Saturday, November 23, 2013

The Saudi Government paying for deportation of illegals – Arab News


(Arab News) The Saudi government will cover the cost of deporting illegal foreign workers, an official said recently.

“Saudi Arabian Airlines has been entrusted with the task of ensuring flight bookings or, if required, charter additional flights to return illegal workers to their countries,” said Col. Bader Al-Saud, director of media and public relations at the Makkah police department.

ethiopia saudi nov 14Meanwhile, Al-Saud said deportation procedures for illegal expatriates include holding them at the general services center in Al-Shumaisi outside Makkah after their arrest.
He said the center does not admit or deport any foreign worker on its own. The center detains violators arrested by the security agencies. It issues a statement with the details of each detainee received at the facility. The operations are digitized and accurate statistics compiled, Al-Saud said.
“The officials at the center ascertain the nationality of each detainee while officials from foreign consulates keep track of the details of their nationals. The detainees are put up in separate areas according to their nationalities,” he said.


Detainees are given documents showing their biometrics and photographs. These documents are then handed to their consulates, which would then issue exit passes. When travel documents are verified, embarkation permits with air tickets are given to the detainees, Al-Saud said. “If a consulate refuses to issue a travel document to a detainee, he will not be deported. However, there has not been such a case so far,” he said.

The center has provided a special area for consulate representatives to issue travel documents to their citizens. An official of the Ministry of Foreign Affairs is also present to coordinate procedures between the consular officials and the security agencies, he said.
In a related development, Brig. Mansour Al-Turki, spokesman for the Interior Ministry, said the Kingdom would not permanently ban any deportees from returning to Saudi Arabia.
He said all illegal workers would have the option to return. “The regulations only stipulate a ban of 10 years,” he said.
Al-Turki said eight planes would deport more than 2,000 Ethiopians on a daily basis to their home country. They would leave the country as soon as the Interior Ministry prepares their documents, he said.
Commenting on the news that some illegal Ethiopians had fled the government-run shelter, Brig. Gen Nasser Al-Qahtani, Riyadh police spokesman, said workers were free to move around. “They are not in detention. All the doors are open for everyone to go out and buy necessities.”


Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

ፋሽስት ወያኔ በጅዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤቱን ላልተወሰነ ጊዜ መዘወጋቱን አስታወቀ

     በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በተለያዩ ቦታዎች የወገኖቻችን ስቃይ ዋይታና ግድያ አሁንም አላቆመም፤ በእያንዳንዷ ደቂቃ ምን ይፈጠር ይሆን በማለት በጭንቅ በጥብ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው የመመለሰቸው ተስፋ አይሎ ባለበት በአሁኑ ሰአት ፋሽስት ወያኔ አገልግሎት እንደማይሰጥ በማስታወቅ የጅዳውን ቆንስላ ጽ/ቤቱን መዝጋቱን በማስታወቂያ መግለጹ ከወደ ሳዉዲ አረቢያ እየተሳማ ነው።
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በወገኖቻቸው ላይ እየደረሰ ያለውን መስመር የሳተ ግፍና በደል ለማስቆም፤ በያሉበት ድምጽ ለሌላቸው ወገኖቻችን ድምጽ በመሆን የሳውዲውን መንግስት በዓለም ዙሪያ በማጋለጥና የዲፕሎማሲ ውጥረት ውስጥ ለመክተት እየጣሩ ባሉበት ባሁኑ ሰአት፤ ፋሽስት ወያኔ የአንበሳውን ድርሻ መጫወት ሲገባው በጅዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤቱን መዝጋቱ ብዙዎችን አሳዝኗል። ወደ ሀገራችን እንመለሳለን የሚል እንጥፍጣፊ ተስፋ ሰንቀው እየጠበቁ የነበሩ ተጎጂ ወገኖቻችንንም ተስፋ የሰበረ እንደሆነ ታውቋል።
“በአሁኗ ሰአት ወገኖቻችን በሞትና በሂዎት መካከል ተይዘው በርሃብ በጥምና በብርድ እየተሰቃዩ ይገኛሉ” የሚሉ አንዳንድ ወገኖች “ፋሽስት ወያኔ ለዜጎቹ የሚያስብ ቢሆን ኖሮ ዓለመቀፋዊ እገዛ በመጠየቅ አፋጣኝ ርዳታ መስጠት በተገባው ነበር፤ እያደረገው ያለው ግን የነበረውን እንኳ መዝጋት ነው” ካሉ በሗላ “ስለ እኛ የሚቆምና የሚያግዘን መንግስት የሚባል አካል እንደሌለ ራሳችንን እናሳምንና ባቅማችንና በቻልነው ሁሉ ለወገኖቻችን ራሳችን እንድረስላቸው” ይላሉ።
ከዚህ በፊት በቀደመው የፋሽስት ወያኔ የጫካ ዘመን ወቅት ባስር ሽዎች የሚቆጠር የትግራይ ወገናችን በርሃብ ሲረግፍ፤ ፋሸስት ወያኔ በርሃብ እያለቀ በነበረው ወገናችን ስም ከዓለም ዙሪያ የተቀበለውን የትየለሌ ርዳታ ከችግረኛው አፍ እየነጠቀ ለግል ጥቅም በአውሮፓ በሚገኙ ባንኮች ማስቀመጡን የሚያስታውሱ ሌሎች ወገኖች ደግሞ “ወያኔዎች ከራሳቸው በቀር ሌላ ዘመድ የላቸውም የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ ባሁኑ ሰአት በሳውዲ አረቢያ ጥቃት እየደረሰበት ያለውን ወገናችንን ጥቅም እስካስገኘላቸው ድረስ ብቻ ነው ወገኔ የሚሉት ካልሆነ ግን ለምንም ደንታ የላቸውም” ይላሉ።
ፋሽስት ወያኔ ለአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭና የግዳጅ መዋጮ ወቅት በሳውዲ አረቢያም ሆነ በአጎራባች ሀገሮች እየተዟዟረ ከነዚህ ዛሬ ችግር ላይ ከሚገኙ ወገኖቻችን በተደጋጋሚ ገንዘብ መሰብሰቡ ሲታወስ፤ እውነትም ፋሽስት ወያኔ ዜጋ የሚለን ገንዘብ እስካለንና እስከደጎምነው ድረስ ብቻ መሆኑን ያረጋግጣል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። ፋሽስት ወያኔ ጥቃት አድራሹን የሳውዲ መንግስት ለማውገዝ ድፍረት ማጣቱ ብቻም ሳይሆን ድርጊቱን ተቃውመው በአዲስ አበባ በሳውዲ ኢንባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ የወጡ ወገኖቻችንን በቆመት እየቀጠቀጡ ማባረራቸውና ጥቂት የማይባሉትንም ማሰራቸው በሳውዲ ለሚገኙ ወገኖቻችን መከራና ግድያ ከሳውዲ መንግስት ገር ተስማምተዋል የሚሉ ወገኖችን አበራክቷል።
 

በሳውዲ ለሚገኙ ወገኖቻችን በአፋጣኝ እንድረስ፤ በወያኔ ላይ በጋራ እንነሳ!!!

 

በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መጠን የለሽ የመብት ጥሰት ለመቃወም በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በየአገራቱ የሚገኙ የሳውዲን ኢምባሲዎችን በተቃውሞ እያጨናነቁ ነው። በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ዘግኛኝ በደል የተሰማቸውን ጥልቅ የመጠቃት ስሜት ኢትዮጵያን በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በሚያሰሟቸው መሪር የሐዘን እንጉሮችና የቁጭት ንግግሮች እየገለፁ ነው። ከሐዘንና ቁጭት ባለፈም ለበደል ለተጋለጡ ወገኖቻችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍን ለማሰባሰብ ዓለም ዓቀፍ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራውን ጀምሯል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን ዓለም ዓቀፍ ጥረት ለመደገፍ በውጭ አገራት የሚገኙ አባላቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል።
ይህ ሁሉ በውጭ አገራት እየተደረገ ያለ ጥረት ነው። ኢትዮጵያዊያን ባሉበት አገራትና ከተማዎች ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድነት መንቀሳቀሳቸው የሚያስደስት ነገር ነው። ሌላው ቀርቶ በሳዉዲ ዋና ከተማ ሪያድ ውስጥ እንኳን ኢትዮጵያውያን የሳውዲን መንግሥት ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል።
የሳውዲ መንግሥት በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ የያዘውን ጨካኝ አቋም እና በመንግሥት እውቅና በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል መቃወም ያልተቻለው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ!!! ይህ እጅግ ያማል፣ ልብን ያደማል።
ወያኔ የሳውዲ የንግድ ሸሪኮቹን ለማስደሰት የፈንሳይን ግማሽ የሚያህል ለም መሬት በነፃ መስጠቱ በቂ አልመሰለውም። በአገራቸው ኢትዮጵያዊያንን ሲጨፈጭፉ፣ ሲገሉና ሲደፍሩ በቸልታ መመልከቱ በቂ የወዳጅነት ስጦታ መስሎ አልተሰማውም። እናም ሸሪኮቹ የበለጠ እንዲደሰቱና ከእስከዛሬ በበለጠ ገንዘብ እንዲደጉሙት ለማበረታታት አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲያቸው ፊት ለፊት ኢትዮጵያንን ደበደበላቸው።
ወያኔ ከሳውዲ ጋር ያለው ግኑኝነት “የቢዝነስ ሽርክና” ነው። ቢዝነሱም ኢትዮጵያዊያንን በቁማቸው መሸጥንም ያጠቃልላል። የወያኔ ሹማምንት እና የሳውዲም ቱጃሮች በዘመናዊ ባርነት ንግድ ውስጥ አቀባይና ተቀባይ ናቸው። ለዚህም ነው እየተነገደበት ያለው ምስኪን ኢትዮጵያዊ እጣ ፈንታ በአዲስ አበባና በሪያድ አንድ ዓይነት የሆነው። እዛ ዱላ፤ እዚህም ዱላ። እዛ እስር፤ እዚህም እስር። እዚያ ስድብ፤ እዚህም ስድብ። እዚያ ቶርቸር፤ እዚህም ቶርቸር። በባርያ ንግድ ውስጥ አቀባዩም ተቀባዩም ባርያዉን መግዛታቸው፣ መስበራቸው፣ መግደላቸው የማይቀር መሆኑ የታወቀ ነው።
ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ ደግሞ የወያኔ ድኩማን ሹማምንት የሚሰጡት አስተያየት መስማት ነው። በሳውዲ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍትህ ለመጠየቅ በመላው ዓለም እና በአዲስ አበባ ደግሞ በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት ወደ ጎዳና በወጡ ኢትዮጵያዊያን የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ተብየው “የፋሺሽት መፈክር አንግቦ በተጎሳቆሉ ዜጎች ስም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መጣር ብሎም መንግሥት በዜጎቹ ግዴለሽ እንደሆነ አስመስሎ ማቅረብ” ሲል ተሳልቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተብየው ጨምሮ ሁሉም የወያኔ ሹማምንት “ሳውዲዎች በግዛታቸው ውስጥ ያሻቸውን የማድረግ “ሉዓላዊ” መብት አላቸው፤ መንግሥታችን የሳውዲ አረቢያን ሉዓላዊ መብት ያከብራል” እያሉ ይከራከራሉ። ለመሆኑ ይህንን የሚሉት ከልባቸው ነው? ፈጽሞ። ኢትዮጵያዊያንን ማሰቃየትና መግደል የቢዝነሳቸው አካል ስለሆነ ነው እንጂ የሉዓላዊነት ትርጉም ይህን ያህል ተምታቶባቸው አይደለም።
ሰብዓዊ መብቶች አገር፣ ድንበር፣ ዜግነት፣ ወይም ሌላ ማናቸው ሰው ሠራሽ ህግጋት ሊጥሷቸው እንደማይገቡ የወያኔ ሹማምንት ቢያንስ ሲነገር ሰምተው ያውቃሉ። ማንኛውም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገደል፤ ሰቆቃ (ቶርቸር) እንዲደርስበት ማድረግ፤ ጾታዊ ጥቃት እንዲደርስበት ማድረግ እንደማይቻል ሰምተው ያውቃሉ። ሰብዓዊ መብቶች ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ ሊያገኙት የሚገባ ክብር መሆኑ በተሳተፉባቸው በርካታ ዎርክ ሾፖች ሰምተዋል። ያም ሆኖ ግን በዘመናዊው ዓለም እንስሳ እንኳን ያገኘውን ክብር ኢትዮጵያዊያን ተነፍገው በሪያድ ጎዳናዎች ሲታረዱ፤ በጭካኔ ሲደበደቡና ሲገረፉ፤ ሴቶች ሲደፈሩ፤ ሕፃናት በረሀብና በእርዛት ሲቀጡ የወያኔ ባለሥልጣኖች የበዳዮች አፈቀላጤ ሆነው የሚከራከሩት በዳዮቹ ሸሪኮቻቸው ስለሆኑ ነው።
ይህ ድርጊት በወያኔ እየደረሰብን ያለው በደል ምን ያህል ሥር የሰደደ እንደሆነ እና የኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ ምንጭ የት እንዳለ አመላካች ሆኗል።
“ትግላችን የነፃነት ትግል ነው” ስንል “ከማን ነፃ ለመውጣት?” እያሉ የሚሳለቁ እንደነበሩና እንዳሉም ይታወቃል። በወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያዊያን ወደ ባርነት ማሽቆልቆላቸው ይህ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። ከወያኔ የባርነት አገዛዝ ነፃ እስካልወጣን ድረስ ሌሎች አገሮች መብቶቻችን የሚያከብሩልን በየአገራቱ ልምድ እና ከወያኔ ጋር ባላቸው ሽርክና መጠን ነው።
ለሳውዲ መንግሥትና ቱጃሮቹ ከነዳጅ ቀጥሎ የሀብታቸው ምንጭ ከየአገሩ የሚመጣላቸው የድሀ ጉልበት ነው። የሳውዲ ቱጃሮች ድሆችን ከባርነት ባልተሻለ መንገድ ረግጠው በመግዛት ኑሮዓቸውን ያደለቡ ናቸው። ለወያኔ አገዛዝ ደግሞ ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛው የገቢ ምንጩ ዜጎቹን በመሸጥ የሚሰበስበው ነው። ለወያኔ፣ ኢትዮጵያዊያን ወንዶችና ሴቶች ትርፍ አምጪ ሸቀጦች ናቸው። ወያኔና ሳውዲ – ሻጭና ገዢ ናቸው።
ባርያ ከሻጩ ነፃ ሳይወጣ ከአንድ ገዢ ነፃ ቢወጣ ሌላ ገዢ ስለሚመጣ ዘለቄታነት የለውም። እኛም ከወያኔ ነፃ ሳንወጣ ከሳውዲ ነፃ መወጣት አይቻለንም፤ ቢቻልም ነፃነታችን ዘላቂነት አይኖረውም።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሳዉዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ በሚደርሰው ጥቃት ክፉኛ ተቆጥቷል። በዚህ የመከራና ጭንቅ ሰዓት ለወገኖቻችን ለመድረስ የሚቻለውን ጥረት ሁሉ ማድረግ እንዳለብን ያምናል። አባላቱ በነብስ አድን ርብርብ በግንባር ቀደምትነት እንዲሳተፉ መመሪያ አስተላልፏል። ይህ አጣዳፊ ሆኖም ጊዜዓዊ መፍትሔ ነው። በግንቦት 7 እምነት የችግሮቻችን ሰንኮፍ ያለው አዲስ አበባ ነው። ሰንኮፉን ሳንነቅል የሚደርስብንን ውርደት በዘላቂነት መቀልበስ አንችልም። ስለሆነም በችግር ላይ የወደቁትን ወገኖቻችን እየረዳን፤ የችግሮቻችን ምንጭ በሆነው ወያኔ ላይ የተባበረ ክንዳችንን እናንሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰሜን አሜሪካ፣ ነፃነት ያለ ደም …. ክብርስ ያለ መስዋዕትነት እንዴት ሊገኝ ይችላል?

