Friday, October 31, 2014

ደስተኛ ለመሆን ትፈልጋላችሁ? እነዚህን 20 አመለካከቶች ቀይሩ

ደስተኛ ሰዎች እያንዳንዱ እርምጃቸው ላይ በራስ መተማመን ይታያል፡፡ የሚናገሩትን ነገር የሚያደርጉት ይመስላል፡፡ የትኛውም ስፍራ ሲገኙ ዙሪያ ገባውን በአስደሳች ስሜት መሙላት ያውቁበታል፡፡ ደስተኛ ሰዎች ህይወትን በደስታ እያጣጣሙ መኖር የሚችሉበትን ምስጢር የደረሱበት ይመስላልየእነዚህ ሰዎች ደስታ ምስጢር በአመዛኙ ከአንዳንድ አይነት ልማድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ማህበረሰቡ ‹‹ይሄ ብቻ ነው ልክ ብሎ›› ሙሉ እውቅና የሰጠውን ነገር እነርሱ ሌላ ልክ ነው ወይም የተሻለ ነው ብለው በሚያስቡት ልምድ የመተካት ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡ ደስተኛ ሰዎች ደስተኛ ለመሆን ወደ ውጪ አይመለከቱም፡፡ ይልቁንም የውስጥ መሪ ኮምፓሳቸው ላይ እምነት ይጥላሉ፡፡
ደስታ ኮትኩተው ሊያሳድጉት የሚችሉት ነገር ነው፡፡ እናም ማህበረሰቡ ልክ ናቸው ብሎ ያጠመቀንን ልማዶች በገዛ ራሳችን የውስጥ ምሪት በተገኙ ልማዶች በምንተካበት ልክ ደስተኛ እንሆናለን፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 20 አመለካከቶች ኑሮ የሚባል ትምህርት ቤት ውስጥ ቀስመናቸዋል የምንላቸው ነገር ግን መለወጥ የሚገባቸው የህይወት አተያዮች ናቸው፡፡ መቀየር የሚጠበቅብንን እነዚህን አመለካከቶች እስኪ አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡
1. አንድ ነገር የሚሰራበት ልክ እና ስህተት የሆነ መንገድ አለ፡፡
አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እና የተለዩ ሂደቶችን መፈተሽ የዕድገት አካል ነው፡፡ ለአንድ ሰው የሚሰራ ነገር ለአንተ/ለአንቺ አይሰራ ይሆናል፡፡ የራሳችሁን እምነት እና የራሳችሁን ሂደት ፈልጉ እና እርሱን ተከተሉ፡፡ ሌሎችም እንዲሁ የራሳቸውን ፈልገው ይከተሉ፡፡2. ሌሎችን መምሰል ህብረት መፍጠር ነው፡፡ ሌሎችን ለመምሰል ስንሞክር የራሳችን የውስጥ ፍላጎት ላይ እስር እናውጃለን፡፡ ሌሎችን ለመምሰል መሞከር ለራስ ታማኝ አለመሆን ነው፡፡ ሌሎችን ለመምሰል ከመጣር ይልቅ ከገዛ የውስጥ እና የእውነት ማንነታችን ጋር ለመሰለፍ፣ በአንድነት ለመቆም ጥረት ማድረግ ይበልጣል፡፡ በራሳችሁ መተማመን ስትጀምሩ እና በራሳችሁ ደስተኛ ስትሆኑ ከሌሎች ጋርም ራሳችሁን ሳታጡ የላቀ ግንኙነት እና ትብብር መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ 3. ጠንክሮ መስራት ስኬታማ ያደርጋል፡፡ ከልክ በላይ ትዝላላችሁ፡፡ በጥረታችሁ ያን ያህል አትደሰቱም፡፡ በጥንካሬ በመስራት ምትክ በብልሃት እንዴት መስራት እንደምትችሉ አስቡ፡፡ ስኬታችሁን በምታገኙት ደስታ መጠን መዝኑ፡፡ 