Saturday, June 1, 2013

አባይና የሲና በረሃ መተላለቅን የሚያስከትሉ አደገኛ የቀውስ ምንጭ

Image
    


ኢትዮጵያ ከትናንት ግንቦት 20/2005የአባይ ወንዝን የተፈጥሮ አቅጣጫ መቀየሯ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ሀገራት መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ ዋናው ጉዳይ ምሽት ላይ አልጀዚራ በኢንሳይድ ስቶሪ /inside story/ ፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ አቶ በረከት ስምዖንን፤ ከግብፅ ላማ ኤል ሃሎንና ከእንግሊዝ ሊዮ ፓስካልን በማስገባት ዉይይት ያደረገበት ነው፡፡ በዚህ ላይ በኋላ እመለስበታለሁ፡፡ አሁን ግን መገናኛ ብዙሃን፤ ግብፅና ሱዳን ምን አሉ የሚለዉን እንመልከት፡፡
በጉዳዩ ላይ ሰፊ ዘገባ የሰጠው አህራም የተባለዉ የግብፅ ድረ-ገፅ ነው፡፡ ቢቢሲ፤ አልጀዚራና ዋሽንግተን ፖስትም እንዲሁ፡፡ ሁሉም ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን በተለያየ መጠን ለጉዳዩ ሽፋን ሰጥተውታልማለት ይቻላል፡፡ ከብዛታቸውና ከምንጫቸው ተመሳሳይነት አንፃር የያንዳንዱን ዘገባ አቅጣጫ ከማየት ይልቅ በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት አስተያየታቸውን ወደሰጡት ግለሰቦች አትኩሬአለሁ፡፡
ከላይ ከቁንጮው እንነሳ፡፡ ማለቴ ከግብፅ መንግስት አቋም፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ያወጣው መግለጫ አሁን በአባይ ወንዝ ላይ እየተካሄደ ያለው ግንባታ በውሃ መጠኑ ላይ መቀነስን ሊያስከትል የሚችል እንዳልሆነ የሚገልፅ ነው፡፡ በአባይ ላይ የሚገነባ ማንኛውም ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር ቦታውን ለግንባታ ምቹ ማድረግን ይጠይቃል ብሏል መግለጫው፡፡ ስለሆነም ከተለመደው ውጭ የሆነ አዲስ ነገር የለም የሚል ይመስላል፡፡
የግብፅ ካቢኔም በጉዳዩ ላይ ትናንት በዝግ ከመከረ በኋላ ባወጣት ቁራጭ መግለጫ የግድቡ ግንባታ ተጀመረ ማለት ግብፅ እውቅና ሰጥታዋለች ማለት አይደለም ብሏል፡፡ ያም ሆኖ የግብፅና ሱዳን የውሃ ድርሻን የማይቀንስ እስከሆነ ድረስ ማንኛዉንም የልማት ፕሮጀክት እደግፋለሁ ብሏል ካቢኔው፡፡ ካቢኔው ጨምሮ እንደገለፀው ለማንኛውም የሶስትዮሽ ኮሚቴውን የጥናት ሪፖርት ይፋ መሆን እንደሚጠብቅ ገልጧል፡፡ ሪፖርቱን ተከትሎ የሚይዛቸዉን አቋሞች /የሚወስዳቸዉን እርምጃዎች/ ከወዲሁ እንዳዘጋጀም ካቢኔው ጠቁሟል፡፡ ምን እንደሆኑ ፍንጭ ከመስጠት ቢቆጠብም፡፡ በዝች መግለጫ መጨረሻ የገባችዉ አረፍተ ነገር ደግሞ ግብፅና ሱዳን በአንድ ልብ ሆነን በጉዳዩ ላይ ተባብረን እየሰራን ነዉ” ትላለች፡፡ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እያደላች ነው የሚለዉን ዘገባ ለማጣጣል የገባች አረፍተ ነገር ሳትሆን አትቀርም፡፡
ዘግይቶ እንደተረዳሁት ደግሞ ዛሬ ግንቦት 22/2005 ፕሬዝዳንት ሙርሲ ከተመረጡ ሚንስትሮች ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡
የሃገሪቱ የሹራ ምክር ቤት ደግሞ በመጭው እሁድ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከር የአስቸኳይ ስብሰባ ቀን ቆርጧል፡፡ በስብሰባው የውጭ ጉዳይና የደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎችን ጨምሮ 6 ኮሚቴዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
እኔ እንዳገኘሁት መረጃ ከሆነ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርበሃገሪቱያሉትንየኢትዮጵያአምባሳደርሞሃሙድድሪርንአስጠርቶበጉዳዩላይቃላቸዉን
ተቀብሏቸዋል፡፡ምስኪን!ምንብለዉይሆን?የሚኒስቴሩየስራሃላፊዎችከበውበጥያቄ ሲያዋክቧቸው፡፡እንደመረጃውሰዎቹበኢትዮጵያዉሳኔመከፋታቸዉንለአምባሳደሩገልፀውላቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ቴዎድሮስ /ዳግማዊ/ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ጣልቃ ገብተው ነገር እንዲያበርዱ በግብፅ ፕሬዝዳንት ተጠይቀዋል፡፡ አንድ የቤተክርስቲያኗ የህግ ባለሙያ እንዳሉት ፕሬዝዳንቱ ለጳጳሱ ደውለው የጋራ መፍትሄ በሚገኝበት መንገድ ላይ ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር እንዲመክሩ ጠይቀዋቸዋል፡፡ ሆኖም ይሄ ሃሰት ነው፤ ማንም ምንም አላለንም የሚል ማስተባበያ ከቤተክርስትያኗ ወጥቷል፡፡
ከአባይ ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ ማስቀየር ጋር በተያያዘ ስማቸው በተደጋጋሚ የተነሳዉ የግብፅ ውሃና መስኖ ልማት ሚንስትሩ ሞሃመድ ባሃ ኢልዲን ናቸው፡፡ እሳቸዉ የንግግራቸው መጀመሪያ ያደረጉት ግብፅ በጥቅሟ ላይ የሚመጣን ማንኛውንም አይነት ፕሮጀክት እንደማትደግፍ መግለፅ ነው፡፡ ይህ አቋማቸው እንዳለ ሆኖ የወንዙ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩ ግን ለግብፅ ምንም ጉዳት እንደሌለው ለጋዜጠኞችአረጋግጠዋል፡፡ የተለመደ የግንባታ ሂደት መገለጫ ብቻ ነዉ” ብለውታል፡፡የአንድ ሃገር ሚኒስትር ከዚህ በላይ ሊሉት የሚችሉት በጎ ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ የሃራቸውን ጥቅም የሚጎዳ ነገር ካለ እሱን መቃወም አለባቸው፤ ከሚጠቅማቸው ጋር ደግሞ መተባበር፡፡ እሳቸው ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ አሁን በግብፅ ላይ የተደቀነ አደጋ የለም፤ የጋራ ኮሚቴው ሪፖርት እስከሚወጣ እንጠብቃለን ነው ያሉት፡፡
እኝህ ሰው በቅርቡ በሃገሪቱ በተደረገው የስልጣን ሽግሽግ ባሉበት እንዲቆዩ ሲደረጉ እንኳን ደስ አለዎት በማለቴ የተረቡኝ እንደነበሩ አስታውሳለሁ፡፡ ሰውየው ምንም ያህል ትችት ቢሰነዘርባቸውም ስለኢትዮጵያ ያላቸውን በጎ እይታ በአደባባይ ከመግለፅ ያልተቆጠቡ ናቸው፡፡
ሌላዉ በዚህ ጉዳይ በንቃት የተሳተፉት በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደር ሞሃመድ እድሪስ ናቸው፡፡ የህዳሴው ግድብ ግብፅ የግዷንም ቢሆን ልትቀበለው የሚገባ የማይቀር ክስተት /reality/ ነው ብለዋል፡፡ የግብፅ የድርድር ግብ መሆን ያለበትም ግድቡን ማስቆም ሳይሆን ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ በሚሆኑበት መንገድ ላይ ሊሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ የአስዋን ግድብ ለኛ አንደሚያስፈልገን ሁሉ የህዳሴዉ ግድብም ለኢትዮጵያውያን ብሄራዊ ሃብታቸው ነዉ” ሲሉ ነው እዉነታውን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ የቆረጡት፡፡ አምባሳደሩ አሁን ኢትዮጵያ ያደረገችው ነገር ዱብ እዳ ሳይሆን ካለፈው ህዳር ጀምሮ የምናውቀው ነው ብለዋል፡፡
“በሁሉም መድረኮቻችን ኢትዮጵያ በኛ ላይ ጉዳት እንደማታስከትል ደጋግማ አረጋግጣልናለች፤ እኛም ይህንኑ አምነን ተቀብለናል” ያሉት አምባሳደሩ ግብፅ ሶስቱም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር እየፈለገች መሆኗን ተናግረዋል፡፡እኔ የነዚህን ባለስልጣናት ንግግር በአወንታዊ መልኩ ነው ያየሁት፡፡ ምክንያቱም ቢያንስ ኢትዮጵያ እነሱን የመጉዳት ሃሳብ እንደሌላት መረዳታቸዉን ገልፀውልናል፡፡ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ቀስ በቀስ ቅቡል እየሆነ መምጣቱን አመላካች አስተያየት ነው፡፡
ሆኖም የሀገሪቱና የአለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ አሉታዊ ነው፡፡ መገናኛ ብዙሃኑ ከግድቡ ጋር ያሉ አወንታዊ ጎኖችን ዘወር ብለዉ እንኳን ሳያዩ ሊያስከትል ይችላል ብለዉ ባሰቡት ተፅዕኖ ላይ ብቻ ነዉ ያተኮሩት፡፡
ባለስልጣኖቹ ከተናገሩት ውስጥ ሲመርጡ እንኳን ይህንኑ ፍላጎታቸውን የሚያሟላላቸዉን ንግግር ብቻ እንጅ በመቻቻልና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩትን አገላለፆች በተደጋጋሚ ዘለዋቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያክል ሞሃመድ ባሃ ኢልዲን ግብፅ በጥቅሟ ላይ የሚመጣን ማንኛውንም አይነት ፕሮጀክት እንደማትደግፍ መግለፃቸውን ሲያራግቡ በግብፅ ላይ የተደቀነ አደጋ የለም ማለታቸውን ግን ብዙዎቹ አድበስብሰውት አልፈዋል፡፡ምሁራኖቻቸውም እንዲሁ ናቸው፡፡ አንድ ምሁር “ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ሙርሲ ጉብኝት ማግስት የናይል ወንዝን የፍሰት አቅጣጫ ማስቀየሯ የግብፅና ህዝብና መንግስት ለማታለል የምትከተለውን ስልት የሚያሳይ ነው” ብሏል፡፡ የግብፅ ባለስልጣናት የህዝባቸውን ጥቅም አሳልፈው ሰጥተዋል ሲልም ወቅሷል፡፡ ለዚህም የግብፅ ህዝብ የጃቸውን ሊሰጣቸው ይገባል ነው ያለው፡፡
ሌላው የሚጠበቅ ግን ቢሆንም መታወቅ ያለበት የግብፅ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋም ነዉ፡፡ ፓርቲዎቹ ይህንን ጉዳይ ለፖለቲካ ጥቅም ማግኛ ሲጠቀሙበት ተስተውለዋል፡፡ እነሱ እንደ ጠንካራና ለግብፅ ህዝብ የቆሙ፤ ሙስሊም ብራዘርሁድ የሚመራው መንግስት ደግሞ እንደ ልፍስፍስና የህዝቡን ጥቅም አሳልፎ የሰጠ አድርገው አሳይተዋል፡፡ የናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንቱ ኤል ባራዲ በቅርብ ሰዓት በግል ቲዊታቸው የሲና በረሃና ኢትዮጵያ መተላለቅን የሚያስከትሉ አደገኛ የቀውስ ምንጭ እንደሆኑ ተንብየዋል፡፡ይችን ነገር ከኛ ሃገር ተቃዋሚዎች የኮረጇት ሳትሆን አትቀርም፡፡ በነገራችን ላይ የኛዎቹ እስካሁን ድምፃቸዉ አልተሰማም፡፡ የአባይ መንገዱን መቀየር አልሞቃቸውም፤ አልበረዳቸውም፡፡
በአንፃሩ የቀድሞው የአረብ ሊግ ዋና ፀሃፊና የዚሁ የናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንት ሌላው አመራር የሆኑት አሚር ሙሳ የታችኛው ተፋሰስ ሃገራት በተለይም ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ በሚካሄድ ፕሮጀክት የተነሳ መጎዳት እንደሌለባቸውና በዚህ ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ ውጥረት ውስጥ መግባት እንደሌለበት አሳስበዋል፡፡ ለዚህም በመፍትሄነት ያቀረቡት ኢትዮጵያ የግብፅን ፍላጎት፤ ግብፅም የኢትዮጵያን ፍላጎት ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው ነው፡፡ ግብፅ በአስቸኳይ ወደ ድርድር መግባት እንዳለባት ጠይቀዋል፡፡
በሰሞኑ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ውስጥ ግብፅ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባት የሚጠቁሙ አስተያየቶችም ተስተናግደዋል፡፡ ወታደራዊ እርምጃና የሲዊዝ ቦይን መዝጋት በዚህ ስር የታዩ ናቸው፡፡ሼክ ሃሚድ የተባሉ የአንድ ሃይማኖታዊ ቡድን መሪ እንዳሉት ሁኔታው ሲገመገም አሁን ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ጦርነት አውጃለች እንደማለት ነዉ፡፡ ስለሆነም እኛም ያለንን አቅም ሁሉ ተጠቅመን መብታችንን እናስከብራለን ብለዋል፡፡ ያም ሆኖ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቅድሚያ ሊሰጠዉ ይገባል ብለዋል፡፡ ይህ እንግዲህ በግልፅ ሲቀመጥ ጦርነት ተከፍቶብናልና ለጦርነት እንነሳ ማለት ነው፡፡ሆኖም ይህ ሀሳብ በአንድ የቀድሞ ጦር አዛዥ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ጀነራል ሞሃመድ አሊ ቢላል የህዳሴዉን ግድብ በአውሮፕላን ለመምታት መሞከር ከብዙ የአለም ሃገሮች ጋር ያጣላል ነው ያሉት፡፡ ከነዚህም ውስጥ እስራዔልንና ቻይናን አንስተዋል፡፡ ሁሉ ካልተሳካ ግብፅ ያላት አማራጭ ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤት፤ ለፀጥታው ምክር ቤት ወይም ለአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ነው ብለዋል፡፡ ሌላ ወታደራዊ ባለስልጣንም ይህ ሃሳብ የግድቡ ግንባታ በተበሰረበት የሆስኒ ሙባረክ ዘመን ተነስቶ እንደነበር ለጋዜጦች ተናግረዋል፡፡ ያኔ የጦርነት አማራጭ በጥብቅ እንደተወገዘ አስረድተዋል፡፡በሌላ በኩል ግብፅ ኢትዮጵያን በግንባታው ዙሪያ የሚያግዙ ሀገራት መርከቦች በስዊዝ ቦይ እንዳይጠቀሙ ብትከለክል ውጤት ልታገኝ ትችላለች ሲል አንድ የግብፅ ተቃዋሚ ፓርቲ ሃሳቡን አካፍሏል፡፡
ይህ በንዲህ እንዳለ የሱዳኑ የውሃ ሃብትና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ሞሃመድ ሃሰን በጉዳይ ላይ ለመምከር ወደ ካይሮ ሄደዋል፡፡ እዛ እንደደረሱም ከግብፁ አቻቸው ጋር ተመካክረዋል፡፡ ምን እንደዶለቱ ግን እስካሁን ወሬ አላገኘሁም፡፡ ወደ ሱዳን ከገባሁ አይቀር በዚሁ የሱዳን ሁኔታ እንመልከት፡፡
በግብፅ የሱዳኑ አምባሳደር ከማል ሃሰን የአባይ ወንዝ አቅጣጫ የመቀየር ዜና አስደንጋጭ እንደሆነና ሱዳንና ግብፅ የአረብ ሊግን ጣልቃ ገብነትሊጠይቁ እንደሚችሉ ተናግረዋል በሚል ትናንት በርካታ መገናኛ ብዙሃን ተቀባብለውት ነበር፡፡ ሆኖም ከምሽት ጀምሮ በአንዳንድ የግብፅ ጋዜጦችና በሱዳኑ ሱዳን ትሪቡን ድረ ገፅ የወጣ ዘገባ አምባሳደሩ ይህንን ማለታቸውን የሚያስተባብል ነው፡፡የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እኛ እንዲህ አይነት ንግግር ካፋችን አልወጣም ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችው ነገር በሱዳን ላይ ምንም ጉዳት እንደሌለው አረጋግጠናል፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም ተጠቃሚ በምንሆንበት ነገር ላይ ከኢትዮጵያም ሆነ ግብፅ ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነን ሲል አቋሙን አሳውቋል፡፡
እስኪ አሁን ደግሞ ትናንት ምሽት በአልጀዚራ ስለተላለፈዉፕሮግራምላንሳ፡፡በኢንሳይድስቶሪፕሮግራምላይከአዲስአበባየመንግስትኮሚዪንኬሽን
ሚኒስትሩአቶበረከትስምዖን፤ከካይሮየአካባቢጥበቃባለሙያዋላማኤልሃሎናከለንደንደግሞ
ደራሲዋሊዮፓስካልቀርበዋል፡፡
የፕሮግራሙ አዘጋጅ ገና ሲጀምር የህዳሴውን ግድብ በግብፅ ህልውና ላይ የተደቀነ አደጋ አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡ የግብፅ ህዝብ በ2050 /በነሱ አቆጣጠር/ 150ሚሊዮንስለሚደርስግብፅተጨማሪ21 ቢሊዮንኪዉቢክሜትርውሃያስፈልጋታል፤ግድቡግንእንኳንይህንእድልሊሰጣት18 ቢሊዮንኪዩቢክሜትርውሃያሳጣታልሲልበመደምደምይነሳል፡፡የሃይልማመንጨትአቅሟንና
የግብርናምርትመጠኗንምይቀንሰዋል፤በዚህምሚሊዮኖችለረሃብይጋለጣሉይላልጋዜጠኛዉ፡፡አቶ በረከት በሰጡት ምላሽ ታዲያ እንደማስበው የኢትዮጵያ ፍላጎት በግብፅም ሆነ ሱዳን ላይ ይህን ያህል ጭንቅ መፍጠር ሳይሆን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ነው አሉ፡፡
ጋዜጠኛዉ ፍላጎታችሁ ጉዳትማድረስላይሆንይችላልግንሂደቱይህንጣጣሊያመጣይችላል”ሲል አቋረጣቸው፡፡በረከትምሂደቱየሚያስከትለዉእንደውምየተሻለየዉሃመጠንነዉ፡፡ምክንያቱምእኛ
በአካባቢያችንየምናከናውነውየተፈጥሮሃብትእንክብካቤስራየከርሰምድርዉሃመጠንንየሚያሳድግነው
ሲሉተከራክረዋል፡፡
