Friday, May 16, 2014

Cooperation for Fragmentation: Reflection on Ethiopians Conceptualization of Freedom and Independence


by Tsegaye Tegenu, PhD
I understand Ethiopians concept of freedom as to mean not to be restricted by others and not to be dependent on others. Since freedom is attained through community, we cooperate with others for the purpose of keeping our individual right to determine own actions. There is a relation between social co-operation and individual independence and freedom. In our case social cooperation is done for the purpose of ensuring our individual independence and right of doing whatever we love to do. We do not cooperate with those who do not respect our thoughts and actions. It is the individual and not the society which is the source of cooperation. If we want, we can scale up the individual right and independence to family,
community, ethnic and country levels. Injustice can easily be perceived, sensed and feel because we see no difference between us as individuals and the community we love. In scaling up process the essence is still the love for own freedom and independence, which is the mother of all kinds of social cooperation.
This habit of behavior and mindset has implication for economic development. Under the current Ethiopian economic situation and the state of the global economy, freedom means the right to specialization and interdependence. Cooperation is needed for interdependence and not for the promotion of individual independence. My view is that we find ourselves at a time in which the Ethiopian society needs organic cooperation and not the usual mechanical
cooperation grounded on the tradition of preserving individual independence.
I will try to ground my simple observation on empirical evidence which I analyzed in my research works. My first evidence comes from my current observation on the mechanism of economic progress in Ethiopia. Economic activities are chosen and organized in the Ethiopian society along the lines of two types of living organisms: rural households and firms in urban centers. The rural households are based on the land economy, while firms are based on capital/wage employment economy. I use the term living organism as a reference to underline their capability to response, self preserve, reproduce, grow and self-regulate in the process of resource creation and use in the society.
According to the recent 2012/13 agricultural sample survey of CSA (Central Statistical Agency) of Ethiopia, there are over 15 million agricultural households cultivating 17,5 million hectors of land. According to CSA definition “a household is considered an agricultural household when at least one member of the household is engaged in growing crops and/or raising livestock in private or in combination with others.” Be it a one person ousehold or a multi-person household (in fact over 90 percent is a multi person household), the person/s living in the household makes provision for their own living.
In rural Ethiopia households are a self-organizing beings. In my research I defined a household as a group of people who are organized themselves into families to occupy a separate farming and dwelling unit. Rural households are both a consumption and production units. The most important concerns of households is the security of household food supplies and cash needs. I have used different methods to standardize their consumption requirements and to estimate the quantity of resource needs. For example, a household can provide an average of four adult-equivalent labor and needs an average of four hector land to maintain the level of output needed for reproduction (an average of 12,8 quintal per subsistence household per year). The rural households are similar in purposes and live side by side. The question is what happens to their input and output proportional requirements and ratio as the their number increases over time.
Increase in Household Numbers in Rural Ethiopia, 1984-2013
As shown in Figure 1 in between 1984 and 2005 the household number increased by an average of 7,8% per year. Annually many new subsistence households are established and in a matter of one generation the number of agricultural households has more than doubled. The multiplication of the subsistence households increases the consumption requirements and land demand of the households and the number of subsistence labor. As their number and resource needs increases over time, the households intensified their co-operation for existence. The cooperation takes different forms including labor exchange, share cropping and land rent. For detailed empirical study you can down load our village report from http://people.su.se/~bmalm/Sodo.pdf.
As the household multiplied economic resources are fragmented and social cooperation is used as a means for peaceful existence of independent and self provisioning households. In cases where social cooperation could not manage the severity of resource scarcity, we observe armed conflicts, internal and international migration.
Experiences of other countries show that as the population growth pressure increases, there should be an increase in division of labor and specialization to introduce technology and increase labor productivity and mass production. What we observe in rural Ethiopia is the reverse: staunch effort to preserve the self provision mechanism and independent existence of the households. The EPDRF government is investing close to 15 billion Birr in this process of fragmentation with hope of changing the tide. What is at the root of all the household, however, is the freedom to be self sufficient (not to be dependent on others and not to be restricted by markets). What the evidence in the last 30 years show is that cooperation, coming from either the village or the state, nurtured the peaceful fragmentation of resources and household multiplications in the country. The household size numbering 15 million did not happen by miracle. Independent minded households received support from villages and governments. Rural household labor does not think what to specialize and how to be interdependent with others (market thinking). They prefer independence against the advantages of market interdependence.
My research experience in studying the habitual behavior of the business people and industrial firms is limited. Last year in Addis Ababa I presented a paper in a seminar and workshop on promoting industrial development in Ethiopia. I discussed about the construction of Special Economic Zones and Clusters and what Ethiopia can learn from Asian and European experiences. In a discussion following my presentation, a person whom claims to have many years of experience in the business sector and who himself is actively working for the promotion of the private sector in Ethiopia dismissed the relevance of cluster idea (geographical concentrations of economic and innovation activities) to Ethiopian conditions.
In my presentation I emphasized internal linkages, whereby cluster gains are furthered by local firm cooperation (joint action), local institutions and local social capital. Contrary to my model, the person underlined the need for industrial firms to work independently without trying to elaborate the advantages of operating in isolation. Since I understand the behavior of suspicion on claims and zero-sum cognition, I did not see any point in challenging his belief. I came to learn that I have to marshal a vast array of empirical evidence to convincingly argue about the advantages clusters in enhancing the individual capacities of small firms to access markets, acquire skills, knowledge, credit and information. I took it for granted that business people know from experience the advantages of connections between firms and institutions.
Political cases on the behavior of working independently or cooperating to work independently can be traced back to the Era of Princes (Zemene mesafint). By the beginning of the 19th century territorial aristocrats were dominant both in northern and southern Ethiopia. Kings were puppet in the hands of the territorial princes. For instance, King Tekle
Giorgis was dethroned six times in eleven years (1779-84, 1794-95, 1795-96, 1797-99, 1800). The territorial princes, though they were powerful, did not assume the title of King of Kings for practical reasons. Since regions were geographically very much interdependent, any expansion or contraction of a territorial power was at the expense of the neighboring power. Kings had to intervene to restrain and check conflicts among territorial powers. Kings had the ideological, traditional and legal grounds to intervene and restrain the territorial power. The Era of princes was the best political case of cooperation for fragmentation.
Emperor Tewedros, Yohannes and Menelik tried to standardized the system and created institutional interdependence and specialization. Their efforts of modernizing the political and military institution is currently interpreted as regional domination and ethnic subjugation. What is the point of “discovering the ethnic past” at a time when economic processes both at nation and globally level requires specialization and integration to promote technology and create mass production and employment.
The source lies in our habitual behavior to be independent and self reliance against all odds. What has happened to the multiplication of the rural households can happen to other instances. In fact those who advocate Ethiopian unity are also splintered into different political parties and they create forum or alliance (cooperation) to nurture their respective
organizational independence. Why? I do not mean that they should merge out of love; but I do not see the parties configuring what to specialize and how to be interdependent program wise.
Common to all Ethiopians including myself is the core habit of appreciating individual independence, no matter the level at which we project the idea. I am wondering why our mind remains static or fixed to this habit of “independence” no matter the costs while socioeconomic dynamic shifts overtime requiring new approaches and solutions? Global economy and consequences of population growth in Ethiopia require organic cooperation rather than mechanical cooperation used to nurture territorial/individual independence during the era of princes. In a country where I live (Sweden) administrative and economic actors are working hard to interconnect regions functionally thus making geographical division and administrative boundaries antiquated. Political parties are working on the idea and basis of “class struggle” to create unity among the people and create interdependence between party programs. What is the basis of our concept of freedom and independence? Is this concept fixed or relative changing with time? My view is that in a globalized world functioning on value chains and at a time of massive resource scarcity facing the Ethiopian people, freedom should lead to cooperation, specialization and interdependence.
I have not informally or formally discussed this idea with anyone and I apologize in advance for simplifying such sensitive issue.
For comments I can be reached at: tsegaye.tegenu@epmc.se

Messob Ethiopian Restaurant in Little Ethiopia,Los Angeles selected as Small Business of the Year in California


Messob Ethiopian Restaurant has been selected as Small Business of the Year in the State of California by the CaliforniaMessob Ethiopian Restaurant Google Map State Assembly. Messob Ethiopian Restaurant was selected by District 50 State Assembly member Richard Bloom. Messob Ethiopian Restaurant is one of 80 small businesses selected for 2014 from 3.3 million businesses in the State of California.
The ceremony will be held in Sacramento on June 16.
We would like to congratulate both bathers and owners of Messob Restaurant Berhanu Asfaw and Getahun Asfaw.
Click here to read California Small Business Assn. letter to Messob Restaurant.
