Tuesday, March 26, 2013

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡ የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።
ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በዘረኝነት ገመድ አስሮ እየረገጠ የሚገዛዉ ወያኔ ለዚህ የበቃዉ በዘረኝነትና በጥላቻ አነሳስቶ ያሰታጠቃቸዉ ገበሬዎች በከፈሉት መስዋዕትነት ነዉ ያለዉ ይሄዉ ህዝባዊ ኃይል ሠላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ከእነዚህ የቀን ጅቦች ለማላቀቅና አገራችንን የእኩሎች አገር ለማድረግ ማንኛዉንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት አለበት ብሏል። የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረዉ የፍትህ፤የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ግቡን እንዲመታ የመጀመሪያዉን እርምጃ የወሰደዉና ትግሉ የሚፈልገዉን የደም መስዋዕትነት ለመክፈል የትግሉ ግንባር የመጀመሪያዉ ደጃፍ ላይ የተሰለፈዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ካሁን በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔን ዘረኝነት፤ዝርፍያ፤ጥላቻና ንቀት ለማስቆም መፍትሄዉ ከአገር እየተሰደዱ በየባህሩና በየበረሀዉ መሞት ሳይሆን ለስደታችን፤ ለመዋረዳችንና ለመረገጣችን ቀንደኛ ምክንያት የሆነዉን የወያኔ ስርአት እዝያዉ አገር ቤት ዉስጥ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ብቻ ነዉ ብሏል።
የወያኔ እህአዴግ ዘመን አብቅቷል፤ከአሁን በኋላ ዘመኑ የኛ የኢትዮጵያዉያን ነዉ ያለዉ የግንቦት ሰባት ዝብባዊ ኃይሎች ቃል አቀባይ ይህንን የኛ የሆነዉን ዘመን እዉን የምናደርገዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ከዘረኝነት ነጻ የምናወጣዉ እንደአንድ ሰዉ ቆመን በጋራ ስንታገል ነዉ እንጂ የአገር ማዳኑንና የመስዋዕትነቱን አደራ ለተወሰኑ ወገኖች ብቻ በመተዉ አይደለም ብሏል። በመቀጠልም ወያኔን ፊት ለፊት ተፋልሞ ወንድሞቹንና እህቶቹን ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአባቶቹ በአደራ የተረከባትን ኢትዮጵያን ለልጆቹ ለማስተላለፍ የሚናፍቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከዛሬ በኋላ ዬት ሄጄ ወያኔን ልታገል የሚል ስጋት እንዳይሰማዉ አሳስቧል።ባለፈዉ ታህሳስ ወር እራሱን ለህዝብ ይፋ ይደረገዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ አያሌ ኢትዮጵያዉያን በየቀኑ እየተቀላቀሉት ሲሆን ይህንን የህዝብ ተገንና አለኝታ የሆነ ኃይል በመቀላቀል የአዲስቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ለመሆን የምትፈልጉ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገራት የምትገኙ ኢትዮጵያዉያን ህዝባዊ ኃይሉ በተከታታይ ለሚያወጣቸዉ መግለጫዎችና ህዝባዊ ጥሪዎች ምላሽ በመስጠት እንዲትተባበሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ጥሪዉን ያስተላልፋል።

በአረመኔው የወያኔ አገዛዝ በግፍ እስር ቤት የታጎሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸው ታወቀ

ድምጻችን ይሰማ የሚል መፈክር አንግበው ላለፉት አስራ ሶስት ወራት አፋኙን የወያኔ አገዛዝ መቆሚያና መቀመጫ በማሳጣታቸው በጭካኔ እስር ቤት የተጣሉት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ፣ ፣ እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በዘረኛውና አረመኔው የወያኔ አገዛዝ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ታፍሰውና ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ በግፍ ታስረው የሚገኙት ሙስሊም የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ፣ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ ባለማወቃቸው በቀለብ እና በልብስ እጦት እየተቸገሩ ነው ብሏል።
ዘጋቢያችን እንደገለጠው በአቃቂ እስር ቤት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ተማሪዎችና መምህራን እስር ቤቱን አጨናንቀው እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ ከነኝህ ታሳሪዎች ውስጥ እጂግ በርካቶቹ ቶርቸር ( አሰቃቂ ድብደባ) ተፈጽሞባቸዋል። ይህም አልበቃ ብሎ ተማሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ የረባ ምግብ አጥተው በመሰቃየት ላይ እንደሚገኙና ልብሶቻቸው በላያቸው ላይ እያለቁባቸው ለእርዛት እየተዳረጉ እንደሆነም ታውቋል።
አሁንም ጭካኔአዊ አሰራው አለማብቃቱና የተለያዩ ታማሪዎች በየጊዜው እየተያዙ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን በማእከላዊ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ከሚገኙት መካከል የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆኑት ኑርየ ካሲም እና ካሊድ ሙሀመድ፣ የጅማ ዩኒቨርስቲዎቹ ያሲን ፈይሞ፣ ሙሀመድ አሚን ከድር፣ እና ጁነዲን ሁሴን፣ የሚዛን ተፈሪው አብዱላኪም አህመድ፣ የወሎ ዩኒቨርስቲዎቹ ጣሂር ሙሀመድ ፣ ሙሀመድ አብዱራሂም እና ሰኢድ ሙሀዲን፣ የጎንደር ዩኒቨርስቲዎቹ ሰኢድ አብርሀም ፣ኦማር ሙሀመድ፣ እና ሊና ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው አብዱላዚዝ ሰኢድ እንዲሁም የአዋሳ ዩኒቨርስቲዎቹ አብደላ ሙሀመድ ይገኙበታል ብሏል።
የሙስሊም ጉዳይ አምደኛ የነበረው ሶሎሞን ከበደ፣ የከሚሴው ዳኢ ጀማል ከበደ፣ የሻሸመኔው ዳኢ አብዱረዛቅ ሼህ አህመድ፣ የከሚሴው ዳኢ ኢክርሀም አብዱ፣ የሀረርጌው ሁሴን ሮባ፣ የድሬዳዋው ሙሀመድ ሀሰን፣ የከምሴው ሁሴን አሊ እና አደም አህመድ አሊ በማእከላዊ እስር ቤት ከታሰሩትና ከፍተኛ ስቃይ ከደረሰባቸው መካከል ይገኙበታል።
የወያኔ ኢህአዴግ ፈረስ የሆነው ሀይለማርያም ደሳለኝ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እርምጃ እንወስዳለን በማለት ሰሞኑን በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የወያኔ ኢህአዴግ ጉባኤ ላይ መዛቱንም ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

Chinese trade with Africa and fears of neocolonialism

Chinese trade with Africa keeps growing; fears of neocolonialism are overdoneA GROUP of five tourists from Beijing passes low over Mount Kenya and into the Rift Valley in their private plane before landing on a dusty airstrip surrounded by the yellow trunks and mist-like branches of fever trees. They walk across a grassy opening where zebras and giraffes roam, snapping pictures while keeping an eye out for charging buffaloes. When they sit down at a table, they seem hungry but at ease. “Last year I went to the South Pole with some friends,” says one of two housewives, showing off iPhone pictures of a gaggle of penguins on permafrost.
Chinese are coming to Africa in ever greater numbers and finding it a comfortable place to visit, work in and trade. An estimated 1m are now resident in Africa, up from a few thousand a decade ago, and more keep arriving. Chinese are the fourth-most-numerous visitors to South Africa. Among them will be China’s new president, Xi Jinping, who is also going to Tanzania and the Democratic Republic of Congo on his first foreign outing as leader.
The origin of China’s fascination with Africa is easy to see. Between the Sahara and the Kalahari deserts lie many of the raw materials desired by its industries. China recently overtook America as the world’s largest net importer of oil. Almost 80% of Chinese imports from Africa are mineral products. China is Africa’s top business partner, with trade exceeding $166 billion. But it is not all minerals. Exports to Africa are a mixed bag (see chart). Machinery makes up 29%.
The size of China’s direct investment in Africa is harder to measure than trade. Last summer China’s commerce minister, Chen Deming, said the number “exceeded $14.7 billion, up 60% from 2009”. Around the same time the Chinese ambassador to South Africa, Tian Xuejun, said: “China’s investment in Africa of various kinds exceeds $40 billion.” Apparently, the first figure is for African investments reported to the government. The second includes estimates of Chinese funds flowing in from tax shelters around the world.
