Tuesday, November 12, 2013
ብሄራዊ ውርደት፤ የምንመጻደቅበት ‘ሌጋሲ’ (ክንፉ አሰፋ)
ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል[1]። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው። በስውር ሳይሆን በግልጽ። እንደ ኦሽዊትስ በታጠረ የማጎርያ ካምፕ ሳይሆን በአደባባይ።
ሰው ከሞተ በኋላ ለምን ሙት አካሉን ማሰቃየት አስፈለገ? ምን አይነት ጭካኔ ነው? ምን አይነትስ ጥላቻ ነው? ለሳውዲዎች ግማሽ ፈረንሳይን የሚያህል መሬት ሰጥተናቸው የለም እንዴ? ሀጥያታችን ምኑ ላይ ነው ታዲያ? አስከሬኑን ውሻ፣ ውሻ ሲሉ ሲሳለቁበት ከማየት በላይ የሚያም ነገር የለም። በአደባባይ እንደዋዛ የተጣለው አስከሬን በእርግጥ የዉሻ አስከሬን ቢሆን ኖሮ የእንስሳ ተከራካሪዎች አለምን ቀውጢ ባደረጓት ነበር። Read full story in PDF…
EMF
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment