Tuesday, May 13, 2014

ዓባይ እንደዋዛ “ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው” (ክፍል ሶስት፣ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ)


አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)፣ ክፍል ሶስት
ክፍል ሁለት ዓባይና ኢትዮጵያ አንድና የተያያዙ መሆናቸውን ያሳያል። አንድና የተያያዙ ናቸው የሚለውን ሃሳብ ከተቀበልን ዓባይ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እስካገለገለናEthiopia's dam on Abbay/Nile river ኑሮውን እስካሻሻለ ድረስ የኢትዮጵያን ይገባኛልነትና የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች መቀበል የኢትዮጵያውያን ግዴታ ነው። ዓባይ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥሪት መሆኑን አምናለሁ። ጎሳዊ ወይንም ክልላዊ ሃብት አይደለም። ስለሆነም፤ ዓባይን የምንታደገው “ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው” ብለን እንጂ በጎሳ መታወቂያችን አይደለም። ከዚህ ጋር አያይዠ ለማሳሰብ የምፈልጋቸው ብዙ ትችቶች አሉኝ፤ ጥቂቶቹ። አንድ፤ የህወሓት መንግሥት ጎሳዎች እርስ በርሳቸው እንዲጨፋጨፉ ዋና ቀስቃሽ መሆኑ፤ ጭፍጨፋዎችና ዛቻዎች ሲካሄዱ ችላ ማለቱ ኢትዮጵያን ወደ አደገኛ ስርዓት ሰራሽ የእልቂት ጎዳና እየመራት ነው። አንዳንድ የውጭ መንግሥታት ለዚህ የእርስ በርስ ግጭት መጋቢ ሆነዋል። ሁለት፤ ዶር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝትዎች” በተባለው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊያነቡት ይገባል ብየ በምገምተው መጽሃፉ ያቀረበው ትችት ከፊታችን የተደቀነውን አስኳል የፖለቲካ ኃይሎች አሰላለፍ መጠላለፍ በግልፅ ያሳያል። ይኼም፤ ህወሓት ሆነ ብሎ ያገለላቸው አብዛኛውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚወክሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥቃቅንና ከለውጥ በኋላ ሕዝብ ተወያይቶ ሊፈታቸው የሚችለውን ልዩነቶች ወደጎን ትተው ሰብሳቢ ወደሚሆነው ወደ ማህል የሚስብ ዲሞራሳዊ አጀንዳ አለመቅረጻቸው ነው። አብዛኛውን ሕዝብ የሚወክለው “የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ፖለቲካ በዋናነት በሁለቱ ጫፎች ላይ ቆሞ ገመድ ከመጎተት ወደ መሃል መጥቶ የጋራ ዲሞክራቲክ አጀንዳ መቅረጽ አልተቻለውም። ብዙዎቹ ሂሳብ የመወራረድ ፖለቲካን የዛሬ 30 እና 40 ዓመታት ብቻ ሳይሆን፤ የዛሬ 130እን 140 ዓመታት በፊት የነበረውም ጭምር እንተሳሰብ የሚሉ ይመስሉኛል። የኦሮሞ ልሂቃን ዋናው ችግራቸው የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ ለመቅረፅ ከመጣር ይልቅ ለብቻ የሚደረገው ትግልን የመንግስተ-ሰማያት አስተማማኝ መንገድ አድርግው ማምለካቸው ነው። የአማራው ልሂቃን በሽታው በዋናነት በአማራ ልሂቅ የተፈጠረች የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደዛው እንድትቀጥል ነው። እምነታቸው መቀጠል ትችላለች ነው።” ከዶር መረራ ትችት ዋና ትምሕርት ነው ብየ የተቀበልኩት የኦሮሞን ልሂቃን የመገንጠል አምልኮ፤ ወይንም የአማራን ልሂቃን ኢትዮጵያን ወደ ነበረችበት ንጉሳዊ ወይንም ደርጋዊ ስርዓት የመመለስ ተልእኮ ሳይሆን የሁለቱ አንጋፋ ሕብረተሰብ ክፍሎች ልሂቃን ኢትዮጵያን ከመገነጣጠልና ከእልቂት አደጋ ለመታደግናን ሕዝቧን ዘላቂና ፍትሃዊ ወዳለው የእድገት መሰላል ለማመቻቸት እየተነጋገሩና እየተወያዩ የጋራ ዲሞክራሳዊ አጀንዳ ለመቅረፅ አለመቻላቸውን ነው። ይኼን ባለማድረጋቸው የውጭ ኃያላን መንግሥታት፤ በተለይ አሜሪካ በተናጥል ለሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍና ጠበቃነት ዋጋ አልሰጡትም። ወደፊትም ዋጋ የሚሰጡት አይመስለኝም።[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

No comments:

Post a Comment