Saturday, December 21, 2013

የክፉ ቀን አለኝታዋ ትዝታ (በአበራ ለማ)


በአበራ ለማ
Click here for PDF

አበራ የማነአብ እና ገነት ግርማ

Ethiopian politicians Genet Girma and Abera Yemaneab
ከግራ ወደ ቀኝ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ እና አቶ አበራ የማነአብ
አንጋፋው የዲሞክራሲና የለውጥ አርበኛ፥ አበራ የማነአብ፥ የሰባ ሁለት ዓመት አዛውንት ናቸው። ከዚህ እድሜያቸው ውስጥ የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ባፈላማ ይዟቸው፤ ሃያ አምስቱን ዓመታት ባለም በቃኝና በቃሊቲ ወህኒ ቤቶች ቀርጧቸዋል። ከዚህ ውስጥ ባመክሮ ጥቂት ዓመታት አራግፈው፤ አሥራ ስድስት ዓመት ከስምንት ወራት በሕሊና እስረኝነት አሳልፈዋል። ደሞም ድፍን ሁለት ዓመታትን በጨለማ ቤት በመታገት፤ መራር ግፍና መከራን በመቋቋም፤ ከሞቱት በላይና ከቆሙት በታች በመሆን አቻ እንዳልተገኘላቸው ጉምዙ ትዝታቸው ያረዳናል፡፡
ይህም አልበቃ ያለው አጋች ክፍል አንዲት ጠባብ ክፍል ከሳምባ በሽተኞች ጋር የግድ እንዲጋሩ አድርጎ፤ ለሳምባ በሽተኝነት ዳርጓቸው ኖረዋል። ከዚህ ደዌ ለመፈወስ (ባገር ቤትም ሆነ በቅርቡ እዚህ አውሮፓ ከመጡ በኋላ) አጥብቀው ሕክምናቸውን በመከታተላቸው፤ ዛሬ በሙሉ ጤንነት ላይ ሊገኙ ችለዋል። ለሁለት ዓመታት በካቴና ታስረው እጨለማው ክፍል ውስጥ በሚማቅቁበት ወቅት የጃቸው ቆዳና ሥጋ ተበልቶ አልቆ፤ አጥንታቸው ገጦ ይታይ የነበረበትን የሰቆቃ ዓመታት ሲያስታውሱት እምባቸው ባይኖቻቸው ሙሉ ይሾማል። የኔ ብጤው ሆደባሻ አወያይ ደሞ፤ ሰቆቃቸውን ባይነ ሕሊናው ጭምር እየቃኘ፤ መግቢያ መውጪያው እንደጠፋበት የተከበበ አውሬ ጭንቅ ይለዋል።
“ለመሆኑ እኒህን በምድረ አሜሪካን ከተከበረ ቤተሰባቸው ጋር በሰላምና በተድላ ይኖሩ የነበሩን ትሁት ሰው ምን ተከርቸሌና ተቃሊቲ ወስዶ ዶላቸው?” የሚል መሪ ጥያቄ ያዘለ ሰው ብቅ ቢል አይፈረድበትም። የዚህ መጣጥፍ አቅራቢም ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤልጅግ ብቅ ብሎ በነበረበት ወቅት፤ ይህን ጥያቄ ለሞክሼው ለአቶ አበራ ማስቀደሙ አልቀረም ነበር። አካሄዱ እሳቸውንና እሳቸውን የመሳሰሉ ጎምቱ የፖለቲካው ዓለም ምህዋር አርበኞችን የሕይወት ታሪክ ውርስ ለተሰኘ የዘጋቢ ፊልም ግብዓት ለመቃረም ነበር። (ይህ ለመጪው ትውልድ ቅርስነት የሚቀመጥ የተንቀሳቃሽ ፊልም ዘገባ አገር ቤትና እውጭ የሚኖሩትን ተጠቃሽ ያገር ልጆችን አውደ ሰብእና የሚያካትት ነው።) እናም የዚህ መጣጥፍ አቢይ ጭብጥ የሆነው ጉዳይም የተጨለፈው ከዚያው ከታሪካዊው ጭውውትና ቃለ መጠይቅ ላይ እንደሁ ምስጢር ብጤ ላውጣ። የዚህ ሠናይ ሥራ ዋልታና ማገር የሆኑት ባልደረቦቼ ጋዜጠኛና የፊልም ባለሙያው ክብረት መኮንን፥ ረዳቱ ጋዜጠኛ ሥዩም ደገፋ ይሁንታቸውን አይነፍጉኝም በሚል ተስፋም ምስጢሩን ለተደራስያን ሳካፍል ለይቅርታ እጅ እየነሳሁ ነው።
አዎን… ወደ ተነሳው መሪ ጥያቄ ልመለስና “…ሞክሼ እንዲያው ምን እግር ጥሎዎት ለዚህ ዓይነት ዳፋ ተዳረጉ?…” ለሚለው ጥያቄዬ አቶ አበራ የማነአብ የክፉ ቀን ትዝታን ጀልባ እየቀዘፉ፤  ከአሥራ ሰባት ዓመታት በፊት የሆነውን ሁሉ አጫውተውኛል፡፡ በተፈጥሯቸው እርጋታንና ጸጥታን የተላበሰው ገጽታቸው፤ የዘመኑን አንዳንድ ቀዥቃዣ መነኮሳትና ጳጳሳት ያስንቃል። ታንደበታቸው የሚወጣው እጅግ ቁጥብ አስተያየትና ረጋ ያለው ትረካቸው፤ ሲጠጡት ተዋንጫው እንዳያልቅ የሚጨነቁለትንና የሚሳሱለትን የወይን ጠጅ ያህል ያስጎመጃል። ያውም ከጠይም የመልካቸው ቀለም ጋር እየተናበበ… እየተጨዋወተ… እየተሟዘቀ… [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ ( የዕለቱ ዜና ዘገባ )