ነፃነት ያለ ደም …. ክብርስ ያለ መስዋዕትነት እንዴት ሊገኝ ይችላል?
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰሜን አሜሪካ
በሳውዲት አረቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየተካሄደ ያለውን አሰቃቂ ግድያና ሰቆቃ አጥብቆ ያወግዛል !
አድዋ ላይ የፈሰሰው ደም ፣ በማይጨው የተከሰከሰው አጥንት ፣ በመተማ ግንባር ላይ የተቀላው አንገት ፣ በዶጋሊ በደም የተፃፈው ጀግንነት …… ለግል ታሪክ ማዳመቂያ ሳይሆን እኛ ኢትዮጵያኖች በገዛ አገራችን በባርነት ቀንበር ስር እንዳንማቅቅና በነፃነት ተከብረንና ኰርተን እንድንኖር አድርጐናል ።
ዘርዓይ ደረስ ለአገሩ ባንዲራ የከፈለው መስዋዕትነት …. አብዲሳ አጋ ያስመዘገበው ወደር ያልተገኘለት ጀግንነት …. አብረሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በየካቲት አስራ ሁለት ጀነራል ግራዚያኒ ላይ የቃጡት ጥቃት ፣ አቡነ ጴጥሮስ ለህዝባቸውና ለአገራቸው ክብር ሲሉ ነፍሳቸውን መስጠታቸው እኛ ልጆቻቸው ፣ የልጅ ልጆቻቸው ባለ አገርና ያልተገደበ ነፃነት እንዲኖረን ነበር ።
የኦጋዴንን ድንበር ሰብሮ በመግባት …… ልጆቻችንን ፣ ሚስቶቻችንና እናቶቻችንን እፊታችን ስር ሊደፍርና ሊያዋርድ የመጣውን እብሪተኛ ጦር እውነተኛው ኢትዮጵያዊው ሰራዊት በሰማይ ፣ በባህርና በምድር ተሞ ድባቅ መምታቱ ባንዲራችንን የሰንደቆች ሁሉ አውራ አድርጓት ኖሯል ።
ታዲያ ዛሬ ያ ! ሁሉ የዜግነት ክብር እንዴት ተናደ ? ዜጐቻችን ባባህር ሲያቋርጡ የአሳ ነባሪ እራት ለምን ይሆናሉ? እህቶቻችን የፈላ ዘይትና ውሃ በአካላቸው ለምንስ ተቸለሰባቸው ? ከፎቅ ላይ እራሳቸውን እያምዘገዘጉ ለምን ጣሉ ? በጠራራ ፀሃይ በመሃል ከተማ ውስጥ የድረሱልኝ እሪታ እያሰሙ እንደ በግ መሬት ለመሬት ሲጐተቱና በመኪና መስኰት እንደወረቀት እያጣጠፉ በግድ ሲጭኗቸው በገሃዱ አለም ለምን አየን ? ሳውዲት አረቢያ ለዜጐቻችን የምድር ሲዖል ለምን ሆነች ? ወንድሞቻችን እንደ ረከሰ ውሻ ያለርህራሄ ተቀጥቅጠው ሲሞቱ በዓይናችን በብረቱ አየን ። ሰንደቅ ዓላማችንን በአናቱ ላይ ያሰረው ወንድማችን እንዲሁ ምህረትን እንደተማፀነ ነፍሱ ከስጋው ስትለይ በሰቀቀን ተመለከትን …… ገዳዮቹ ውሻው አበሻ (ኢትዮጵያዊ) ሞቷል እያሉ ሲሳለቁበት እርር ድብን እያልን ተከታተልን ።
እህቶቻችን አይናችን ፊት በጐዳና ላይ ለአምስትና ለአሥር ሆነው ሲደፍሯቸው ተጐልተን እያየን በቁጭት አነባን ።
አባችቶቻችን ያቆዩልንን አኩሪ ነፃነት መጠበቅ አቅቶን በባርነት በተሸጥንበት አገር የውሻ ስም ተሰጥቶን የውሻ ሞት ሞትን ። ከዜጐች ሁሉ መጨረሻ የተናቅንና የተዋረድን ሆንን ።
እነሆ የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰሜን አሜሪካ ይህንን በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ፍጅት አጥብቆ እያወገዘ ፤ ለዚህ ሁሉ ውርደትና ሥቃይ የዳረገንን ዘረኛ መንግስት ተጠያቂ ያደርጋል ።
የኢትዮጵያ ሰራዊት ሆይ ስማ ! አገርህ ኢትዮጵያ ናት ፣ ህዝብህ ኢትዮጵያውያን ናቸው ።
የኢትዮጵያ ሰራዊት እንጂ የዘረኞች የግል ዘበኛ አይደለህም ።
ህዝብህ ተዋርዷል ! ዜግነትህ ከእንስሳ ባነሰ በቁሻሻ ላይ ተጥሏል ። እናትህ ፣ አባትህ ፣ ወንድምህና እህትህ ከለላና መከታ አጥተው ደማቸው በየጐዳናው እየፈሰሰ ይገኛል። የህዝብህን ዋይታ ስማ !
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰሜን አሜሪካ

ለዜጎች ስደት እንዲሁም በስደት ለሚደርስባቸው ሰቆቃ ተጠያቂ ሥርዓቱን የሚመራው ወያኔ/ህውሃት ነው!!

