Wednesday, April 16, 2014

Gunmen kill nine in western Ethiopia bus attack: state media


ADDIS ABABA Wed Apr 16, 2014 4:40am EDT
(Reuters) – Gunmen ambushed a bus carrying dozens of people in western Ethiopia near the Sudanese border, killing nine and wounding six others, state-run media said on Wednesday.
There was no claim of responsibility and no group was blamed for the attack, but Ethiopia says it has thwarted several plots in recent years by Ethiopian insurgents as well as Somali al Qaeda-linked al Shabaab Islamist militants.
A handful of rebel groups are waging low-level separatist insurgencies in Ethiopia, while Ethiopian troops are part of an offensive against al Shabaab in neighboring Somalia.
The bus ambush on Tuesday evening – near the $4 billion-Grand Renaissance Dam – was the second attack on public transportation in the Benishangul Gumuz region in five months. Four people were killed by a bomb on a minibus in November.
“The bus was targeted while travelling 100 kilometers (62 miles) south of (regional capital) Assosa,” a report on state-owned Ethiopian Television said.
No further details were given, and officials were not immediately available to comment.
In September, two Somali suicide bombers accidentally blew themselves up in Addis Ababa while preparing to detonate explosives among football fans during Ethiopia’s World Cup qualifying match against Nigeria.
(Reporting by Aaron Maasho; Editing by Louise Ireland and James Macharia)

ሮቢንሰን ክሩሶና ሕወሓት-ጦርጦስ፣ ልማት ወይስ ፅዳት? ወቅታዊ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ትንተና


ከአየለ ታደሰ
አጭር መግለጫ
ይህ ጦማር አሁን ባለው የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ዙሪያ መጠነኛ ትንተና ለማቅረብ ያዘጋጀሁት ሲሆን በተለይም የ”አንድ ሰው ምጣኔ ሃብት” ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ ጋር በማዛመድ ለየት ያለ የአቀራረብ ዘዴ በመጠቀም የ”ዘመናችንን” የሕወሓት-ጦርጦስ ምጣኔ ሃብትን ለመቃኘት ሞክሬያለሁ። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ረዥም ጥቁር ጥላዉን በ(መካከለኛው) አፍሪካ ጥሎአል


ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የ1994 የሩዋንዳ የጭፍጨፋ እና የእልቂት ጸጸት በ2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰማይ ላይ እያንዣበበ ነው!
ባለፈው ሳምንት የሩዋንዳ ህዝብ እርስ በእርስ የተራረደበትን 20ኛውን ዓመት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት መጥፎ ገጽታ ለማስታወስ የሀዘን ሳምንት አውጆ ድርጊቱን በመራር ሀዘን ዘክሮታል፡፡ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 6/1994 በመንግስት የስልጣን እርከን ላይ የነበሩ አክራሪ የሁቱ ጎሳ አመራሮች፣ የእነርሱ የፖለቲካ አመለካከት ደጋፊዎች እና የተደራጁ ታጣቂ ሚሊሻዎች  ስልታዊ የግድያ ወንጀሎችን በማቀናጀት እና በግንባር ቀደምትነት በመምራት 100 ተከታታይ ቀናት የወሰደ እልቂትን በማደራጀት ከ800 ሺ በላይ ሰላማዊ ህዝቦች በተለይም የቱትሲ እና አክራሪ ያልሆኑ የሁቱ ጎሳ አባላትን ፈጅተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1994 ሩዋንዳ 5.5 ሚሊዮን ህዝብ የነበራት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 14 በመቶ የሚሆኑት የቱትሲ ጎሳ አባላት ነበሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሩዋንዳ 11.5 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን ከዚህ ውስጥ የቱትሲ ጎሳ አባላት ህዝብ ብዛት ከ10 በመቶ ያነሰ ነው፡፡Last week, the people of Rwanda began a solemn week of official mourning
ባለፈው ሳምንት የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ (መአሬ) “የሩዋንዳ አምሳያ” የሆነ ለመናገር የሚዘገንን አስፈሪ ቅዠታቸውን መጋፈጥ ቀጥለዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ ባንኪሙን በመአሬ እየተካሄደ ባለው “የዘር-ኃይማኖታዊ የማጽዳት” ዕኩይ ድርጊት ላይ ልባቸው በሀዘን የተሰበረ መሆኑን በመግለጽ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፣ “የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከ20 ዓመታት በፊት በሩዋንዳ ህዝብ ላይ የደረሰውን ዕልቂት በግዴለሽነት ከዳር ቆሞ ሲመለከት ነበር… እናም አሁን ደግሞ ለመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ህዝቦች ህይወት ደህንነት በቂ የሆነ ምንም ነገር ባለማድረግ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ ወድቀን እንገኛለን… ለአንዳንድ ሰዎች ይህ ጉዳይ የተረሳ ታላቅ አደጋ ነው፡፡ እኔ እዚህ ያለሁት የዓለም ህዝብ ጉዳዩን እንዳይረሳው ለማሳሰብ እና ለማገዝ ነው… እናም በአሁኑ ጊዜ ለመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ደህንነት በቂ የሆኑ ተግባራትን ባለማከናወን በትልቅ አደጋ ውስጥ ወድቀን እንገኛለን…በዚህች አገር የዘፈቀደ የጅምላ ግድያ ወንጀሎች በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ የዘር-ኃይማኖት የማጽዳት ዘመቻ እውን በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ አናሳዎቹ የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት አገራቸውን ጥለው በመሰደድ ላይ ናቸው፡፡ እንዲህ ያለ ድርጊት ‘በፍጹም እንደገና አይደረግም’ እያልን እራሳችንን እያታለልን መቀጠል የለብንም፡፡ ይህንን አዘናጊ አባባል ብዙ ጊዜ ደግመን ደጋግመን ብለነዋል፡፡ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ እና በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየተፈጸመ ያለውን የጅምላ ፍጅት በአስቸኳይ ማስቆም ይኖርብናል…“ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡
ከ20 ዓመታት በፊት የሁቱ የዘር ግንድ የሆኑት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ጁቬናል ሀብያሪማና ተሳፍረውበት የነበረው አውሮፕላን በተተኮሰ መሳሪያ ከተመታ በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡ እ.ኤ.አ በ1993 የሁቱ እና የቱትሲ ጎሳ አባላት በጋራ የጥምር መንግስት ለማቋቋም የተጀመረውን ጥረት ወደ ጎን በማለት እና አክራሪ የሁቱ ጎሳ አባላት ቀደም ሲል በሁለቱ የጎሳ አባላት መካከል ተደርጎ የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ የቱትሲ ጎሳ አባላትን እነርሱ በረሮዎች እያሉ በሚጠሯቸው የቱትሲ የጎሳ አባላት ላይ እልቂት በመፈጸም “የመጨረሻውን ጦርነት” ወደ ተግባር አሸጋገሩት፡፡ አካዙ (የሁቱ ጎሳ አባላት የፖለቲካ አመራሮች እና ልሂቃን) እየተባሉ የሚጠሩት የጅምላ ዘር ፍጅቱ ከመጀመሩ ቢያንስ ከአንድ ዓመት በፊት የቱትሲ ጎሳ አባላት የሆኑትን ሩዋንዳውያን/ት ዜጎችን ለመፍጀት የታሰበበት ዕቅድ ነደፉ፡፡ የእራሳቸውን ሬዲዮ ጣቢያ (ኮሊንስ) አቋቋሙ፡፡ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 1994 የዘር ማጥፋት ፍጅቱ በተጀመረበት ወቅት እነዚህ የሁቱ የፖለቲካ አመራሮች ሬዲዮ ጣቢያቸውን ነፍሰ ገዳዮችን ለማደፋፈር እና ለማበረታታት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ግድያ እንዲፈጸምባቸው ያዘጋጇቸውን የቱትሲ ጎሳ አባላት ስም ዝርዝር የሚያነቡበት እና እነዚያን ዘግናኝ የዘር ፍጅት ወንጀሎች እንዲፈጽሙ ለሚታዘዙ ገዳይ ሚሊሻዎች (ኢንተርሀሞይ እና ኢምፑዛሙጋምቢ) የትዕዛዝ መልዕክቶች የሚተላለፉበት ነበር፡፡ ሁቱዎቹ በተደጋጋሚ በሬዲዮ ጣቢያው እንዲህ የሚል መልዕክት ያስተላልፉበት ነበር፣ “በእውነት ሁሉም የቱትሲ ጎሳ አባላት ከምድረ ገጽ መጥፋት አለባቸው፣ ቱትሲዎች ከዚህች አገር መጥፋት አለባቸው… ቱትሲዎችን እያነጣጠረ ለሚመታው መሳሪያ ምስጋና ይግባውና ቱትሲዎች ቀስ በቀስ በመጥፋት ላይ መገኘታቸው ብቻ አይደለም ዋናው ጉዳይ ሆኖም ግን እንደ አይጥ እየታደኑ መገደላቸው ጭምር እንጅ፡፡” እ.ኤ.አ በ1994 ከሩዋንዳ ከተማ ኪጋሊ በ30 ማይል ርቀት ላይ ከምትገኘው እና በሩዋንዳ ታላቅ ከተማ ከሆነችው ኒያማታ በምትባለው ከተማ የሚኖሩ 120 ሺ የሩዋንዳ ዜጎቸ ነበሩ፡፡ በአንድ ወር እና በአንድ ወር ከግማሽ ጊዜ ውስጥ በዚህች ከተማ ውስጥ 50 ሺ ብቻ ሰዎች ቀሩ፡፡ ከስድስት ቱትሲዎች መካከል አምስቱ ይገደሉ ነበር፡፡”