Sino-African links have broadened in the past few years. The relationship is now almost as diverse as Africa itself. But Mr Xi will searchThe size of China’s direct investment in Africa is harder to measure than trade. in vain for the e-mail address of a single African leader who can speak for the rest, rather as Henry Kissinger legendarily struggled to find a single phone number for Europe.

የትግራይ ህዝብ ‘ብኡ የሕልፎ’ በሚል የህወሓትን ጭቆና የተቀበለው ለምንድነው? (ኣብርሃ ደስታ ከመቐለ)

“… የትግራይ ህዝብ በሙሉ የህወሓት ደጋፊ ነው ማለት ኣይቻልም። ብዙ የሚቃወም ኣለ። ብዙ የሚጨቆን ኣለ። በትግራይ የሌለው ጭቆናን የሚያጋልጥ ሰው ነው። በሌሎች ኣከባቢዎች (ከትግራይ ውጭ) ሰው ሲታሰር ወይ ሲገደል የሚናገርለት ወይ የሚጮህለት ወገን ኣለው። በትግራይ ግን የለም። ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም ይላል። ይሄ ነው ልዩነቱ እንጂ በትግራይ ጭቆና ስለሌለ ኣይደለም።”
ከዚህ በመነሳት Prof. Mesfin Wolde-Mariam እንዲህ ጠየቁ:
“አብርሃ ደስታ፤ ያልከውን አምናለሁ፤ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህና አንተ በተመቸህ መንገድ መልስልኝ፤ በትግራይ ሰዎች ሲበደሉና ሲጠቁ ሌላው ሰው ዝም የሚለው በምን ምክንያት ነው?”
መልስ
ኣብዛኛው የትግራይ ሰው የህወሓት መንግስት በዜጎች በደል ሲያደርስ ከመቃወም ይልቅ “ብኡ የሕልፎ” የሚል ብሂል (ወይ ኣባባል) ተግባራዊ ያደርጋል። “ብኡ የሕልፎ” የትግርኛ ኣባባል ሲሆን Literally ‘በዛ ይለፍልን’ (ወይ ‘የባሰ ኣታምጣ’) ዓይነት ትርጉም ኣለው።
ለምንድነው የትግራይ ህዝብ ‘ብኡ የሕልፎ’ (የባሰ ኣታምጣ) በሚል የህወሓትን ጭቆና ‘ኣሜን’ ብሎ ለመቀበል የሚገደደው?
(1) ደርግ በትግራይ ህዝብ ብዙ ግፍ ያደረሰ ቢሆንም ህወሓት ከደርግ የባሰ ኣደገኛ ገዳይ መሆኑ የትግራይ ህዝብ በደምብ ያውቃል። የህወሓት የኣገዳደል ወይ ጭቆና ስልት በጣም የረቀቀ ነው። በዚህ የረቀቀ መንገድ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ተገድለዋል ወይ እንዲጠፉ ተደርገዋል። ስለዚ የትግራይ ህዝብ ‘ህወሓት ከደርግ የባሰ ኣደገኛ ነው’ ብሎ ያስባል፤ ይፈራልም። ለምሳሌ እኔ ህወሓትን ፊት ለፊት ስቃወም ብዙ ጓደኞቼ ህወሓት ሊገድለኝ እንደሚችል ስጋታቸው ያካፍሉኛል። (የህወሓት ተግባር በደምብ ስለሚረዱ)። ይህም ሁኖ ግን በኣሁኑ ሰዓት ብዙ የሚቃወም ኣለ። (ፓርቲውም እየተዳከመ ነው)።
(2) የትግራይ ህዝብ: ህወሓት ደርግን ማሸነፍ በመቻሉ (ደርግ ኣስፈሪ ነበር) ‘ሃይለኛ ነው’ የሚል የሃሰት ግምት ተሰጥቶታል። በዚ መሰረት ህወሓት በሰለማዊ ተቃውሞ ስልጣን ሊለቅ ይችላል የሚል እምነት የለውም። የህወሓት ካድሬዎች (ፖሊት ቢሮ ኣባላትን ጨምሮ) ለህዝቡ የሚናገሩት ይሄንን ነው። “ጫካ ገብተን፣ ብዙ መስዋእት ከፍለን ያመጣነው ስልጣን በምላሳቸው ለሚቃወሙን የደርግ ርዝራዦች ስልጣን ኣሳልፈን ልንሰጥ ኣንችልም ይላሉ።
የትግራይ ህዝብ ታድያ እንዴት በሰለማዊ ተቃውሞ ስልጣን ሊለቅ የማይችልን ስርዓት ይቃወም? ህዝቡ ህወሓቶች ከስልጣን እንደማይወርዱ ኣምኖ ከተቀበለ ፣ መቃወም ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መረዳቱ ኣይቀርም። መቃወማቸው ዉጤት ካላመጣ የሚቃወሙ ሰዎች ይገለላሉ፣ የባሰ በደል ይደርሳቸዋል። (የEDU ደጋፊዎች ነበሩ ተብለው የተፈረጁ ሰዎች እስከኣሁን ድረስ በመጥፎ ዓይን ይታያሉ)።