4. ውድቀት ክፉ ነገር ነው፡፡ መውደቅ ስለራሳችሁ ድንቅ ትምህርት የምትቀስሙበት መንገድ ነው፡፡ አንዳንድ ነገሮችን ሞክረን ሳይሳካልን ሲቀር ለምን ሊሳካልን እንዳልቻለ እና በቀጣይ ደግሞ ምን ምን ብናደርግ ስኬታማ መሆን እንደምንችል እንማራለን፡፡ አለማችን ላይ እጅግ በጣም የተሳካላቸው ሰዎች ብዙዎቹ ብዙ ጊዜ ወድቀው የተነሱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ‹‹በቂ ውድቀት ውድቄያለሁ ወይ?›› 5. ብቻችሁን ሆናችሁ ማለት ብቸኛ እንደሆናችሁ ትዘልቃላችሁ ማለት ነው፡፡ ከራሳችሁ ጋር በምትኑበት ወቅት ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የምትችሉ ከሆነ ብቻችሁን የምትሆኑበት ጊዜ ያለ ምንም ጥርጥር መጠኑ እያነሰ ይመጣል፡፡ 6. ህይወት አልጋ በአልጋ መሆን አለበት፡፡ የህይወት ከፍታና ዝቅታዎች ሚዛናዊ ህይወት የምንኖርበት መንገድ ነው፡፡ እያንዳንዱን ሂደት በፀጋ ተቀበሉ፡፡ ግብግብ መግጠማችሁን ስትተዉ ሰላም ማግኘት ትጀምራላችሁ፡፡ 7. ሰዎች ስለ እናንተ የሚያስቡት ነገር ወሳኝ ነው፡፡ ዋናው እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር እናንተ ስለ እናንተ የምታስቡት ነው፡፡ ከራሳችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ላይ ስሩ፡፡ ከአሰባችሁት በላይ ደስታ እና ፍቅር ይሰማችኋል፡፡ 8. ቀጭን፣ ቆንጆ፣ ብልጥ፣ ሀብታም፣ ጤነኛ ብትኑ ኖሮ ደስተኛ ትሆኑ ነበር፡፡ ከእናንተ ቁጥጥር ውጪ ያለ ነገር ላይ ደርሳችሁ ደስተኛ እንሆናለን ብሎ ማሰብ ከንቱ ድካም ነው፡፡ የምትፈልጉት የክብደት መጠን፣ የምትፈልጉት አይነት አፍቃሪ ግንኙነት፣ ፍፁም ለእናንተ የሚስማማ ስራ አግኝታችሁ ይሁን እንጂ ደስተኛ መሆን ያልቻላችሁት ምን ያህል ጊዜ ነው? ሁልጊዜ! ደስታ ከእኛ ውጪ የሚገኝ ነገር አይደለም፡፡ ይልቁንም እውስጣችን የሚገኝ ፈርጥ ነው፡፡ 9. ህይወታችሁ ከመንገድ ዝንፍ ብሎ ወጥቷል፡፡ ‹‹መድረስ ያለብኝ ቦታ አይደለም የደረስኩት›› አልያም ደግሞ ‹‹ህይወቴን እንደ አሰብኩት አይደለም እየመራሁ የምገኘው›› የሚል ሃሳብ ዛሬን በደስታ እንዳታሳልፉ እንቅፋት ይሆንባችኋል፡፡ የምትፈልጉት ቦታ ነው ያላችሁት፡፡ ሁሉም ነገር ያለ ምንም መዛነፍ እንደሚከናወን እመኑ፡፡ 10. መተው መሸነፍ ነው፡፡ ወደ ታች የሚጎትታችሁን ነገር መተው ስኬት እና ደስታ የምታገኙበት አንድ አዲስ መንገድ ነው፡፡ ጥቅም እየሰጣችሁ ያልሆነን ነገር ስትተዉ ከልብ የምትፈልጉት ነገር ወደ ህይወታችሁ እንዲገባ በራችሁን ወለል አድርጋችሁ ከፈታችሁ ማለት ነው፡፡ ‹‹መተው ነገሬን ከተተው›› አደል ከነተረቱስ? 