Saturday, October 5, 2013

ወዮዉልህ ወያኔ የፍርድ ቀን ቀርቦልሃል


           መስከረም 05/2013
            ናትናኤል አባተ(nathy de saint)

  የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ገቢማሰባሰቢያ ዝግጅት ወቅት የወያኔ ተላላኪ ቡችላዎች ባሉበት መንጫጫታቸዉና፣ የተለያዩ ቦታዎች ስለዝግጅቱ አሉባልታ ወሬዎችን ስያናፍሱ ስለነበር ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፍት ሁለት ነገሮች ትኩረቴን ስቦው ነበር ፣፣ አንደኛዉ ምክንያት ዝግጅቱ ቢሳካ ወያኔ ምን እንደምሆንና ሁለተኛዉ እነሱ እንደተመኙት ዝግጅቱ ባይሳካስ የሚሉ ሃሳቦች ነበሩ፣፣ ምኞታቸው ከስሞ ሴራቸዉ ከሽፎ  ዝግጅቱ ከተጠበቀዉ በላይ በከፍተኛ ስኬት መጠናቀቁ ምን ያህል እንቅልፍ እንደነሳቸዉ ለማወቅ ፈለኩ፣፣ የዛን ቀን ማለትም ሴፕቴምበር 28 የስብሰባው ቀን ማታ እርስበርስ እንደተደባደቡ ሰማሁ፣፣ ከአካላዊ ጉዳታቸዉ በላይ ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳትና የወደፍት ተስፋ ማጣት ክስረት እንደደረሰባቸው የተከሰተዉ ነገር ያሳያል፣፣ ይህም እርስ በርስ የምለያይ መንግስት ይጠፋል የምለዉን የመጻፍ ቅዱስ ቃል አስታዎሰኝ፣፣

ወያኔ የምተማመንበት የስለላዉ መሃረብ የቱንም ያህል ጠንካራ ቢሆን፣እስከ የትም ድረስ ብዘረጋ እዉነተኛ እትዮጵያዊነትን፣የነጻነት ታጋይነትን ከታጋዮች ዉስጥ ማጥፋት ወይም ማቆም አልቻለም፣፣ በአሁኑ ሰአት ቃልቲና ለሎች ወህኒ ቤቶች ዉስጥ ከምገኙ ታጋዮች ጀምሮ በዱር እስከሚገኙ ተዋግዎች ድረስ የተለያዩ የነጻነት ታጋዮች በየሃገሩ በየቦታዉ አሉ፣፣ ከስሩ የበሰበሰ ከላዩ የቆመ የሚመስል የወያኔ መንግስት ይሄ ሁላ ተቃዉሞን መቋቋም ስለማይችልና መዉደቅያዉ እንደደረሰ ስለሚያዉቅ ባለበት ለመቆየት የማያፈናቅለዉ ድንጋይ የለም፣፣ የነጻነት ጎህ ለሃገራችን መቅደድ ጀምሯል፣፣ስቃያችን አብቅቶ በሃገራችን ተከብረን የምንኖርበት ጊዜ ፣በገዛ ሃገራችን እንደሁለተኛ ዜጋ የማንታይበት፣ መሬታችን ለባዕዳን የማይስጥበት፣ዜጎች የማይፈናቀሉበት፣ እኩልነት፣ፍትህ፣ነጻነት የሰፈነባት ሃገር እንድትኖረን ወያኔን የሚንዋጋበት ሰዓት አሁን ነዉ፣፣ ያለምንም ማመንታት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እጅ ለእጅ ተያይዞ የወያኔን እድሜ ማሳጠር ያስፈልጋል፣፣ በተለያዩ ቦታ ያሉ ኢትዮጵያዉያን የተለያዩ አጥጋቢ ገንቢና ወቅታዊ መረጃዎችን በመስጠት፣በማስተላለፍ ድጋፉን ማሳየት አለበት፣፣ የነጻነት ትግል ጉዞ ከባድ ሊሆን ይችላል ግን እያንዳንዳችን የየበኩላችን ብናደርግ ይበልጥ ይቀላል አንድነት ሃይል ነዉ ባንድነት እንገንባ ሃገራችንን፣፣ የየበኩል ትግል ከትንሹዋ ብዕርና ወረቀት አንስቶ ፣ጊዜ ገንዘብ ጉልበትና እስከ ህይዎት መስዋዕትነት ሊጠይቅ ይችላል፣፣ አፋኙ የወያኔ ስርአት ሃገር ዉስጥ ያሉ ትግሎችን ለማፈን ቢሞክርም ትግሉን መግታት አልቻለም ለወደፍትም አይችልም የማይችልበት ምክንያት ኢትዮጵያዊነት የላያችን ሽፋን ሳይሆን የዉስጣችን የስጋና ነፍስ ጉዳይ ነው፣፣ አባቶቻችን በኢትዮጵያዊት መንፈስ ጥንካሬ ነው ጣሊያኖችን ከአፈር የቀላቀሏቸዉ፣፣ወያኔ በመግደል በማሰር በማስፈራራትና የተለያዩ ስቃይና እንግልት ብያደርስም እዉነተኞቹ ኢትዮጵያዉን ባሉበት በሄዱበት ትግላቸዉን አላቁዋረጡም፣፣ የትግላቸዉን ፍሬም ማየት ጀምሯሉ፣፣