ከተቃወሙ ስራ ኣያገኙም ወይ ከስራቸው ይባረራሉ። የመንግስት ኣገልግሎት (መብታቸው ቢሆንም) ይነፈጋሉ። ለምሳሌ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የደገፉ ሰዎች፣ ከመንግስት ምንም ዓይነት ድጋፍ (የፖሊስ፣ ዳኝነት፣ የደህንነት ከለላ ባጠቃላይ) ‘ኣንፈልግም’ ብለው እንዲፈርሙ (መቃወምን ከመረጡ ማለት ነው) የሚያስገድድ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል (በተለይ በገጠር ኣከባቢ)።
ስለዚ በትግራይ መቃወም ማለት የመንግስት (ፓርቲ) ለውጥ ለማምጣት መታገል (ከተሳካም ገዢው ፓርቲ መቀየር) ማለት ሳይሆን የመንግስትን ኣገልግሎት ላለማግኘት መወሰን (በራስ ላይ ችግር መፍጠር) ማለት እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር በትግራይ መቃወም ክፉኛ እንደሚጎዳ ነው። ለዚህ ነው ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም የሚለው።
(3) የህወሓት የጥላቻ ፖለቲካ ወይ ፕሮፓጋንዳ ሌላው ምክንያት ነው። ህወሓት ደርግን የፈፀመው ግፍ እንደ ጥሩ ኣጋጣሚ በመጠቀም “እኔ ከሌለሁ ጅብ ይበላችኋል” ይለናል። በደርግ ዘመን ደርግና ህወሓት ትግራይን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጦርነት የትግራይ ህዝብ ብዙ ስቃይ ኣሳልፈዋል። በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ግድያ ነበረ፣ ትምህርት ኣልነበረም፣ ሰላም (መረጋጋት ማለቴ ነው) ኣልነበረም፣ ገበሬው፣ ነጋዴው … በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ኣልቻለም ነበር። ባጠቃላይ ያ ዘመን ለትግራይ ህዝብ (ለመላው የኢትዮዽያ ህዝብም ጭምር) መጥፎ ነበር። ህወሓት ታድያ (ደርግን በማባረሩና ጦርነቱ ጋብ ስላለ) ‘ከዚህ ሁሉ ችግር ያዳንኳቹ እኔ ነኝ። እኔ ባልኖር ኖሮ የደርግ ወታደር ይበላቹ ነበር። ህወሓቶች ከሌለን ደርግ መጥቶ ይገድላችኋል” ይለናል።
ይባስ ብሎ ደግሞ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት የደርግን ኣስከፊነት ያስታውሳል፤ የተከፈለ መስዋእትነት 24 ሰዓት ይተርካል። ይህ የትግራይን ህዝብ ቁስል በመንካት ድጋፉን እንዲሰጥ የማስቻል ስትራተጂ ነው። ለዚህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ ኣንድ ሬድዮ (ድምፂ ወያነ) ና ሦስት ኤፋኤም FM ሬድዮ ጣብያዎች ኣሉ።
ከዚህ በተያያዘ ህወሓት ህዝብን ሲሰብክ ደርግ ኣማራ ኣድርጎ ያቀርበዋል (የደርግን ዓይነት ጨቋኝ ስርዓት የመምጣት ዕድል እንዳለ ለማመልከት ተፈልጎ ነው)። ደርግ ላይመለስ ሞተዋል። ስጋት ሊሆን ኣይችልም፣ ተመልሶ ሊመጣ ኣይችልም። ህወሓት ግን ህዝቡን ለማጭበርበር እስከኣሁን ኣደጋው እንዳለ ለመጠቆምና የትግራይን ህዝብ ድጋፍ እንዳይለየው ለማድረግ ‘ፀረ ደርግ’ የነበረ ትግል ‘ፀረ ኣማራ’ እንደሆነ ኣድርጎ ኣቀረበልን። (በኣንደኛ ደረጃ ትምህርታችን ሳይቀር ተምረነዋል።)
በኣሁኑ ሰዓት ታድያ ሰው (ከትግራይ) ሲቃወም: “ከነዚህ የጠላት ቡድኖች (በብሄር ደረጃ ኣማራ ወይ ሸዋ) ወይ የደርግ ርዝራዦች (Remnants of the Derg Regime) ወግኖ ደርግን ወደ ስልጣን ለማስመለስ ህወሓትን ይቃወማል” በሚል ሰበብ ስሙ ይጠፋል። (እኔ ህወሓት ስለ ተቃወምኩ የሚሰጠኝን ስም መመልከት ይቻላል)። ይሄ ነገር ታድያ እየታፈንክ ዝም ኣያሰኝም???