በአሁኑ ጊዜ የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ (መአሬ) በኃማኖት ጽንፈኝነት፣ በጅምላ ጥላቻ እና በእርስ በእርስ ጦርነት ማጥ ውስጥ ተዘፍቃ ተበታትና ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 ሰለቃ ሚሊሻ (እ.ኤ.አ በማርች 2013 የመአሬን መንግስት በኃይል ያስወገዱት የአማጽያን ህብረት ቡድኖች) “በአገሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ እና በመላ አገሪቷ የጭካኔ ግድያዎችን ማድረግ ጀመሩ፣ እናም የአገሪቱን ዋና ከተማ ባንጉይን በመቆጣጠር የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ፍራንኮይስ ቦዚዝን ከስልጣን አባረሩ፡፡ በቀጣዮቹ አስር ወራት የሰለቃ ኃይሎች ለቁጥር የሚያታክቱ ሰላማዊ ህዝቦችን ፈጁ፣ ብዙ መንደሮችን በእሳት አጋዩ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ዘረፉ፡፡ “ከስልጣን የተወገዱትን ፕሬዚዳንት ቦዚዝን ጨምሮ 90 በመቶ የሚሆነው የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ህዝብ የክርስትና እምነት ተከታይ ቢሆንም ቅሉ አብዛኞቹ የሰለቃ ኃይሎች እና መሪያቸው ሚሸል ጆቶዲያ የእስልምና ኃይማኖት እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡ እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ ከሆነ የሰለቃ አማጽያን የበቀል ጥላቻ ባላቸው የክርስትና እምነት ተከታይ በሆኑት እና ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ለምሳሌም ያህል ጎራዴ ባልታጠቁት እንዲሁም ባልተጠናከረ መልክ በተደራጁት በሳንጎ በሚኖሩት ጸረ ባልካ ተዋጊዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ፈጣን የሆነ የማጥቃት እርምጃ ወሰዱባቸው፡፡ እ.ኡ.አ በ2013 የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ውስጥ የጸረ ባልካ ተዋጊ ኃይሎች በሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ላይ በተለይም በመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ሰሜናዊ ምስራቅ በሚኖሩት ዜጎች ላይ ዘግናኝ የሆነ የጥቃት እርምጃ ወስደውባቸዋል፡፡ ጥቃቱ በተጠናከረ መልኩ የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሰላም አስከባሪ ኃይል በምዕራብ የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ የሚኖሩ የሲቪል የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጽዳት ዘመቻ ማስቆም አልቻለም፡፡ ከሩዋንዳ ዋና ከተማ ከባንጉይ በ150 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው ያሎኬ በምትባል ከተማ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ 30 ሺ የሚገመቱ የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት በስምንት መስጊዶች አማካይነት እምነታቸውን እያራመዱ በሰላም እና በፍቅር ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች እማኝነት ከሆነ በአሁኑ ጊዜ ከ500 ያነሱ የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት እና አንድ መስጊድ ብቻ ቀርተዋል፡፡
ባለፈው ዓመት የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በመካከለኛው አፍሪካ ሬፑብሊክ እየተካሄደ ያለውን የዘር-ኃይማኖት የማጽዳት አደገኛ ዘመቻ በማስመልከት የመጀመሪያ የማስጠንቀቂያ ደዎል አሰምተው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 አምነስቲ ኢንተርናሽናል በመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ በመካሄድ ላይ ያለው “የሰብአዊ መብት ቀውስ ከቁጥጥር ውጭ መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት በማውጣት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ” ነበር፡፡ የኃይል እርምጃው እና እልቂቱ እየጨመረ በመጣ ጊዜ ብዙ ሺ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች (2 ሺ የፈረንሳይ ወታደሮች እና ወደ 6 ሺ የሚጠጉ የአፍሪካ ህብረት ወታደሮች) ወደ መካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ተልከዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት 12 ሺ የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ተመደበ የተባለው የሰላም አስከባሪ ኃይል እ.ኤ.አ እስከ ሴፕቴምበር 2014 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በቦታው አልደረሰም፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “በመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ላይ ገደቡን ባለፈ መልኩ እየተካሄደ ያለው የኃይል እርምጃ ሁነኛ ገደብ ካልተበጀለት በስተቀር በጠቅላላው በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩት ማህበረሰቦች በሙሉ አገሪቱን ጥለው ለመሰደድ ይገደዳሉ” የሚል ጠንካራ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የጉዳዩን አሳሳቢነት በውል አመላክቷል፡፡ በዚህ የሰው ልጅ እልቂት የአካሄድ ፍጥነት መጠን ከተሰላ እና የዘር ማጽዳት የኃይል እርምጃ ዘመቻው ዒላማ በዚሁ ፍጥነት የሚቀጥል ከሆነ በአብዛኛው የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ምንም ዓይነት የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት የሚባል ነገር ሊገኝ አይችልም፡፡” በማለት ስጋታቸውን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሳውቀዋል፡፡
የሩዋንዳን የ1994 እና የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ የ2014 ሁኔታ በጎንዮሽ በንጽጽር ሲታይ አስደንጋጭ ሁኔታ ነው፡፡ እ.ኤ.አ የ1994 ሩዋንዳን ሁኔታ ስንመለከት የአፍሪካ ህብረት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዩናይትድ ስቴትስን እና የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ለነበረው የዘር ማጽዳት እልቂት እና ፍጅት ጆሮ ዳባ ልበስ የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት፡፡ እ.ኤ.አ የ2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ሁኔታ ሲገመገም ደግሞ “በዘር-ኃይማኖት ማጽዳት” ዕኩይ ምግባር ምክንያት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ሲጨፈጨፉ እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ከቀያቸው ሲፈናቀሉ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የይስሙላ የሰላም አስከባሪ ኃይል በመመደብ የታዕይታ ስራ ለማሳየት ከመሞከር ባለፈ የንጹኃን ዘጎችን ህይወት ለመታደግ የሚያስችል ተጨባጭነት ያለው ስራ ሲሰራ አልታየም፡፡ ለድፍን ሙሉ ዓመት በመካለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ በግልጽ ሊታይ የሚችል ጥላቻ እና አደጋውንም መከላከል የሚያስችል ዕድል የነበረ ቢሆንም የአፍሪካ ህብረት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጋጣሚውን በበጎ መልኩ ሳይጠቀምበት ባክኖ ቀርቷል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዲህ የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል፣ “ለ10 ወራት በስልጣን መንበር ላይ በመቆየት  ለደረሰው ዕልቂት፣ ከህግ አግባብ ውጭ ለተፈጸሙ ግድያዎች፣ ለአስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት እና ዝርፊያ እንዲሁም በገፍ ለክርስቲያን መንደሮች በእሳት መጋየት እና መውደም ሰለቃዎች ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ሰለቃዎች ጥቃታቸውን ከሰነዘሩ በኋላ ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉ ዓለም አቀፉ ኃይል ለጸረ ባልካ ታጣቂዎች ድጋፉን በመስጠት ከተማ በከተማ ላይ እየተቆጣጠሩ ኃይላቸውን እንዲያጠናክሩ አጋጣሚውን ፈጥሮላቸዋል፡፡ የተከሰተው የኃይል እርምጃ እና የሙስሊም ማህበረሰብ አባላትን የማፈናቀሉ ሁኔታ የሚጠበቅ ክስተት ነበር፡፡“
በታሪክ የምጻት ቀን፣
አፍሪካ ከ1994ቱ የሩዋንዳ እልቂት እና ፍጅት ትምህርት ቀስማለችን? ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለአፍሪካ ደህንነት በእርግጠኝነት በጽናት ቆሟልን? በሩዋንዳ ላይ አጥልቶ እንደነበረው የእርስ በእርስ እልቂት አፍሪካ ጆሮ ዳባ ልበስ ብላ ዝምታን በመምረጧ ምክንያት እንደተከሰተው ዘግናኝ ድርጊት ሁሉ አሁንም ልትወገዝ ትችላለችን? በዘር-ኃይማኖት ማጽዳት እና በዘር ማጥፋት ዘመቻ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው (በቀልቀሎ እና ስልቻ ያለ  ዓይነት ልዩነት)? በሩዋንዳ ላይ ተከስቶ የነበረው አስከፊ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ተመልሶ በመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ መምጣቱ ይሆን? ሩዋንዳ የወደፊቷ መካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ነበረችን? እናም የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ የወደፊቷ የአፍሪካ ተምሳሌት ልትሆን ትችል ይሆን?
