Friday, July 12, 2013

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ከባድ ተቃውሞ ገጠማቸው !

 ህዝብን ከመግስት ጋር ለማጋጨት እየፈጸሙ ባለው ደባ አንባሳደሩን ጨምሮ አንዳንድ ዲፕሎማቶች ከቦታቸው እንዲነሱ ተጠየቀ።

እሁድ ቀን Aug 7 2013 ሪያድ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ በተጠራው ስብሰባ አንባሳደሩን ጨምሮ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እየፈጸሙ ያለውን ግፍ እና በደል ህዝቡ በዝርዝር በመግለጽ ቅሬታ እና ተቋውሞውን አሰምቷል። በተለይ ከህዝብ አይታ ተሸሽገው የከረሙት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አንባሳደር ክቡር መሃመድ ሃሰን በወቅቱ ከተሰብሳቢው ከሚሰነዘርባቸው ሂስ ለማምለጥ፡ ሲሞክሩ መያዛቸውን የሚገልጹት ውስጥ አዋቂ ምንጮች አንባሳደሩ ከተስበሳቢው በቀረበ ጥያቄ መሰረት እንደ ተራ ሰው ተደብቀው ስብሰባውን የከታተሉ ከነብረበት ቦታ ተነስተው እስከ ዛሬ አይቶቸው ለማያውቀው ህዝብ እይታ በክብር መድረክ ላይ እንዲወጡ በመጋበዝ በአንባሳደሩ የአስተዳደር ድክመት አንዳንድ ዲፕሎማቶች ህዝብ እና መግስትን ለማራራቅ እየፈጸሙ ያለው ደካማ ጎን በነዋሪው ተዘርዝሯል።

በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች የሃገራችንን በጎ ገጽታ የሚያጎድፉ ጸያፍ ተግባራት በጥቂት ስረአት አለበኛ ወገኖች ሲፈጸም እንደ ሃገር ተወካይነታቸው ቀድመው እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የዝሆን ጆሮ ይስጠን በሚል ግትር አቋማቸው ዛሬ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት አሳፋሪ ገጽታ ላይ መድረሱን ተከትሎ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የዜጎች በሰላም የመኖር ዋስትና አደጋ ላይ ለመውደቅ ግንባር ቀደም ምክንያተ መሆናቸው ተወስቷል ።

የሪያድ ማህበረሰብ በነዚህ ዲፕሎማቶች ደባ ከኮሚኒቲው ማህበር እንዲረቅ የተደረገበት ምክንያት ለህዝበ ነዋሪው እስካሁን እንቆቅልሽ መሆኑንን የተናገሩ አንድ አስተያየት ሰጪ « የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ቀደም ሲል ከህዝብ ጋር ለመገናኘት በብሄር አዋቅሯቸው የነበሩ የልማት ማህበር ማዕከላት በዲፕሎማቱ አውቆ አጥፊነት በአባላቱ መሃከል መቃቃርን በመፍጠር ጽ/ ቤቶቹ ታሽገው ከ10ሺህ አባላት እንዳሉት የሚነገርለት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጥቂት የነሱ ተላላኪዎች ብቻ የሚርመሰመሱበት ከመሆኑም ባሻገር በነዚህ ዲፕሎማቶች አይዞ ባይነት የኮሚኒቲው ቀዋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ላይ አይን ያወጣ ምዝበራ እና ዘረፋ ስፈጸም « ለምን »ብለው የጠየቁ የኮሚኒቲውን አባላት በመንግስት ዘንድ እንደ አመጸኛ እንዲታዩ በማድረግ ህዝበ ነዋሪውን የባለቤት ነት ስሜት እንዳይሰማው አድርገዋል ብለዋል»።