(4) ደርግ የትግራይን ህዝብ ጠላት ተደርጎ ነው የሚወሰደው (በፈፀመው ግፍ)። የትግራይ ህዝብ ያን የደርግ ኣገዛዝ ኣይፈልግም። ‘ደርግ ይመለሳል’ ከተባለ ታድያ (ማመዛዘን ቢያስፈልግም) ህዝቡ ከደርግ ህወሓትን መምረጡ እንዴት ይቀራል?
የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ሲቃወም ከተቃዋሚዎች ጎራ እንደተሰለፈ ይቆጠራል። ተቃዋሚዎች ደግሞ ‘ደርጎች’ መሆናቸው ነው ለህዝቡ ሲነገር የቆየው። ስለዚ ኣንድ ሰው (ወይ ብዙ ሰዎች) ህወሓትን ከተቃወመ ከደርግ ጋር እንደተባበረ ነው የሚቆጠረው። በትግሉ ወቅት ከደርግ ጋር የተሰለፈ ሰው ምን ዓይነት ቅጣት ይሰጠው እንደ ነበር ህዝቡ በደምብ ያውቃል። ስለዚ የትግራይ ህዝብ ‘የመቃወም ቅጣት’ ይፈራል። ፈርቶም … ሲጨቆን ዝም ይላል (የባሰ ኣታምጣ ወይ ብኡ የሕልፎ ብሎ)።
(5) ኣብዛኛው የትግራይ ህዝብ ድሃ ነው። ድህነት በራስ የመተማመን ዓቅማችን ያሽመደምደዋል። ለመቃወም የኢኮኖሚ ነፃነት ወይ ዓቅም መገንባት ያስፈልጋል (ከገዢው መደብ ለሚደርሱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሽብሮች ለመቋቋም)። ድሃ ጭቆናውን ቢቃወም እንደውጤቱ የባሰውን ይጨቆናል። ለኣምባገነኖች; ጭቆና ተቃውሞን ለመቀነስ ይጠቀሙታል። ስለዚ የባሰውን ጭቆና ለማስቀረት ያለውን ጭቆና ‘ኣሜን’ ብሎ መቀበል (የትግራይ ህዝብ) እንደኣማራጭ የወሰደው ይመስለኛል።
ሌላው ችግር ደግሞ የትግራይ ህዝብ የመረጃ ዓፈና (ከሌሎች ክልሎች በባሰ ሁኔታ ሊባል በሚችል ሁኔታ) ይፈፀምበታል። የመረጃ ችግር ኣለ። ወደ ትግራይ የሚገባ መረጃና ከትግራይ የሚወጣ መረጃ በተቻለ መጠን ሳንሱር ይደረጋል። የትግራይ ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ ይደረጋል። በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ስለ የኢትዮዽያ ፖለቲካ በቂ መረጃ ኣለው ብዬ ኣላምንም።
በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ የሚፈፀሙ ችግሮች፣ በደሎች፣ ጭቆናዎች የሚዘግብና የሚያጋልጥ ሚድያ የለም። በፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚድያ ሚና የማይናቅ ነው። በትግራይ ያሉ ችግሮች በኣግባቡ ስለማይዘገቡ ሰሚ ኣያገኙም። ሰሚ ካላገኙ (1) ሰዎቹ ተቃውመው ምንም ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ስለሚረዱ እየተጨቆኑም ዝም ብለው ዝም ይላሉ፤ (2) ካልተዘገቡ በሌሎች ህዝቦች በትግራይ ችግር እንደሌለ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
ስለዚህ ገዢው ፓርቲ ዓፈናን ለመሸፈን ዓፈናን (ራሱ) እንደመሳርያ ይጠቀመዋል። እንደውጤቱም በትግራይ ተቃውሞ እንኳ ቢኖር ስለማይዘገብ ግን ህዝቡ ህወሓትን እንደሚደግፍ ወይ እንደማይቃወም ተደርጎ ይወሰዳል። ትልቁ ችግር ይሄ ነው።
(6) የትግራይ ህዝብ የገዢው ፓርቲ ዓፈናን ተቋቁሞ ዝምታን የሚመርጥበት ዋናው ምክንያት ስለተቃዋሚዎች ትክክለኛና በቂ መረጃ ስለሌለውና ተቃዋሚዎችም ለህዝቡ ቀርበው በማነጋገር ዓላማቸውና ማንነታቸው በግልፅ ማስረዳት ባለመቻላቸው ነው።
ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብ በሙሉ ህወሓትን እንደሚደግፍና ‘ጠላት’ እንደሆነ ኣስመስለው እንደሚያቀርቡ በብዙ የትግራይ ተወላጆች (በህወሓት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት) ይታመናል። ይህንን እምነታቸው ህወሓትን የሚጠቀመው “ተቃዋሚዎች ደርጋውያን ናቸው፣ ደርግ ሙሉ በሙሉ ሞቶ ስላልተቀበረ ህወሓት እስከኣሁን ድረስ ከደርግ ጋር እየተዋጋ ነው ወዘተ” የሚል የማጭበርበር ፕርፓጋንዳ ለመቀበል ይገደዳሉ።
በዚ መሰረት ህወሓትን እየተቃወመም ቢሆን የተቃዋሚ ድርጅቶች ግን ከህወሓት ሊብሱ ይችላሉ ብሎ እንዲያስብ ስለሚገደድ ግራ ተጋብቶ ‘የባሰ ኣታምጣ’ ብሎ ኣብሮ ዝም ይላል።
ስለዚ ተቃዋሚዎች ከትግራይ ህዝብ ጋር መወያየትና መግባባት ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም ሳያውቁት (በሚጠቀሙት የፖለቲካ ስትራተጂ) የትግራይን ህዝብ (target የሚያደርጉ ስለሚመስሉ) በህወሓት ቢጨቆን እንኳ ህወሓትን ላለመቃወም እንዲወስን (የባሰ እንዳይመጣ) ያደርጉታል። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ዝምታ ምክንያት ኣለው (ህወሓት ስለሚደግፍ ግን ኣይደለም)።
“የትግራይ ህዝብ” የሚወክለው ኣብዛኛውን ህዝብ እንጂ ጥቂት የስርዓቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚዎችን ኣያጠቃልልም። ጥቂት የስርዓቱ ተጠቃሚዎች በሚሰሩት ተግባር ሁሉም የትግራይ ህዝብ ህወሓት እንደሚደግፍ ኣስመስለው ለማቅረብ ስለሚሞክሩ ሌሎች ሰዎች እውነት ሊመስላቸው ይችላል።
… ግን ዝምታ መፍትሔ ሊሆን ኣይችልም።

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የመደራደር አቅማቸው (ክፍል 1)

በዳዊት ተ. ዓለሙ
ምንጩ ከ ዞን ዘጠኝ ጦማር
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመደራደር አቅም (Bargaining power) ለዴሞክራሲያዊ ፖለቲካ ስርአት ግንባታም ሆነ በዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ላይ ተመስርቶ ለሚደረጉ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ስኬታማነት ወሳኝ ነው:: ሁሉን የፖለቲካ ቡድኖች ያማከለ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ምስረታም ሆነ የተቋማቱ ዘላቂነት በዋናነት የሚወሰነው የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚኖራቸው የመደራደር አቅም ልክ ነው:: ሚዛናዊ ያልሆነ የመደራደር አቅም ባላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መሀካል በሚደረግ ስምምነት የሚፈጠሩ ተቋማትና ስርዓቶች በአመዛኙ ሊያስጠብቁ የሚችሉት ይበልጥ ጠንካራ የመደራደር አቅም ያለውን የፖለቲካ ኃይል ፍላጎቶች ነው:: ይበልጥ የዴሞክራሲ ስርአት ሰፍኖባቸዋል በሚባሉ ሀገራት ውስጥ በትንሹ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑና የተቀራረበ የመገዳደር አቅም ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚገኙባቸው ናቸው:: የተቀራረበ የመገዳደር አቅም ባላቸው ፓርቲዎች (መሪዎች) ድርድር የሚመሰረቱ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት በአብዛኛው የሁሉንም