Wednesday, October 16, 2013
Africa's journalists honor jailed editor Woubshet Taye
By Sue Valentine, CPJ Africa Program Coordinator
Journalists and media owners across Africa gave Ethiopian journalist Woubshet Taye a standing ovation in Cape Town on Saturday night at the CNN MultiChoice African Journalist Awards 2013, but he wasn't there to see it. Instead his wife and son accepted the Free Press Award on his behalf.
Part of the citation for the award reads: "Ethiopia is a jewel in the African crown for its beauty, its people, its history and, most recently, for its astonishing growth rates. It is the judges' view that journalists like Woubshet Taye and his colleagues Reeyot Alemu and Eskinder Nega should be out of prison and working to build the prosperity and the freedom of a new Ethiopia. The judges make this award in recognition of Mr. Taye's work and in solidarity with his condition." Presenting the award to Berhane Tesfaye and the couple's not-quite-five-year-old son, who were dressed in matching white and blue outfits, chair of the judging panel and editor-in-chief of the South African weekly City Press Ferial Haffajee said it was disappointing that "once again there were too many cases" for the judges to consider in this category, which recognizes "excellence and provides support to African journalists who report at continuing risk to their lives and safety." Woubshet, deputy editor of the Awramba Times, has been in jail for more than two years. He was detained in June 2011and held incommunicado before being convicted on terrorism charges and sentenced to 14 years imprisonment in January 2012. After Woubshet's arrest, the paper stopped publishing in Ethiopia and the editor fled into exile. Accepting the award on his behalf, Berhane Tesfaye said her husband was grateful for the solidarity and received the award in the name of all journalists who are oppressed.
In April this year, Ethiopian authorities moved Woubshet to the remote Ziway prison about 83 miles (160 kilometers) from the capital Addis Ababa. His wife said that although it is a long way to travel, she is usually able to visit her husband every two weeks. However, she said that Woubshet's parents--his father is 102 and his mother 90--are too old to make the journey. In September, Woubshet's application for a presidential pardon was rejected, according to news sources. The CNN MultiChoice African Journalist Awards began in 1995. A panel of 10 independent judges selected finalists and winners in 14 categories before naming an overall 2013 winner.
የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?
የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?
October 16, 2013 06:28 pm
ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው።
በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሃገራችን አሁንም እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው።
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው።
ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ 1. አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር 2. ዘርኡ ገሰሰ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ገሰሰው አየለ 5. አባይ ፀሃየ 6. ሥዩም መስፍን 7. አለምሰገድ መንገሻ 8. አስፍሃ ሃጎስ ተመርጠው ተሓህትን መርተዋል።
በዚህ ጊዜ ነበር የማገብትን ውርስ ተሓህት ተረከበው ብሎ በጊዜው የነበረ ታጋይ ደስታውን የገለጸው። ውርስ ማለት ፕሮግራሙ ነው። በጊዜው የነበረ ሁሉም ታጋይ ግን የፕሮግራሙን ይዘትና ምንነትቱን አያውቅም ነበር። ይህ ፕሮግራም ነበር በ1968 ቀስ በቀስም ተሓህትን ለሁለት የመሰንጠቅ አደጋ የፈጠረበት።
የተሓህት-ህወሓት የመጀመሪያ መሰንጥቅ
ተሓህት ገና ከደደቢት በረሃ ሳይወጣ በፊት በሁለት ጎራ የተሰነጠቀበት ወቅት ነው። ይህን መከፋፈል የፈጠረው የፕሮግራሙ ባለቤት ነን የሚሉ አመራር በድብቅና ከታማኝ ታጋዮች ጋር በመተባበር ወስጥ ለውስጥ ፕሮግራሙ ይዘጋጅ ነበር። ይህን የማይደግፉና የሚቃወሙ አመራርም ነበሩ።
አክራሪና በአቋማቸው የጸኑ ግን ፕሮግራሙ በትክክል የተዘጋጀ ሃቀኛ የትግራይ ሕዝብ ምኞትና ፍላጎትን በጭብጥ ያስቀመጠ፤ ትግራይን እና ሕዝቧን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነፃ የሚያወጣ፣ የትጋላችን መርህ ፕሮግራም ነው አሉ። የዚህ ተሳታፊውች፤ 1. አረጋዊ በርሄ 2፣ አባይ ፀሃየ 3. ሥዩም መስፍን 4. ግደይ ዘራጽዮን 5. ስብሃት ነጋ 6. መለስ ዜናዊ 7. አስፍሃ ሃጎስ 8. አውአሎም ወልዱ 9. ስየ አብርሃ 10. ሃይሉ መንገሻ ናቸው። እነዚህ ሁሉ አመራር የነበሩና ጥቂቶቹ ደግሞ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አመራር የመጡ ናቸው።
በሁለተኛ ደረጃ በተቃውሞ የቆሙትና ፕሮግራሙ በጣም አደገኛ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ፣ ሕዝብ በታኝ፣ ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው በማለት የተነሱት ደግሞ 1. ገሰሰው አየለ 2. አግአዚ ገሰሰ 3. አጽብሃ ዳኘው 4. ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ሲሆኑ፣ ከሻእቢያ መጥቶ ተሓህትን የተቀላቀለው መሃሪ (ሙሴ) ተክሌም 5ኛ ሆኖ ከነገሰሰው አየለ ጋር ተቀላቀለ። እነዚህ ሁሉም የተሓህት አመራር የነበሩ ናቸው።
ማህበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) ገና ሲፈጠር ጎባጣ፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ሆኖ ነው የተመሰረተው። ይህንን ውርስ ያስረከበው ለተሓህት በየካቲት ወር 1967 ነው። በደደቢት በረሃ ተጠናክሮ ፕሮግራም ሆነ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፕሮግራሙን በመቃወም የተሰለፉት ያነሱት ነጥብ፤
- ተሓህት በጸረ ኢትዮጵያና በሕዝቧ ተቀናጅቶ መፈጠሩ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር መበታተን አለባት የሚለው በገጽ 8 የተዘጋጀው የባእዳን ሴራና ጸረ ሃገር ነው፣
- አማራ የትግራይ ሕዝብ ጨቋኝና ረጋጭ፤ ለድህነት፣ ለሽርሙጥና፣ ለስደት፣ ለመከራ የዳረጋት ጠላት ነው የሚለው ትንተና ሃቅነት የሌለው የፈጠራ ወሬ ነው። የተጻፈው አማራን ሆን ብሎ ለማጥቃት ነው። ይህም ከፕሮግራሙ መወገድ አለበት፣
- ኤርትራ የአማራው (ኢትዮጵያ) ቅኝ ግዛት ናት የሚለው ቅንጣት ታህል ሃቅነት የሌለው እናንተ አመረር የፈጠራችሁት የተገንጣይ ዓላማ ነው፣
- ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት ማለት የአእምሮ ድህነትና ጠባብ ዘረኝነት ነው፣ ስለሆነም መወገዝ አለበት።
- ተሓህት የኢትዮጵያ ጥንታዊና ታሪካዊ ግዛትዋን እና የባሕር በሯን የሚያስነጥቅ ፕሮግራም ነው። ስለሆነም ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው። ፕሮግራሙ ይለወጥ ወዘተ. የሚሉ ሃሳቦች በማንቀሳቀስ ቀሪው ታጋይም የእነገሰሰው አየለን ሃሳብ መደገፉን በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች በትክክል ተናግረውታል።