በዚህ ግዜ ጋዜጠኛው ሊዎ ፓስካልን ግብፅ የሱዳንን መሬት ተጠቅማ በኢትዮጵያ ላይ የሃይል እርምጃ ልትወስድ የምትችልበት እድል እንዳለ ጠየቃት፡፡ እርሷም ስትመልስ ግብፅ ይህን ስልት ቀድማም ትጠቀምበት እንደነበር አስታውሳለች፡፡ በተለይም ሶማሊያንናኤርትራንበመጠቀምኢትዮጵያንየማዳከምስልትትከትልእንደነበርአውስታለች፡፡
አሁንግንየኢትዮጵያጡንቻበአካባቢውእየፈረጠመመሆኑንታነሳናየጦርነትአማራጭለግብፅአዋጭ
እንዳልሆነ በተዘዋዋሪ አስረድታለች፡፡
ጋዜጠኛው ውሃን እንደጦር መሳሪያ አድርጎ ማየቱ ያላስደሰታቸዉ አቶ በረከት እኛዉሃያጣላናልብለንአናስብም፡፡ይህአንተየምትለዉምግዜያለፈበትተረትነዉ”
ብለውታል፡፡እንደሚኒስትሩኢትዮጵያወጭውንብቻዋንትሸፍነውእንጅጥቅሙ የሁሉም ሀገሮች ነው፡፡ ግብፅም ሆነች ሱዳን በበጋ ወራት ሳይቀር ወጥነትና ብዛት ያለው ዉሃ ሊያገኙ እንደሚችሉ የተከዜው ግድብ ለሰሜን ምስራቅ የሱዳን አካባቢዎች ያስገኘዉን ጥቅም በአብነት በማንሳት አብራርተዋል፡፡
በቅኝ ግዛት ወቅት የተፈረሙ ስምምነቶች ኢትዮጵያን ያገለሉ እንደሆኑና ይህንን በመቀየር ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎቹ ሃገራት በጋራ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት እንደሚገባ ተከራካሪዎቹ አንስተዋል፡፡ ፓስካ ኢትዮጵያየድርሻዋንካልተጠቀመችማለውሃው/ለወንዙ/ ደህንነት ለምንትጨነቃለች?”ስትልመልሳጠይቃለች፡፡ኤልሃሎበበኩሏየቀድሞውጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ንግግርንበማስታወስግድቡየኢትዮጵያብቻሣይሆንየአካባቢውሃብትእንደሆነአሳይታለች፡፡
በአጠቃላይ ሲታይ ውይይቱ መግባባት የሰፈነበት ነበር፡፡ ሆኖም ከኢትዮጵያው ሚኒስትር በስተቀር ሌሎቹ ጉዳዩ በቀጥታ የማይመለከታቸውና የመወሰን ስልጣንየሌላቸዉመሆኑየውይይቱንፋይዳያሳንሰዋል፡፡ውይይቱበሶስቱሃገራትከፍተኛ ባለስልጣኖች መካከልቢሆንይሻልነበር፡፡ነገርግንሱዳንናግብፅበአሁኑሰዓት/ቢያንስየገምጋሚውቡድንሪፖርት
ይፋእስኪሆን/ለመነጋገርዝግጁየሆኑአይመስልም፡፡
ስለብዙ መገናኛ ብዙሃን ብዙ አውርቼ ስለ ኢሳት ትንሽ እንኳን ካላልኩ ወዳጆቼ ይቀየሙኛል፡፡ በመጨረሻ ኢሳት ምን እንዳለልንገራችሁ፡፡የወንዙንአቅጣጫየማስቀየሱስራለግንቦት20 በዓልየድረስድረስስለሆነስራውበአግባቡ አልተፈፀመም” ብሏል፡፡ እዛው በቦታው ያነጋገርኳቸው ሰዎች እንደነገሩኝ የግንባታዉ ሂደት እጅግ ተጓትቷል ሲል ዘግቧል፡፡ ሶስተኛ አማራጭ ይሏችኋል ይህ ነዉ፡፡ ግብፅና ሱዳን አባይ ተቀየሰ ብለው ሲደነግጡ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ትንሽ ዘወር አለ እንጅ ከናንተው አይቀርም እያለ ነው፡፡
እንግዲህ ዛሬ እንዲህ ተዉሎ ተመሽቷል፡፡ ነገም ሌላ ቀን ነዉ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ደግሞ ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው የአለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን ሪፖርት ይፋ ይሆና፡፡ ያኔ ደግሞ የሚወራዉን እንሰማለን፡፡
ስለ አባይ ምን ተባለ? /የተሻሻለ/

No comments:

Post a Comment