Messob Ethiopian Restaurant

ኢትዮጵያዊነት ክፍል ሁለት ትግሬ ሆነህ አታንብበው (ሄኖክ የሺጥላ)


ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት ፣ ” መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚለው መጽሐፋቸው ላይ በሚደር ውይይት ካንድ ተሳታፊ ለቀረበላቸው ትያቄ ሲመልሱ፣
“አንዳን የሚያሳዝኑ ነገሮች ተነስተዋል እዚህ አካባቢ ነው መሰል ትግሬ ነኝ ያለ ልጅ አለ፣ ትግሬ ነኝ ብለሃል፣ እኔም ትግሬ ነኝ፣ ነገር ግን ልዩነታችን ትግሬ ሆነህ በማንበብህና ኢትዮጵያዊ ሆነህ በማንበብህ ላይ ነው። እውነት ነው፣ ትግሬነትን እያሰቡ እንደ ኢትዮጵያዊ መኖር አይቻልም፣ ኦሮሞነት ኢትዮጵያዊ ለመሆን ባሰበ ቁጥር የተበዳይነት እና የተገፊነት ስሜት የሚጭር ከሆነ በምንም መልኩ ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም። ፋሲለደስን ስንመለከት አማራ አደረሰብን የምንለው በደል ከሆነ ትዝ የሚለን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም ፣ አክሱምን ስንመለከት የትግሬዎች ክፋት ከሆነ ትዝ የሚለን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም፣ ሰንደቅ አላማችንን ስንመለከት አሁንም ሰንደቁ ከተሸከመው ምልክታዊ ትርጉም ውጪ የአማራነት መለኪያአንድን ጎሳ የጥፋት ብብሃር ታሪክ ካደረግነው አሁንም ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም። ስለ ብራና እና መሰንቆ ስናወራ ወደ አእምሮዋችን ቀድሞ የሚመጣው ቁሶቹ የኢትዮጵያውያኖች እሴት ስለ-መሆናቸው ካልሆነ ኢትዮጵያዊ መሆን ይከብዳል።Henok Yeshitla
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ ማርያም በዚሁ ከላይ በጠቀስኩት መጽሐፋቸው ላይ “ድሃነት የጥቃት መከታ መሆኑ የልማቱ መንገድ ፍጽሞ መክሸፉን የሚያረጋግጥ መንገድ ነው ” ይላሉ።
አዋ! የተጠቂነት ስሜትን አዝሎ የተጠያቂነት ባለቤት ነው ከምንለው አካል ጋ የፖለቲካ ውህደት ሲደረግ ጥምረቱ ሳይመሰረት ይፈርሳል ። ሁለት በፍጹም የተለያየ አላማ ያላቸው አካላት ፣ በጋራ ጠላትነት የሚፈርጁት አንድ የጋራ ጠላት ስላላቸው ብቻ ውህደታቸው መፍትሄ ያመጣል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። አንበሳም ጅብም ሚዳቆን አድነው ይበሉ ይሆናል፣ የሚዳቁ’ዐ ምግብነት ግን አንበሳ እና ጅብን ዘመድ አያደርጋቸውም ፣ ምክንያቱም በአመጋገብ ስርዓታቸውም ይሁን ፣ በተፈጥሮ ባህሪያቸው የተለያዩ ፍጥረቶች ናቸውና።
የተበዳይነትን ስሜት የትግል አላማው አድርጎ የተነሳ ድርጅት የተሸነፈው ሲመሰረት ነው። የተፈጠረበትን ምድር፣ መልካም ምድራዊ አቀማመጥ፣ የህዝቡን ባህል፣ ስነልቦናና ታሪክ ወደ ጎን ጥሎ ፣ መሆን አለበት ብሎ ስለሚያስበው ነገር ብቻ እያሰበ በርሃ የወረደ ታጋይ ቢያሸንፍም እንኩዋ ተሸንፎዋል ፣ ለዚህ ከወያኔ የተሻል ጥሩ ምሳሌ ማግኘት አንችልም። ግን ማሸነፍ ብለን የምንለው፣ መንበሩን መቆናጠጥ፣ ወዲህ ሂድ፣ ወዲህ ተመለስ የሚል ት’ዛዝን መስጠት ከሆነ እሱ ሌላ ነገር ነው። እንደምሳሌ ብዙ ግዜ የምሰማው እና የሚገርመኝ ነገር አለ። አብዛኛዎቹ የትግል አቀንቃኞች ” ወያኔን አሸንፈን መስቀል አደባባይ ተሰብስበን እንዲህ እናደርጋለን፣ እንዘፍናለን፣ አንተም ሄኖክ ግጥም ታነብልናለህ ወዘተ ወዘተ ሲሉ መስማት አሁን አሁን የተለመደ ነገር ሆኖዋል። ቁም ነገሩ እኮ መስቀል አደባባይ ላይ መደነስ አይመስለኝም ፣ዳንሱ የድሉ ማድመቂያ እንጂ የድሉ የመጨረሻ ግብ መሆን አለበትም ብዬ አላስብም። ሕልማችን ከድል አጥቢያ ጭፈራ ልቆ መሄድ ያለበት ይመስለኛል። ፍጹም ተገዢዎች ሆነን ሳለ ከድል ማግስት ስለምንረግጠው ጮቤ ከሆነ የምናስበው፣ ገና ስንነሳ ነው የወደቅነው። የትግል አላማ ከዚህ ሁሉ ፍሬ ከርስኪ ሃሳቦች ይልቃል የሚባለው ለዚያ ነው። ታግለው አሸንፈው ለውጥ ማምጣት በቻሉትና ምንም ባልተሳካላቸው ( እንደውም ወደ ባሰ መቀመቅ በመሩን) መሪዎቻችን መሃከልም ያለው ልዩነት ይሄው ነው ። የትግላቸው መነሻ እራሳቸውን ደርሶብናል ብለው ያሳመኑት በደል ሲሆን፣ መድረሻው ደሞ በቀል ነው።
ጆን ዶኔ (ትርጉም በቀብጽ እና በግርድፉ ) ብቻህን ተነጥለህ የምትኖር አንተ ማነ ነህ? ደንመና ውቂያኖሱን ቢጠርገው አውሮጳ ታንሳለች፣ የማንም ሰው ሞት እኔን ያጎለኛል ምክንያቱም ሰው ነኝና ምናምን ይላል ) በሱ ቁዋንቁዋ
No man is an island,
Entire of itself,
Every man is a piece of the continent,
A part of the main.
If a clod be washed away by the sea,
Europe is the less.
As well as if a promontory were.
As well as if a manor of thy friend’s
Or of thine own were:
Any man’s death diminishes me,
Because I am involved in mankind,
And therefore never send to know for whom the bell tolls;
It tolls for thee.
እኔም ከሱ የተለየ ስሜትም እምነትም የለኝም፣ ግን ሞትህ የሚያሳዝነኝ ቢያንስ ቢያንስ አንተ በኔ ሞት ባታዝን እንኩዋ ደስተኛ እስካልሆንክ ነው። አንተ ለኔ መቆም ባፀራ እንኩዋ ለጥፋቴ እስካልታተርክ ድረስ ነው። አዎ ሞትህ ያሳዝነኛል፣ በደልህ ያመኛል፣ ስቃይህ ይቆጨኛል፣ ግን ቢያንስ ቢያንስ የሃዘኔን ያህል ባይሆንም እንኩዋ የሰው ልጆች የመሆናችንን ያህል አንተም ለኔ ፍቅር ይኑርህ። እኛ ግን እንደዚያ አይነት አይደለንም እኛ
“ No man can Judge his agony against an objective scale, his toothache is more than a 1000 death in another part of continent “
እንዳለው አይነቶች ሆንን። ላይቤርያ ውስጥ አንድ ሺ ሰው አለቀ ሲሉን ” የራሳቸው ጉዳይ እኔ ጥርሴን አሞኛል ” የምንል ሆነን። የበደል ትንሽ የለውም፣ የሞት ግማሽ የለውም።
አንተ አንቦ ላይ ስትገደል ለምን አላዘንክም አትበለኘን ይልቅ እኔ ሌሎች ሲበደሉ ተሙዋግቼላቸዋለሁ ወይ ብለህ ራስህን ጠይቅ፣ እምነት ቢኖርም ባይኖርም በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም፣ ተሰፋፋሪ ሆኖ ከመኖር ግን የሚሻለው ተፋቅሮ መኖር ነው። ፍቅርን መሰረት ያላደረገ ትግል ፣ እሱም ላይ ሌላ ትግል እንዲነሳ ያደርጋል እንጂ የለውጥ ምሰሶ አይሆንም። በእርግጥ እወድሃለሁ፣ በእርግጥ ግማሽ ማንነቴ አንተ ነህ፣ ግን ፍቅሬን መሰረት አልባ አታድርገው፣ ካንተም፣ ከራሴም ፣ ከማውው ጥሩ ነገር ሁሉ ሃገሬን አስቀድማለሁ፣ ምክንያቱ ደሞ አማራ ወይ ኦሮሞ ስለሆንኩ አይደልም፣ ምክንያቱ እኔና አንተ አላፊና ጠፍ መሆናችንን ስለማውቅ ነው። ስለዚህ አስብ ይሄ የምለውን ነገር ትግሬ ሆነህ አታንብበው ይልቁንስ ኢትዮጵያዊ ሆነህ አንብበው።

ተቃውሞ እና ጭፍጨፋ በኦሮሚያ (ተመስገን ደሳለኝ)


ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ዕለተ-ሐሙስ፤ ሚያዚያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም የታሪካዊቷ አምቦ ከተማ ጀንበር አዘቅዝቃ ሰማዩ መቅላት ሲጀምር፣ ከወትሮው ለየት ያለ ጉዳይ በሰደድ እሳት ፍጥነት ጠቅላላ የዩንቨርስቲ ግቢውን አዳርሶ ተማሪውን ከባድ ሃሳብ ላይ ጣለው፡፡ ሌሊቱ ዕኩሌታ ላይ የግቢው ኦሮምኛ ተናጋሪ ተማሪ በሙሉ ስለጉዳዩ መረጃው እንደደረሰው ያረጋገጡ ጥቂት አስተባባሪዎች በተረፈችዋ ሰዓት ቢያንስ ጎናቸውን ለማሳረፍ ወደየመኝታቸው ሲያዘግሙ ተስተዋሉ፡፡ …ነገስ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን? አንዳቸውም ይህን አስቀድመው የማወቅ መለኮታዊ ፀጋ አልነበራቸውም፤ የሚያውቁት በግቢው ስታዲዮም ለመሰብሰብ ቀጠሮ መያዛቸውን ብቻ ነው፡፡ ከዚያስ? አንድ ስሙን መናገር ያልፈለገ የዩኒቨርስቲው ሁለተኛ ዓመት ተማሪ እና የተቃውሞው አስተባባሪ ክስተቱን በእኔ ብዕር እንዲህ ይተርክልናል፡-
አርብ
የንጋት ፀሐይ ዓይኗን ከመግለጧ በፊት ተማሪው አንድ፣ ሁለት… እያለ በቀጠሮው ቦታ መሰባሰብ ጀመረ፡፡ ረፋዱ ላይም ምልአተ ጉባኤው የተሟላ መሰለ፤ ኦሮሞ ያልሆኑ ተማሪዎችም አብረውን ነበሩ፡፡ ከዚያም ‹በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙት ሱሉልታ፣ ቡራዩ፣ መናጋሻ፣ ለገጣፎ፣ ለገዳዲ፣ ገላን፣ ዱከም እና ሰበታ ከኦሮሚያ ክልል ተወስደው ከአዲስ አበባ ጋር ሊቀላቀሉ ነው› ስለሚባለው ጉዳይ፣ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በቦታው የተገኙት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ምትኩ ቴሶ ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠየቅን፡፡ ፕሬዚዳንቱም በቂ ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡ ግና፣ እንቅስቃሴያችን እምብዛም ጠንካራ አልነበረምና ተከታዮቹ ሶስት ቀናት ያለፉት የጎላ ድምጽ ሳይሰማ በተለመደው ፀጥታ ውስጥ ነበር፡፡
