Addis Ababa – Ethiopia has flown home over 50,000 citizens from Saudi Arabia after a crackdown against illegal immigrants, the Ethiopian Foreign Ministry said on Wednesday.
“We projected the initial number to be 10,000 but it is increasing,” Foreign Ministry spokesman Dina Mufti told AFP, adding that the final total once the mass airlift ends is now expected to be around 80,000.
Ethiopia started repatriating citizens living illegally in Saudi Arabia after a seven-month amnesty period to formalize their status expired on Nov. 4.
Dina said the government is spending $2.6 million (1.9 million euros) on the repatriation program to bring citizens home, the majority women.
Ethiopia has said relations with Saudi Arabia remain “sisterly,” with Dina saying the government’s main priority was to bring citizens home.
Large numbers of Ethiopians — often women seeking domestic work — travel to the Middle East each year looking for jobs.
Around 200,000 women sought work abroad in 2012, according to Ethiopia’s Ministry of Labor and Social Affairs. — AFP
Thursday, November 28, 2013
Saudi Arabia should withdraw from UN Human Rights Council
By Darara Gubo and Nina Shea
At the very moment that the U.N. General Assembly was voting to elect Saudi Arabia to the Human Rights Council earlier this month, Saudi police officers, assisted by vigilante mobs, launched an iron-fisted effort to round up and deport millions of undocumented foreign workers. The campaign reportedly entailed imprisoning, killing, and raping African and Asian migrants within its borders and provoked a violent protest by some migrants in the capital.
As reported to one of us (Darara Gubo) in a telephone call from Saudi Arabia, at least ten Ethiopians have been killed and over a dozen raped since the state began the round up in early November. The fact that many of the raids that turned lethal occurred in the middle of the night, together with the closed nature of the Kingdom generally, precludes ascertaining the precise numbers of victims.
This harsh crackdown bears the hallmarks of Saudi religious and racial bigotry. Based on local interviews, the Wall Street Journal reported, “Saudi security forces had come to the neighborhood the night before to declare that all illegal African migrants had to leave . . . immediately. Pakistani laborers began trying to help police by catching African workers, and clashes began.”
In the riots that accompanied the crackdown in Riyadh’s desperately poor Manfuhah district, home to many migrants, at least five people were reportedly killed , including Ethiopian and Sudanese migrants and several Saudi nationals. Ethiopian diplomatic sources reported that three Ethiopian citizens had been killed.
It appears that the state’s crackdown was not only directed at immigrants, who lacked documentation, but a video posted on YouTube shows graphic violence indiscriminately directed against a group of people because of their national origin. In it, mobs brutally attack Ethiopian immigrants, several of whom are then pictured dead and injured.
A discriminatory dragnet was also described by Migrante International, a support group for Filipino overseas workers. It warned that Filipinos in Saudi Arabia are now in danger of being “violently dispersed, arrested and detained by Saudi authorities as crackdowns against undocumented migrants resume.”
The Catholic AsiaNews.it interviewed domestic helper Amor Roxas, 46, who was among 30 Filipinos recently deported, who said, “Filipino workers were treated like animals, locked in a cell for days with their feet shackled.” As of two weeks ago, the Philippine government estimated that over 6,700 undocumented Filipino workers are being held in prison in the Saudi cities of Jeddah, Riyadh, Al Khobar, and Damman.
The Filipino migrants said that the Saudi police rounded them up and placed them in a crowded cell for four days where they had no access to their embassy or any other outside assistance. “Our feet were chained,” added Yvonne Montefeo, 32.
Saudi Arabia’s crackdown on undocumented workers began last January as part of a Saudi policy to increase employment for Saudi nationals but was suspended until early November to allow millions of migrant workers to obtain permits. In all, there are thought to be 7.5 million foreign workers in that country, nearly a third of the total Saudi population. The campaign, which continues, is expected to force out 2 million workers. Many thousands of Ethiopians, Bangladeshis, Indians, Filipinos, Nepalis, Pakistanis, and Yemenis have already left the country in the past three months.
Even migrants with legal permits to work in the Kingdom lack fundamental rights, including the right to worship. They are not permitted a single church. If Christian and non-Muslim foreign workers die on the job, their remains cannot be buried in Saudi Arabia and must be deported back to their home countries. Many live and work in Saudi Arabia as chauffeurs, domestic workers, and common laborers for decades, yet they are not adequately covered by the labor law, which can leave them without redress for employer abuse and exploitation. Women domestic workers are at particular risk of sexual violence and slave-like conditions .In its May 2013 report on Saudi Arabia, entitled “Unfulfilled Promises” in reference to Saudi pledges to reform made to another U.N. human-rights body, Amnesty International describes human-rights violations faced by migrants:
The Saudi government recently declined to take its seat on the U.N.’s Security Council. For the sake of decency, it should do the same for the Human Rights Council. -- The article was first published on National Review

Typical abuses include long working hours, non-payment of salaries, refusal of permission to return home after completing contracts, refusal to transfer sponsorship and withholding of passports. Domestic workers who flee their employers can be arrested and charged with absconding. Some migrant workers experience physical abuse by their employers, but face enormous challenges in seeking legal remedies. Migrant workers who are able to take their employers to court find themselves embroiled in court cases that can last for years.Here’s an example from the Amnesty report:
In 2011, L P Ariyawathie, a Sri Lankan employed as a domestic worker, was found to have 24 nails and a needle driven into her hands, leg and forehead when she returned to Sri Lanka. She said that the injuries had been inflicted by her employer when she complained about her heavy workload. It is unclear whether the Saudi Arabian authorities investigated the matter.Countless other egregious human-rights violations are occurring simultaneously in Saudi Arabia, of course, including against its large foreign-worker population. The Saudi government is infamous as a gross violator of human rights across the board. This will not, however, prevent the Saudi government, over the next three years, to sit in judgment of the human-rights record of the United States and the rest of the world.
