Sunday, October 5, 2014

ጤናችን

ብልሃርዚያና ጉዳቶቹ

አዘጋጅ ናትናኤል አባተ

By Nathnael Abate

በዛሬዉ ጤናችን ዝግጅታችን ስለብልሃርዚያ የሚናቀርብ ሲሆን በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለዉን የብልሃርዝያ ስርጭትና እንድሁም  ብልሃርዚያ  የሚያስከትላቸዉን ጤናዊ ኢኮኖሚያዊና  ማህበራዊ ጉዳቶ ችን እንዳስሳለን፣፣ ብልሃሪዚያ በአንድ ሃገር ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ላይ ከፍተኛ  ተጽዕኖ ያሳድራል ፣፣ የህጻናትን እድገት በመግታት፣ተማሪዎችን ከትምህርት በማድከምና በማስቀረት፣የማገናዘብ ችሎታቸዉን በመቀነስ፣ አዋቂዎችንና አምራች ሃይሎችን ከስራ ገበታቸዉ በማስቀረትና እንድሁም መንግስታት በሽታዉን ለመቆጣጠር የሚያወጡት ከፍተኛ ወጭዎች በጠቅላላ የአንድን ሃገር ኢኮኖሚ በእጅጉ ይጎዳሉ፣፣በሃገራችን ኢትዮጵያ ሽስቶዞማ ማንሶኒ  የሚባል ሲገኝ ሃገርቱዋ በአለም ላይ ለበሽታዉ ተጋላጭነትና ስርጭት ከፍተኛ  ድርሻ ትወስዳለች፣፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከባህር ጠለል 1200 ሜትር እስከ 2000 ሜትር ባሉ አከባቢ ወንዞ ፣ኩሬዎችና  ለሎች ዉሃማ አካላት ላይ በሙሉ ሽስቶዞማ ማንሶኒ ይገኛል፣፣ ለምሳሌ ያህል ብልሃርዚያ ከሚገኝባቸዉ ሃይቆች መካከል ዚዋይ፣ ሃዋሳ፣ቢሾፍቱ፣ ሃሮማያ፣ ላንጋኖ ፣ጂማ፣ ባህር ዳር እንድሁም በለሎች ወንዞች ዉስጥ ጎጃም፣ወሎና ትግራይ ይገኛሉ፣፣ የእነዚህ አከባቢዎች 60% ያህል የትምህርት ቤት ህጻናቶች የበሽታዉ ሰለባ እንደሆኑ በአከባቢዉ የተደረጉ የናሙና ጥናቶች ያሳያሉ፣፣ 2010 ሴሜን ኢትዮጳያ ዉስጥ ጎርጎራ የሚባል ቦታ በተደረገው  1  እስከ 8 ክፍልተማሪዎች ላይ በተደረገዉ ሁለት የተለያዩ  የናሙና ጥናቶች አብዛኞቹ ተጠቂዎ የገጠር አከባቢ ልጆ ችና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ እንደሆኑ አመልክቱዋል፣፣ለናሙና ጥናት ከተወሰዱ ተማሪዎች መሃከል ልብሶቻቸዉን በወንዝ ወይም ኩሬ ዉሃ ዉስጥ የሚያጥቡ ልጆች 15.6 ጊዜ ከለሎች አንጻር ለበሽታዉ የተጋለጡ ሲሆኑ ለሎች እቃዎ ችን የሚያጥቡ 2.6 ጊዜ፣እርሻ ላይ የሚሰሩ7.08 ጊዜ፣ የሚዋኙ 4.5 ጊዜ ለበሽታዉ የተጋለጡ መሆናቸዉን ጥናቱ አመልክቱዋል ፣፣ እንድሁም ስለብልሃርዚያ ምንም እዉቀት ወይንም ግንዛቤ የለላቸዉ ልጆች 20.36 ጊዜ ለበሽታ የተጋለጡ ናቸዉ ግንዛበ  ካላቸዉ አንጻር፣፣ ጥናቱ እንዳመለከተዉ 15 እስከ 19 እድሜ  ክልል ዉስጥ የሚገኙ  የአከባቢዉ ልጆ በከፍተኛ ሁነታ ተጋላጭ ናቸው፣፣ ጥናቱ አያይዞ እንደ ጠቀሰው በሃገርቱ የሽስቶዞማ ማንሶ ስርጭት  እንደየአከባቢዉ 1% እስከ 90% እና  ከዚያ በላይ እንደምሆን ጠቁሙዋል፣፣  ከዚህ በተጨማሪ በሃገሪቱ ቆላማ አከባቢዎች የሚገኘዉ ሽስቶዞማ ሂማቶቢየም አዋሽ፣ዋቢሸበለና ለኢትዮ ሱዳን ድንበር አከባቢ ይገኛል፣፣