በሌላ በኩል ትላንት በከፈተኛ ወጪ በሪያድ የአንባሳደሩን ቤት ጨምሮ ለኤንባሲ አገልግሎት የሚውል ታቦት ቀረሽ የተንጣለለ ህንጻ አሰርቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስረከበን ታላቅ ( ማህበረሰብ ) ድርቅ እና የሃገራችን ዳር ድንበር ተደፈረ ሲባል የገንዘብ ድጎማ ከማድረግ አንስቷ እስከ ህይወት መስወአትነት ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን በደጀንነት እንደቆመ እና ወደፊት በማንኛውም ጉዳይ እንደሚቆም የሚነገርለትን ጨዋ የሪያድ እና አካባቢው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ «ከአባይ ግድብ በፊት ድምጻችን ይሰማ » ማለቱ የትህምክትኝነት አባዜ ተጸናውቶት ሳይሆን በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች የአስተሳሰብ ውጤት በህዝብ ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተጽዕኖ መሆኑንን አብዛኛው ወገኖች ይገልጻሉ።

በተለያዩ ግዜያት በሚከሰቱ የሃገራችን ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ወቅታዊ ጉዳዩች ዲፕሎማቱ ከማህበረሰቡ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ የሃገራችንን ህገ-መንግስታዊ ጽንሰሃሳቦች መሰረት አድርገው ዝቅ ብለው ህዝብን ከማነጋገር ይልቅ ይህን ልማታዊ የሆነን ወገን በመናቅ እና በማንቆሸሽ ሲሻቸው በማስፈራራት አሊያም እንደ አመጸኛ እና አጥፊ በመፈረጅ ለመንግስት በሚያቀርቡት የተሳሳተ መረጃ ማህበረሰቡ ከመንግስት ጋር የነብረውን መልካም ግንኙነት እንዲሻክር አድርገዋል። ለዚህም በቅርቡ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ በአሰሪዎቻቸው ይደርስባቸው ከነበረ ስቃይ እና እንግለት ለመታደግ ጠፍተው ህገወጥ፡በሆነ መንገድ ከእጅ ወደ አፈ የሆነ ኑሯቸውን የመሩ ከነበሩ እህቶቻችን ጉሮሮ «ደሃ የሚበላው እንጂ የሚከፍለው አያጣም» በሚል ምጸታዊ አስተሳሰብ ፓስፖርቶቻቸውን ለማሳሳደስ እና ለመቀበል ወደ ኢትዮጵያ ኤንባሲ የጎረፉ እህቶቻችንን ለአባይ ግድብ የሚውል ቦንድ መግዣ እንዲከፍሉ ግዳጅ በማስቀመጥ፡ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን በሃገራዊ ልማት የነበራቸውን ታሪካዊ ተሳትፎ ጥላሸት በመቀባት ! ዲፕሎማቱ የዘቀጠ አስተሳሰባቸውን በግልጽ ያሳዩበትን አሳዛኝ እና ሳፋሪ አጋጣሚ እንደነበር ተሰብሳቢው አውስቷል።

ይህ በዚህ እንዳለ ክቡር አንባሳደር መሃመድ ሃሰን በቅርቡ በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት በወላጆች የተቋቋመ አንድ ኮሚቴ ሰደተኛውን ወገናችንን የት/ቤት ባለቤት የሚያደርግ እና በሪያድ የሚኖር ወገናችንን በተመጣጣኝ ዋጋ ልጆቹን ሊያስተምር የሚችልበትን ት/ቤት ለመግዛት ተይዞ የነበረውን እቅድ በማደናቀፍ የአብዛኛውን ወላጅ ልጆቹን በሰው ሃገር የማስተማር ተስፋው እንዲጨልም ምክንያት ሆነውል። ክቡር አንባሳደር መሃመድ ት/ቤት ውስጥ፡ባስቀመጦቸው ደጋፊዎቻቸው እየተመሩ የት/ቤት የቦርድ አመራር አባላት ከወላጆች እንዳይመረጥ የራሳቸውን ተጽዕኖ በማሳረፍ ት/ቤቱን ባለቤት አልባ እንዲሆን አድርገውታል። ክቡር አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ኢትዮጵያ ውስጥ የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ፡ኤጀንሲ እንዳላቸው ከሚነገርላቸው ከኮሚኒቲ ሊቀምንበር አቶ ሙስጠፋ ሃሰን ጋር ባላቸው የእከክልኝ ልከክልህ ግንኙነት በተጠቀሱት ግለሰብ ኤጀንሲ አማካኝኘት የሚመጡ ሴት እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና በደል አይተው እንዳላዩ ማለፋቸው ከወገን ተቆርቋሪነታቸው ይልቅ ለግል ለጥቅም የቆሙ መሆናቸውን ታዛቢዎች ይገልጻሉ። ቀደም ሲል በኮሚኒቲው ሊቀንበር አቶ መስጠፋ እጄንሲ በኩ የመጡ 2 ኢትዮጵያውያን በአሰሪዎቻቸው በደረሰባቸው ድብደባ እና እንግለት ወደ ኢትዮጵያ ኮሚኒት ግዜያዊ መጠለያ በመግባት የጉዞ ትኬት አጥተው ከብዙ ስቃይ በሃላ በጭንቀት ሲሰቃዩ ኖረው እራስቸውን አንቀው መግደላቸው የቅርብ ግዜ አሳዛኝ ዜና መሆኑ ይታወሳል ።

