Wednesday, February 12, 2014

በኖርዌ የሚገኙ የወያኔ ጉጅሌዎች ኢትዮጽያ ውስጠ ወገኖቻችንን አፍነው ዓገራችንን በመረጃ ፅልመት ውስጥ አንድትቀመጥ የሚጫወቱት ሚና ሳይሳካላቸው ቀርቷዋል ።


       በትሮንዳሂም ከተማ ሲዘጋጅ የነበረው ኢሳት የኔነው ዝግጅት በዓስደሳች ሁኔታ                                      ተጠናቋል።
   

ኢሳት የኔነው ዝግጅቱን በተለያዩ መንገዶች ለማክሽፍ ያልተሳካላቸው በኖርዌ የሚገኙ የወያኔ ጉጅሌዎች ኢትዮጽያ ውስጠ ወገኖቻችንን አፍነው ዓገራችንን በመረጃ ፅልመት ውስጥ አንድትቀመጥ የሚጫወቱት ሚና ሳይሳካላቸው ቀርቷዋል ።

በዓገር ወዳድ ኢትዮጽያዊያን የተዘጋጀ እና አስደሳች በሆነ ሁኔታ የተጠናቀቀው ኢሳት የኔነው በሚል መርሆ በመነሳት በመካከለኛው ሰሜን ኖርዌ የሚገኙ የኢሳት ቤተሰቦችን ያሳተፈ ልዩ ዝገጅት ሲሆነ ለዘግጅቱ መሳካት ኮሚቴዎች የበኩላቸውን ዓስተዋፆ ዓድርገዋል ።
በዓገሪቷ የመሬት አቀማመጥ ምክንያት አንድ ላይ ለመኖር አመቺ አለመሆኑ ሳይገድባቸው ዝግጅቱን ለመካፈል ከያሉበት ቦታ በመሰባሰብ የኢሳት ቤተስቦች መሆናቸውን የኢትዮጽያዊያንን አይን እና ጆሮ የሆነውን ኢሳትን በመደገፍ ወገናዊነታቸውን ዝግጅቱ በተካሄደበት በትሮንዳሂም ከተማ ተገኝተው አሳይተዋል ።

ከ100 ሰው በላይ በተገኘበት ይሄው ኢሳት የኔነው ዝግጅት የፕሮግራሙን መጀመር የሚያበስረውን በኮሚቴው ተወክለው ተጋባዥ እንግዶች እንኳን ደና መጣችው በማለት ለ10 ደቂቃ ያህል የዝግጅቱን አላማ በተመለከተ ሲያብራሩ ቆይተዋል በመቀጠልም ተጋባዥ እንግዶች የሆኑት:-
የኢሳት ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን ከአምስተርዳም ተመልካቾችን ያሳተፈ ሰፋ ያለ ዉይይት   ይዛልን ቀርባለች።
ዶ/ር ሙላለም ዓዳሙ ከኦስሎ በዓንድ አገር እድገት ላይ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ሁኔታሆች ላይ የብዙሃን መገናኛ ሚዲያ ስለሚኖረው ፋይድ ገለፃ አድርገዋል።
አ/ቶ አበበ ደመቀ  የኢሳት ተወካይ ኖርዌ ከኦስሎ ቅርንጫፍ ጣብያው በዘላቂነት አንዲጎለብት የሚያስችለውን በኖርዌ ዓገር የተያዘውን እቅድ አቅርበዋል።

በዝግጅቱ ላይ  ስለኢትዮጽያ ወቅታዊ እና አንገብጋቢ ጉዳይ የተነሳ ሲሆን አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ፕሮግራሞች ዓገር ወዳድ በሆኑ ኢትዮጽያዊያን ቀርቧል።
በተጋባዥ እንግዶች አስተማሪ እና ወቅታዊ የሆኑ የተለያዩ ንግግሮች የቀረቡ ሲሆን እንዴውም ባዘጋጅ ኮሚቴሆች የቀረቡ የተለያዩ ንግግሮች ተመልካችን ያስደመመ ነበር።

በመቀጠልም በዝግጅቱ ድምቀት ዓስተዋፆ ያደረገው በራሄል ኤፍሬም ተፅፎ በሪያድ ኢብራሂም የተቀነባበረው 11ሰው የተሳተፈበት ኢትዮጽያዬ የሚል መጠርያ ያለው ድራማ ሲሆን ዓገራች ስላለችብት ከባድ ችግር የሚያሳይ ሲሆን በዚህ ከፉ መንግስት ታፍና እንባ በተናነቀው ድምጽ ለልጆቿ የይድረሱልኝ ጥሪ ስታሰማ ታይቷል በመቀጠልም ከተለያዩ ብሄር የወጡ ልጆቿ ለእንባዋ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል የኢትዮጽያ ሳተላይት ቴሌቭዥን(ኢሳት)የያዘውን እውነት እና የኢትዮጽያ ቴሌቭዥን(ኢቲቭ) ውሸት በማጉላት ተመልካቾችን እያዝናና እውነታውን እንዲገነዘቡ እንዲውም የዓገራችንን መሬት በመሸንሸን ሲቸበቸብ ቆርጦ የተነሳው ጨካኙ እና አረመኔውን መንግስት በዓማራው ህዝብ ላይ የሚደረገውን ግፍ፣ስቃይ፣ መንከራተት፣የዘር ማጥፋት እርምጃ እና በገዢው መንግስት ላይ ያለውን የስነምግባር ጉለት በይፋ አሳይተዋል ።
በመቀጠልም በወጣት ሪያድ እና ሐይለሚካዬል የቀረበው መነባንም አስተማሪ እና ተመልካቾችን ያዝናና ሲሆን የተለያዩ አስደሳችና ማራኪ ስራሆች ቀርበዋል።

ወደ መድረክ ስትገባ ነበር የተመልካችን ቀልብ የሳበችው ባገር ባህል ልብሷ ዓምራ እና ተውባ ወደ መድረክ ብቅ ያለችው እንግዶችን እያስፈነደቀች ለናት ዓገራቸው ዓለንልሽ ብለው ከጎና በመቆም የዓገር ፍቅር አንዲያሳዩ እና ተመልካቾችን ያሳተፈ ሰፋ ያለ ዉይይት ይዛልን በመቅረብ የዝግጅታችን ቅመም በመሆን ዓብራን ያመሸችው የኢሳት ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን ነበረች

ሴቶች ከማጀት ስራ በስተጓዳኝ በፖለቲካው ያላቸው ትልቅ ሚና የሚያሳይ በራሄል ኤፍሬም የቀረበ ሲሆን
የሴቶች ዓስተዋፆ የሚያብረከተውን ትልቅ ሚና ከጥንት ጀግና እናቶቻችን ጋረ በማመሳሰል በቤት ውስጥ ያለባቸውን የስራ ጫና እና ልጅን የመንከባከብ አላፊነት እየተወጡ ለዓገራቸው ያላቸውን ፍቅር  እና ዘብ በመቆም ያሳዩትን ምሳሌ በመውሰድ ለዓገራችንን በመቆም የራሳችንን ዓሰተዋጾ እንወጣ በማለት ደምድማለች::
በመጨረሻም አዝናኝ እና አስተማሪ ጉዳዮችን በማንሳት ውይይት የተደረገ ሲሆነ በተለያዩ ሙዚቃሆች ዝግጅቱ ተጠቃሏል።

No comments:

Post a Comment