11. አልሆን ያለን ነገር መጠበቅ ጥሩ ነው፡፡ ከአዲስ እና እንግዳ ዓለም ጋር በስምምነት መኖርን እወቁበት፡፡ አልሳካ ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሁ የማናውቀውን መልዓክ ስለፈራን ብቻ የምናውቀው ሰይጣን ላይ ተጣብቀን መኖር የለብንም፡፡ 12. ደስታን ለነገ፣ ለነገ ወዲያ ይደርስበታል ብሎ ማለፍ ያስፈልጋል፡፡ ጡረታ፣ የዓመት ረፍት፣ ቅዳሜ እና እሁድ ወዘተ… የምንላቸው ነገሮች በአሁኑ ሰዓት ደስታን ለአለማጣጣም በምክንያትነት የምንደረድራቸው ሰበቦች ናቸው፡፡ እያንዳንዱን ቀን በደስታ ለማሳለፍ ሞክሩ፡፡ 13. ከልባችሁ ይልቅ ጭንቅላታችሁን መስማት አለባችሁ፡፡ ጭንቅላታችሁ አንዳንዴ ልክ እንደሆነ ከሚሰማችሁ ነገር ውስጥ ጎትቶ ያወጣችኋል፡፡ የልባችሁን ምሪት መከተል ስህተት አይደለም፡፡ ያላችሁበት የትኛውም አይነት ሁኔታ ልክ እንደሆነ ይሰማችሁ እንደሆነ ራሳችሁን ጠይቁ፡፡ 14. እንዴት እውን እንደምታደርጉት/እንደምታሳኩት ያላወቃችሁትን ነገር አትሞክሩ፡፡ ህልማችንን እንዴት ማሳካት እንደምንችል እግረ መንገዳችንን እንማራለን፡፡ ስለዚህ ሞክሩት፡፡ የወደፊቱ ማንነታችሁ (Future self) ያመሰግናችኋል፡፡ 15. የማይተባበሯችሁ ሰዎች ስለ እናንተ ግድ የላቸውም፡፡ ሌሎች የሚናገሩት እና የሚሰሩት ነገር ከእናንተ ጋር ምንም የሚያያይዘው ነገር የለም፡፡ ይበልጥ በራሳችሁ እና በህልማችሁ መተማመን በጀመራችሁ መጠን ያን ያህል ሌሎች አመኑባችሁ አላመኑባችሁ ግድ አይሰጣችሁም፡፡ 16. ራስን መውደድ ስህተት ነው፡፡ ለራሳችሁ መቆም ስትችሉ ነው ለቀሪው ዓለምም መቆም የምትችሉት፡፡ ሁሌም ቢሆን ፍቅርን ከራሳችሁ እንደጀመራችሁ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ሙሉ ነገር ነው ለሌላውም የሚተርፈው፡፡ 17. ህልማችሁን ወደ ጎን ተወት አድርጋችሁ ኃላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ፡፡ ህልማችሁ ኃላፊነታችሁ ነው፡፡ በመሆኑም በረባ ባልረባ ሰበባ ሰበብ የነፍስ ጥሪያችሁን ቸል አትበሉ፡፡ 18. መዳረሻው ነው ሽልማቱ፡፡ መድረስ የሚባል ነገር የለም፤ ሂደቱ እና ጉዞው ነው ሽልማቱ፡፡ ስለዚህ እመንገዳችሁ ላይ ሃሳባችሁን ሰብስባችሁ መገኘታችሁን አረጋግጡ፡፡ 19. ምስጢርን ማካፈል የድክመት ምልክት ነው፡፡ የውስጥ ስሜታችሁን እና ሃሳባችሁን ለሌሎች ማካፈል ደስተኛ መሆን የምትችሉበት ምስጢር ነው፡፡ ስሜታችሁን ማካፈል ማለት ግልፅ መሆን እና ነገሮችን ለመሸፋፈን አለመጣጣር ማለት ነው፡፡ ግልፅነት አሁን የምትገኙበትን ማንኛውም አይነት ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ መቀበል እና በኩራት ይህንን ማንነት ማንፀባረቅ ስራችሁ ነው፡፡ 20. ማንነታችሁ ስራችሁ ነው፡፡ እናንተ ተውላጠ ስም አይደላችሁም፡፡ ከስራችሁ እና ከለት ተለት እንቅስቃሴያችሁ በላይ እጅግ የላቃችሁ ናችሁ፡፡ ሁሉን ነገር ማንነትንም ጨምሮ ከሥራ ጋር ማያያዝ ተገቢ አይደለም፡፡ ሥራችሁ የማንነታችሁ አንድ አካል እንጂ ማንነታችሁ አይደለም፡፡