የዘር የዘር ማጥፋት ወጀልና የኃይማኖታዊ ወገንተኝነት ኢቦላ ከሚባለው አጥፊ  በሽታ (ቫይረስ) ተማሳሳይ ነው፡፡ እንደ ኢቦላ ቫይረስ የዘረኝነት እና የኃይማኖት ወገንተኝነት ሲጀምር አሳሳቢ አይደለም ፡፡ የኃይማኖት ጭቆናን እና ዘረኝነትን የሚዋጉ ህዝቦች እራሳቸውን እንደ ትክክለኛ ዜጋና ለፍትህ ታጋይ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ በትግላቸው ጽናት መሰረት ድልን ሲቀዳጁ የተነሱለትን ዓላማ ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ ለሚሊዮኖች ስቃይ እና ሞት ምክንያት በመሆን ሌሎች በተቃራኒው ከቆሙት ጽንፈኞች እኩል የሆነ ወይም የበለጠ የህዝብ እልቂት ወንጀሎችን ይፈጽማሉ፡፡ እንደ ኢቦላ ቫይረስ ሁሉ ዘርኝነት እና የኃይማኖት ጽንፈኝነት የአፍሪካ የፖለቲካ ሰውነት ውህዶች ሆነዋል፡፡ አፍሪካ ከኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ከዘረኝነት እንድትጸዳ ከተፈለገ በአስቸኳይ የክትባት መድኃኒት መገኘት አለበት፡፡
በወደፊቷ አፍሪካ የዘር ፍጅት እና በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸም የሚችል አስፈሪ ሁኔታ ፣
ካርል ማርክስ “የኮሙኒስት ማኒፌስቶ” በሚለው መጽሀፋቸው ላይ ለዓለም ህዝብ እንዲህ በማለት አሳውቀው ነበር፣ “በአውሮፓ ላይ አስፈሪ መዓት እያንዣበበ ነው- የኮሙኒዝም አስፈሪ ሁኔታ፡፡“ እንደዚሁም በተመሳሳይ መልኩ “በአፍሪካ ላይ አስፈሪ መዓት እያንዣበበ ነው- የዘር ፍጅት አስፈሪ ሁኔታ እና በሰው ልጆች ላይ ሊፈጸም የሚችል አስፈሪና አሰቃቂ ሁኔታ፡፡“ ማርክስ እንዲህ በማለት ተናግረው ነበር፣ ”እስከ አሁን ድረስ ያለው የህብረተሰብ ታሪክ የመደብ ትግል ታሪክ ነው፡፡“ ሁኔታው ከዚህ አንጻር ሲቃኝ የወደፊቷ አፍሪካ የዘር ፍጅት እና በሰው ልጆች ላይ የሚደረግ እልቂት የሚተወንባት መድረክ አህጉር ልትሆን ትችል ይሆን? በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሮማ ስምምነት አንቀጽ 5 (a) ስር የተደነገገው በዘር ማጽዳት እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በሚመለከት የህግ ጥበቃ መብትን ያጎናጽፋል፡፡ አንቀጽ 6 “የዘር ማጽዳት” ውሱን የሆኑ ድርጊቶችን በማካተት ማለትም “የብሄራዊ፣ የጎሳ፣ የዘር ወይም ደግሞ የኃይማኖት ቡድንን በአጠቃላይ ወይም በከፊል ለማጥፋት ሆን ተብሎ ታቅዶ የሚፈጸም  ድርጊት“ ነው በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ከሌሎች በተጨማሪ “በአንድ ቡድን አባላት ላይ ሆን ተብሎ በተጠና ስልት ዕቅድ ተነድፎ ግድያ ለመፈጸም ወይም ደግሞ በአካል ወይም በአእምሮ ላይ ሙሉ ለሙሉ ወይም ደግሞ በከፊል ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ጉዳት ለማድረስ“ የሚሉትን ያካተተ ነው፡፡
አንቀጽ 7 በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በሚለው አንቀጽ ስር “ግድያ፣ ባርነት፣ ማጋዝ ወይም ደግሞ ህዝብን በኃይል ማፈናቀል፣ በእስር ቤት ማማቀቅ ወይም ደግሞ ዓለም አቀፍ መሰረታዊ የህግ ድንጋጌዎችን በመጣስ ማሰቃየት፣ አስገድዶ መድፈር እና በማንኛውም የታወቀ ቡድን ወይም በፖለቲካ፣ በዘር፣ በብሄር፣ በጎሳ፣ በባህል፣ በኃማኖት እና በጾታ በተዋቀረ ስብስብ ላይ ሌሎች የአካላዊ ነጻነቶችን መገደብ“ በሚል በማያሻማ መልኩ አስቀምጦታል፡፡
በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እና መለስተኛ የዘር ማጥፋት ዕኩይ ምግባሮች በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ተደጋግመው የሚከሰቱ ባህሪያት ሆነዋል፡፡ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በስተቀር ጥቂት አፍሪካውያን/ት (መሪዎች እና የአፍሪካ ልሂቃን አባላትን ጭምሮ) እና ጥቂት የምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙሀን እና የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ አባላት በአፍሪካ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ግልጽ ውይይት ለማካሄድ ዝግጅት አድርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1994 የፕሬዚዳንት ክሊንተን አስተዳደር በሩዋንዳ ላይ በተፈጸመው ለመናገር በሚዘገንን የሰው ልጆች ዕልቂት ላይ ያልሰማ በመምሰል በአሁኑ ጊዜ የፕሬዚዳንት ኦባማ የደህንነት አማካሪ በሆኑት ሱሳን ራይስ ከእርሳቸው የስራ ባልደረቦች ጋር ድንገተኛ ስብሰባ በማድረግ “’የዘር ማጥፋት’ የምትለዋን ቃል የምንጠቀም ከሆነ እና ምንም ነገር ሳናደርግ እጃችንን አጣጥፈን በመቀመጥ ሁኔታውን የምንመለከት ከሆነ በኖቬምበር በሚካሄደው የኮንግረሱ ምርጫ ላይ የሚያስከትለው እንደምታ ምን ሊሆን ይችላል?“ የሚል የሸፍጥ ንግግር ማሰማታቸው የሚታወስ ነው፡፡
እ.ኤ.አ ከ2003 መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ የሱዳን መንግስት በዳርፉር ግዛት ላይ የጎሳ/የዘር ልዩነቶችን በማጉላት የአረብ ዘላኖች ከአፍሪካ ዘላኖች ጋር የጥላቻ ስሜት እንዲያድርባቸው በመስበክ ጥላቻን ሲያራግብ ቆይቷል፡፡ የሱዳን መንግስት ጃንጃዊድ (እንደ ሩዋንዳ ኢንተርሀሞይ ተመሳሳይ የሆኑትን) እየተባሉ የሚጠሩትን የአረብ ሚሊሻ አባላትን የአፍሪካን የጎሳ ቡድኖች እንዲወጉ እስከ አፍንጫቸው ድረስ ያስታጥቃል፡፡ የሱዳን መንግስት ከሰማይ የቦንብ ናዳ ሲያዘንብ የጃንጃዊድ ታጣቂ ኃይሎች ደግሞ መንደሮችን በእሳት ያጋዩ ነበር፣ የውኃ ጉድጓዶችን በመርዝ ይበክሉ ነበር፣ ሴቶችን አስገድደው ይደፍሩ ነበር፣ እንዲሁም ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ህዝቦችን የገደሉ ሲሆን ከሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሀን ዜጎች ደግሞ እንዲፈናቀሉ አድርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ብዙ ህዝብ ያለቀበትን ዘመቻ በመሩት፣ አስገድደው በደፈሩት እንዲሁም በሰላማዊ የዳርፉር ዜጎች ላይ ዘረፋ በፈጸሙት በሱዳኑ መሪ በኦማር አልባሽር እና በሌሎች ባለስልጣኖች ላይ የመያዣ ደብዳቤ ትዕዛዝ ቆርጦባቸዋል፡፡ አልባሽር ይህንን ሁኔታ በማስመልከት በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ላይ እንዲህ በማለት አፊዘዋል፣ “ሁሉንም ነገር ልቅም አድርጋችሁ ንገሯቸው፣ ለICC ዋና አቃቤ ህግ፣ ለፍርድ ቤቱ አባላት ዳኞች እና ለማንም ይህንን ፍርድ ቤት ለሚረዳ ሁሉ ከእኔ ጫማ ስር መሆናቸውን ንገሯቸው“ ብለዋል ትዕቢት እና እብሪት በተቀላቀለበት አንደበት፡፡