The Saudi government recently declined to take its seat on the U.N.’s Security Council. For the sake of decency, it should do the same for the Human Rights Council. -- The article was first published on National Review
ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ሽሬ ለመሄድ ወደ መቀሌ አውቶብስ ተራ ሄድኩና በሰላም ባስ አውቶብስ ተሳፍሬ ጉዞየን ጀመርኩ:: እየተጓዝን እያለን በተቀመጥኩበት ወንበር አጠገብ ሁለት ሰዎች ነበሩ:: ሰዎቹ ከዛ በፊት አይቻቸው አላውቅም:: ሁለቱም አካል ጉዳተኞች ናቸው:: በመንገዳችን እየተጓዝን እያለን ሁለቱ ሰዎች የድሮ ትዝታቸው እያነሱ እያወሩ ነበሩና እኔም የነሱ ወሬ አዳምጥ ነበርኩ:: እንደዛ ቆየሁና ወሬያቸው ታሪካዊና የድሮ ትዝታቸው ስለጣመኝ በመሃላቸው ገባሁና ተዋወቅኩዋቸው:: እነዛ ሰዎች ሁለቱም የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች የነበሩና በትግሉ ጊዜ አካላቸው የተጎዱ መሆናቸው አወቅኩ:: እንደዚህ እያወራንና እየተጨዋወትን ረጂም ጊዜ አለፈ:: በጨወታችን ማሀል አንዳንድ ጥያቄዎች አቀርብላቸው ነበር:: እነሱም ለምጠይቀውን መልስ ይሰጡኝ ነበር:: በመቀሌ ከተማ ፍረስወአት የሚባል የእንጨትና የብረት ሥራዎች የሚሰራና ሥራው በአካለ ጉዳተኞች የሚካሄድ ድርጅት አለ:: ከአስር ዓመት አካባቢ በፊት በድርጅቱ ብዙ ረብሻዎች የሥራ ማቆም አድማና ሰላበማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ እንደአደረጉና በፀጥታ ኃይሎች እንደታገዱ አውቅ ነበር:: በዛን ጊዜ ያን ችግር በሚመለከት ብዙ ጊዜ በጋዜጦች ፅፌ ነበር:: የችግሩ መነሻ የሆነው በድርጅቱ ብልሹ አስተዳደርና በሰራተኞች መካከል የነበረ የአሰራር ብልሹነት ችግር ምክኒያት ነው:: ምክኒያቱም የአስተዳደር ሥራ በአካለ ጉዳተኞች ያልሆኑ ሰዎች ይካሄድ ስለነበረና እነሱ ደግሞ የሚፈጥሩት ችግር ነው:: ይህን ሁሉ እያነሳን ብዙ አወራን ሃሳብ ለሃሳብ ተለዋወጥን:: ህወሓት በመጀመርያ አደረጃጀቱ እንዴት ነበር? የሚል ጥያቄ አቀረብኩላቸው:: መጀመርያ ላቀረብኩት ጥያቄ ተሎ ብለው መልስ አልሰጡኝም:: ስለዚህ የኔ ጥያቄ ያስቸገራቸው መሆኑ ተረዳሁና ዝም አልኩ:: ከዛ በኋላ ቀጠልኩና ይህን አሁን ያለ የህወሓት (1/5) የሚል አደረጃጀት አሁን ነው የጀመረው? ወይስ ቀደም ብሎ ነው የሚል ጥየቄ ሰነዘርኩ:: ከዛ በኋላ ተዘግቶ የነበረ አንደበታቸው እንደገና ተከፈተና ብዙ ነገሮች መናገር ጀመሩ:: ከዛ በኋላ እየተግባባን ሄድንና ብዙ ነገሮች ለማወቅ ቻልኩ:: ለምሳሌ ወደ ህወሓት የገባው ሁሉ ለማለት ይቻላል በፍላጎቱና የቢሄር ጭቆና ለመታገል ብሎ ነው የገባው:: ነገር ግን ወደ ህወሓት ከተቀላቀለ በኋላ የህወሓት መዋቅር ምን ይመስል ነበር? የሚል ጥታቄ መነሳት ያለበት ጉዳይ ነው:: ህወሓት ከተመሰረተ ጀምሮ የሚከተለውን የአደረጃጀት መዋቅር የነበረው:: 1ኛ ከፍተኛ ታመኝ ካድሬ ወይም የማለሊት አባል:: 2ኛ የማለሊት አባል:: 3ኛ የማለሊት እጩ አባል:: 4ኛ የማለሊት መሰሶ (ዓንዲ ውዳበ) አባል:: 5ኛ ዋህዮ የመሰረታዊ ህዋስ አባል:: እነዚህ መዋቅሮች የህወሓት መሰረታዊ መዋቅሮች ናቸው:: ይህን ዓይነት አደረጃጀት ልክ እንደኮመኒስት አደረጃጀት ነው ምንም ልዩነት የለዉም:: ይህን መዋቅር በአርሶ አደሩ በከተማ ነዋሪ እንደታጋዮች አደረጃጀት እኩል ነበር:: ልዩ የሚያደርገው ግን በሕብረተሰቡ የሚደረግ የነበረ አደረጃጀት እስከ ቤተሰብ በቤት ውስጥ የመአድ አደረጃጀት ነበር:: ይህ ደግሞ ባል ለሚስቱ ሚስትም ለባሏ ልጆች ለወላጆቻቸው እንዲሳለሉና በቤተሰቡ አንድነት እንዳይፈጠር ያደርግ ነበር:: እስከ ባልና ሚስት ማፋታት ይደርሱ ነበር:: እንደዚህ እያወራን አክሱም ከተማ ደረስን እዛም ምሳችን በላን:: በምሳ ጊዜም ብዙ ነገሮች እያነሳን አወራን:: ነገር ግን ወሬያቸን በህወሓት ዙርያ ነው ሁልጊዜ የሚሽከረከረው:: እነዚህ ላይ የተዘረዘሩ መዋቅሮች የህወሓት መሰረታዊ አካሎች ናቸው:: በነዚህ መዋቅሮች አባል የሆነ ሰው ህወሓት እንዳለው መሆንና መሄድ አለባት:: ይህን ዋና መሰረታዊ ግዴታ ነው አለበለዚያ ከህወሓት አስተሳሰብ ወይም አመለካከት ለመውጣት ከፈለገ ወይም ከህወሓት አስተሳሰብ ለየት ያለ ሃሳብ ለሚሰነዝር ወይም የሚሞክር ሰው በራሱ ላይ የሞት ፍርድ እንደበየነ ማለት ነው:: እንደዛ ያደረገ ሰው ወድያውኑ ተይዞ ወደ 06 (ባዶ ሹሽተ) የሚባል እሱር ቤት ይወሰዳል:: ከዛ የሆኑ ቀናቶች ወይም ሳምንታት ወይም ወራት ታስሮ ከወጣ በጣም ዕድለኛ ነው:: አለበለዚያ ነበረ ሆኖ ይቀራል ማለት ነው:: ይህን