Thursday, March 21, 2013

የባህር ዳሩ ጊዮን ሆቴል ህወሀትንና ብአዴንን ዱላ ቀረሽ ፍጥጫ ዉስጥ መክተቱ ተሰማ

በደርግ ዘመነ መንግስት የአገር ሀብት የነበረዉና ባለፉት ሃያ አንድ አመታት የትግራይ ተወላጅ በሆነ ግለሰብ አላግባብ ተይዞ የነበረዉ የባህርዳሩ ጊዮን ሆቴል ባለቤትነት ለአማራ ክልል የመንግስት ቤቶች ኤጄንሲ እንዲዘዋወር መወሰኑ የህወሀትንና የብአዴንን ከፍተኛ ባለስልጣኖች ግጭት ዉስጥ እንዳስገባ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉ ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩልን ዜና ገለጹ። በ1983 ዓ.ም ወያኔ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር በመንግስት ይዞታ ስር የነበረዉን የባህርዳሩን ጊዮን ሆቴል ለመለስ ዜናዊ የቅርብ ዘመደ ለሆነዉ ወልዱ ለሚባል ግለሰብ በ5000 ብር በኪራይ ስም መሸለሙ ይታወሳል። የአድዋ ተወላጅ የሆነዉ ወልዱ የሚባለዉ ግለሰብ ወያኔ የትጥቅ ትግል ያካሄድ በነበረባቸዉ 17 አመታት ባህርዳር ዉስጥ የህወሀት ሰላይ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን መለስ ዜናዊ ያንን የመሰለ ዘመናዊ ሆቴል በ5000 ብር የሸለመዉ ለዚሁ የስለላ አገልግሎቱ እንደሆነ ብዙ የባህር ዳር ነዋሪዎች በግልጽ ይናገራሉ።
ባለፉት ሃያ አንድ አመታት ጊዮን ሆቴል ለወልዱና ለልጁ ለብስራት ወልዱ እጅግ በጣም ከፍተኛ ትርፍ ሲያስገኝ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህ በሆነባቸዉ አመታት ሁሉ የባህርዳር ከተማ ህዝብ አንድ ኪዎስክ በ5 ሺ ብር እየተከራየ እንዴት ጊዮን ሆቴልን የሚያክል ትልቅና ዘመናዊ ሆቴል በ5 ሺ ብር ብቻ ይከራያል እያለ ተቃዉሞዉን ቢያሰማም የሚሰማዉ ጠፍቶ ሃያ አመታት አልፈዋል። ሆኖም በቅርቡ መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ የፌደራል የኪራይ ቤቶች ድርጅት የአማራ ክልል መንግስት ሆቴሉን እንዲረከብ ለአማራ ክልል የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ደብዲቤ በመጻፉ ጉዲዩ ከክልል አልፎ ገዢዉ ፓርቲ ጽ/ቤት መድረስ ችሏል። ሆቴሉን ለከልል መንግስት እንዲያስረክቡ ደብዲቤ የደረሳቸዉ ወሌደና ሌጁ ብስራት ጉዳዩን በቀጥታ ለበረከት ስምኦን፤ ለፌዳሩሽን ምክር ቤት ሰብሳቢው ካሳ ተክለብርሀንና ለአዲሱ ለገሰ የመለስ ዜናዊን ሞት ተክትል ሆቴሉን እንዱያስረክቡ መጠየቃቸውን በመናገራቸው፣ ባለስልጣኖቹ የክልሉ መንግስት የጻፈውን ደብዳቤ እንዱያነሳ ጠይቀዋል።
የክልሉ የመንግሰት ቤቶች ኤጀንሲ ጉዲዩ ከፍተኛ ዝርፊያ መሆኑን ገልጾ ዉሳኔዉን ለመለወጥ ፈቃደኛ አለመሆኑን ቢገልጽም የሆቴለ አስተዳዳሪ የሆነዉ ብስራት ወልዱ የክልሉን ባለስልጣናት በማስፈራራት እርምጃ እንደሚወስድ በመዛት ሆቴሉን ለማስረከብ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገልጿል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የዝግጅት ክፍላችን በስልክ ያናገረዉ አንድ የኪራይ ቤቶች ድርጅት ሰራተኛ የሆቴሉ አስተዳዳሪ ብስራት ወልዱ ሆቴሉን እንዲያስረክብ ደብዳቤ ሲጻፍለት “ዋጋህን ታገኛለህ” የሚል መልስ መስጠቱን ተናግሯል። የባህርዳር ከተማ ህዝብ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በአንድ ተራ የህወሀት አባል መደፈረቸዉን አስመልክቶ እያሾፈ ሲሆን እንደ ብዙ ታዛቢዎች እምነት የክልሉ መንግስት ከዚህ አይነቱ ህዝባዊ ትችት ነጻ መሆን የሚችለው ግለሰቡ ሆቴሉን እንዱያስረክቡ ሲያደርግና እንደማንኛውም ሰው ተጫርቶና ለጨረታዉ ተገቢውን ክፍያ ማስከፈል ሲችል ብቻ መሆኑ ታውቋል።

ከሳሊኒ በመቀጠል የህዳሴ ግድብ ተብየው ተጠቃሚው የአዜብ መስፍን ቤተሰብ ድርጅት መሆኑ ተዘገበ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴላቪዥን ኢሳት ቀደም ብሎ ከሁለት አመታት በፊት በአዜብ መስፍን የእህት ልጅ አቲኮ ስዩም አምባየ የተመሰረተው ኦርቺድ ቢዝነስ ግሩፕ በጣሊያኑ ሳልኒ ኮንስትራክሽን አማካኝነት በሚገነቡት ግልገል ጊቤ አንድ እና ግልገል ጊቢ ሁለት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች ስሚንቶ እና የግንባታ እቃዎችን እንዱሁም ከፍተኛ ማሺነሪዎችን በማቅረብ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማጋበሱን መዘገቡን አውስቶ ይሄው ኩባንያ ከሳሉኒ ጋር ግልጽነት የጎደለው የቢዝነስ ስምምነት በማድረግ በአሁኑ ጊዜ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ስሚንቶ እንዱሁም ከባድ ማሺኖችን በማቅርብ ላይ እንደሚገኝ አጋልጧል።
ኢሳት በአባይ ወንዝ ላይ የሚሰራውን የህዳሴውን ግድብ ፕሮጀክት በቅርብ የሚያውቁ ሰዎችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው ግድቡን እየገነባሁ ነው ከሚለው ሳልኒ በመቀጠል ከፍተኛ የሆነ ትርፍ የሚያገኘው ኦርቺድ፣ ከየትኛውም ድርጅት ጋር ሳይወዳደር በእነ አዜብ መስፍን አማካኝነት የስሜንቶና ማሸንሪዎች አቅራቢ ሆኖ ቀርቧል ብሏል።
ይሄው ኩባንያ ቦዲ ዋይዝ ጂም፣ ካፌ ፓኒኒ፣ ኦርቺድ ጄኔራል ኮንትራክተር፣ ኦርቺድ ትራንስፖርት፣ ኦርቺድ ትራንዚት፣ ኦርቺድ ማሽነሪ ሬንታል፣ ኤስ ኤንድ ኤስ እርሻ፣ ሂላል ቱር ኤን ትራቭል፣ ሜትሮሉክስ ፍላወር፣ ናይል ስፕሪንግ ውሀ፣ ሬንቦው ጊፍት ሾፕ፣ ሪል ሳልን፣ ወንደር ዊሌ ቢዝነስና ሌሎችም በአዲስ አበባና በመላው አገሪቱ ታዋቂ የሆኑ የንግድ ድርጅቶችን በስሩ አቅፎ መያዙን ኢሳት በማያያዝ ዘግቧሌ።
አቲኮ ስዩም ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ይህ ነዉ የሚባሌ ኃብት እንዳልነበራት ታሪኳን ያጠኑ ዘጋቢዎቹ ማረጋገጣቸውን የዘገበው ኢሳት ባለፉት 20 አመታት ግን በልዩ ትዕዛዝ “ኦርቺድ” ቢዝነስ ግሩፕ የሚባል ድርጅት ተከፍቶላት ሆን ተብሎ አያሌ የግንባታ ጨረታዎችን አንድታሸንፍና በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ካለ ቱጃሮች ተርታ ለመመደብ እንደቻለች መግለጹን አውስቷል።
የህወሀት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት በዘመዶቻቸው ስም የሚገነቧቸው የቢዝነስ ተቋማት እየተበራከቱ መምጣቱን በተደጋጋሚ ሲዘግብ እንደነበር ያስታወሰው ኢሳት የባለስልጣናትን የሀብት ምዝገባ ጨርሶ በአጭር ጊዜ ይፋ አድረጋለሁ በማለት ሲፎክር የነበረው ጸረ ሙስና ኮሚሽንም ቃሉን ለመጠበቅ እንደተሳነውና ኮሚሽኑ ባለስልጣናቱ በዘመድቻቸው ስም የያዙትን ሀብትና ንብረት ለመመዝገብ ስልጣን እንዳልተሰጠው ገልጿል።

