቀን ወደ ቀን የተለያዩ ስቃዮ ች እየደረሱባቸዉ ይገኛል፣፣ እነዚህ ሰዎች እንደለሎች ለሆዳቸዉ አናድርም ብለዉ፣ ለለሎች ነጻና እኩል ካልሆኑ እኛም ነጻ አይደለንም በማለት የነጻነት ተምሳለት ሆነዉ ታስሩዋሉ፣፣ እነዚህ ታላቅ  የነጻነትታጋዮች  በአምባገነን ሃይል የታሰሩ ቢሆንም ስራቸዉና ለነጻነት ትግል የጣሉት መሰረትን ከሰማይ በታች ባለዉ በማንም እጅ መታሰር ባለመቻሉ በሁላችንም ዉስጥ አለ፣፣ይህንን መሰረት የተጣለለትን የነጻነት ትግል ከዳር የማድረስ ግደታ  እያንዳንዳችን ላይ ተጥሉዋል፣፣ ትግላችን፣ በስሜት የታከለ ጊዚያዊ ሳይሆ ን ከዉስጣችን የመነጨና በፍጹም ሃይላችን የሚናከናዉነዉ እንደሁም የወያነን ዙፋን ለዘላለም የሚያፈርስ መሆ ን አለበት፣፣ ትግላችን፣የነጻነት የፍትህ የእኩልነትንና የአንደነት ክስረት የሚመልስና  ብሄራዊ አንድነትን የሚያለመልም መሆን አለበት፣፣ ትግላችን የአንዳርጋቸው ጽጌ፣የርእዮ ት አለሙ፣የእስክንደር ነጋ ለሎ ችም ለሃገር አንደነትና ነጻነት ስታገሉ የነበሩትን ህልም የሚያሰምር መሆን አለበት፣፣ ትግላችን የሃገርና  የህዝብ የዉርደት ጠባሳ የሚሽርና የነጻነትነት ሰባኪያኒና የአንድነት ሃዋሪያት መሆናችንን የሚያስመሰክር መሆን ፣፣በሃገራችን ነጻነት እንደተራራ ጎልቶ እስከሚታይ ፣ እንድሁም ፍትህም፣ነጻነት፣እኩልነት እንደ ጅረት ሞልቶ እስከሚፈስ  ትግላችንና መስዋእትነታችን ይቀጥላል፣፣
       ነጻነትን ማንም አይሰጥህም፣ ጀግና  ከሆንክ ነጻነትን በራስህ ተቀዳጅ
       አስተያየትዎን በዚሁ አድራሻ ይላኩልን  nathanialoret@gmail.com
            Facebook Nathnael Abate

            Twitter @nathysaint
http://www.ethiolion.com/Pdf/09272014seqayena-yemesewaete-ferie.pdf

http://www.assimba.org/Articles/Yetagaupc_Sikayna_Meswatenet.pdf

http://wwwfreedomstar.blogspot.no/2014/09/blog-post_29.html