Wednesday, March 19, 2014

Foreign spies target refugees in Norway


flgdecl1000004767_-00_norway-flag-decal[17.03.2014, 09:11am, Mon. GMT]
The head of Norway’s security policy has warned that many asylum-seekers who are granted refuge in the country are under threat by their country’s secret service.  “We do not know the scope of this due to the high volume of unreported numbers. However, we experience that the scope of refugee espionage has increased along with the number of refugees that come to Norway,” Trond Hugubakken was quoted as saying in an interview with Oslo’s daily Vårt Land.
According to the newspaper report, officials in Norway say they are monitoring the situation and investigating reports of refugees who are being kept under surveillance in Norway by agents from their home countries.
Short of naming specific countries, the report said certain states involved in refugee espionage have recently tightened the rules for freedom of speech in their own country. The goal of these states is to silence the critics of authoritarian regimes.
In a recent interview with the Norway Post, Mahmood Amiry-Moghaddam, a Norwegian-Iranian human rights activist and the head of the Oslo-based organisation Iran Human Rights, said:
“We have several examples of Iran’s secret services approaching family members of refugees who have criticised the regime here in Norway.”
(neuroe)

11% እድገታችን’ ከሚታየው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር:-


Sebhat Amare( Norway)
Imageእንደሚታወቀው በአንድ ሃገር የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ክንውኖች የቀን ተቀን ለውጥ ውስጥ የህብረተሰብ ተሳትፎ(አስተዋጽኦ) ጉልህ ሚና አለው፡፡ እንዲሁም በሂደቱ ውስጥ የሚያጋጥሙ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ጉዳዮችም ይሁኑ ወይም በተቃራኒው የሚከሰት ተፈጥሯዊም ሆነ በመልካም አስተዳድር ችግር ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች ዞሮ ዞሮ ከህብረተሰብ ጫንቃ ላይ አይወርድም፡፡ ይህ ስለሚታወቅ ሃላፊነት የሚሰማቸው፣ ለሃገርና ለሕዝብ ታማኝ የሆኑ፣ በሕዝብ ይሁንታ ስልጣን የያዙ መንግስታት ያላቸው ሃገሮች በየትኛውም ሃገራዊ እንቅስቃሴ ላይ ሕዝባቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ በማድረግ በብሔራዊ ስሜት የታነፀና በሃገሩ ጉዳይ ላይ ቅንጣት ታህል የማያመነታ ብርቱ ህብረተሰብን ይገነባሉ፡፡ የእንደኛ አይነቶቹ የሃገርና የሕዝብ ፍቅር የሌላቸው አምባገነን የወያኔ መሪዎች ግን እንኳን ‘የሃገርህ ጉዳይ ያገባሀል’ ብለው ሊያሳትፉት ቀርቶ የአንድን ሕዝብ የዴሞክራሲ መሰረት የሆነውን የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፈጥሮዊ የሆነውን መብቱን እንኳ ገፍፈው ሃገሪቱን የቁም እስር ቤት አድርገዋታል፡፡
የወያኔ ጁንታ ’11% እድገት አሳይተናል’ እያለ በሌለ ተስፋ ላይ ተቀምጦ በሚኮፈስበት እና ሳተላይት ልናመጥቅ ነው፤ አውሮፕላን ፈበረክን፤ ልማታዊ መንግስት ……. እያለ ትምክህቱን በሚያሳይበት በአሁን ወቅን በሃገራችን መኖር ያልቻልን ኢትዮጵያውያን ድንበር አቋርጠን በተፈጥሮ የበለጸገች ሀገራችንን ጥለን ወደ ተለያዩ ሀገራት በስደት ተበትነን እንገኛለን፡፡ በአንጻራዊ የተሻለ የመኖርያ ቦታ ፍለጋ ለስደት የወጣው ወገናችን ያሰበበት ቦታ ሳይደርስ በበረሃ አሸዋ የተበላውና በባህር ሰጥሞ የቀረውን ቤቱ ይቁጠረው፡፡ እንደ ሰው አንድ የያደርገን ባሕርይ፤ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት ያልታየበት በደል ባለፈው ሰሞን በሳዑዲ ዐረብያ ግዛት እንደተፈጸመን መጥቀስ በቂ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። የዱር አውሬ እንኳን ከዚህ የተሻለ ክብር አለው። እነዚህ እጅግ ኋላ ቀር የሆኑ አረመኔዎች ከእንስሳ እንኳን አንሰው አንዲት በፍርሃት ነብሷን የሳተችን ሴት የሚደፍሩትን እያየን የተደፈሩት ‘ህጋዊ’ ናቸው ‘ህገወጥ’ የሚል የሕግ አንቀጽ መረጣ ውስጥ ልንገባስ እንዴት ይቻለናል? ህዝባችን እረኛ እንደሌለው መንጋ ተበትኖ፤ ተዋርዶና ክብሩን ጥሎ መኖር ከጀመረ እነሆ 23 አመታትን አስቆጠሯል፡፡ ዜጎቻችን በቄያቸዉ በሰላም ሰርተዉ እንዳይኖሩ በወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ መሬታቸውን ተቀምተውና ተማርረው በስደት የበረሀና የባህር ሲሳይ እየሆኑ ከዛም የተረፉት ይኸዉ አሁን እንደምናየዉ በጨካኝ መንግስታት ፖሊሶች ለእንግልት እና ለአሰቃቂ ሞት ተዳርገዋል፡፡ በሰለጠነ ዘመን ወደኋላ እንደ ጋርዮሽ የጨለማ ዘመን በወገኖቻችን ላይ በአረብ ሀገራት መንግስታት የሚደርሰዉን እንግልት የአለም አይን እና ጆሮ እንዲያይ እና እንዲሰማዉ በየቦታው ባሉ የሳዑዲ ኤምባሲዎች የተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች በመጠኑም ቢሆን የአለም ህዝብ ችግሩን እንዲረዳ ለማድረግ አስችሏል፡፡
”ነፃነት፣ አንድነት፣ ፍትህ እና እኩልነት በወሬና በዲስኩር አይመጣም” እንደተባለው የመስዋዕቱ አይነት ይለያይ እንጂ አነሰም በዛም ለነፃነት የሚደረግ ትግል ወይ ሃብትን ወይም የህይወት መስዋዕትነትን ይፈልጋል፡፡ ይህንን ሁሉ በህዝብና በሃገር ላይ የሚደርሰውን ለከት ያጣ ጭቆና የምናይ እና የምንሰማ በተለይ በሰለጠነው አለም የምንኖር ወገኖች እኛ በሰው ሃገር የምናገኘውን እንዲህ ያለውን የመፃፍ፣ የመናገር፣ የመሰብሰብና ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ወገናችን በገዛ ሃገሩ ሲያጣ፣ ይህ ነው የማይባል ችግር ሲወርድበት በተግባር መልካም ውጤት የሚያመጣ ስራ ለመስራት ቆርጠን ልንነሳ ይገባል፡፡ በአንድነትና በቁጭት ለሃገራችን ህዝብ ነጻነት ካልተነሳን በስተቀር የወያኔን ተንኮል ችላ ማለት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የወገኖቻችንንና የውዲቱ ሃገራችንን የመከራ ጊዜ ማራዘም ማለት ነው፡፡ ዘረኛው ወያኔ በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት የማፍረስና የመበተን የመገነጣጠሉንና ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለባዕዳን የመስጠቱን እኩይ ተግባር መመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬዋ ዕለት የሚታይ እውነታ ነው፤ ለዚህም ለማስረጃ ያህል ሰሞኑን በስፋት እንደሚወራው የ’ድንበር ማካለል’ ስም ተሰጥቶት የምዕራቡን የሃገራችንን ክፍል ለሱዳን አሳልፈው መስጠታቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በኢትዮጵያችን መልካም አስተዳደር ጠፍቷል፤ ሙስና እንደ ሸረሪት ድር በየቦታው አድርቷል፤ ‘የሕግ የበላይነት አለ’ በሚባልበት አገር ፍትህ ርቋል፤ ዘረኝነትና ጎጠኝነት ከመቼውም በላይ ተንሰራፍቷል፤ በሕገ መንግሥት የተረጋገጡ መብቶች ተጨፍልቀዋል፡፡ 
በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የኋሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ወያኔ ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ አስተሳሰብና የሃይል አምባገነናዊ አገዛዝ ተሸብቦ ያላስነባው ህዝብ፤ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፤ ያላፈረሰው አንድነት፤ ያላዋረደው የህዝብ ስብዕና፤ ያልገባበት የእምነት ተቋም፤ ያልበተነው የሞያ ማህበራት፤ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም:: 
ባለፉት አመታት በወያኔ አገዛዝ በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገውን ትግል ለማኮላሸት እርስ በርሱ የሚቃረኑ ህጎችና መመርያዎችን አርቅቆ አያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ አንገላቷል፤ ገድሏል፤ ከአገር በግፍ እንዲሰደዱም አድርጓል። ይሄንኑ የወያኔን ግፍ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተፈፀሙ ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት ሰሞኑን አውጥቷል፡፡ በሪፖርቱ የተካተቱት የመብት ጥሰቶች በህዝባችን ላይ በተደጋጋሚ እና በከፍተኛ ሁኔታ ወያኔ እያደረሰ ያለውን ግፍ በእማኝነት ያሳየ ሪፖርት ነው፡፡ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሪፖርቱ ያካተታቸው እንደተጠበቁ ሆኖ፤ በወያኔ የተፈጸሙ እና እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከዚያም የላቁ እንደሆኑና ሃገራችንና ህዝቧ ምን ያህል ውጥንቅጥ ውስጥ እንዳለን ያሳየ ሪፖርት ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ሃገራችን ሀሳብን በነፃነት ያለፍርሀት መግለፅ የማይቻልባት፤ የዜጎች የኑሮ ደረጃ ከዕለት ዕለት እየተባባስ የሚሄድባት፤ ዘመናዊ የመረጃ መገናኛዎች ሆን ተብለው የታገዱባት፤ የህዝቦቿን ጥንታዊና ብርቅዬ የሆነውን መከባበርና አንድነት በዘር ጥላቻና በሀይማኖት ለመከፋፈል አገዛዙ የሚጥርበት፤ ዜጎች አለአግባብ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት፤ ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰደዱባት፤ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያልተካሄድባት፤ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ከቀዬአቸው የሚፈናቀሉባት፤ ለሕግ ተገዢ ያልሆነ መንግሥት ያለባት፤ ዜጎች የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆኑ በስተቀር በነፃነት ሠርተው መኖር የማይችሉባት፤ ነፃ ሚዲያ የሌለባት፤ ዜጎች ለሀብት ንብረታቸው ዋስትና የማያገኙባት፤ ህዝባዊ መንግሥት የሚናፍቅ ህዝብ ያለባት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት የገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ መጠቀሚያ የሆኑባት፤ ቤቶች በቁመታቸው ማደጋቸው እንደዕድገት የሚቆጠርባት ሀገር ሆናለች። ስለሆነም ኢትዮጵያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማድረግ ለነፃነት፣ ለፍትህ እና ለእኩልነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡ 
ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ’ገዢዎቻችን’ ከተፈጥሮ ባህሪያቸውና የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት ከማፍረስ አንፃር የፈለጉትንና ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብና በሃገር ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ በአንድነት በማበር በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብለን ለለውጥ እንድንነሳ በህብረት በመስራት ውዲቱ ሃገራችንን ከውድቀትና ከጥፋት ለማዳን የኢትዮጵያዊነት ሃላፊነታችንንና ድርሻችንን እንወጣ፡፡ 
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

source:- http://ethiopianewsforum.com/viewtopic.php?f=2&t=74165

የፈረሰው ቅንጅት ሶስት አራተኛው እንደተመለሰ ይሰማኛል፤ (የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ)