ማክሰኞ
ከምሳ በኋላ ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ አድፍጦ የነበረው የተቃውሞ ድምጽ ድንገት ፈንድቶ በዩኒቨርስቲው ሰማይ ስር ናኘ፡፡ ከሶስት ቀናት በፊት በሰላማዊ መንገድ ላቀረብነው ህጋዊ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ የሚሰጠን አካል በማጣታችን ቁጣችን ከመቅፅበት ሰማይ ጥግ ደረሰ፡፡ በሰከንዶች ሽርፍራፊም ግቢው ከዳር እስከዳር በመሬት አርድ ጩኸት ተናወጠ፡፡ መፈክር እያሰማን፣ በታላቅ ሆታ እየዘመርን፣ ከአሁን አሁን የሚያነጋግረን ባለሥልጣን ይመጣል ብለን ስንጠብቅ ባልገመትነው አኳኋን ከአንገት በላይ እና ከጉልበት በታች ድንጋይ መከላከያ ያጠለቁ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግቢውን ከብበው ውጥረቱን ይበልጥ አባባሱት፡፡ በዚህ አስፈሪ ድባብ ውስጥ በሚከት የከበባ ቀለበት አስገብተውን ለደቂቃዎች ያህል ሁኔታውን ሲያጤኑ ከቆዩ በኋላ ድንገት ወደ ግቢው በመዝለቅ መብቱን በሰላማዊ መንገድ እየጠየቀ የነበረውን ተማሪ እያሳደዱ ፍፁም በሆነ ጭካኔ በቆመጥ አናት አናቱን እየቀጠቀጡ በወደቀበት ይረጋገጡት ጀመር፡፡ እግሬ አውጭኝ ብለን አጥር እየዘለልን ሽሽት ከጀመርን መሀል ዕድለቢሶቹ በአይን ፍጥነት እየተወረወሩ በቆመጥ ወገብን ከሚሰብሩና በወታደራዊ ስፖርት በዳበረ ክንዳቸው ጨምድደው ይዘው መሬት ላይ ከሚደፍቁ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ማምለጥ አልተቻላቸውም፡፡ ብዙዎቻችን ግን ባለ በሌለ አቅማችን ሮጠን ባቅራቢያው ወደሚገኝ ጫካ ገብተን ተደበቅን፡፡ ዕለቱም ምንም እንኳ ህይወት ባይከፈልበትም፣ በድብደባ፣ ሽብር፣ ዋይታ ተጥለቅልቆ ሲተራመስ አለፈ፡፡
ረቡዕ
የትላንቱ የፌደራል ፖሊስ ተገቢ ያልሆነ አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ያስቆጣቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በብዛት ከእኛ ጎን ከመቆማቸውም በላይ ጥያቄውም በአራት ተባዝቶ አደገ፡፡ እነሱም ‹ኦሮሚኛ የፌዴራል ቋንቋ ሊሆን ይገባል፣ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ፊንፊኔ መሆን አለበት፣ አማራና ትግሬ ከክልላችን ይውጡልን፣ የጨፍጫፊው ምኒልክ ኃውልት ይፍረስ› የሚሉ ነበሩ፡፡ ይሁንና ቅንጣት ታህል ርህራሄ ያልፈጠረባቸው ፖሊሶች ህፃን-አወቂ፣ ሴት-ወንድ ሳይመርጡ መደብደብ መጀመራቸው፣ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን እያቀረበ የነበረውን ሕዝብ ስሜታዊ አድርጎት ጎማ ማቃጠል እና መንግስታዊ ቢሮዎች ላይ ድንጋይ እስከ መወርወር ደረጃ አደረሰው፡፡ ይህን ጊዜም በእንዲህ አይነት ሕዝባዊ ተቃውሞ ወቅት አነጣጥሮ ተኩሶ በመግደል የተካነው ‹‹አግአዚ›› ተብሎ የሚጠራው ክፍለ ጦር ድንገት ደርሶ ከተማዋን የቀለጠ የውጊያ ቀጠና አስመሰላት፡፡ ከዚህ በኋላማ ምኑ ይወራል! ምህረት የለሾቹ አነጣጥሮ ተኳሽ የአግአዚ አባላት ቀጥታ ወደ ሕዝቡ ጥይት በማርከፍከፍ አምቦን ከመቅጽበት በደም-አበላ አጠቧት፡፡
በዩኒቨርስቲያችን ግቢ በር እና አበበች መታፈሪያ ሆቴል አካባቢ ብዛት ያላቸው ሰዎች በጥይት ወድቀው ተመልክቻለሁ፡፡ ከተማሪዎችም መካከል ቢያንስ አስር የሚሆኑት መገደላቸውን በዓይኔ በብረቱ ያየሁት እና ከጓደኞቼም ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል፡፡ ዛሬም ድረስ (28/8/06) የት እንዳሉ የማይታወቅ ተማሪዎች መኖራቸውን ሰምቻለሁ፡፡…በዚህ ጽሑፍ የማነሳውን አጀንዳ በደንብ ግልፅ ለማድረግ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ከተካሄዱት ሕዝባዊ ተቃውሞዎች መካከል አንድ ማሳያ ልጨምር፤ ወለጋ፡፡ ደህና! ይህንንም ክስተት እንደ አምቦው ተማሪ ስሙን መግልፅ ላልፈለገው የወለጋ ዩንቨርስቲ መምህር ብዕሬን ላውሰውና እንዲህ ያውጋን፡- በወለጋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብሔርን መሰረት ያደረገ ውጥረት እንደ አዲስ ለማገርሸቱ የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ፡፡ በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ወቅት በባሕር ዳር የተከሰተው ቋንቋን መሰረት ያደረገ የጥላቻ ዘለፋ እና የአኖሌ ሐውልት ምርቃት ዋነኛዎቹ ሲሆኑ፤ ከአካባቢው ነዋሪዎች እንደሰማሁት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከደንቢዶሎ ቡና ጭኖ የተነሳ አንድ ኤፍ.ኤስ.አር መኪና ‹ጎጃም ላይ ተዘረፈ› ተብሎ በከተማዋ የተናፈሰው ወሬም ተጨማሪ ቤንዝን የሆነ ይመስለኛል፡፡ ወደ ተቃውሞው ትዕይንት ደግሞ እንለፍ፡፡
ማክሰኞ
እንደሚታወቀው የወለጋ ዩኒቨርስቲ በነቀምት፣ ግምቢ እና ሆሩ ግድሩ ካምፓሶች የተከፈለ ሲሆን፤ ሰሞነኛው ተቃውሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳው በዕለተ ዓርብ በዋናው የነቀምት ካምፓስ ውስጥ ነው፡፡ ኦሮምኛ ተናጋሪ ተማሪዎች አዲሱን ማስተር ፕላን በተመለከተ ላቀረቡት ጥያቄ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ፍቃዱ በየነ ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ይጠይቃሉ፡፡ ሀገር ውስጥ እንደሌሉና ወደ ቻይና ማቅናታቸው ይነገራቸዋል፡፡ በዚህም ተበሳጭተው በተቃውሞ ጩኸት ታጅበው ግቢውን ለቀው ለመውጣት የሞከሩ ቢሆንም፣ ከአጥር ውጪ ባደፈጡ የከተማዋ ፖሊሶች ትዕዛዝና ማስፈራሪያ ወዲያውኑ ተበታተኑ፡፡ በመጪው ሰኞም የሶሻል ሳይንስ ትምህርት ብቻ በሚሰጥበት የግምቢው ካምፓስ ለመገናኘት ውስጥ ለውስጥ ይነጋገሩና ቀጠሮ ይይዛሉ፡፡ በዚህ መልኩ በተጠቀሰው ዕለት በግምቢው አዳራሽ የተሰበሰበው የሁለቱ ካምፓስ ተማሪ የነቀምቱን ጥያቄ ለዲኑ ያቀርባል፡፡ ነገር ግን ተማሪውና ዲኑ መግባባት ላይ ካለመድረሳቸውም በተጨማሪ ጥቂት ተማሪዎች ለድብደብ በመጋበዛቸው ስብሰባው ያለምንም ውጤት ይበተናል፡፡ ዕለቱም ፍሬ አልባ ሆኖ ያልፋል፡፡
ረቡዕ
በዚህ ቀን ከሰዓት በኋላ ተማሪው ግቢውን እየዞረ በከፍተኛ ድምፅ ‹‹ቡራዩ ኬኛ፣ ሰበታ ኬኛ፣ ለገዳዲ ኬኛ….›› እያለ ተቃውሞውን በሰላማዊ መንገድ ሲገልፅ ዋለ፤ ምሽት ላይ ግን ድንገት መንፈሱ ተቀይሮ ያልተጠበቀ መልክ በመያዙ፣ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሆኖ የዋለውን ሂደት ከማደፍረሳቸውም በላይ፣ የአካባቢው ተወላጅ ያልሆኑ ጥቂት የማይባሉ የንግድ እና መኖሪያ ቤቶችን ወደ መዝረፍ ተሸጋገሩ፡፡ በማግስቱ ወደ ዩኒቨርስቲው ግቢ ሄጄ ስለሌሊቱ ክስተት የኦሮሞ ተወላጅ ከሆኑ ባልደረቦቼ ጋር ስንወያይ፣ ቢያንስ ዘረፋውን ይኮንናሉ ብዬ ስጠብቅ፤ በተቃራኒው ‹‹ንብረታቸውን ነው ያስመለሱት፤ ሀጢአት አልፈፀሙም!›› በማለት ድርጊቱን ሲደግፉ በመስማቴ በእጅጉ ተገረምኩ፡፡ ከተማዋም ቀኑን ሙሉ ለተቃውሞ በወጡ ነዋሪዎቿ መናጧን ቀጠለች፡፡ አልፎ ተርፎም በግምቢ አቅራቢያ ባለችው የጉትን ወረዳም የአንድ ብሔር ተወላጆች በአስቸኳይ አካባቢውን ለቀው ወደ ክልላቸው እንዲሄዱ በሚጠይቁ ተቃዋሚዎች ተጨናንቃ እንደዋለች ስሰማ፣ ያ ሀገሪቱን አንድ ቀን ሊያፈራርሳት እንደሚችል ሲነገርለት የነበረው ብሔር ተኮሩ ፌዴራሊዝም ዕውን መሆኛው ጊዜ በጣም እንደቀረበ ስለተሰማኝ የቀኑ ግርምቴ በከባድ ፍርሃት ተተካ፡፡ ምክንያቱም የዚህች ወረዳ አብላጫው ነዋሪ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው አይደለምና ሊፈጠር የሚችለው ትርምስና ዕልቂትን መገመት የሚከብድ አይመስለኝም፡፡
ሐሙስ
በግምቢ ከተማ ኦሮሞ ያልሆኑ ነዋሪዎችን ንብረት መዝረፉ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከፍተኛ ፍርሃት በመንገሱ የብሔሩ ተወላጅ ያልሆንን ሰዎች ከቤታችን መውጣት አልቻልንም፡፡ እቤት ውስጥ ምግብ የማሰናዳት ልምዱ ስለሌለኝ ቁርስም ምሳም ምንም ሳልቀምስ በመዋሌ ረሀብ ክፉኛ እየሞረሞረኝ ነው፤ እንደዚያም ሆኖ ወደ ምግብ ቤቶች ለመሄድ ድፍረቱ አልነበረኝም፡፡ ተከታታይ የጥይትና የዋይታ ድምፅ ያለማቋረጥ በቅርብ ዕርቀት ይሰማኛል፡፡ በርግጥ ዘግይቶ እንደተረዳሁት በነቀምት ፖሊሶች ተገድሎ፣ በማግስቱ ወደመኖሪያው ግምቢ ማርያም ሠፈር አካባቢ አስከሬኑ ከመጣ አንድ ተማሪ በቀር ስለተገደሉ ሌሎች ሰዎች የሰማሁት ምንም ነገር የለም፡፡ የሆነው ሆኖ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት አከራዬ ከራሳቸው ቤት ምግብ አምጥተውልኝ ረሀቤን ማስታገስ ቻልኩ፡፡ እኚህ ከዘር ሐረግ መዘዛ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ የሰጡ ደግ ኢትዮጵያዊት እናት ወደውጪ እንዳልወጣ መክረውና አፅናንተውኝ ቢሄዱም፣ ሌሊቱስ እንዴት ያልፍ ይሆን? እያልኩ በጭንቀት ተጠፍንጌ ስገላበጥ አደርኩ፡፡ ልክ ጎህ ሲቀድም ጨርቅ-ማቄን ሳልል ቀጥታ ወደ ትውልድ ቦታዬ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ፡፡
ኦሮምያ-የጦር ቀጠና?
ባለፉት ሁለት አስርታት ሊካዱ ከማይችሉ ሀገራዊ እውነታዎች አንዱ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው ከሌላው አካባቢ ኢትዮጵያውያን በተለየና በከፋ መልኩ ለሞት፣ ለስቃይ፣ ለእስር፣ ለስደት… ተጋላጭ ሆኖ መቆየቱ ነው፡፡ ሰሞኑን በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙ ዜጎች ላይ የደረሰው ርህራሄ አልባ ጭፍጨፋም የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው፡፡ የተቃውሞው መነሾ ‹በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ሰባት የኦሮሚያ አነስተኛ ከተሞች በአዲስ ማስተር ፕላን ወደ ፌደራል መንግስቱ መቀመጫ ሊቀላቀሉ ነው› መባሉን ተከትሎ ስለጉዳዩ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ አለመሰጠቱ ያስነሳው ቁጣ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የአዲስ አበባውን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የስምንት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በእንቅስቃሴው ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በአምቦ፣ ወለጋ፣ መደወላቡ እና ሐሮማያ ደግሞ
ከሌሎቹ በተለየ መልኩ ተቃውሞው ጠንከር ያለ ነበር፤ ከተማሪዎቹ በተጨማሪ የከተሞቹ ነዋሪዎችም መቀላቀላቸው ተስተውሏል፡፡
አገዛዙም ይህንን አስታክኮ ‹‹ንብረት ማውደም››፣ ‹‹ባንክ መዝረፍ›› ገለመሌ በሚሉ ውሃ በማይቋጥሩ ምክንያቶች የበርካታ ዜጎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡ ይሁንና ይህንን መሰሉ ሕዝባዊ ተቃውሞን የእነ አባይ ፀሀዬ እና በረከት ስምኦን መቀለጃ የሆነው ሕገ-መንግስት እንኳ ሊከለክል እንደማይችል ይታወቃል፡፡ አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳም በሳምንቱ መግቢያ ላይ ለ‹‹ቪኦኤ›› ራዲዮ ‹‹በሁሉም አካባቢ ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ፍትሓዊና ሕጋዊ ነው›› ሲል የተናገረበት መግፍኤ ይኸው ነው፡፡ ሆኖም ሀገሪቱ ለዘመናት ተፈራራቂ አምባገነን ገዥዎቿን አቀማጥላ መሸከም የማይታክታት ኢትዮጵያ ናትና፣ የጭፍጨፋው መሪዎችም ሆኑ አስፈፃሚዎቹ በሕግ እንደማይጠየቁ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ እዚህ ሀገር ከሥርዓቱ የተለየ የፖለቲካ አቋም የሚያራምደውንም ሆነ ሰላማዊ ተቃውሞ አድራጊዎችን መግደል አያስኮንንም፡፡ ግፋ ቢል አባዱላ ገመዳ ለጠቀስኩት ራዲዮ ጣቢያ ‹‹መንግስትም ሐዘኑን ገልጿል፤ እኔም በቦታው ደርሼ አይቻለሁ፤ አዝኛለሁ!›› ሲል ከገለፀው የለበጣ ንግግር አይዘልም፡፡ ግና፣ እስከ መቼ ወገኖቻችን እየታሰሩ፣ እየተሰቃዩ እና እየተገደሉ ዝምታው እንደሚቀጥል ግራ አጋቢ ነው፡፡ …ይህ አይነቱ ነውረኛ ድርጊት በኦሮሚያ እንግዳ ባይሆንም፣ አጀንዳችን የተቃውሞውን ገፊ-ምክንያት መፈተሽ በመሆኑ፣ ከሁለት የቢሆን መላምቶች (Sinarios) አኳያ በአዲስ መስመር ለማየት እሞክራለሁ፡፡
አዲሱ መንፈስ
የክልሉ አስተዳዳሪ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ከተቃውሞው ጀርባ ሊኖረው የሚችለውን ድርሻ መፈተሹ ቀዳሚው ነው፡፡ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች የውዝግቡ መነሾ ዕቅድ በአቶ መለስ ዜናዊ የመጨረሻ ዘመን የተዘጋጀ እና የኦህዴድ መሪዎችም ያለአንዳች ጥያቄ ለማስፈፀም አምነው የተቀበሉት እንደነበረ ያስታውሳሉ፡፡ በርግጥም መለስ የቱንም ያህል ከሕገ-መንግስቱ እና ከፌዴራል ስርዓቱ የሚቃረን ነገር ማድረግ ቢፈልግ፣ ለሁሉም የግንባሩ አባል ድርጅቶች አመኑበትም አላመኑበትም በፀጋ ከመቀበል ውጪ ተቃውሞ ቀርቶ፣ ጥያቄ ለማቅረብ መሞከሩ የሚያስቀስፍ ሀጢያት እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ይህንንም ዕቅድ ያለ ኦህዴድ ስምምነት አዘጋጅቶ ሲያበቃ፣ ለከፍተኛ አመራሮቹ በተለመደው ያሰራር ትዕዛዝ ተላልፎ ተግባራዊ የሚሆንበትን ወቅት ሲጠብቅ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ዛሬ እርሱ ከሕይወት አፀድ በመለየቱ ጊዜው ተቀይሮአል፤ አገዛዙም ከግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት ወደ ቡድናዊ አምባገነንነት ተሸጋግሯል፤ በዚህም የዕዝ ክፍተት በመፈጠሩ፣ ያያኔው ኦህዴድ ‹‹አሜን›› ብሎ የተቀበለውን ዕቅድ፣ ዛሬ ወደታች ለማውረድ ሲሞክር ጠንካራ ተቃውሞ ቢያጋጥመው ያልተጠበቀ ክስተት አይሆንም፡፡
በአናቱም ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ወዲህ የኦነግ መዳከም ተስፋ ያስቆረጣቸው በርካታ ወጣቶች፣ ክልላዊ ጥያቄያቸው በኦህዴድ በኩል መልስ እንዲያገኝ ለመሞከር ድርጅቱን የተቀላቀሉ ስለመሆኑ ተደጋግሞ በፖለቲካ ተንታኞች መነገሩ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ልባቸው ከኦህዴድ ይልቅ ለኦነግ የቀረበ አባላት በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ በትምህርታቸው ገፍተው፣ በድርጅቱ መካከለኛ የሥልጣን እርከን ላይ የመገኘታቸው አጋጣሚ፣ ‹ከኦሮምኛ ተናጋሪውም ሆነ ከኦህዴድ እውቅና ውጪ የተዘጋጀ ኢ-ሕገ መንግስት› ሲሉ የኮነኑትን ዕቅድ በመቃወም ተማሪውን ከጀርባ የሚያነሳሱበት ዕድል መኖሩን ሌላው ዓብይ መላምት አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡ በርግጥ በዚህ መስመር በርትተው ቢሄዱ፣ ሥርዓቱ ካነበረው ፌዴራሊዝም አኳያ መብት እንጂ ሕገ-ወጥነትም ዘውገኝነትም አለመሆኑ አያከራክርም፡፡ እንዲያውም የአንድ ወቅት ጠርዘኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች የተሰበጣጠረ ተቋማዊ አቅማቸውን በዚህ መልኩ ለመፈተሽ ከሞከሩ፤ ለልባቸው ከአባዱላ ይልቅ ሌንጮ ይቀርባልና፣ ለቀጣዩ ምርጫ ኦቦ ሌንጮ ሸገር ከደረሰ የሚሆነውን ለመገመት ከባድ አይመስለኝም፡፡ …እነዚህ ሁለት ትንተናዎችም የሚያስማሙን
ከሆነ፣ ኩነቱ ኦህዴድን ወደሚከፋፈልበት ጠርዝ መግፋቱ አይቀሬ ነው ብለን ልናምን እንችላለን፡፡የሆነው ሆኖ እንደ ኦህዴድ ምንጮቼ፣ መካከለኛ ካድሬዎቹ ከጉዳዩ ጀርባ መኖራቸውን የሚጠቁመው፣ እንዲህ በሰላይና በአንድ ግዙፍ ፓርቲ መዳፍ ስር ባደረች ሀገር ንቅናቄው ያለእንከን ከአምቦ እስከ ሐረር፤ ከወለጋ እስከ ባሌ፤ ከቡራዩ እስከ አዳማ… መስፋፋት የመቻሉ ምስጢር አንዱ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በርካታ የከተማ ሰዎች በተሳተፉበት የአምቦውና የወለጋው ሕዝባዊ ንቅናቄ በላኤ-ሰቡ ‹‹የወገን›› ጦር በወቅቱ ለቅሞ ካሰራቸው ሰላማዊ ዜጎች በቀር፣ እንቅስቃሴውን ማን አስተባበረው? እንዴትና በምን መልኩ? የሚለው ጥያቄ በደፈናው የፈረደባቸው ተቃዋሚ ድርጅቶችን እና የውጭ ኃይሎች ላይ ከመደፍደፍ ያለፈ ምንም የታወቀ ነገር አለመኖሩ ነው፡፡ የኦህዴድ የበታች ካድሬዎችም ይህንን መሰል ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ እንደተለመደው ከመኖሪያ ቤታቸው የሚታፈሱትን ዜጎች ቁጥር ለመቀነስ የሄዱበት ርቀት በጎ ጅምር ይመስለኛል፡፡ ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ ቢያንስ ኦሮምኛ ተናጋሪ መኮንኖችና ወታደሮች ‹ከአብራኩ በተገኘን ሕብረተሰብ ላይ አንተኩሰም› የሚሉበት ታሪካዊ ቀን ይቃረባል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ከዚህ በግልባጩ አባዱላ ገመዳ ለሶስት ቀናት ያህል የሕዝባዊ ንቅናቄው ማዕከል በሆነችው አምቦ ከተማ ተገኝቶ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እና