Sunday, December 1, 2013

የጅዳ ሸረፍያ እስከ ሽሜሲ የተሰማው የወገን ዋይታ (ነቢዩ ሲራክ)


jiddah

ፈታኙን ወቅት ለማለፍ …
የሳውዲ የምህረት አዋጅ አልቆ በሪያድ መንፉሃ ላይ አለምን ያሳዘነ ሰቆቃ ተፈጸመ …ስጋት ነግሶ ፣ ኑሮ ከብዶን ጨንቆን ጠቦን ከርመናል ! በዚህ ክፉ ቀን ወገን ወገኑን ለመርዳት ደፋ ቀና በማለቱ ረገድ የሃገሬ ልጅ ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁጭት ስሜት ሲንቀሳቀስ የፖለቲካው ትኩሳት ወላፈን እያጓተተን አልሰነበትንም አይባልም። ግልጥልጥ አድርግን እናውራ ካልን የኑሮ ውድነት እና ድህነቱ እየደቆሰን ቢያስቸግረን ከወገን ቤተሰቦቻችን ተለይተን ፣ የእማማ ኢትዮጵያውያን ምድር ለቀን በስደት ስንባዝን በደረሰብን የከፋ አደጋ ለመቋቋም ከምናደርገው ትግል ባልተናነሰ ልዩነትን የሚያገዝፉ መሰናክሎችን ማለፉ የከበደ አበሳ ሆኖብን ሰነባብቷል!
Read story in PDF. የማለዳ ወግ …የጅዳ ሸረፍያ እስከ ሽሜሲ የተሰማው የወገን ዋይታና እዚህ ያደረሰን መንገድ!

No comments:

Post a Comment