Saturday, April 19, 2014

የ2007ቱ ምርጫ በተቃረበ ቁጥር የወያኔ አፈና፤ እስርና እንግልት እየጨመረ መሆኑ ተነገረ


በትጥቅ ትግል እንፋለመዋለን የሚሉትን ሀገር ወዳድ ሃይሎች ሁሉ በታዛዥ ባርለማው “ሽብርተኞች” ያለውና በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን የሚሉትንም “እንዳለመታደል ሆኖ ጠንካራ ተቃዋሚ የሉንም” ሲል የነበረው ሕወሃት መራሹ ወያኔ በ2007 ዓ/ም ይደረጋል ተብሎ ከሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ እጅግ ቀድሞ እየታየ ያለውን የሀገር ውስጥ ተቃዋሚዎችን የተደራጀና ጠንካራ እንቅስቃሴ መቋቋም ባለመቻሉ ወደ አፈናና እስራት እየተሸጋገረ መሆኑ ታወቀ።
በተቃዋሚው በኩል የተጠየቁ ሰላማዊ ስፎችን ከመከልከል ጀምሮ የተፈቀዱትንም በተለያዩ መንገዶች እስከማደናቀፍ የደረሰውና በነጻ ውድድር የማያምነው ፋሽስት ወያኔ ሰልፈኞችን ማዋከብን ጨምሮ በመደብደብና በእስራት እያንገላታ መሆኑን ተጎጅዎች አጋለጡ።
በአዲስ አበባና በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው የተቃዋሚዎች ከፍተኛ እንቅስቃሴ አልጋ ባልጋ እንዳልነበር የሚጠቅሱት አንዳንድ ታዛቢዎች ሆኖም ግን አሁን ሕወሃት መራሹ ጉጅሌ እየወሰደው ያለው እርምጃ ተስፋ የመቁረጥ ይመስላል ይላሉ።
ከዚህ በፊት ተቃዋሚዎች ሰልፍ ወይም ስብሰባ ሲጠሩ ሕወሃትም በጎን ሌላ ዝግጅት በማዘጋጀት ባልመጡት ላይ ከፍተኛ ቅጣት በመጣል ያስፈራራ እንደነበር ያስታወሱት ታዛቢ በዚህ መንገድም አልሳካ ያለው ይህ አገዛዝ ወደ ስብሰባም ሆነ ወደ ሰልፍ መውጫ ቦታዎችን በወታደር በማዘጋት ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ለማደናቀፍ ሙከራ አድርጓል ብለዋል። ሆኖም ግን ይህ ሁሉ ባለመሳካቱ የተነሳ ሰዎች እየተመረጡና እየተጠኑ ወደ እስር ቤት መጋዛቸው ቀጥሏል በማለት የህወሃትን አፈና ያማራራሉ።
በአዲስ አበባ የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲ አባላት እስር ቤት ገብተው እንደነበር የተጠቆመ ሲሆን በትግራይ ደግሞ የእረና ፓርቲ ሰዎች በተደጋጋሚ እስርቤት እንዲገቡ ተደርጓል ተብሏል። ይሁን እንጅ ይህን ሁሉ አፈናና እስራት በመጋፈጥ አረና በትግራይ አንድነት ፓርቲ ደግሞ በደሴ የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርህ ውጤታማ የነበረ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል

No comments:

Post a Comment