Friday, October 17, 2014

ከኢንቨስትመንት በፊት ሰባዊ መብት ይከበር ::

ከኢንቨሰትመንት በፊት የሰባዊ መብት ይከበር በሚል ታላቅ ሰላማዊ ሰልፈ ዛሬ በኦስሎ ከተማ ተካሄደ

ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ በሚል  NABA(Norwegian African Business Association )  ባዘጋጀው የኖርወ ድርጀት ዛሬ በኦስሎ ከተማ ሴሚናር ተካሂዱኣል::
በዚ ሴሚናር ላይ የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴድሮስ አድሃኖም አንዲሁም በሲውዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር
ወይንሸት ታደሰ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የኖርዌ አምባሳደር ሚ/ር እንድርያስ ጋርደር በተገኑበት ስብሰባው ተካሂዱዓል::
ይህ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ  የሚለወን በመቃወም በርካታ ቁጥራቸው የበዛ ኢትዮጵያውያን የተቋሞ ሰልፍ ሲአደርጉ ቆይተዋል::
በዚ የተቋሞ ሰልፍ ላይ በኖርዌ የሚገኙ ተቋዋሚዎች የቀሩ አይመሰልም ነበር በአከባቢወ ከፈተኛ ጩህትና ተቃውሞ የበዛ ነበር ።
በሰዓቱ ይሰማ የነበረው መፈከር

፩) ከኢንቨስትመንት በፊት ሰባዊ መበት ይከበር
፪)  የታሰሩ ፖለቲከኞች ይፈቱ
፫)   ጋዜጠኝነት አሸባሪነት አየደለም
፬)   ኖርዌ የሲውዲንን ተሞክሮ ትከተል
፭)   የኖርዌ መንግስት የወያኔ መንግስት መርዳት ያቁም
፮)   የወያኔ መንግስት ዘረኛ ነው
፯)  ወያኔ ገዳይ ነው
     እያሉ ደምጻቸውን ሲያሰሙ ነበር።
                                                                          
የተቋሚዎች ተወካዮች የሰልፉን አላማ በተመለከተ የተዘጋጀወን መልክት ያለው ደብዳቤ ለኖርዌጂያን ተወካዮች አስተላለፈዋል።
http://www.ethiotube.net/video/32210/Ethiopins-Portest-in-OSLO-Norway--Respect-Human-Rights-Before-Investments-In-Ethiopia

https://www.youtube.com/watch?v=q45la5hBk7k

No comments:

Post a Comment