በአንድነት እና መኢአድ የዉህደት እንቅስቃሴ ላይ አስተያይተ የሰጡት የፓርላማ እና የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ምክር ቤቶቹ ይሄን ታሪካዊ ዉሳኔ ባሳለፉበት ወቅት የሚከተለውን ብለዋል።

«ዛሬ በመኢህአድ ፅ/ቤት የመኢህአድ እና የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት የጋራ ስብሰባ አድርገው አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል። ይህውም ለቀጣይ ሐሙስ መጋቢት 11/2004 ዓ/ም የቅድመ ውህደት ሰምምነት እንዲደረግ እስከ አሁን ውህደቱን ለማዘግየት የተወሰደው ጊዜ ከበቂ በላይ በመሆኑ አጅግ አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ ይህን ጉዳይ አጠናቆ የጋራ ጉባዔውን የሚያመቻች ኮሚቴም በእለቱ ይፋ እንዲደረግ ከስምምነት ተደርሶዋል። እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ውህድ በሚሆኑበት ወቅት ፈታኝ ይሆናሉ የተባሉ የፕሮገራም እና የደንብ ልዮነቶች የሚባሉት ውሕዱን ፓርቲ የተሻለ ደንብና ፕሮግራም እንዲኖረው ከማድረግ የዘለለ ውህደቱን ለማዘግየት ምክንያት እንዳይደሉ መግባባት ላይ ተደርሶዋል። የውህዱን ፓርቲ ስያሜ በተመለከተም ተሳታፊዎቹ በአዲስ መሆን እንዳለበት እና ይህም ተጠንቶ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ የሚወሰን እንደሆነ ግንዛቤ ተይዞዋል። ትልቁ ነጥብ የነበረው በሁለቱም ፓርቲዎች በኩል አመራሮች በምንም ሁኔታ ውህደቱን ለማዘግየት ቢሞክሩ አባላት ተዋሕደው አመራሮች ተንጠልጥለው እንደሚቀሩ በተደጋጋሚ የገለፁ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ጭብጨባ ድጋፍ አግኝቶዋል። እውነት እውነት እላችኋለው ይህ ጉዳይ ከሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ እውን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ይህ ከሆነ ደግሞ የፈረሰው ቅንጅት ሶስት አራተኛው እንደተመለሰ ይሰማኛል። ቸር ወሬ ያሰማን። የመጋቢት 11 ሰው ይበለን።»

ቀዳማይ ወያኔ፤ ዓድዋ እና የካቲት 11 በወያኔ ትግሬዎች እይታ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ)


Ethioia's Territorial Integrity
እኛ በታሪክ አጋጣሚ ተገኝተን ጸረ ወያኔ አቋም ይዘን የምንተነትን ጸሐፊዎች የተቻለንንን ያህል የወያኔ ቅጥፈቶች እያጠናን ስናቀርብ ማንበብ ሰልችቶአቸው ግማሽ ገጽ አንብበው ወደ ቀላል ዜና እና ትንታኔ የሚሮጡ ብዙ እንደሆኑ አገምታለሁ።እንዲህ ዓይነት ልምድ ጥልቅ እውቀት እንዳይኖረን ያግደናል።እንድያ ከሆነ የሚሞግቱንን ጠላቶች በማስረጃ ለመመከት ደካሞች እንሆናለን።መረጃ ሲያጥረን ሕዝቡ የጠላት ‘ፕሮፓጋንዳ’ ተማሪ ይሆናል።። ስለዚህም ብርቱ ድካም፤ምርምር ጌዜ እና መስዋእት የተደረገባቸው ጽሑፎች ማንበብ ድርሻችሁ እንደሆነም አትዘንጉ።

Ethiopian Ambassador doubts need for mediator between Egypt and Ethiopia

By Daily News 

Ethiopia’s ambassador to Egypt said he doubted the need for mediation between Egypt and Ethiopia on the Grand Ethiopian Renaissance Dam, stressing the importance of constructive dialogue as the only alternative.
Ambassador Mahamoud Dirir said in a statement published by the Ethiopian Foreign Ministry on Monday that it is “naïve” to consider that ties between the two countries should “solely be viewed through the prism of the Nile issue.”
Dirir denied reports of third party mediation between the two Nile Basin countries and said, “there are only two, and only two, countries in the entire world which are well-placed to mediate between Egypt and Ethiopia; and these are, of course; Ethiopia and Egypt, themselves.”
He added that the role of Sudan as a partner has been pivotal to “ironing out” difficulties in the dialogue between Egypt and Ethiopia.
Dirir said the countries have enough experience to ensure that the Nile is a source of cooperation between Nile Basin countries, not a source of conflict.
On Monday, Prime Minister Ibrhaim Mehleb held talks with Egyptian Foreign Minister Nabil Fahmy in which they focused on relations with Nile Basin countries and the possibility for developing them. The cabinet said in a statement after the meeting that Egypt is currently dealing positively with all Nile Basin countries in order to preserve its strategic interests and out of recognition of the ambitions of these countries for development.
Ethiopia began diverting water from one of the Nile River’s tributaries in May 2013, and is currently building the Grand Ethiopian Renaissance Dam, expected to be completed within three years. Egypt fears that the electricity-generating dam will have a detrimental effect on its lion’s share of Nile water.
The latest round of talks between Egypt and Ethiopia ended on 10 February without the two sides resolving “sticking points”. The “sticking points” that remain regard the formation of a committee to oversee the implementation of recommendations of a report detailing confidence-building measures concerning the dam and its effect on downstream nations.
Ethiopia said the talks in February “made no progress” because of a difference in opinion regarding the involvement of international experts. It said that while Egypt wants the involvement of foreign experts, Sudan and Ethiopia, do not see the need.
Sudan, which is also an interested party and, like Egypt, is a downstream country, was part of a series of tripartite talks between the three countries in November, December and January. However, they have not reached an agreement.

“ነገረ-ኢትዮጵያ” የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጣ (ቅፅ 1 ቁጥር 4)


Negere Ethiopia Issue 4ነገረ-ኢትዮጵያ ርዕሰ አንቀጽ የህዝብ የአገልግሎት ጥያቄ አስቸኳይ ምላሽ ያሻል!

…በውሃ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችና አዛውንቶች ካለ አቅማቸው ከሰፈር ሰፈር እየተንከራተቱ በጀርባቸው ለመሸከም ተገደዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ምክንያት ህዝብ ስልክና ኢንተርኔት መጠቀም አልቻለም፡፡ ባልታቀዱ ግንባታዎች ምክንያት የሚፈራርሱት መንገዶች ህዝብ በሰዓት ወዳሰበበት ቦታ እንዳይደርስ አድርገዋል፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች የሰማይ ያህል በራቁበት ወቅት ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ህዝብ ሊያገኘው በሚገባው አገልግሎት ላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነውበታል… 
[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