እ.ኤ.አ በ2007 መጨረሻ አና በ2008 መጀመሪያ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የኬንያ የድህረ ምርጫ ውዝግብ ምክንያት በተወሰደው የኃይል እርምጃ ድርጊቱን በበላይነት ያቀነባበሩት እና የመሩት ኡሁሩ ኬንያታ ከሌሎች ተከላካዮች ጋር የእርሳቸውን ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶን ጨምሮ በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው የፍርድ ሂደቱ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡ በዚያ አጨቃጫቂ ውዝግብ በተነሳው ሁከት ምክንያት ከ1,100 በላይ የኬንያ ዜጎች እንደተገደሉ የሚታመን ሲሆን 600 መቶ ሺ የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡ ኬንያታ በሮማ ደንብ መሰረት በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ማለትም ግድያ፣ ማጋዝ ወይም ደግሞ በኃይል ማፈናቀል፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በማሰቃየት እና በሌሎች ኢሰብአዊ በሆኑ የወንጀል ድርጊቶች በሚል ስድስት ዓይነት ክሶች ቀርበውባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ኡሁሩ ኬንታ በሄግ የICCን የፍርድ ቤት ክፍሎች በጭራሽ ሊያዩ አልቻሉም፡፡ እውነት ለመናገር በሰው ልጆች ላይ ወንጀል ፈጽመው ከፍትህ ያመለጡት ኬንያታ እና አጋሮቻቸው ብቻ አይደሉም፡፡ ሌሎች ብዙዎች የአፍሪካ “ዘር አጥፊዎች” እና በሰው ልጅ ላይ ወንጀልን የሚፈጽሙ አፍሪካውያን ወንጀለኞች በICC እና በሌሎች ችሎቶች ላይ አፍንጫቸውን  በትቢት ቀሰረው ይነፋሉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ የሚኖሩት የአካባቢው ቀዳሚ ኗሪ ህዝቦች በጊቤ ሶስት ግድብ ግንባታ በመንደር ምስረታ ሰበብ በመፈናቀላቸው ምክንያት የመጥፋት ችግር እያንዣበበባቸው ይገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 በዓለም ዕውቅናን ያተረፉት የተፈጥሮ ሀብት ክብካቤ እና ጥንታዊ የሰው ዘር ተመራማሪ የሆኑት ባለሙያ ዶ/ር ሪቻርድ ሊኬይ የጊቤ ሦስት ግድብ ግንባታ የግል ጥቅም ማሳደጃ “ሳይንሳዊ” ጥናት በስነምህዳሩ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን ውጤቶች አሳንሶ የሚያይ መሆኑን የምር በመሞገት “ግድቡ በርካታ የሆኑ አሉታዊ ውጤቶችን እንደሚያስከትል እንዲያውም አንዳንዶቹ በሁለቱም በኩል ማለትም በአካባቢው ስነምህዳር እና ለዘመናት ህይወቱን በዚህ ወንዝ የታችኛው ክፍል ላይ መስርቶ ለሚኖረው ማህበረሰብ ህይወት ፍጅት እና ዕልቂት“ ሊሆን እንደሚችል አስረግጠው ተንብየዋል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥአካል በቀዳሚ የጊቤ ሸለቆ ኗሪ ህዝቦች ላይ የጊቤ ሶስትንግድ በመገንባት የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች  ወንጀል በመፈጸም ድርጊትተጠያቂ ሊሆን ይችላል?
በምዕራብ ኢትዮጵያ የጋምቤላ ህዝቦች ለዘመናት ቅድመ አያቶቻቸው ሲጠቀሙበት የነበረውን የህዝቡ አንጡራ ሀብት የሆነውን ለም መሬታቸውን እና ቤቶቻቸውን በመንጠቅ ለህንድ ባለሀብቶች አስረክበዋል፡፡ አንድ የህንድ ኩባንያ “2,500 ካሬ ኪ/ሜ ስፋት ያለው ድንግል ለም መሬት – በእንግለዝ የዶርሴት ግዛትን የሚያህል” ከታክስ ነጻ በሚባል መልኩ በሳምንት 150 ፓውንድ (245 ዶላር) ሂሳብ “አከራይቷል፡፡” ለካራቱሪ ኩባንያ ጥቅም ሲባል በጋምቤላ የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሚኖሩበት ቀዬ እንዲፈናቀሉ በማድረግ የገዥው አካል የመንደር ምስረታ ፕሮግራሙ አካል አድርጎታል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ጥናት መሰረት “ቀዳሚ ኗሪ ህዝቦችን ጥንት አያት ቅድመ አያቶቻቸው ይኖሩበት ከነበረው ቀያቸው መንቀል በአሁኑ ጊዜ በገጠሪቱ የጋምቤላ አካባቢ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የአኙዋክ (ምናልባትም የሌሎች አናሳ ብሄረሰቦች) ባህል ፍጹም በሆነ መልኩ ይጠፋል የሚል ግምት አለ፡፡“ በማለት ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በጋምቤላ በመንደር ምስረታ ፖሊሲውጠቀሜታ ሰበብ በዘር ጥፋት እና በሰው ልጆች ላይእየፈጸመ ላለው ወንጀ ተጠያቂ ነውን?
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ወደ ሩብ ምዕተ ዓመት ያህል በዘር ላይ የተመሰረተ ያልሰለጠነ የጎሳ ፖለቲካ ፓኬጆችን እየነደፈ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን “የጎሳ ፌዴራሊዝም” እያለ በሚጠራው የእውር ድንብርብር ዘረኛ ስርዓት በጭፍን ፍላጎት ግላዊ እና ቡድናዊ ጥቅመኝነትን በማራመድ ላይ ይገኛል፡፡ ገዥው አካል የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር እና በጎሳ በመከፋፈል በአስፈሪ የአከላለል ስልት ሰውን ያህል ክቡር ፍጡር እንደ ከብት በቦታ በመከለል “ክልል” (በተለምዶ የተቀነበበ የሚል ትርጉም ሲኖረው በተመሳሳይ ትርጉም ቃሉ የተከለከለ ወይም የተቀነበበ ዞን የሚል ትርጉም ይዞ ይገኛል) በሚል የዜጎችን የመዘዋወር እና በመረጡት ቦታ ሰርቶ ለመኖር ያለውን መብት የሚደፈጥጥ የፖለቲካ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ “የክልልነት” ፍልስፍና የአፓርታይድን “ባንቱስታኒስም” (“ጥቁር ደቡብ  አፍሪካውያን/ት የጎሳ ቤቶች”) ብዙዎችን ባህሪያቶች ይጋራል፡፡ ሁለቱም የፖለቲካ ፍልስፍናዎች በዘር እና በቋንቋ በመለያየት በአንድ መንደር ላይ እንዲሆኑ የፈረጇቸውን የጎሳ ቡድኖች በመጨረሻ ወደ አንድ ወጥ “እራሱን የቻለ” ብሄር በመመስረት ላይ ዓላማ ያደረገ ስልት ነው፡፡ “ክልላዊነት” “የመንደራዊነት“ መገለጫ አንዱ አካል ሲሆን ኢትዮጵያን ወደ ተበጣጠሱ የተለያዩ መንደሮች፣ ሰፈሮች እና ጎጦች ያሳንሳል፡፡ “ክልሎች” በመሰረቱ የዳበሩ እና የተጠናከሩ የአፓርታይድ ቅጅ ባንቱስታንስ ናቸው፡፡ “ክልላዊነት” የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ ወንጀል የመፈጸም መፈልፈያ ቦታዎች ናቸውን? በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ከህዝቦች ፍላጎት ውጭ በኃይል እየተገበረ ባለው “ክልላዊ” ፖሊሲው ሰበብ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ ለሚፈጸም ወንጀል ሙሉ ኃላፊነቱን ሊወስድ ይችላልን?
ከአስርት ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል “የዘር ፌዴሪያሊዝምን” በመተግበር ላይ የሚገኝ ቢሆንም እንኳ የኦጋዴን አካባቢ ህዝቦችን የነጻ ብሄርነት ጥያቄን በኃይል በማፈን በኢትዮጵያ የኦጋዴን ህዝቦች ላይ በማያቋርጥ መልኩ የጥቃት ዘመቻዎችን በማድረግ ህዝብን ለእልቂት እና ፍጅት ዳርጎ በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ አገዛዙ የኦጋዴን ህዝብን በማስራብ እና የኦጋዴንን ከተሞች እና መንደሮች በኢኮኖሚ እንቅስቃሲያቸው ዝግ እንዲሆኑ የማድረግ ፖሊሲን የመተግበር ዓላማን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ገዥው አካል በቅርብ ርቀት በሚተኮሱ የአውሮፕላን ላይ ጥቃቶች የኦጋዴንን ሰላማዊ ህዝብ በጅምላ ይደበድባል፣ እንዲሁም በድርቅ ለተጎዳው የአካባቢው ህዝብ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የሚመጣውን እርዳታ እንዲቋረጥ በማድረግ ሰብአዊ መብትን ይደፈጥጣል፡፡ ግድያዎችን፣ ማሰቃየትን፣ አስገድዶ መድፈርን እና አፍኖ የደረሱበትን የማሳጣትን ዕኩይ ተግባራት የኦጋዴንን ህዝብ ለማጥቃት ገዥው አካል የሚጠቀምባቸው ስልቶች ናቸው፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች “የጅምላ ቅጣቶች፡ በኢትዮጵያ በኦጋዴን አካባቢ በሶማሊ ክልል የጦር ወንጀሎች እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች“ በሚል ርዕስ የገዥውን አካል ጽልመታዊ የዕልቂት ወንጀሎች የሚያትት ባለ130 ገጽ ዘገባ አውጥቶ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በኦጋዴንዝብ ላይ እየተፈጸመላለው የዘር ማጥፋት፣ በሰው ልጆች ላይ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች እና የጦር ወንጀለኝነት ኃላፊነቱን ይወስዳልን?