     የአምባገነኑ ወያኔ መንግስት ስም አጥፍዎቹ ተላላኪ ቡችሎቹ በተቻላቸዉ አቅምና መልኩ የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ስም ሲያጠፉና የሀሰት እምቢልታቸዉን ሲነፉ ነበሩ፣፣ የሃሰት ነጋሪት ከጎሰሙት መሃከል http://www.abesha.no/P%C3%A5-Amharisk/1372 ይሄ ድህረ ገጽ አንዱ ነዉ፣፣ባለቤቱ Av Girmay Assemahegn እንደሆነ የሚገምተው ይህ ድህረ ገጽና ባለቤቱ ታማኝ የወያኔ ቡችሎች ናቸዉ፣፣ታድያ የጮሄ ዉሻ ሁሉ አይናከስም እንደሚባለዉ ወያኔዎች ተንጫጩ እንጅ ዝግጅቱን ማቆም ወይም ማስተጓጎል አልቻሉም፣፣ ሴፕተምበር 28 ቀን ማታ እኛ የኢትዮጵያዉያን ቤት የደስታና የሃሴት ከበሮ ሲመታ የወያኔዎች ቤት ደግሞ ታላቅ ለቅሶ ሆኖ የሃዘን ድንኳን ተተክሎ ነበር፣፣  ወዳጆቼ ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች እኔን ከምንም በላይ የምገርመኝ እነኝህ ወያኔዎች የሃሰት ዉንጀላና የዉሸት መንፈስ ተጠናዉተባቸዉ ከሃገር ርቀዉ ድንበር ተሻግረዉ መተዉ እንድህ አይነት የሀሰት ብዜቶችን ማናፈሳቸዉ፣ እኩይ ተግባራቸዉን በገሃድ የሚያሳይ ከመሆኑም በተጨማሪ ይህ ወያኔ የሚሉት ነገር በማፈንና በጉልበት ሃሰትን እዉነት አድርጎ የሚገዛ፣ እውነት የሚባል ነገር  በዉስጡ የለሌ ሃሰታዊ ገዥና የሀሰት ስርዓተኛ ነው ነው፣፣ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ይህንን ያህል ተቀባይነት ማግኘቱንና፥ ስብሰባው በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን ሲያዉቅስ ዎያኔ ምን ይሆን? እንግዲህ በሰላማዊ ትግል ማመን ያልቻለ ወያኔ በሚገባዉ ቌንቌ ምላሽ እየተሰጠዉ መሆኑንና ምላሹም በጅማረው ይሄን ያህል ድል ማግኝቱ ራስምታት እንደሚሆንበት እርግጠኛ ነኝ፣፣ ዘርን ከዘር፥ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር ሲያባላ የኖረ ኢ_ሰብአዊዉ ወያኔ የመጨረሻ ቀናቶቹ እንደቀረቡለት ያዉቃል፣፣ ወያኔ በሄደበት ሁላ እንደ እብድ ዉሻ መጮሁና ለመናከስ ጥርሶቹን ማሾሉ ሃገር ጉድ የሚያብስል  ሌላኛው ባህሪዉ ነው፣፣ለነገሩ ወያኔና እብድ ዉሻ አንድ ናቸዉ አንድነታቸዉም ሁለቱም ከዱር መሆናቸዉና አራዊታዊነታቸዉ ነዉ፣፣

ያም ሆነ ይህ አንድ ወያኔ ማወቅ ያለበት ነገር ግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከወያኔ ጋር በሚያደርገው የትግል ጉዞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ጋር መሆኑን እንድሁም ህዝባዊ ሃይሉ ድል እንደምቀዳጅ ማወቅ አለበት፣፣የንጹሃን ደም የድሃዎች እምባ የሚስኪኖች ጩሄት የእናት ኢትዮጵያ እሮሮ ፍትህ የሚያገኝበት ጊዜ ደርሱዋል፣፣ታፍኖ ቁጣውን በትዕግስት ሸሽጎ የኖረ ህዝብ፣ በአያት ቅድመአያት ተከብሮ የኖረዉ ማንነቱ የተዋረደበት ያ ያገረ ሰው ተነስቱዋልና ወዮለት ለወያኔ!!  ታላቁ የፍርድ ቀን በወያኔ ላይ ደርሷል የፍርድ ቀን ዳኞቹ የእትዮጵያ ህዝቦች ናቸዉ፣፣ ክብሩን የተገፈፈው፣ማንነቱን ያጣዉ፣የወላድ መካን የሆነዉ ህዝብ፣አርሰዉና አርብተዉ የተራበ ያ ህዝብ ይፈርድበታል ወያኔ ላይ፣ ፍርዱም ይሄዉ ተጀመረ፣፣                                      

                                                                                      ወያኔ ይውደም
                                                                                     ኢትዮጵያ ትቅደም  
                                                                                   ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!!!
ጸሃፊዉን በዚህ አድራሻ ያገኛሉ;- nathanialoret@gmail.com

Twitter;- @nathysaint

Facebook;- Nathy De Saint

No comments:

Post a Comment