በተጨማሪም አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጨመሩበት ነጥብ ተሓህት በትግራይ ሕዝብ ተቀባይነት ወይም የውክልና መሰረት የሌለው፣ ፕሮግራሙን በትግራይ ሕዝብ ስም መዘርጋት አግባብነት የሌለው፣ በሕዝብ ስም ማጭበርበር ነው ብለው በማመን በወቅቱ የነበሩ አነስተኛ ታጋዮች በዚህ ሃሳብ ተስማሙ። በዚህ ጊዜ 1. በስብሃት ነጋ 2. መለስ ዜናዊ 3. አውአሎም ወልዱ 4. ስየ አብርሃ ወዘተ. ተባብረው በአቶ ገሰሰው አየለ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ። በስብሃት ነጋ እየተመሩ የገሰሰው አየለን ስምና ዝና በጥቁር ቀለም ቀቡት። ሻእቢያም ገሰሰው ከተሓህት ተቀላቅሎ መታገሉን ከመጀመሪያው ያልተቀበለው ስጋት ወስጥ ስለጣለው ነው። ሻእቢያ ለተሓህት አመራር ያስተላለፈው መልእክት፣ ገሰሰው አየለ በዚህ ከቀጠለ ተሓህትም ሆነ ሻእቢያ ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ተናግሯል። ገሰሰው አየለ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት የሚለውን የተህሓት ጥቂት አመራር ሃሳቡን ተቀበሉት።
የእነ ስብሃት ነጋ ቡድን በገሰሰው አየለ ላይ ሲያስፋፉት የነበረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ጥቂቱን እንመልከት፤
- ድርጅታችን ተሓህት የገሰሰው አየለ ፊውዳል ድርጅት ነው እየተባለ ነው። ይህንን ግለሰብ ከድርጅቱ ማስወገድ ስላለብን እንተባበር (መለስ ዜናዊ)፣
- ገሰሰው አየለ ፊውዳል፣ ጸረ-ትግራይ ትግል በመሆኑ በተመቸው ጊዜ ጠብቆ ተሓህትን ከማጣፋት አይመለስም። የትግራይን ነፃ ሃገርነትና የትግራይን መንግሥት አይቀበልም። ጸረ-ኤርትራ ትግል ነው። የመትከል አገራችን ሻእቢያም ተማረውበታል። (ስብሃት ነጋ)፣
- ኤርትራና ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት አይደሉም፣ አልነበሩም። ሁሉም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ግዛትና አካል ናቸው፣ ስለዚህ የተሓህት ፕሮግራም ውድቅ ነው እያለ እንደ ምስጥ ውስጥ ለውስጥ እየተሽሎከሎከ ከሕዝብ እየነጠለን ነው (ስብሃት ነጋ)።
በዚህ ጊዜ የነበሩ ታጋዮች እንደሚናገሩት ከሆነ በገሰሰው አየለ ላይ በስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ የሚመራው ቡድን የተሰማሩበት የስም ማጥፋት ዘመቻ በየቀኑ ይደርሰው ነበር። በመጨረሻ ተማሮ በህዳር 1968 ከማ/ኮሚቴ ሃላፊነቱ ራሱን አግልሏል። ይህ በመሆኑ በሃዘን እና በቁጭት የሚናገሩ በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች ነበሩ። አክራሪውን አመራር ለመቆጣጠር አቅም ነበረን ግን ስህተት ፈጸምን ያሉም አልታጡም።
የዲማ ኮንፈረንስ
የዲማ ኮንፈረንስ የተካሄድው በመጋቢት መጀመሪያ በ1968 ነበር። በዚህ ጊዜ አቶ ገሰሰው አየለ በስብሰባው አልታየም። በወቅቱ በዚህ ጉባኤ የተሳተፉት ታጋዮች ገሰሰው/ስሁል የት ሄደ ብለው ሲጠይቁ የተሰጠው መልስ በሥራ ምክንያት ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል የሚል እንደነበር ይናገራሉ። ኮንፈረንሱ ከመድረሱ በፊት የስብሃት ነጋ ቡድን በአግአዚ ገሰሰ፣ በጥቂቱም ቢሆን በግደይ ዘርአጽዮን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። ነገር ግን ውጤት አልባ ነበር።
በዲማ ኮንፈረንስ የተመረጡት 1. አረጋዊ በርሄ፣ የተሓህት ሊቀመንበር 2. ስብሃት ነጋ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ሥዩም መስፍን 5. አግአዚ ገሰሰ 6. አባይ ፀሃየ 7. ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ ነበሩ። ምርጫው ጸረ-ዲሞክራሲ ስለነበር የነበረው አመራር ስብሃት ነጋን መርጦ መለስ ዜንዊን ድምጽ ነሳው። በዚሁ ሁሉም ወደየሥራው ሄደ።
ቀደም ብዬ በአርእስቱ ላነሳሁት ጥያቄ መልስ ለመስጠት፣ የተሓህት – ህወሓት ጸረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማን በመቃወም ለሁለት መሰንጠቁና የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው? ለሚለው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እነሆ ፎቶግራፋቸውን ከዚህ በማያያዝ አቀርባለሁ።
ገሰሰው አየለ አግአዚ ገሰሰ ሙሴ መሃሪ ተክሌ አጽብሃ ዳኛው ዶ/ር አታክልት ቀጸላ
አቶ ገሰሰው አየለ የበረሃ ስሙ ስሁል፣ ተወልዶ ያደገው ሽሬ አውራጃ ነው። ገና በወጣትነቱ የሽሬ አውራጃ ማዘጋጃ ቤት ዋና ሹም በመሆን አገልግሏል። በ1950 አጋማሽ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል በመሆን ሠርቷል። ለሶስት ተከታታይ ምርጫ በማሸነፍ 15 ዓመት ሙሉ የፓርላማ አባል ነበር። በኢትዮጵያ የተቀጣጠለው አብዮት እየተጠናከረ ሲመጣ በ1966 የማገብት አባል ሆነ።
አቶ ገሰሰው አየለ የማገብትን አላማ፣ ተግባርና ፕሮግራም በጸረ-ኢትዮጵያነት የተሞላ መሆኑን ትኩረት ሳይሰጥ በየካቲት 11 ቀን 1967 ለተመሰረተው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም መስራች በመሆን በአመራር ደረጃ ግንባሩን ሲመራ ነበር። የተሓህትን ፕቶግራምና ዓላማ ካየ በኋላ ፍጹም ጸረ-ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብነትን የጨበጠ ፕሮግራምና በፋሽስት ጣልያን የተዘጋጀ ነው እስከማለት ደረሰ። በህዳር 1968 ከአመራሩ ወረደ።
አቶ ገሰሰው አየለ ያነሳው ተቃውሞ ብዙ ቢሆንም ከተራ ቁጥር 1-4 ያሉትን አንኳር ሃሳቦች አስነስቷል። ታጋዩም ድጋፍ ሰጠው። ከአመራሩም እንደነ አግአዚ ገሰሰ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክለት ቀጸላና መሃሪ ከጎኑ ተሰለፉ። በተሓህት ውስጥም ጭንቀትና ሽብር በአመራሩ ወስጥ ተፈጠረ። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድንም ገሰሰው አየለን በዘዴ ለማጥፋት እቅዱን ዘረጋ።
የገሰሰው አየለ ደብዛ መጥፋት
ከዲማ ኮንፈረንስ በኋላና ክዛም ትንሽ ቀደም ብሎ ገሰሰው አየለ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ሲሉ የት ገባ የሚሉ ታጋዮችም በዙ። በዚህ ጊዜ የተሓህት አመራር እርስ በርሱ የሚጋጭ ወሬዎች በድርጅቱ አሰራጨ።
- በአዲ ነብራኡድ ወስጥ በኢዲዩ ወይም ጠርናፊት ድንገተኛ ጦርነት ከፍተው ጠርናፊት ገደለችው፣
- እኔ ስለሸመገልኩ አልታገልም ገንዘብ ስጡኝና ሱዳን ሄጄ ልኑር በማለት ገንዘብ ከድርጅቱ ተሰጥቶት በመኪና ተሳፍሮ ሲሄድ በመኪና ውስጥ የነበሩ የኢዲዩ አባላት ገደሉት የሚል ነበር። ሁሉም ውሸት ነው።
ኢዲዩም ይህንን በተመለከተ ሰፊ መግለጫ በተነ። ገሰሰው አየለን እኛ አልገደልነውም፣ ልንገድለውም አንችልም። የወንድማቻቾች ደም በከንቱ አናፈስም የሚል ሲሆን፣ የገደለችው ተሓህት ናት አሉ።
በአዲ ነብራኡድ ተገደለ የተባለበት ምክንያት ሕዝቡ ራሱ ምስክርነቱን በሰጠበት በመጋቢት ወር ጦርነት አልነበረም። የደም መፋሰስ አልታየም አለ። የገደሉት ራሳቸው ወያኔዎች ናቸው ሲል ሕዝቡ ምስክርነቱን ሰጠ። አዲ ነብራኡድ የገሰሰው አየለ ቤት ነው። ጊዜው የአቶ ገሰሰው አየለ ስሁል አሟሟት እውነቱ ግልጽ ሆኖ የወጣበት ጊዜ ነበር። ገሰሰው በስብሃት ነጋ የሚመራው የተሓህት አመራር በማይታወቅ ቦታ ደብቀው ወይም እንደ ግዞተኛ አቆይተው በሰኔ 1968 በጥይት ደብደበው ሽላሎ ቡምበት አካባቢ ተገደለ። በግድያው የተሳተፉትም አውአሎም ወልዱና አሰፋ ማሞ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን አልታወቁም። ይህንን እውነታ ተከታትለው ሃቁን ያገኙት በተሓህት ወስጥ ለትግል የተሰለፉት የገሰሰው አየለ የቅርብ ዘመዶቹ ናቸው። በጊዜው ሃቁን አስቀምጠው አለፉ። ላደረጉት ጥረት የሚመሰገኑና ባለውለታም ናቸው። ጥቂቶቹ፣ ማለትም እንደነ አዘናው ገ/ጻዲቅ ታፍነው የት እንደገቡ የማይታወቁም አሉ።
የአቶ ገሰሰው አየለ በተሓህት ፕሮግራም ያስቀመጠው ነቀፌታና ሃሳቡን የደገፉት ግለሰቦች በከፍተኛ ዲግሪ ከቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ እንደነ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋህድ የመሳሰሉ ዘጠኝ ምሁራን የተሓህትን አመራር የውሸት ስም በመስጠት የሥልጣን ሱሰኞች ተብለው ሽራሮ ውስጥ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። እነዚህም በተሓህት አመራር ቅጥራኛ ባንዳዎች ተገድለዋል። ይሁን እና መልእክታቸውን አስተላልፈው ከዚች ዓለም በግፍ ተገድለው አልፈዋል። ስማቸው ግን አልጠፋም፤ ለዘላለም ይኖራል።
2. ዘርኡ ገሰሰ
ዘርኡ ገሰሰ የበረሃ ስሙ አግአዚ ሲሆን፣ በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነበር። ማገብትን ከመሰረቱት አንዱ ነው። በአመራርም እስክ እለተ ሞቱ ተሓህትን ከሚመሩት መካከል ነበር። ዘርኡ ገሰሰና አቶ ገሰሰው አየለ በተሓህት ፕሮግራም ጠማማነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑ በሁሉም ነጥብ አይለያዩም፣ አንድ አቋም ነበራቸው።
ዘርኡ ገሰሰ የተሓህትን ፕሮግራም አጥብቆ ያወግዘዋል፣ በታጋዩም ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ክብርም ያገኘ አመራር ነበር። ይህች ግን ለነስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ አትዋጥላቸውም። አደገኛ መሪ ብለው ፈርጀው የሚጠበቀው ልክ እንደ ገሰሰው አየለ በዘዴ ማጥፋት ነበር።
ዘርኡ ገሰሰ በተሓህት ፕሮግራም በገጽ 8 ላይ የሰፈረውን እና ሌላውን ፕሮግራም ሁሉ አደገኛ ስለሆነ ፈጽሞ መወገድ አለበት በማለት ከብዙ አመራሮች ጋር መነጋገሩ የቅርብ ሰዎች የሚሉት ሃቅ ነበር። ነገር ግን ሰሚ አላገኘም። እነ ስብሃት ነጋ የሚገደልበትን ዘዴ ለማመቻቸት ይሯሯጡ ነበር።