ሁሉ እያወራን ሽሬ ደረስንና ሁላችን ወደ መጣበት ተሰማራን እኔ ግን የሰማሁትን ሁሉ መላልሼ ሳስብ ሳወጣና ሳወርድ ዋልኩና አደርኩ:: ነገሩ ሁሉ ገርሞኝ ራሴ በራሴን ማውራት ጀመርኩ እላቹሁለሁ እናንተም ሳትገረሙ አትረሩም!!:: ቀስ በቀስ ለጥያቄ መልስ እያገኘሁ ሄድኩ በተለይ ደግሞ ከዛ በፊት ስለአካል ጉዳተኞች ቀደም ብየ በጋዜጦች የፃፍኩ መሆኔ ከነገርኩዋቸው በኋላ በኔ ላይ የበለጠ አመኔታ ላድርባቸው ቻለና ከዛ በኋላ በኔ ላይ የነበራቸው ፍራቻ እየተዋቸው ሄደ:: እንደሚታወቀው በአመሪካ መንግስት እርዳታ የተቋቋመ የአካል ጉዳተኞች ድርጅት የሚያስተዳድሩት ሰዎች አካል ኢንጂኔር አብደልውሀብ ቡሽራ – መቀሌ ጉዳተኞች አለመሆናቸው አውቅ ነበርኩና ጥያቄዎቹ እዛ ዙርያ እንዲያተኩሩ አደረግኩ:: ምክኒያቱም ከብዙ ዓመታት በፊት እሱን የሚመለከት ብዙ ጊዜ ፅፌ ስለነበርኩና ከዛ የተያያዘ የቢሄር አስተዋፅኦ በሚል ሽፋን ብዙ ታጋዮች ዳንሻና ወደ ሌላ ሰፈራ በሚል ሰበብ ስለተባረሩ የህወሓት መሪዎች ይህን ዕድል በመጠቀም ብዙ ሐቀኛ ታጋዮች ያባረሩበት ጊዜ ስለነበረ እኔም ይህንን ሁኔታ በሚመለከት በተከታታይ በጋዜጣ ፅፌ ስለነበርኩ:: እነዚህ የተባረሩ ታጋዮች ጥያቄዎች ያነሱ ስለነበሩና ህወሓት ደግሞ እንደዛ ያሉ ጥያቄዎች ሲነሱ የራስ ምታት ስለሚሁበት ነው:: ለምሳሌ ስለኢርትራ ጉዳይ ማናቸውም ጥያቄ መነሳት የለበትም ባይ ነው ህወሓት:: ምክኒያቱም ህወሓት ሻዕቢያን ሊያስቀይም አይፈልግም:: ህወሓት ያን ሁሉ መዋቅር ለምን አስፈለገው? ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ራሱን ለመጠበቅ ነው የሚል የሚሆን ይመስለኛል:: ምክኒያቱም ህወሓት ህዝብን አቅፎ ወይም በህዝብ ታቅፎ አይደለም የኖረው:: ህዝብ በማስፈራራትና ከህዝብ በመፍራት የኖረ ድርጅት ነው:: ምክኒያቱም ሁልጊዜ በሃይልና በአፈሙዝ የሚያምን ድርጅት መሆኑ ከጅምሩ ጀምሮ የታወቀ ነው:: ምንጊዜም ችግሮች ሲያጋጥሙት በውይይት ከመፍታት ይልቅ በጦርነት መፍታት ያስቀድማል:: ምክኒያቱም ሁልጊዜ እየተፈራ እንዲኖር ይወዳል ወይም አመራሩ እንደዚህ ይወዳሉ ማለት ነው:: የመሪዎቹ ዕቅድም ስትራተጂም እንገዛ ነው ጥይት ነው የሚቀናቸው:: ከነዛ ሰዎች ብዙ ካወራን በኋላ ወደ መተማመን ደረጃ ደረስን እኔም ቀለል አለኝና ላይ ያቀረብኩዋቸው ጥያቄዎችና መልስ ያላገኘሁባቸው ቀስ እያልኩ እንደገና መጠየቅ ጀመርኩ ነገር ግን ቀለል ያሉ ጥያቄዎ በማስቀደም ነው:: እነሱም ስለንሮ ውድነትና የአካለ ጉዳተኞች ንሮ ምን ይመስላል የሚሉ ዓይነት ናቸው:: እኔ ራሴም ብዙ ወንድሞችና ዘመዶች በትግል ጊዜ ታጋዮች የነበሩ ከፊሎቹ በጦርነት የተሰዉ እንደ ጃዕፈር ወሃብረቢና መንሱር ወዲ ካድራይ የመሰሉ:: ጃዕፈር ከኢድዩ ጋር በተካሄደ ጦርነት ሸራሮ ላይ የተሰዋ ነው:: መንሱር ወዲ ካድራይ ደግሞ የበጦሎኒ (ሻለቃ) መሪ የነበረና ምጉላት በሚባል ተራራ ላይ በተገረው ጦርነት የተሰዋ ነው:: ሌሎች ደግሞ በትግሉ የነበሩና የት እንደገቡ የማይታወቁ አሉ:: እነዚህ ሰዎች የት ሄዱ የሚል ጥያቄ እስከ አሁን መልስ አላገኘም:: በዚህ ላይ ደጋግመህ ጥያቄ ማቅረብ እንደወንጀል እንጂ እንደመብት አይወሰድም:: ስለዚህ እየፈሩ መጠየቅ ደግሞ አደገኛ ስለሚሆን ይቅር እየተባለ ቆይተዋል:: መጨረሻው ምን እንደሚሆን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው:: ወደ መቀሌ ከተመለስኩ በኋላ ከነዛ ሰዎች አንዱ አገኘሁትና አብረን አንድ ቦታ ላይ ሻሂ ቡና ካልን በኋላ ወደ ቤት ወሰድኩትና እዛ ብዙ ጊዜ እየተገናኘን ጭውውታችን ቀጠልን:: ስለህወሓት ተነግሮ ወይም ተፅፎ የማያልቅ ታሪክ በየጊዜው እያነሳንና አዳዲስ ነገሮች እያገኘን እናወራለን:: እሱም እንደተለመደው የችግር ታሪክ ነው እንጂ ደስ የሚል ታሪክ አልነበረም:: እንደዚህ የሆኑበት ምክኒያት ላይ እንደተገለፀው የህወሓት መሪዎች በህዝቡ ውስጥ ሽብርና ፍራቻ እንዲሰፍን ስለያዘወትሩ ነው:: ምናልባት የስልጣን ዕድሜያቸው ያራዝምላቸው እንደሆነ ምን ይታወቃል በማለት ነው የሚመስለው:: ይህን ዓይነት አስተሳሰብ ጊዜ ያለፈበትና ደስ የማይል ሁኔታ ይፈጥራል:: ምክኒያቱም የህወሓት መሪዎች ቀና አስተሳሰብና ጥሩ ሥራ መስራት እንደድክመት አድርገው ስለሚያዩት ነው:: ይህን ደግሞ የደካሞች አስተሳሰብ መሆኑ አልተረዱትም:: ማንም ሰው ስለህወሓት ካወራህ እባክህ ተወይ ይለሃል ከፍራቻው የተነሳ እንጂ ስለህወሓት የሚለውን ነገር አጥቶ አይደለም:: ነጋዴ ከሆነ ተወይ ባክህ አምና የከፈልኩት ግብር ይበቃኛል አሁን ደግሞ ሌላ ምክኒያት ፈጥረው በግብር ይቀጡኛል ይላል:: ማንም ሰው ስለህወሓት ብታነሳለት ተው ባክህ እነዚህ ሰዎች ያው ናቸው እንደውሃ ቢወቅጡት እንቡጭ ናቸው ይላል ሌላ ደግሞ ያውም ብሶባቸዋል ይላል ስለህወሓት እረ ስንቱ:: ህወሓቶች ጎደሎቻቸው ብትነግራቸው ጎደሎውን በማረም ፈንታ ይባስ ብለው ይቀጥሉበታል ይለሃል አንዱ:: የነዚህ ሰዎች አካሄድና አሰራር ምኑ ቅጡ አይታወቅም ያው ነው ብትወቅጠው እንቡጭ ነው:: ይህን (1/5) የሚባል አደረጃለት ህወሓት አዲስ ፋሽን አመጣ ብየ አስብ ነበር ለካስ የድሮና ከመጀመርያው ጀምሮ ይጠቀምበት የነበረ ነው:: —- ኢንጂኔር አብዱልውሀብ ቡሽራ – abdulwehab2005@yahoo.com ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com posted by Aseged Tamene