U.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist


Press Statement
Jen Psaki
Department Spokesperson
Washington, DC
October 30, 2014
The United States is deeply concerned by the October 27 sentencing of Ethiopian journalist Temesgen Desalegn to three years in prison forU.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist “provocation and dissemination of inaccurate information.” Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elements of a democratic society, and the promotion and protection of these rights and freedoms are basic responsibilities of democratic governments.
As President Obama stated during his meeting in September with Ethiopian Prime Minister Hailemariam, it is important that Ethiopia’s progress and positive example on economic development and regional conflict resolution extends to civil society as well. We urge Ethiopia to make similar progress with regard to respect for press freedom and the free flow of ideas and reiterate our call for the Ethiopian government to release journalists imprisoned for exercising their right to freedom of expression.

Ethiopian Muslim arbitration committee letter to President Obama

President of the United States of America 1600 Pennsylvania Ave NW
Washington, DC 20500
United States
October 22, 2014
Dear Mr. President,
We are 19 Ethiopian Muslims writing to you from within the Ethiopian gulags. Since we were arrested and detained on fabricated charges under the country’s notorious anti-terrorism laws more than two years ago, we have been going through Stalinist political show trial designed to intimidate and silence us into submission in the face of the government’s audacious and grotesque program of re-indoctrinating Ethiopian Muslim.
Mandela+Obama+The Ethio-Muslims cause
We categorically reject the ridiculous allegations against us. Our only crime is to demand respect for the principle of secularism and the freedom of religion and conscience guaranteed by the Ethiopian Constitution and universal human rights. If there is a criminal in this whole saga, if there is a terrorist, it is the government that has the audacity to re-indoctrinate the entire Muslim community by transgressing and overstepping the limits set by our Constitution. Our struggle is a struggle for civil rights, for the protection of the principle of separation of state and religion, for the guarantees of freedom of religion and conscience. Our protest is a protest to keep our hope for a dignified life alive – to preserve the right to believe, preach, and practice a religion of our choice.
Mr. President, what goes on in the name of fighting terrorism in this part of the world is a stain on your conscience and the conscience of all those who value freedom and justice. The war against terrorism provided the normative language and the ethical framework for oppressive and silencing Anti-terrorism legislation being used to silence journalists, politicians, activists, and all those opposed to the policies of the state. Mr. President, the legal system in Ethiopia is being used as a weapon against innocent citizens whose only crime is to protest against the government’s outrageous imposition of a little known sect of Islam on the more than 35 million Ethiopian Muslims. This is a fact thoroughly documented not only by major human rights organizations like Amnesty International, and Human Rights Watch but also by governmental bodies including your own State Department’s Bureau of Democracy and Human Rights and the bi-partisan United States Commission on International Religious Freedom.
Mr. President, the United States is responsible for defining, rationalizing, justifying and leading the ‘global war of terror’. Indeed, the United States defined the war on terror as a war of good against evil and defended it as a ‘war to protect human rights’. Just like the war against communism before it, this war too has provided the conceptual and political framework within which to code and decode the friend-foe distinction within autocratic systems that lacks independent institutions. Just like anti-communism laws were used to repress and silence black liberationist movements in Apartheid South Africa and other places, the Anti-terrorism laws are being used with the same logic and to obtain the same oppressive result. The ‘strong men’ of Africa that you spoke about in Accra are using the war on terror for a completely different end – to suppress and subjugate our voices from being hear, our claims from being recognized, and grievances from being acknowledged.
Mr. President, as a man of law who practiced and taught law, you know too well the unfinished character of legal rules, and how violent they can be. You know how they can be bent and used for entirely different
purposes even in a system that operates under the rule of law. You know too well how law has been used in Jim Crow South and Apartheid South Africa to quickly and efficiently smash the very possibility of dissent and opposition, to mute and paralyze the very possibility of protest and activism. Just like Apartheid South Africa used Anti-Communism laws to eliminate any form of resistance against its racist policies, today’s Ethiopia uses Anti-Terrorism laws to smash those who oppose its oppressive and totalitarian policies. Ethiopia’s war on terror is a war against freedom and justice: a weapon against all those who seek to demand the most basic of rights that many in the world take for granted.
We are neither the first nor will we be the last prisoners of conscience in this country. The legal system is used to tie the hands of justice and deliver a verdict in the image of the ruling party. Your own government has documented the procedural irregularities and undue interferences used to secure convictions of prominent politicians and journalists including Birtukan Midaksa, Eskindir Nega, Andualem Arage, Bekele Gerba, Olbana Lelisa, Reyot Alemu and many other victims of Ethiopia’s thriving show trial industry.
Mr. President, you should be disgusted and outraged with the naked honesty with which the legal system is mobilized as a weapon to silence, intimidate, and eliminate those who raise issues that will one day turn into politically vital questions. You should be haunted by the specter of an innocent man tormented and dehumanized in Ethiopian prisons for no fault of their own, for believing and cherishing in the imperatives of human dignity, equality, and liberty. You should be troubled by the fact that your own actions are openly invoked in this country as a reference and as a justification for the greatest crime against innocent individuals and society. Imposing a new religion through coercion and violence is the greatest terror against society and to be denied the right to dissent this outrageous act, and then to be tried for terrorism is the ultimate travesty. You should be woken up by the cries of injustices done in the name of a war whose policy and strategy your country helped to formulate.
Mr. President, you stated on several occasion that America’s commitment to freedom and human dignity is among the essential expressions of American exceptionalism. In your speech in South Africa, you talked about how the struggle against Apartheid opened your eyes at a time when “my government is supporting Apartheid.” But Mr. President, your administration is doing the exact same things that your predecessors did. The situation under Apartheid South Africa is much different from our own circumstances. However, much like Apartheid South Africa deployed the ‘Suppression of Communism Acts’ and terrorism against black South Africans to delegitimize their struggle in the eyes of white South Africans and the broader West, the Ethiopian government is using its anti-terrorism laws to achieve the same results.
Mr. President, let me get to the germ of the matter. In your Accra speech, you said that ‘Africa doesn’t need strongmen, it needs strong institutions’, and your promised to help build institutions. More recently in your speech at Nelson Mandela’s memorial, you challenged the Heads of States and Governments from across the world to ask themselves a deceptively simple question: “How well have I applied [Mandela’s] lesson’s in my own life?” And you went on to say that “There are too many leaders who claim solidarity with Madiba’s struggle for freedom, but do not tolerate dissent from their own people. And there are too many of us who stand on the sidelines, comfortable in complacency or cynicism when our voices must be heard.”
Mr. President, insignificant as we are in the grand scheme of things, we wanted to ask you that same question: how well have you applied Mandela’s lessons to your own life? As a leader of the most powerful state on earth and chief executive of a government that provides diplomatic and financial aid to my country – a country that deprived me of the most basic of legal guarantees, a country that, according to consistent reports by your own administration, abused every principle of fair play and scorned institutions of law and justice, how well have you applied Mandela’s lesson in your dealings with Africa’s strongmen? How well have you tried to use you power to build institutions of justice and the rule of law?