እ.ኤ.አ በ2005 በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በግንቦት ወር የተደረገውን አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሁከት በመቶዎች የሚቆጠሩ ያልታጠቁ ንጹሀን ዜጎችን የመግደል ትወናውን ፈጽሟል፡፡ ፖሊስ እና የደህንነት ኃላፊዎች በቅርቡ በህይወት በተለዩት በአቶ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ስር በመሆን እንዲሁም በእርሳቸው ቁልፍ አዛዦች አስተባባሪነት የንጹሀን ዜጎች እልቂት እንዲፈጸም ተደርጓል፡፡ በአቶ መለስ የተቋቋመው የአጣሪ ኮሚሽን ቢያንስ 193 ንጹሀን ሰላማዊ አማጺዎች ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን፣ ሌሎች 763 ዜጎች ደግሞ መቁሰላቸውን እና 30 ሺ ዜጎች ደግሞ የዘፈቀደ እስራት የተፈጸመባቸው መሆኑን በዘገባው አካትቶ ለመንግስት አቅርቧል፡፡ የኮሚሽኑ ማስረጃ በመቀጠልም እ.ኤ.አ ኖቬምበር 3/2005 በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ታዋቂው ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው የማጎሪያ እስር ቤት ተፈጠረ በተባለ ሁከት ሰበብ የግቢው ጥበቃዎች በ15 ደቂቃ የጊዜ ርዝመት ውስጥ ከ1,500 በላይ ጥይቶችን በመተኮስ በእስር ቤቶች ላይ ያርከፈከፉ ሲሆን በዚሁ የተቀነባበረ ዕኩይ ተግባር 17 ንጹሀን የህግ ታራሚ ዜጎች ሲገደሉ 53 ዜጎች ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ አቶ መለስ በግላቸው በሰው ልጆች ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ኃላፊነትን መውሰድ ይኖርባቸው ነበርን? በአሁኑ ጊዜ በአገዛዙየስልጣን ወንበር ላይ ያሉት ባለስልጣኖች ወይም ደግሞ ሌሎች በህገወጥ ድርጊቱ ላይ ተሳትፎየነበራቸው ሆኖም ግን አሁኑ ጊዜበአገዛዙ የስልጣን ወንበር ላይ የሌሉ የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች .. 2005 የኢትዮጵያ አገር አቀፍምርጫ በሰው ልጆች ላይለተፈጸመው ወንጀል እና ዕልቂት ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው?
እ.ኤ.አ በሜይ 2012 የአማራ ተወላጆችን ከደቡብ ኢትዮጵያ “በዘር ማጽዳት” የዘመቻ ስልት ሀብት እና ንብረት አፍርተው ከኖሩበት ቦታቸው በመባረራቸው በይስሙላው ፓርላማ ተገኝተው ይህንን ዘገባ ያቀረቡት እና ለህዝብ ይፋ ያደረጉት ሰዎች ኃላፊነት የማይሰማቸው ዜጎች ናቸው በማለት የይስሙላ ጩኸታቸውን በማሰማት የእርሳቸውን የግዳጅ ማፈናቀል (አንዳንዶች “የዘር ማጽዳት” እያሉ የሚጠሩትን) ለማስተባበል ሞክረዋል፡፡ አቶ መለስ እንዲህ ብለዋል፣ “አማራዎች ወይም ከምስራቅ ጎጃም መጥተው የሰፈሩት “ሰፋሪዎች” (ሰውን በእራሱ ሀገር ላይ “ሰፋሪ” ወይም “በህገወጥ መልክ የሰፈሩ“ እያሉ መጥራት ምን ያህል አዋራጅ ነው ንቀት ነው!) በአካባቢው ስነምህዳር ጥበቃ አንጻር ታሳቢ ሆኖ በደቡብ መጥተው ከሰፈሩበት ቀያቸው መነሳት አለባቸው” ሲሉ አስረግጠው ተናግረው ነበር፡፡ አቶ መለስ በግል በእራሳቸውበሺዎች የሚቆጠሩ “የአማራ” ዜጎችን ከደቡብኢትዮጵያ ከሚኖሩበት ቀያቸው ከፍላጎታቸው ውጭ በግዳጅ በማባረራቸ በሰው ልጆች ላይበተፈጸመ ወንጀል ኃላፊነትመውሰድ ይኖራባቸው ነበርን?
በዚሁ ዓመት ባለፈው ኤፕሪል በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል የአማራ ተወላጆችን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ (በኢትዮጵያ ካሉት ዘጠኝ ክልሎች አንዱ የሆነ “ክልል”) በግብሩ “የዘር ማጽዳት” ተብሎ በሚገለጸው መሰረት በግዳጅ እንዲባረሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ታዋቂው የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራር እና በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሩዋንዳ ዋና አቃቤ ህግ የነበሩት ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም የአማራ ተወላጅ የሆኑ ዜጎችን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ በግዳጅ እንዲባረሩ መደረጉ በውስጠ ተዋቂነት “የዘር ማጽዳት” መሆኑን ከሙያ አንጻር ያላቸውን አስተያየት በማከል ሀሳባቸውን አካፍለዋል፡፡ አንድ ዓይነት ውሱን ቋንቋ በመናገራቸው ምክንያት ብቻ በግዳጅ ኃይልን በመጠቀም እንዲባረሩ መደረጉ በክልሉ ውስጥ አለመረጋጋትን ሊፈጥር ይችላል፣ እንዲሁም ደግሞ ይህ ዓይነቱ ስልታዊ የዘር ማጽዳት በአግባቡ ተጠናቅሮ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ቢቀርብ ድርጅቱ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በማዘዝ ወንጀሎችን እንዲመረምር ማስጀመር ይቻላል፡፡
በአሁኑ ጊዜ  በአገዛዙ የስልጣን ወንበር ላይ ያሉት ባለስልጣኖች  ሚስጥር አድርጎ የያዙት ቢሆንም ብዙ የኢትዮጵያ አካባቢዎች  በድርቅ እና በረሀብ እየተጠቁ ነው፡፡ በዚህ ዓመት በፌብሯሪ ከ91 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ 2.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በረሀብ የተጠቁ መሆናቸውን ቢሮክራሲያዊ በሆነ መልኩ የአገዛዙ ባለስልጣኖች  ይፋ በማድረግ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚፈልግ  አስታውቀዋል ፡፡ አጠቃላይ የምግብ ፍላጎት (ቀደም ሲል ገዥው አካል ዝቅ አድርጎ የገመተው ቢሆንም) 388,635 ሜትሪክ ቶን እንደሚያስፈልግ ተገምቷል፡፡ በረሀቡ በይበልጥ የተጠቁት ክልሎች ጋምቤላ (16.7%)፣ ሶማሊ (13.8%)፣ ትግራይ (11.3%) እና አፋርን (10%) ያጠቃለለ ነው፡፡ ገዥው አካል ለዚህ ችግር 51.6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብቻ ማለትም በጠቅላላው ከሚያስፈልገው ውስጥ 12.8 በመቶ ብቻ የሚሸፍን በጀት መድቧል፡፡ እየመጣ ላለው ረሀብ የማስጠንቀቂያ ደወሉ እየተደወለ ቢሆንም የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት ባለ “ሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት” ያስመዘገበ መሆኑን በታላቅ ኩራት ተናግረዋል፡፡ በድርቅ ከተመቱ አካባቢዎች የሚገኙ መረጃዎች በገዥው አካል ተጽዕኖ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ይፋ የማይደረጉ ሲሆን መረጃዎች ስለማይታዩ እና ስለማይዘገቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት በረሀብ በየወሩ ይሞቱ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በሚያሳየው ቸልተኝነት እና ለረሀቡ በቂ በጀት ባለመመደብክንያት የተሟላ መረጃእያለው የረሀብ እልቂቱ እንዲከሰት በማድረጉ ሰበብ በረሀብ ለሞቱ የዘር ማጥፋት ኃላፊነት ይወስዳልን?