  ብልሃዚያ  ወይም snail fever or katayama fever  በጥገኛ  ትሎች  ወይም worms  የሚመጣ በሽታ ሲሆን  በሽታዉን የሚያስይዙ ትሎች blood flukes (trematode worms) የሚባሉ genus Schistosoma የሚመደቡ ናቸው፣፣ በሰዉ ላይ በሽታ ከሚያስከትል ከሽስቶዞማ ዚርያዎች አንዱ  Schistosoma mansoni የሚባለዉ ሲሆን  በሃገራችን እትዮጵያ በሰፍዉ ይገኛል፣፣

  ሽስቶዞሚያስስ ማንሶኒ  የሰዎች ሰዉነት ከገባ በሁዋላ አብዛኛዉን ጊዜ አንጀትና ሆድ አከባቢ ጉዳት ስለሚያደርሱ  intestinal schistosomiasis ወይንም የአንጀት ሽስቶዞማ  ይባላል፣፣  ሁለተኛዉ Schistosoma haematobium የሚባለው ሲሆን እንደ ማንሶኒ ስርጭቱ ባይበዛም ቆላማ አከባቢዎች ይገኛል፣፣ ይሄ  ሽስቶዞማ  Urogenital schistosomiasi  ተብሎ  የሚጠራ ሲሆን የሽንት ቱቦና ፍኛችን አከባቢ ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል፣፣በዓለማችን ወደ  700 ሚሊዮን  የሚደርሱ ሰዎ በበሽታው እንደተጠቁ  2012 የተለያዩ  ርፖቶች ያሳያሉ፣፣  የአለም ጤና ድርጅት ባወጣዉ መረጃ መሰረት ብልሃሪዚያ  78 የተለያዩ  የዓለማችን  ሃገሮች ዉስጥ ይገኛሉ፣፣

ሁሉም በሽታ የሚያስከትሉ  ተዋህሳት ወይንም  pathogenesና ጥገኛ  ትሎች  የራሳቸዉ  የሆነ በሽታ የማስተላለፊያ መንገድና የህይወት ዉዴት አላቸዉ ፣፣  አንዳንድ ፓቶጅንስ በቀጥታ  ሆስት ሴል (host cell) በማጥቃት በሽታ የሚያስከትሉ  ሲሆኑ  ለሎቹ ደግሞ የህውታቸዉን ዑዴት ለመፈጸም ከአንድ በላይ ተሸካሚ ይፈልጋሉ፣፣  ሽስቶዞሚያሲስ የህይወቱን ዑዴት ለመፈጸም በሽታ ለማስከተል ከአንድ በላይ ሆስት ይፈልጋል፣፣ 

አንድ በብላሃርዚያ  የተጠቃ  ሰዉ  በዉስጡ ወንድ ወይም ሴት  የሽስቶዞማ  ትል ሲኖርበት እንቁላሎቹን በዉሃ ሽንትና ዓይነ ምድር ጋር ወደ ዉጭ ይልካል፣፣ በሽተኛዉ ሽንቱን በስርአቱ ካላስወገደ በጎርፍ ወይንም በዝናብ ዉሃ  ዓማካኝነት ከወንዝ ወይም ኩሬ  ይገባና ዉሃዉ በሽስቶዞሚያስስ እንቁላልይበከላል፣፣ በዚህ ጊዜ የሽስቶዞማ  እንቁላሉ፣ ከቀንድ አዉጣ ጋር በመጣበቅ ወደ ላርቬ ካርሰሪ (LARVAE CARCERI) ያድጋል፣፣ ቀንደ አዉጣ  መሃከለኛዉ  ተሸካሚ ወይም በእንግልዘኛ  intermediate host በመሆን ያገለግላል፣፣ የሽስቶዞማ ላርቬ ቀንድ አዉጣ ላይ በጥገኝነት እየኖረ  ከሰዉ ጋር ንኪኪ ሲኖረው የሰዉን ቆዳ በመብሳት ወደ  ሰዉነት ዉስጥ ይገባል፣፣ብልሃሪዚያ  በብዛት የሚያጠቃቸዉ ሰዎች በሽስቶዞሚያስስ ላርቬ በተበከለ ዉሃ ዉስጥ የሚዋኙ  ፣የሚታጠቡ ፣የሚጠጡና ለለሎች ግልጋሎት የሚጠቀሙ ህጻናትንና  አዋቂዎችን ናቸዉ፣፣ ሰዉነት ወስጥ ከገባ በሁዋላ ላርቫ  ወደ አዳልት(adult) ሽስቶዞሚያሲስ  በማደግ  የሰዎች ደም ቧንባዎችና ሆድ ዉስጥ የሚኖሩ ሲሆኑ እንቁላል መፍጠር ይጀምራሉ፣፣