 ዳዊት ደመላሽ
dawitdemelash@gmail.com

ቀደም ባሉት ዘመናት ወደ ውጭ ሀገር በተለያየ ምክንያት የተጓዙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን፤ የእናት ሀገራቸውን ምድር የሚረግጡበትን ቀናት ይቆጥሩና ይናፍቁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በዋናነት ወደ ውጪ ሀገር የሚሄዱት ለትምህርት ሲሆን የዚያን ዘመን ወጣት ትምህርቱን ጨርሶ በመመለስ የሀገሩን እና የሕዝቡን ውለታ ለመክፈል የነበረው ጉጉት ከፍተኛ ነበር፡፡ ተምሮ በውጪ ሀገር መቅረት ሀገርን እንደመክዳት የሚያስቆጥር በመሆኑ በኢትዮጵያውያን ህሊና ስደት ተቀባይነት አልነበረውም፡፡
ዛሬ ዛሬ ሁኔታዎች ሁሉ ተለዋውጠው የኢትዮጵያ ህዝብ እጣ ፋንታ ፍልሰትና ስደት ሆኗል፡፡ ስደት የማያባራ የኢትዮጵያውን የሕይወት ገጽታ ሆኗል፡፡ የገጠሩም የከተማውም ሰው ወደ ውጭ ሀገር ይሰደዳል፡፡ ወጣቶች ይሰደዳሉ፡፡ እህቶቻችን ይሰደዳሉ፡፡ ሕፃናት ጭምር በጉዲፈቻ ስም ይሰደዳሉ፡፡ ‹ሕጋዊ› በተባለውም ሆነ በሕገ-ወጥ መንገድ ሕዝባችን ወደ ውጭ ሀገር ይነጉዳል፡፡ በዚህ የተነሳም በወሊድ ምጣኔ ሳይሆን በሰደት ምክንያት አምራች የሆነው የህዝብ ቁጥር ሊቀንስባቸው ከሚችሉ ሀገሮች ኢትዮጵያ አንዷ ሆናለች፡፡
ለዚህ ሁሉ ማለቂያ የሌለው ስደት መንስኤው በደርግ ተጀምሮ በወያኔ/ህውሃት ተጠናክሮ የቀጠለው አምባገነናዊ አገዛዝ የፈጠረው አስከፊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ውድቀት መሆኑ አይካድም፡፡ ዜጎች በሀገራችን ከተንሠራፋው ድህነትና ሥራ አጥነት በማምለጥ ሠርቶ ለማግኘትና የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመለወጥ ስደትን ቢሹም ከኢኮኖሚያዊ ፍላጎት በስተጀርባ አምባገነናዊ የፖለቲካ ሥርዓቱ የወለዳቸው ችግሮቹ ለስደቱ መንስኤነት ዋነኛውን ሚና ይጫወታሉ፡፡
የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት አለመረጋገጥ፣ ለሕዝብ ፍላጎት ተገዢና ተጠያቂ መንግሥት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት አለመከበር፣ የፍትሕ፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት፣ በዜጎች ላይ በቀበሌ ካድሬዎች የሚደርስ አፈናና ወከባ፣ ከመሬትና ከንብረት መፈናቀል እንዲሁም የወያኔ/ህውሃት የተሳሳተ የትምህርት ፖሊሲ ውጤት ለዜጎቻችን ስደትና ወጥቶ ላለመመለስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት ከሀገር ወደ ሀገር በስፋት ይንቀሳቀሳል፡፡ ከሀገሩም ወጥቶ በተለያዩ ሀገሮች ኑሮውን መስርቶ ይኖራል፡፡ የየሀገሩ መንግሥታት በሌላ ሀገር የሚኖሩ ዜጎቻቸውን መብት ለማስከበር የሚከተሉት ፖሊሲና የሚወስዱት ዲፕሎማሲያዊ ርምጃ ዜጎቻቸውን የሚያኮራና የሚያስከብር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በተቃራኒው የኛ ሀገር መንግሥት  ተብዬው ግን በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚፈልጋቸው ለኢንቨስትመንት ለሚያውሉት ገንዘባቸው ካልሆነ በስተቀር በሰው ሀገር ለሚደርስባቸው ውርደትና አስከፊ ሰቆቃ መድህን ሲሆናቸው አይታይም፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት በሊባኖስ በአሠሪዋ ስቃይ የደረሰባትና ራሷን ያጠፋችው የዓለም ደቻሳ ሁኔታ የኢትዮጵያውያንን አንገት ያስደፋ ሲሆን መንግሥት ተብዬው ለዜጎቹ ህልውናና ክብር ደንታ ቢስ መሆኑን በገሀድ አስመስክሯል፡፡
በሌላም በኩል ዜጎቹ በሕገ-ወጥ ደላሎች አማካይነት በሁሉም የጎረቤት አገሮች በኩል ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሰደድ መጉላላትና አደጋ ሲደርስባቸው የወያኔ/ህውሃት የሕገ-ወጥ ደላሎች ቁጥር መጨመሩን በልማታዊ ጋዜጠኞቹ በሚዲያው ከሚነግረን በቀር ጉዳዬ ብሎ ችግሩን ከምንጩ ለመቅረፍ የሚወስደው እርምጃ ባለመኖሩ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ያቃተው መሆኑ በግልፅ አሳይቶናል፡፡
በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በየሀገሩ የሚደርሰው ሰቆቃ አዲስ ባይሆንም በቅርብ ግዜ ወዲህ በማዕከላዊ ታንዛኒያ በጫካ ውስጥ ተጥለው የተገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እጅግ በጣም አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከሀገራቸው ከወጡ በኋላ በማላዊ አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሉ በኮንቴይነር ተጭነው በታንዛኒያ በኩል ሲጓዙ አየር አጥተው በመታፈናቸው 43ቱ ሕይወታቸው ሲያልፍ በርካቶቹ ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ይህ ድርጊት የወያኔ/ህውሃት  መንግሥት በካድሬያዊ የአፈና አገዛዙ ከቀዬአቸው እያፈናቀለ በሰው ሀገር ለስቃይ የሚዳርጋቸው ዜጎች ስፍር ቁጥር የሌለው መሆኑን ማሳያ ነው፡፡
ወያኔ/ህውሃት ይህ አልበቃ ብሎት በሞኖፖል በሚቆጣጠረው ኢቲቪ በሟቾች ቀብር ስነሰርዓት አስታኮ በሀገሪቱ ስለአለው ልማት፣ ልማቱን ተከትሎ ስለአለው ፍሰሃና ደስታ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ዜጎችን ለስደት የሚያበቃቸውን ዋናኛ መንስዔ ለመደበቅ ሲዋትት፤በተጎጂዎችም ላይ ሲያላግጥ ማየት አሳፈሪ ክስተት ሆኖ አግኝቸዋለው፡፡
ስደት ድህነት ነው ድህነት የብልሹ ፖለቲካ ስርዓት ውጤት ነው
በሳውዲ ውስጥ ሆኜ ስቃይ፣ግፍ፣ግድያ፣ደብደባ እያየ የሚዳክረው ወገኔ ሳውዲ ዋና ከተማ ሆኜ ስንቱን ጉድ አየሁ አለ ወገኔ፡፡ ስንቱ ስደተኛ ላይ የደረሰውን እያየሁ አለቀስኩ፡፡ ኡኡኡ….ድረሱ አልኩ፡፡ኢትዮጵያን እንወዳለን የምትሉ ሰዎች ህዝቡን ሳይሆን ባዶ መሬቱን ድንጋይ አፈሩን ነው እንዴ የምትወዱት ወገን አለቀ ድረሱ…ብያለሁ፡፡ከሳውዲ የወገኖቻችን ጩኸት ነው!።
እውነት ለህዝብ ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት ካልሆነ በስተቀር ከዚህ በፊት ኧረ!…የወገን ያለህ ይህን ያህል ዜጋ አለቀ ስንል ምነው ምላሽ የሚሰጠን ጠፋ? አንድ በሉ፡፡ ይህን ያህል ዜጋ ታፍኗል፣ 14 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ሀረጥ የሚባለው ካምፕ ውስጥ ታጉረው ወደሀገር የሚመልሰን ጠፋ ሀገራችን መልሱን ብለው ሰላማዊ ሰልፍ እስኪወጡ ድረስ በርሃብ ሲቆሉ…ሲረግፉ መልስ መቼ ሰጡ? ሁለት በሉ፡፡ በስንት ሺህዎች በየጎዳናው እስኪረግፉ ቀባሪ አጥተው በየመንገዱ ወደቁ ኧረ የሰሚህ ያለህ ስንል ዝምታው ለምን ነበር?
አሁንም ይሄ ሁሉ አታሞ ድሰቃ እውነት ለስደተኛው ሊሰራ ታስቦ ከሆነ አልረፈደም፡፡ ግን ከልብ አለመለቀሱ እነሱ ውይይት ብለው በተቀመጡበት ቀን እዚህ የመን ውስጥ ስንቶች በአፋኞች መከራቸውን እየበሉ ነው? ስንቶች ተደብድበው አካላቸውን አጥተዋል? እውነት ድንበሩ ከተዘጋ በዚህ ሳምንት ብቻ ወደ የመን የተሻገረው ህዝብ ብዛት በሺህዎች መሆኑ እና የIOM (ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት) ሰራተኞች ከቁጥጥራቸው ውጭ መሆኑን ማሳወቃቸው ምን ያሳያል፡፡ ዛሬም እየተዋሸ ፖለቲካዊ ድስኮራ መሆኑን አያሳይም? ተሰብስቦ ከማውራት ወደ ተግባር መሸጋገር ነው የሚያስፈልገው፡፡
ስለቻይና እድገት ባልተያያዘ መልኩ የከተማልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ ብዙ አወሩ፡፡ ባለ ሁለት ዲጂት ተከታታይ እድገት አስመዘገበች በተባለው ኢትዮጵያ ድህነት የለም ለማለት ሞከሩ፡፡ በድህነት አይደለም የሚሰደዱት አሉንም፡፡ እግዚአብሄር ይስጣቸው አንባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሆዳቸው ብለው የአይጥ ምስክር…ያስባሉንን እውነቱን ነገሯቸው፡፡ ሁለቱን ነጣጥለን አንመልከት ድህነት አይደለም ያሰደዳቸው ማለት ስህተት ነው አሉም፡፡ የውይይት አቅጣጫውን ግንዛቤ በማነስ ስደት እንደሚወጣ ለማድረግ የሞከሩ ሰዎች በዝተው መታየታቸውና እንዲያውም በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ መሆናቸው መናገራቸው ደግሞ ድራማውን አስቂኝ ያደርገዋል፡፡ ጥናት ቢያደርጉ እውነት ይሄን ነበር የሚናገሩት? ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ቢያገላብጡ የውጭ መገናኛ ብዙሀንን ቢከታተሉ እንኳን ችግሩ ገብቷቸው ይናገሩ ነበር፡፡ ግን ባልሰሩት፣ ባላዩት ጥናት አቅራቢ ሆነው ለተከራከሩት ሰዎች አንድ እውነት አስረግጬ ልነግራቸው ወደድኩ፡፡
ግንዛቤ ማጣትም ሆነ ገንዘብ ማጣት ሁለቱም ደህነት ነው፡፡ ስደት በየትም አልነው በየትም አሽሞነሞነው ስደት ድህነት ነው፡፡ ድህነት ደግሞ የብልሹ ፖለቲካ ስርዓት ውጤት ነው፡፡ ሰላም አጥቶ መብቱ ተረግጦ የሚሰደደው ኪሱ የዳለበውም ቢሆን የሰላም ደሀ ሆኖ ነው፡፡ ሌላ ታፔላ መለጠፉም ሆነ ማሽሞንሞኑ ስደትን አያጠቁረውም አያቀላውም፡፡ ጥናት አጥንተናል ባዮችም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ነውና ይልቅ የመፍትሄ ሀሳብ አቅርቡ…ህገ-ወጥ ደላሎች ያላቸውን ተዋረድ እና ሰንሰለት መናገሩ ብቻ ምን ፋይዳ አለው፡፡ እዚህ የመን፣ሳውዲ ያለ ኤምባሲ ስንት የሚያዙትን ህገ-ወጥ ደላሎች ሲፈቱ ዝም ከማለት ውጭ ምን አደረገ? አሁን በቅርቡ ያየነው እንኳን ስልሳ ኢትዮጵያዊያንን አፍኖ የተያዘ ሰው ሲፈታ ዝም አይደል ያሉት ያውም ከነደበደባቸው 60 ልጆች ተይዞ እሱ ወጥቶ ልጆቹ ታስረው ቀርተዋል፡፡ አሁንስ ቢሆን በየመን ህገ-ወጥ አጓጓዦች ከኤምባሲው ምን ደረሰባቸው ገብተው ይወጣሉ፡፡ እጅና ጓንት ናቸው፡፡ የመንግስት ስራ ሁሉ የይምሰል ነው፡፡
ማፈሪያ የሆነው ETV ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በሚል ዶክመንተሪ የሚመስል ነገር አሳይቶናል፤በጣም የሚያሳዝን ነው።ስለ ወገንም የማያዝን ልብ የለንም።ነገርግን ይህ ስርሃት አልበኛ መንግስት ያወጣው ወገንን የመፍጀት ስትራቴጂ አንዱ አካል ይመስለኛል፤ለወገን ተቆርቋሪም ሆኖ አይደለም ይህንን ዶክመንተሪ ያሳየን።
ወገኖቻችን ለምንድነው ለዚህ አደጋ ራሳቸውን የሚያጋልጡት?
ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን እያወቁ ለምን ይህን አደጋ ይጋፈጣሉ?አማራጭ ማጣት ነው።
ህዝቡ ተስፋ እንደቆረጠ ያሳያል፤እንጂ ወያኔዎች እንዳሰቡት ምንም ትርፍ አያመጣም።
ምነው በየአረብ አገራቱ ከደረሱ በኋላ እንኳን ቆንስላ ፅ/ቤት ሄደው አቤቱታቸውን እያሰሙ ለ3ናለ4 ቀናት በየቆንስላው በር ላይ ተቀምጠው የሲሚንቶ ቅዝቃዜና ውርጭ ሲፈራረቅባቸው እያዩ አላየንም ነበር ሊሉን አስበው ይሆን?
ታዲያ አሁን አዝነናል ለማለት በምን ሞራል ነው የሚነፋረቁት?
እውነታው ግን የኛ መንግስት ሁሉ ነገር ለፓለቲካ ጥቅም እንጂ ለሀገር:ለህዝብ ተብሎ የሚሰራው ነገር የለም ማለት ነው ?
እስከ ዛሬ ድረስ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን እመኛለሁ፡፡ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እውን እስኪሆን ድረስም ትግሉን የኢትዮጵያ ህዝቡ  አጠናክሮ መቀጠል አለበት ፡፡
ከሁሉም በላይ ለዜጎች መፈናቀል፣ ፍልሰትና ስደት መንስኤ የሆኑ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮች እንዲወገዱ  የወያኔ/ህውሃት  የሕግ የበላይነትን ለማክበርና ለማስከበር እንዲሁም መልካም አስተዳደርንና ፍትሕን ለማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ በአፋጣኝ እንደማይወስድ ተረድተን እኛ መፍትዬ ልናበጅ ይገባል።
በመጨረሻም ሕዝባችን  ለዜጎች ሰብአዊና ደሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ትኩረት ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስና የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነትን እንዲያረጋግጥ አስፈላጊውን ጫና እንዲያደርግ ጥሪዬን አሰተላልፋለው፡፡

የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የምንል መልካም አጋጣሚው አሁን ነው !!!


ገረመው አራጋው ክፍሌ/ኖርዌይ
ኢትዮጵያዊነት በአደባባይ የወደቀው በአረብ አደባባይ አይደለም፤ በአረብ አደባባይስ ኢትዮጵያዊነትን ለመግደል፥ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ለዘመናት ተጎንጉኖ፥ ተቋጥሮ ተፈቶ አልተሳካም ነበር። የአልጄሪያው ደባ፥ የሊቢያው ስጦታ፥ የሳውዲው ስለት፥ የደማስቆው ፖለቲካ ምንም አላመጣም ነበር። ኢትዮጵያውያዊነት የወደቀው በራሷ በኢትዮጵያ አደባባዮች ላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት ክብር ሳይሆን መርገም እንደሆነ የተነገረው በራሷ አደባባይ ነው። በሰሞኑ ያየነውም በአረብ ሀገራት የወያኔን አንባገነን ስርዓት ሸሽተው የተሰደዱ ዜጎች በሳዉዲ ወሮበላ ፖሊሶች እንደ በግ ታርደዋል ሴቶቻችን የወሲብ ትቃት ሰለባ ሆነዋል በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በስውር ሳይሆን በአደባባይ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው።
በስልጣኔ ለመገስገስ ያልታደልክ የሳአኡዲ ሕዝብ በተፈጥሮ በታደልከው የቤንዚን ሃብት በእርካት ከመኖር አልፈሕ ከየሃገሩ በኑሮ የተቸገሩ ቤተሰቡን ለመርዳት ሲል ለናንተ የማይገባችሁ ግልጋልሎት በመስጠት ያቀማጠላችሁ አገልጋይ ዛሬ ከልክ አልፎባችሁ ሕግና ስራአትን ባልተላበሰ ሰብአዊ ነት በጎደለው የድንጋይ ዘመን ስራዓት ስልጣኔ ለማመዛዘን ያልቻልክ በስሜት የምትጓዝ ብር ያሳበደህ እውቀት ያነሰህ ሕዝብ፡
በወሲብ በግድያ አሳሩን እያሳያችሁ ያገኘውን የድካሙ ዋጋ እየቀማችሁ ለአይምሮ በሽታ የዳረጋችሁት ህዝብ አያንስ ብሎ በሰሞኑ የሃገሬን ሕዝብ ጭካኔ በተመላበት ስርአተአልባ ያልሰለጠነ ወጣት ሕዝባችሁን በማቀናጀት ይፈጸማችሁት አሰቃቂ በደል፡ አለም አቀፍ ሕግጋትን በመጣስ በሰባዊ ፍጡሮች ላይ የፈጸማችሁት አረሜናዊ ተግባር፡ በማን አለብኝ የተደረገው ሁሉ በዓለም ፊት ይህን አስነዋሪ ተግባራችሁን በማጋለጥ የሳአኡዲ መንግስት በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ባደረሳችሁት የጅምላ ቅሌት እንፋረዳችሁለን ።
ይህም ዓለም አቀፍ ፍርድቤት በትክክል ላደረጋችሁት በደልና ሶቆቃ በሕግ የተደነገገ ውሳኔ ቢሰጥም በሃገራችንና በሕዝባችን ያለው የቆየ ግኑኝነት የሻከረና በፍጽም ሊያቀራርበን እንድማይችል ተመሳሳይ እርምጃ በአጸፋ ለመመለስ ወደኋላ አንልም፡ ምክንያቱም የንጹህ ሕዝባችን ሴት እሕቶቻችን ከባሎቻቸው ፊት ያደረጋችሁት አስነዋሪ ወሲብ በናንተም ቤተሰቦች በየትኛውም ዓለም ተመሳሳይ እንድሚሆን በተገኛችሁብት ደማችሁ ደመከልብ እንድሆነ ይህንንም ስናደርግ ያላችሁ ማንኛውም አይነት ተቋማት አገልግሎታቸው በሙሉ ማሰናከል፡
ከኢትዮጵያ የሚላክላችሁ ማንኛውም የምግብ አትክልት ፍራፍሬ ሥጋና ጥራጥሬ ወሃም ጭምር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለማግኘት እንደማትችሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በትብብር እርምጃ እንዲወስድ እናደርጋለን፡፡
ለዚህ አይነት እርምጃ ለመውሰድ ያስገደዱን ምክንያቶች ሀገራችንን የሚጠብቅ ሕዝባዊ መንግስት ስለሌለን ሀገርንና ሕዝብን መከላከልና ማዳን የዜጎች ኃላፊነት በመሆኑ ይህን ውሳኔ በግልና በማህበር ለመወሰን ያስገድዶናል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ዝርዝሮች በሳአኡዲ የተፈጸሙት የወገኖቻችን ስቃይና መከራ አስግድዶ መድፈር ግድያ እስራት ግንኙነት ያለውና በተግባር እንዲውል ያደረጉት የወያኔ አሸባሪዎችና አላሙዲ ሚስጥር እንዳለበት ህዝባችን እንዲያውቅ ያስፈልጋል፡፡
1ኛ. የወያኔ ሀገርን ለመሸጥ ከጅምሩ የተነሳበት አላማው ለማሳካት ወንጀለኛ መንግስት በመተባበር የዜጎችን መሬት በመቀማት በአላሙዲ አስተባባሪነት ለሳኡዲ በመሸጡ፡ የወያኔ አሸባሪ ስርዓት ተባባሪም ለመሆኑ፡፡
2ኛ . አላሙዲ የሚባል ግለሰብ ከሳአኡዲ መስፍንት ጋር ባለው ግንኙነት ሀገራችንን ከወያኔ ጋር በመመሳጠር ቦንድ አልገዛ ያለውን ዜጋ አሳልፎ ለዝህ አስከፊ ጥቃት እንዲደርስበት ያደረገው ታላቅ ሴራ (Saudi star) የሳአኡዲ ኮከብ የሚባለው የዘራፊ ቡድንም ከጋምቤላ ግዛት ባስቸኳይ ለቆ እስካልወጣ በንብረቱና በሰዎቹ የከፋ እርምጃ መውሰድ:
3ኛ. የሃገሪቱን ግማሽ ሃብት በማግበስበስ በተለያየ የንግድ መስክና ማእድናችንን በመበዝበዝ ለርሱ ባደሩ የወያኔና በጎጠኝነት ያሰባሰባቸው ጋር በመሆን ባደረገው የኑሮና የሰፈራ ጉስቁልና
4ኛ. በኑሮ ተመጣጣኝ የሌለው ክፍያ በጋምቤላ ተወላጆች የሚደረገውን አዲስ የባርነት (modern slavery) ድርጊት በፍጹም በሃገራችን ይሁን በሌላው ዓለም የማይታሰብ ተግባር በማካሄድ ላደረሰው በደል
ይህ ድርጀት ተጠያቂ የሚያደርገው ወንጀሎች በማከሄዱ መሬቱን ከተረከበው ጊዜ አንስቶ ያፈናቀላቸውን ዜጎችን ለረጅም ጊዜ በሰፈራ ያሳለፉት ስቃይና መከራ ሙሉ ካሳቸውንና ያለቅድመሁነት ከፍሎ መሬታቸውን አስረክቦ በአስቸኳይ እንዲወጣ፡፡
በሳአኡዲ መንግስት ተባባሪዎቹ በሃገራችን ያላቸው ተቋማት በሙሉ ምንም አይነት ዋስትና እንደሌለውና በወያኔም በኩል የሚደረግ ሁሉ ሕጋዊ ተቀባይነት የሌለው እኛ ኢትዮጵያዊያን ስለምናምን ባስቸኳይ ከግዛታችን መልቀቅ እንዳለባችሁ አልያ ለሚደርሰው ጥፋት ኃላፊነቱን ተጠያቂ አላሙዲና የወያኔ አሸባሪ ቡድን መሆናቸው እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሆይ ከንግዲህ ወዲያ ተሸክመሕና ታፍነህ የምትኖርበት ጊዜ አብቅቷል እንደቀድሞ አባቶችህና አያቶችህ እምቢ ላገሬ ውርደቱ ይብቃኝ ብለህ የምትነሳበት ወቅቱ አሁን ነው ጥይት እስከሚተኮስ አትጠብቅ የወያኔን ጋሻ ጃግሬን አንገት ላንገት በመተናነቅ አንተው ከመሃል ተፋለመው ጦርነት በአዋጅ ለውጭ ጠላት እንጂ ይህን አረመኔ አሸባሪ ሆድ የገዛው ስብስብ በአንድነት መብትህንና ሀገርክን ለማዳን አንተው ተነስ የፍራቻ ብልኮን ከላይህ አንሳ አንተም ካያቶችህ የወረስከው ነፍጥ አሳያቸው ኩርምት ብለህ በስቃይ ከምትኖር ልጆችህን ጀግንነትና ትባትን አንድነትን አላብሰህ እለፍ፡፡
አዲሱ ትውልድ ወጣቱ ሆይ ስደት ይብቃህ ለለውጥ ተነስ ወይ በተገቢው ለመኖር አለያም ለክብር ሞት ራስህን አዘጋጅ የአህዛብ መቀለጃ የደደቦች መጫዎቻ የመሆን ታሪክህን አድስ፤ ሃገርህ እንኳን ላንተ ለነዚህ ደንቆሮ ጀማላዎች የተረፈ ወርቅ ተፈጥሮ አላት፤ ከበረታህ አንተ ሳትሆን እነሱ ወዳንተ ይመጣሉ። ትላንትም በአባቶችህ ዘመን ክፉ ቀን በክብር ያሳለፉት ባንተ ሃገር ነበር፤ እንዲህ ሊያወርዱህ እድል ያገኙት ሃገርህን የወረረው የትግሬ ነፃ አውጪ ሌባ ቀማኛና ሰዶማዊ አገዛዝ ታፍሮና ተከብሮ የኖረ ሃገራዊና ታሪካዊ ክብርህን በዓለም ፊት ያቀለለ በመሆኑ ክንድህን ማንሳት ያለብህ በዚህ ሃገር በቀል የአረቦች የጭን ገረድ በሆነ የወያኔ አገዛዝ ላይ ነው ። ስለዚህም በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ በሰላም ይሁን በአመጽ በጓንዴ ይሁን በጎራዴ በቀለም ይሁን በፍራፍሬ አብዮት ስደት በቃኝ ብለህ አገርህን ሳትለቅ ለውርደትና ለስቃይ አሳልፎ የሠጠህን መሪር ጠላትህ የሆነውን የወያኔ ቡድን አፈርድሜ ለማስጋጥ ተነስ፤ ታጠቅ፤ ዝመት፤ የውርደት ማርከሻ መድሃኒቱ እንደአባቶችህ እንቢኝ በማለት ባንዳና ቅጥረኛውን ማስወገድ ብቻ ነው። ድርጅት ሳይሆን የጎበዝ አለቃ መርጠህ ግፋበት ቀድሞ አያቶቻችን ሀገር ድንበር ተነካ ሲባል ልጄን ንብረቴን ሚስቴን ሳይሉ ለዳር ደንበራቸው ክቡር ሕይወታቸውንና አከላቸውን በማበርከት ተከብረንና ታፍረን የኖርን በዓለም የጦር ሜዳ በኮርያ በኮንጎ ያሳየነው ጀቡድነት ዘላለማዊ ታሪክ ሆኖ ሲታወስ ይኖራል፡፡ ታድያ ምን ነክቶን ነው አንጀት ያጣነው ምነው ቀብቶአችን ላላ ወኔው ዶላር በላው ሞት እንደሆን የማይቀር ጽዋ ነው ተዋርዶ መሞት ሁለት ሞት ነው እስቲ ራስህን መርምር በንቅፋት ሞት በትንታ ሞት በመኪና አደጋ ሞት ታሞ ባልጋ ሞት ለማይቀር ታሪክ ሰርቶ በክብር ማለፍ ያስፈልጋል እንዲሁም ምን ብለው ነበር ቀደምት አባቶቻችን ጠላትማ ምን ዜም ጠላት ነው አስቀድሞ መግደል አሾክሻኪውን ነው የውያኔ (ካድሬዎች) ሎሌዎችን መጀመርያ ኢላማ አድርግ ሁሉም ሆድ የገዛው ስለሆነ ቆርጠን ከተነሳን ጽናትና ወኔ የለውም አኛ ስናብር ሰንሰላታቸው ላልቷል ይበጠሳል ምንዜም ሕዝብ አሸናፊ ነው።
ኢትዮጲያና ኢትዬጲያዊነት ለዘላለም ይኖራል። ወያኔ ግን በተባበረ የኢትዮጲያዊያን ጠንካራ ክንድ ይወገዳል!!
g.araghaw@gmail.com

The people who lost there identity…


Author of "the people who lost there identity..."
Bora Pawlos
The question of why so many Ethiopians are forced to flee their own country in the first place. Why are millions of Ethiopians suffering around the world as helpless refugees, undocumented aliens, and, in many cases, beggars? What relegated Ethiopians to live a life of second-class, even third class citizens around the world is nothing but the repression, discrimination, and brutality they face in their own country in the hands of an ethnocratic regime well -equipped with the tools and arsenals of repression.
Millions are forced each day to choose between a wretched existence at home and uncertain search for hope in a strange land. Fed to the brutal whips of the unscrupulous and racist slave drivers in Saudi Arabia by their own government, Ethiopians cannot look for their leaders at home to come to their aid. To those unwitting sympathizers of the criminal regime in Ethiopia, the continuing suffering of helpless Ethiopians at the hands of racist Arabs should come as a wake up call. We should not only blame the perpetrators of the crime; we must also hold accountable those who made life unbearable at home for millions of Ethiopians.
Ethiopians cannot look for their leaders at home to come to their aid.
A government that demonstrates no concern for the suffering of its people that it systematically drives to a life of exile, servitude and inhuman treatment should be held accountable, condemned, and ultimately removed. Today the blood of innocent Ethiopians colors Arab streets. Let there be no doubt that their blood will not be spilled in vain. This tragedy should serve as a cause for action and for redemption. It is a call for action for those of us in the Diaspora and back home, who have served as apologists for the criminal regime, trading the time-honored Ethiopian pride and patriotism for petty material gains.
Today, Ethiopia is a country that is ruled by corrupt despots who have utter disregard for basic human rights. They are thugs that have no allegiance to the flag and depraved souls without eye of national and patriotic ethos. The sacred and time honored ethos that were protected by the blood and sweat of generations of Ethiopian compatriots are being replaced by the callous deeds of morally debauched thugs who have condemned millions to a life of abject poverty, ignorance, disease and abysmal sense of hopelessness.
For those who have paid attention to the reality in Ethiopia, it is abundantly clear that the dehumanization and humiliation of our brothers and sisters in Saudi Arabia did not begin on Saudi streets. Many found themselves facing the brutality of the Saudi police after being forced to leave their country because of a similar form of brutality at home. The fact is that most young Ethiopians, besides facing high rate of unemployment, are subject to some of the most serious rights abuses, including extrajudicial killings, incommunicado-detention, arbitrary arrest, torture, and inhumane prison conditions in Ethiopia.
Ethiopians must unite against the unscrupulous and decadent ethnocentric dictatorship that has condemned its citizens to a life of misery, dehumanization, repression both at home and in exile. We must hold those in power responsible for the tragic predicaments of our fellow citizens in Arab lands. The ultimate remedy, therefore, is for all Ethiopians to unite in common cause to bring about freedom, democracy, hope and all the requisite social and economic conditions to lead a free and dignified life in our homeland.

ኦቶ ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ


ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ

Obang Metho Solidarity Movement for New Ethiopia
በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡
ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
“አልዘገዩም” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “አኢጋን ችግር በተከሰተ ቁጥር የሚቋቋምና የሚፈርስ የዕቁብ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ወይም እሣት ሲነሳ ድምጽ እያሰማ እንደሚከንፍ የእሣት አደጋ መኪና የሚመሰል ድርጅት አይደለም” በማለት የጋራ ንቅናቄውን የተጠና አካሄድ በመጠቆም የመለሱት አቶ ኦባንግ ይህ ችግር እንደሚከሰት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
ችግሩ አስቀድሞ እንደሚከሰት ቢታወቅም ምላሽ የሚሰጥ ብቃት ያለው አካል ባለመኖሩ አንገት የሚያስደፋና ኃፍረት የሚላብስ፤ “አገር አለኝ ወይ?” የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ኃፍረት ሊደርስብን ችሏል፡፡ “ይሁን እንጂ” አሉ ኦባንግ “ይህ መራር ዜና ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የጋራ ንቅናቄው የበኩሉን” ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡
“ከተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ አግባብ ካላቸው መንግሥታዊ አካላትና በተለያየ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረናል” በማለት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ ለዓብነት ያህልም የሳዑዲ ም/ጠ/ሚ/ር እና የመከላከያ ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፍትሕ ሚ/ር እና ሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የመንግሥት መ/ቤቶችን ጨምሮ በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን የሳዑዲ ኤምባሲዎችን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርን፣ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ACHPR)፣ ወዘተ ማነጋገራቸውንና በየደረጃውም ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡
በመላው የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዕረፍት የሚሰጥ እንዳልሆነ የጠቆሙት “ጥቁሩ ሰው” ሳዑዲ ካላትና ከምትከተለው “የበርህን ዝጋ ፖሊሲ” አንጻር በአካል በቦታው ላይ ከመገኘት ይልቅ አቅም ካላቸው ዓለምአቀፋዊ አካላት ጋር በአፋጣኝና በቅርበት መሥራቱ ድርጅታቸው የወሰደው አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሎጂስቲክሱ ጉዳይ መስመር ሲይዝም የጋራ ንቅናቄው ከዚህ በፊት በየአገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ሲያስፈጽምበት የነበረውንና በውጤታማነቱ የሚታወቀውን አማራጭ እንደሚተገብር ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኢህአዴግ አገርን እንደሚያስተዳድር ድርጅት በዜጎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን አስነዋሪ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ አለመመከቱ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ወገኖቻችንን ድንበር በማሻገርና ኤጀንሲ ከፍተው ወደ አረብ አገራት ሲልኩ የነበሩት ሁሉ ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የተለያዩ ተግባራት” እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሼክ መሐመድ አላሙዲ የሠራተኛ ኃይል ወደ ሳዑዲ እንዲላክ ከኢህአዴግ ጋር በይፋ ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ከሚፈልጉበት ክልል መሬት ለመውሰድ፣ ከሚፈልጉበት ባንክ ኮሪደር ገንዘብ ለመበደር ገደብ የሌላቸውና በሞቀበት ሁሉ ባለመጥፋት በጀት መድበው በሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች እንዲሁም አንደበታቸውን በሙስና ላሰሯቸው ባለሥልጣናት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያሉ በተገኙበት ቦታ ሁሉ ለሚዲያ ፍጆታ የሚደሰኩሩትና ግጥም የሚያስደረድሩት ሼክ መሐመድ አላሙዲ፣ “ወገኔ” የሚሉት ሕዝብ በአባታቸው አገር ወሮበሎች ሲያልቅና ሲጨፈጨፍ ዝም ማለታቸው ኢንቨስትመንቶቻቸውን ጥያቄ ውስጥ ከትቷል፡፡
አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ አሰቃቂ ድርጊት መስመር ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት የሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ከርስ እንዲሞላ በኢትዮጵያ የተቋቋመው ሳዑዲ ስታር ኩባንያ በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ እንደሚችል መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ ስታር በኪሣራ ወደ መዘጋት መድረሱ የኩባንያው “ባለቤት የሆኑትን ሼክ ሙሐመድ አል አሙዲንና የሳዑዲ ዓረቢያን ስም የሚያጎድፍ ከመሆኑም ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪታክት የተወራለት ይህ ፕሮጀክት መና መቅረቱ ሁለቱን አካላት በሕዝቡ ዘንድ ለከፍተኛ ትችትና ወቀሳ እንደሚያጋልጣቸውም” ጠቁሞ ነበር፡፡
በአሁኑ ጊዜ “ሕገወጥ ናችሁ” በሚል ሰብዓዊነት የጎደው እርምጃ እየተወሰደባቸው ያለው የበርካታ አገራት ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር ሕገወጦችን የማባረር “ዘመቻ” በማለት ያቃለሉት የሳዑዲው አገር ውስጥ ሚ/ር ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ ወንጀለኛ ሬንጀር ለባሾችን፣ ፖሊሶችንና ወሮበሎቹን ሸባቦች አደፋፍረዋል፡፡ “ዘመቻው ይቀጥላል … በተወሰነ ጊዜ የተገደበ አይደለም” በማለት “እስክንጨርስ እንጨርሳችኋለን” የሚመስል የማፊያ መሪ መሰል መልዕክት ለአንጋቾቻቸው አስተላልፈዋል፡፡
አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊነት የሚኖሩትም ጭምር በሳዑዲ ያለው ሁኔታ አሳሳቢነት ወደፊት ችግር ውስጥ ሊከትታቸው እንደሚችል በመገመት ወደ አገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ሰቆቃ የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን “ቤት አለን ቤታችን መልሱ” እያሉ የሰቆቃና የድረሱልን ጥሪ በሚያስተላልፉበት ወቅት ሰብዓዊነት የጎደላቸው የኢህአዴግ መሪዎች ይህ ነው የሚባል አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸው “በእርግጥ ኢትዮጵያውያን አገር አላቸው?” ብሎ የሚያስጠይቅ እንደሆነ በርካታዎች የሚጋሩት ነው፡፡
አቶ ኦባንግ በበኩላቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንድ ሳምንት ሥራውን አቋርጦ እንኳን ቢሆን ስደተኞቹን ባፋጣኝ የማመላለስ ተግባር መፈጸም ይገባው ነበር በማለት ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ህይወታቸው እየተቀጠፈ “3ሺህ ዛሬ ገቡ … ድምሩ 10ሺህ ሆኗል …” የሚል የሞላ ጎደለ ቁማር ዓይነት ጨዋታ በትዊተር መጫወት የቴድሮስ አድሃኖምን ዘመነኛነት ሳይሆን ለሰውልጅ ህይወት ያላቸውን ደንታቢስነት የሚያሳይ መሆኑን ሁኔታው ያስቆጣቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ኦባንግም “ቤቴ መልሱኝ” ብሎ ለሚለምን አንድ ዜጋ የተከፈለው ተከፍሎ ትራንፖርት በማቅረብ ክቡር ህይወትን በአስቸኳይ ለመታደግ አለመቻል ለትውልድ የሚተላለፍ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡

Ethiopian Migrants Victimized in Saudi Arabia (GRAHAM PEEBLES)


by GRAHAM PEEBLES
Counter Punch

In the last 10 days persecution of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia has escalated. Men and women are forced from their homes by mobs of civilians and dragged through the streets of Riyadh and Jeddah. Distressing videos of Ethiopian men being mercilessly beaten, kicked and punched have circulated the Internet and triggered worldwide protests by members of the Ethiopian diaspora as well as outraged civilians in Ethiopia. Women report being raped, many repeatedly, by vigilantes and Saudi police. Ethiopian Satellite Television (ESAT), has received reports of fifty deaths and states that thousands living with or without visas have been detained awaiting repatriation. Imprisoned, many relay experiences of torture and violent beatings.
Ethiopian immigrants kept in a concentration camp in Saudi Arabia, they do not get enough food and drink
Earlier this year the Saudi authorities announced plans to purge the kingdom of illegal migrants. In July, King Abdullah extended the deadline for them to “regularize their residency and employment status [from 3 rd July] to November 4th. Obtain the correct visa documentation, or risk arrest, imprisonment and/or repatriation. On 6th November, Inter Press Service (IPS) reports, Saudi police, “rounded up more than 4,000 illegal foreign workers at the start of a nationwide crackdown,“ undertaken in an attempt (the authorities say), to reduce the 12% unemployment rate “creating more jobs for locals”.
Leading up to the “crackdown” many visa-less migrants left the country: nearly a million Bangladeshis, Indians, Filipinos, Nepalis, Pakistanis and Yemenis are estimated to have left the country in the past three months. More than 30,000 Yemenis have reportedly crossed to their home country in the past two weeks,” and around 23,000 Ethiopian men and women have “surrendered to Saudi authorities” [BBC].
The police and civilian vigilante gangs are victimizing Ethiopian migrants, residing with and without visas; the “crackdown” has provided the police and certain sectors of the civilian population with an excuse to attack Ethiopians. Press TV reports that “Saudi police killed three Ethiopian migrant workers in the impoverished neighborhood of Manfuhah in the capital, Riyadh, where thousands of African workers, mostly Ethiopians, were waiting for buses to take them to deportation centers.” Hundreds have been arrested and report being tortured: “we are kept in a concentration camp, we do not get enough food and drink, when we defend our sisters from being raped, they beat and kill us,” a migrant named Kedir, told ESAT TV. Women seeking refuge within the Ethiopian consulate tell of being abducted from the building by Saudi men and raped. ESAT, reports that several thousand migrants have been transported by trucks to unknown destinations outside the cities.
Whilst the repatriation of illegal migrants is lawful, the Saudi authorities do not have the right to act violently; beating, torturing and raping vulnerable, frightened people: people, who wish simply to work in order to support their families. The abuse that has overflowed from the homes where domestic workers are employed onto the streets of the capital reflects the wide-ranging abuse suffered by migrant workers of all nationalities in Saudi Arabia and throughout the Gulf States.
Trail of Abuse
This explosion of state sponsored violence against Ethiopians highlights the plight of thousands of migrant workers in Saudi Arabia. They tell of physical, sexual and psychological abuse at the hands of employers, agents and family members. The draconian Kafala sponsorship system, (which grants ownership of migrants to their sponsor), together with poor or non-existent labour laws, endemic racism and gender prejudice, creates an environment in which extreme mistreatment has become commonplace in the oil-rich kingdom.
There are over nine million migrant workers in Saudi Arabia, that’s 30% of the population. They come from poor backgrounds in Sri Lanka, the Philippines, Indonesia and Ethiopia and make up “more than half the work force. The country would grind to an embarrassing stand still without their daily toil. “Many suffer multiple abuses and labor exploitation [including withholding of wages, excessive working hours and confinement], sometimes amounting to slavery-like conditions”, Human Rights Watch (HRW) states.
The level of abuse of domestic workers is hard to judge: their isolation combined with total control exerted by employers, together with government indifference, means the vast majority of cases go unreported. Until August this year there was no law covering domestic abuse. Legislation has been passed: however, the authorities, HRW reports “are yet to make clear which agencies will police the new law…without effective mechanisms to punish domestic abuse, this law is merely ink on paper.” All pressure needs to be exerted on the rulers of Saudi Arabia to ensure the law is implemented and enforced so victims of domestic violence feel it is safe to come forward.
Ethiopian Governments Negligence
Whilst thousands of its nationals are detained, beaten, killed and raped, the Ethiopian government hangs its negligent head in silence in Addis Ababa, does not act to protect or swiftly repatriate their nationals, and criminalises those protesting in Addis Ababa against the Saudi actions.
Although freedom to protest is enshrined within the Ethiopian constitution (a liberal minded, largely ignored document written by the incumbent party), dissent and public demonstrations, if not publicly outlawed, are actively discouraged by the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) regime. In response to the brutal treatment meted out by the Saudi police and gangs of vigilantes in Riyadh and Jeddah, outraged civilians in Addis Ababa staged a protest outside the Saudi Embassy, only to be confronted by their own police force, wielding batons and beating demonstrators. Al Jazeera reports that police “arrested dozens of people outside the Saudi embassy [in Addis Ababa] in a crackdown on demonstrators protesting against targeted attacks on Ethiopians in Saudi Arabia.” A senior member of The Blue Party, Getaneh Balcha was one of over 100 people arrested for peacefully protesting.
The government’s justification, rolled out to defend yet another suppressive response to a democratic display, was to assert that the protest “was an illegal demonstration, they had not got a permit from the appropriate office”: petty bureaucratic nonsense, hiding the undemocratic truth that the government does not want public protests of any kind on the streets of its cities: effectively, freedom of assembly is banned in Ethiopia. The protestors, he said, “were fomenting anti-Arab sentiments here among Ethiopians.” Given the brutal treatment of Ethiopians in Saudi Arabia, anger and anti-Saudi sentiment (not anti Arab) is, one would imagine understandable, and should be shared by the Ethiopian government.
The people of Ethiopia are living under a duplicitous highly repressive regime. The EPRDF consistently demonstrates it’s total indifference to the needs and human rights of the people. Freedom of expression, political dissent and public assembly is denied by a regime that is committing a plethora f human rights violations in various parts of the country, atrocities constituting in certain regions crimes against humanity. In fact, according to Genocide Watch, the Ethiopian government is committing genocide in the Somali region, as well as on the “Anuak, Oromo and Omo” ethnic groups (or tribes).Freedom of expression, political dissent and public assembly is denied by a regime that is committing a plethora f human rights violations in various parts of the country, atrocities constituting in certain regions crimes against humanity.
The recent appalling events in Saudi Arabia have brought thousands of impassioned Ethiopians living inside the country and overseas onto the streets. This powerful worldwide action presents a tremendous opportunity for the people to unite, to demand their rights through peaceful demonstrations and to call with one voice for change within their beloved country. The time to act is now, as a wise man has rightly said, “nothing happens by itself, man must act and implement his will”.
Graham Peebles is director of the Create Trust. He can be reached at: graham@thecreatetrust.org