ኢንቨስትመንት፤ “ከዝንጀሮ” ፖለቲካ ጋር ምን አንድ አደረጋቸው?
በሕገ ወጥ መንገድ ሀገሬ ገብተዋል በማለት ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ በስራ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን ላይ በሳዑዲ አረቢያ ምድር ከተፈጸመ ሳምንት አለፈው። ሰብዓዊነት የጎደለው የሰው ህይወት ማጥፋት፣ የአካል ማጉደል እና የስነ ልቦና ድቀት በዜጎቻችን ላይ ሲፈጸም የዓለም ሕዝብን ያሳዘነ ተግባር ነበር። በተለይ የኢትዮጵያን መንግስት እና ሕዝብን ክፉኛ ያስቆጣ ፀያፍ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነበር። አሁንም የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ በፈጸመው ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ በይፋ ይቅርታ የጠየቀበት ሁኔታ አለመኖሩ የሚያስቆጭ ነው።
በዚህ ጽሁፍ ሳዑዲ አረቢያ ከሕዝቧ ሥነ-ሕዝብ (ዲሞግራፊ) አንፃር እየቀረበ ያለው የመከራከሪያ ነጥቦች ምን ይመስላሉ? የሰነድ አልባ ስደተኞች ፍልሰት መነሻዎች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ምን ይመስላሉ? የስደት የፖለቲካ ቀውሶች በምን መልኩ ሊታዩ ይገባል የሚለውን ለመመለስ ይሞክራል።
የሳዑዲ አረቢያ ዲሞግራፊ ምን ይመስላል?
እ.ኤ.አ. አፕሪል 2010 በሳዑዲ አረቢያ በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ አጠቃላይ የሕዝብ ብዛታቸው 27 ሚሊዮን 136 ሺህ 977 ነው። ከዚህ ውስጥ 18 ሚሊዮን 707 ሺህ 576 የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት ያላቸው ሲሆን 8 ሚሊዮን 429 ሺህ 401 የሳዑዲ ዜግነት የሌላቸው በሳዑዲ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው።
በእድሜ መዋቅር ሲተነተን፤ ከዜሮ እስከ አስራ አራት ዓመት፣ ሰላሳ ሁለት ነጥብ አራት ከመቶ (32.4%)፤ ከአስራ አምስት እስከ ስልሳ አራት አመት፣ ስልሳ አራት ነጥብ ስምንት ከመቶ (64.8%) እንዲሁም ከስልሳ አምስት ዓመት፣ በላይ ሁለት ነጥብ ስምንት ከመቶ (2.8%)ናቸው። የአጠቃላይ የሕዝቡ አማካኝ እድሜ 25.3 ነው። ከዚህ ውስጥ የወንዶች አማካኝ እድሜ 26.4 ሲሆን የሴቶች አማካኝ እድሜ 23.9 ነው። የሕዝብ እድገቱ በዓመት 1.536 ከመቶ ነው።
የመኖሪያ ዕድሜ ጣሪያቸው ሴቶች 75.9 ሲሆን የወንዶቹ 71.93 ናቸው። ሰማንያ አምስት በመቶ በከተማ ውስጥ የሚኖር ሕዝብ ነው። የሕዝቡ ስብጥር ዘጠና ከመቶ (90%) አረብ ሲሆን የተቀረው አፍሮ አረብ ነው። በሃይማኖት ደረጃ ሰማንያ አምስት ከመቶ ሱኒ ሲሆኑ አስራ አምስት በመቶ የሚሆኑት ሺአት ናቸው። የሳዑዲ መንግስት በመካና መዲና ከተሞች ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች እንዲገቡ አይፈቅድም።
በሳዑዲ አረቢያ ግዛት ውስጥ በተለይ ከኤዢያ ሕንድ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽ፣ ኢንዲኔዢያ እና ፊሊፒንስ በብዛት ይገኛሉ። ከምዕራቡ ዓለም በብዛት ባይሆኑም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ሲሆን አኗኗራቸው ግን በግል በተዘጋጁ ማረፊያዎች ውስጥ ነው።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ8 ሚሊዮን 429 ሺህ 401 (ከስምንት ሚሊዮን አራት መቶ ሺ ሃያ ዘጠኝ አራት መቶ አንድ) የሳዑዲ ዜግነት ከሌላቸው ነዋሪዎች መካከል 350ሺ ኢትዮጵያዊያን በሕጋዊ መንገድ ተቀጥረው በመስራት ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ ከ60 እስከ 80ሺ ሰነድ አልባ ስደተኛ (undocumented immigrant) ኢትዮጵያዊያን በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እንደሚገኙ ይገመታል።
ከላይ ከሰፈረው የሳዑዲ አረቢያ ዲሞግራፊ አንፃር አብዛኛው የሳዑዲ አረቢያ ዜጋ ወጣቶች መሆናቸውን መረዳት አስቸጋሪ አይደለም። ለእነዚህ ወጣቶች ስራ ማቅረብ ያቀተው ንጉሳዊ አገዛዝ እንደአማራጭ የወሰደው የስደተኛውን ቁጥር መቀነስ ነው። በተለይ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከሀገሩ በከፍተኛ ፍጥነት እያስወጣ ይገኛል። ይህ ተግባራቸው ከሉዐላዊነት አንፃር እንደመብት ቢወሰድም የስደተኞችን ሰብዓዊ ክብር መንካትና ለሕልፈት መዳረጋቸው ዓለም ዓቀፍ ውግዘት ያስከተለባቸው ተግባር ሆኖ አልፏል።
ሰነድ አልባ ስደተኞ ከኢኮኖሚ ሞዴል አንፃር
የስደተኞች አጠራር በራሱ አከራካሪ ነጥቦች አሉት። እነሱም ሰነድ አልባ ስደተኞች (undocumented immigrants) እና ሕገ ወጥ ስደተኞች (illegal immigrants) ሲሉ ይጠሯቸዋል። ሕገ ወጥ ስደተኞች ተብለው የሚጠሯቸው የአንድ ሀገር የደህንነት ሕግ በመተላለፍ ድንበር አቋርጠው የሚገቡ በመሆናቸው ሲሆን፤ ሰነድ አልባ የሚባሉት ደግሞ በሰነድ አንድ ሀገር ውስጥ ገብተው ሆን ብለው ሰነዳቸውን በመጣል ወይም ከተሠጣቸው የጊዜ ገደብ በማሳለፍ ከሰነድ ውጪ በአንድ ሀገር ውስጥ በስደት ለመቀመጥ የሚሹትን የሚመለከት ነው።
ከኢኮኖሚ ሞዴል አንፃር፤ የኒዮ ክላሲካል ሞዴል ለስደት የሚሰጠው መሰረታዊ መነሻ ‘push-pull’ incentive በሚል ነው። ይህ ማለት ጥገኝነት የሚሰጠው ሀገር ውስጥ ያለውን የህይወት ደረጃ ከሚሰደዱበት ሀገር በአንፃራዊነት በመውሰድ የሚሞግቱበት አቀራረብ ነው። ለተሻለ ጥቅም ፍለጋ የሚደርግ ፍልሰት ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
ሌላው ነፃ የንግድ ቀጠና በምክንያትነት ያነሳል። ግሎባላይዜሽን የፈጠረው የኢኮኖሚ ዕድል ዓለም ለነፃ የንግድ ስርዓት እንድትጋለጥ ዳርጓታል። በዚህም የተነሳ ይህ ነፃ የንግድ ስርዓት ለእርሻ እና ዕውቀት ለማይፈልጉ ትንንሽ ስራዎች ብዙ ሰዎች ከሀገር ወደ ሀገር እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗቸዋል። በተለይ የቀን ሠራተኛ የሚፈልጉ የበለጸጉ ሀገራት ይህን መሰል የሰው ኃይል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ በመፍጠር ከሀገር ወደሀገር ያስኮበልላሉ።
ሌላው መዋቅራዊ የበለፀጉ ሀገራት ፍላጎት አንድም የስደት ምንጭ ነው። “structural demand in developed states” በበለጸጉ ሀገሮች ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ለመስራት በማይፈልጓቸው ወይም በማይሰማሩበት የስራ ዘርፎች በማደግ ላይ ካሉ ሀገሮች በመውሰድ የሚፈልጉትን ስራዎች ያሰራሉ። ይህን የስራ ክፍተት ለመሙላት በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች ስደትን በአማራጭነት ይወስዱታል።
ድህነትም ሌላው የስደት አንዱ ምንጭ ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ በሚፈጠር ስር የሰደደ ድህነት ዜጎች ወደ ሌላ ሀገር እንዲሰደዱ አንድ ምክንያት ነው። በተለይ ድህነት በተንሰራፋበት ሀገር ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ሲኖር ነገሮች ሁሉ ወደከፋ ሁኔታ ይቀየራሉ። ይህን መሰል ሁኔታን ለማምለጥ ስደት በአንድ አማራጭነት ይቀርባል። ሌላው የተበታተኑ ሰዎች ወይም ቤተሰቦች አብረው ለመኖር ካላቸው ፍላጎት (family reunification) የተነሳ በአንድ ለመሰብሰብ በሚያስችላቸው ሀገር ውስጥ ለመሰባሰብ በሚያደርጉት ጥረት ስደትን በአንድ አማራጭነት ይወስዱታል።
ሌላው ጦርነት በምክንያነት ይወሰዳል። በአንድ ሀገር ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የእርስ በእርስ ጦርነት ሲካሄድ ዜጎች ከጦርነት ለማምለጥ ወደ ጎረቤት ሀገራት ይሰደዳሉ። በሚኖሩበት ሀገር በፖለቲካ ወይም በሃይማኖት ወይም በዘር ወይም በተለያዩ ችግሮች ለአደጋ ሲጋለጡ ዜጎች ስደትን በአንድ አማራጭነት ይወስዱታል። በዚህ አይነት ሁኔታ በአንድ ሀገር ውስጥ ሲሰደዱ ከስራ ፈላጊነት ወይም ከተራ ጥገኝነት ጥያቄ ባሻገር የፖለቲካ ጥገኝነት ያነሳሉ።
ሌላው ዜጎች፤ ዜግነታቸው በአምባገነን መንግስታት ሲነጠቅ ወይም ሲሻር ወደ ሌላ ሀገር ለመሰደድ ይገደዳሉ። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆኑት በማይናመር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የሮሂነረገሬያ ብሔሮች በማይናመር መንግስት ሙሉ ለሙሉ ዜግነታቸው በመገፈፉ ሀገር አልባ አድርጐ በትኗቸዋል። በተለያዩ ቦታዎች ተሰደው ቀርተዋል።
የስደት የፖለቲካ ቀውሱ እንዴት ሊያዝ ይገባል?
ከላይ በአሃዝ እንደተቀመጠው በሳዑዲ አረቢያ 350ሺ ኢትዮጵያን በሕጋዊ መንገድ ተቀጥረው ስራቸውን እየሰሩ እንደሚገኙ ይገመታል። በሕገወጥ መንገድ አስከ 80ሺ ኢትዮጵያዊያን ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። እስከ ትላንት ድረስ ከ37ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵዊያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በቀጣይ የቀሩት ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አሁን የተፈጠረው ችግር ለመፍታት የመጀመሪያው አማራጭ ሁሉንም ነገር በሰከነ መልኩ መመልከት እና አማራጮቹን ማየት ነው። ነገሮች ሁሉ ብስለት ከጎደለው እርምጃ ሊፀዱ ይገባል። ይህም ሲባል ሁሉም የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በሕጋዊ መንገድ እየሰሩ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የስራ ዋስትና የሚያረጋግጥ፣ ከማኛውም የስነ ልቦና እና አካላዊ ጥቃት የሚጠብቅ መሆን አለበት። እንደሙሴ ጊዜ አይን ያጣ አይኑን የሚባልበት ዘመን በዘመነ ስልጣኔ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው።
በተለየ በሳዑዲ ዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ በአገራችን የሚገኙ የሳዑዲ ባለሃብቶች ላይ እርምጃ እንዲወሰድና በዚህም የገደለ፣ ይገደለ የሚለው የሀሙራቢ ሕግ እንዲተገበር የሚናፍቁ ወገኖች አልፎ አልፎም ቢሆን ኃላፊነት የጐደለውን ኀሳባቸውን በመገናኛ ብዙሃን ጭምር ለማሰራጨት ሲሞክሩ መስተዋላቸው አልቀረም።
የክብር ዶ/ር ሼህ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ ኢትዮጵያ የተወለዱባት፣ የተማሩባት አገራቸው መሆኗን እንኳን በመካድ ከሳዑዲ ችግር ጋር ነገሩን በማቆላለፍ በሺህ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻቸው የከፈቱትን የሥራ ዕድል ዘግተው እንዲወጡ የሚወተውቱ እንዳሉ ታዝበናል። ሼህ መሐመድ ሐብታቸውን በማፍሰስ ሥራ ከመፍጠር ባሻገር በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር በግብርና ታክስ መልክ ለአገሪቱ በማስገባት እያደረጉ ያሉትን አስተዋፅኦ እንኳን ግምት ውስጥ አለማስገባት መከራከሪያ ነጥባቸውን ምክንያት አልባ ማድረጉ አሻሚ አይደለም። የክብር ዶ/ር ሼህ መሐመድ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያላቸውን ጠቅላላ ኩባንያዎች ብዛት ከ70 በላይ የደረሰ ሲሆን፤ ጠቅላላ ኢንቨስትመንታቸውም ከአምስት ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት እንደሆነ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ወገኖቻችን ከሳዑዲ ማባረር እኚህን ባለሃብት ከማባረር እኩል ለማየትና ለማነፃፀር መሞከርም መነሻው ከወገናዊነት የመነጨ ሳይሆን የታመቀ የራስ ፍላጐትን ለማስፈፀም ያስመስላል። አሁንም ቢሆን ተፈናቅለው ለመጡ ወገኖቻችን የክብር ዶ/ር ሼህ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ ድጋፍ እንደማይለያቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። ይህን ሊያደርጉ የሚችሉበት መሠረታዊ ምክንያት ሊሆን የሚችለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በስሎ በሚገኝ አጀንዳ ላይ በመንጠላጠል የኢንቨስተሮችን ስም የፖለቲካ አጀንዳ ማወራረጃ ማድረግ ሃላፊነት የተሞላት ተግባር አድርጎ መቀበል አደገኛ ነው። ሁሌም የበሰለ ነገር ብቻ እንደ ዝንጀሮ ማደን ለማን እንደሚጠቅም አዳኙ ብቻ ነው የሚያውቀው። ሕዝባዊ መሰረት ጥሎ ገዢ ፓርቲን መታገል በራሱ አንድ መንገድ ሆኖ ሳለ ሀገራቸውን ጠቅመው ለብዙ ዜጎች የስራ እድል የፈጠሩ የሀገሪቷ አንጡራ ሃብት የሆኑ ኢንቨስተርን የጦስ ዶሮ ለማድረግ መመሞከር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።
ስለዚህም እንደዝንጀሮ ሁሌም የበሰለውን ከማደን ሕዝባዊ መሰረት ያለው የፖለቲካ ትግል ውስጥ መግባት አጥብቆ ይመከራል።
Source/http://ethioforum.org/
ከሳዑዲ የተመለሱ 7000 በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በየመን ችግር ላይ ናቸው – ግሩም ተ/ሃይማኖት (ጋዜጠኛ) ከየመን
በባህር ተሻግረው በየመን በኩል ያንን እልህ አስጨራሽ በረሃና ፈተና አልፈው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ከአበሀ፣ ከሚስ ምሽት፣ ናጂራንና አሲር… ከመሳሰሉት የመን ድንበር አቅራቢያ ያሉ የሳዑዲ ከተማዎች ላይ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን እየገቡ ነው፡፡ ጅዳ ሄደው ወደ ሀገራቸው ለመግባት የማይችሉ በመሆኑ የመን መግባት አማራጭ ሆኖባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ወደ ጅዳ ለመሄድ በየቦታው ሊፍጸምባቸው ወይም ሊገጥማቸው የሚችለውን ችግር በማሰብ ነው፡፡