በአካባቢው ዙሪያ ካሉ 18 ወረዳዎች የተሰባሰቡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይቶ ‹መግባባት ላይ ደርሷል› መባሉ በመንግስት ሚዲያ ተነግሯል፡፡ ይህ ግን የልጆች ዕቃ-ዕቃ ጨዋታ መሆኑ ከራሱ ከአባዱላም የተሰወረ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ይህን መሰል ተቃውሞ በገጠመው ቁጥር ‹ተግባብተናል› የሚለው በካድሬ መዋቅር ከሚሰበስባቸው አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር ተወያይቶ እንጂ ከጥያቄ አቅራቢዎቹ ጋር አለመሆኑ የተለመደ ነውና፡፡ እንዲህ አይነቱ ‹‹ውይይት›› ሲጠናቀቅም ‹‹የእገሌ ከተማ ነዋሪዎች ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴውን አወገዙ››፣ ‹‹አጥፊዎቹ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠየቁ››፣ ‹‹የፀረ-ሰላም ኃይሎች እጅ አለበት አሉ›› እና መሰል ዜናዎች እስኪቸኩ ድረስ መተላለፋቸው ነባር ስልቱ ነው፡፡ ሰሞኑንም የታዘብነው ይህንኑ ነው፡፡
ስውሩን እጅ ፍለጋ
ከመጀመሪያው መላምታችን በተቃራኒው ሊጠቀስ የሚችለው ተማሪዎቹን ለተቃውሞ ቀስቅሶ ለዘግናኙ ጭፍጨፋ የዳረጋቸው የአገዛዙ ስውር እጅ ሊኖር ይችላል የሚለው ጥርጣሬ ነው፡፡ ይኸውም አብዮታዊው ግንባር ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የግብፁ ሆስኒ ሙባረክ እና የሊቢያው ሞሀመር ጋዳፊን የመሳሰሉ ጉልበታም መሪዎችን ሥልጣን ያሳጣው የአረቡ የፀደይ አብዮት ያነቃቃቸው ኢትዮጵያውያን በምርጫ ፖለቲካው ረገድ ካላቸው ጥቁር ታሪክ አንፃር በተመሳሳይ መንገድ መንግስት እንዲለወጥ ይሞክሩ ይሆናል የሚል ስጋት ላይ ከመውደቁ ጋር ይያያዛል፡፡ ለዚህም ከእነ እስክንድር ነጋ እስከ ሶስቱ ጋዜጠኞችና ‹‹ዞን ዘጠኝ›› ጦማሪዎች ድረስ በአርምሞ የተመለከትነው የጅምላ እስር አይነተኛ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በዚህ ስሌትም የኢህአዴግ የቀድሞ አመራር ‹‹ጦርነትን እንሰራለን!›› እንዲል፤ ከቀጣዩ ምርጫ አስቀድሞ ታማኝ በሆኑ የኦህዴድ ካድሬዎች አማካይነት ተቃውሞውን ቀስቅሶታል ወደሚል ጠርዝ እንገፋለን፡፡
ይህ አይነቱ ስልት በ97ትም መተግበሩን የሚያሳየን፣ ለብጥብጡ ተጠያቂ የተደረገው የቀድሞው ቅንጅት የሰኔውም ሆነ የጥቅምቱ የአደባባይ ተቃውሞን እንዳልጠራ በማስረጃ አስደግፎ ማቅረቡ ነው፡፡ ከዚህም አኳያ ተማሪዎቹንና የከተማ ነዋሪውን ስሜታዊ እንዲሆኑ ገፋፍቶ፣ ጥቂት የመንግስትና የግል ንብረቶች እንዲወድሙ ካደረገ በኋላ ጭፍጨፋውን አካሄዷል ብለን መገመታችን አይቀሬ ነው፡፡ በሰሞኑ ዘግናኝ እልቂትም የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀሩ በአምቦ እና አጎራባቿ ተኪ ብቻ ከአርባ በላይ ንፁሃን በአደባባይ የጥይት እራት መሆናቸውን ዘግበዋል፡፡ በበኩሌ ገዥው ግንባር በእንዲህ ያለ ዲያብሎሳዊ ሥራ በመላ አገሪቱ ፍርሃት በማንበር፣ ውስጣዊ መፈረካከሱን ሸፍኖ ምርጫውን እንደ መለስ ዜናዊ ዘመን ያለጎላ መንገራገጭ በአሸናፊነት ማለፍን አላማው አድርጎ እየሰራ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ሌላው ቀርቶ በድህረ-ምርጫ 97 በዕድሜ ከገፉ አዛውንት እስከ የአስር ዓመቱ ህፃን ነብዩ ድረስ ለፈፀመው ግድያ ምክንያት ያደረገውን ‹ባንክ ለመዝረፍ መሞከር›፤ ከአስር ዓመት በኋላም በአምቦና ጉደር አካባቢ ከልጆች እናት እስከ አስር ዓመት ህፃን ድረስ ያሉ ንፁሀንን ረሽኖ ሲያበቃ ምክንያቱ ይኸው መሆኑ ግጥምጥሞሽ አይመስለኝም-አንዳች ስውር መልዕክት ለማስተላለፍ አስቦ ያዘጋጀው እንጂ፡፡ በርግጥም ጉዳዩን ለጥጠን ካየነው የ97ቱን ጭፍጨፋ በቀጥተኛ ተሳታፊነት ለመገንዘብ ያልደረሱ (አሁን ዕድሜያቸው 18/19 ዓመት ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል) ሰሞኑን በዘጠኙ ዩንቨርስቲዎች ለተቃውሞ የወጡ ወጣቶች እና ከአንድነት እስከ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፎች የተሳተፉ በዚሁ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ለውጥ ፈላጊዎች (በብዛት ሥራ-አጥ ወጣቶች) የመኖራቸውን ሀቅ ህወሓት መረዳቱ ሌላ ቀጣይ አስር የሥልጣን ዓመት ዕውን እስኪሆን ድረስ ለመቅጣት መፈለጉ ነው፣ በኦሮምያ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎችን ሳይቀር ያለምህረት በጥይት እስከመጨፍጨፍ ያደረሰው ልንል እንችላለን፡፡
ኦሮሞ ብቻውን?
ሰሞነኛው የኢህአዴግ ወታደራዊ ጭፍለቃ እና ተያያዥ ጉዳዮች የኦሮሞ ጥያቄን መልሶ ወደ ጠረጴዛ ለማምጣት ገፊ መራራ ፅዋ ሊሆን ችሏል፡፡ ብዙ የኦሮሞ እናቶችን ደም እንባ ያስለቀሰውን ይህንን አሳዛኝ ክስተት ተከትሎ ድምፃቸውን ካሰሙ የብሄሩ ልሂቃን መካከል ኦቦ ሌንጮ ለታ ያስቀመጣቸው ነጥቦች፣ ወቅቱን ተንተርሰን ልንነጋገርባቸው የሚገቡ እንደሆኑ አምናለሁ፡፡ ‹‹ኦሮሞ ሲጨፈጨፍ ሌላው የሕብረተሰብ ክፍል ዝም ሊል አይገባውም፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ላይ የደረሰው ነገ በሌላውም ላይ ይደርሳልና›› የሚለው የመጀመሪያው ጭብጥ ነው፡፡ በህወሓት የብረት ክንድ ስር ያሳለፍናቸው ሃያ ሶስት አመታት፤ ኦሮምኛ ተናጋሪውን ዋነኛው ግፉዕ ቢያደርጉትም፣ ሌሎቻችንም የአገዛዙን ግፍ እንደየድርሻችን ተጋርተናል፡፡ ከኦጋዴን እስከ ትግራይ፣ ከጋምቤላ እስከ አፋር፣ ከደቡብ እስከ አማራ. የሥርዓቱ ምህረት አልባ ክንድ ህልውናውን ያላደቀቀውን የትኛውንም ቋንቋ ተናጋሪ ማግኘት ዘበት ነው፡፡ ይህም ሆኖ የዘመናዊት ኢትዮጵያን ምስረታን ተከትሎ፣ በብዙዎቹ አካባቢዎች የተስተዋለው የየዘውጎቹ የማንነት መለዮ መናድ፣ አንድም በየቋንቋው ተናጋሪ ልሂቃን ስልጣንን ያሰላ ትንታኔ እና የገዢው ስብስብ ተቋማዊ መልክ መስጠት፤ የአንዳችንን መከራ ሌላኛችንን እንዳይሰማን (እንዳያመን) ሳያደርገን አልቀረም፡፡ ያሳለፍናቸው ሩብ ክፍለ-ዘመን ሁለት ቀሪ ዓመታት ግን፣ ህመሞቻችን ልንጋራ፣ ስለጋራ ህልውናችን እንድናሰላስል፣ አልፎም አንዱ ላይ የሚርከፈከፈው የደመ ቀዝቃዞቹ ጥይት የእኛንም ቁስል እንዳመረቀዘ እንድናምን የሚያደርጉ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ ለዚህም አሁን ያየነው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ስቃይ የሁላችንም መከራና ቁስል ነውና በደምና በዜግነት ስለቆመው ጠንካራው አሀዳዊ ማንነታችን ስንል፤ በሕብረት ድምፃችንን ከፍ አድርገን ልናሰማ፣ አብረናቸውም ልንጮኽ ግድ ይለናል፡፡
ሌላው ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ፣ ኦሮምኛ ተናጋሪው ብቻውን ይህን ስርዓት ሊጥልም ሆነ የተሻለች ሀገር ሊገነባ እንደማይጠበቅበት ማመን ነው፡፡ ‹‹ስለቀጣይቱ ኢትዮጵያ ሁሉን ያሳተፈ ውይይት እናካሂድ›› የሚለውን የሌንጮን ሰሞነኛ ጥሪ “እህ” ብለን በንቃት ልናደምጠው ይገባል፡፡ እርሱና ጓዶቹ ያመጧቸውን የፖለቲካውን ክስረት የሚያሻግሩ ሀሳቦችን እየገሩ መሄድ፣ ወቅቱን ተንተርሰን በጽሞና ልናስብበት እንደሚገባ አምናለሁ፡፡ የኦሮሞ ጥያቄ ከሌሎቹ ዘውጎች ጩኸት ተለይቶ ለብቻው እልባት ሊያገኝ አይችልም፤ ‹ኦሮሞ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ በማድረጉ ረዥም ጉዞ ላይ ዋነኛው አዋጪ መሆን አለበት› የመሰሉትን አቋሞች ለተሻለች ኢትዮጵያ ልናውለው የምንችለው፣ እንደሰሞኑ ባለ የብቻ የዘውጉ መከራ ፊት ዝምታችንን ሰብረን ስናብር ነው፡፡ ይህ ሂደትም፣ ቅጥ-ያጣውን ወታደራዊ ስርዓት ለማስቆም ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ልንዘነጋ አይገባም፡፡ ቀድሞስ ነገር ታንጎ ለብቻ የሚደነሰው እንዴት ተሆኖ ነው?
ምንጭ ኢትዮሚድያ

እናስራችኋለን? ለካንስ የነአጅሬ ጋጠወጥነት ከድንበርም ተሻግሯልና!


ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
በሀገራችን ባደመነው አጠቃላይ የሀዘን ድባብ ሳቢያ ፈገግታ እያማረኝ ፈገግ ለማለት ምንም ዕድል ሳላገኝ ብዙ ሰሞኖችን ባጀሁ፡፡ ዕድሜ ለዚህ ነገረኛ ኢሳት የሚባል ቴሌቪዥን ዛሬ ማታ ግና በሣቅ የሚያፈርስ ዜና ሰማሁና ምሽቱን ብቻ ሳይሆን ትዝ ባለኝ ቁጥር ሌቱን ሁሉ በሣቅ ስፈርስ አደርኩ – የግራ ጎን አጥንቶቼ ክፋይ ጉድ እስክትለኝ፡፡ ሣቅ ጥሩ ነው፡፡ አንዳንዴ በሣቅ የሚገድል ነገር ማግኘት የመታደል ያህል ነው፡፡ እውነተኛው ሣቅ ሞቶ ቢቀበርም ወያኔን መሰል ጅላንፎ ጉጅሌ የሚሠራቸው አንዳንድ ነገሮችን በመታዘብ ለጊዜውም ቢሆን ፈገግ መሰኘት ሲያስፈልግም ሆድን ያዝ አድርጎ በሣቅ መንፈርፈር ሰውነትን ያፍታታል፤ ወቅታዊ እፎይታንም ይሰጣል፡፡ እኔ – እውነቴን ነው – ለብዙ ጊዜ ያጣሁትን ሣቅ ዛሬ አገኘሁትና ከልቤ ተዝናናሁ፡፡ ወያኔ እኮ አልታወቀለትም እንጂ ደምበኛ የኮሜዲ መፍለቂያ ውድብ ነው፡፡ ልዩ የኢትዮጵያ ቻርሊ ቻፕሊን ሆነው የለም እንዴ!President Salva Kir of Sudan
ይህን የወያኔን ሞኝነት ጉዳዩ ለሚመለከተው የዓለም ክፍል ያንጸባረቀ ጉዳይ ለፖለቲካችን ቅርብ የሆነ ሰው ባያጣውም ለእንደኔ ዓይነቶች የማይሞላላቸው አንዳንድ ባዘኔዎች ማስታወሱ ደግ ይመስለኛል – ‹ቦዘኔ› እንዳላልኩ ይታወስልኝ፡፡ ብዙ ሰው እኮ የማይሞቀው የማይበርደው ሆኗል፡፡ ደንዘናል፤ በቁም ሞተናል፤ ‹ብታምኑም ባታምኑም› ብዙዎቻችን ከሰውነት ተራ ወጥተን የአምልኮተ ንዋይ ሰለባዎች ሆነናል፡፡ በሀገር ውስጥ ትንሽ ትልቁን ብታዩት ከሞላ ጎደል ሁሉም ሊባል በሚችል ሁኔታ ገንዘብ እንዴት ሊያገኝና በአቋራጭ ሊከብር እንደሚችል ሲጨነቅና ሲጠበብ ይታያል፡፡ ኅሊና ብሎ ነገር ጠፍቷል፡፡ ወንድም ወንድሙን፣ እህት እህቷን እስከመግደል በሚደርስ ሰይጣናዊ ጭካኔ ተሞልተን እየተፋጀን ነው፡፡ ወያኔ በቀደደው የጥፋት ጎዳና እየተመምን ከሰውነት ደረጃ በሚያስወጣ የሀብት ፍቅር ተነድፈን ልንጨራረስ የቀረን ጊዜ ሩብ ሐሙስ ቢሆን ነው፡፡ አልተነሳሁበትም እንጂ በዚህስ ትንሽ ባወራሁ፡፡
ወያኔም ባቅሙ አስታራቂና የሰላም አባት ሆኖ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎችን በዕርቅ ለማስማማት አዲስ አበባ ይጠራቸዋል፡፡ ሳልቫኪር የሚሉት ባለባበሱና በዐይነ ውኃው ፊውዳላዊ አምባገነን የሚመስለኝ አማቻችን ሰውዬና ዶክተር ማቻር የሚባለው ሞገደኛ ሰውዬ ወደ አዲስ አበባ መጥተው (እንዳሁኑ ሁኔታ ደግሞ በመስፈራርቾ ተጠርተው) ሼራተን ሆቴል ሁለት ክፍሎች ውስጥ ይመሽጋሉ – ‹አማቻችን› ያልኩት የሳልቫኪር ይሁን የማቻር ልጅ የኛን ሀገር ልጅ እንዳገባ/ች በሚዲያ ስለሰማሁ ነው፡፡ ድርድሩም በወያኔ ጉጅሌ አማካይነት ተከናወነ ይባልና የዕርቁ ስምምነት ተፈረመ ተብሎ በወያኔው ቱሪናፋ ሚዲያዎች ይለፈፋል – (ከብቱ ወያኔ በሰሞኑ ጭፍጨፋው የጠለሸ ስሙን ያደሰ መስሎት በገባበት ወጥመድ የኋላ የኋላ ራሱ ገብቶበት ተተበተበበት እንጂ)፡፡ የወያኔ ኢትዮጵያ ለራሷ ብቻ ሣይሆን ለጎረቤት የሚተርፍ ሰላምና ዴሞክራሲ መጋዘኗ ውስጥ ጢም ብሎ እንዳለና ለሱዳንም፣ ለሶማሊያም፣ ለግብጽም፣ ለሦርያም፣ ለአፍጋኒስታንም፣ ለኢራቅም፣ ለቬንዝዌላም፣ ለ“ዴሞክራክ ሪፓብሊክ” ኮንጎም፣ ለሤንትራል አፍሪካ “ሪፓብሊክ”ም፣ ለሃይቲም፣ ለኡክሬንና ራሽያም፣ ለሰሜን ኮሪያም፣ ለ‹ኤርትራ›ም፣ ለሊቢያም፣ ለፓኪስታንም፣ ለበርማም፤ ለፍልስጥኤምም፣ (እንዴ፣ ዓለም ለካንስ በትርምስ ላይ ናትና ጎበዝ – የወያኔ የሰላም በረከት የሚላክላቸው ሁከት የነገሠባቸው ሀገሮች ዝርዝር አላልቅልኝ እኮ አለ!) ኤክስፖርት ለማድረግ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች በነዚሁ በእውነት ዕርሙ የወያኔ ሚዲያዎች ከጥንፍ እስከ ጥንፍ ተስተጋባ፡፡ እኛም ይሄ የቤት ቀጋ የውጪ አልጋ የሆነ የወሮበሎች ቡድን ምን መተት ቢኖረው ይሆን እንዲህ ዓለምን ጉድ ባሰኘ መልክ የሰላም አባት ሊሆን የበቃው ብለን ተገረምን፡፡ የገዛ “ዜጎቹ”ን ባልተወለደ አንጀት እየጨፈጨፈና የስምንት ዓመት ሕጻን ሣይቀር ደረቱን በጥይት ዝናብ እየበሳሳ ባለበት ወቅት እንዲህ ያለ ሰላም ለሱዳናውያኑ ማስገኘቱ በርግጥም አንዳች ነገር አለው አልንና በጣም ተደነቅን፡፡ ኢትዮጵያችንም ስሟ ታደሰልን ብለን ደስ አለን – ደስታችን አንድ ጀምበር እንኳን ሳይዘልቅ ጠወለገብን እንጂ፡፡
ነገሩ ለካንስ ሌላ ኖሯል፡፡ ሳልቫኪር ሀገሩ እንደገባ ለሀገሩ መገናኛ ብዙኃንና ለባለሥልጣናቱ ሲናገር እንደተደመጠውና በሚዛናውያን ሚዲያዎች ሲዘገብ እንደተከታተልነው የሰላሙ ስምምነት የተፈረመው በወያኔ አስገዳጅነት ነበር፡፡ የአስገዳጅነቱ አካሄድም ነው በአስቂኝነቱ ወደር ያልተገኘለት፡፡
ከፍ ሲል እንደተገለጸው ወያኔ ሁለቱን ሰዎች ሼራተን ውስጥ በሁለት የተለያዩ ክፍሎች ያስቀምጣቸዋል፡፡ ፊት ለፊት ሳይገናኙም በተላላኪ ሃሳብ እንዲለዋወጡ ያደርጋል፡፡ መገናኘት ያልፈለጉት ምናልባት ራሳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ እንገምት፡፡ ወያኔ ግን የሁለቱ ሰዎች ያለመታረቅና ዕርቁን በፊርማ ያለማጽደቅ አዝማሚያ ሲገባው ያቺን የጫካ ህግ በመምዘዝ “ካልፈረማችሁ እዚሁ አስራችኋለሁ፤ ወደ ሀገራችሁ መሄድ ህልም እንደሆነባችሁ እንደነ እስክንድር ነጋና ርዕዮት ዓለሙ ከርቸሌ ትወረወራላችሁ፤ ከዚህ የሚያወጣችሁ አንድም ኃይል የለም” ብሏቸው ያርፋል፡፡ ይህ ያላሳቀ ምን ሊያስቅ ይችላል? እንዴ፣ በዚህማ ድዳችንን ተወቅረንም ሆነ ተነቅሰን መሣቅ አለብን፡፡ ግሩም እኮ ነው እናንተ ሆዬ!