የሃይማኖት እርጅና አያድርስ

ይሄይስ አእምሮ

ይህችን ጽሑፍ ባልጽፋት በወደድኩ፡፡ ግን ያበጠው ይፈንዳ እንጂ እጽፋታለሁ፡፡ በስንቱ ታፍኜ እዘልቀዋለሁ? ብዙ ሚዲያዎች እንደማይቀበሉኝ ከወዲሁ አምናለሁ፤ በዚያ ብቻ ከማሩኝም እሰዬው ነው – ትልቅ ዕድለኝነት፡፡ እውነት በጠፋችባትና ሀሰት በነገሠችባት ዓለማችን ውስጥ ለሺዎች ዓመታት ዜጎችን እሥረኛና ባሪያ አድርጎ እግር ከወርች በማሠር ኮድኩዶ ያስቀረን ጉዳይ ድንገት ተነስቶ መተቸት በትንሹ ውግዘትን ማስከተሉ የሚጠበቅ ነው፡፡ And I am ready to welcome everything of anything.
በዓለም የሚገኙ ሃይማኖቶችን ብዛት ለመቃኘት ሞክሬ ያገኘሁት መልስ በጣም የሚለያይ ነው፡፡ አንዳንድ መረጃዎች የዓለም ዋና ዋና (ግንድ የሚባሉ) ሃይማኖቶችን ወደ 21 ሲያወርዷቸው አንዳንዶች ደግሞ ከአሥርና ከሃያ ሺዎች በላይ ያዘልቋቸዋል፡፡ አንድ ምንጭ ደግሞ 4200 አካባቢ እንደሚደርሱ ያትታል፡፡ የሆነ ሆኖ እንደመነሻዎቹ እንደአይሁድ እምነትም ይሁን እንደስንጣቂው የክርስትና እምነት ከዚያም ቀጥሎና ቆይቶ እንደመጣውም የእስልምና እምነት መሠረት የሰው ልጅ አጠቃላይ ብዛት ከሁለት ሰዎች ተነስቶ አሁን ወዳለበት ሰባት ቢሊዮን ገደማ እስኪደርስ ድረስ ከአንድ ወይም ከምንም ሃይማኖት ተነስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶችን አሁን ሊከተል መቻሉ ሃይማኖትን ከመለኮታዊነት ይልቅ ይበልጡን ሰውኛ እንደሚያደርገው መገመት አይከብድም፡፡ ይህን ስል የሰው ልጅ ሃይማኖት ሊኖረው እንደሚገባ የማምን መሆኔን መግለጥ እወዳለሁ፡፡ የሃይማኖትን መብዛት ግን ከሰዎች ፍላጎት በዘለለ እግዚአብሔራዊ ነው የሚል የሞኝነት እምነት የለኝም፡፡ በመሆኑም በሃይማኖታዊ የአመስጥሮ ሥልት (mystification)  ሰዎች በሰዎች ሲታለሉና ጤናማ አእምሯቸውን በማስመሰያ ወጥመድ ሲሰለቡ ስመለከት አዝናለሁ ብቻ ሣይሆን ክፉኛ እበሳጫለሁ፡፡
እውነት አትመነዘርም፡፡ እውነት አትሸቀጥም፡፡ እውነት ምን ጊዜም መልኳን አትለውጥም፡፡ እውነት በሃይማኖት መለያየት ሰበብ አትከፋፈልም፤ ተከፋፍላም አራት ሺህና አሥር ሺህ እውነቶችን አትሆንም፡፡ ከዚህ አንጻር ታዲያ ይህ ሁሉ የሃይማኖት ልዩነት መንስኤ የሥጋ ፍላጎት እንጂ የነፍስ ፈቃድና የፈጣሪ ፍላጎት እንዳልሆነ መረዳት ይገባል፡፡
ሰሞኑን በተለይ በውጪ ሀገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አድባራት መካከል የተወሰኑት በግልም ይሁን በቡድን የጻፏቸውን የቅዋሜና የግዝት/የውግዘት ጦማሮች (ex-communication) የሚያነብብ የእምነቱ ተከታይ በሃይማኖቱ ማፈሪያ መሪዎችና አግለጋዮች ምን ሊሰማው እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ በበኩሌ በእጅጉ ማፈርና መሳቀቅም ይገባኝ ነበር፤ ነገር ግን የዘመኑን ማብቃት ከተረዳሁ ጥቂት የማይባሉ ጊዜያትን በማስቆጠሬ ከፈገግታ ባለፈ የተሰማኝ ብዙም ነገር የለም፡፡ አጠገቤም ብዙና ብዙ ስለምታዘብና ይህን መሰሉ ዘግኛኝ ነገርም እንደሚከሰት ቀድሞውን የተተነበየ በመሆኑ አላስደነቀኝም፡፡ ይልቁናም እነዚህ ራቁታቸውን የወጡ የቀድሞ ድብቅ ነውሮች የሃይማኖት ተቋማት የሰይጣን መናኸሪያ መሆናቸውን ላላወቁ የዋሃን ጥሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሆኑና በሰዎች ማመን እንደማይገባ የሚያስረዱ ክስተቶችን በግልጽ በማየታችን የፈጣሪን ዕድሜ ለምኛለሁ፡፡ የማውቀውን ብቻ መናገር ስላለብኝ ቤተ ክርስቲያን – የየትኛውም ዘርፍ ትሁን (ካቶሊክም ኦርቶዶክስም ሉተርያንም) – በታላቁ የጨለማው ንጉሥ በዲያብሎስ መንግሥት ሥር ከወደቀች ዘመናትን እንዳስቆጠረች ካነበብኩትና ከማየውም ተነስቼ መመስከር እፈልጋለሁ፡፡ ጣፋጭ ፍሬ ዛፍ ላይ እያለ ይታወቃል፡፡ ሰዎችንም በሥራቸው እናውቃቸዋለን፡፡ የዓለምን ፖለቲካና ኢኮኖሚ ሙሉ ለሙሉና ለብቻ በመቆጣጠር አንድ የተማከለ ሲዖላዊ ምድራዊ መንግሥት ለመመሥረት በልጆቹ ኢሊሙናቲዎች አማካይነት ጫፍ የደረሰው የአውሬው መንግሥት ከፈጣሪ በቀር አለኝታና መመኪያ የሌላት ቤተ ክርስቲያንን ደፍጥጦ አገልጋዮቿን በብልጭልጩ አሳሳች ዓለም ውስጥ ለመክተት የሥርዓቱ የበላይ አለቃ ሰይጣን የሚያቅተው አልሆነምና በጉልህ እንደምናየው ከቫቲካን እስከ አሌክሳንደርያ ከዚያም አልፎ እስከ ኢትዮጵያና ከዚያም ማዶ በክርስትናው ብቻ ሣይሆን በሁሉም ሃይማኖቶች እጁን ሰድዶ ሁሉንም በቁጥጥሩ ሥር አውሏል፤ የተደገሰልን ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ በመሆኑና የሚጠበቅም ስለሆነ አይገርምም፡፡ የሚገርመው በዓለም ላይ የፈጠጠውን ይህን እውነት ለመገንዘብ ብዙ ሰዎች አለመቻላቸውና በዚህ ወጥመድ ውስጥ ዘው ብለው የመግባታቸው ምሥጢር ነው፡፡ ይህን ገሃድ እውነት ለመረዳት የሦስትና አራት ገጽ ጦማር ስለማይበቃ ኢንተርኔትን በመጎልጎል መዳሰስ ነው፡፡
ይሁንና በየትኛውም የክርስትና እምነት ቅርንጫፍ ውስጥ – ከንፍሮ ጥሬ እንደሚወጣ ሁሉ – በትክክለኛው የፈጣሪ መንፈስና ህግጋት የሚመሩ እጅግ ጥቂት የዓለም ዜጎች መኖራቸው አይቀርምና ለእነሱ ያለኝን አክብሮትና ፍቅር የምገልጸው ሃይማኖታዊ ተጋድሏቸውና ጸሎት ምህላቸው ለኛ ለብዙኃኑ ምሕረትን እንዲያመጣልን ሁሉን ማድረግ ለሚችለው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመጸለይ ነው፡፡ አብዛኛው የሃይማኖት መሪ ግን ራሱ በእግዚአብሔር የሚያምን መሆኑን እስክንጠራጠር ድረስ ጭልጥ ብሎ ጠፍቷል፡፡ ጽላት የሚሰርቀውን፣ ንዋየ ቅድሳት እየዘረፈ የሚሸጠውን፣ ከየሴተኛ አዳሪውና ከየአባውራ ሚስት እየወሰለተ ቅዳሤ የሚገባውንና ድጓና መዋሲት የሚያንበለብለውን … ስንመለከት በሱ ድፍረትና በፈጣሪ ትግስት መደነቃችን አይቀርም – ያ የፈጣሪ ትግስትም የልብ ልብ እየሰጣቸው በመንበሩ የሌለ ያህል በመቁጠር ይሄውና የጥንታውያኑ ፀረ- ክርስቶስ “ጻፎችና ፈሪሣውያን፣ ቀራጮችና ሰዱቃውያን” በዘመናችን የሃይማኖት እረኞች ሰውነት ውስጥ በሥውር ተመልሰው በመግባት በክርስቶስ መምጫ ዋዜማ ላይም የአባቱን ቤት እንደዱሮው ሲሸቃቀጡበትና ሲሸራሞጡበት ይታያሉ፡፡ በዘመናችን ሰዎች ለራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ሲሉ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ቅዱሣት መጻሕፍትን በርዘውና ከልሰው በተቃርኖዎችም ሞልተው ምዕመናንን በጭፍን ሲያሞኙ ስናይ በሰው ልጅ የዋህነት መገረማችን ከገደቡ ያልፍብናል፡፡
ወደ 97 ዓ.ም ግርግር ለአፍታ ልውሰዳችሁ፡፡ በግርግሩ ሰሞን በግርግሩ አካባቢ አንድ የንግሥ በዓል ነበር – ከታማኝ ሰዎች እንደሰማሁት፡፡ ቀሳውስት በዝማሜና በወረብ ታቦት አጅበው ወደ መንበሩ ሊያስገቡ ሲሉ የወያኔ ፌዴራል በአካባቢው የጦፈ ተኩስ ይከፍታል፡፡ ያኔ ሌላው ቄስና ምዕመን ይቅርና ታቦት ተሸካሚው ራሱ ጽላቱን ሜዳ ላይ ጥሎት እግር አውጪኙን ይሸሻል – ይህ ዓይነቱ አሳዛኝ ትርዒት ለወያኔና ለአባቱ ለሰይጣን ትልቅ ድል ነው – በደስታ የሚሰክሩበት ታላቅ ድል፡፡ በኋላ ላይ ነው ጽላቱ ከወደቀበት ተፈልጎና በጠቋሚ ምሪት ተገኝቶ ወደመንበሩ የገባው፡፡ ምን ማለት ነው? ብዙ መናገር አልፈልግም፡፡ አንድ የቀድሞ ወታደር ሲሰለጥን ወታደራዊ ሠልፍ ላይ በተጠንቀቅ ባለበት ጊዜ እባብ እንኳን መጥቶ ቢጠመጠምበት አንዲትም ኢንች እንዳይንቀሳቀስ ትምህርት ይሰጠዋል – እንኳንስ አይግባኙን ሊፈረጥጥ፡፡ በሃይማኖትማ እንዴቱን ያህል ይበረታ! ታዲያ ከምዕመናንና ከካህናት ይበልጥ በእግዚአብሔር የሚያምኑት የትኞቹ ናቸው? ትንሽ ነገር ነው የተናገርኩት፡፡ ሌሎች ሃይማኖታዊ ህፀፆችን ልዘርግፋቸው ብል ወኔው ቢኖረኝም አንባቢዎችን ተስፋ ላለማስቆረጥና በጭፍን ልማድ ላይ ድንገተኛ “መብረቃዊ ማጥቃት” ላለመሰንዘር ለአሁኑ ሆን ብዬ እተወዋለሁ፡፡ ግን ግን የሃይማኖቱ መምህራን ኦሪትን ከሃዲስ፣ የሰይጣንን ከእግዚአብሔር፣ እውነቱን ከሀሰት፣ ልማዳዊውን ከእውነተኛው የክርስቶስ አስተምህሮ በመለየት ሕዝቡን በትክክለኛው መንገድ ቢመሩት የመጀመሪያ ተጠቃሚዎቹ እነሱ መሆናቸውን ብጠቁም የሚያስነውር አይመስለኝም፡፡ ለገንዘብ ሲሉ የሚጨማምሩትን እንቶ ፈንቶና ኢ-እግዚኣብሔራዊ የአምልኮ ልማድ ሁሉ እርግፍ አድርገው ሊተው ይገባል – እንዲህ ማድረግ ያለባቸው ትዝብት ውስጥ ስለሚጥላቸው ብቻ ሣይሆን ስለማይጠቅማቸውና ፈጣሪን ስለማያስደስት ጭምርም ነው፡፡ በስሜትና በግለሰባዊ ቅዠት በእውር ድንብር እየተመራን – እየተነዳን ቢባል ይበልጥ ያስኬዳል -  እዚህ ደርሰናል፡፡ በዚህ ጉዟችንም ፈጣሪን ከእኛና ከሀገራችን አራቅነው እንጂ አላቀረብነውም፡፡ ከንቱ መኮፈስና ገመናን በአልባሳት እየሸፈኑ ሃይማኖተኛ ለመምሰል መሞከር የምንገኝበት ዘመን የሚያሳየኝ አጠቃላይ ውጤት ምሥክር ነውና የትም አላደረሰንም፤ የትምም አያደርሰንም፡፡ ያወቅነው የሚመስለን ነገር ግን ብዙ የማናውቀው ነገር መኖሩን እስካሁን አልተረዳንም፡፡ ስለዚህ መንገዳችን እሾሃማ ነው ማለት ነው፡፡ አያችሁ – “ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል፡፡”