እነዚህ ኢትዮጵያዊያ ወደ የመን የገቡት በሁለት መንገድ ሲሆን አንደኛው ከላይ እንዳልኩት ያላቸው አማራጭ በመሆኑ ባሳቸው ፍላጎት ሲሆን ሁልተኛው እና ወደ 3000 የሚጠጉትን ግን የሳዒዲያ መንግስት የመናዊያኑን እንደ ቆሻሻ በጭነት መኪና አምጥቶ ድንበር ላይ ሲገለብጣቸው አብሮ የጫናቸው ናቸው፡፡
እነዚህ የሳዑዲ መንግስት አምጥቶ የገለበጣቸው ራሱ በሁለት መንገድ ይከፈላሉ፡፡ ድንበር ድረስ እንሂድ ብለው ለምነው የተጫኑ መኖራቸውን ካናገርኳቸው ልጆች ተረድቻለሁ፡፡ ሁለተኞቹ የሳዑዲ ፖሊሶች አፍነው ጭነዋቸው የሚያመጧቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከጅዳ ታፍነው የተጫኑ ሁለት ልጆች በስልክ አግኝቻለሁ፡፡ እርጉዞች የተደበደቡ የተደፈሩ ሁሉ ህዝቡ፣ መንግስት እንዳዳያቸው ተብሎ ወደ የመን እንደተጣሉ ነው ያናገርኩት ልጅ የገለጸልኝ፡፡
ሀረድ የሚገኘው IOM (International organization of migrant) ካምፕ እየተቀበላቸው ሲሆን በአሁኑጊዜ በፊት MSF( medical san frontan) ያዘጋጀውን ካምፕ IOM እየተጠቀመበት ስለሆነ እሱንም ከፍተውታል፡፡ ቢሆንም ይህ ቦታ ከሳዑዲ እና የመን ድንበር ከ 100 ኪ.ሜ በላይ ርቀት ስላለው ይህን ሁሉ መንገድ በእግር መጓዝ ግድ ብሏቸዋል፡፡ ያም ቢሆን መንገዱ በሰላም እንዳያልቅ መካከል ላይ አፋኞች ከሳዑዲ ገንዘብ ይዘው ነው የሚመጡት በማለት የተለያየ ጉዳት እያደረሱባቸው ነው፡፡ ዘርፈው፣ ደብድበው፣ ደፍረው ለፖሊስ ስለሚያስረክባቸው እንዲሁም መንገድ ላይ በቁጥጥር ስር ስለሚያውላቸው በአሁኑ ሰዓት ሰነዓ ኢሚግሬሽን (ጀዋዛት) እስር ቤት ከ3200 በላይ እንደሚገኙ አይቻለሁ፡፡
ባለፈው እርብ በወርሃዊ ፕሮግራማችን መሰረት እስረኞች ለመጠየቅ ስንሄድ 2700 አካባቢ ኢትዮጵዊያን ስደተኞች እስር ቤቱን አጣበውት ነበር፡፡ አሁን ግን ከ3200 በላይ በመሆናቸው እስር ቤቱ ሞልቶ ጊቢው ውስጥ እና ከጊቢው ውጭ ሁሉ ፈሰው ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ወገኖች በርሃብ እንዳይሞቱ ሁላችንም ማድረግ ያለብንን ማድረግ አለብን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሳዑዲ ላለው ስደተኛ በኢሳት ቴሌቪዥን አሰባሳቢነት የተጀመረው ነገር ከሳዑዲ ሸሽተው የመን ለሚገቡትም በርሃብ ሊያልቁ ነው እና ትኩረት እንዲደረግበት ጥያቄዬን አቀርባለሁ፡፡ በይበልጥ ሰሞኑን ወደ ቦታው በድጋሚ ሄጄ ማየት ስለምፈልግ ያለውን ሁኔታ አሳውቃለሁ፡፡
በግሩም ተ/ሀይማኖት

ዶክተር ሀይሉ የተቃዋሚዎችን ድክመት በድፍረት ተናገሩ
የዛሬዋ ኢትዮ ምህዳር ስለ ተቃዋሚዎች ውህደትና ህብረት ሰፊ ሀተታ ይዛ ወጥታለች፡፡ በተለይ ዶክተር ሀይሉ አራዕያ ስለ ተቃዋሚዎች ውህደት ያነሱት ሀሳብ ወቅታዊና አንገብጋቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
ዶክተር ሀይሉ የተቃዋሚዎችን ድክመት በድፍረት ጽፈዋል፡፡ ዶክተሩ ተቃዋሚዎች ካልተዋሃዱ፣ ካልተባበሩ በስተቀር ምርጫ ሊያሸንፉና ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ አስረግጠው ነግረዋቸዋል፡፡ ዶክተሩ የሚሉት ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ተዋሃዱ፣ ካለፈው ስህተት፣ ከሌሎች አገራትም ተማሩ፣ ህዝብን አታስገዙ፣ ጥቂት ተስፋ ሰጥታችው ዋናውን ተስፋውን አትንጠቁ ነው፡፡
እንደ እሳቸው አባባል ግን የተቃዋሚው ጎራ ለመዋሃድ የሚያስችል አላማም ሆነ ወኔ አይታይበትም፡፡ እስካሁን ያዳከመውና፣ ህዝብን ተስፋ ያስቆረጠውም ይህ አመሉ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ያሉትን ሁሉ በሰፊው ተንትነዋል፡፡ እንደ እኔ ዶክተሩ ያነሱት እጅግ ወቅታዊ ጥያቄ ነው፡፡ አጀንዳውን ያነሱትም በገለልተኝነት መሆኑን ከጽሁፋቸው መረዳት ይቻላል፡፡ ውጥንቅጡ ለወጣው የተቃዋሚው ጎራም ከዚህ ውጭ መፍትሄ ያለው አይመስለኝም፡፡ ዶክተሩ ጉዳዩን በሚዲያ ብቻ ሳይሆን ለተቃዋሚዎች እንዲወያዩበትም መድረክ አዘጋጅተው አቅርበውታል፡፡
የዶክተሩን ጩኸት የሚሰማቸው ከተገኘ በተቃዋሚው ጎራ መልካም ነገር እንደሚኖር የሚጠበቅ ነው፡፡ ግን ይች በተናጠል ሰላማዊ ሰፍል ከመጥራት፣ አዳራሽ ውስጥ በጥቂት ሰዎች ስብሰባ ከማድረግ፣ መግለጫ ከማውጣት፣ በዓመት አንድ ቀን በኢቲቪ ከመከራከር ውጭ ግብ የሌላቸው በርካታ ፓርቲዎች በተሰበሰቡበት ማን ይሰማቸው ይሆን? እጅ መጠቋቆሙን፣ መጠላለፉን፣ ግለሰብ ማግነኑን እንደ ትልቅ ስኬት የሚያዩት፤ ከህዝብ ስልጣን ይልቅ ‹‹ፓርላማ›› ለመግባት የሚቋምጡት ‹‹ፖለቲከኞች›› ያዳምጧቸው ይሆን? ምሁራን ምን ያህል ይደግፏቸዋል?
የጥናቱን ሶፍት ኮፒ ያገኛችሁ ኢትዮ ምህዳርን ለማያገኙ ኢትዮጵያውያን ፌስ ቡክ ላይ ብትለጥፉላቸው መልካም ነው፡፡
Getachew Shiferaw
አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር የሚሆኑት መቸ ነው?!!!