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እ.ኤ.አ በሜይ 1991 ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ “በአማራ” እና በሌሎች ዜጎች ላይ ሰንፋጭ በሆነ የጎሳ ተኮር የማጠልሸት ንግግር ላይ ተጠምዶ ቆይቷል፡፡ አሁን በቅርቡ ከሶስት ወራት በፊት ገዥው አካል በ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪ የነበሩትን እና በኢትዮጵያ አቆጣጠር የመቶኛ ሙት ዓመት በዚህ ዓመታ ተከብሮላቸው የዋሉትን የዳግማዊ ዓጼ ምኒልክን ስም የማጠልሸት እና የማዋረድ ዕኩይ ምግባር ላይ በመተወን እና በማስተባበር ዘመቻ ላይ ተሰማርቶ ነበር፡፡ ገዥው አካል በጎሳ ቡድኖች መካከል ጥላቻን በመዝራት እና መሰሪ ተግባራትን በመስራት አጼ ምኒልክን እንደ መሳሪያ በመጠቀም የጥላቻ ዘመቻውን ቀጥሎበት ነበር፡፡ የጥላቻ ዘመቻው በይበልጥ ይካሄድ የነበረው በገዥው አካል የቅርብ ታማኝ ሎሌዎች፣ መሰሪ ተዋንያኖች እና አሻንጉሊቶች አማካይነት ነበር፡፡ በሎሌዎቹ አማካይነት ገዥው አካል ጥላቻን የሚቀሰቅሱ ቃላትን፣ ሰንፋጭ ንግግሮችን እና የአጼ ሚኒልክን ጨካኝነት የሚል ውንጀላን በማራገብ በዘለፋ ላይ በመሰማራት ተልዕኮውን ለማሳካት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አጼ ሚኒልክ ከሞቱ ከ100 ዓመታት በኋላ ገዥው አካል ምኒልክ ሰይጣኑ ገዳይ እንደነበሩ አድርጎ ለመሳል ጥረት አድርጓል፡፡ የዚህ ዓይነቱ መሰረተቢስ ፕሮፓጋንዳ ዓላማው ምንድን ነውበአሁኑ ጊዜ እየተደረገ ያለው ሰንፋጭንግግርበጎሳ ጥላቻው ላይ ነዳጅ ለመጨመር የተሰላ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነውን?
በቅርቡ በህይወት የተለዩት አቶ መለስ ዜናዊ የብሩህ አእምሮ ባለቤት ናቸው (የውጭ አድናቂዎቻቸው ማዳም ሱሳን ራይስ እና ክላሬ ሾርት እንደሚያምኑት) ትንሽ ጥበብ እና በዘልማድ የሚመሩ ቢሆኑም እንኳ፡፡ ህጻናት እርስ በእርሳቸው እንዲፈራሩ ምዕናባዊ ጭራቅን እንደሚጠቀሙ ሁሉ አቶ መለስም የዘር ማጥፋትን በህዝቡ ላይ በማስፈራሪያነት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 አቶ መለስ የሩዋንዳን የዘር ማጥፋት ሰለባዎች ትዝታ ክብር የማዋረድ እና ዘለፋ ማካሄድ ብቻ አይደለም ያደረጉት፣ ሆኖም ግን ሰንፋጭ የሆነ ንግግሮችን በማሰማት የአሜሪካ ደምጽ የአማርኛው አገልግሎትን ከሩዋንዳው ሚሌ ኮሊን የሬዲዮ ጣቢያ ጋር በማነጻጸር የፖለቲካ ጠቀሜታ ትርፍን ለማግኘት የዳከሩበት ዕኩይ ምግባር እንጅ፡፡ አቶ መለስ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የሩዋንዳን ሬዲዮ መጥፎ ባህሪያት በመቅዳት ዝቅተኛውን የጋዜጠኝነት የሙያ ስነ ምግባር በማያሟላ መልኩ እና በጎጅ የፕሮፓጋንዳ ስራ ላይ ተጠምዶ በብዙ መልኩ ለበርካታ ዓመታት እያስተላለፈ ያለው ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ እናምናለን፡፡“ አቶ መለስ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ለኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን ፕሮግራም ለማፈን በሚል ህገወጥ ተግባር ለረሀብ ሰለባዎች ረሀብ ማስታገሻ እና ለጤና ክብካቤ እንዲሁም ለትምህርት አገልግሎት ሊውል ቢችል ኖሮ ብዙ ጠቀሜታ ሊኖረው የሚያስችል በርካታ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለዘር ማጽጃ ህገወጥ ተግባር አውለዋል፡፡
እንደዚህ ያሉ አስደንጋጭ ቃላት ናቸው ከአቶ መለስ አፍ ግልጽነት በጎደለው መልኩ የሚወረወሩት፡፡ አቶ መለስ “የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እንደ ሬዲዮ ሚሌ ኮሊንስ የመሳሰሉ መጥፎ ልምዶችን በመኮረጅ“ ሲሉ ለማስተላላፍ የፈለጉት መልዕክት ምንድን ነበር? በመስመሮች መካከል ያሉ መልዕክቶች ነበሩን? የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የመጨረሻውን ጦርነት ለማድረግ ጥሪ በማቅረብ ጥቂት ኢትዮጵያውያንን/ትን እንደ “በረሮ”፣ “ ጎጅ ነብሳት“ እና “አይጦች“ ለመጨፍጨፍ መደምደማቸው ነበርን? በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ስርጭት ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ ሊንቀሳቀሱ የሚችሉት ዘር “አጽጅዎች” እነማን ናቸው? አቶ መለስ  ለዘር ማጥፋት ተግባራት ጥቂት ኢትዮጵያውያንን/ትን “ከአገሪቱ ለማስወገድ እና ለማጥፋት” ገዳይ ሚሊሻዎችን እና አፋኝ ቡድኖችን የሚመራው እና የሚያስተባብረው የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አግልግሎት ነው ማለታቸው ነበርን? አቶ መለስ ሆን ብለው የሩዋንዳን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለፖለቲካ ዓላማ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት እና ለኢትዮጵያውያን/ት እንዲሁም በገንዘብ ለሚረዷቸው የውጭ ለጋሽ ድርጅቶች ከእርሳቸው እና ከአገዛዛቸው ውጭ ኢትዮጵያ ሌላዋ ሩዋንዳ እንደምትሆን በተጨባጭ ለማሳመን ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ ማንም ገዥ አካል ቢሆን የዘር ማጽዳት ስልትን በመጠቀም በስልጣን ላይ ተጣብቀው ለመቆየት ለሚፈልጉ አምባ ገነኖች ለዘላለም ተቃውሞ ሊደረግባቸው ይገባል!
