የሕዳሴው ግድብና ዐባይ፣ የሚሊኒየሙ ዐባይ ተጋቦት
አዘጋጅ ለኢትዮጵያ ፍቅር ከቃሊቲየዐባይ ሥረ_መሠረትና የሕዳሴው ግድብ ማነጣጠሪያ እነሆ!
- ጥናቱ የተፈጸመው ሚያዚያ 2003 (2011 እ ኤ አ) ነው።
- አቅርቦት የፀሐፊው ትክክለኛ ቅጂ (በአቀራረባዊ ጥንቅር)
- የጊዜው የኢትዮጵያ ጉዳይ ሆኖ የቀጠለውና ሕዝቡም የጠየቁትን እያደረገ ያለበት የሚሌኒየሙ ታላቅ የዐባይ ግድብ እንደተነገረው፤ የሚገደበው ከሱዳን ድንበር 17 (አሥራ ሰባት) ኪሎሜትር ባለ ቀረቤታ በዐባይ ወንዝ ላይ ነው።
- ግድቡ ወደ 62 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም አለው።
- የውኃው መጠን የጣና ሐይቅ ከሚይዘው ውኃ እጥፍ ይሆናል።
- በሚቋረው ውኃ 5250 (አምስት ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ) ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል ሊመረት ታቅዷል። የሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይል ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሱዳንና ለግብፅም ሊሸጥ ታስቧል። ይህ ግንባት 80 ቢሊዮን ብር ይፈልጋል።
- ገንዘቡ በግብፅ ተፅዕኖ ሳቢያ የውጭ ብድር ወይም ዕርዳታ እንዳያገኝ ሰለሚጠናወት፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ የመዋጮና ቦንድ ሺያጭ ሊሸፈን ነው ተብሏል።
- ለሕዝቡም ታሪካዊ ተዐምር ሊሠራ እንደሆነና የልማት ሁሉ አንጋፋ እንደሆነ ተነግሮት የቻለውንና ያልቻለውንም ከማድረጉ በላይ ለሃገር የሚበጅ ልማታዊ ድንቅ እንደተፈጠረ ተበስሮለታል።
- ባለፈው ሚያዚያ (April) 2013 እ ኤ አ ወር ማብቃያ አካባቢ በወጣው ዜና ደግሞ (ይህ ጥንቅር ከቀረበ ከሁለት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው። ቻይና ለሚሌኒየሙ ግድብ ግንባታ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ልታበድር ነው ተብሏል።
እኮ ቢጠቅማቸውማ ነው ዝምታቸው፤ የዐባይ ልጅ ይህ እንዴት ያየዋል?
ዝርዝሩን ምድር ላይ ያለውን እንየው፤
አባይ (ናይል)እየተባለ የሚጠራው በዓለም ረዥሙ ወንዝ፣6671 ኪሎ ሜትር እርዝማት ሲኖረው፣ከዘጠኝ አገሮች ይመነጫል።ግብፅ ምንም የምታመነጨው የውኃ አስተዋፆ የላትም። ሆኖም በናይል ውኃ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ አገር ናት። ግብፅ 100% የሰሐራ በረሃ አካል በመሆኗ በሜዲቴሪንያን አካባቢ ጥቂት ዝናብ ጠብ ከማለቱ ሌላ ከዓመት ዓመት ዝናብ አይጥልም።
በሌላ በኩል ደግሞ ከሁሉም የናይል ተፋሰስ አገሮች ይበልጥ የ80% በመቶ ከአባይና ከሌሎች የኢትዮጵያ ወንዞች የሚገኘው ውኃ አባይን ይገልጸዋል። በጠቅላላው የናይል ወንዝ 74 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ በዓመት ሲሰጥ ከዚህ ውስጥ ከኢትዮጵያ የሚገኘው የውኃ ድርሻ መጠን 54 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ ነው። የዚህ ሁሉ ውኃ ምንጭ ኢትዮጵያ ስትሆን፤እንደ ሱዳንና ግብፅ እምነት ጥቂት ውኃ እንኳን ለመጠቀም መብት የላትም።ሌሎቹንም የናይል ውኃ አመንጪና ባለቤት የራስጌ አገሮችን በማግለል መብታቸውን ገፍፈው ሱዳንና ግብፅ ተከፋፍለውታል።
እ ኤ አ 1959 ዓ ም በተፈራረሙት ስምምነት መሠረት ግብፅ 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ፤ሱዳን ደግሞ 18.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ ይወስዳሉ።በተለይ ግብፅ የውኃው ዋና ባለቤት እራሷን አድርጋ በመቁጠር አመንጪዎቹን የራስጌ አገሮች ለአነስተኛ የውኃ ጠቀሜታ እንኳን ፈቃጅ መሆን አለብኝ ባይ ናት። ለዚህም ኢትዮጵያን ማዳከም ወይንም ማጥፋት ተልኮዋ ሆኗል።