የወያኔ ቡድን ከጦሩ ያሰናበታቸውና ከጦሩ የለቀቁ  መከታተያ ህግ አወጣ፣
የወያኔው የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ተብዬው አለማየሁ አቶምሳ ጤንነት እየከፉ መምጣቱ ተገለጸ፣
በደቡብ ሱዳን በጦር ሀይሉ ውስጥ በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች  የሚቆጠሩ ተገደሉ፣ 
በዙምባቤ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የደርጉን መሪ መንግስቱን ለማስኰብለል አሜሪካ ሚና እንደነበራት አመነ፣፣

    በመጨረሻም፣ ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ በሚል የቀረበውን ፅሑፍ እናሰማለን  በማስከተል የይቅርታና እና የሶሪ የሶሪ ባንክ የለንም በሚል ርዕስ የተላከልን አጭር የትዝብት ጽሁፍ እናቀርባለን በመጨረሻም አዕምሮ በለጠ ከአዲስ አበባ የሜኤሶንና የኢህአፓን ልዩነች የተላከ ፅሑፍ ክፍል አንድን አሰምተን የዝግጅቱ ፍፃሜ ይሆናል ፣፣

ዜናው ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑት፣ http://www.finote.org/Finot18_12_2013.mp3

የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን በማሰጠትና ለዜጎች ሞት የሚጠየቁት አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን ለቀቁ


የአማራ ክልል መሬቶች ለሱዳን እንዲሰጡ ከገዢው ሕወሓት ጋር በመተባበር ወንጀል፣ እንዲሁም ከጉራፈርዳ ተባረው ወደ አማራ ክልል የመጡ ዜጎች የሚቀበላቸው የክልል መስተዳድር ጠፍቶ ለርሃብና ለሞት በመዳረጋቸው በዚህም ወንጀል እንደሚጠየቁ የሚነገርላቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን አስረከቡ።
                 አቶ አያሌው ጎበዜ