ማንኛውም አፍሪካዊ ወንድ እና ሴት አንድ ሺ አንድ ምክንያቶችን በመፍጠር ለተስፋ መታገል አለባቸው፣
በማንኛውም የአፍሪካ አገር ላይ የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ ወንጀል መፈጸም በእያንዳንዱ የአፍሪካ አገር ላይ የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ ወንጀል እንደመፈጸም መቆጠር አለበት፡፡ በሩዋንዳ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ የአፍሪካ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ነው፡፡ የቱትሲ እና ጽንፈኛ ያልሆኑ የሁቱ የጎሳ አባላትን ለመፍጀት የተቀነባበረ ወንጀል ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ድርጊት በሁሉም አፍሪካውያን/ት እና በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ የፈሪዎች ወንጀል ነው፡፡ ይህ ዕኩይ ምግባር በማንኛውም ህያው በሆነ/ች አፍሪካዊ/ት ላይ ሊረሳ የማይችል ጥልቅ ትውስታን እና ጠባሳ ጥሎ የሄደ ወንጀል ነው፡፡ አፍሪካውያን/ት ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ይህንን አስቀያሚ ክስተት ማስታወስ አለባቸው፡፡ ከዕልቂት የተረፉት እና የኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆኑትን የኤሊ ዋሲልን አባባል በመዋስ “ሁሉም አፍሪካዊ/ት ገዳዮችን ማስታወስ አለበት፡፡ እያንዳንዱ/ዷ አፍሪካዊ/ት የወንጀሉን ሰለባዎች ማስታወስ አለበት/ባት እያንዳንዳቸው ለተስፋ ሲሉ አንድ ሺ አንድ ምክንያቶችን ለመፍጠር ቢችሉም አንኳ፡፡ ምክንያቱም ስናስታውስ ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ ምክንያቱም ስናስታውስ ተስፋን ለማስወገድ ኃላፊነት ይኖረናል፡፡ ተስፋ ከተስፋ ማጣት የበለጠ ተፈጻሚነት አለው፡፡“
ለዘር ማጥፋት እና በሰው ልጅ ላይ ለሚፈጸም ወንጀል የሰው ልጅ ልብ ዋና ማስቀመጫ ሳንዱቅ ነው፣
በሩዋንዳ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል እ.ኤ.አ ኤፕሪል 6/1994 ጎራዴዎችን የታጠቁ ወሮበሎች መንገዶችን በወረሩበት ጊዜ አልተጀመረም፡፡ የዚያ የዘር ማጥፋት ዘር የተዘራው ከጎሳዊነት አስተሳሰብ ውጭ ቀደም ሲል ከአስርት ዓመታት በፊት በመጥፎ አካሄድ በሚመሩ እና በተወገዙ ሩዋንዳውያን/ት ልብ ውስጥ የተጸነሰ ነበር፡፡ ጥላቻ እና ታጋሽየለሽነት ዘር ወይም ኃይማኖት የላቸውም፡፡ የዘር ማጥፋት ቀስ በቀስ ጥላቻን በሚንከባከቡ እና ቀስ በቀስ ወደ ታላቅ ብስጭት ውስጥ በመግባት በወንዶች እና በሴቶች አእምሮ ውስጥ የሚበቅል እርኩስ መንፈስ ነው፡፡ በዋሻ ጨለማ ውስጥ እንደሚበቅል እንጉዳይ የዘር ማጥፋት እንጉዳይም በጨለማ ልብ ውስጥ የሚበቅል አረም ነው፡ አፍሪካውያን/ት ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም፡፡ የዶ/ር ማርቲን ሉተርኪንግን እንዲህ የሚል መልዕክት ማስታወስ አለባቸው፣ “ጨለማን ጨለማ አያስወግደውም፣ ብርሀን ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችለው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ጥላቻን ጥላቻ አያስወግደውም፣ ፍቅር ብቻ ነው ያንን ለማድረግ የሚችለው፡፡“ የእውነት ብርሀን ብቻ ነው የጨለመውን ልብ ሊያበራ የሚችለው፡፡
ዝምታ እና ግዴለሽነት ለዘር ማጥፋት እና በሰው ልጅ ላይ ለሚፈጸም ወንጀል ኦክስጅን ናቸው፣
የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም ወንጀል የዝምታ እና የምንቸገረኝነት ወንጀሎች አስፈላጊ ወንጀሎች ናቸው፡፡ ታላላቆቹ ኃያላን አገራት በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ጊዜ ዝምተኛ ምስክሮች ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 6/1994 ጀምሮ ምን እንደሚካሄድ በእርግጠኝነት ያውቁ ነበር፡፡ ሆንም ግን ዝም ማለትን መረጡ፡፡ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት እና የአውሮፓ ህብረት ዝምታን መረጡ፣ ሆኖም ግን ሁኔታውን በሚገባ ያውቁ ነበር፡፡ የእርስ በእርስ መተራረዱ ከ100 ቀናት በላይ ወሰደ፣ እናም የ800 ሺ ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ ምክንያቱም ይህንን ሰይጣናዊ ድርጊት ሊያስቆሙ ይችሉ የነበሩት ኃይሎች ለጉዳዩ ደንታ አልነበራቸውም፡፡ አፍሪካውያን/ት እራሳቸውን ለማዳን ሌሎችን የውጭ ኃይሎች መጠበቅ የለባቸውም፡፡ እራሳቸውን ከእራሳቸው መጠበቅ አለባቸው፡፡ ለዚህም ነው ሁሉም አፍሪካውያን/ት የጎሳ ጥላቻን እና የኃይማኖት አለመቻቻልን የሚያራግቡትን የሰይጣን ፈረሰኞች በአንድ አእምሮ እና ቃል ማውገዝ ያለባቸው፡፡ አፍሪካውያን/ት በዘር፣ በጎሳ፣ በኃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በጾታ ወይም በማንኛውም ሌላ ጉዳት ሊያስከትል በሚችል መልክ ክፍፍል እየፈጠሩ ጥላሸት በመቀባት የሚለያዩትን መሰሪ ግለሰቦች እና ቡድኖች በንቃት መቋቋም አለበት፡፡
ከእርቅ በፊት እውነት እና ፍትህ፤
የዓለም አቀፋዊ ወንጀሎች ቡድን ተጠሪ የሩዋንዳ አቃቤ ህግ የሆኑት በቅርቡ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በህይወታችን ሙሉ እነርሱን እንከታተላቸዋለን፣ እናም ከእኛ በኋላ የሚመጡትም እንደዚሁ ይከታተሏቸዋል፡፡ ያለእውነት እና ትክክለኛው ፍትህ ሳይሰጥ ምንም ዓይነት ዕርቅ ሊኖር አይችልም፡፡“ ይኸ ለሁሉም አፍሪካውያን/ት ትልቁ መልዕክት ነው፡፡ ፍትህ እና እውነት/ዕርቅ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ በየትኛውም ጎን ሳንቲም ወደ ላይ ቢጓን አንድ ጎኑን የሰብአዊ መብት ፊት ያሳያል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዕርቅ ማለት ያለፈውን ኢፍትሀዊ ውርስ ለማስተካከል በጋራ መስራት ማለት ነው፡፡“ ያለፉት ኢፍትሀዊነቶች ለወደፊት በአፍሪካ ዕድል ላይ የሚያጠሉ ረዥም የጨለማ ጥላሸቶች ናቸው፡፡
የማስተማር ኃላፊነት፣
በሩዋንዳ እና በዳርፉር የተፈጸሙ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ሰለባዎችን ማስታወስ እና በመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ በመካሄድ ላያ ያለውን “የጎሳ-ኃይማኖት ማጽዳት” ዘመቻ ማውገዝ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ የአፍሪካ ወጣቶች ስለዘር ማጽዳት እና በሰው ልጆች ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች መማር አለባቸው፡፡ የዚህ ዓይነቱ መረጃ የአፍሪካ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት ስርዓት አካል መሆን አለባቸው፡፡ ድንቁርና የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ማዳበሪያ ነው፡፡ ባንኪሙን ለሩዋንዳ ህዝቦች እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ “’ድጋሜ በፍጹም’ እንደገና እና እንደገና የሚሉትን ቃላት በማለት ብቻ ተወስነን መቅረት የለብንም፡፡“ እነዚህ ህይወታቸውን ያጡትን እና በተስፋ መቁረጥ ህይወታቸውን ለማትረፍ የሚሰደዱትን የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ ነጻ ወንዶችን፣ ሴቶችን እና ልጆችን ለማገዝ በጣም ዘግይተው የመጡ ባዶ ቃላት ናቸው፡፡
የአፍሪካ መሪዎች ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ከመተቸት እና በጥላቻ መልክ ከማየት ይልቅ ድርጅቶቹ የአፍሪካ ወጣቶችን ስለሰብአዊ መብት ትምህርት እንዲሰጡላቸው  መጋበዝ እና እነርሱም በተራቸው ያገኙትን ስልጠና እና እውቀት በመጠቀም ሌሎች አቻ ጓደኞቻቸውን እና ማህበረሰቡን በእውቀት፣ በክህሎት እና በአመለካከት አቅማቸውን በማሳደግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን የሰብአዊ መብት መርሆዎች ማስፋፋት ይችላሉ፡፡ በአፍሪካ የሰብአዊ መብት ትምህርት መስጠት በጣም አስፈላጊ እና በአፍሪካ ግጭቶችን ለማስወገድ ቅድመ የክንውን ተግባር ነው፡፡ ከቀደሙት የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ ከተፈጸሙት ወንጀሎች የማይማሩ እራሳቸውን ይደግሟቸዋል፡፡
የአፍሪካ አጭር ወንዶች እና ረዥሙ ጥላቸው፣
የአፍሪካ ምሁራን በአፍሪካ ያለ የአስተዳደር ችግር የታላቅ ሰው አገዛዝ ህግ የሚለው መሪዎች መንግስትን የእራሳቸው መጠቀሚያ መሳሪያ በማድረግ የመንግስት ሀብትን ለእራሳቸው እና ለደጋፊዎቻቸው በማከፋፈል በተራቸው እነዚህ ደንበኞች ደግሞ መንግስት በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ በማገዝ የእራሳቸውን ግላዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ጥረት ያደርጋሉ በማለት ትንታኒያቸውን ያቀርባሉ፡፡ የአፍሪካ አስተዳደር ትልቁ ችግር ግን በተቃራኒው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ የቆየ አባባል እንዲህ በማለት ያስተምረናል፣ “አጭር ወንዶች  (ያፍሪካ መሪዎች ) ጥላቸው በረዥም ሲዘረጋ ለጸሐይ  መጥለቂያዋ ጊዜ መሆኑን ይነግራል ፡፡“ በአፍሪካ በትልልቅ የስልጣን ደረጃ ላይ ያሉ ታላላቅ ሰዎች እና ታላላቅ መሪዎች ለመምሰል የሚያስመስሉ እጅግ በጣም ብዙ አጫጭር ወንዶች አሉ፡፡ የአፍሪካ አጫጭር መሪዎች በእርግጠኝነት ህዝብን እያሳደዱ የሚያድኑ የተኩላ ጅብ መንጋዎች ናቸው፡፡ በጣም አናሳ የሆነ እውቀት ያላቸው እና ገደብ የሌለው ጉዳት ለማድረስ ሌት ከቀን የሚታትሩ ጭራቆች ናቸው፡፡ የአፍሪካ አጫጭር መሪዎች ትንሽ ራዕይ ያላቸው እና ያልተገደበ ስልጣን ያላቸው ናቸው፡፡ አናሳ ፍቅር ያላቸው ትንሽ ወንዶች ናቸው፡፡ በጥላቻ እና ነገሮችን ሁሉ በኃይል ለመጨፍለቅ የሚተጉ ናቸው፡፡ እነዚህ በአፍሪካ ያሉ አጫጭር መሪዎች መጥፎ መሪዎች ብቻ አይደሉም፣ ሆኖም ግን መጥፎ ወንዶች መጥፎ የሰው ዘሮች ጭምር እንጅ፡፡ ረዥሙን ጥላቸውን ይዘረጋሉ፣ እናም አፍሪካን “ጨለማው አህጉር” እንድትሆን አድርገዋል፡፡ “ያለፉ (አሮጌ) ኃጢያቶች ረዥም ጥላዎችን ይዘረጋሉ፡፡”ይባላል ::  የትንንሽ ሰዎች (ያፍሪካ መሪዎች ) ኃጢያቶች በአፍሪካ ረዥም የጨለማ ጥላ ጦርነት፣ የዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ይዘረጋሉ፡፡
ከአጭር አፍሪካ  መሪዎች  በላይ ከፍ ብለው በመቆም ረዥሙን የጨለማ ጥላቸውን በማስወገድ በብርሃናማው የፍቅር ጸሀይ፣ እውነት፣ መቻቻል ስምምነት፣ ፍትህ እና ዕርቅ መለወጥ የእያንዳንዱ/ዷ አፍሪካዊ/ት ኃላፊነት ነው፡፡
የ1994ን ሩዋንዳ አስታውሳለሁ፡፡ የ2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክን አስታውሳለሁ፡፡ ተስፋ ከተስፋ ማጣት የበለጠ መሆን የሚችል ክስተት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሚያዝያ 7 ቀን 2006 ዓ.ም

A Call to Amhara Ethnic People


By Zelalem Eshete (PhD)
This is a call to Amhara ethnic people from an Amhara ethnic individual. This is a about looking at ourselves inwardly first than looking at others outwardly. In doing so, it is my intention to demonstrate how we can put the problem of unity at the center and look at other ethnic people using different sets of eyeglasses thereby taking the unity dialogue to a new level in truth and love.