በዓለም ላይ እግራችን እስኪነቃ ብንሄድ ብዙው የሃይማኖት አገልጋይ ወደዓለም ገብቶ ጠፍቷል፤ ጠቅልሎ ወደዓለም ቢገባ ምንም አልነበረም – ዕዳው የርሱ ብቻ በሆነ፡፡ ነገር ግን በምሽትና በሌሊት በቤተ ክርስቲያን እንደቁራ በከንቱ እየጮኸ፣ ቀን ቀን ባሳቻና በግልጥ በቤተ ሣጥናኤል ያሻውን እያደረገ የተከለከለውን ለሁለት ጌቶች ያለመገዛት ወይም ያለማደር መለኮታዊ ቃል በመጣስ ላይ የሚገኝ በመሆኑ የዚህን መሰሉ የሁለት ዓለም ዜጋ ጸሎት ለብራቅ የሚዳርግ ካልሆነ በስተቀር ለጽድቅ የሚያበቃ ባለመሆኑ እያስመሰለ መኖሩ አደገኛ ነው፡፡ እንደሰዎች የማጭበርበርና የማስመሰል ሃይማኖታዊ ድራማ ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ሰዓት ምናልባት ሁላችንም በጠፋን ነበር፡፡
ወደሀገራችን ስንገባ በባህልና በይሉኝታ ገመዶች ተጠፍንገን ገብስ ገብሱን ብቻ እናውራ ካላልን በስተቀር ጉዳችን ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ ቤተ መቅደስን ከጥንት ጀምሮ ተቆጣጥሮ የሚገኘው ማን እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ደግነቱ እነሱ ራሳቸው “የምናደርገውን ሣይሆን የምንለውን አድምጡ” ማለታቸው በጄ እንጂ ብዙዎቹ የሚያደርጉትን ከተመለከትን አንድም ሰው ወደቤተ ክርስቲያን ባልሄደ ነበር፡፡ እኛም “የነሱን ኃጢኣት ምን አስወራን? ፈጣሪ ራሱ እንደሥራቸው ስለሚከፍላቸው አገልግሎታቸውን እንቀበል እንጂ ግድፈታቸውን ማየት የለብንም” እያልን የልብ ልብ ስለምንሰጣቸው የሰይጣን ፈረስ የሚጋልቡ ካህናትና ጳጳሣት ኪሳችንን ብቻ ሣይሆን የተቀደሰውን አልጋችንንም ሣይቀር ተጋርተው የልጆቻችንን መልክ እስኪለዋዉጡና በገዛ ቤታችን ውስጥ የማንነት ኪሣራ እስኪያስከትሉ ድረስ ነፃ እንተዋቸዋለን፡፡ በኋላ ግን በጸጸትና በንዴት የምንሠራውን አጥተን ሃይማኖት መለወጥ መፍትሔ ይሆን ይመስል ማተባችንን በጥሰን ገደል የምንገባ ሞልተናል፡፡ ግን ግን መጥኖ መደቆስ ቀድሞ ነበር ወገኖች፡፡ ‹ጅቡ ከሄደ በኋላ ውሻው እንዳይጮህ፡፡›
ቀደም ባለ አንድ የቅርብ ታሪክ ልጀምር፡፡ ዘመኑ ነው እንዳትሉኝ ነው የዛሬውን ያላስቀደምኩት ነው፡፡ ታሪኩን በቅርብ አውቀዋለሁ፡፡ የቤተሰብ ጉዳይ ነው፡፡ እልም ያለ ገጠር ውስጥ፡፡ የዛሬ ሃምሣ ዓመት ገደማ የተፈጸመ፡፡ በነገራችን ላይ እንደዚህ ዓይነቶቹን ቅንጫቢ ታሪኮች እናውራቸው ብንል በመሠረቱ ዘርዝረን አንጨርሳቸውም፡፡ በየመንደሩ ከሁለትና ሦስት በላይ ይኖራሉ፡፡
የአጎቴ ነፍስ አባት ነበሩ፡፡ የወለዱ የከበዱና ከሰማይ ከምድር የከበዱ፡፡ አጎቴም በአጥቢያው የተከበረና ከአሥር ልጆች በላይ ያሉት ነበር፡፡ ቄሱም አጎቴም በሃምሣዎቹ እኩሌታ የዕድሜ ክልል ውስጥ ነበሩ፡፡ ቄሱ እንደማንኛውም ንስሃ አባት ወደ አጎቴ ቤት ለጠበልም ለዝክርም ለምንም ለምንም አዘውትረው ይመላለሱ ነበር – ወደአንተታው መግባቴ ነው እባካችሁን፡፡ በዚህ መሃል አጎቴ ይሞታል፡፡ ቀብሩ ተፈጽሞ ዐርባው እንኳን ሳይወጣ ቄሱ ሚስቱንና ልጆቹን ጥሎ አጎቴ ቤት ይገባል፡፡ ሰይጣናዊ የፍትወት ፍቅር ዐይን የለውምና ሀገር ምድር ጉድ እያለ እነዚያ የአጎቴ ሚስትና ቄሱ የፍቅር ቄጤማቸውን ያለ አንዳች ይሉኝታ ይቀጩ ጀመር፡፡ ከአጎቴ ልጆች አንድኛው ግን አንድ እርምጃ ወሰደና የሁሉንም ቤተሰብ “ያስደሰተ” አስቀያሚ ድርጊት ተፈጸመ፡፡ ከዚህ በላይ መሄድ አያስፈልግም፡፡
የዛሬውንማ አታንሱት፡፡ ስንቱ ተጠቅሶ ስንቱ ሊቀር? የትኛው ተነግሮ የቱስ ሊተው? “በኃጢኣት ሊመላለስ ያልፈቀደ ካህንና መነኩሴ በነፍሱ እንደፈረደ ይቆጠራል!” የሚል ማስጠንቀቂያ የተላለፈ ይመስል ከሞላ ጎደል ሁሉም ተያይዞ የጥፋትን መንገድ የሚከተል ሆኗል፡፡ በወንጌሉ “ከእናንተ አንድስ እንኳ ካለ ኃጢኣት የሚኖር የለም፤ ሁላችሁም በኃጢኣት ሥር አድራችኋል” ተብሎ እንደተጻፈ ምድረ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከእኔው ባልተናነሰ በቁሙ በክቷል፡፡ የሚገርመኝ የምዕመናኑ ዐይን መጨፈንና ድግምት እንደተዞረበት ፈዝዞ በዕውር ድንብር መከተሉ ነው፡፡ ለነገሩ አማራጭም ከማጣት ሊሆን ይችላል፤ አሊያም ከፍ ሲል እንደተናገርኩት ፍርዱን ለፈጣሪ በመተውም ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላም በኩል ለዘመናት በሥነ ልቦናው ላይ በተደፈደፈበት  የአፍዝ አደንግዝ  ስብከትም ሊሆን ይችላል፡፡ መንስኤው ምንም ይሁን ምን ምዕመናን ከእግዚአብሔር ይልቅ ጠፍተው የሚያጠፉ ካህናትን ማመናቸው እየጎዳቸው ነው፡፡
ባህታዊ ገብረ መስቀል የሚባለውን አጭበርባሪ ሌባ ብንመለከት ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል፡፡ (እዚህ ላይ የሕዝብ ጊዜ ገና ባለመምጣቱ ምክንያት በእውነተኛው ስሜ ይህን ጉዳይ መጻፍ እየፈለግሁ ባለመቻሌ ከፍተኛ ቅሬታ የተሰማኝ መሆኔን ሳልገልጥ ማለፍ አልፈልግም፡፡) በጊዜው ባህታዊ ተብዬውን እንደክርስቶስ ያህል ለማምለክ ከተሰለፉ ሰዎች አንዱ ነበርኩ፡፡ በርሱ ምክንያት የምጣላቸው ጓደኞች ነበሩኝ፡፡ “ይሄ አጭበርባሪና ሌባ ሰውዬ የሚለውን አምነህ እንዴት ትቀበላለህ? ፊደል ቆጥረህ የለም እንዴ?…” በማለት ከዚያን ጊዜ በፊት ሠራቸው የሚሉትን ገመናዎች በመጥቀስ ሲነግሩኝ ያኮረፍኳቸውና በጅልነቴ የሚያዝኑልኝም ነበሩ – ይቅር ይበሉኝ፡፡ በዚያኑ ወቅት ገደማ በምኒልክ ጋዜጣ አንዲት ሴት በዚህው ሌባ ባህታዊ ነኝ ባይ ሰውዬ የደረሰባትን ወሲባዊ ገጠመኝ ስታጋልጥ ዐይኔን መግለጥ ጀመርኩ፡፡ ቀጥሎም ተደጋጋሚ ማጋለጫዎች ወጡ፡፡ ቀጥሎም አንዲት ሕጻን ልጅ አግብቶ ሥውር ማጭበርበሩን ገሃድ ማውጣቱን ተረዳሁ – ከዚያን በኋላ “ነፍስ አወቅሁ”ና ከሰውዬው የበሸቀጠ የሰይጣን መንፈስ ተለየሁ፤ “ለሰይጣን ለሰይጣንማ የኔውስ ምን አለኝ?” በማለት – ይህን ዓይነቶቹ አታላዮች ቁጥር አይገልጻቸውም – በልጆች ቋንቋ በዬአካባቢው “ነፍ” ናቸው፡፡ ይሄ ሰውዬ ትልቁን ሰው አቶ ሽመልስ አዱኛን ሳይቀር ከጎኑ በማሰለፍ በድሆች ስም ላቋቋመው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የቦርድ ሊቀ መንበር እስከማድረግ የቻለ የተዋጣለት አሰለጥ ነው፡፡ በወቅቱ በሥሩ ያዘጋጃቸው ጋሻጃግሬዎቹ ሰውዬው ሲታሠር “መላእክት መብራት ሲያበሩላቸው ያድራሉ፤ ምግብም ከሰማየ ሰማያት በመና መልክ ይመጣላቸዋል፤ እንደተክልዬ ሰባት ክንፍ ሊያወጡ አራቱን አብቅለው ሦስቱ እያጎነቆሉ ነው …” የሚል ወሬ እያሠራጩ የአዲስ አበባን ሕዝብ አማለሉት – በቀላሉ የማይናጋ ትክለ ሰውነትም ገነቡለት፡፡ ጠንቋዮችም እንዲሁ ናቸው፡፡ ጠንቋይና ቄስና ደብተራ የሚመሳሰሉባቸው ብዙ ባሕርያት አሏቸው፡፡ ዝናቸውን በወሬና አሉቧልታ ያዛምቱና ሕዝቡን አጥንቱ ድረስ እየዘለቁ ያለ የሌለ አንጡራ ሀብቱን  ይግጡታል፡፡ እዚህ አካባቢ አንድ ወሬ አውራ፤ በሴከንድ ውስጥ ከሬዲዮና ቴሌቪዥን በበለጠ ፍጥነት አገር ምድሩን ያዳርስልሃል፡፡ ደግሞም በኛ ሀገር፡፡ በዚህ መልክ ስማቸው የመላእክትን ያህል በየቦታው ይናኛል፡፡ ባህታዊ ተብዬው የሰይጣን ፈረስ በመሳጭ አንደበቱ አዳሜን አነሆለለና በገንዘብ የተመቻቸ ኑሮውን ካረጋገጠ በኋላ “ያጠመቃት” ፈረንጅ – ወለተ መስቀል ‹ጆንሃንሰን› – ሰጠችው በተባለው ላንድክሩዘር እየተምነሸነሸ ሚስቱን አግብቶ ዓለሙን ይቀጭ ጀመር – መቅጨቱ አያስቀናም – በእግዚአብሔር ስም ማጭበርበሩ እንጂ የሚያበሳጭ፡፡ አሁንም ቀጨኔ መድኃኔ ዓለም ግርጌ ትልቅ ግቢ ገዝቶ አለላችሁ፡፡ እሱን መሰል አጭበርባሪ “ባህታውያንና መነኮሳት” ሀገር ምድሩን አጥለቅልቀውታል፡፡በሌባና አጭበርባሪ ቄስና ባህታዊ ሕይወቱ የተመሰቃቀለ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ውጪ ሊገኝ እንደማይችል ባለኝ ሁሉ እወራረዳለሁ፡፡ ግን ምን አለኝና? ወግ ነው አሉ ሲዳሩ ማልቀስ?
