Friday, March 28, 2014

መከላኪያ የህዝብ ወይስ የህወሓት?

መከላኪያ የህዝብ ወይስ የህወሓት?

ህወሓት ደርግን ማሸነፍ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብን ማሸነፍ ማለት ነው ብሎ ስለሚያስብ ተግባሩ ሁሉ የንቀት፣ የማንቋሸሽና የማዋራድ ስራ እየፈፀመ ይገኛል። ሌላውን ትተን ጥቂት የሻዕቢያ ተላላኪ የሆኑትን የህወሓት መሪዎች የግንጠላ አጀንዳቸውን ይዘው በረሃ የሸፈቱበት ቀን ልክ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የትግራይ ህዝብ “ደደቢት ሂዳችሁ ታገሉሉኝ” ብሎ ወክሎ የላካቸው ይመስል “እኛ ታግለን ነፃ ስላወጣንህ እንደፈለግን እናደርጋሃለን” በማለት ዓይን አዉጣ በሆነ መንገድ ሰሞኑን “የካቲት 11 የትግራይ ህዝብ ዳግም ልደት ነው” እየተባለ በመከላኪያ ሰራዊት ታጅቦ በመከበር ላይ ስለሚገኘው የህወሓት አስቂኝ፣ አስገራሚና አሳዛኝ ድራማ የሚከተሉትን ጥቂት ነጥቦችን በአጭሩ እንመልከት።
ethio military
የህወሓት ድራማ ቁጥር 1.
የህወሓት መሪዎች እናስተዳድራለን የሚሉት 90 ሚሊዮን የኢ/ያ ህዝብ ነው እየገዙ ያሉት። ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ጨምሮ ካድሬዎቻቸው፣ አባላቶቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በቀጥታም ሆነ በስውር እየጋጡ ያሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ነው። የገጠሩን ትተን በሀሪትዋ ዋና ዋና ከተሞች ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ 90 ከመቶ የትግራይ ባለሀብቶች የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸውን የሚያካሂዱትና ባለቤት የሆኑት በሌሎች ክልሎች ነው። በአጠቃላይ የሀገሪትዋ ሀብት በተለያየ መልኩ የተቆጣጠሩት የህወሓት መሪዎች፣ ካድሬዎችና አጃቢዎቻቸው ናቸው። በመሆኑም በመሬት ላይ ያለው ህዝቡ የሚያውቀው ሐቅ ይህ ሆኖ ሳለ እነሱ የሚሉን ግን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነን” ነው። ልብ በሉ!! ስልጣን ላይ ያሉት እነሱ። ሀገሪቱን የተቆጣጠሩት እነሱ። ሀገሪትዋን እየዘረፉ ያሉት እነሱ። ነገር ግን ነፃ እናወጣለን የሚሉት ህዝብ አንድ ክልል ነው። ታዲያ!! ቆም ብሎ ላሰበውና ላስተዋለው ሰው ይህ መንግስት ከኛ አብራክ የወጣ ኢትዮጵያዊ መንግስት ነው ለማለት ያስችላልን?።
የህወሓት ድራማ ቁጥር 2.
የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን ከነ ባንዴራዋ ከፈጠሩት የታሪክ አስኳል አንዱ መሆኑን ዋቢ የሚያስፈልገው አይደለም። ቢያንስ አንድ ሶስተኛው የትግራይ ህዝብ በመላ ሀገሪቱ ከሌላው ወገኑ ጋር ተሳስሮ፣ ሀብት አፍርቶ፣ ተጋብቶና ተሰባጥሮ በነፃነት ይኖራል። በኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጅ የሌለበት መንደር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሲኖርም እንደ መጤ ወይም እንደ ስደተኛ አይደለም ራሱም ሆነ ሌላው ሰው የሚያስበው “ሀገሬ!! መብቴ!! ነው” በማለት በልበ ሙሉነትና በመተማመን ይኖራል። በሌላ አነጋገር ህዝቡ ለዘመናት በጋራ የኖሮው በመልካም ጉርብትና ብቻ ሳይሆን በራሱ ፈቃደኝነት በፍቅር፣ በወንድማማችነት፣ በመከባበርና በመተማመን ላይ የተመሰረተ ባንድ እናት ሀገር ጥላ ስር ተቃቅፎ ባህሪያዊ ዝምድናን በመመስረት ነው። ዛሬ 90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ እሴት አለን የምንለውም ይኸው ነው።
ታዲያ!! ይህ ከሆነ ሐቁ የትግራይ ህዝብ ነፃ የሚወጣው ከማን ነው? ነፃ የሚያወጣውስ ማን ነው? እውነት ለራሱ ነፃ ያልወጣና የሻዕቢያ ሎሌ የሆነውን ዘራፊና ከሃዲ ድርጅት የትግራይ ነፃ አውጪ ነኝ ማለቱ ለታላቁ ህዝብ ውርደትና ሀፍረት አይሆንም ወይ? ለመሆኑ ባድመን ጨምሮ የትግራይን መሬትና ህዝብ የተደፈረው በሀይለ ስላሴ ግዜ ነውን? በሀይለ ስላሴ ስርዓት በትግራይ ምድር ሰው እንደ አራዊት በአደባባይ ተደብድቦስ ያውቃልን? ሀገርን እያፈረሱ ነፃ አውጪ ነኝ ማለቱስ የትግራይ ህዝብ ፍላጎትና ጥቅም መጠበቅ ማለት ነውን? በኢትዮጵያ ደረጃ ትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ፍትሕ ሳይረገጋጥ በትግራይ ብቻ ትክክለኛ ለውጥ ሊረጋገጥ ይችላል ወይ? ህወሓት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪና መድህን ቢሆን ኖሮ ህዝቡን ከሻዕቢያ ወረራ ያዳነው ማን ነው? እናንተ የትግራይ ነፃ አውጪ ነን ትላላችሁ ነገር ግን ሌሎች ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰቦችስ ማን ነፃ ያውጣቸው?
አዎ!! ይህ ዓይነቱ ድራማና ጥያቄ ላለፉት ሶስት ዓሰርተ ዓመታት እንቆቁልሽ ሆኖ የቆየና ገና በሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዘንድ በሆድ ውስጥ ታምቆ አንድ ቀን ሊፈነዳ የተቃረበ እሳተ ጎመራ መሆኑን አልጠራጠረም። ከላይ ለተጠቀሱት ጥያቄዎች ህወሓቶች መልስ ይሰጡኛል ብዬም አልጠብቅም። “ከኛ በላይ ወንድ የለም። ተልባ ቢንጫጫ በአንድ መውቀጫ። እኛ እንብላ እነሱ ይጩኹ። እኛ እንግዛ እነሱ ያልቅሱ። ያበጠው ይፈንዳ!! ብለው በንፁኃን ደም የሰከሩ፣ በፍቅረ ንዋይ ዓይናቸው የታወሩ፣ በቂም በቀል አእምሮዋቸው የደነዘዙና በጠባብነት ሻማ የተሸበቡ ካድሬዎችና መሪዎች ዛሬ ዊስኪ እየተራጩና ጮማ እየቆረጡ የልደት በዓላቸውን ቢያከብሩ ብዙም አዲስ ነገር አይደለም።
meles and his milltery
የህወሓት ድራማ ቁጥር 3.
የህወሓት መሪዎች ህዝቡን ለማታለል ከሚሰሩት ድራማ አንዱ በሀገሪትዋ ላይ ሕገ መንግስት፣ መድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ነፃ የመከላኪያ ኃይልና ፍትሕ መኖሩን ለማስረዳት ይሞክራሉ። እነዚህ መሰረታዊ መርሆዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የአንድ ድርጅት ሞኖፓላዊ ስልጣን ለመጠበቅና ለማገልግል ሲባል ሌላ ቀርቶ ሰሞኑን የህወሓት መሪዎች ልደት ለማከበር እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከሚከተሉት ጭብጦች መረዳት ይቻላል።
 ሕገ መንግስት አለ ይሉናል። ነገር ግን በሕገ መንግስቱ የሰፈሩ መብቶች ሌላ ዜጋ እንዳይጠቀምባቸው በተግባር ተገድበዋል። ሕገ መንግስቱ በነፃ መደራጀት ይፈቅዳል በነፃ መንቀሳቀስ ግን በሽብርተኝነት አዋጅ ተገድበዋል። ሕገ መንግስቱ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ይፈቅዳል ነገር ግን በህዝብ ሀብት የሚተዳደሩ የብዙሓን መገናኛ አውታሮች በአንድ ድርጅት በሞኖፓል ተይዟል። የፃፈ ወይም የተናገረ ዜጋ ሁሉ ሰፈሩ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ሆኗል። ሕገ መንግስቱ ምርጫ ይፈቅዳል ነገር ግን የምርጫው መወዳደሪያ ሜዳ ተዘግቷል። በአጠቃላይ አንድ ድርጅት ራሱ ሕግ አውጪ፣ ራሱ ሕግ ፈፃሚ፣ ራሱ ገዳይ፣ ራሱ ከሳሽ፣ ራሱ ዳኛ የሆነበት ስርዓት ነው ያለው።
 በሀሪቱ መድብለ ፓርቲ ስርዓት አለ ይሉናል። ነገር ግን አውራ ፓርቲ ወይም ልማታዊ መንግስት በሚል ፓሊሲ ትርጉም ያለው ተቀናቃኝ የፓለቲካ ድርጅት እንዳይበቅል በሩ ተዘግቷል። በሕገ መንግስቱ ላይ አንድ ፓርቲ ከሌሎቹ ፓርቲዎች የበለጠ መብት እንዲኖረው ወይም በአውራ ፓርቲነት የሚፈርጅ አንቀፅ የለም። ነገር ግን ህወሓት ከሌሎቹ የተለየ መብት ያለው የበኩር ልጅ በመሆን የሀገሪትዋን ገንዘባዊ፣ ተቋማዊ፣ ማተሪያላዊና ሰብኣዊ ሀብት በቀጥታም ሆነ በተለያየ መልክ በመጠቀም በዓሉን ሲያከብር እናያለን። ሌላው ሀገር በቀል ኢትዮጵያዊ ድርጅት ያልተሰጠው መብት ለህወሓት ግን ከደደቢት በረሃ በመምጣቱና የመከላኪያ ሰራዊት ከጎኑ ስላሰለፈ ብቻ ሀገርንና ህዝብን እንደፈለገ እንዲንድ፣ እንዲዘርፍ፣ እንዲገድልና እንዲያፍን መብት ተሰጥቶታል።
 መከላኪያ ሰራዊት ከፓለቲካ ነፃ ነው፣ የሕገ መንግስት ዘብ ነው፣ የህዝብ ሰራዊት ነው፣ የልማት ሰራዊት ነው፣ ወዘተ ይሉናል። ነገር ግን በተግባር ሲታይ የአንድ ድርጅት ህወሓት ጠበቃና አጃቢ እንጂ የህዝብ ወገንና መድህን ሲሆን አላየንም። ለምሳሌ ሰሞኑን እንዳየነው ሁሉ የመከላኪያ ሰራዊት ሳምንት በሚል ሽፋኝ እየተካሄደ ያለው ሰልፍና ኤግዚቪሽን ሆን ተብሎ ከህወሓት ልደት ጋር የተያያዘ እንዲሆን ተደርጓል።
“አትረፍ ያለው በሬ ቆዳውን ለከበሮ ይውላል እንዲሉ” የትግራይ ህዝብ ላለፉት አርባ ዓመታት ያሳለፈውን መከራና ስቃይ እንዳይበቃው ዛሬም ከጀርባው አልወረዱም። እንደ ህዝብ መከበር ሲገባው በአንፃሩ ህወሓት ከሕግ በላይ በመሆን አማራጭ መንገዶችን በመዝጋት የአንድ ድርጅት አገልጋይ ሆኖ እንዲኖር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በተለይም የትግራይ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ!! ድርጅትና ግለ መሪዎች አላፊ ናቸው።ህዝብና ሀገር ግን ነባሪ መሆናቸውን አምነን ህዝባችንን ከጅብ ምንጋጋ እንዲላቀቅ እጅ ለእጅ ተያይዘን መነሳት አለብን እላለሁ። ዋስትናችን፣ መድህናችንና ጋሻችን አንድ ድርጅት ሳይሆን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን አማራጭ የሌለው የህልውና ጥያቄ ነው። ስለዚህ አንድ ድርጅት ወይም ግለሰቦች መምረጥ እንችላለን ነገር ግን አንዲት እናት ሀገር ነው ያለችን ሌላ አማራጭ የለንም።