We, Amahra of today, need to take the responsibility on our own initiative and stand in the gap to be accountable to the ills of our forefathers. The brokenness of the marginalized, abused and neglected people begets that they are the soul of Ethiopia. This is because the new unity of Ethiopia is championed and realized first by those who are marginalized and abused.
To that end, we rise up and address the problem at hand with three-pronged solutions. How desperately we need to be part of the solution towards a national reconciliation for the transformation of Ethiopian history from marginal unity to authentic unity.
Confession: deal with the past
The Greek word for “confess” is homologeo which means: “to say the same thing” and then “agree, admit, acknowledge”. It is time we say the same thing as the truth. There is debt in the history books. It doesn’t matter if we personally do not have a prejudice against another ethnic group. The debt of past tragedy needs to be settled. It is real and grave. There is nothing more tragic than considering and treating another human being as sub-human because they are of a different ethnic group. We need to teach history to our kids so that they too stand in the gap and become a part of this historic healing process by acknowledging the shame.
The people who suffered a lot shouldn’t be burdened to convince us about what happened. We need to learn on our own and come to the realization that the flaw of a fallen humanity also tarnished the Ethiopia we admire. We need to be burdened by the gravity of the situation so much that our soul is sick of the mistakes made.
Repentance: deal with the present
The Greek word for repentance means: “think differently after” or “after a change of mind”. This is the second step we need to take. Unless we repent, confession is just a lip service with no value whatsoever. Real confession, a realization and acknowledgment of the mistakes done, brings us to repentance. This activity moves us from the past to the present. Repentance or change of thinking is the one that unstuck us and get us moving on the path to healing and reconciliation.
The new Ethiopia is built on this new thinking birthed out of confronting the reality as it is. Lack of repentance (change of thinking), forces us to perpetuate the ills of the past right into the future. It is inexcusable to march on the same or engage in reactive mode in the 21st century.
Discover: deal with the future
When we right the wrongs of the past through confession and repentance, then only we are free from the shackle of the past to envision the future together as a family of one. Together, we discover our new identity that unites us all in truth as never before. Remember that only love is meant to bind us together.
When we come to the light and experience genuine unity based on equality and nobility – we will know that our past unity is just a shadow crying out for the real one. As our identity crises exits and makes a way for the new identity to come forth defining Ethiopia anew – the whole world would witness the other face of Ethiopia: One Family under our Creator!
In conclusion, fulfilling our responsibility would pave the way for the healing process to begin. Unless we move ahead with a new wholesome identity, we relive the mistake of the past reformatted differently that even makes us a victim today.
I conclude by echoing the words of Nelson Mandela:
“Great anger and violence can never build a nation. We are striving to proceed in a manner and towards a result, which will ensure that all our people, both black and white, emerge as victors.”

You can find other writings of Dr. Zelalem Eshete at: www.EthioFamily.com

Ethiopians in Norway discussed the current political situation in Ethiopia and the role of the Diaspora


This meeting was organized by the Democratic Change in Ethiopia Support Organization in Norway (DCESON) and took place on the 12th of April 2014 in Oslo from 15.00-21:00 p.m.The meeting attended by around 200 Ethiopians who live in Oslo and the other parts of Norway.
It was attended by around 200 Ethiopians who live in Oslo and the other parts of Norway. The guest speaker at the meeting was ato Bizuneh Tsige who is the member of the leadership of Ginbo7 movement for justice, democracy and freedom. The guest speaker held a broad speech.
The public meeting was opened by holding a minute of silence to remember the victims of the TPLF racist rulers and prisoners of conscience in Ethiopia. The minute of silence was led by ato Abi Amare who is in charge of the public relations part of the DCESON. Following this, ato Yohannes Alemu, the chairman of the DCESON spoke about how the DCESON was established and its objectives. He told the participants that the organization at the moment supports the UDJ party that is based in Ethiopia and Ginbot7 that is based in exile (abroad). Moreover, he stressed that all Ethiopians should overcome their differences and contribute to the decisive all sided struggle to get rid of the racist rule of the TPLF in Ethiopia.Public meeting in Oslo (Norway
The guest speaker ato Bizuneh Tsige spoke about the history of the struggle of Ethiopians beginning from the period of the rule of Emperor Haile Selaasie to the present one. He pointed out that the current racist TPLF rule is totally different from the preceding governments because it is based on and fosters ethnicity. Ato Bizuneh Tsige also mentioned the causes for the collapse of the two former governments and dealt in detail with the clear causes that can bring about the rapid collapse of the TPLF regime. He mentioned the following two issues as the significant ones in the present Ethiopian politics.
1. The current conflict between the Muslim community and the TPLF regime.
2. The opposition to the renaissance dam.
In relation to the opposition of the Muslim community, he indicated that the struggle is peaceful and the TPLF regime has not been able to suppress it. He admires the struggle. The regime has not addressed and answered the demands of the Muslim community and he does not expect any positive or constructive response from the TPLF regime. The evidence for this view is the fact that the regime has not met any of the four demands of the Muslim community so far. Besides, the regime has arrested the leaders of the Muslim community on the basis of fabricated charges. The prisoners are languishing in the regime`s prison without the due process of law. He could not say how long the struggle of the Muslims will continue as it is now but he said he does not believe the struggle will continue and go long without changing its present direction. He stated that the struggle of the Muslim community can succeed as part of the overall struggle of Ethiopians for their basic human and democratic rights. This struggle should go further and include all the rights.
Concerning the issue of the renaissance dam, he explained that the regime has come up with this idea or project to distract the attention of the public from the repression and crisis in the country. The TPLF dictatorship does not have any national vision and has gone to the extent of giving away Ethiopian land.
The opposition forces in the Diaspora have foiled all the attempts of the TPLF regime to mobilize and collect money through selling bonds and direct contributions from the Diaspora. Ethiopians living in Norway have also foiled the same attempts of the regime to sell bonds and collect money in Norway. He concluded his speech by stating that the issue of the dam can cause the fall of the TPLF regime and its current confrontation with Egypt can create a dangerous condition and be harmful to Ethiopia.
Following this, the guest speaker responded to the several and various questions raised by the participants and wide ranging discussions were held. Later on, the vice chairman of the DCESON ato Daniel Abebe made s statement of declaration of position and said that the DCESON condemns the repression and human rights violations the TPLF is committing against the people of Ethiopia. He also reiterated that the DCESON will continue to stand by and support Ginbot 7. He thanked ato Bizuneh for coming and speaking to the participants.
The song of Ginbot 7 popular force was sung in the beginning and end of the meeting by the singers and the participants were entertained by Ethiopian cultural music. Ethiopian dishes prepared by the women`s section of the DCESON were also served during the meeting. The whole meeting was led by ato Fikre Assefa. In the end, the DCESON thanks all who contributed to the success of the meeting, came from the other parts of Norway and members of the organization.
Victory to the people of Ethiopia.
The DCESON.