ሰሞኑን ደግሞ እንዲህ ሆነላችሁ፡፡ ከሰሜን ኢትዮጵያ ወደአዲስ አበባ የመግቢያ በር አካባቢ አንድ ባዶ እግሩን የሚሄድ መነኩሴ አንድ ቤተ ክርስቲን ያቋቁማል – በተለይ በአሁኑ ስድ የወያኔ ግዛት ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ማቋቋም ማለት አንዲት ትንሽ ፒ.ኤል.ሲ የማቋቋምን ያህል እንኳን አይከብድም – ሰው እንደሆነ ክፉኛ ስለተጨነቀ ይቅርና የሰው ባህታዊ የዝንጀሮ ግመሮ ባህታዊና የጦጣ መነኩሴ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ፈዋሽ ጠበል አፈለቁ ተብሎ ቢወራ ወደዚያ ሥፍራ የሚነጉደው ሕዝብ መሬት አይበቃውም – እርሱ ይርዳን እንጂ ተጨንቀናል፤ ተጠበናል፡፡ ይህንን ጭንቀት ጥበታችንን ታዲያ አሰለጦች ሃይማኖትንና የዛር ጥንቆላን ተገን አድርገው እየተጠቀሙ ሙልጭ እያወጡን ናቸው፤ አባባ ታምራትንና ማርያም ነኝ ብላ አዳሜን “የቀፈለችው”ን አስታውሱ፡፡ ይሄ “የበቃ መነኩሴ” ታዲያ የሚለብሰው ወይባ፣ በእጁ የሚይዘው ባለመስቀል የብረት ከዘራ፣ የሚታጠቀው አስኬማ፣ የሚጫማው እሾህና ጋሬጣ ነበር፡፡ ስብከቱ ያፈዝዛል – የክርስቶስን የተራራውን ስብከት ያስታውሳል የሚሉትም ነበሩ፡፡ ምዕመናን ምግብ ሲያመጡለት ይቆጣል፡፡ “‹መንኮሰ› ማለት ሞተ ማለት ነው፡፡ ለመነኮሰ ሰው ደግሞ ከባቄላ አሹቅና ከሽንብራ ቆሎ ውጪ ሥጋን የሚያወፍር ምግብና ሙቀት የሚሰጥ ልብስ አያስፈልገውም …” እያለ ሲሰብክ መላእክትን ከሰማይ ይስብና የስብከቱ ተካፋይ ያደርግ ነበር፡፡ … ምን አለፋችሁ – አሁን አንዷን ምዕመን አግብቶ የሚይዘው መኪናና ሞባይል እንዲሁም የሚለብሰው ሱፍ እኔና አንተ በሎብሣንግ ራምፓ ሃይማኖታዊ ቲዮሪ መሠረት ለዘጠኝ ጊዜያት ደጋግመን ብንወለድ አናገኘውም፡፡ ሃይማኖት ማለት እንግዲህ እንዲህች ናት ወንድሜ! ይችንስ እኔም ባገኘኋት፡፡ የመንገዱ ግማት ኅሊናዊና አካላዊ አፍንጫን ቆርጦ ስለሚጥል እንጂ ይህን ዓይነቱን ወደሀብቱ ጉዞ አቋራጭ ማን ይጠላል? ወደድህም ጠላህም የምልህ እውነትና እውነት ብቻ ነው፡፡ ብታምን የራስህ ጉዳይ፤ ባታምንም እንዲሁ፡፡ ፖለቲካና ሃይማኖት ለሥጋዊ ፍላጎቶች ስኬት እንደሚውል ካልገባህ እንደተሞኘህ ትኖራለህ ማለት ነውና የምልህን ነገር አዟዙርህ ለመቃኘት ሞክር፡፡ በሰዎች የማምታታት ተፈጥሮና የወንጀለኝነት ባሕርይ ተደናግጠህና አኩርፈህ ግን ከፈጣሪህ ጋር እንዳትጣላ አደራህን፡፡ የእርሱና የሰው መንገድ ለዬቅል ናቸውና፡፡ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ጥፋትና ልማት የሚለካ አይደለም፡፡ ለነገሩ በፈጣሪ ባታምንም መብትህ ነው፡፡ ምን አገባኝ? የሚያዋጣህን እምታውቅ አንተ፡፡
ማርክስ ይሁን ኤንግልስ “ሃይማኖት የመበዝበዣ መሣሪያ ነው” ብሎ ነበር፡፡ መቶ በመቶ እውነት ነው፡፡ በዚህ ዘመን የሚገኙ ሃይማኖቶችን ስንመለከት የብዙዎቹ መሪዎችና አገልጋዮች ይህን ነባራዊ ኹነት የሚያረጋግጡልን ብዙ ነውሮችን ሲሠሩ እንታዘባለን፡፡ እኔ በመሠረቱ ሃይማኖትን አልቃወምም ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ አንዳች የሚፈራው ነገር መኖር እንዳለበት የማምንና ሃይማኖት ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ የሃይማኖቶቹ መሪዎች የሚከተሉትን የአሠራር መንገድ ግን አጥብቄ እቃወማለሁ፡፡ ሃይማኖተኛ ለመሆንም በግድ በተጣመመ መንገድ በይሉኝታና በፍርሀት መጓዝ እንደሌለብኝ እረዳለሁ፡፡ ባለፈው የሰማነውን በ42 ሚሊዮን ዶላር የግል ቤት የሠራውን የጀርመኑን የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ታሪክ የምታስታውሱት ይመስለኛል፡፡ እርሱስ በሀብት ነው – ሌላ ሌላው በሆድ ይፍጀው ይቀመጥና፡፡ አለላችሁ እንጂ ሌላ አስቀያሚ ታሪክ – በነሱም በኛም፡፡ ይታያችሁ – ሆሞሴክሽዋል ካህንና ሌዝቢያን መነኩሴ ፈጣሪን በቃለ ዐዋዲው የክህነት ማዕረግና በፆታዊ የድንግልና ክብር ለማገልገል የገቡትን ቃል አፍርሰው ከህገ እግዚአብሔርና ከህገ ማኅበረሰብ ሲወጡ ፈጣሪን ምን ሊሰማው ይችላል? ሰውን በመፍጠሩስ ቢጸጸት ይፈረድበታልን? ወደዚች የጎስቋሎች ምድር ምን ዓይነት መቅሰፍት ሊልክስ እንደሚችል አስባችሁት ታውቃላችሁ? የጽዳት ዘመቻ የለም የምትል ከሆነ ስህተት ነው፡፡ የዘመነ ኖኅ የውኃ ጥፋትንና የዘመነ ሎጥ የሶዶምና ገሞራ የእሳት ድኝን ማሰብ ይገባል፡፡ ሁልጊዜ ፋሲካ የለም ወዳጄ፡፡ ጠብቅ … ግን ቶሎ እንዲሰበስብህ ጸልይ – ካንተ ይለፍ፡፡
የኦርቶዶክስ ቄስ አንዲት ሴት ማግባት ይችላል፡፡ አንዲት ብቻ! መፍታትም ሆነ ሌላ ማግባት አይችልም፡፡ እንዲያ ቢያደርግ ክህነቱ ይፈርሳል፡፡ ብትሞትበት ወይም ብትፏንንበትና ሌላ ወድዳ ብትከዳው በራሱ ንጽሕና ጸንቶ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ሊመነኩስና ክህነቱን ሊያስጠብቅ ህግ ይፈቅድለታል፡፡ የካቶሊክ ቄስ ምንም ማግባት አይችልም – ሶሬላዋም እንዲሁ፡፡ ምንም! ግን ግን ያገባውም ያላገባውም ሁሉም ሌባና ቀላዋጭ ነው – እነዚህን የሰይጣን ሎሌዎች በቅርበት የማውቅበት ዕድል ስለነበረኝ በምለው ነገር ጥርጣሬ አይግባህ፡፡ አንዲት ማግባት የሚፈቀድለት ከአንዲቷ በላይ ማየትን ይፈልጋል፤ ምንም ማግባት የማይፈቀድለት ደግሞ ሁሏንም ማየት ይፈልጋል፡፡ ሌላዋም ሆነች ሁሏም በበኩሏ የሚያገባውንም ሆነ የማያገባውን ማየት ትፈልጋለች – ቀድሞውን ለፈተና ተፈጥራለችና፡፡ ጀብራራው ካህን ከርሷው ወጣ – በፈተናና ለፈተናም ባልተፈቀደለት አቅጣጫ ተጉዞ ወደርሷው ተመልሶ ገባ፡፡ እርሷም መነሻዋን አትክድምና ለምስነቱ ታበረታታዋለች፤ ታጃግነዋለች(አስቸጋሪ ቃል ተጠቀምኩ መሰለኝ – ለምስነቱ ማለት ለጥፋቱ ማለት ነው – ሁሉም ፊደላት እኩል ላልተው ይነበቡ)፡፡ ቀድሞ በፍራፍሬ፣ በኋላም ሱባኤን በማስተጓጎል አሁን ደግሞ ቃል ኪዳንን በማሳጠፍ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ለውድቀቱ ሥምረት ከጎኑ እንደወጣች በጎኑ አለችለት፡፡ የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ሉካንዳ ደጅ ሲልከሰከስ እንደሚገኝ የት ይደርሳል የተባለ ካህን በሴት ተፈትኖ በሴት ሲወድቅና መስቀሉን አልባሌ ቦታ ሲጥለው፣ በቀኖናው መሠረት ባልተፈቀደለት የሴት ጭን ውስጥ ከትቶ ሲያርመጠምጠው የምናስተውለው የታቀፈውን እሳት መቆጣጠር ስላቃተው ነው፡፡ የሥጋን ፍላጎት መቆጣጠር እጅግ ከባድ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የምንወድቀው በሥጋ ፈተና ነው፡፡ በካህን ሲሆን ደግሞ ኃላፊነቱ ስለሚከብድ ለብዙዎች መሰነካከል ምክንያት ይሆናልና ጠንቁ አነስ ሲል የሃይማኖት ተቋምን ከፍ ሲልም ማኅበረሰብን እስከማነቃነቅ ይደርሳል፡፡ “ብፁዓን አባቶቻችን” አቡነ ጳውሎስና አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ቫቲካናዊያኑ “ብፁዓን አባቶቻቸው” ፖፕ ሮደሪጎ 15ኛ እና ቤኔዲክት 16ኛ  በልበ ድፍንነት ቀልባቸው ካረፈባቸው እንስቶች ጋር ይሸራሞጡ የነበሩት የክርስቶስን ጴጥሮሳዊ መንበር ለማዋረድ በላያቸው ላይ የሰረፀው የሰይጣን ኃይል አስገድዷቸው ብቻ ሣይሆን የሥጋ ፍላጎታቸውን ለመግታት እነሱ ራሳቸውም አቅም በማጣታቸው ጭምር ነው – ለሰይጣን ፊት አሳይተውት ቀርቶ እንዲሁም የሚቻል ባላንጣ አይደለም፡፡ እነሱ እንዲህ ከሆኑ እንግዲህ በዕውቀትም በትምህርትም ከነሱ በታች እንደሆነ የሚገመተው ተከታይ ጭፍራማ እንዴቱን አይሳሳት? ብሂሉ “ እህል ቢያንቅ በውሃ ይዋጣል፤ ውሃ ቢያንቅ በምን ይዋጣል?” ይላል፡፡ ይለጥቃልም “ሰውነት ቢያብጥ በምላጭ ይበጣል፤ ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጣል?” አዎ፣ ከላይ የሚጀምርን ህመም ለማከም ከባድ ነው፡፡ ከታች የሚነሣ ህመም መፍትሔው ብዙም አይቸግርም፡፡ በማስተማርም ሊመለስ ይችላል፡፡ አለበለዚያም ካልተመለሰ ማባረርም ይቻላል፡፡ የጫፍ በሽታ ግን ሁሉንም ያጠፋል፤ እንደሰደድ እሳት በቀላሉና በፍጥነት ሀገር ምድሩን የሚያዳርስ ወረርሽኝ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-አማራ፣ፀረ-ታሪክ፣ ፀረ-ሃይማኖት፣ ፀረ-መልካም ሀገራዊ ዕሤቶች በመሆኑ የርሱ ተከታዮችና ደቀ መዛሙርት ሁሉ እንደርሱው መርዘኛ ሆኑና ሀገር ከነታሪኳ ገደል ገባች – ቢያንስ እስከትንሣኤዋ፡፡ በዚያም ምክንያት ዓሣማና ጅብ በመላዋ ሀገር ናኝቶ ያገኘውን ሁሉ ሳይመርጥ መቆርጠም ያዘ፡፡ ይህ የመለስ ባሕርይ በቤተ መንግሥት ብቻ ሣይወሰን በቤተ ሃይማኖቱም አለተቀናቃኝ ሰተት ብሎ ገባና በአንጻራዊ አነጋገር የብርቅ ያህል ይታይ የነበረው ብልግና አሁን አሁን የማያስነውር ፋሽን ሊሆን በቃ፡፡ ሙት ወቃሽ አያድርገኝና በፓትርያርክ ቢሮ ውስጥ ምን ይደረግ እንደነበር አውቃለሁ፤ የውቢት ጓድ ፍስሐ ገዳና የእጅጋየሁ አባ ጳውሎስ ቢሮ አንድ ከሆኑ የእግዚአብሔር ቢሮ የትኛው ሊሆን ነው??  የእጅ ሰላምታ ያህል የረከሰውን ፍትወታዊ ግንኙነት እንተወውና ዛሬ ሃይማኖትን በሽፋን በመጠቀም የፈለገውን የዘረኝነት ቅርሻት የማያቀረሽ ወያኔያዊ ካህን የለም፤ የዘረኝነትን ሰይጣናዊ የመከፋፈያ ሥልት በመጠቀም ጥቅም የሚገኝባትን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታ ያልተቆጣጠረ ወያኔያዊ ማይም ቄስና ጳጳስ የለም፡፡ ከዚህ በላይ ሃይማኖትን ለብዝበዛና ለጭቆና መጠቀም ካለ ኢትዮጵያን ከላይ አስከታች የሚያውቅ ይፍረደኝ፡፡ እነታደሰ ሲሳይ በዘር ሐረጋቸው የሆኑትን ይሁኑ ተክለ ሰውነታቸው የታነፀው ግን በወያኔያዊ አስተሳሰብና በሰይጣናዊ ሁለንተናዊ አገዛዝ ነው፡፡ እናም ቤተ ክርስቲያንን የተቆጣጠረው ሊቀ ሣጥናኤል ነው፡፡ ሰይጣን በጦርነት ያላገኘውን ዕድል በወያኔ አገኘና በቀላሉ ተቆጣጠራት፡፡ ይህ እውነት ሊገባው የማይፈልግ ወገኔን “አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም” የሚለውን ብሂል አስታውሼው ልለፍ፡፡ ኦሮሞ “ፈርዳን ኢንጌሳ መሌ ኢወራኑ” ይላል፡፡ እንደ ወንድሙ “ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም ለማለት፡፡”
ሁሉን ቢያወሩት አያልቅም – ሆድም ባዶ መቅረቱ የሚያሳዝነን አንጠፋም፡፡ እንደመፍትሔ ልጠቁም የምፈልገው መዳን በቄስ እንዳልሆነ በግልጽ በመናገር ነው፡፡ ቄሶች እኮ የመንግሥተ ሰማይ መግቢያ ካርድ እስከመሸጥ የሚደርስ ድፍረት ያላቸው ደንቁረው የሚያደነቁሩ ናቸው፡፡ በመካከለኛው ዘመን የሮማ ካቶሊኮች Indulgnce Card – ሥርየትን የሚያሰጥ ካርድ – ይሸጡ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ የኞቹ ቂላቂል ቀሳውስትም እንዳቅሚቲ ብዙ የሚሉት አላቸው፡፡ ትናንት አነበብኩት ባልኩት የውግዘት ደብዳቤ ላይ እንኳን “ካህናት ዐውደ-ምሕረቱ ላይ አሳዛኝና አሳፋሪ ስብከታቸውን ቀጠሉ። ለአብነት አንድ ላቅርብ፦ ‹እኛ ካህናት የምንለውን የማይቀበል በመንግሥተ-ሰማያት ቦታ የለውም።›” የሚል የቃቃ ጨዋታ ዓይነት ነገር ታዝቤያለሁ፡፡ የዚህን ቄስ ቃል ተቀብሎ ለመታዘዝ የሚሞክር ምዕመን ችግሩ የቄሱ ሳይሆን የምዕመኑ ነው፡፡ ለሰው ልጅ አለማወቅን የመሰለ መጥፎ ጠላት የለውም፡፡ እርግጥ ነው ማወቅም ካለማወቅ ባልተናነሰ ትልቁ ጠላቱ መሆኑ ሊካድ አይገባውም – የሕይወት ዕንቆቅልሽ እንደዚህ ነው እንግዲህ – ሕይወትን ጣዕም የሚሰጠው የዚህ ዕንቆቅልሽ የዞረ ድምር ይሆን? ይሆን ይሆናል፡፡ ከመጠምጠም መማር መቅደሙን ያልተረዱት እነዚህ ደናቁርት ካህናት ከነሱ ባልተናነሰ በማይምነት የጨለማ ግርዶሽ ውስጥ የሚኖረውን ገበሬና ባላገር ከፈጣሪ ህግጋት ውጪ ካለሥራ ቁጭ ብሎ ወደላይ ወደሰማይና ወደመንግሥት ብቻ እያንጋጠጠ እንዲኖር ፈርደውበት ከዓለም ሕዝብ በታች በችግርና በችጋር እየማቀቀ እንዲኖር አስገድደውታል – ለምሳሌ የበዓላትን ቁጥር ተመልከቱ፡፡ የወሩ ሠላሣው ቀናት አልበቃ ብለው ብዙ ተደራቢ በዓላት መኖራቸውን ታውቁ የለም? ብዙ፣ በጣም ብዙ፣ እጅግ እጅግ በጣም ብዙ የሞኝነት ሥራ በአምልኮተ እግዚአብሔር ስም ከበፊት ጀምሮ እየተሠራ ነው፡፡
በየጊዜው የሚመጡ መንግሥታትም እነዚህ ራስፑቲኖች የፈጠሩላቸው ሃይማኖተ-ማኅበረሰባዊ መደላድል ምቹ ሆኖ ስለሚያገኙት ሕዝቡን በፈለጉት አቅጣጫ እንደከብት ለመንዳት ይጠቀሙበታል፡፡ ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ እንዲሉ ነውና ከሕዝቡ መካከል የሚቃወማቸው ወገን ሲነሳም እየነጠሉ በመምታት ሀገርን ካለተቀናቃኝ በፈለጉት የአገዛዝ ሥልት እያርበደበዱና ሕዝብን በፍርሀት እያራዱ ይገዛሉ፡፡ በዚህ ሂደት የሃይማኖትን ሚና አለመርሳት ይገባል፡፡ ስለዚህ በነዚህ ፀረ-ሃይማኖት የሃይማኖት ሰዎች እምነት መጣል ለከፋ ጉዳት እንደሚዳርግ መረዳት አግባብ ይመስለኛል፡፡ በበኩሌ ከፈጣሪየ ጋር በግሌ ከማደርገው የጸሎት ግንኙነት ውጪ እንደዱሮው ልቤን ለሰው አልሰጥም፡፡ ሰው ለራሱ ሳያውቅ የኔን ሸክም ይሸከምልኛል፣ በርሱም ሰበብ እኔ እጸድቃለሁ ብዬ ለማመን እየተቸገርኩ በመምጣቴ ግንኙነቴ ከርሱ ከራሱ ጋር እንዲሆን ወስኛለሁ፡፡ በዚያም ምክንያት ብዙ ንዴቴን ቀንሻለሁ፡፡ መቀነስ የሚቻልን ንዴት ለመቀነስ መሞከር ደግሞ ንዴትን ይቆጥባል፡፡ ከሃይማኖት ተቋሜ ጋር ያለኝ ግንኙነት ገደብ ያለውና በድርበቡ ነው፡፡ የጦዘ ፍቅር ለጠጠት እንደሚዳርግ ከተሞክሮ በማረጋገጤ በ“ያዋከቡት ፍቅር” ከሚመጣ ዳፋ ራሴን ለመታደግ እጠነቀቃለሁ፡፡ ሃይማኖቴ የግሌ መሆኑንም አምናለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች የሚሰናከሉት በአርአያነት ከፊት ለፊታቸው የሚያስቀምጡት ሰው ከጠበቁት በታች ወርዶ ሲያገኙት ከሚሰማቸው መጥፎ ስሜት የተነሣ መሆኑን እገነዘባለሁ፡፡ ለምሳሌ አንድ ጎረቤቴ የነበረ የአንድ ደብር አለቃ ታላቅ ካህን የአንድ ምዕመን ሚስትን ይዞ ለሃይማኖታዊ ጉዞ(pilgrimage) ወደ ቁልቢ ይሄዳል፡፡ በዚያም ከዚያች ሴት ጋር አሼሼ ገዳሜ ሲል ቆይቶ ይመጣል፡፡ … አቶ ባል ከእንቅልፉ ሲነቃ ሃይማኖቱን ለወጠ – ፈታትም፤ ነፍሳቸውን ይማር፡፡ ይቺ ከከተማ የምታስወጣ ሃይማኖታዊ የጸሎት ጉዞ ያዘለችውን ጉድማ ብትሰሙ እናንተም ጉድ ብላችሁ አታባሩም፡፡ እንዴ -  እናውራ ካልን እኮ ብዙ ገመና – ብዙ ጉድ – ስንክሳርን እሚበልጥ ተራራ እሚያህል መጽሐፍ መጻፍ እንችላለን፡፡ (ማን ነበረች – “ብለነው ብለነው የተውነውን ነገር፤ ሚስቱ ዛሬ ሰምታ ልትታነቅ ነበር፡፡” ብላ ያቀነቀነችዋ አረሆ?) ከተናግሮ አናጋሪ ይሠውራችሁ፤ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ጊዜው ቀርቧል፤ እስከዚያው ግን ጠንቀቅ በሉ፡፡ ግን በርትታችሁ ጸልዩ፡፡ የሚዳነው በራስ ሥራና በግል እምነት እንጂ በደቦ አለመሆኑን ተገንዘቡ፡፡ … በቃኝ፡፡
ለገንቢ አስተያየት ምነዜም ዝግጁ ነኝ፡፡ yiheyisaemro@gmail.com