Mr. President, you often invoke the names of Martin Luther King and Nelson Mandela and you emphasize the need to honor the legacy of these extraordinary men. And because you often spoke about them, commemorated and celebrated their legacy and the ideals that they left behind, because of the visions and ideas you outlined in your books and in your speeches, because of all those promises and undertakings, your name has become synonymous with the names of these iconic figures and the ideals and values they exemplify. Your speech in Accra and during Mandela’s memorial was received as a promissory note issued by the leader of the “free world” to those under repressive systems. This promise is accepted by oppressed people all over the world, including us, as a binding undertaking. Mr. President, if your country has a role, direct or indirect, in creating the conditions of possibility for this oppressive weapon, that imposes on you a great responsibility to use the enormous resources at your disposal to ameliorate its unmitigated violence.
If your government cannot empathize with the suffering of people in this corner of the world, at least you have the ethical obligation not to aid and abet, not to legitimize and defend these strongmen. Ethiopians want the same rights and freedoms that “the free world” take-for-granted. As prisoners of conscience, we ask that you show some care to the millions of faceless and nameless victims of legalized violence in which you may have a direct or indirect part. We ask that you take steps to fulfill the promises you have made and to secure the freedom of all prisoners of conscience in Ethiopia. These are the cries constantly heard in the Ethiopian gulags. If you write them off as trivial distractions undeserving of your time; it will be a tragedy for the ideal of hope that so distinctively informs your own life.
Yours respectfully, Addis Ababa Ethiopia

አብርሃ ደስታ; ሀብታሙ አያሌው; የሽዋስ አሰፋ ; ዳንኤል ሺበሺ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው።‹‹የሽብር ቡድን አመራር በመሆን›› የሚል ሲሆን በተለይም የአንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹የሽብር ቡድኑ አመራር በመሆንና አባል በመመልመል›› በሚል የክስ ጭብጥ ቀርቦበታልል፡፡