አግአዚ ገሰሰ ከግደይ ዘርአጽዮን እና ከአረጋዊ በርሄ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው የሚያውቁ ታጋዮች በዚሁ ሴራ ሁለቱ ምንም ዓይነት ተሳታፊነት አልነበረባችውም የሚሉም ብዙ ናቸው። የሴራው አካላት ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ናቸው በማለት ያረጋግጣሉ።
ይህ በእንዲህ እያለ የተሓህት አመራር ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ሆነው ዘዴውን አቀነባብረው ከጨረሱ፣ አግአዚን ጨምሮ በአክሱም ከተማ ትልቅ ሥራ እንዳለ አስመስለው ሃሳባቸውን በማቅረብ የሚፈጸመውም በአመራር ደረጃ ስለሆነ አግአዚ ተዘጋጅ ብለው በትንሽ ቀናት እንደሚገናኙ ተወሰነ። ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጠላት በብዛት የሚገኝበት ለመንቀሳቀስም ሆነ መንገዱን መጠቀም በማይቻልበት ቦታ ወቅሮ ማራይ መሆኑ በሕዝብ ግንኙነት ጥናት አግኝተዋል። ወቅሮ ማራይ በደርግ ሚሊሺያ የታጠረ ነው። ቀኑ ደረሰ፣ አግአዚ ገሰሰና ነፃነት ሰንደቅ አብረው ከነስብሃት ጋር ሰመማ በሚባል ቦታ ተገናኙ። ስብሃት ነጋ ለአግአዚ በየትኛው ቦታ ለመሄድ አስበሃል ሲለው በመደባይ ታብር በኩል ሲለው የመረጥከው መንገድ አደገኛ ነው በማለት በሕዝብ ግንኙነት አጥንተን ወቅሮ ማራይ ነፃ መሆኑን፣ ሚሊሻም ሆነ የደርግ ሰራዊት የሌለበት ነው ካሉት በኋላ በህሳቡ ተስማምተው መንገዳቸውን ቀጠሉ። ነፃነት ሰንደቅ አብሮት ስለነበረ ሁሉንም ሰምቶታል። ወቅሮ ማራይ እንደገቡ በሚሊሻ ተከበው በተተኮሰ ጥይት አግአዚ ገሰሰ ወዲያውኑ ወድቆ ሞተ። ነጻነት ግን አመለጠ። እንደምንም ብሎ ዘና ወረዳ ገባ። እዛ ላገኛቸው ታጋዮች የደረሰባቸውን ሲነግራቸው፣ ነፃና ጥሩ መንገድ ነው ብለው ስብሃትና አባይ ፀሃየ አግአዚም የተናገሩትን አምኖ በሚሊሻ ተከበን የጥይት ናዳ ወርዶብን አግአዚን ገደሉት፣ እኔ አመለጥኩ። ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ባዘጋጁት የግደያ ዘዴ የሚቃወማቸውን አግአዚ ገሰሰውን አጠፉት ብሎ የተናገረው በተሓህት ውስጥ ተሰራጨ። ስብሃትና አባይ ተከታትለው ነፃነትን ለማግኘት የተፈጠረው ነገር ለማንም እንዳይነገር አስጠነቀቁ። ሆኖም ግን ነገሩ ተሰራጭቷል። አመራሩም የአግአዚን ሁኔታ አንዲት ቀንም ሳያነሳ ቆይቶ በ1ኛው ጉበኤ በጠላት ተገደለ ብለው ተናገሩ። የስብሃት የግድያ ሴራም ሰመረለት።
3. መሃሪ ተክለ
መሃሪ ተክለ የበረሃ ስሙ ሙሴ ነው። በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ሲማር የቆየ፤ ከሻእቢያ ጋር የተሰለፈ የሻእቢያ ታጋይና አመራር የነበረ ሰው ነው። ሻእቢያና ማገብትን በማይበጠስ የብረት ሰንሰለት ያቆራኘው መሃሪ ተክሌ ነው። ማገብትን የመሰረቱት እነ አረጋዊ በርሄ በጥር 1967 ሳህል ኤርትራ በረሃ ወርደው በሻእቢያ ወታደራዊ ትምህርት ሰልጥነው ብረት ታጥቀው ደደቢት በረሃ እንዲወርዱ ትልቅ ሚና የተጫወተው መሃሪ ተክሌ ነው። መሃሪ ተክሌ በሻእቢያ ተፈቅዶለት በተሓህት ውስጥ እንዲታገል ደደቢት በረሃ ከነ አረጋዊ በርሄ ተቀላቅሎ የተሓህት ተዋጊም ሆነ።
የሙሴ ያልተጠበቀ የአቋም ለውጥ
ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
ማስታወሻ ለአንባቢው፡፡ ባለፈው ሳምንት ሐተታዬ ‹‹የዘር አደን›› በሚል አሉባልታዊ ክስ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተሰነዘረበት ክስ ደግፌው ተሟግቼለታለሁ፡፡ በዚህም ሳምንት ድጋፌን በመቀጠል እነዚህ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የፈጠሙትን ግፍና በደል ጭቆና በመዘርዘር ራሳቸውን ነጻ በማድረግ የአይ ሲ ሲን (የኣለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤት) ስም በማብጠልጠልና የቆመለትን ዓላማ የሳተ በማስመሰል ገዢዎችና አስፈጻሚዎ ቡችሎቻቸው ያነሱዋቸውን ማስረጃ ቢስ ውንጀላዎች በተጨባጭ ማስረጃ ድርጊቶታቸውንና ሸፍጣቸውን ይፋ ለማድረግ ወስኛለሁ፡፡ የኦክቶበር 11-12, 2013 የአፍሪካ አንድነት ‹‹መሪዎች›› የጨረባ ስብሰባ የተጠራውም ቴአትራዊ የልብ ወለድ ሴራ ለማካሄድና ነጻ ለመምሰል የሚያስችላቸውን ቅጥፈት ለማናፈስ ነው፡፡
በኔ እምነት አይ ሲ ሲ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሕግጋት ትክክለኛውና ጠንካራው ምልክት ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ስራውን በማከናወን ላይ ነው፡፡እስካሁን ያስመዘገባቸው ውጤቶች ጥቂት ቢሆኑም ለወደፊቱ ግን ያሻቸውን በደልና ግፍ ፈጥመው ግድያና አስገድዶ መድፈርን ሰብአዊ መብት በደልን አዘው በማስፈጸም በሥልጣናቸውም አላግባብ ባልገውና ተጠቅመው፤ ሃገርን አራዉተው፤ ሕዝብን በበደልና ግፍ ጫና አጉብጠውና አንበርክከው፤ በነጻ ሲቀመጡና ሲንደላቀቁ የነበሩትን እያጋለጠ ለፍርድ ለማቅረብ የሚችል ጠንካራ ተቋም እንደሚሆን እምነቴ ነው፡፡ የአፍሪካ ጨቋኝና የግፍ በደል ባለቤት የሆኑት ገዢዎች በሕዝቡ ላይ ሊኩራሩና ሊደነፉ፤ የሕግ የበላይነትን በመጨፍለቅ ሊቀጥሉ ይጥሩ ይሆናል፤ አሁን ግን አይ ሲ ሲ ስለመጣባቸውና ለሕዝቡ ወግኖ ስለቆመ ስሙ በተጠራ ጊዜ እየተርበደበዱና መግቢያ እያጡ በመሄዳቸው የአይ ሲ ሲን ስም በማጉደፍ ነጻ ለመሆን ቢጥሩ መንገድ ሁሉ፤ በደላቸው ሁሉ፤ ግፋቸው ሁሉ አይ ሲ ሲን እየቀሰቀሰባቸው በመሆኑ ኦክቶበር 13 2013 የቁም ተዝካራቸው ማውጫ አድርገው ሊሰባሰቡ ነው፡፡