የኦህዴድ ምርጫ ውጤት ተራዘመ

tplf meeting


ህወሃት አባረረ፣ ብአዴንና ደኢህዴን ባሉበት ቀጠሉ

ድሮ “ላዩ ካኪ ውስጡ ውስኪ” እየተባለ በኢሰፓ አባላት ዩኒፎርም ይቀለድ ነበር። ዛሬ ደግሞ ኢህአዴግ ተመሳሳይ ልብስ አልብሶ በየክልሉ የሰየማቸውን ፓርቲዎችና አመራሮቻቸውን የተመለከቱ “ስቱኮ” እያሉ እንደሚቀልዱባቸው ተሰምቷል።
“ስቱኮ” ግልብጥና ግጭት የበዛበት መኪና ተቀጥቅጦ አልስተካከል ሲል፣ የተገጣጠበና አልመሳሰል ያለ ግድግዳ “በግድ” ለማመሳሰል የሚያገለግል ቶሎ የሚፈረካከስ ጭቃ መሰል የቀለም አይነት ማጣበቂያ ነው።
“ኮሚኒስቶች በችግርና በቅራኔ ውስጥ ሆነው በግድ ለመመሳሰል አንድ ዓይነት መለያ መልበስ ይወዳሉ። ኢህአዴግም በተመሳሳይ በችግር ውስጥ ተዘፍቆ ሳለ፣ ለተመልካችና ለካሜራ ተመሳሳይ ልብስ ለብሶ በግድ አንድ ነኝ ሲል ማየቱ ብዙም የሚገርም አይደለም” የሚለው አስተያየት በስፋት እየተሰጠ ነው። “በግድ አንድ” ሆነው በየክልሉ ስብሰባ የሚያካሂዱት እህት ፓርቲዎች የለበሱትን መለያ የሚያመርተው ደግሞ የህወሃት የንግድ ድርጅት አልሜዳ ጨርቃጨርቅ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ባህር ዳር ላይ ለሚያካሂደው ጉባኤ በዝግጅት ላይ ያሉት “እህት” ፓርቲዎች በየክልላቸው በስብሰባና በምርጫ ተጠምደው ሰንብተዋል። ውሉ ያልታወቀውና ምስጢር የተደረገው የኦህዴድ ጉባኤ የምርጫውን ውጤት ማጠናቀቅ አልቻለም። ህወሃት በመተካካት ስም ነባሮቹን አራት አመራሮች ሲያሰናብት፣ አቶ በረከትና አዲሱ ለገሰ የኢህአዴግ የመተካካቱ ስልታዊ በትር ሳይነካቸው ማለፉ ተደምጧል። ደኢህዴን በነበረበት እንደሚቀጥል ይፋ ሆኗል።
ኦህዴድን ለመምራትና ሰባት አመራር በሚሰየምበት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለመሆን አባ ዱላ ገመዳ፣ ግርማ ብሩ፣ ድሪባ ኩማ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ አለማየሁ አቶምሳ፣ አስቴር ማሞና ደግፌ ቡላ ከተጠቆሙት መካከል ይገኙበታል። የህወሃት የንግድ ተቋምና አንደበት የሆነው ሬዲዮ ፋና “የተጠቆሙትን አመራሮች ለማሳወቅ የድምጽ ቆጠራው ጊዜ ስለሚወስድ ለነገ ተላልፏል” የሚል ዘገባ አሰራጭቷል።
ፋና ይህን ይበል እንጂ የጎልጉል ምንጮች ከስፍራው እንዳሉት የኦህዴድ ስብሰባ ከፍተኛ ንትርክ የተስተናገደበት ሆኗል። ምንጮቹ እንዳሉት የበታች አመራሮች፣ የቀበሌና ወረዳ የስር መዋቅሮች በድፍረት የድርጅቱን አመራሮች ነቅፈዋል። በራሳቸው ውሳኔና መንገድ የማይመሩበት ምክንያት መነሻና ይህ አካሄድ መቼ ሊያቆም እንደሚችል ሊገባቸው እንዳልቻለ የተናገሩ አሉ።
“ውርስና ቅርስ” እየተባሉ የሚወደሱት አቶ መለስ በህይወት እያሉ ህወሃት ድምጽ ነፍጎ ሲያባርራቸው “መለስ ይሁን” በማለት የተሰጣቸውን የህወሃት ሊቀመንበርነት ስልጣን ላለመቀበል ያፈገፈጉት አቶ አርከበ እቁባይ በመተካከት ስም ከህወሓት መሰናበታቸው ይፋ ሆኗል። ዊኪሊክስ ይፋ ባደረገው መረጃ ህወሃትን እንዲመሩ ተመርጠው የነበሩት አቶ አርከበ አዲስ አበባ ፎቶግራፋቸው ከተለጠፈበት ጊዜ ጀምሮ “የድስትና ማማሰያ” ምሳሌ በመሆን ጥግ ተደርገው ከተረሱ በኋላ በመጨረሻ አማካሪ ተብለው ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ተዛውረው ነበር።