ትርፋ ትርፉን እንተወውና ቃል በቃል ወያኔ ያላቸው “ስምምነቱን በፊርማችሁ ካላጸደቃችሁ ትታሰራላችሁ!” የሚል ነው – ከሌሎች የማስፈራሪያ አንድምታዎች ጋር፡፡ አስገዳጁ ደግሞ ራሱ ተገድዶ ቤት ጠባቂ የሆነው ደሳለኝ ነው አሉ – ማነው – ኃይለማርያም – ከአለቆቹ በተነገረው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መሠረት፡፡
ልብ አድርጉ! እነዚህ ሰዎች – እነሳልቫኪር – አነሰም አደገም የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር መሪዎች ናቸው – አሁን ቢጣሉምና ከሁለት አንድኛቸው ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው መንግሥት በመምራት ላይ መገኘቱ እንዳለ ሆኖ፡፡ ወያኔን ታዲያ ምን ገጠመው? ይህችን እጅ እየጠመዘዙ ማስፈረምን ከሀገር ደረጃ አውጥቶ አህጉራዊ ቅርጽ እንዲኖራት የማድረግን ከፍተኛ ጉጉት ማን አሳደረበት? “የገቡበት የፖለቲካ ቀውስ የሚሠሩትን አሳጥቷቸው ለአንዳች የፖለቲካ ትርፍ ብለው ይሆን እንዲህ ያለ ‹ሪስክ› ውስጥ የገቡት?” ብዬም ተጨንቄላቸዋለሁ – ለወያኔዎቹ – እንዲያ ካልሆነ መቼም ጡት ያልጠባ ማለቴ ያልጣለ ሕጻን ሣይቀር መዘዙን ጠንቅቆ ሊገምተው የሚችለውን ይህን የመሰለ ጅልነት ውስጥ ባልገቡ ነበር፡፡ አሁን አስገድዶ ቢያስፈርማቸው ወደሀገራቸው ሲመለሱ ጉዱን ማለትም ምሥጢሩን እንደሚያወጡት እንዴት ወያኔዎች ሊገምቱ አልቻሉም? እንዴትስ ቢንቋቸው ነው? በኛ የለመዱትን ንቀት እኮ ነው በ‹ኮፒ ፔስት› እነሱም ላይ እውን ያደረጉት፡፡ በውነቱ እነዚህን የመርገምት ፍሬዎች ሰው ናቸው ብሎ መቀበል እንዴት ይቻላል? ኢትዮጵያ በታሪኳ እንዲህ ያለ አሣፋሪ ነገር የፈጸመባት በስሟ የተቀመጠ “መንግሥት” የለም፡፡ እዚህ ላይ አንዲት ብጫቂ ማሳሰቢያ አለችኝ፡- በተለይ ኢሳቶች ይህንን የወንበዴ ጥርቃሞ ቡድን “የኢትዮጵያ መንግሥት” እያላችሁ በዜና ዕወጃችሁ የምትናገሩትን ነገር ባፋጣኝ ብታርሙ ይሻላል፡፡ ይህ ‹መንግሥት› መንግሥት ሣይሆን የከተማ ሽፍታ ነው፤ በአንድ ጎሣ የተዋቀረ፣ ለአንድ ጎሣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ያደረ፣ ለዓለም አቀፍ የውንብድና ተቋማት የሰገደና አንዲትን ሀገር ከነሕዝቧ መቀመቅ ለማውረድ ታጥቆ የተነሣን ወሮበላ የአማጊዶዎችን ስብስብ መንግሥት ማለት በመንግሥት ተቋማዊ ምንነት ላይ መቀለድ ነው፡፡ ስለዚህ ቢያንስ “የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬው” በሚል ቢነገር የተሻለ ነውና አንዳንድ ወገኖች አታቁስሉን፡፡ የነሱው ይበቃናል፡፡
አንድ ፈረንጅኛ አባባል አሁን ትዝ አለኝ፡፡ A man cat take a horse to a river; but twenty cannot make it drink. ወዳማርኛው ሲመለስ – አንድ ሰው አንድን ፈረስ ወደ ወንዝ ሊወስደው ይችላል፤ ሃያ ሰዎች ግን ውኃ(ውን) እንዲጠጣ ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ የወያኔ ቂልነት፣ የወያኔ ባልጩት ራስነትና አባጉልቤነት እዚህ ላይ ነው፡፡ እነሱ የሚያስቡት ነገር ሁሉ ገዢ ይመስላቸዋል፡፡ የድንቁርናቸው መጠን በምንም ምድራዊ መለኪያ የሚሠፈር አይደለም፡፡ በመንግሥትነት ለሃያ ሦስት ዓመታት የቆዬ አንድ ኃይል የዚችን ፊርማ መነሻና መድረሻ ከነመዘዟ ጭምር ካላወቀ ትልቅ የአስተሳሰብም እንበለው የአመለካከት ችግር አለ ማለት ነው፡፡ እንዲያው ግን ኢትዮጵያ ምን ያህል ብትረገም ፣ እኛም ምን ያህል ባንታደል ይሆን ፈጣሪ እነዚህን ሰዎች የሰጠን? አይጨንቅም? ሳስበው በጣም ይጨንቀኛል – ማይግሬይን የተሰኘውን ከፍተኛ ራስ ምታት የሚለቅ ችግር ነው የገጠመን፡፡
የዚህ ችግር መባቀያ ደግሞ ውስብስብ ነው፡፡ ምዕራባውያንም ይጠየቁበታል – አሉበትና፡፡ ማፈሪያ የሰውነት አካል እንደወያኔው የላቸውም እንጂ ካላቸው በእጅጉ ሊያፍሩበት ይገባል፡፡ በብዙ ነገር እየደገፉ ከበረሃ ወደ ቤተ መንግሥት ያስገቡ ኃይሎች ቆም ብለው ሊያስብቡበት የሚገባ ወቅት ላይ መድረስ የሚገባቸው ይመስለኛል፡፡ እኛን ማመን ስላልፈለጉ እስካሁን አላመኑንም፡፡ የወያኔን ጉድ ቢያውቁትም እንደዚህ ቁልጭ ብሎ የወጣበት ዘመን ባለመኖሩ ይህን ሃቅ ማመን ባይፈልጉና በቆዬ ወያኔን የመደገፍ አቋማቸው የሚጸኑ ከሆነ ከሌላ ከማንም ጋር ሣይሆን ከገዛ ኅሊናቸው ጋር የሚጣሉበት ጊዜ እየደረሰ መሆኑን እየመረራቸውም ቢሆን መገንዘብ አለባቸው፡፡ ወያኔ የአንድን ሉዓላዊ ሀገር ፕሬዝደንት “አስርሃለሁ!” ካለና ካለውድ በግዱ ካስፈረመ ከዚህ በላይ ዓለም አቀፍ ውንብድናና ማፊያነት የለም፤ ወያኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፕሬዝደንታዊ ስብዕናንና ሀገራዊ ክብርን የሚነካ እንዲህ ያለ ጠያፍ የማንአለብኝነት ተግባር ከፈጸመ የገዛ ምድሩን ዜጎች ምን ሊያደርግ እንደሚችል ማንም ወገን በዚህ ኹነት አማካነት ሊረዳ ይገባዋልና ይህ የሰሞኑ ወያኔያዊ ቅሌት ውርደታዊ ክስተት ለሀገራችን በጎ ገጽታ አለው (ፈረንጆቹ blessing in disguise እንደሚሉት ማለቴ ነው)፡፡ ይህ ነገር እንደሚመስለኝ ወያኔን ብቻ ሣይሆን ምዕራባውያንንም ከነሤራዊ ተንኮላቸው ለማጋለጥ ፈጣሪ ያመቻቸው ነገር መሆን አለበት፡፡ ከፍ ሲል እንደጠቆምኩት ዓለም እስኪታዘበን ድረስ የወያኔን አምባገነንነትና ገዳይነት ስናጋልጥ ብንቆይም ያመነን አልነበረም፡፡ የማቻርንና የሳልቫኪርን ምስክርነት ግን ሊጠራጠር የሚገባ ሰው አይኖርም ብዬ እገምታለሁ ፤ ምንም እንኳን እነሱ ራሳቸውም የአፍሪካዊ አምባገነንነት ወረርሽኝ ሰለባ ቢሆኑም፡፡
አሁን ፈረሱም ሜዳውም ያለው በወያኔ ደጋፊዎች ደጅ ነው፡፡ እስካሁን ያርመጠምጡት የነበረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማቃናት የሚያስችላቸው ወርቃማ ዕድል አሁን እፊታቸው አለ፡፡ አንዳንድ ልፍስፍስ ፖለቲከኞቻችንንና ወያኔ ተከል ተቃዋሚ ተብዬዎችን እንዲሁም በወያኔ ቅኝት የሚዘምሩ የነገ ራስ ምታቶችን ትተው ሁነኛ ዴሞክራሲ በሀገራችን የሚመጣበትን መንገድ ሊደግፉ የሚችሉበት ዕድል አሁንም አለ፡፡ አለበለዚያ በኃይል የሚመጣ ሥልጣን ለነሱም ሆነ ለሀገራት እንደማይበጅ የታወቀ ነውና እነዚህ ምዕራባውያን የእጃቸውን የሚያገኙበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ ብዙዎቹ በዓለም የሚታዩ አመፆችና የሽብር ተግባራት ሥረ መሠረታቸው ሲጠና መነሻቸው እነሱው ራሳቸው ምዕራባውያኑ ናቸው፡፡ ለዐይን ይበጃል ብለው የሚኳሉት ኩል ዐይንን እንደሚያጠፋ ሁሉ ለአንዳንድ ሤራዎቻቸው ስኬታማነት ብለው – ለምሳሌ እንደ አዲሱ የዓለም ሥርዓት (NWO) – የሚተልሟቸው ዕቅዶች በጊዜ ሂደት ወደነሱው እየዞሩ በመተኮሳቸው ባላስፈላጊ ጥቃቶች ዜጎቻቸውንና ንብረታቸውን አስፈጅተዋል፤ እያስፈጁም ነው – 9/11ን፣ 5/7ንና የናይሮቢን የሽብር ጥቃት ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ቢን ላደንን ማነው እዚያ ላይ አድርሶት የነበረው? አዎ፣ ሁሉም የሥራውን ነው የሚያገኘው፡፡ የተከልካት ተክል ትጸድቃለች፤ ጠቃሚ ከሆነች ትጠቀምባታለህ፤ ጎጂ ከሆነች ግን ትጎዳባታለህ፤ ሰውን አለኃጢኣቱ ልታጠቃ ብለህ የወረወርካት ጦር ዞራ ተመልሳ ወዳንተው እንደምትመጣ ካላወቅህ ተሳስተሃል፤ ጊዜ ይፍጅ እንጂ በቆፈርከው ጉድጓድ የመግባት ዕድልህ እጅግ ሰፊና የማይቀርም የመጨረሻ ዕጣ ፋንታህ መሆኑን ማወቅ አለብህ፡፡ የበግ ግልገል መስላህ መንገድ ላይ ያገኘሃትን የጅብ ግልገል ቤትህ ውስጥ ብታሳድጋት ተፈጥሯዊ ባህርይዋን አትለቅምና የኋላ ኋላ የምትጎዳው አንተው ነህ፡፡ እናም ወያኔም ሆነ የስምሪት ኃላፊዎቹ ሁሉ የዘሩትን ያጭዳሉ፤ የጊዜና የቋት መሙላት/አለመሙላት ካልሆነ በስተቀር ወያኔ በኢትዮጵያ ምድርና ሰማይ እንደፏለለ የሚኖርበት ዘመን ያከትማል፤ ጦስ ጥምቡሱ ግን ለብዙዎች ይተርፋል፡፡ አርቆ ማሰብ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ ዛሬ ለምሳሌ አማራውና ኦሮሞው እንዲሁም ሌላው በገርጂም ሆነ በሰሚትና በቦሌ ከመሬቱና ከንብረቱ እየተነቀለ ለባለጊዜው የጎሣ አባላት እንደልብ ቢታደል ይህ ዘመን ሲገለበጥ ተከፍሎ የማያልቅ ዕዳ ይመጣል፡፡ ይህን የምለው ውሻ ሆድ ውስጥ ቅቤ አያድርምና ሰሞኑን ወደሰሚት ሄጄ ሰዎች ያሳዩኝ ትልቅ መንደር ውስጥ ካለሀብቶምና ካለአብረኸት በስተቀር አንድም – ለውርርድ ያህል እንኳን – አንድም ዘበርጋና ደቻሳ ወይም ሸዋርካብሽና አሰጋኸኝ የሚባሉ ዜጎች የማይኖሩበት ምድረ ገነት በአዲስ አበባ መኖሩን ስለተረዳሁ ነው፤ አዲስ አበባና መቀሌን መለየት የማንችልበት አስገራሚ የታሪክ አንጓ ላይ መድረሳችንን የምገልጥላችሁ ነገ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ከወዲሁ በማጤን በታላቅ ፍርሀት ተውጬ ጭምር ነው – ወያኔና ይሉኝታ የማይተዋወቁ መሆናቸውን ቀድሜ ባውቅም ተጋሩ(ትግራውያን) ወገኖቼ ይህን ያህል ኅሊናቸውን ስተው የወያኔን የአድልዖ አሠራር በጭፍን ይከተላሉ ብዬ አምኜ አላውቅም – አዝናለሁ – ሀዘነይ ካብ ልበይ ኢዩ፡፡ ይህ ሁሉ ግፍ ጊዜው ሲደርስ የሚያስከትለውን ጠንቅ የማይረዳ ሰው ካለ የመጨረሻው ከንቱ ነው፡፡ “ፍቅር ያዘኝ ብለህ አትበል ደንበር ገተር፤ እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አርጎን ነበር” አለች አሉ ያቺ ምስኪን አቀንቃኝ፡፡ የተራ ጉዳይ ነው፡፡ ተራ ሲባል ደግሞ እንደወያኔ ያለ ዐይን ያወጣ አድልዖና ፍርደ ገምድልነት በእስካሁኑ ታሪካችን በግልጽ ታይቷል ለማለት እንዳልሆነ ይሰመርበት፡፡ በአፄው ዘመን በፊውዳላዊ መድሎ፣ በደርጉም በወታደራዊ መድሎ የተወሰነ ብልሹ አሠራር እንደነበር መናገር በደልን ያጥባል እንጂ ክፋት የለውም፡፡ የአሁኑ ግን በሀገራችን ቀርቶ በየትም ሀገር ያልተመዘገበ የአንድ ጎሣ ሁሉንም ነገር የማግበስበስ ሁኔታ በግልጽና ክፉኛ በሚያሳፍር አኳኋን እየታዬ ነው፡፡ በነዚህ ልጆቿ የነገይቷ ትግራይ እንዴት እንደምትሸማቀቅ ሳስበው የትግራይ መሬት ራሷ ታሳዝነኛለች፡፡ በርግጥም ላም እሳት ወለደች፡፡ አሁንም አዝናለሁ፡፡ እግዚአብሔርና አስተዋይ የአብራኳ ክፋይ የሆኑ ልጆቿ ይሁኗት ከማለት ውጪ ምን እላለሁ፡፡ እየታዬ ካው አሰቃቂ መድሎ አኳያ ለጊዜው ከዚህ የዘለለ ነገር መናገር አይቻለኝም – ችግር አለ!!!!!!!!….
ሕዝብን የሚመለከት፣ የሕዝብን ዕንባ የሚጠርግ፣ የሕዝብን ብሶት የሚያዳምጥ፣ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ዓለማቀፋዊ ዘመቻ ያስፈልገናል፡፡ የየሀገሩ ሕዝብ በአንድ ወይ በሌላ ምክንያት እያለቀሰ ነው፡፡ ጥቂቶች በሚፈጥሩት ችግር ቢሊዮኖች እየተሰቃዩ ነው፡፡ ይህ የጥቂቶች የበላይነትና ችግር ፈጣሪነት እስካልተወገደ ድረስ መዘዙ ለሁሉም ነው፡፡ ያስለቀሰ እያለቀሰ፣ ያለቀሰም እያስለቀሰ የሚሄድበት መጥፎ አዙሪት እስካልተወገደ ድረስ ዘላቂ መፍትሔ የለም፡፡ … የሰው ልጅ አእምሯዊ ይዘቱ የተዛባ ይመስለኛል፡፡ ራስህን በማለፊያ ምግብ አጥግበህ ሌላውን ስታስርብና ስታሰቃይ የምትደሰት ከሆነ ከእንስሳነትም ወርደሃል ማለት ነውና ሰብኣዊ ዕድገትህ ላይ ችግር መከሰቱን ልብ ማለት ሊኖርብህ ነው፡፡ አሳዛኝ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
ወያኔን ግን በደምብ ዐወቅናት አይደል? እስኪ እዚች ላይም ትንሽ እንሳቅና እንዝናና – “ካልፈረማቸሁ እናስራችኋለን!!!” ጥጃ ገዝተው ወይም ወደማርካቶ ወጣ በማለት አንድ አምስትና ስድስት ሺህ ኢትዮጵያውያን የሰው እንስሳትን እንደለመዱት አያስሩም? ቅብጠታቸው ግን ለከትና ድንበር አጣ፡፡ ለነገሩ በጌታዋ የተማነች በግ ላቷን ቀለበት መንገድ ላይና አባይ ላይ ታስራለች ይባል የለም? ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈኔ፡፡ ጉድ ነው፡፡
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሰሞኑ ግርግር በአምቦና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍሳት በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ ያኑርልን፣ በጠባቡ ቃሊቲ የታሰሩትንም፣ በሰፊው “ዞን 9” የታሰርነውን እኛንም ፈጣሪ በቸርነቱ ይጎብኘን፡፡ አስቡ – ቀኒቷ ቀርባለች፡፡ ምልክቶች ሁሉ ታይተዋልና “ፕሊዝ” ወደየኅሊናችን በመመለስ ውስጣችንን እናጽዳ፡፡ ተመልሰን ሰው እንሁን፡፡ ሰው መሆን እንችላለን፤ መብትም አለን፤ ሰው ለመሆን ደግሞ በሕይወት እስካለን ድረስ ሁላችንም ልንሞክረው የሚገባን ታላቅ አምላካዊ ፀጋ እንጂ ቀነ ገደብ የተጣለበት ለማንም የተከለከለ ጉዳይ አይደለም፤ እናም ተስፋ ሳንቆርጥ ሰው ለመሆን እንሞክር፡፡ ያኔ ነው ከነዚህ ጉግማንጉጎች ነጻ የምንወጣው፡፡ አለበለዚያ በባርነት እየዳከርን ብዙ ጊዜ እንቆያለን – የባርነቱ ዘመን ይረዝምብናል፡፡ እናም ሰው በመሆን ፈጣሪን እናግዘው – የነጻነታችንን ጊዜም እናቅርብ፡፡

እምዬ ምኒልክ ሲመጥቅ፣ ወያኔ ሲወድቅ


ከሮበሌ አባቢያ፤ 14/5/2014
ቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ
ወያኔ በ1983 አዲስ አበባ ሲገባ እግረ መንገዱን የገበሬውን ልጆች፣ ጋዳፊና የአረብ ሀገር ከበርቴዎች ባስታጠቁት ዘመናዊ ታንክና መሣሪያዎች፣ እያጨደ በሬሳቸውና በደማቸው ላይ እየተረማመደ እንደነበር መሪር የቅርብ ትዝታ ነው። በቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ይመራ የነበረው ጎጠኛው የወያኔ መንግሥት፣ የኢጣልያ ፋሺስት ያወጣውን በተለይ በአማራና በኦሮሞ ላይ ያነጣጠረውን የከፋፈለህ ግዛው ፖሊሲ ኮርጆ በመከተል፣ የአፄ ምኒልክ ሐውልት እንዲፈርስ ለማደረግ ሕዘቡን አነሳስቶ እንደነበር ይታወቃል።ሆኖም ሙከራው ወያኔ አስቦት በነበረበት ወቅት ባይሳካም፣ ሐውልቱን የማንሳት ሃሳብ አሁንም አለ። ስለዚህ ሕወሐት የሚመራው በውስጡ በሚስጥር በተሰገሰጉ ባንዳዎች እንደሆነ እያደር ሊታወቅ ስለቻለ የእምዬ ምኒልክ ወደጆች መዘናጋት የለባቸውም።Ethiopian king Atse Menelik
ሐውልቱና ከኢጣልያን ጋር የተደረጉት ሁለት ከባድ ጦርነቶች
እምዬ ምኒልክ፣ እስከ አፍንጫው ድረስ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ በገፍ ታጥቆ ኢትