Wednesday, April 30, 2014

ይድረስ ‘ለጆን ኬሪ’፣ የእኔን ኑሮ ሳያዩ እንዳይመለሱ


ይድረስ…. ከእናት ሀገራችን ቀጥሎ አባት ሀገር ከሆነችን አሜሪካ ለምትመጣው ‘ጆን ኬሪ’….John Forbes Kerry current United States Secretary of State.
ለጤናህ እንደ ምንድን ነህ…
ባገራችን ባህል መሰረት የማተዋወቁ ሰዎች ሲገናኙ ሰላምታ ስለሚለዋወጡ እንጂ አንተስ ደህና እንደሆንክ አውቅ ነበር…
የአለምን ድህነት ሆነ ብልጽግና ቁልቁል የምተመለከትበት ነጩ ቤት (Whitehouse) ውስጥ ሆነህ ምን ትሆንና…
ብቻ አገራችን ልትመጣ አየር ላይ መሆንህን ሰማሁ….
ካገራችን ዘርፈ ብዙ ችጋር የተነሳ ውሀ የተሞላበት ጄሪካን፣ 24 ሰዓት የሚያበራ ባትሪ፣ ኢንተርኔት ያለው ላፕቶፕና፣ ኔትወርክ ያለው ስልክ…ይዘህ እንደምትመጣ አያይዤ ሰማሁ…
ኸረ እንደውም ሌላ ሊያጋጥምት የሚችልን ችግር ንገረኝ አይበሉኝ እንጂ….
የለበሷት “ቶክሲዶ” ሱፍ አገራችንን መሬት ገና እንደረገጡ ወደ አምባሳደር ሱፍነት እንደምትለወጥ ጥርጥር የለኝም….
ብቻ ሁሉ ይቅርና እንኳን ደህና መጡ ….
የቤተ መንግስት ሰዎች እርሶን ለመቀበል ሽር ጉድ እያሉ ነው፡፡ ትላንት እርሶ ባወጡት አመታዊ ሪፖርት ምክንያት ጠልተዎት አይኖን ላፈር ያሉ፤ ቢሆንላቸው እንደሌሎች ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን እርሶንም ቢያስሩ ደስ የሚላቸው…
ሰሞኑን ምን አግኝተው ይሁን ወይም ምን ቃል ገብተውላቸው እንደሆነ ባላውቅም…. በየመንገዱ ባንዲራዎች ተሰቅለዋል፣ መንገድ ጠራጊዎች የቦሌን አስፓልት በኦሞ ዘፍዝፈው ማጠብ ነው የቀራቸው. ቤተመንግስት ከዚህ በላይ እንደሚጠብቆዎ የወጣው ሪፖርት ያሳያል….
ኸረ እንደውም አሉባልታ ነው እንጂ ፤ ከቤተ መንግስቱ በር ጀምሮ ጥቃቅንና አነስተኞች ሀ/ማርያም ቢሮ ድረስ አዝለው እንደሚያደርሶው ሰምቻለሁ….
ብቻ ይሁን እንኳንም ይህ ሁሉ ተደረገልዎ….
እኔ የሚያሰጋኝ ይህ ሁሉ ሽር ጉድ የመጡበትን ሀሳብ እንዳያስቀይሮት እና… የታሰሩ የህሊና አስረኞችን፣ አሸባሪ ጦማሪያኑን ደግሞ አመጸኞች እንዳይሏቸው ነው…..
እንዲሁም እኔን መተው ሳያዩ… አገሪቷ በኢኮኖሚ አድጋለች አሜሪካ ላይ ለመድረስ ትንሽ ነው የቀራት እንዳይሉን አደራ እላለሁ፡፡..
እርሶ ብቻ እቤቴ ይምጡ…
አገሪቷ ያለችበትን ድህነት ገና እቤቴ ሳይገቡ ሊወድቅ ትንሽ የቀረው የጊቢዬ አጥር ይነግሮታል….
ጆን ኬሪ…
እንደው የእረሶ አለቃ የሆኑት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ ኢንተርቪው አድርገው ‹‹ገበሬው እየተለወጠ እንደሆነ ነግሮኛል ይሄም ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል ለውጥ እንዳለ ይህ ማሳያ ይሆናል›› ብለው እንደዘባረቁት እርሶም እንዳይዘባርቁ እለምኖታለሁ…
በመጨረሻም አንድ ቃል ልግባሎት….
እርሶ የብዙ ጭቁን ህዝቦች አጋር ሆነው፣ ለምናደርገው የነጻነት ጉዞ የጀርባ ስንቅ ሆነው…
ፍትህ፣ እኩልነት ፣ ሰብዓዊነት የምትታይበት አገራችን እንድትፈጠር ከረዱን….
የእርሶንና የአገርዎን ስም ልቤ ላይ እንደምነቀስ ቃል እገባሎታለሁ፡፡
‹‹የመጡት ኢትዮጵያ ነውና ኢትዮጵያን ይመልከቱ ባለስልጣናቱን ሳይሆን…››
…………………………..አክባሪዎ አቤል ኤፍሬም

No comments:

Post a Comment