አባ መላ ሳይበላ ተበላ !



ሆዳም! ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም!

አዜብ ጌታቸው
አባ መላ ነኝ የሚለው የፓልቶኩ ብርሃኑ ዳምጤ ሰሞኑን የሰራው ስራ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው።  ከአንድ ድርጅት ውልቅ ብለው በዚያው ጀንበር ሌላው ድርጅት ጥልቅ የሚሉ፤ ያም ሳይጥማቸው ወይም ሳይመቻቸው ይቀርና ወዲያው ደሞ ወደ ሌላ 3ኛ 4ኛ….. ድርጅት ጥልቅ ውልቅ የሚሉ ጥቂት የማይባሉ ቅብዝብዞችን አውቃለሁ።እነኚህ አይነቶቹ የቻሉትን ያህል እንደ ፌንጣ ዘለው ዘለው በመጨረሻ እዩኝ እዩኝ ያለ ……እንዲሉ፦ ራስን ብቻ አባል በሚያደርገው ዲፕሬሽን ወደ ተሰኘው ድርጅት ይገቡና ፍጻሜያቸውም እዛው ይሆናል።
ሰሞኑን በአባ መላ የታየው ዝላይ ግን በፌንጣ ተምሳሌት ከተገለጹት ቅብዝብዞች የተለየ ነው፡፡ አባ መላ ውልቅ ካለበት የወያኔ ጓዳ ያሞሌ ተመኑን ቀንሶ ዳግም ጥልቅ ብሏል። ስለዚህ ለአባ መላ ተግባር በተምሳሌነት የምትጠቀሰው ፌንጣ ሳትሆን የተፋውን መልሶ የሚውጠው ጉማሬ ይመስለኛል ።
ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ወያኔን ጉማሬ ብለው የገለጹበትም ምክንያት ይህው ነበር፡፤ በነገራችን ላይ ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ቃለ ምልልስ ላይ “አባ መላ” የሚለውን ቅጽል ያወጡለት ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን መሆናቸውn (he was my best friend) አይነት ድምጸት) ሲናገር ሰምቸዋለሁ፡፤ የሞተ አይጠይቅ ሆነና ዝም ብለን ሰማነው።
ይሁን እንጂ በበኩሌ እንደሚታየኝ ብርሃኑ ዳምጤ የተሰ|ኘ የተሰፋ ሙዝ የሚሸጥ የምናለሽ ተራ ቁጭ ይበሉ (ምንጭ አብሮ አደጉ)ና የብርቅየውን ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬን ጓደኝነት እንኳን በዕውን በልቦለድ ድርሰትም ቢካተት ለአንባቢ የሚጥም አይመስለኝም፡፤  ልቦለድም ቢሆን እኮ የገሃዱ ዓለም እንጂ የከሃዲው አለም ነጸብራቅ  ነው አልተባለም።….
ወደ ቀምነገሩ ልመለስ፦ አዎ ብርሃኑ ዳምጤ እነ ሎሬት ጸጋዬን እየጠቃቀሰ ፕሮፊይሉን ከፍ ከፍ እያደረገ ቢቆይም ሰሞኑን በሰራው ታሪካዊ ክህደት ያበገነው አብሮ አደጉ ያለ ከፈን ምናለሽ ተራ ቀብሮታል።
ለዚህም ነው ብርሃኑ በሰሞኑ ተግባሩ ከማንም በላይ የጎዳው ራሱን ነው ያልኩት፡፤
ከልብ አጢናችሁት ከሆነ የብርሃኑ ዳምጤ ችግር “ሞራል አልባ” መሆኑ ነው። ሞራል አልባ ሰዎች የሌላውንም ሞራል ለመጨፍለቅ ሁለቴ ማሰብ አያስፈልጋቸውም። ሞራል አልባ ሰዎች ፤ ምን ይሉኝ? አይሉም።ምን ይሉኝ የሚለውን ጥያቄ በአግባቡና በቦታው ማንሳት፤ የሞራል ድቀት ከሚያስከትል አደጋ ያድናል። ብርሃኑ ዳምጤን መሰል ሰዎች ይህን ጥያቄ አያውቁትም።
ለዚህም ነው ትናትና እንኳን ለተሰዳቢው ለሰሚው በሚዘገንን ጸያፍ ስድብ ያበሻቀጣቸውን የወያኔ ባለስልጣናት  ዛሬ  “ማሪኝ ብዬሻለሁ” እያዜመ የሚለማመጠው።
ግን ለምን?
ጥሩ ጥያቄ ነው…ሞራል አልባ ሰው የማንነቱ ነገር ብዙም አያስጨንቀውም። ተደፈረብኝ። ተገሰሰብኝ የሚለው እሱነት የለውም። ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም። ለሱ ማንነት? ከሚለው “የስብዕና” ጥያቄ ይልቅ ምቾት፤ ድሎት፤ ቅንጦት፤…..የተመቸ ህይወት ቅድሚያ አላቸው። በአጭሩ ሞራል አልባ ሰዎች ከምንም ከምንም ይልቅ ለሆዳቸው ቅድሚያ ይሰጣሉ።ብርሃኑ ዳምጤም ያደረገው ይህንኑ ነው።
ከወያኔ ኩብለላ
የወያኔ ባለ ስልጣናት የአውራቸውን ሞት ተከትሎ በራሳቸው የውስጥ ችግር ተንጠው፤ ውጭ ለታሰሩት ውሾች ይሰ|ጡ የነበሩትን መደበኛ መሽሩፍ አቋረጡ። በዚህ ምክንያት አለን ከሚሏቸው ተናካሽ ውሾቻቸው አንዱ (አባ መላ) ሰንሰለቱን በጥሶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ተቀላቀለ።