አቶ በረከትን ተከትሎ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ዘርአይ አስገዶምና አቶ ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ህወሃትን በይፋ መሰናበታቸው ታውቋል። ፋና “በክብር ከማዕከላዊ ኮሚቴ ተሰናብተዋል” ሲል አሞካሽቶ መርዶ አብስሯል። ፋና በነካ እጁ የዋናውን የሚዲያ ፊት አውራሪ አቶ በረከትን ዜና ይፋ አደርጓል።
መለስ ያዘጋጁት “የማጽጃ በትር” የሚባለው መተካካት ብአዴን ውስጥ ተግባራዊ አልሆነም። ታማኞቹ የወ/ሮ አዜብ መስፍን ቡድን የሆኑት አቶ በረከት፣ ሰሞኑን በተዘጋጀ ዶክመንታሪ ፊልም በትግርኛ ተረት ሲያወርዱ የታዩት አቶ አዲሱ ለገሰ፣ አቶ ጉዱ ካሳና ፓርላማ ውስጥ የስነስርዓት ጥያቄ ሲቀርብላቸው “ታዝዤ ነው፣ ከታዘዝኩት ውጪ የማደርገው የለም” በማለታቸው የሚታወቁት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በአዲሱ ምርጫ ተካተዋል።
ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ደኢህዴንን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ምክትል ሆነው እንዲቀጥሉ ተሰይመዋል። በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት የሞባይል ስልክ ማነጋገር አስቸጋሪ እንደነበር የጎልጉል መረጃ አቀባይ ከስፍራው አስታውቋል። አቶ ሃይለማርያም የአገሪቱ መሪ ከሆኑ በኋላ ሃዋሳ ሲገኙ ለደህንነት በሚል የስልክ መስመሮች ላይ ማዕቀብ መደረጉን ተገልጋዮች በቅሬታ ሲገልጹ ተሰምቷል።
ከሁሉም ጉባኤዎች ጎልቶ የወጣው የህወሃት ጉባኤ ሲሆን የትግራይ ክልል ሃብትና እድገት በታላቅ ትዕይንት ከጉባኤው በፊት ለህዝብ እንዲተላለፍ መደረጉ የተለያየ አስተያየት እየተሰነዘረበት ነው። መቀሌ በትዕይንት አቅራቢ ህዝብ ተጨናንቃ ሲጨፈርና ከበሮ ሲደበደብ ያሳየው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዳለው ትዕይንቱ የተዘጋጀው መለስን ለመዘከር ነው። ዜናው በተመሳሳይ ሌሎች ክልሎች የደረሱበትን የልማትና የዕድገት ደረጃ የሚያሳይ ትዕይንት እንመራዋለን ለሚሉት ህዝብ በይፋ ያላሳዩበትን ምክንያት ግን አልገለጸም።
ጋዜጠኛ ተመስገን “ሽክ” ብሎ ፊቱ ላይ ርካታ እየተነበበት ያነጋገረው ጋዜጠኛ መቀሌ ባየው ነገር መገረሙን ደጋግሞ አመልክቷል። በተሽከርካሪ ላይ በተዘጋጁ ሞዴል ማቀናበሪያና ምስሎች ትግራይ የደረሰችበትን ደረጃ የተመለከቱ “ልማት ያስደስታል። ከሰባ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚያለቅስበት ልማት መሆኑንን ስናስብ ያሳዝነናል” ሲሉ ተደምጠዋል።
አርቲስት መሐሙድ አህመድ “ትግራይ ልትሰምጥ ነው የሚባለው ውሸት ነው” በማለት የተናገረውን ያስታወሱ አስተያየት ሰጪ፣ “ብሶት ሁሉም ቦታ፣ በየትኛውም ጊዜና ወቅት የሚከፋቸውንና በቃን የሚሉ ዜጎችን ይፈጥራል። የትግራይ ህዝብም ብሶት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ትግራይ ብቻዋን ስትለማና ስታድግ ሌላው እየተረገጠ መሆኑንን በመገንዘብ ከመጨፈር ይልቅ በማስተዋል በስማቸው የሚፈጸመውን ግፍ እንዲቆም የመጠየቅ ሃላፊነት አለባቸው” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

Two top OLF leaders abandon organization

WASHINGTON, DC (Ethiomedia) - Amin Jundi, general secretary of the Oromo Liberation Front (OLF), and fellow OLF senior Taha Abdo Tuko said on Wednesday they bid farewell to the organization for their own reasons.
The two top leaders of OLF under the chair of Eritrea-based former Ethiopian Army General Kamal Galchu said in a press statement that they were not only withdrawing from leadership positions but also rescinding their membership.Amin Jundi has been a familiar face in North America as he had often wowed audiences with his charismatic features and oratorical skills focused on unifying the Ethiopian people for democracy and justice and against tyranny (watch video clip).
In 2008, some of the OLF members launched a renewal movement to what they called "remedying the maladies" that had severely restricted the growth of the organization and crippled the struggle.But with the passage of time, their expectations fell far short of the standards they set for themselves, and the struggle didn't help the struggle of the great Oromo people."Under a circumstance in which our yearning to renew OLF is not materialized and in the absence of an enabling internal environment, finding that not only will our continuing with this faction not meet our own standards but also does not serve the interests of the Oromo struggle and unconvinced that our involvement with the faction would in anyway benefit the cause of the great Oromo people, we want to make public our decision to willingly withdraw from the leadership as well as membership of the faction of OLF led by General Kamal Galchu effective March 15, 2013," they said in a press statement.However, they warned that their withdrawal from OLF shouldn't be miscontrued as giving up on the struggle of the Oromo people for freedom and justice. "We will persevere... and join a platform that we believe would advance the Oromo people's legitimate struggle for freedom and justice," they said.