Cairo Analyst Says Ethiopia Dam Won’t Hurt Egypt

VENTURES AFRICA – A water expert from the AUC University in Cairo has confirmed that Ethiopia’s hydroelectric dam will not hurt Egypt’s share of the Nile waters. According to the Egypt-based water resource management specialist Richard Tutwiler, the Ethiopian dam will never stop the flow of water downstream to Egypt.
“It is unlikely that Ethiopia will severely choke or stop the flow of water. Ethiopia needs the electricity…and hydroelectric dams don’t work unless you let the water through” said Mr. Tutwiler.
The Sudanese government has also supported the Ethiopian dam because “the dam would have minimal impact on its (sudan’s) water allotment…and the mega-project’s other benefits became clear. ”
Water experts have confirmed that the dam is expected to improve flood control, expand downstream irrigation capacity and, crucially, allow Ethiopia to export surplus electricity to power-hungry Sudan via a cross-border link. Some studies indicate that properly managed hydroelectric dams in Ethiopia could mitigate damaging floods and increase Egypt’s overall water share. Storing water in the cooler climes of Ethiopia would ensure far less water is lost to evaporation than in the desert behind the Aswan High Dam in Egypt.
Despite these assurances from the international community and water experts, some Egyptian warmongers and politicians have unnecessarily threatened Ethiopia and other upstream African countries. Some Egyptian generals have been seen undercover in southern Somalia and the Ogaden, arming rebels and agitating more anti-Ethiopia sentiment among the public. Analysts say that Egyptian military leaders want to distract the pro-democracy movement in Egypt from domestic problems by diverting their attention to a nonexistent external threat.
Some Egyptian politicians also claimed that Egypt deserves to eternally keep over 90 percent of the Nile even though it contributes less than 1 percent to the Nile. They cite outdated colonial agreements from 1959 signed between Egypt and Britain, which excluded eight out of ten Nile African countries. The Mubarek Cairo regime also took advantage of the civil war in Ethiopia to sign vague agreements in 1993. However, for the first time in history, the majority of Nile basin African countries signed in 2010 the binding international treaty, the Cooperative Framework Agreement (CFA), for the fair and equitable utilization of the Nile River among all countries.
Egypt ignored the 11 years of negotiations that led toward the CFA treaty, which was adopted by all other Nile African countries. Despite threats from Egypt, Ethiopian government has continued the dam construction. Analysts say that Ethiopia’s growing population need to utilize the Nile river since it can not depend on erratic rains to produce energy or to feed its people who have already suffered numerous famines over the last few decades.

Ethiopia Orthodox Church takes roots in Ghana

The Ethiopia Orthodox Tewahedo Church will take firm roots in Ghana with the establishment of a branch of the church in Ghana after the acceptance of a fact-finding report that recommends that it is apt to have the church in the country.

When approval is given, a priest and a monk will be sent to the country to take charge of the liturgy and spiritual needs of the community of a deacon, baptised and non-baptised members of the church.
In an interview with Public Agenda, KesTesfa Michael, a priest of the Ethiopia Tewahedo Orthodox Church who came to the country to undertake the fact-finding, said, barring any unforeseen circumstances, the report that he would submit to the Archbishop of the Continent of Africa, AbunaYacob, would lead to the setting up of the Ghana branch of the church. Kes Michael was sent to the country by Archbishop of the Diocese of England, Abuna Enthons.
“The prospects look good for the formal establishment of the church in Ghana. There are many people who really need the church here,” Kes Michael said, before departing to London on March 19, 2014 after a two-week stay in the country.
He said copies of his report would be given to the Secretary of the Arch-diocese of the Continent of Africa and it would be discussed at a meeting of the Holy Senate of the church before a final decision would be taken whether to set up or not to establish a branch of the church.
He said when it is approved that a branch be set up, the next step is for the Christian Council of Ghana and AmdeTsion, an elder of the church whose untiring efforts resulted in the fact-finding mission, to be contacted to prepare the grounds for the founding of a branch.
By then, a Mahiba, a group of members and potential members of the church which study the Bible and take care of their social needs, and an appropriate building for liturgical services would have been put in place for a priest and a monk to come and live in the country.
During his visit, Kes Michael conferred with Rev. DrKwabenaOpuniFrimpong, the Secretary-General of the Christian Council and other clergy; met with members of the Ethiopia World Federation and Rastafarians; and held services with members of the church. He also featured on several Accra-based radio stations to explain the theology, philosophy and doctrine of the church.
One of the few pre-colonial Christian churches in Sub-Saharan Africa, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church has a membership of between 40 and 45 million people, the majority of whom live in Ethiopia. Thus, it is the largest of all the Oriental Orthodox churches. The church is a founding member of the World Council of Churches. Tewahedo is a Ge’ez word which means’being made one’ or ‘unified.’ The word refers to the Oriental Orthodox belief in the single unified Nature of Christos (Christ). That is the belief that a complete, natural union of the Divine and Human Natures of Christ into one is self-evident in order to accomplish the divine salvation of humankind. This tenet is opposed to the ‘two Natures of Christ’ belief (unmixed, but inseparable Divine and Human Natures, called the Hypostatic Union) which is held by the Roman Catholic Church and Eastern Orthodox churches.

ጨዋታና ቀልድ ይድረስ ለወንድሜ ዳዊት ወዬሳ ከበደ


ሰሎሞን ታምሩ ዓየለ
ውድ ወንድሜ ዳዊት ሆይ! በቀልድ መልክ የጫርካትን መጣጥፍ ሳነብ ጊዜና እኔም ተማርኬና እጅ ሰጥቼ ይኽው መንገድ በብርቱ ጠቃሚና ተፈላጊ ነገር ግን ትኩረት ያልተቸረው የመልዕክት ማስተላለፊያ ቱቦ እንደሆነ ተረዳሁኝ። በተለይ የአገሬ ምሁራን፤ የዕውቀት ልካችው ጥግ የደረሰባቸውና ተሕዝብ ጉያ ወጥተው ወደ ሕዝብ ተመልሰው ገብተው ለማስተማርና የአስተምህሮቱ ዘዴ ጠፍቷቸው ዕውቀታቸውና ችሎታቸው ለሳይንሳዊው ወይም በነሱ አጠራር ለአካዳሚኩ ኅብረተሰብ ክፍል ለሚሉት ብቻ ተገድበው የቀሩቱን፤ ወደ ህዝብ ለመመለስ ዓይነተኛ ዘዴ መሆኑን ለማመላከት ጭምርም ፈልጌ ነውና ተማጽኖዬን ተቀበለኝ ስል የድጋፍ መልዕክቴን እንዲህ ከምኖርበት ተወደ ካሊፎርኒያ በዚሁ ድረ ገጽ በሚሉቱ በትኜዋለሁኝ። ትምህርት፤ ዕውቀት፤ ልምድና ክህሎት ማኅበራዊ ዋጋቸውና ጠቀሜታቸው የሚለካው በማኅበራዊው ኑሯችን ውስጥ በምናገኘው  የተስተካከለ ለውጥ፤ በማኅበራዊ አስተሳሰባችንና ምግባራችን እንጂ በግለሰቦች ክብርና የአካዳሚክ ዕውቀት መራቀቅ ብቻ አይደለም። ዕውቀታችንና ችሎታችንም ጭምር ሕዝባዊ ማድረግ ልምድ ማድረግ አለብን። ታለባለዚያ ዕውቀት ሙትና በድን ነው። አይጎተጉትም፤ ለለውጥና ለመሻሻል አያነሳሳም።  ዕውቀት ልኳ የሚታወቀው በጆርናል፤ በፔሮዲካልስና በሌሎች ህትመቶች ተጠርዛ ከመደረደሪያ ላይ ተቀምጣ ከማገናዘቢያነት ባሻገር ከፍ ያለ አገልግሎት እንደየደረጃውና እንድ አቅሚቲ መስጠት ስትችል ብቻ ነው። ለሕዝብ መገልገያነቷን እናመቻቻት። ካልሆነ ደግሞ ከጋን መብራትነት የዘለለ አቅም የላትም። ይሄንን ደግሞ አንሻውም። መሆንም የለበትም። ትንሽ የማሰብ ችሎታችንን መጨመር ብቻ ነው። ሁልግዜ የቁጥር ሰንጠረዥና ግራፍ ወዲያም ሲል ትንተና ብቻ ወደ ሕዝብ መቅረቢያና መልዕክት ማድረሻ አይሆንም። መናቄና ማንኳሰሴም አይደል። ወይም ደግሞ አስፈላጊም አይደለም ማለቴም አይደለም። ለሁሉም የሕዝብ ክፍል ግን እኩሌታ አገልግሎት አይሰጥም ማለቴ ጭምር መሆኑ ይታውቅልኝ። መልዕክቱ  በቀላሉ በቶሎ ተቀነባብሮ በፍጥነት ለኛ ለመልዕክት ተቀባዮቹ ፈጥኖ ከች አይልም ለማለት ፈልጌ ነው። የቸኮለና ሃሳቤ ያልገባው ለወቀሳ እንዳይቸኩልም ማስገንዘቤ እንጂ።
ቀልድ፤ ጨዋታ፤ ትዝታ፤ አሽሙር፤ ፌዝ፤ ሙሻዙር፤ ትረካ፤ ተረት ተረት፤ ነገር በምሳሌ አባባል፤ ብሂልና ሌሎችም የጥንት አባቶቻችንና እናቶቻችን ችግራቸውን፤ ብሶታቸውን፤ እሮሮዋቸውን፤ ስጋታቸውን፤ ፍርሃታቸውን፤ ጭንቀታቸውን፤ ተስፋ ማጣታቸውን፤ ሃዘናቸውን፤ ደስታቸውን፤ ፍላጎታቸውን፤ ምኞታቸውን፤ ጥጋባቸውን፤ ቆራጥነታቸውን፤ አይበገሬነታቸውን፤ ጀግነነታቸውንና ጥንካሬያቸውን ሌላም ባህሪያቸውንና ጠባያቸውን ጭምር መግለጫም እንደነበር እናስታውሳለን። በአንዳንዶቻችንም ውስጥ ዛሬም እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ሁኔታዎች ይንጠባረቃሉ፤ ይታያሉ፤ ይገለጣሉ።
ቀልድና ጨዋታ በአግባቡ ከተያዙና ከተገለገልንባቸው የሕይወታችን ቅመም ናቸው። ኑሮንም ትርጉም ይሰጡታል። ሳይበዙ በመጠኑ ደግሞ እንደ ብትን ጨው፤ ስኳርና ማርም ናቸው። በተለይ በተለይ ድግሞ በቁም ነገር ከታጀቡና እንደ ጭብጦ በቅቤ ከታሹ ጉልበት አላቸው። አስተማሪዎች፤ አዝናኖኞች፤ ለፍትህና ርትዕ አነሳሶች፤ አደራጆችና አነቃቂም ናቸው። ሰውነታችን በድብርትና ጭንቀት ብዛት የሚያመነጨውን ማንትስ የሚባል “ጎጂ ኤንዛይም “ እያዝናና ድራሹን ያጠፋል በምትኩም ሌላ ሰውነት የማይጎዳውን ቅመም ያመነጫል። በሽታ የመፈወስም ባህርይ ሊኖራቸውም ይችላል። የደነደነን ልብ ይከፍታሉ፤ አእምሮንም በማነቃቃት መልዕክትን በፍጥነት በመልካም ፍቃደኝነት መቀበሉን ያረጋግጣሉ፤ መንፈስንም ያረካሉ፤ ነፍስንም ደስ ያሰኛሉ፤ በስተመጨረሻም እንደ ጂምናስቲክ እንቅስቃሴ የተወጠረ አካልን ያበረታታሉ፤ያዝናናሉ።
ቀልድ፤ ጨዋታ፤ ትረካ፤ ትዝታና ሌሎችም ትክክለኛ ፍቺያቸው ምን እንደሚመስሉ፤ አንዱ ከአንዱ የሚለይበትም ሆነ አንዱ በአንዱ ውስጥ የመገኘትና አንዱ አንዱን አጉልቶ የማሳየት ሚስጥሩ፤ ማኅበራዊ መስተጋብራቸው ምን መልክ እንዳለው የተረጋጋጠ ማስረጃ ማቅረብ ግን አልችልም። እንደው በደምሳሳው ሳስበው ግን ቀልድም ሆነ ጨዋታ የጥበብ ዕውቀት ዘርፍ መሆናቸው ግን ፍንትው ብለው ይታዩኛል። በቀልድና ጨዋታ የጠለቀ ዕውቀትም ትምህርትም የለኝ። ለመማር ግን ዝግጁ ነኝ ። ብርቱና ፈጥኖ የሚያደርስ አስተማሪ ካገኘሁኝና ጊዜው ያላለፈብኝ ተማሪ ካልሆንኩኝ በስተቀር። ግን እንደ አንድ የህብረተሰቡ ክፍልፋይ አካል፤ ጤናማና ሰላም ወዳድ ዜጋ ደግሞ  አጔጉል ቀልዶችም ሆኑ ጨዋታዎች አደግኝነታቸውንም ያሳስበኛል። ጎጂና አፍራሽ ቀልድም ጨዋታም ፍቅር ያበላሻል። ከነሱ ድግሞ መራቅና ጆሮ አለመስጠት ነው። አበውና እማዎች ሲተርቱ “ቀልድና       ቤት ያበላሻል “ መባሉንም አንዘንጋ። ገንቢ ቀልዶች ደስታን ይፈጥራሉ፤ ወዳጅም ደንበኛም ያበዛሉ።
ቀልድና ጨዋታ የትም አለች። ትኖራለችም። በጊዜና በቦታም ልትወሰን ብትችልም ቅሉ፤ ምንአልባትም አንድ ቀን ከህዋው ወይም ከጠፈሩ ዓለምም እንሰማት ይሆናል። ይኽው ከመንግስተ ሰማያት ከሚኖሩ ሰዎችና ወደ ፊትም አምባገነኖችና አንዳንድ የመንግስት ሰዎች ገነ ለገና አያ ሞት ሲመጣባቸውና  ስልጣናቸውን ነጥቆ ጉዞ ወደ መቃብር ሲሉ ስለሚጠየቁትና ሰለሚሰጡት መልስ ከወዲሁ እየተቀለደ አይደለም እንዴ? እስቲ ማነው የማይቀልድ ? ማንስ ነው የማይጫወት? መልሱ ምንም የሚል ነው። በፓርላማ ታዋቂ ፖለቲከኞቻችንና ሚኒስትሮቻችን፤ ከዜና ማሰራጫዎቻችን ኢቲቪና የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጥሩ ቀልደኞችና ፌዘኞች አይደሉምን? በተለይ ደግሞ “የዜና ምርቶቻቸው” በሽ አይደለም እንዴ! በቁጥር፤ በብር፤ በዕድገትና ልማት፤ በድራማና በትዕይንት ዝግጅታቸው የታወቁ ቀልደኞች አይደሉም የሚለኝ ካለ ለፍልሚያው በየትም ዝግጁ ነኝ። ወይ ጉድ! ነፍሳችንን ጮቤ እያስረገጧት አይደለም። ድሮ እንደተባለው ልድገመውና “ኢቲቪና ሬዲዮ ኢትዮጵያ”  ትክክለኛውን የሚናገር ሰዓቱን ብቻ ነው ከተባለ ቆየ። መንግስትም ይቀልዳል፤ ያፌዛል፤ እኛም በአጸፋው እንቀልዳለን።
ቀልድና ጨዋታ መንግስትም ቤት በፓርላማም አለች። ጠ/ሚንስትር መለስ ጥሩ ቀልደኛና የሚያፌዙ ሰው ነበሩ። አብረዋቸው በም/ ቤቱ ደፋ ቀና በሚሉት አገልጋዮችም ሲያፌዙ አይተናል። ከበረከት ጋር በመሪ ተዋንያንነት “አኬል ዳማንና” ትንሽ ዘግየት ብሎ ከሳቸው መጥፋት በኋላ “ጂሃዳዊ ሃረካትን “ተመልክተናል። በቅርቡም እነሱ” አክራሪ አርቶዶክስ “ ብለው በሚጠሯቸውም ላይ የተለመደ ትዕይንታቸውን እያቀነባባሩ እንደሚገኙ ያነበብኩኝ መሰለኝ። አይጣል ነው! ይህ መንግስት የሚባል ተቋም ይሄንን ስራዬ ብሎ ከሚሰራ ለምን ኑሮ እንዲሻሻልል ማድረግ የሚችለውን አያደርግም? ዕድገትና ልማት ድራማና ትዕይንት ማምረት ነው እንዴ? እውነትም ይሄ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ጭንቅላት ሳይሆን ድንጋይ ብቻ እንደሚያመርት ማራጋጫ እራሱ እየሰጠ መሰለኝ። በ1985 የአ አ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ቡጥሮስ ጋሊ ከቤታቸው መጥቶ ሳለ ተቃውሞ ለማድረግ ግቢዋን በር ወጣ እንዳሉ በጥይት የሚችሉትን ከገደሉ በኋላ ለምን ጥይት አስተኮሱ ?ሲባሉ የሚያስለቅስ ጢስና ግፊት ያለው ውሃ የሚረጭ መኪና የለኝም ብለው አስገርመውን ነበር። የታምራት ላይኔ ስኳር ቀመሳን ቅሌት እንዴት አድረገው በፓርላማቸው እንዳብራሩታ አይጣል ያሰኛል። በተጨማሪም በሳቸው አገዛዝ ዘመን የአገሬ ገበሬ ሻይና ቡና በስኳር መጠጣት መጀመሩንና ስኳር ከገበያ ጠፍቶ መወደዱን መግለጻቸውንም እናስታውስ። አባ ዱላም አንዱ ቀልደኛና ፌዘኛ ነበር። በሙስና የሰራውን ቤት ለድርጅቱ ኦሕዴድ ገቢ አደረገ። ወ/ ሮ አዜብም በቀልድ ጨዋታና ፌዝ ከቀዳሚ እመቤቶቻችን ዋና ናቸው። ባለቤታቸው መለስ ሚስኪን ሰው እንደነበሩ፤ የቀበሌና የመንጃ ፍቃድ ጊዜ ኖሯቸው ሳያወጡ እንደሞቱና በፔሮል ላይ ብር 4ትሺ ብቻ  የሚያስፈርም ደመወዝ እንደነበራቸው አሳዝነው አስለቅሰውናል። የሙስናው ቀልድም ጨዋታም እጅግ ያሳዝናልም፤ ያበሳጫልም። የፍርድ ቤቶቻችን አሰራርም፤ ብያኔ አሰጣጣቸውም እንዲሁ በፌዝ የተሞላ ነው። በቅርቡም ጠ/ሚንስትር ኃይሌም ስለ ድርጅታቸው ዲሲፒሊን አክባሪነት ሲናገሩ ድርጅቴ ” ሊስትሮ ሆነህ ስራ ቢለኝ እሰራለሁ “ ማለታቸው የቅርብ ጊዜ  ትውስታችን ነው። ፕሮፌሰር መራራም ቀላል ቀልደኛና ፌዜኛ አልነበሩም። “ተባበሩ፤ አለባለዚያ ተሰባበሩ “ ብሎናል። “ኢሕአድግ አፍ እንጂ ጆሮ የላትም “  “ ምርጫ፤ ቅርጫ” ብሎም ፈገግ አስደርጎናል። አንድ ውቅት በተለይ በ1984ቱ አካባቢ “በሙዳይ “ መጽሄትም ላይ ከፋብሪካው የሚፈጭ ስንዴ ጠፍቶ ስብሰባ የሰለቸው ላብ አደር “ዴሞክራሲ እየፈጩ” እንደሆነ ቀልዶ አልፏል። አንድ በግል የምትታተም ጋዜጣም በ1993ቱ መሰለኝ የጠ/ሚንስትር መለስ እናትን ከዚህ ዓለም በሞት መለየትና የቀብራቸውም አፈጻጸም በአድዋ መደረጉንና  የመንግስት ሄሊኮፕተሮች አስክሬን ይዘው ከስፍራው በቶሎ መገኘታቸውን መረጃ የደረሰው ጋዜጠኛ በሁኔታው በመገረም መሰለኝ (ቀብሩ የግል ጉዳይ መሆኑን ለመግለጽ መሰለኝ) “ጠ/ሚንስትሩ መዘዙ ወይስ አዘዙ” ብሎ በመጻፉ በጠዋቱ ፈገግ አስደርጎናል። ቀልድና ጨዋታ ጦር ሜዳ ድረስ ዘልቃ ከሻዕብያ ጋር ፍልሚያ ላይ የነበረውን የሃገር መከላከያ ሠራዊትም ለአፍታ አዝናንቶታል። አንባቢያን ሰለ ጦር ሜዳዋ ቀልድ ማውቅ ከፈለጉ በሻለቃ ማሞ የተጸፈውን “የወገን ጦር ትዝታዬን “ እንዲያነቡ ይመከራሉ። እኔ ግን ከዚያም ባሻገር በቀነ ቅዳሜ የሬዲዮ ፋና እንግዳ ሆኖ ቃለ መጠይቅ ለሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ (ወጋየሁ ራሱ ኢጆሌ ካራ ሚሌ ስለሆነ ጨዋታና ቀልዱ አይጣል ነው። ነፍስ ይማር_ሃርኬ ሁማ።) ሲደረግለት በጆሮዬ ትረካውን በራሱ አንዳበት ስለሰማሁኝ ሳቅ በሳቅ ሆንኩኝ የጀኔራል ረጋሳ ጅማ አመራር ሃይለኛ ነበር።    ቆርጦ   ቆርጦ መጣል ነበር የምትል ዘፈኑ ነች ለዛ ያበቃችው። አንዳንድ የወያኔ ኢሕአድግ ፖለቲካ ደጋፊዎች ደግሞ በቅርቡ የጤፍ ሰብል እንዲህ አነጋጋሪ በሆነችበት ዘመን ንብረትነቷ ኢትዮጵያዊ መሆኗ ቀርቶ በዕውቀት ማነስ ነው መሰለኝ ” መለስ ጤፍን ዲስከቨር “ አደረገ ብሎ የሚከራከርም አንብቤአለሁ። በስራ ዘመኔም አንድ የወሎ ገበሬ ያለኝን ላጫውታችሁ። ከዚያ ከአስከፊው ድርቅ በኋላ በምግብ ለስራ ፕሮግራም ተሳትፎ የሚያገኛትን ተጨማሪ ምግብ በዘመነ ወያኔ ያጣ እንዲህ ነበር ግጥሚቱን በፊቴ ያነበነባት። ” ከልማቱ እንጂ ምን አለኝ ከፊቱ፤ እንደገና ይምጣ ኮሎኔል መንግስቱ።” ቀልድ በሕዝብ ፊት ንግግር በሚያደርጉ ታላላቅ ሰዎችም ትዘወተራለች። ታዋቂ መምህራንም የዕለቱን ትምህርት ከመጀመራቸው አስቀድሞም ቀልድና ጨዋታ የተለመደ ተግባራቸው አድረገዋታል። የመድረክ አስተዋዋቂ ሰዎችማ መደበኛ ስራቸው ነው። ቀልድና ጨዋታም “ቢዝነስ” ነች። የገቢ ምንጭም መሰብሰቢያም ሆና ገበያ ላይ ወይ በክር አሊያም በሲዲ ላይ ተቀርጻም እኛው ገዝተናት አብረን ነፍስ አስደስትነንባታል። በቅርቡ ደግሞ አንድ ራሱን ” አባ መላ “ እያለ የሚጠራ ቀባጣሪና አንድ ጎበዝ እህቴ ደግሞ ” አባ በላ” (በላን ጠበቅ ተደርጎ ይነበብ) ብላ የጠራችውና ውርደት እንደ አሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ቀለቡ የሆነ ሰውዬም ተፈጥሯል። ደረጃውና ምደባው ግን ከተራ ቅሌት ሰፈር ነው። እንደ አቶ ስብሃት ነጋ ዓይነቱ ደግሞ ቀልድ የሚባል የማይገባውም እንዳለ ማወቅ ደግ ነው። ስብሃት የአማራና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን አከረካሪ በመስበር ብቻ ነው መታወቅ የሚፈልግ። ሲሰራም፤ ሲበላም፤ መለኪያም ሆነ ብጭርቅ ሲጨብጥና ከተቃራኒ ጾታም ሲዳራ የሚታየው አማራን ሰባብሮ ገደል መጣል ነው። አከርካሪውን ብሎ ሺባ ማድረግ ነው ምኞቱ ሁሉ።  የ፲ አለቃ( የምን ጄኔራል ነው!) ሳሞራ የኑስም እንደዛው ጸረ አማራ ነው። ነገር አልጥምና ቶሎ አልገባ ሲለው” ኧረ የሰው ባህሪ” እያለ የሚደጋግም ወድ ጓደኛ ነበረኝ። እኔም ይቺኑ እንደ ሞኝ ይዤ “ኧረ የስብሃትና ሳሞራ ባህሪ” ብልስ?
ስለ ቀልድና ጨዋታ ስናወሳ ቀልደኞችንም ዝም ማለት አይቻለንምና ማነው ቀልደኛ መሆን የሚችለው ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው። ጥሩ ስብእናና መልዕክት የማስተላለፍ፤ ሃሳቡን በቀላል ቋንቋ መግለጽ የሚችል፤ አመቺ ቦታና ጊዜን መምረጥ የሚችል መሆን አለበት። ልማታዊ የሆነ ቀልደኛ ደግሞ ለአምባገነኖች ጥሩ ፈረስ ነው። ቀልደኞችና ጨዋታ አዋቂዎች ቀልዶቻቸው ወጥነት (ወሪጅናሌ) ቢይዙ ይመረጣል ። ግልባጭ ከሆኑ ብዙም አያስፈግጉንም፤ አያዝናኑንም። ለምሳሌ፦ ገበሬ ስኳር ገዝቶ ቡናና ሻይ ጠጣን፤ ገበሬው ጤፍ ገዝቶ መብላት ማብሰሩን እንደ ኑሮ ውድነት ምክንያት አድሮጎ ማቅረብ ደስ አይልም። ግልባጭ መሆን ነው። ራስን አቅል ማጣት እንጂ የነገር አዋቂነትን አያሳይም። ድግግሞሽ ነው። አንዳንድ ሕዝብ ደግሞ አብዛኛው ነዋሪው ጥሩ የመቀለድና የተጫዋችነት ባህርይ ይይዛል። ለምሳሌ በቡልጋሪያ አገር ጋብሮቭስኪ ክልል የሚኖሩቱ ጥሩ ቀልደኞች ናቸው። አንድ ደራሲም በአማርኛ ቋንቋ ” የጋብሮቮ ቀልዶች” በሚል ዐርዕስት ተጽፋ ለገበያ ከቀረበች እነሆ ከ25 ዓመት በላይ ሊሆናት ነው። በኛም አገር ቢሆን የሐረርጌ ልጆች ጥሩ ቀልድ ይሰራሉ። ምንአልባትም ያቺን አረንጓዴ ጓደኛቸው(ጅማ) ዛፍ ላይ ለመውጣትና ለመቃም (ለመብላት ሳቅ!) ሰብሰብ ስለሚሉም ይሆን? እንግዲህ ይህንን በምርምር፤ በጥናትና ክትትል ማረጋገጥ የማኅበራዊ ሳይንስ ወይም ጥበብ  ሰዎች ተግባርም አይደል?
እንግዲህ ልጠቅለለውሳ። ቀልድ፤ ጨዋታ፤ ፌዝ፤ አሽሙር፤ መሸወድ፤ ማታለል፤ ማጭበርበር፤ ቁጭ ይበሉ   ሌላም   ሌላም ትክክለኛ ፍቺዋንና ትርጉማንና አመዳደቧን እስከምናውቃት ድረስ ዝም ብለን እንደዛ እንደ ” ዴሞክራሲ ወፍጮ መፍጨት” ነው። ይሄ የዴሞክራሲ ወፍጮ ደግሞ አንዳንዴ ይከካል፤ ይሸረክታል፤ ክኩን ከጥሬው መለየት ያዳግተዋል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ አድቅቆና አልሞ ይፈጫል። የወፍጮውን ጥርሶች እሽክርክሪት የሚያስተካክል ጥሩ መሃንዲስና ሜካኒክ ያሻናል። ብቻ ዕውቀትና ምንትስ እያደር ይጠራል ብልስ ስህተት የሰራሁ አይመስለኝም። ለጊዜው ሁሉ ነገር ዝብርቅርቅና ድብልቅ ነው። ገና እንደ ፖለቲካችን አልጠራም። ሚናውንም አልለየም። ቀልዱ ከፌዙ፤ ጨዋታው ከሃሜቱ፤ አሽሙሩ ከሹፈቱ፤ ሽወዳው ከማታለሉ፤ ሙስናው ከስርቆቱ፤ ቢዝነሱ ከዝርፊያው     ሌላም    ሌላም። መንግስት ያሾፋል፤ ፖለቲከኞች ይዋሻሉ፤ ይቀልዳሉ፤ ሕዝቡም በራሱም ኑሮ ይጫወታል ፤ ይቀልዳል አንዳንዴም ግጥም እያወረደ ያቀነቅናል። ለመሆኑ በኢትዮጵያችን የመጀመሪያው ቀልደኛና ጨዋታ አዋቂ አለቃ ገብረሃና ናቸው የሚባለው እውነት ነውን? እህሳ ምን ይሰማሃል? አበቃሁ! እናመስግናለን!!!!!
ሠሎሞን ታምሩ ዓየለ

ፓስፖርት ሸርካቹ ወይም ቀዳጁ መንግሥት


ሰሎሞን ታምሩ ዓየለ
መጋቢት 18 2006 ዓም
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በመጋቢት 12 2006 ዓም በሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር በኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የጉዞ ሠነድ ለይ ጉዞውን ወደ ምድረ አሜሪካ ለማድረግ የነበረውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ የተደረገውን የወረደና የዘቀጠ፤ ጥላሸት ያነጠፈበትና ሸረሪት ያደራበት  በዝምታና በተንኮል የተውተበተበውን ስንኩል የመንግስትን ቁሻሻ አሰራር ለማውገዝና ድርጊቱን ፈጻሚ ሰዎችም በህግ እንዲጠየቁና በዋናነት የዜግነት ድርሻዬን ለመጠየቅ ነው። መንገድና ድልድይ ሰራሁ፤ ት/ቤት፤ የመኖሪያ ሕንጻ፤ ግድብ፤ መስኖ፤ የሃይል ማመንጫ፤ ስኳር ፋብሪካ፤ ትልልቅና ግዙፍ የሆኑ የኢንጂነሪንግ ተቋሞችን ገነባሁ፤ ሰፋፊ እርሻ እያስፋፋሁ ነኝ የሚል መንግስት ድንገት ምን ቢነካው ነው እንዲህ ወርዶ ወረቀት የሚቀድ? አንድ ግለሰብስ ይሄን ያህል ምን አስፈራው? ትናንት የተመሰረቱበትን በዐል ሲያከብሩ ” ኮሌኔል ማራኪና ደርጊ ማራኪ” እያሉ በድላቸው ፈንጠዚያ  ወደ ሰማይ ላይ ሲዘሉና ሲጨፍሩ የነበሩ ሰዎች እንዴት እንዲህ ከመቅጽበት ወርደው የመንገደኛን የጉዞ ሰነዱን በመንጠቅ ወረቀት በመቅደድ ያንገላታሉ? ለመሆኑ ከነሱ በፊትስ ከአገር መውጫ ቪዛ ለማግኘትስ የአገሪቱ የሰደተኞችና የቪዛ አገልግሎት መስጫን በሰላም ያለፈና የአሜሪካን ኤምባሲ ለቪዛ ያለፈ ፓስፖርት እንዲህ በጋጠ ወጦቹ ደህንነት ተብዬዎች ከመቅጽበት ወረቀቱ ሲጎድል አያስገርምንምን?
በመሰረቱ መንግስት የሚባለው ፖለቲካዊ ተቋም በምርጫም፤ በቅርጫ፤ በጡጫም ሆነ በጠመንጃ  መጣ የሚፈጽማቸው ተግባራቶች አሉት። በዋናነት የአገሩን ግዛት ሉዓላዊነት ማስከበርና ሕዝብ በውጭ ወራሪ ሃይሎች ጥቃትና ወረራ እንዳይፈጸምበት፤ ህግና ሥርአት ደንብና ትዕዛዝ በማዘጋጀት ካለምንም አድልዎ ለዜጎች ፍትህና ርትዕ ማጎናጸፍ፤ የሃገሪቱን የተፈጥሮ ሃብቶች ለሕዝብ ዕድገትና ልማት ማዋል መጠበቅና መንከባከብ፤ የተሟሉ ሕዝባዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ( ስራ መፍጠር ትምህርት ማስፋፋት ጤና መጠበቅና ሽፋን መስጠት  የባህልና ስፖርት መዝናኛ  ማበልጸጊያዎችን የመጓጓዣ አገልግሎቶችን ማስፋፋትና ማቅረብና) ሌላም ሌላም ናቸው። ጠቅለለ ባለ አነጋገር መንግስት ከሕዝብ፤ ለሕዝብና በሕዝብ መሰረታዊ ተፈጥሮአዊ፤ ታሪካዊና በህላዊ እሴቶች ላይ ከተመሰረተ  የጸናና የሕዝብ መንግስት ይሆናል። ለዚህም መሰለኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስት ምንድር ነው ብለህ ብትጠይቀው መንግስት ሕዝብ ነው ብለው አባቶቻችንና እናቶቻችን ትርጉሙን የሚሰጡት። ዛሬ ግን ደረጃውን ዝቅ አድርጎ ፓስፖርት ቀዳጂና ሸርካች ተቋም መሆኑን አልሰሙም። አብዛኛው የአኅጉራችን አፍሪካና የኛው መንግስት ግን ሲተረጎሙ ከመንግስት ዋና ተግባሮች መቶ በመቶ በተቃራኒው የቆሙ ናቸው። ግፍ፤ ፍትህ አልባነት፤ ሙስና ሲያስፋፉ፤ ውረደትና ቅሌት የተሞላበት ተግባር በተደጋጋሚ ሲፈጽሙ ነው የሚታይ። ደግሞ ሌላውን የሕብረተሰብ ክፍል ጸረ ሰላም፤ ጸረ ልማት፤ ጸረ ሕዝብ፤ ሸብረተኛ እያሉ ሲፈረጁ እንኳን ለአፍታ አያፍሩም።  የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ ተብሎ የለ ።ስሟን ለሰው አወረሰች አሉም ይባላል።
ይህንን ሳስብ አንድ ተመሳሳይ የሆነና የወረደ ተራ ውስልትናና በሙስና የተውተበተበ አገር ጨዋታ ትዝ አለኝና ምንአልባት በኔ ዕይታ ድርጊቱ አንድ የሆነብኝን ነገር ግን ግዝፈቱ ከኛ ሰዎች ተግባር በአፈጻጸም ስልቱ ዝቅ የሚለውን ጨዋታ ልቅደድላችሁ። ይህንን ድርጊት የተፈጸመበት ሰው በስራ ላይ እያለ በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ በሕይወት የለም (ነፍስ ይማር)። አገልግሎቱን የሚሰጠው መ/ ቤቱ ለአጭር ጊዜ ሥልጠና በናይጄርያ አገር በኢባዳን ከተማ በሚገኘው የትሮፒካል አገሮች የእርሻ መካነ ጥናት ተቋም ባዘጋጀው የሙያ ማዳበሪያና ማሻሻያ ኮርስ ላይ እንዲሳተፍ ዕድሉን ይሰጠውና የጉዞ ሰነዱን ከጠናቀቀ በኋላ በረራ ወደ ሌጎስ ያደርጋል። ከዚያም እንደደረሰ ተርሚናሉን ከመልቀቁ በፊት ግን ያልጠበቀው ሁኔታ ተፈጠረ። የተለየ ሳይሆን በምግባረ ብሉሽነታቸው የሚታወቁቱ የናይጄ ሪያው ፓስፖርት ተቆጣጣሪዎቹ ለራሳቸው የፈጠሩት ንቅዘት የተሞላበት አሰራር ሰለባ መሆኑ ነው። ተቆጣጣሪው እንዲህ አለው። “One paper is missing from your passport.” ለጊዜው የተደናገጠው የሥራ ጓደኛዬና የችግሩ ተጠቂ ግን የገዛ ፓስፖርቱን ካለማመን ደጋግሞ ቢፈትሽም የተሟላ ሆኖ ስላገኘው ክርክሩን ይጀምራል ፤ ሙከራው ግን አልተሳካም። ወደ ጎን በተዘጋጀለት ማረፊያ እንዲቀመጥ ይታዘዝና የሚሆነውን ሲጠብቅ ሁኔታውን በጎን ትከታተል የነበረች ወይዘሮ / ወይዘሪት ጠጋ ብላ የጎደለውን ወረቀት ዋጋ ነገረችውና ለመንገድ ተመንዝራ በኪሱ ከያዛት የአረንጓዴ ኖት $20 በፓስፖርቶቹ ቅጥል መሃል አድርጎ እንደገና ወደ ተቆጣጣሪው ብቅ ያለው ወንድሜ “now, it is okay!” የሚል መልስ እንዳገኘና መግቢያውን ይዞ ወደ ስፍራው እንደ ሄደና ሥልጠናውን ለመሳተፍ እንደቻለ አጫውቶኛል።
የናይጄሪዎቹ ሙስናና ንቅዘት የፈጠረው አሰራርን ወንድሜ በትንሽ ገንዘብ ፈታው። የኞዎቹ ግን ከሕግ በላይ ሆነውና ማን ከኛ በላይ አለ በሚል ይመስላል የፈለጉትን ያደርጋሉ። እንኳን አይደለም ፓስፖርት ወረቀት መቅደድና መሸርከት ይኽው የአገርስ ድንበር መሬት ለሌላ ባእድ አገር አሳልፎ ለመስጠትእየቀደዱና እየቀረደዱ አይደለምን? ሕዝቡንስ በርሃብ አለንጋና በኑሮ ውድነት እየገረፉት አይደለምን? በፍትህና ርትዕ እጦት የተነሳ ሕዝቡ ከመክሰስ፤ መከሰስን የመረጠበት ወቅት አይደለምን የምንገኘው? በልማትና በዕድገት ስምስ ከተሞቻችን በሰይጣናዊ ምግባርና አገልግሎት እየተሞሉና እየደመቁ አይደለምን? እነሱ በቅጡ ሳይማሩና ከመጽሃፍ ሳይታገሉ ቤታቸው ቁጭ ብለው ባገኙት ዲፕሎማና ዲግሪ አለቃና ስራ መሪ ሆነው፤ የተማሩትና ከመጽሃፉ የታገሉት ኮብል ድንጋይ አንጣፊ ስራ ተፈጥሮላቸው የለምን? ሃይማኖት የለሽስ ሆነው ይኽው የእስልምናውንና የኦርቶዶክሱን ሃይማኖት እያመሱትና እየገለባበጡት አይደለምን? ይኽው የአንድ አገር ሕዝብ አንድ አድረገው መግዛትና በፍትህ ማስተዳደር ሲገባቸው በጎሳ፤ በቋንቋ፤ በፖለቲካ ደጋፊነትና ተቃዋሚነት፤ በመደብና በሌላም ሕዝብን ይከፍልልናል ብለው በሚያምኑት መንገድ ሁሉ በመክፈል ለግጭቶች ምክንያት አልሆኑምን? የመንግስት ሥልጣንስ ዋና ባለቤት በመሆን የመንግስት ዋና ዋና ተቋሞች ውስጥ ግምባር ቀደም ተሿሚዎችና አዛዥ፤ ናዛዥ አልሆኑምን? የነሱን ፖለቲካ ያልተቀበለውንና ያልደገፈውንስ የተማረና ልምድ ያካበተውን በግምገማ ስም ስራውን እንዲለቅ፤ ከፍ ሲል ደግሞ ከአገሩ እንዲሰደድ አላደረጉትምን?
በመጨረሻም ዛሬ በፓስፖርት የጀመረው የመረጃ ቀደዳስ ነገስ በሌሎቹ  ጋጠ ወጦቹ የደህንነት ሰዎች በሌሎቹ የአገሪቱ ዜጎች የማይደገምበት ምንስ ዋስትና አለን? በእርግጥ የመታውቂያችን፤ የልደት፤ የጋብቻ፤ የንብረት፤ የትምህርትና ሌሎችም ሰነዶቻችን በመንግስት ሰዎች ስንኩልና ዕኩይ ምግባር ለአንዴና ለመጨረሻ ላለማግኘታችን ማስረጃችን ምንድር ነው? ይህም በመሆኑ ድርጊቱን የፈጸሙት ስርዓተ አልበኞቹና ጋጠ ወጦቹ የደህንነት የመንግስት ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡና ከዚህም ተግባራቸው ለወደፊቱ እንዲታቀቡ የም/ቤቱ ተወካዮች፤ የሚንስትሮች ም/ ቤት፤ የፍትህ ሚኒስቴር፤ ፖሊስና ዐቃቤ ህግ ጉዳዩን ትኩረት ችረው ውሳኔአቸውን ለሕዝብ እንዲያሳውቁ አጥብቄ እጠይቃለሁኝ። የደንበኞቹን ፍላጎ ት ለማርካት ሌት ተቀን የሚማስነው የኢትዮጵያ አየርመንገድስ ምነውዝም አለ ? ድርጊቱ የተፈጸመው በድርጅቱ ግቢም አይደል? ደንበኛ በስንኩሎች ሴራ ተመንገዱ ሲስተጓጎል ዝም ነው መልሱ? ድንቄም የመንገደኛን ምቾት ጠባቂ!! አልሰማንም እንዳይሉ የአሜሪካው ሬዲዮ የአማርኛው ክፍል፤ የጀርመኑ ዶቼ ወሌና የኢሳትና የኅብር ሬዲዮ እንግዳ ሆነው የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/ መንባበር ቃለ መጠይቅ መስጠታቸው ተደምጧል፤ ተዘግቧል።

ያልታሰረው ማን ነው??


ከአንተነህ መርዕድ
ሰሞኑን አንድ ኢትዮጵያዊ በቶሮንቶ የህሊና እስረኞችን ለመዘከር በግሉ አዳራሽ ተከራይቶ የአንዱዓለም አራጌን “ያልተሄደበት መንገድ” የሚለውን መጽሃፍ ለሽያጭ በአቀረበበት ቦታ ተገኝቼ ነበር። በዚህ አዳራሽ አንዱዓለምን፣ እስክንድርን፣ ርዕዮትን …ወዘተ ለመዘክር ብለው የተሰባሰቡ ሰዎች ብዛት ስመለከት “በእውነቱ እስረኞች እኛ ነን ወይስ እነ ዓንዱአለም?” የሚል ጥያቄ ጫረብኝ። አገርን ያህል ትልቅ ነገር ከራሳችን የፖለቲካና የግል ጠባብ ፍላጎት ዙርያ ቀንበበን ልንከተው ስንቸገርና አልሆንልን ሲል ደግሞ እርስ በርሳችን ስንጎነታተል አሁን አለንበት የመከራ ዘመን እንድንቆይ በራሳችን የፈረድን መሆኑ ግልጽ ይሆናል።
ትንሹን ህይወታቸውንና ጠባቡን የግል ፍላጎታቸውን በትልቁ ለሚያይዋት ኢትዮጵያ የሰውትን ወንድሞቻችንን ልናስታውስ በሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ ብዙዎቻችን በተረባረብንና የነሱን ከባድ መስዋዕት በትንሽ በትንሹ በተጋራናቸው ነበር። እውነቱ ግን ያ አይደለም። ለብዙዎች የእንቅስቃሴያችን ማዕከል ሁሉ “እኔ” ስለሆነ ከዚያ የተለየን ማውገዝ፣ ማደናቀፍ፣ አለመተባበር…ተግባራችን የሆነ ይመስላል።
አንዱዓለም እንዳለው ከዚህ በፊት ያልተሄደበትን የመቻቻልና የመከባበር መንገድ መጀመር የጊዜው ጠቃሚ እርምጃ ነው። ይህ ሁኔታ መጽሃፍ ቅዱስ ላይ የዮሃንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር3 እስከ 11 “ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘች ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርስዋን አቁመው መምህር ሆይ ይች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴ እንደነዚህ ያሉትን እንዲወገሩ በህግ አዘዘን። አንተስ ስለእሷ ምን ትላለህ? አሉት።….ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በደንጋይ ይውገራት አላቸው።…እነሱ ይህንን ሲሰሙ ህሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ” ይላል። ከኛም መካከል ህሊናው የሚወቅሰው ካለ ከተሳሳተ ድርጊቱ መቆጠብ አለበት። በዚሁ መጽሃፍ ቅዱስ የሉቃስ ወንጌል ላይም “በወንድምህ ዐይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፤ በራስህ ዐይን ግን ያለውን ምሰሶ ለምን አትመለከትም?” ሲል ይደግመዋል። እያንዳንዳችን የምንከተለው መንገድ ትክክል ሊመስለን ይችላል። የሌሎችን ሆነ የእኛን ትክክለኝነት የሚዳኘው ተግባራችንና ጊዜ ነው። እስከዚያው ግን መከባበርና መተባበርን የመሰለ ትልቅ ነገር የለም።
ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት ሰዎች ሆነ ተራው ግለሰብ የራሳቸውን ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ስህተት ላይ ብቻ ማተኮር ሲጀምሩ የውድቀታቸው መነሻ ይሆናል። ማንም ሰው ሲሠራ ሊሳሳት ይችላል። መጥፎው ነገር ከስህተት አለመማር ነው። ስህተቱን በጸጋ የሚቀበልና የሚያርም ትልቅ ነው። በእስልምና እምነትም ሃዲስ ላይ (በትክክል መጥቀስ ባልችል ይቅርታ ይደረግልኝ) እንዲህ ይላል “የማያውቅ ሆኖ የማያውቅ መሆኑን ማወቅ የማይፈልግ ቂል ስለሆነ ሽሸው። የማያውቅ ሆኖ አለማወቁን የሚያውቅ ከሆነ ልጅ ነውና አስተምረው። የሚያውቅ ሆኖ አዋቂ መሆኑን የማያውቅ ከሆነ ቀስቅሰው፤ ተኝቷልና። አዋቂ ሆኖ አዋቂነቱን የሚያውቅ ከሆነ ጥበበኛ ነውና ተከተለው” የብዙዎቻችን ባህሪ ባንዱ ሁሉ የሚካተት ነውና ቦታችንን ማወቅና እርምጃችንን ማስተካከል የተገባ ነው። ስለሆነም የታሰሩ ወንድምና እህቶቻችን የተሸከሙት እዳ ከግላችንና ከቡድናችን ፍላጎት በላይ አገራዊ ስለሆነ ከመጎነታተል፣ ከመከፋፈል ወጥተን አገራዊ ስፋት ባለው አላማ ዙርያ በጋራ መቆም ይኖርብናል።
ወደ ተነሳሁበት ርዕስ ልመለስና “ኢትዮጵያ የብሄረሰቦች እስር ቤት ናት” የሚለው ለትናንቶቹና ለዛሬዎቹ ጠባቦች መንደርደርያ ማዕከላዊ ሃሳብ ቢሆንም ደጋግመው እንደሚናገሩት ይህንን ብሂል በሃቅ ለብሄር ብሄረሰብ ነፃነት አልተጠቀሙበትም። ያ ቢሆን ምንኛ በታደልን። ድርጊታቸው ግን ተቃራኒ በመሆኑ ኢትዮጵያን ወደ ገሃነምነት ቀይረዋታል።
በአምደጽዮን፣ በፋሲለደስ፣ በቴዎድሮስ፣ በዮሃንስ፣በምኒልክ፣ በሃይለስላሴ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ማበብ ነበረበት ብሎ የሚያስብ አእምሮ ቅንነት አለው ብለን አንጠብቅም። እነዚህ ነገስታት ግዛታቸውን ለማስፋት፣ በስልጣናቸው ላይ ለመቆየት ባደረጉት እንቅስቃሴ ጭካኔ የተሞላበትን መንገድ መሄዳቸው ግልጽ ነው። በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እናስተዳድራለን ብለውም አያውቁምና የሚጠብቅም አልነበረም። ዳኝነታቸው ርህራሄና ፈሪሃ እግዜብሄር ያለበት እንዲሆን ሁሌ ባያከብሩትም ይናገራሉ፤ ህዝቡም ይጠብቃል።
ዛሬ በትናንት ታሪክ ታስረን፣ ለዚያ የከፋ ድርጊት ከመካከላችን ተጠያቂ ፍለጋ ስንኳትንና አጽም ለማውጣት መቃብር ስንቆፍር የሁላችን መቀበርያ አዳዲስ መቃብር እየተዘጋጀልን መሆኑን ዘንግተናል። በተለይም በዴሞክራሲ ስም እየማሉ የገዙን ሁለቱ ስርዓቶች ማለትም ደርግና ወያኔ ካለፉት ነገሥታት በባሰና በዘገነነ ሁኔታ ጨካኞች ናቸው። አገሪቱንም ወደ ሙሉ እስር ቤትነት የቀየሯት እነዚህ አምባገነኖች ያለፉትን አገዛዞች በኮነኑበት አንደበት የራሳቸውን ትልቅነት ከመስበክ ወደ ኋላ አላሉም። በነዚህ አገዛዞች “ኢትዮጵያ የዜጎች ሁሉ እስር ቤት ናት” የሚለው ከፀሃይ የደመቀ ዕውነት ነው።
ይህን ዓለም ያወቀውን እውነት በመካድ የትናንቶቹ አምባገነኖች መንግስቱ ኃይለማርያምና ፍቅረስላሴ ወግደረስ የነሱ አገዛዝ ፍትህ የሰፈነበት፣ ዴሞክራሲ የሞላበት የሚያስመስል ስንክሳራቸውን አሳትመው እንደጲላጦስ እጃቸውን ሊታጠቡ ይዳዳቸዋል። ፍቅረስላሴ “እኛና አብዮቱ”ባለው መጽሃፉ ቢያንስ ለታሪክና ለህዝብ ክብር ትንሽ የቅንንነት ጥፍጣፊ እንኳ ጨምሮበት ‘ሰርተን ያለፍነው ስህተት ይህ ነበር፣መጪው ትውልድ ከእኛ ስህተት ተምሮ መልካም አገር መገንባት አለበት’ የሚል እውነት በመጠኑም ይዞ ይቀርባል ተብሎ ሲጠበቅ ለብቻቸው ያዝዟቸው በነበሩት ሠርቶ አደር ጋዜጣ፣አዲስ ዘመን፣ የዛሬይቱ፣ ሄራልድ፣ ሬድዮና ቴሌቪዥን ላይ ሲያደነቁሩን የኖሩትን ፕሮፓጋንዳ ሃያ ሶስት ዓመታት ሲያመነዥከው ቆይቶ ለህትመት ሲያበቃ የህዝቡንም የማስታወስ ችሎታ መናቁን አሳይቷል። ፍቅረስላሴ በእስር ባሳለፈው ሃያ ዓመታት ወደ ኋላ በትዝታ መለስ ብሎ የሄዱበትን መንገድ ሁሉ በመቃኘት ወደ እውነቱ ቀርቦ መገኘት ሲገባው ሲታሰር ተኝቶ ሲፈታ የነቃ ይመስል። የኢትዮጵያ ህዝብ ቀድሞ ያለፈበትን የመከራ ዘመን ሆነ አሁን እየደረሰ ያለበትን ጭቆና ዳግም እንዳይመለሱ በመታገል ላይ እያለ ፍቅረስላሴ ባንኖ በመንቃት ድሮ የጻፈውም ሜሟር እንዳለ ይዘምርልናል። “በማይጨው ጊዜ የደነቆረ ስለማይጨው ሲተርክ ይኖራል” እንዲሉ ስልጣን ሲለቁ እንደደነቆረና ከዚያ ወዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ በምን አስተሳሰብ ላይ እንዳለ ለመገንዘብ ያልታደለ መሆኑ እንድናውቅ ያደርጋል።
ፍቅረስላሴ አሁን ድረስ የሚያመልክበትና በፍርሃት የሚያሸረግድለት መንግስቱ ኃይለማርያም ብቸኛ አላማው የሆነውን የስልጣን ጥማቱን ለማርካት የህዝቡን ለጋ ወጣቶች ብቻ ሳይሆን በእድሜና በልምድ መከበር የሚኖርባቸውን አዛውንት ኢትዮጵያውያንን፣ ጓደኞቹን ሳይቀር ተራ በተራ ሲያርዳቸው ቆሞ ሲንቀጠቀጥ፣ ማረጃ ሰይፍ ሲያቀብል እንዳልነበረ የነሱን የፍጅት ዘመን ከወያኔ ጋር እያነጻጸርን እንድንናፍቀው በተዘዋዋሪ ሊነግረን ይሞክራል።
የኢትዮጵያን ጠላቶች በየፈፋው ያርበደበዱት እነጄኔራል ታሪኩ ላይኔ፣አማን አንዶም፣ አምሃ ደስታ፣ ፋንታ በላይ ….ወዘት ዛሬ ተርፈው የተንሸዋረረ ታሪክ ሊነግሩ እንዳሉት በፍርሃት አልራዱም። አምባገነኑን አምባገነን ነህ እያሉ ነው የሞቱት። ታሪካቸውን ራሳቸው ባይናገሩም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ያውቀዋል። ሲያከብራቸውም ይኖራል። እነሱንና አገሪቱ የገደሉት የታሪክ ዝቃጮች ስለሥራቸው ምን ቀለም ቢቀባቡ ማንነታቸውን ሊደብቁ አይችሉም።
ለመሆኑ የአስራ ሰባት ዓመቱ የ“እኛና አብዮቱ” ውጤት ምን እንዳስገኘ ፍቅረስላሴ ይዘረዝረዋል? ህዝቡንና አገሪቱን ቀፍዶ አስሮ ለወያኔና ለሻዕብያ ያስረከበው ማን ነው? “ወርቅ ሲያነጥፉለት ፋንድያ የሚመርጥ” ብሎ መንግስቱ ሃይለማርያም የሰደበውን ህዝብ አንተም በተጠያቂነት ታቀርበው ይሆን?
አዎ ኢህአፓዎች፣ መኢሶኖች፣ወዝሊጎች፣ ማልሬዶች፣ ሻዕብያዎች፣ ወያኔዎች፣ ኦነጎች…..በዚች አገር ውድቀት አውቀውም ሆነ ሳያውቁ አስተዋጾ ማድረጋቸውን ለማወቅ ህዝቡ የፍቅረስላሴንና የጓደኞቹን ምስክርነት የሚፈልግ አይደለም። ምንም እንኳ ይህ ነበር የኛ ድርሻ ለማለት ድፍረቱን ባያገኙትም ህዝብና ታሪክ የሁሉንም አስተዋፆ አይረሳውም።
ቀበሌዎችን፣ የጦር ካምፖችን፣ መኖርያ ቤቶችን፣ ትምህርት ቤቶችን ሁሉ ወደ እስር ቤትነት የቀየረ፣ ወላጆች የልጆቻቸውን  አስከሬን ለመቀበል የተገደሉበትን ጥይት ዋጋ ያስከፈለ፣ አልቅሰው እርም እንዳያወጡ የከለከለ፣ አዛውንቱን ኃይለስላሴን ያለፍርድ ገድሎ መቃብራቸው ላይ መፀዳጃ ቤት የሰራ…ወዘተ ይህን ሁሉ ያደረገ የደርግ ስርዓትና መሪዎቹ የሌሎችን ያነሰ ስህተት የሃጢያታቸው መጠራረጊያ ፎጣ ሊያደርጓቸው የሚያስችል የሞራል ብቃት የላቸውም።
የመሬት አዋጅን እንደትልቅ ድል ደጋግሞ ማንሳቱም የሚገርም ነው። ብዙ ኢትዮጵያውያን የተዋደቁለ የመሬት ጥያቄ በደርግ ሆነ በወያኔ አልተመለሰም። አዋጁ መሬትን ከመሬት ከበርቴዎች ነጥቆ ገበሬውንና መሬቱን የአምባገነኖች ንብረት ነው ያደረገው። ወያኔዎችም ካባታቸው ደርግ ደህና አድርገው ተምረዋልና  ኢትዮጵያዊ የመሬት ባለቤት የሚሆነው “በኢህአዴግ ሬሳ ላይ ነው” ሲል መለስ ዜናዊ ደምድሞታል።
ከገበሬው የወጣን ነን የሚሉት የደርግ አባላት ሆኑ ለገበሬው ቆሜያለሁ የሚሉት ወያኔዎች በካድሬዎቻቸው አማካይነት ንብረቱና ራሱን ገበሬውን የራሳቸው የግል እቃ፣ በቤቱም ውስጥ እስረኛ አድርገውታል። በህብረት እንዲያርስ የተገደደውና በችጋር የተጠበሰው የአርሲ ገበሬ “በናንተ ህብረት እርሻ ያተረፍነው በርሃብና በተባይ ማለቅን ነው” ብለው ብልቃት ሙሉ ቅማል ለደርግ ባለስልጣን ማሳየታቸውን በወቅቱ በቦታው የነበርነው ጋዜጠኞች ተመልክተናል። ይህን እውነት በአብዛኛው  አገሪቱ ለሥራ በተዘዋወርሁባቸው ወቅት ባይኔ አይቻለሁ።
ደርግ የጀመረውን የአፈና መንገድ ወያኔዎች በረቀቀና በሰላ መልኩ ተጠቅመውበታል። የመሰረት ደንጋዩን ያስቀመጡላቸው ግን እነፍቅረስላሴ ናቸው። ወያኔ አገርን በመበተን ከደርግ የከፋ ቢሆንም የደርግን ዘመን የሚናፍቁ ካሉ የዚያ ስርዓት ተዋናዮችና ተጠቃሚዎች የነበሩ ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከሁለቱም አምባገነኖች የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይገባዋል።
ወደ ተነሳሁበት የእስር ጉዳይ ልመለስና በደርግ ሆነ በወያኔ መታሰርን በተደጋጋሚ ቀምሼዋለሁ። ለምን ታሰርሁ ብዬ አልቆጭም። ከህዝቡ መከራ የተጋራሁበት እውነተኛ የህይወቴ ምዕራፍ ስለነበር ባሰብሁት ቁጥር መጠነኛ የመንፈስ እርካታ ይሰማኛል። ሁለቱም ስርዓቶች በጣም ፈሪዎች ስለሆኑ በጣም ጨካኞች ናቸው። የተማሩትንና ለስልጣን ተቀናቃኝ ይሆናሉ ያሉትን ማሰርና በግፍ መግደላቸው እንዳለ ሆኖ በሁለቱም ስርዓቶች የሰባና የሰማንያ ዓመት በጤና የደከሙ ከፊሎችም ዐይናቸው የታወሩ አዛውንቶች ያለፍርድ እስር ቤት ቀስ እያሉ በሞት ሲያሸልቡ አይቻለሁ። መደገፍያ ከዘራቸውን ማንሳት የማይችሉትን አዛውንትና ክፉና ደግ የማያውቁ ህፃናትን የስርዓታቸው ተቀናቃኝ አድርገው የሚባንኑ አምባገነኖች ናቸው ሁለቱም።
ያ ሁሉ መጨፍጨፍ፣ ያ ሁሉ እስር የደርግን ስርዓት ከመፈራረስ፣ መንግስቱን ከመፈርጠጥ፣ ጓደኞቹን እነፍቅረስላሴንና ለገሰን እንደበግ ከመጎተት አላዳናቸውም። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ወያኔዎች ግድያውን፣ እስሩን ካስተማራቸው ከደርግ በባሰ ሰልጥነው ውድቀቱንም እየወረሱት ነው። የተፈጥሮአቸው እድገት ጣርያ (ክላይማክስ)ላይ ደርሰው ቁልቁለቱን ጀምረዋል። የገነቡት ሁሉ እየተናደ እንዳይቀብራቸው ራስን የማዳን ጥድፊያ ላይ ተጠምደዋል። ይህ መንፈራገጥ ግን የበለጠ ሚዛናቸውን እያሳታቸው ቁልቁል ይወረውራቸዋል። ሲወድቁ በሚያደርጉት መንፈራገጥ ብዙ ጉዳት ማድረሳቸው ግን የተጠበቀ ነው። የወያኔ የአጥቂነት ጊዜ አልፎበት አሁን በመከላከል ላይ ተጠምዷል። ጅኒው ከጠርሙሱ ወጥቷልና መልሶ የመክተት አስማት የሚሠራ አልሆነም።
ታላቁ ሩስያዊ ደራሲ፣ የታሪክ ምሁርና የሶብየትን አምባገነንነት አጥብቆ ይተች የነበረው አሌክሳንደር ኢሳየቪች ሶልዝሄንጺን የሩሲያውያንን መከራ ለዓለም በሚገባ ካሳወቀባቸው በርካታ ሥራዎቹ ዘ ጉላግ አርፒላጎ የዘረዘራቸውን ስናነብ ደርግና ወያኔዎች ያንን እያነበቡ የፈጸሙ ይመስለናል። በአንደኛው ጽሁፉ  “እኛ በሚሊዪን የንምቆጠር ሩስያውያን ሴቶችና ወንዶች ከቀን ቀን፣ ከዓመት ዓመት ራሳችንን ደፍተን ወደ እስር የምንጎተትበት ምክንያት ይህ ነው። የማስጠንቀቂያ ደወል አናጮህም። በጎዳናዎች ተቃውሟችንን አናሰማም። እንዲያውም በተቃራኒው በጎዳና ላይ በጓደኞቻችን ፊት ስንነዳ እኛ ግዞተኞች ምንም እንዳልተፈጸመብን ፊታችንን ቅጭም አድርገን አንገታችንን ደፍተን፤ እነሱ የነገ ግዞተኞችም እኛን እንዳያዩ ዐይናቸውን መሬት ላይ ተክለው እንተላለፋለን። ህዝባችን ይህንን ድርጊት ሂደቱን ሳያዛባ ተግባራዊ ማድረጉን ተክኖበታል። በብዙ ማሰቃየት የታጀበው ምርመራ ሲጠናቀቅ እኛ ትንንሾቹ አሳዎች መረባቸው ውስጥ ዋኝተን እንገባላቸዋለን። …ባህሩን የሞላን ጥሩ አሳዎች፤ የአጥማጆቻችንን መንጠቆ ጉሮሮአችን ውስጥ ለማስገባት የምንሽቀዳደም፤ እኛን በመጎተት እንዳይደክሙ  ወደ ላይ ቀዝፈን የምንቀርብላቸው…..” እያለ ለአምባገነኖች የመከራ ማገዶነት ምንም ሳይንፈራገጡ ወደ ማረጃው፣ ወደ እስሩ የሚሽቀዳደሙ ሩሲያውያንን የሸነቆጠበት አነጋገር እኔንም እንዳለንጋ መንፈሴን ይተለትለዋል።
በአሁኑ ሰዓት በመደበኛ እስር ቤቶች፣ በጦር ካምፖችና በድብቅ እስር ቤቶች የሚማቅቀውን ኢትዮጵያዊ ቁጥር ማወቅ ይከብዳል። በደፈናው እኛና ዓለም የሚያውቃቸው ደፋርና ለዴሞክራሲ ስርዓት ማበብ ከፍተኛ መስዋዕት በመክፈል ላይ ያሉትን አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ፣  አቡበከርና ጓደኞቹ ……እያልን ብንዘረዝር ቁጥራቸው የትየለሌ ነው።
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው በአካል የተገደቡ እስረኞች ናቸው ብንልም በመንፈስ ልዕልና ያላቸው ንፁሃን ናቸው። በእኔ አስተያየት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ቀሪው ኢትዮጵያውያን ነን እስረኞች እላለሁ። እስክንድር፣ አቡበከር፣ ውብሸት፣ ርዕዮትና አንዱዓለም በአካል ከታሰሩበት ወህኒ ዘልቀው በመንፈስ ነጻ መሆናቸውን አሳውቀውናል። ያሉበትን መከራ እንደ ኢምንት በመቁጠር የምንከፍለው ቀላል ነው እያሉ ምንም ለመክፈል ያልተዘጋጀነውን፣ ከዳር ቆመን በፍርሃት የምንርደውን ህሊናችን እንዲሞግተን በመተው ባለ እዳ አድርገውናል።
ርዕዮት፡ “በኢትዮጵያ ፍትህ ማጣትና ጭቆና የተንሰራፋ በመሆኑ ለህይወቴ አዳጋ ይኑረውም አይኑረው ለእውነት እቆማለሁ” ብላለች። ይብላኝ ለእኔና ለእናንተ ዳር ለቆምነው።
አንዱዓለም፡ “ያልተሄደበት መንገድ” በሚል ርዕስ ከእስር ቤት ጠባብ ክፍል በጻፈው መጽሃፉ “እስር የስቃይ ብቻ ቢሆንም ከነፃነትና ከዴሞክራሲ እጦት አይከብድምና በጸጋ መቀመል ነበረብኝ”  ሲል የአካል ስቃይን ፈርተን ህሊናችንን ለአሰርነው አማራጩን ይነግረናል። ከዚያም አልፎ “ይህ ሁሉ የመከራ ሸክም የማን ነው? የታሳሪ ፖለቲከኞች ብቻ ወይስ የነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን ሁሉ?”  በማለት የፍትህና የነፃነት ናፍቆታችን አፋዊ በመሆኑ ህሊናችን እንዲወቅሰን ጥያቄውን ወረወረልን።
እስክንድር፡ ሰሞኑል ለልጁ (ርዕሱ ለልጁ ይሁን እንጂ መልዕክቱ ለእኛ ነው) ከእስር ቤት በፃፈው ደብዳቤ “በጣም ናፍቄሃለሁ። እናትህንም ጭምር። ስቃዩ አካላዊ ስቃይ ብቻ ነው የሚሆነው። የቤተሰባችን ስቃይ ለረጂም ጊዜ መከራ ከተሸከመው ህዝባችን ተስፋ ጋር የተቆራኘ ነው።ከዚህ የበለጠ ክብርም የለም።ስቃዩን ሁሉ በመቋቋም፣ የሚቻለውን ሁሉ ርቀት በመሄድ፣ማንኛውንም አቀበት በመውጣት፣የትኛውንም ባህር በማቋረጥ ነፃነት ላይ በመድረስ ጉዞአችንን ማጠናቀቅ አለብን። ከዚህ ያነሰ ትግል ህሊናን ማደህየት (ባዶ ማስቀረት)ነው” ሲል ጽናቱንና የምንሄድበትን እርቀት አመልክቶን “አምባገነንነት ፍርሃት የነገሠበት በመሆኑ መንግስታዊ ሽብር፣ እስራትና ማሰቃየት ዋነኛ ተግባሩ ነው። በዚህ መንገድ ግን ሁሉንም ህዝብ ማንበርከክ አይቻልም። ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎችን የጥቃት ኢላማ በማድረግ ብዙውን ሰው በፍርሃት ማደንዘዝ ይችላሉ። በጥቁር ዓለም ጥንታዊ የመሆናችን የጋራ ኩራት ይህንን አስማት ለመጨረሻ ጊዜ እንድንሰብረው ያስገድደናል” ሲል በነሱ መታሰርና መሰቃየት ሩቅ ሆነን በፍርሃት ተሸብበን የታሰርነውን ሊፈታን ይታገላል።
ሌሎችም እስረኞች ደጋግመው በተለያዬ መልክ ያስተላለፉልን መልዕክት ይሄው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ህዝብ በአጠቃላይ እስረኛ መሆኑ ቢታወቅም ውጭ ያለነው እንኳ በፍርሃት፣ በራስ ወዳድነት፣ በክፍፍል፣ በመከነና የትም ባላደረሰን የትናንት አስተሳሰብና ከዚያም አልፎ በስሜታዊነት እስረኛ ነን። አንዱዓለም፣ እስክንድርና ሌሎችም የሚሉን ‘አሳሪ ሳይኖራችሁ ራሳችሁን ያሰራችሁ ራሳችሁን ነፃ አውጡና ትልቅ አገራዊ ዓላማ ይዘን አገር ነፃ እናውጣ’ ነው የሚሉን።
የጽሁፌ ማጠቃለያው ሁላችንም እስረኞች ነን።በመጀመርያ ራሳችንን ነፃ እናውጣ። ከዚያ የታሰሩ ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንንና አገራችንን ነፃ ማውጣት እንችላለን።
ግለሰብ ሆኖ በህሊናው፣ ድርጅት ሆኖ በአሰራሩ ነፃነት ከሌለው ለነፃነት ቆሜያለሁ ማለት ከአፋዊነት አይዘልም። እስከ አሁንም የሆነውና ያየነው ይህንኑ ነው። ራሳችን ለራሳችን የነፈግነውን ነፃነት ከአምባገነኖች በልመና አናገኝም።
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ!
ጸሃፊውን በamerid2000@gmail.com ማግኘት ይቻላል

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ደማቅ የተቃውሞ ትእይንት ተደረገ::


ሳዲቅ አህመድ
በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስኪድን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ዋናዋና ከተሞች ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!›› በሚል መሪ ቃል ህዝበ ሙስሊሙ እያካሄደው ያለው መስጂድ ተኮር የዘመቻ እንቅስቃሴ አካል የሆነው እና የዘመቻው ማጠናቀቂያ የጁምኣ የተቃውሞ ትእይንት በደመቀ መልኩ ተካሂዷል::Ethiopian Muslims protest, Addis Ababa (March 28, 2014)
ህዝቡን ከመስጂዱ ለመነጠል በመንግስት በኩል እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥና ኢ-ህገ መንግስታዊ ስራም ለራሱ ተረድቶ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማትና መስጂዶቹን በዒባዳ በማድመቅ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ወቅታዊና አንገብጋቢ የመስጂድ ባለቤትነትን የማረጋገጥ እንቅስቃሴ የመንግስትን እና የመጅሊስን ሴረኞች እንቅልፍ ማሳጣቱንም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ የውስጥ መረጃዎች እያጋለጡ ነው፡፡ ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!››ዘመቻ የዛሬው ጁሙአ ድረስ ቀጥሎ የቆየ ሲሆን በአዲስ አበባና በተመረጡ የክልል መስጂዶች ላይም አስቀድሞ የነበሩንን ቋሚ ትዝታ ጥለው ያለፉ ግዙፍ ተቃውሞዎችን በሚያስታውስ መልኩ የደመቀ የተቃውሞ ስነስርአት በማድረግ በሰላማዊ ሁኔታ ዘመቻው መጠናቀቁ ታውቋል::
በዚህም መሰረት ከቀኑ ስድሰት ጀምሮ በአዲስ ወደ አዲስ አበባ አንዋር መስኪድ እና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የተቃውሞ ወደተመረጡ መስኪዶች የተመመው ህዝበ ሙስሊሙ የመስኪዶችን ውስጥ እና ደጅ በመሙላት መስኪዶቹ የራሱ ሃብት መሆናቸውን እና ሙስሊሙ ህዝብ ሰላም ፈላጊ መሆኑን በደመቀ ተቃውሞ ነጭ ምልክቶችን በማውለብለብ ገልጿል::
ህዝበ ሙስሊሙ ዘመቻውን በተሳካ መልኩ በማድረግ ሰላማዊ ተቃውሞውን አሰምቶ ከኮሚቴው ጎን ዛሬም ቃሉን አክብሮ እንደቆመ በማሳየት በሰላም መመለሱን ለማረ

Ethiopian Journalists Forum (EJF) warns leaders of three Journalists Associations


by Betre Yacob
Ethiopian Journalists Forum (EJF), the newly established journalists association in Ethiopia, warned leaders of three journalists associations operating in the country.Ethiopian Journalists Forum is a nonpartisan and independent professional association
In a statement issued yesterday, the association accused the officials of Ethiopian journalists Association (EJA), Ethiopian National Journalists Union (ENJU), and Ethiopian Free Journalists Association (EFJA) of fabricating false accusations against the association and members of media organizations.
Ethiopian Journalists Forum is a nonpartisan and independent professional association intended to defend the freedom of speech and of the press in Ethiopia.
The press statement says that the officials have been deliberately engaged in fabricating false accusations ranging from terrorism to conspiracy— aiming to intimidate journalists and members of the association. “They are trying to spoil the name of our association, which is getting a wider acceptance among journalists and media workers”, the statement explains.
“For instance, in an interview published at Addis Admass weekly newspaper issued on March 30, 2014 they said that journalists had been preparing to commit terrorism against the nation and its citizens. They also accused two unnamed countries of backing the journalists. In another article published at Reporter, a weekly newspaper, issued on March 9, 2014 they once again said the same thing accusing journalists”, it further explains.
The statement says the association doesn’t have a response for the groundless accusations of these depraved individuals—who are barking to retain their own cheep benefits. It says it only would like to warn them once and for all to refrain from their unlawful acts.
The EJF was established on 20 January, 2014 considering the harsh working conditions of journalists in Ethiopia; and the importance of a unified media workers and journalists’ voice. In a few months only, the association has been able to get acceptance among journalists and media institutions.
Particularly, the EJF has been welcomed by almost all journalists operating in the free press. Its formation has been good news to those who wish to see an independent institution—which is loyal only to the journalists.
The EJF is supposed by many to be a best framework to work against the deteriorating press freedom in the country and bring about change on the safety of journalists. It is, however, seen as a threat by EJA, ENJU, and EFJA. According to the association, it has begun to experience their accusation since its inception.
The EJF has a vision to become a leading professional association in Ethiopia, which defends the freedom of speech and of the press as well as the rights of journalists.
The Wake of Non-operational Associations
Ethiopian journalists Association (EJA), Ethiopian National Journalists Union (ENJU), and Ethiopian Free Journalists Association (EFJA) were in active for a long period. They came to the stage following the formation of EJF.
Both the associations are accused of being loyal to the regime and of failing to play their role. None of them have ever been seen doing anything to bring about change on the deteriorating press freedom and safety of journalists.
Despite the fact that journalists are still subjected to violence, EJA, ENJU, and EFJA believe freedom of speech and of the press is respected in Ethiopia, and accuse CPJ and other international organizations of defaming the name of the country.
They also accuse Ethiopian journalists of using their rights to incite violence in the country. They even don’t accept the journalists, who are currently behind the bar in the country, are prosecuted because of their job.

The reason TPLF handing over Ethiopian land to Sudan

In this video during Tigray People’s Liberation Front (TPLF) 39th Anniversary Sudanese official exposed the relation b/n TPLF (Woyane) and the Sudan government, that explain the reason TPLF handing over chunk of fertile Ethiopian land to Sudan with a secret back door deals.