የአባይ ጠቀሜታ
- ግብፅና ሱዳን ፍፁም ተጠቃሚዎች ሲሆኑ፤ በተቃራኒው የውኃ መነሻ የሆነችው ኢትዮጵያ ተጠቃሚ አልሆነችም።
- ግብፅ 3.0 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በመስኖ ታለማለች።
- ሱዳን 1.8 ሚሊዮን ሄክታር እንደዚሁ በናይል ወሰኗ ታለማለች።
የግብፅ በረሃ በናይል ውኃ በሺ ዓመታት የሚቆጠር የመስኖ እርሻ ልምድ ለምቶ እራሳቸውን ከመመገብ አልፈው የዳበረ ኢኮኖሚ ገንብተውበታል። አባይን ወደ ምዕራብ የግብፅ በረሃ ቀይሰው በመውሰድ ተጨማሪ 1.2 ሚሊዮን ሄክታር በረሃ ለማልማት መንቀሳቀስ ከጀመሩ ቆይተዋል።በዚህ ምዕራባዊ ከተማ ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የሚኖርበት ዘመናዊ ከተማ እየተገነባ ነው። የሲናይንም በረሃ ለማልማት በዓመት 4.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የአባይ ውኃ የሚያስተላልፍ ቧንቧ ዘርግተዋል። የመስኖ ሥራቸውን ለማካሄድ ያስቻላቸውም ታላቁ የአሳዋን ግድብ ነው።ግድቡ 162 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የማከማቸት አቅም አለው። በክረምት ወራት ከኢትዮጵያ የሚፈሰውን ውኃ አጠራቅመው በመያዝ በሰከንድ 1500 ቶን ውኃ እየለቀቀ በረሃውን ያለማል። ይህም ሆኖ በግብፆች ዕቅድ ተጨማሪ በረሃ ለማልማት 15ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ ተጨማሪ ያስፈልገዋል። ለዚህም የተለያዩ ፕሮጀክቶች አስጠንተዋል። ጥናቱ ተጠናቆ ግንባታውም ተጀምሮ የነበረው አንዱ ፕሮጀክት በደቡብ ሱዳን ክልል ያለው የጀንገሌ ካናል ፕሮጀክት ነበር። የናይል ወንዝ በደቡብ ሱዳን ሱድ እየተባለ የሚጠራውን ረባዳና ረግረግ ሰፊ መሬት አቋርጦ ያልፍል።ወንዙ በክረምት ከአፍ እስከ ገደብ ሲሞላ ግደቡን ጥሶ ለጥ ወዳለው ሜዳ መፍሰስ ይጀምራል።ግድቡን አልፎ የተንጣለለው ውኃ ተመልሶ ወደ ወንዙ ሊገባ ስለማይችል፤እንደተንጣለለ ይደርቃል።ይህም በፀሐይ ሙቀት እየተነነ ይጠፋል። ታዲያ ግብፃውያን የጀንግሌ ካናልን ፕሮጀክት ያጠኑትና ሥራውንም የጀመሩት በትነት የሚባክነውን ውኃ በማግኘት የናይልን ውኃ መጠን 10% ከፍ ለማድረግ ነበር።
1ኛ የጀንግሌ ካናሉ ግንባታ የተጀመረው የደቡብ ሱዳን ነፃ አውጪ ድርጅት የነፃነት እንቅስቃሴ በጀመረበት ወቅት ስለነበር ፕሮጀክቱ ሳይገፋ አገራችን ይደርቃል፣ ኢኮሎጂውም ይለወጣል፣ በማለት ኤስ .ፒ .ኤል. ኤም ፕሮጀክቱ ላይ ጥቃት በመሰንዘር አጨናገፈው።
2ኛ ተጨማሪ ውኃ ለማግኘት ያስችላል ተብሎ የተጠናው ሌላው ፕሮጀክት ደግሞ በኢትዮጵያ ትልልቅ ግድቦች መገንባትና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ነው። ግብፅ በረሃማ አገር በመሆኗ የፀሐይ ሙቀት ያጠቃታል፤በዚያ የተነሣ በአገራቸው ከተገነባው ቃላቁ የአስዋን ግድብ በፀሐይ ሙቀት ብቻ በትነት ከተከማቸው ውኃ 12% ይባክናል።ይህ በጣም የሚያሳስባቸው ጉዳይ ነው። ብዙ ውኃ ሊይዝ የሚችል ሌላ ትልቅ ግድብ ለመገንባት የሚቻለበት ቦታ ስለሌላቸው ተጨማሪ ውኃ በሃገራቸው ውስጥ ለማከማቸት ያላቸው ዕድል በጣም የመነመነ መሆኑን ተረዱት። በዚህ የተነሣ ጥረታቸውን በኢትዮጵያ ላይ አድርገዋል።በደጋው ኢትዮጵያ ትላልቅ ግድቦች ለገነቡባቸው የሚችሉበት ቦታዎች በርካታ ናቸው። በሚገደቡት ግድቦች የሚከማቸው ውኃ በትነት የመባከን አደጋ አያጋጥመውም።ውኃው ሳይባክን ለብዙ ጊዜ ተጠብቆ የመቆየት ዕድል አለው።ኤሌክትሪክ ለማምረት እየተባለ