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ እና ጅዳ ከተማ ከአሰሪዎቻቸው ግፍ እና በደል ለመታደግ እያመለጡ ወደ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ለሚመጡ እህቶቻችን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለውጭ ሃገር ዜጎች የሰጠውን የምህረት አዋጅ መሰረት አድረገው የተጠቀሱትን ወገኖች የእድሉ ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል እነዚህ ወገኖቻችን ተበድረው የመጡበትን ገንዘብ እንኳን በወጉ ሳይመልሱ ባዶ እጃቸውን ሃገር እንዲገቡ ማድረግ ባእዳኖች በወገኖቻችን ላይ ከሚፈጽሙት አካላዊ ገፍ የከፋ ጭካኔ መሆኑንን አያሌ ወገኖች ይገልጻሉ። በተለይ ከሪያድ እና ከጅዳ የሚወጡ ሚስጥራዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በኮሚኒቲው ግዜያዊ መጠለያ የሚገኙ እህቶቻችን ወደ ሃገር በተሳፈሩ ቁጥር አየርመንገዱ ለያንዳንዱ ተግዥ 40 ኪሎ ሻንጣ በነጻ መጫን ስለሚፈቅድ በተጠቀሱት ሴት እህቶቻችን ስም የተለያዩ እቃዎችን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ዲፕሎማቱ የተጠቀሱትን ሴት እህቶቻችንን እንደ ቀዋሚ የግል ኪስ ማደላቢያ እንደሚጠቀሙባቸው ይነገራል።

በአጠቃላይ እነዚህ የሪያድ ነዋሪዎች ስለዲፕሎማቱ ሲገልጽ ህዝብ የሚላቸውን የማይሰሙ ከህዝበ ሰደኛው ወገናቸው ብሶት ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም የሚያስቀድሙ መንግስት ከጣለባቸው ስልጣን እና ሃላፊነት ውጭ፡ በእጅ አዙር በሳውዲ አረቢያ የተለያዩ የመንደር ንግድ ተቋማት ውስጥ እጃቻቸውን በማስገባት የግል ህይወታቸውን ለመለወጥ የሚራወጡ የኛቢጤ ነጋዴዎች እንጂ የሃገር እና የህዝብ ተወካይ (ዲፕሎማቶች) ሊባሉ የማይችሉ መሆናቸውን አስረግጠው በመግለጽ ከቦታቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም አንባሳደሩን ጨምሮ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ላይ ያለውን ተቃውሞ በምሬት የገለጸው ተሰብሳቢ ዲፕሎማት ክቡር አቶ መስፍን ድባብ እና ዲፕሎማት ክቡር አቶ ከደር ሁሴን ደከምን ሰለቸን ሳይሉ ለህዝብ እያበረከቱ ያለውን አስተዋጾ ተሰብሳቢው በማድነቅ ለተጠቀሱት ዲፕሎማቶች ያለውን ድጋፍ በጭብጨባ በመግለጽ ስብሰባው በታቀደለት ግዜ በሰላም ተጠናቋል።

Ethiopian Hagere ከጅዳ ( በዋዲ )

No comments:

Post a Comment