Friday, April 11, 2014

ትግል እምቢታ እንጅ አቤቱታ አይደለም (ኢሕአፓ ወክንድ)


Ethiopian Peoples Revolutionary Party Youth League (EPRP YL)ምንም እንኳን ወያኔን እንቃወማለን የሚሉ ድርጅቶች ሁሉ ተቃዋሚ ሃይሎች በመባል በአንድ ጎራ ተጠቃለው ይታወቁ እንጅ በውስጣቸው የተሰሉፉት ሃይሎች አንድ አይነት የትግል ስልትም ሆነ ብሄራዊ ራዕይ ያላቸው እንድልሆኑ ግልፅ ነው። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በጥገና ለውጥ ስርዓቱ እንዲሻሻል ማስገደድ ይቻላል የሚሉ፣ ሌሎች ደግሞ ስርዓቱ መቀየር አለበት የሚሉ፣ ነገር ግን የሃገሪቱን ሉአላዊነት ግምት ውስጥ የማያስገቡና የባዕዳንን የቆየ ተፅዕኖ በአዲስ ቀለም ለማስቀጠል የሚፈልጉና ዴሞክራሲን ከይስሙላ ምርጫ ጋር ቀላቅለው የሚያዩ፤ ጥቂቶች ደግሞ መገንጠልን በግልፅ እሚያራምዱ ወይም ይህንኑ ዓላማ በአዲስ ቋንቋ አለዝበው ሁኔታው እስኪመቻች የሚጠብቁና ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ነን ቢሉም እነዚህኑ ክፍሎች የሚያግዙና የሚያበረታቱትንም ያጠቃልላል። ከነዚህ ሁሉ ተለይተው የቆሙት ሃይሎች ደግሞ፣ ያለው አገዛዝ ከስረ መሰረቱ መነቀል ያለበት ብሄራዊ ጠላት በመሆኑ የሚያምኑና፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነባው፣ ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑ የሚረጋገጠው፣ እንዲሁም የሀገሪቱ አንድነትና ሉአላዊነነት የሚጠበቀው ስር-ነቀል በሆነ ለውጥ ብቻ ነው በሚል የሚገፉትን በሌላ በኩል የያዘ ሰፊ ጎራ ነው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

No comments:

Post a Comment