ፖለቲካ ኃይሎች ፍላጎቶች የማንጸባረቅ እዳላቸው የሰፋ ነው:: ለምሳሌ ያህልም ሮበርት ፑትናም Making Democracy Work ብሎ በሰየመው የምርምር ስራው ለ20 አመታት የኢጣሊያንን ፖለቲካ በቅርብ ከተከታተለ በኋላ ይህንን እውነታ በሰፊው አመልክቷል:: ስለዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተቀራረበ የመደራደር አቅም ለሰላማዊ ፖለቲካና ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ወሳኝ ነው::
በሀገራችን የፖለቲካ ቡድኖች (ፓርቲዎች) የመደራደር አቅማቸው የማይመጣጠን በመሆኑ የመገዳደር ፖለቲካ ባህላችን በአፈሙዝ የበላይነት የሚደመደምበት እንዲሆን አድረጎታል:: በዚህም የተነሳ በየወቅቱ ሲገነቡ የነበሩት ተቋማት በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን ጥቅምና ህልውና የሚያስጠብቅ ባህሪና ቁመና የተላበሱ ሆነዋል:: የፖለቲካ ፓርቲ እሳቤና ተሞክሮ የሀገራችን የፖለቲካ ባህል ከተዋወቀበት ጊዜ አንስቶ የተመሰረቱ ፓለቲካ ፓርቲዎች ሁሉም ሊያስብል በሚችል መልኩ የመደራደር አቅማቸው በጉልበት ላይ ወይም በተወሰ ጉዳዮች ላይ ብቻ የተነጠለጠለ ነው:: ይህም በመሆኑ በሀገራችን ደካማ ወይም ኢ-ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የራቀው ፖለቲካዊ ባህል እንዲሰራፋ ሆኗል::
የመደራደር አቅም ሲባል
የመደራደር አቅም (Bargaining power) በተለያዩ ጸሃፊዎች በተለያዩ የአረዳድና እውቀት ዘርፎች የተለያየ ትርጓሜ ተሰጥቶታል:: በግርድፉ የመደራደር አቅም ሲባል በአንድ በተወሰነ ሁኔታ ላይ አንድ ተቋም/ግለሰብ በሌሎች ተቋማት/ግለሰቦች ላይ ተጽእኖ ለማሳደር የሚያስችለው አንጻርዊ የተቋማት/ግለሰቦች አቅም ማለት ነው:: ጊዲዮን ዳሮንና እቲኢ ሰንድ በጋራ ባዘጋጁት መጸሃፍ (Poltical Bargaining: Theory, Practice and Process) ፖለቲካል የመደራደር (Political Bargaining) አቅምን ትርጓሜ ሲሰጡት:- „a tangible effort made by two or more agents with some conflict of interests to reach an agreement over an authoritative allocation of scarce resources“ በማለት ነው:: በዚህ አረዳድ ውስጥ ፖለቲካ የታየበት አግባብ ወሳኝ ሃብቶችን ስርጭት መሰረት ያደረገ ነው:: ይህም ከክላሲካል „ፖለቲካ“ ትርጓሚ ማለትም „ፖለቲካ ማለት ከስልጣን ጋር የተያያዘ ጉዳይ ሲሆን ስልጣንም የሀብት ክፍፍልን የሚመለከት ነው“ ከሚለው ዕሳቤ የመነጨ ነው:: ስለዚህም የመደራደር ሂደት የተለያዩ ማህበረሰባዊ ወይም ቡድናዊ ፍላጎቶችን ለማስታረቅና ስምምነት ላይ የተደረሰበት የወሳኝ ሃብቶች ስርጭት ስርዓት መዘርጋት ማለት ነው:: በዚህም የተነሳ የመደራደር አቅም በፖለቲካ ሳይንስ ውስጥ የምንረዳበት አግባብ አንጻራዊነትን የሚላበስና ብዙ አላባውያንን (elements) የሚያቅፍ መሆኑን ነው:: የመደራደር አቅም ከሚታይበት አላባውያን መካከል ወሣኞቹ ድርጅታዊ ጥንካሬ፣ ፍላጎቶችን የማስታረቅና ተጽእኖ የመፍጠር አቅም፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለቸው የቅቡልነት ደረጃ፣ፖለቲካል ታክቲክ እንዲሁም ፖለቲካል ውሳኔያቸው ተተንባይነት ነው:: እያንዳንዱን ጉዳይ ብቻ በመያዝ ብዙ ሊያጽፍ ቢችልም፣ በዚህ ጽሁፍ ተከታታይ ጽሁፍ ለሁለት ከፍለን በተወሰነ መልኩ እንደሚከተለው እንዳስሳቸዋለን::