Habtamu abrhayeshiwas daniel
• አብርሃ ደስታ የሁለት ድርጅቶች አባል ነው የሚል ክስ ተመስርቶበታል
• ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ታዟል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በልደታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በተሰየመው ችሎት 10 ተከሳሾች በፌደራል አቃቢ ህግ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ100 ገጽ በላይ የክስ ቻርጅ የተነበበላቸው ሲሆን ከክስ ቻርጁ ጋር ከ300 ገጽ በላይ የምርመራ ሰነድ ቀርቦባቸዋል፡፡ 
የክሱ መዝገብ የተከፈተው ዘላለም ወርቃገኘሁ በተባለውና ‹‹የግንቦት 7 አመራር ነው፡፡›› ተብሎ ክስ በተመሰረተበት ግለሰብ ሲሆን በዚህ የክስ መዝገብ የተካተቱትም፡-
1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ
2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው
3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ
5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ
6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ
7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን
8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ
9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ
10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው
ለሁሉም ተከሳሾች ከዛሬ በፊት ክስ እንዳልደረሳቸውና ዛሬ ፍርድ ቤት ውስጥ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ በችሎቱ 6ኛ ተከሳሽ ከሆነው ዮናታን ወልዴ በስተቀር ሁሉም ያለ ጠበቃ የቀረቡ ሲሆን ጠበቃዎቹ ያልቀረቡበት ምክንያትም ጠበቆቹ ደምበኞቻቸው የሚቀርቡበት ቦታና ጊዜ ስላልተነገራቸው እንዲሁም ቀደም ብለው እንዳይገናኙ በመደረጋቸው መሆኑን አቶ ኃብታሙ አያሌው ችሎቱ ላይ ተናግሯል፡፡ 
ከሳሹ የፌደራል አቃቢ ህግ በ1996 የወጣው የወንጀል ህግ እና የጸረ ሽብር ህግ ጠቅሶ ክስ ያቀረበ ሲሆን ክሶቹ በሁለት ዋና ዋና ጭብጦች ቀርበዋል፡፡ የመጀመሪያው ጭብጥ ‹‹ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር በጋራ በመስራት›› የሚል ሲሆን ‹‹ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ የመንግስትን መሰረተ ልማት በማፈራረስ፣ ህዝብን ለአመጸ በማነሳሳት መንግስትን መለወጥ አላማው አድርጎ ከሚሰራውና ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር አባል በመሆንና በወንጀል ድርጊቶች በመሳተፍ›› በሚል ቀርቧል፡፡ 
ሁለተኛው የክስ ጭብጥ ‹‹የሽብር ቡድን አመራር በመሆን›› የሚል ሲሆን በተለይም የአንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹የሽብር ቡድኑ አመራር በመሆንና አባል በመመልመል›› በሚል የክስ ጭብጥ ቀርቦበታልል፡፡
ከ2-5ኛ የክስ መዝገብ የሚገኙት ማለትም ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽ፣ አብርሃ ደስታና የሸዋስ አሰፋ ‹‹ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ከለላ በማድረግ ግንቦት 7 የተባለውን የሽብር ቡድን አላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ፋሲል የኔ ዓለምና ሌሎች የሽብር ቡድኑ አባላት ጋር በስልክ በመነጋገርና በማህበራዊ ድህረ ገጸ የተለያዩ መልዕክቶችን ተለዋውጠዋል›› የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ አብርሃ ደስታ ከግንቦት 7 በተጨማሪ ‹‹ደምኢት የተባለ ቡድን አባል ነው፡፡›› የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡ 
በስተመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አንደኛው ረቡዕ ጥቅምት 26/2007 ዓ.ም 3 ሰዓት ተከሳሾቹ ዋስትና ይሰጣቸው አይሰጣቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤቱ ከተከሳሾቹ ጠበቆች ጋር ተማክሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል፡፡ በሁለተኛነት ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ቀደም ሲል ለአራት ወራት ወደቆዩበት ማዕከላዊ እስር ቤት እንዳይመለሱ ፍርድ ቤቱን ስለጠየቁ ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት (3ኛ) እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሾቹ ትናንት ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ የነበር ቢሆንም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ጠዋት ወደ ልደታ ፍርድ ቤት ተወስደው የነበረ ቢሆንም እንደገና ወደማዕከላዊ ተመልሰው ከሰዓት እንዲቀርቡ ተደርገዋል፡፡

U.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist

The United States is deeply concerned by the October 27 sentencing of Ethiopian journalist Temesgen Desalegn to three years in prison for “provocation and dissemination of inaccurate information.” Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elements of a democratic society, and the promotion and protection of these rights and freedoms are basic responsibilities of democratic governments. 

As President Obama stated during his meeting in September with Ethiopian Prime Minister Hailemariam, it is important that Ethiopia’s progress and positive example on economic development and regional conflict resolution extends to civil society as well. We urge Ethiopia to make similar progress with regard to respect for press freedom and the free flow of ideas and reiterate our call for the Ethiopian government to release journalists imprisoned for exercising their right to freedom of expression.