በኦክቶበር 11-12, 2013 አድመኞቹ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› አስተጋቢው የእንግዳ መቀበያ የአፍሪካ አዳራሽ በመሰባሰብ አብዛኛዎቹ በሮም ከጸደቀው ደንብ (አለም ኣቀፍ ዉል) በመውጣት በደስታ ተሞልተው የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን የሞት ውሳኔ ያስተላልፋሉ፡፡ ቀብሩንም ለማስፈጸም የኢትዮጵያ የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ አንድነት ተዘዋዋሪ የ2013ቱ ሊቀመንበር ሃይለማርያም ደሳለኝ ነው፡፡ ስብሰባውንም ሲከፍት ‹‹ዛሬ በዚህ የምጽዋት አዳራሻችን የተሰባሰብነው አይ ሲ ሲን ለማወደስ ሳይሀሆን ልንቀብረው ነው….›› በማለት ይሆናል፡፡ የዚህ የቀብር ጥድፍም ሰበቡ የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ በተካሄደው የ2007 ምርጫ ወቅት በፈጸመው የሰብአዊ መብት ግፍ ለመጠየቅ ኖቬምበር 12 2013 ለፍርድ ሊቀርብ በመሆኑ ነው፡፡ በተመሳሳይ ወንጀልም ምክትሉ ዊሊያም ሩቶ ፍርዱ በሄይግ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ መታየት ከጀመረ ሁለተኛ ወሩ ነው፡፡ የአፍሪካ አንድነት በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የተመሰረተውን ክስ ዘዴ ፈልጎ ካላነሳ በስተቀር ‹‹የኑክሊየር ፈንጂ መቃወሚያውን›› በመጠቀም ከአይ ሲ ሲ አባልነት ለመውጣት እንደሚችልም በማስፈራራት ላይ ነው፡፡
ላለፉት ጥቂት ወራት ሃይለማርያም በአይ ሲ ሲ ላይ የቃል ጦርነት ሲያካሂድ ነበር፡፡ ባለፈው ግንቦት የጃጀዉና በቅዠት ዓለም ያለው ሮበርት ሙጋቤን በመደገፍ በአይ ሲ ሲ ላይ ውንጀላ አካሂዷል፡፡ ግልጽና ማስረጃው ከመጠን ያለፈውን ግፍ ለፈጸመ የአፍሪካ ገዢ ጥብቅና መቆምና ሕዝብን ለባሰ ግፍ ማብቃት የሃይለማርያም የአፍሪካ ወቅታዊ ሊቀመንበርነት ተግባር ሆኗል፡፡ ሃይለማርያም ቃላትን በማሰባሰብና ከጀርባ ባሉት ሽነቋጭ አለቆቹ በመመራት ግራ የገባውን አባባል በመጠቀም አይ ሲ ሲ ‹‹99 በመቶ›› የሆኑት በደለኛ ተከሳሾች አፍሪካውያን በመሆናቸው የዘር አደን ላይ ነው የሚል መሰረተ ቢስ ወሬ እየነዛ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት በተካሄደው 68ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ባሰማው ወሬው፤ አይ ሲ ሲ የኬንያታንና የሩቶን ክስ በማንሳት ጉዳዩ በኬንያ ባለስልጣናት እንዲታይ ማድረግ አለበት በማለት የማይገባ የድፍረት ጥያቄ አንስቷል፡፡ ሆኖም ኬንያታ ከተሰነዘረበት ወንጀል ነጻ ሳያደርገው፤ ማድረግ ያሰበው ግን ኬንያታ ራሱ በሚያዘውና መመርያ በሚሰጠው ችሎት ይዳኝ ለማለት ነው፡፡ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ይይላሉ ሲተርቱ፡፡ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያና ናይጄርያ ለአይ ሲ ሲ ይጋባኝ ሰሚ የኬንያው ክስ እንዲነሳ ያቀረቡትን የጽሁፍ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ሃይለማርያም የዚህ ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ጉዳይ አፈጉባኤ ሆኖ የመገኘቱ ምጸታዊ መነሾ አስገራሚ ነው፡፡ 34 የአፍሪካ ሃገራት የሮምን ደንብ/ዉል የፈረሙበት ሲሆን (አይ ሲ ሲ ሰን በማቋቋም ወንጀሎችን በመመርመር ሰብአዊ መብት ጥሰትን የዘር ጭፍጨፋን ግፍ በማጥራት ለፍርድ እንዲያቀርብ ውክልናና ስልጣን ሰጥቶታል):: እስከሁንም ኢትዮጵያ የዚህ ሕግ አባል ለመሆን ፊርማዋን ነፍጋ ቆይታለች፡፡ የሃይለማርያም የሥላጣን አባት ይህን ሕገ ደምብ ላለመፈረም ወስኖ ያቆየው ምናልባትስ አይ ሲ ሲ እንደማይለቀውና ወንጀሉን አጥርቶ እንደሚፋረደው ተገንዝቦ ይሆን? ለፊርማውም ችግር የሆነበት ሰበብ ሕጉን ፈርሞ ከተቀበለው የፊርማው ቀለም ሳይደረቅ በሰራቸው ሕገ ወጥ ተግባራት በፈጃቸውና ባስፈጃቸው ንጹኃን ዜጎች ሳቢያ አይ ሲ ሲ በሩን እንደሚያንኳኳና ለሕግ እንደሚያቀርበው ጠንቅቆ በመረዳቱ ነው? እነዚያስ 34 ሃገራት ሕጉን አጽድቀው አይ ሲ ሲን ሲያቋቁሙ አይ ሲ ሲ የአፍሪካ ጋሻ መከታ ሆኖ ወንጀለኞችን አላንዳች አድልዎ እያደነ ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው አልተገነዘቡትም ነበር?
አይ ሲ ሲን በአፍሪካ አለሳልሶ የመግደል ጥበብ የሃይለማርያም ተንኳሽና የሚያስቆጣው ክሱ የሚያሳየው፤ አይ ሲ ሲን ከአፍሪካ በድል በማስወጣት እራሱን ‹‹ጭራቅ
ገዳዩ ጀግና›› ላመሰኘት የተነሳሳ መስላል፡፡ (የሱ ቀደምት የሥልጣን አባቱም ‹‹የአዲሱ ትውልድ አፍሪካዊ መሪ›› በሚል መጠርያ ለራሱ የፈረስ ስም ሰጥቶ፤ ታላቅ በመሆን በሽታ ተለክፎ ለማይለቅና ለማይድን እጀሰብ ተዳርጎ ነበር::) የነገሩ እውነታ መሰርት ግን በዚህ አካሄድ የሃይለማርያምና የጸረመስቀል ተዋጊዎቹ አካሄድ በኬንያዊያን ባለስልጣናት ላይ የተመሰረተውን ክስ ለማስነሳት፤ በብዛት ከአይሲ ሲ አባልነት መውጣትን እንደማስፈራሪያና ማገቻ በማድረግ ወንድሞቹን ኬንያታንና ሩቶን ከአይ ሲ ሲ ማነቆ በማላቀቅ፤ ወደፊት በእነሱ ላይ ሊደርስ የማይችለውን አይቀሬውን ህጋዊ የክስ እርምጃ አስቀድሞ ለመዝጋት የሚያደርገው የአልሞት ባይ ተጋዳይ የሕልም ሩጫ ነው፡፡ አፍሪካን በሚገባት ከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ላመስቀመጥ የሚጥረውን አይ ሲ ሲን ለማጥፋት ከንቱ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ሃይለማርያምና መሰል ግፈኛ ገዢዎች ራሳቸውን ከግፍ ባህሪና ልምዳቸው በመመለስ እንደሰው በማሰብ ለሰብአዊ ፍጡራን ተገቢውን አገልግሎት ለማከናወን ቢተጉ ይበጃቸዋል፡፡
በኦክቶበር 11-12 2013 በአፈሪካ አንድነት ስለ አይ ሲ ሲ ቀብር ስለሚደረገው ንግግር ቅድመ ትርኢት
የአፍሪካ ‹‹ገዢዎች›› በኦክቶበር 11-12 2013 በአፍሪካ አንድነት በሚሰባሰቡበት ጊዜ ስለሚያካሂዱት እብደት ቀረሽ ጸረ አይ ሲ ሲ ዘመቻ በቂ ግንዛቤ አለን፡፡ የንግግራቸው መነሾና አካሄድየ አይ ሲ ሲን ወኔ ለመገድልና ተግባሩን ለማገድ አስቀድሞ ንድፉ በአምባሳደር ቋሚ ተወካይ ማቻሪያ ካማው፤ በኬንያ በተባበሩት መንግስታታ ቋሚ ሚሲዮን በኩል ለአምባሳደር ሜናንካዶ (የሴኪውሪቲ ካውንስል የሜይ ወር 2013 ሊቀመንበር) በተዘጋጀው ባለ 13 ገጽ ሚስጥራዊ ሰነድ ተዘርዝሯል፡፡
1. መላ የሌለውና ቅጥ ያጣ እርማት የተካሄደበት የካማው ሚስጥራዊ ሰነድ፤
ኬንያታን ሩቶ ከአይ ሲ ሲ ማነቆ ሊላቀቁ ይገባል ምክንያቱም እነሱን ለክስ ማቅረብ የኬንያን ልኡላዊነት ነጻነት የሚጥስ ነው፡፡ እንደ ካማው አባባል ‹‹የኬንያታና የሩቶ ክስ ራሱን ለሚያስተዳድረው መንግስታችን በውስጥ ጉዳያችንና በሃገራችን ኬንያና በልኡላዊነታችን ላይ የተቃጣ ውርደት ነው በማለት ይከራከራል፡፡ የኬንያ ልኡላዊነት ከኬንያ ውስጥና ውጭ የተለያዩ ተዋንያንን በመጠቀም ለወቀሳ እየተዳረግን ነው፡፡እንዳለፈውና እንደተለመደው የሲቪሉን ማህበረሰብ በማነሳሳት የራሱን ፖሊሲ እንዲቃወም በመደረግ የሮምን ስምምነት ሰበብ በማድረግ አይሲሲን በአስፈጻሚነት እየተጠቀሙበት ነው፡፡›› ነጻነት ለአፍሪካውያን ጨካኝና አረመኔ ገዢዎች የመጀመርያው ስደተኛ ነው፡፡ አሁን የአፍሪካን ነጻነት ለማስከበር በማለት የሚንደፋደፉት አስመሳይ የአፍሪካ ጨቋኞች በኖቬምበር 2010 ምርጫ ወቅት ፈረንሳይ በቀጥታ በአይቮሪኮስት ግጭት ጣልቃ በገባችበት ወቅት፤ ገዳም እንደገባች አይጥ ተሸጉጠው ትንፍሽ ሳይሉ ፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛቷን መልሳ ስተወር አንዲት ቃል አልተነፈሱም፡፡ የአፍሪካ አንድነትም ቢሆን በዝምታ ተቀምጦ ጠበይ ተመልካች በመሆን ከጎን ሆኖ ከመመልከት አላለፈም፡፡ በጃንዋሪ 2013 ፈረንሳይ የሰሜን ማሊን ከሽብርተኞች ወረራ ነጻ ለማውጣት ጣልቃ ሲገባ የአፍሪካ መሪዎች የፈረንሳይን ጦር ለማስወጣት የነጻነትንና የልእልና ማስከበርን ጉዳይ አላነሱም፡፡ አሁንም እንደገና የአፍሪካ አንድነት ከተመልካችነት አላለፈም፡፡