ድርጅታዊ ጥንካሬና የመደራደር አቅም ውስኑነት
ድርጅታዊ አቅም የተለያዩ ፍቺዎች ቢኖሩትም በሶስት ቁምነገሮች ላይ ያተኩራሉ:: እነርሱም የሰው ኃይል፣ አደረጃጀት እና አሰራር ናቸው:: ኢትዮጵያ በፖለቲካ ፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹንፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው:: ይህም ሁናቴ በኢትዮጵያ ውስጥ የተመሰረቱት ፖለቲካ ፓርቲዎች በግራ ዘመም ባህል በተለይ ደግሞ ጆሴፍ ስታሊን „የሌኒን ፓርቲ“ ብሎ በሰየመው አረዳድ ላይ የተመሰረቱ ናቸው:: ይህ ግራ ዘመም የፓርቲ ፖለቲካ ባህል በፓርቲዎች ርዕዮተ-ዓለማዊ አቋም ብቻ የሚንጸባረቅ ሳይሆን እንደብረት በጠነከረ የፓርቲ ስነ-ስርዓት፣ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት፣ ጥብቅ ከላይ ወደታች የዕዝ ሰንሰለት ጭምር የሚታይ ነው:: በዚህ ፓርቲ ፖለቲካ ባህል መሰረት ብሎ ያምናል:: ምንም እንኳን የሃገራችን ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ ርዕዮተ አለምን የሚከተሉ ቢሆንም ይህ አስተሳሰብ በከፍተኛ ሁኔታ የተጫናቸው ናቸው:: በዚህ የአስተሳሰብ ማዕቀፍ ውስጥ ነው እንግዲህ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድርጅታዊ ጥንካሬና የመደራደር አቅም የሚታየው::
እንደማንኛውም ታዳጊ ሀገር ፖለቲካ በአብዛኛው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተመሰረቱት ዘመናዊ ትምህርት በቀሰሙ የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸው:: አብዛኛዎቹ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ የተማሪዎች ንቅናቄ የተሳተፉና በተለያዩ የአመራር ደረጃ የነበሩ ናቸው:: ይህም የተቀዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ልምድና ዕውቅት እንዲኖሯቸው አስችሏቸዋል:: በሌላ መልኩ ደግሞ አብዛኞቹ አመራሮች በተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ተሳታፊ ስለነበሩና እርስ በራሳቸው በአይነ ቁራኛ የሚጠባበቁና በከፍተኛ ጥላቻና ቂም በቀል ስሜት የተዋጡ እንዲሆኑ ስላረጋቸው ከጊዜያዊ ትብብር የዘለለ በመርህ ላይ የተመሰረት አንድነትን መፍጠር እንዳይችሉ አድርጓቸዋል:: በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እግጅ በጣም ትናንሽ በሆኑ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሞላቱ የሚያመለክተው ቁምነገር የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች በራሳቸው ዙሪያ የተገነቡ ፓርቲዎችን እንጂ በመርህ ላይ የተመሰረተና የጋራ ፖለቲካዊ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ፓርቲዎችን መመስረት አለመቻላቸውን ነው:: ይህም ወደአንድ ላይ መሰባሰብ ቢችሉ ሊያመጡ ከሚችሉት ውጤት አንጻር እጅግ ዝቅተኛ ውጤት እንዲያመጡ ሲያደርጋቸው፤ ልምድ ያላቸው ከፍተኛ አመራሮችም እንዲበታተኑ ሆነዋል::