በተቃዋሚው ጎራ ቆይታ፦
ሰንሰለቱን በጥሶ የመጣው አባ መላ አክቲቪስት ተባለና(ይታያችሁ ሞራል አልባ ሰው የሰባዊ መብት ተሟጋች ሲሆን)  የድሮ ጌቶቹን አብጠለጠለልን። ሙታንታ ማድረግ የማያውቁ ፍልጦች የሚል ኢ.ሞራላዊ ስድብ አወረደባቸው። እግረ መንገዱንም ሙታንታን ያህል የግል ገበና ሁሉ አውቃለሁ አይነት ራሱን አካበደ።
የጦር ሃይሎች ኤታ ማዦር ሹሙን በዓለማችን የመጨረሻው ደደብ ጀነራል ሲል ተሳለቀበት። የጀኔራሉ ህጻን ልጅ የኦሮሚያውን ፕሬዘዳንት በልምጭ ሲገርፈው “ አባዱላ እንደ ፈርስ ያስካካ እንደነበር ገለጸልን፡፤ ሞራል አልባው አባ ዱላ ለሆዱ ብሎ በህጻን ተገረፈ ብሎ እራት ግብዣ ላይ ያየውን ተረከልን። እረ ማን ቀርቶ… የአዜብን አካላዊ ገጽታ አብጠለጠለ … የበረከትን ሴረኝነት አማሰለ…ስብሃትን በዝሙት በስካርና በገዳይነት ወነጀለ … ብቻ አብዛኞቹ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት እጅግ በሚዘገንነው በምናለሽ-ተራ ጩቤ ምላስ ተተለተሉ።ባለ ስልጣናቱ ተዘናግተው ምሱን ባለመስጠታቸው … በሞራል አልባ አንደበቱ ዘመተባቸው። የአዜብ አፍንጫ ጠማማነት ምን የፖለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው ባይገባንም ፈገግ ማለታችን አልቀረም።
ብርሃኑ ዳምጤ እንዲህ እንዲህ እያለ በተቃዋሚው ጎራ ቆየ፡፤ ወደ ኢሳት ቢያንዣብብም …. በወያኔ የጎደለበትን ምሱን የሚተካበት ምናምኒት ሊያገኝ የቻለ አልመሰለኝም። ቀጠለና በሳውዲ መንግስት ግፍ የተፈጸመባቸውን ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳት በተቋቋመው አለም አቀፍ ግብር ኃይል ገብቶ እድሉን ሞከረ፡፤ እንደ ልኳንዳ ቤት ውሻ አይኑ እየተንከራተተ ምራቁን ገርገጭ አድርጎ ከመዋጥ በስተቀር አሁንም ጠብ የሚል ነገር አልተገኝም። በዚህን ግዜ ብርሃኑ ዳምጤ፤ ከወያኔ ጉያ መውጣቴ ታሪካዊ ስህተት ነው ሲል፡ ታሪካዊ ስህተት ያለውን በታሪካዊ ሞት ሊያርመው ወሰነ።አመቺ ግዜም ጠበቀ።ረዳት ፓይለት ኃይለ መድህንን በቴሬሪስትነት በመፈረጅ ለወያኔ የመጀመሪያውን የምህረት ጥየቃ ደውል ደወለ! ኦሮማይ…….!
ዳግም ወደ ወያኔ…
ብርሃኑ በደርሶ መልሱ ጉዞ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው ያልኩት ያለ ምክንያት አይደለም። በክብር የያዙትን ጌቶቹን አስቀይሞ ሲያበቃ ዛሬ ተመልሶ ለምህረት ደጅ መጥናቱ፤ ዋጋውን ዝቅ አድርጎ ራሱን ለዳግም ሽያጭ ማቅረቡ፤ እንደ ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን እንደ ሰውም ስብዕናውን ማዝቀጡ እየታየኝ እንጂ ።
ከበድን መሃል ምኑን ይመርጧል አትበሉኝ እንጂ፦ በኔ እይታ ዛሬ ከሰሎሞን ተካልኝና ከቤን የዘቀጠ ሞራል ላይ የሚገኘው ብርሃኑ ነው። ይህን ለመረዳት ደግሞ ከቤን ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ማድመጥ ብቻ በቂ ነው፡፡ በ
ቃለ መጠይቁ  ቤን ሌጌቶቹ ባለው ታማኝነት በመኩራራት የሚሰነዝራቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች “ደግ አላደረክም ቢሆንም እንምርሃለን” አይነት ድምጽ ነበራቸው፡፤ አባ መላም በአንጻሩ ጭራውን እየነሰነሰ ጌታው እግር ሥር እንደሚንከባለል ውሻ አይነት በልምምጥ ስሜት ነበር የሚመልሰው፡፤ ከባሪያም ተራ…..!
ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል!
ከብርሃኑ ዳምጤ ድፍረት ሁሉ ያስገረመኝ ፡ ታማኝ በየነንና ማንጓጠጥ መሞከሩ ነው። በርግጥ ወያኔ ከማንምና ከምንም በላይ ታማኝ ቢዋረድላት እንደምትደሰት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፤ በዚህ ስሌት ይመስላል ብርሃኑ ዳምጤ ታማኝን ለማብጠልጠል የሞከረው። ነገር ግን አልተሳካም፡፤ ወያኔም ቢሆን ጀግና ታከብራለች ሲሉ ሰምቻለሁና ከብርሃኑ የገለማ ቃል ይልቅ የታማኝን ግልጽ ጠላትነትን የምታከብር ይመስለኛል፡፤ ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል ይባል የለ። ብርሃኑ ለኛም ለወያኔም ሞቷል።
ይህን የምለው በታማኝ በየነና በአባ መላ መካከል ያለው ፍጹም የሆነ ልዩነት እየታየኝ ነው፡፤ ቃላቶች ካልተመሙብኝ እስኪ በንጽጽር ልግለጻቸው።
ታማኝ ከአላሙዲን የዶላር ማማ ላይ “እረ ወግድልኝ!” ብሎ ወርዶ ከተገፋው ወገኑ ጎን በመቆም ከፍተኛ የሞራል እርከን ላይ የሚገኝ የህዝብ ልጅ ነው።
ብርሃኑ ደግሞ በአንጻሩ በደም ከጨቀየው ከወያኔ ደጅ የወዳደቀ ምንምን አይቶ፤ ይሁን እስቲ ካወጣነው የሞራል ማማ ላይ ቁልቁል ተምዘግዝጎ የወረደ የግፈኞች ወዶ ገብ ባሪያ ነው።አለቀ።
በነገራችን ላይ ብርሃኑ የወያኔን የምህረት ደወል በቤን አማካኝነት ሲያስደውል፤ አብሮም የኢሳትንና የግንቦት ሰባትን ብዙ ሚስጥር ገጸ በረከት እንደሚያቀርብ ነግሮናል። እውነት እውነት እላችኋለሁ ብርሃኑ እስካሁን ከቀበጣጠራቸው ነገሮች ውጭ አንድም የሚያውቀው ነገር የለም። ለምን በሉኝ? ምክንያቱም ዋናው ቁጭቱ ወደ ሚስጥሩም ወደ …ካዝና ሊያቀርቡት አለመፍቀዳቸው በመሆኑ ነው።ጨዋታ በጋራ ሂሳብ በግል ተባለ….አልወደደውም።
አክቲቪስት ስለባሉ….
በኢሳት ጋዜጠኞች አክቲቪስት መባሉ ለኔ ብዙም እንደ ጥፋት አልታየኝም። አክቲቪስት የሚለው ስያሜ እንደ ወታደር ቤት በአገልግሎት ዘመን ተመዝኖ የሚሰጥ ሹመት ሳይሆን አመለካከትን ብቻ መሰረት አድርጎ የሚስጥ በመሆኑ ብርሃኑም ወያኔ ማብጠልጠል በጀመረበት ቅጽበት አክቲቪስት መባሉ አልተገቢነቱ አይታየኝም፡፤  በኔ አመለካከት
በእጅጉ የሚያስቆጨኝና ስህተት የምለው “አክቲቪስት” የሚለውን መጠሪያ መስጠቱ ሳይሆን አንድ የ11ኛቢ ተማሪ  (ከአብሮ አደጉ የሰማሁት ነው) የምናልሽ ተራ ቁጭ በሉ እነ ሙሉጌታ ሉሌን ከመሰሉ በሳል ሰዎች ጎን ፖለቲካ ሊተነትን መቀመጡ ነው። የሚያናድደኝ ከነታማኝ በየነና አበበ ገላው ሌሎችም ብርቅዬ ኢትዮጵያዊያን እኩል አለም አቀፍ ግብር ኃይል ውስጥ መግባቱ ነው። “እኩያ ቢስ ..!” ይሉ ነበር ቀኛዝማች እንቶኔ እንዲህ አይነቱ ያለአቻ… ….ሲገጥማቸው። ይህ አይነቱ ስህተት እንዳይደገም ሊታሰብበት ይገባል ይመስለኛል።
አሁንም በኔ እይታ ብርሃኑ ዳምጤ (ከሟቹ አለቃው ከጠ/ሚ አጸያፊ አባባል ልዋስና) ከመበስበስ… ወደ.. መታደስ…. እንደገና ወደ መበስበስ ያደረገው የደርሶ መልስ እንቅስቃሴ በአጭሩ ሲቀመጥ፡
እንሆ ብርሃኑ ዳምጤ ጥቅም(ሆዱ) ስለጎደለበት ወያኔን ከድቶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ገባ። የወያኔ ባለስልጣናትን በአጸያፊ ስድብ ማዋረድን ለተቃዋሚው ጎራ እንደ ገጸበረከት አቀረበ።አሁንም በተቃዋሚ ጎራ ለህሊና እንጂ ለሆድ የሚሆን ነገር በማጣቱ የአሞሌ ተመኑን ቀንሶ ራሱን ለቀድሞ ጌታው ዳግም ለሽያጭ አቀረበ። ይህው ነው። መጣ እነሱን ሰደበ …ሄደ..ራሱን ሰደበ!
ብርሃኑ ዳምጤ ከዚህ በኋላስ?
ብርሃኑ ከዚህ በኋላ አይደለም ፖለቲካዊ ህይወት ሰዋዊም ህይወት የሚዋጣለት አይመስለኝም።በቅርቡ አንድ አብሮ አደጉ ብዙ ብዙ አሉታዊ  ባህሪያቱን እንዳጋለጠው ሰምተናል። ብርሃኑ የሰሞኑ ተግባሩ ከራሱ ሌላ ማንንም ላለመጉዳቱ ሌላው መገለጫ በይደር ተይዞ የነበረ፤ በቀይ ሽብር ዘመን ከኢህአፓ ውልቅ ደርግ ጥልቅ ብሎ ያስቀጠፋቸውን ሁለት ወጣቶች ጉዳይ ከሟች ቤተሰቦች አንደበት ለማሰማት እንቅስቃሴ መጀመሩ ነው።ይህ ማስፈራሪያ ሳይሆን በቅርብ የማውቀው ወዳጄ እየሰራበት ያለ ጉዳይ ነው።
በኔ እይታ ብርሃኑ የወያኔ ባለስልጣናትን ከሰደባቸው አጸያፊ ስድብ አኳያ እጃቸውን በምህረት የሚዘረጉለት አይመስለኝም። እንደ ሰሎሞን ተካልኝ “የቅንድቡ ውበት” አይነት ሙገሳም የሚያዋጣ አይሆንም። እናም አባ መላ በፓልቶክ ውስጥ ተፈጥሮ በፓልቶክ ውስጥ ኖሮ በፓልቶክ ውስጥ ሞተ ! የሚለውን ዜና የምንሰማበት ግዜ እሩቅ አይሆንም።አባ መላ ሳይበላ ተበላ! ይሏል ይህ ነው…..
ለድህረ ገጾች
ኢሳቶችና ድህረ ገጾች ብርሃኑ የወያኔ ባለስልጣናት በአጸያፊ ስድብ ሲያዋርዳቸው የተቀዳውን ኦዲዮ እየመረጣችሁ በማስደመጥ የምህረት ጥያቄው ተቀባይነት እንዳይገኝ ብታደርጉ እኔን ያየህ ተቀጣ! ነውና አስቡበት….. እያልኩ ከአጼ ቲዎድሮስ ታሪክ ላይ በተዋስኳትና ስሟን ወደ ራሴ በቀየርኳት ስንኝ ልሰናበታችሁ….
ይህንን ሲሰማ ያጓራል ላመሉ
ማናትም ቢላችሁ አዜቧ ናት በሉ!
አዜብ  ጌታቸው
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር

Extractive Industries: Transparency Group Rewards Repression

Ethiopia Approved for Membership Contrary to Rules

Human Rights Watch
(Oslo) – A prominent international natural resource transparency group has damaged its credibility by approving membership for Ethiopia. On March 19, 2014, the governing board of the Extractive Industries Transparency Initiative (EITI), which promotes openness over oil, gas, and mining revenues, admitted Ethiopia as a candidate country despite harsh government repression that has crushed Ethiopia’s once vibrant independent organizations and its independent media.Ethiopia: Stop Using Anti-Terror Law to Stifle Peaceful Dissent
EITI rules call for candidate countries to make a commitment to meaningful participation of independent groups in public debate on natural resource management. Civil society representatives also sit on a national steering committee for EITI.
“The EITI’s decision to admit Ethiopia without insisting on reforms is an affront to the local activists who’ve been jailed or exiled for calling for a more transparent, accountable government,” said Lisa Misol, senior business and human rights researcher at Human Rights Watch. “With this decision, EITI has thrown its principles to the wind and damaged its reputation as a leading good governance group.”
The decision divided members of the EITI board, which includes representatives of governments, companies, and civil society organizations. It also reversed a 2010 decision by the board to defer membership until a draconian 2009 law, still in effect, that sharply limits the activities of independent groups, “is no longer in place.”
Several exiled Ethiopian and international rights advocates called for conditions to be imposed on Ethiopia’s membership bid, but the board did not reach a consensus on such measures.
Under EITI procedures, Ethiopia has three years to prove compliance with the organization’s standards on revenue transparency and other matters. The board can call for an early review based on poor or deteriorating civil society concerns but has never done so.
“EITI’s leadership had an opportunity to stand up for the core principle that civil society participation is a linchpin of good governance,” Misol said. “Instead, it sacrificed EITI’s credibility by allowing Ethiopia to join the ‘transparency’ club despite intense repression.”