በወንጀል ፤ በሰብአዊ መብት ጥሰት፤በጦር ወንጀለኛነት፤በዘር ማጥፋት ለሚሰነዘር ክስ ሉአላዊነት ሕጋዊ መከላከያ አለያም የፖለቲካ ውይይት ሁኖ አይቆምም፡፡ አሁን በአፍሪካ ፈላጭ ቆርጫ ገዢዎች የሚነሳው የሉአላዊነት ጥያቄ አይ ሲ ሲ የተጣለበትን አደራ ላማዘናገት ሆን ተብሎ የተነሳና ቀድሞ ከነበሩት የንጉሳዊ ገዢዎች በምድራዊ ዳኝነት እንጠየቅም ሥዩመ እግዚአብሔር ነን እንደሚሉት ለመሆን የታቀደ ዘዴ ነው፡፡ ሕገ ወጥ የሆነውን የአፍሪቃ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ሊዳኘው የሚገባውና የሚችለው ሌላው ሕገወጥ አፍሪካዊ ገዢ መሆን አለበት ነው የሚሉት፡፡
2. ኬንያታና ሩቶ ከክስ ነጻ የመሆን መብት አላቸው ምክንያቱም በማርች 2013ቱ ምርጫ ‹‹ንጹህ›› ናቸው ስለተባሉ፤ካማው ኬንያታና ሩቶን በተመለከተ ሁለቱ ሰዎች ንጹሃን ብቻ ሳይሆኑ በክፍተኛው የመንግስት ስልጣን ላይ ስለተቀመጡ ሃለፊነትም አለባቸውና ክሱ ሊሰረዝላቸው ይገባል በማለት ይሞግታል፡፡ አይ ሲ ሲ የከፈተው የክስ
መዝገብ የሚዘጋበት ምክንያት ኬንታና ሩቶ የፈጸሙት የሰብአዊ መብት ድፍረትና ጥሰት በፍትህ አደባባይ ቆሞ ስለሚመሰክርባቸውና ለፍርድ ሊያቀርባቸው ስለሚችል የንጹሃን ግፍና በደል በነሱ የስልጣን ወንበር መያዝ ተቻችሎ ነጻ ሊሆኑ ይገባል ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ዋናና ምክትል ገዢዎች የኬንያውያን ሁሉ መተሳሰርያ በመሆናቸውና ሕዝቡም በፍቅር ስለመረጣቸው፤ 86 በመቶ ድምጹን ሰጥቶ መንበራቸው ላይ ስላስቀመጣቸው ክሱ ሊሰረዝላቸው ግድ ነው፡፡ ካሙ ክርክሩን በመቀጠል፤ የሮሙ
ስምምነት ኬንያታንና ሩቶ ሊያካትት አይገባም፤ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛውን የሃገሪቱን አመራር በዋናነትና በምክትልነት የያዙ በመሆናቸውና የኬንያ ሪፑብሊክ የመከላከያ አዘዦች በመሆናቸው፤ነው ይለናል፡፡ ካሙንን ግራ ያጋበው ነገር ኬንያታና ሩቶ ንፁህነታቸውን ለማረጋገጥ መመረጥ አያስፈልጋቸውም፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በፍርድ ሸንጎ ወንጀለኛ እስካልተባለ ድረስ ንጹህ ነውና፡፡ ስለዚህም በተጠረጠሩበት ወንጀል ኣይ ሲ ሲ የሚለው ችሎት ፊት ቀርበው ንጸህናቸውን በነጻ የፍትሕ ስርአት ያረጋግጡ

Four arrested in church supporting Aba Girma and Co
Dear all
Please read and watch the video which is reported by The Wandsworth Guardian (click on the link below). the church dispute is still on going the charity commission has given an appointment for both parties to come to common solution. the Woyanee Aba Girma and co has refused to go. instead WOYANE’s Aba Girma and the Embassy agreed to invite woyanee cadres Abun Gebreail and Abun Enttonos from Ethiopia to open the church forcefully by breaking British law while the matter is in the hands of charity commission. the true Ethiopian went out to protect the church. Aba Girma’s hired mercenaries were arrested and will be brought to court soon. please pass to link to all Ethiopian.
Abbey Desta
http://www.wandsworthguardian.co.uk/archive/2013/10/15/10739816.VIDEO__Election_dispute_leads_to_violence_outside_church/
http://www.wandsworthguardian.co.uk/news/10735602.Four_arrested_in_church_protest/

Subscribe to:
Posts (Atom)