Wednesday, January 15, 2014

ኢትዮጵያዊነታችን ከአማራ ና ከኦሮሞ የዘር ፖለቲካ የላቀ ነው መሆንም አለበት፣፣

    by Nathnael abate      
ሚኒልክን መሃል ያደረገ ፖለቲካዊ ጽንሰ ሃሳቦች በአማራዎች ዘንድ እንደጀብዱ እና በኦሮሞዎች ዘንድ እንደዉርደት፣ማንነት እንደማጣት ተደርጎ ሲያነታርክ፥ስነታረክበት ሰንብቷል፣፣የሃገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞችም ይህንን መሰረት ያደረገ ፖሌቲካዊ ሃሳብ ሲያራምዱ ይታያሉ፣፣
 ይህ በዘር የተመሰረተ ሃሳብ ኢትዮጵዊነታችንን ከዉስጣችን እያጠፋ ይገኛል፣፣ በመጀመርያ ኢትዮጵያዊነታችን የዉስጥ ደማችን ማንነትና የእኛነታችን መገለጫ እንጅ የዘርና ጎሳ ሃረጋችንን እየቆጠርን እርስበርስ የሚንበላላበት የጥላቻ መለያ ሥም ወይም መሳሪያ አይደለም፣፣
እግዲህ ስለሚኒልክ ካወራን እንደማንኛዉም መሪ መልካምና ክፉ ሰርቶ አልፏል፣፣ ነገር ግን አንድ መታወቅ ያለበት ነገር እሱን በሚያደቁና በሚከተሉ ሰዎች ዘንድ ተደጋግሞ የሚነሳዉ የአድዋ ድል የሚኒልክ ብቻ ተደርጎ የሚወስድበት ሁኔታ ይስተዋላል ሆኖም ድሉ የሚኒልክ ወይም የአማራ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ፣የአማራ ፣የወላይታ ፣የሲዳማና የለሎች የኢትዮጲያ ህዝቦች ታርክ መሆኑ መታወስ ያለበት ጉዳይ ነዉ፣፣
ሚኒልክን ለምትጠሉና እንደሰይጣን የሚታዩ ወገኖች ያ ያለፈ ታርክ እያላዘናችሁ ልዩ ነ ት ለማስፋት አትጣሩ፥ ይልቁንስ ያ የትናንት ታርክ እኛን ይበልጥ ያቀራርበን፥አንድ የጋራ ታርክ እንዳለን አስባችሁ ወደፊት በአንድነት የተመሰረተ ጠንካራ ማህበራዊ፥ኢኮኖሚያዊና ፖሌቲካዊ ስርዓት ያለበት ሃገር ለመመስረት ስላለፈው ሳይሆን ስለወደፍት አስቡ፣፣
እንድሁም ሚኒልክን እንደመላአክ የሚታዩ ወገኖች የለሎችን ማንነት ባለመቀበልና የአጼዎችን ጉራ እየነዛችሁ፣ሃገርን ለማፈራረስ የሚትሞክሩን ነገር ከእንግድህ አብቁ፣፣ ባሁኑ ሰዓት ሁሉም ኢትዮጲያዊ ታርኩን ጠንቅቆ ያዉቃል ክፉ ና ደግ መች እንደደረሰበት፣፣
ስለዚህ፣ወደፊት በርግጥ የተሻለ ነገር ለሃገራችን የሚንመኝ ከሆንን፣ስላለፈዉ የአጼዎች ዝና በመጎረርና የአጼዎችን በደል በመዘርዘር፣ ዘረኝነትና ጎሴኝነት ከማራመድ ታቅበን በአንድነት ጠንካራ ሃገር ለመመስረት እንነሳ፣፣

ባሁኑ ሰዓት ለሃገራችን ጠላት፥ለህዝባችን ዉርደት ያለፈዉ ታርክ ሳይሆን ወያነ ነው፣፣ ወያነ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ ቀንደኛ ጠላት ነዉ፣፣ ወያነን በህብረት እንዋጋ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

No comments:

Post a Comment