እንደማንኛዉም  በሽታ  ብልሃርዚያ የራሱ የሆነ  የህመም ምልክቶችን ያሳያል፣፣ የአንጀት ዉስጥ ሽስቶሶማ  ወይም Intestinal schistosomiasis የሚያሳያቸዉ ምልክቶች፣ የሆድ ህመም፣ ተቅማጥና ደም ከሰገራ ጋር መታየት፣ የቆየ እንደሆነ የጉበት ማበጥ በፈሳሽ መጠራቀምና ከፍተኛ የሆነ ደም ግፍት የአንጀት ቱቦዎች ላይ ስለምከሰት እንድሁም የጣፊያ ትልቀትም ያስከትላል፣፣
ፊኛችንን አከባቢ የሚያጠቃው ሽስቶዞሚያሲስ ወይም urogenital schistosomiasis የሚያሳየዉ ምልክት ከዉሃ ሽንታችን ጋር ደም የሚወጣ ሲሆን Fibrosis በፊኛችንና  የሽንት ቱቦ ላይ ይፈጥራል እንድሁም ኩላሊት እንዳይሰራ የሚያደርግ ሲሆን በንዳንድ በቆዩ ምክንያቶች  ካንሰር ያስከትላል፣፣

ሽስቶዞማ የትሮፒካል አከባቢ  በሽታ በመሆኑ በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉት ሃገሮች ወንዞች፣ ሃይቆችና ለሎች ዉሃማ አካላት ላይ ይገኛል፣፣ ከአፍሪካ ዉጪ በደቡብ አሜሪካ ሃገሮች ደቡብ ምስራቅ እስያና መሃከለኛ ምስራቅ ዉስጥ ያለ ቢሆንም 90%  ያህል የሽስቶዞሚያሲስ በሽተኞች በአፍሪካ ዉስጥ ይገኛሉ፣፣  ንጹህ የመጠጥ ዉሃ  በለለበትና ፣ሽንት ቤቶች ጉድለት ያለበት አከባቢዎ በሽታዉ ሰፊ የሆነ የበሽታ ስርጭት ሲለሚታይ የድህነት በሽታ የሚል መጠሪያ አለዉ፣፣ የሚያድጉት ሃገሮች ዉስጥ የከተማዎች መስፋፋትና የሰዉ ቁጥር መጨመር ያለ በቂ ቆሻሻ ማስወገጃ ዜዴ  የበሽታዉን ስርጭት አባብሶታል፣፣ የተበከሉ ወንዞችን፣ሃይቆችንና  ኩሬዎቹን የሚገለገሉ ሰዎች በሰፍዉ ለበሽታዉ ተጋላጭ  ሲሆኑ ልጆችና  ህጻናት በሚዋኙበት፣ልብስ በሚያጥቡበትጊዜና ለሎች የእለት እንቅስቃሰዎቻቸዉን በሚያከናዎኑበት ወቅት ለሽስቶዞሚያሲስ ይጋለጣሉ፣፣

ከሰሃራ በታች ባሉት ሃገራት ማህበረሰብ ላይ በከፍተኛ ሁነታ  ሞትና ጉዳት የሚያደርሰዉ ገዳይ የሆነ  እንድሁም  በአለም ላይ ከፍተኛ  አሃዝ ያላቸዉን  ሰዎች  በመግደል የሚታወቀው በሽታ ወባ ሲሆን በሁለተኛነት በዓመት ከ200000  በላይ ሰዎች በብልሃርዚያ  ህወታችዉን እንደሚያጡ ጥናቶች ያሳያሉ፣በተለይ በህጻናት ላይ ከፍተኛ የጎን ጉዳት የሚያደርስ ሲሆን የህጻትን እድገት ይገታል፣፣  የማገናዘብና  የማስተዋል ብቃት ይቀንሳል፣ ከትምህርት ገበታቸዉ ያስቀራቸዋል፣የምግብ ፍላጎት በመቀነት ለጤናዊ ቀዉስና ሞት ይዳርጋል፣፣ በአዋቂዎች ላይ የተወሰነ ያህል ጉዳት እንደሚያደርስ የታወቀ  ብሆንም  በህጻናት ላይ የሚያደረሰዉን ያህል የከፋ ያለመሆኑን  ጥናቶ ያሳያሉ፣፣ አብዛኞቹ  የሽስቶዞሚያስስ ተጠቂዎች ህጻናት በመሆናቸዉ የበሽታዉ ስርጭት 8 እስከ 19 ዓመት  እድሜ  ባላቸዉ የማህበረሰብ ክፍል ዘንድ ሰፍዉን  ድርሻ  ይወ ስዳል፣፣

ከሰሃራ በታች ባሉት 10 ሃገሮ ከፍተኛ የሽስቶዞሚያስስ ስርጭት ከመኖሩም በላይ 62 ፐርሰንት ያህል የዓለማችን ተጠቂዎ   እዚሁ አከባቢ ይገኛሉ፣፣ ከአስሮቹ ከተዘረዘሩ ሃገራት መሃከል ሃገራችን ኢትዮጵያ አንዷ ናት፣፣ በኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ ሽስቶዞሚያሲስ ስርጭት ብኖርም ህዝቡ ለበሽታዉ ያለዉ ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑ በሽታዉን በጣም የከፋ ያደርገዋል፣፣ እዚህ ላይ አንድ መስተዋል ያለበት ነገር የተማሩ እንኩዋን የሚባሉ ሰዎች ብልሃርዚያ ጠፍቱዋል የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ መያዛቸዉ በጣም የሚያሳዝን ነዉ፣፣


 ለብልሃርዝያ መስፋፋት ትልቁ ምክንያት ስለበሽታዉ ጎጅነት የማህበረሰቡ ግንዛቤ እጥረት ብቻ ሳይሆን የመንግስታትም የተሳሳተ አስተሳሰብና ግድ የለሽነት እንደሆነ  የዘርፉ ጥናት ባለሙያዎች ይናገራሉ፣፣ የአለምጤና ድርጅት ባወጣዉ መረጃ መሰረት ብልሃርዚያ  ባደጉት ሃገሮች ዉስጥ ያለመኖሩና የድሃ ሃገሮች ችግር መሆኑ በሽታዉን ለመቆጣጠር ሰፍዉን ድርሻ የሚወስዱ የሃብታም ሃገሮች ትኩረት ቀንሰዋል  ይላል፣፣ ይሁን እንጅ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአለም ጤና ድርጅት፣ ለሎች በጤና ዘርፍ የተሰማሩ የበጎ ዓድራጎት ድርጅቶችና መንግስታት በጉዳዩ  ዙርያ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፣፣  አብዛኞቹ  የሽስቶዞሚያሲስ ተጠቂዎ አፍሪካ ዉስጥ ሚገኙ በመሆናቸዉ እርዳታ እንደሚያስፈ ልጋቸዉ እሙን ነዉ፣፣  በድሃ ሃገሮች  ዉስጥ የተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና የዉጭ መንግስታት ብልሃርዚያንና መሰል ገዳይ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ብዙ ጥረቶችን እያደረጉ ይገኛሉ፣፣ ከሃብታም ሃገሮች በሽታዉን ለመቆጣጠር የሚሰጡ እርዳታዎች ባንዳንድ ሃገሮች ከተመደበላቸዉ አላማ ዉጭ በመዋሉ በሽታዉን በቀላሉ ለመቆጣጠር አዳጋች አድርጎታል፣፣ ለምሳለ ያህል በሃገራችን ኢትዮጵያ ለተለያዩ  ተቋማት ከሃብታም ሃገሮች የሚሰጡ እርዳታዎች በገዥዉ ወያነ መንግስት መመዝበራቸውና የድሃዉ ዜጋ ጉዳይ ትኩረት ያለመሰጠቱ በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮሚያዊ ዘርፎች ያሉ እልቆቢስ ችግሮችን መቅረፍ አልቻለም ፣፣ በእርዳታ የሚገኘዉን ገንዘብ ሁላ ክንዱን ለማፈርጠም የሚጠቀመው ወያኔ ቤተሰቦቹና ተላላክዎቹን  ተራ ራስ ምታት ሲያማቸዉ አሜርካ፣አዉሮፓና ለሎች በበለጠጉ ሃገሮች ሲያሳክም ምስክን የኢትዮጵያ ህዝብ ለህይወታቸዉ የሚደርስላቸዉን አጥቶ በድህነት አለንጋ ከመገረፋቸዉም አልፎ ህይወታቸዉን በሞትና በሽታ ይቀጠፋሉ፣፣ በሃገርቱ ተንሰራፍቶ የሚገኘው መንግስታዊ ሙሰኝነት ለህክምና ተቋማትና ለህክምና  ምርምር የሚዉሉ የእርዳታ ገንዘብንና ለተቋማቱ የተመደቡ ሃገራዊ ባጄቶችን ለግል ጥቅም  ማዋላቸው በበቂ ሁነታ ለህዝቡ ሂክምናዉንና  የነብስ አድን ስራ ለማድረስ አዳጋች  አድርገዋል፣፣