ነፍሳቸውን ይማረውና(ድንገት ነፍስ ካላቸው፣መንፈስ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ነው)የቀድሞውና ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ በሞት ካረፉና ካረፍናቸው ጀምሮ ታላቋ ኢትዮጵያ ያለ ሀገረ ገዥ የቀረች ይመስላል፡፡ሆደ ቡቡነታቸውን ለመለስ ዜናዊ ሲነፋረቁ ያረጋገጥንላቸው ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ወንበሩ ላይ ቢቀመጡም እንደ ሁለት ወር ህጻን ከተጎለቱበት አላንቀሳቅስ ያላቸውን እርኩስ መንፈስ ሁለት ሰባት ቢታዘዝለት መልካም ነበር፣ነገር ግን ሰውየው በኢየሱሴ የዳኑ ናቸውና ጸበልን ከዚያው በጸበልህ የሚሉ መሆናቸው እኛ የእርሳቸውን ታማኞች መፍትሄ እንዳናዘጋጅ አድርጎናል፡፡ከሰሞኑ ደግሞ ይህ እርኩስ መንፈስ ምንም አላናግራቸው በማለቱ ጭንቀታችን የከፋ አድርጎታል፣መላ ያለህ ሁሉ ወዲ በል፡፡እርስዎስ ቢሆኑ በዚህ ቀውጢ ሰኣት ያልነገሱ መቸ ሊነግሱ ነው፡፡እኔ እንደው የእርስወ ነገር አያስችለኝምና ትንሽ ምክር ቢጤ ጣል ላድርግለዎት፣የ2007 ምርጫ ደርሶ ሱናሜው ሳይጠርግዎት ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቢሞክሯት መልካም ነው እላለው፡፡አይተ በረከት ስሞንስ እስከመቸ ነው የስሁል ሚካኤልን መንበር ተረክበው ሲሽሩና ሲሾሙ ምን አለበት አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚንስትር ቢያደርጓቸው፡፡(ስሁል ሚካኤል በጎንደር የነገስታት ዘመን ከትግራይ የመጡ መስፍን ሲሆኑ ከኋላ ሆነው ሲሾሙና ሲሽሩ የነበሩ ጉልበታም ናቸው)፡፡በመጨረሻም ለሃይለማሪያም ደሳለኝ የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖረኝ እንደሚከተለው ይጠቃለላል፣ታሪክዎ ሲጻፍ ቤተ መንግስቱን ከሚጠብቁት ወታደሮች የተለየ አይሆንምና በጊዜ መላ ቢያበጁ፣ባይሆን ምን ማድረግ እንዳለብዎት ከጠፋብዎ አኔን ያማክሩኝ፡፡የሚሰማን የለምእንጅ ባለ ራዕይውንም መክረናቸው ነበር፡፡ምን ያደርጋል ምክራችን ይዘውት ሽል አሉ እንጅ፡፡Gashaw Mersha
ኢቴቪ ጠፍቷል ያለውን የአኬልዳማ ዶክመንተሪ ፊልም ሙሉ ቅጂ አቀረበ
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር የሆነው አንዷለም አራጌና የብሄራዊ ምክር ቤት አባል ናትናኤል መኮንን በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ እነ አንዷለምን የያዝነው በቂ ማስረጃ ሰብስበን ነው ሲሉ ከቆዩ በኌላ የኢትዩጵያ ቴሌቪዥን ‹‹አኬልዳማ››የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም በማስረጃ መልክ ለእይታ ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡
በፊልሙ የአንድነት የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ የሆነው አንዷለም አራጌ ከግንቦት ሰባት ጋር ግኑኝነት እንዳለው በማስመሰል ከመቅረቡም በላይ የአንድነት አባላት ያልነበሩ በደረቅ ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦችን የፓርቲያችን አባላት መሆናቸውን እንዲመሰክሩ ተደርገዋል፡፡
በህጋዊ መንገድ ፓርቲያችን ከህዝብ ጋር ለመወያየት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የጥናት ጽሁፍ አቅራቢነት አዘጋጅቶት የነበረውን ውይይት በህቡዕ የተዘጋጀ በማስመሰል በፊልሙ ለክስ በሚመች መልኩ መቅረቡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረጃ አሰባስበን ነው የያዝናቸው ማለታቸውን ትዝብት ውስጥ የከተተ ነበር፡፡
አኬልዳማ ፊልም ለህዝቡ በቀረበበት ወቅት በፍርድ ቤት ጉዳያቸው መታየት ያልጀመረን ተጠርጣሪዎች ሽብርተኞች በማለት መፈረጁና በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲያችንን ጭምር ‹‹የግንቦት ሰባት ጉዳይ አስፈጻሚና የሽብርተኞች ተላላኪ››በማለት መፈረጁም አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ የጣብያው ሃላፊዎች እርምት እንዲያደርጉና በአንድነት ፓርቲ የተዘጋጀን ፊልም ለህዝብ እንዲያሳዩ በደብዳቤ ጭምር ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ፓርቲያችን ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ተገድዷል፡፡
ጉዳዩን በ2004 ወርሃ ታህሳስ መመልከት የጀመረው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ልደታ የፍትሃ ብሔር ምድብ ችሎት መዝገቡን ለ15 ጊዜያት ከሳሽና ተከሳሽን ሲያከራክር ከቆየ በኋላ ለታህሳስ 11/2006 ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል፡፡ከትናንቱ ቀጠሮ ቀደም ብሎ የኢቴቪው ጠበቃ አኬልዳማ የተባለው ዶክመንተሪ ፊልም መጥፋቱን እንዲሁም የዶክመንተሪው ሃላፊ የነበሩት ግለሰብ ወደ ውጪ አገር በመሄዳቸው የተነሳ ቅጂውን ለማቅረብ ደምበኞቹ መቸገራቸውን ገልጾ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ዶክመንተሪውን የግዴታ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው በማዘዛቸው በተለዋጭ ቀጠሮ ቅጂውን ይዘው ቀርበዋል፡፡
የአንድነት ጠበቃ ተከሳሽ ያቀረቡትን ፊልም ቅጂ ለማመሳከር እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ይህንን ማዘዝ እንደማይችል በመጥቀስ ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የአንድነት ጠበቃ ተከሳሽ ያቀረቡትን ፊልም ቅጂ ለማመሳከር እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ይህንን ማዘዝ እንደማይችል በመጥቀስ ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ከዳዊት ሰለሞን
Subscribe to:
Posts (Atom)