መንግስታዊ ሚድያዎች አቶ አያሌው ጎበዜበመተካካትሂሳብ ስልጣኔን ተረክበውኛል ሲሉ ይዘግቡ እንጂ የአማራ ክልል ምክር ቤት በአስቸኳይ ተሰብስቦ ይሄን ውሳኔ ማጽደቁ ከበስተጀርባው የተደበቀ ምስጢር ሳይኖር እንዳልቀረ ብዙዎች ይገምታሉ። በተለይም አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ሰሞኑን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ጋር የኢትዮጵያን መሬቶች አሳልፈው ለመስጠት ከተፈራረሙ በኋላ የአቶ አያሌው ስልጣኔን ልልቀቅ ጥያቄ ምንልባትም ለሱዳን ከሚሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አስተያየታቸውን ለዘ-ሐበሻ ሰጥተዋል።
የአማራ ክልል አስቸኳይ ስብሰባውን ከትናንት ምሽት ጀምሮ በባህር ዳር ያካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ክልሉን ላለፉት 8 ዓመት ተኩል የመሩትን የአቶ አያሌው ጎበዜን ጥያቄ ወዲያውኑ በመቀበል ከስልጣን ያወረዳቸው ሲሆን በምትካቸውም በሕወሓት ተላላኪነታቸው ከአቶ ደመቀ መኮንን አይተናነሱም የሚባሉት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተተክተው ተሾመዋል።
                        አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ተሾመዋል። አቶ ገዱ የአማራ ክልል / ፕሬዚዳንትና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን አቶ አያሌው አልፈጽምም ሲሉ የነበሩ ሥራዎችን ለሕወሓት በማደር ይሰሩ እንደነበር እርሳቸውን የሚያውቁ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል። በተለይም አምባገነንና እኔ ያልኩት ይድመጥ የሚል ባህሪይ እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ ገዱ የአማራ ክልል ስር ያሉ የኢትዮጵያ መሬቶችን ለሱዳን በመስጠት ከሕወሓት ጋር አብረው እንደሚሰሩ ይጠበቃል።
አቤል የተባሉ በክልሉ የሚኖሩ በፌስቡክ -ሐበሻን የሚከታተሉ አንድ አስተያየት ሰጪ በሰጡት አስተያየትክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ክቡር አቶ አያሌው ጎበዜ ዛሬ በአቶ ደጉ አንዳርጋቸው የተተኩበት አስቸኳይ ጉባኤ አንደምታው ምን ይሆን? ምን አልባት ከሠሞኑ የሚሠሙ ወሬዎችን እልባት ለመስጠት ይሆን? ማለt ዐድርቃይን ለትግራይ፣ መተማን ለሱዳን፣ ጃዊ አካባቢ ያለ የአማራ ክልል ግዛቶችን ለመስጠት መሠናክሉን ከወዲሁ ለማቅለል ይሆን እንዴ? ምርጫ፣  ዘመን ሣይጠናቀቅ ከስልጣን አቶ አያሌውን ማንሣት ምን ማለት ነው? እርሣቸው ለክልሉ ልዑላዊነት መከበር ጥብቅና የሚቆሙ ታማኝ መሪ ስለነበሩ ገለል ለማድረግ የታለመ ሹም ሽር ነው የሚል ግምት አለኝብለዋል።
ሌላው የዘሐበሻ የፌስቡክ ተከታይም እንዲሁየአማራን ክልል መሬት ለሌላ አሳልፌ አልሰጥም በማለታቸው ስልጣናቸውን እንደለቀቁ ነውየማምነው ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተውናል።
አንድ ቀን በኢትዮጵያ ነፃነት ሲመጣ ምንም እንኳ እርሳቸው አልፈረሙም፤ የፈረሙት አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው የሚባል ወሬ ቢኖርም አቶ አያሌው ጎበዜ ለሱዳን በተሰጠው መሬት፣ በአማራ ክልል ለደረሱ ጭፍጨፋዎች፣ በዜጎች መፈናቀል ዙሪያ ላሳዩት ቸልተኝነት ለፍርድ ይቀርባሉ የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው።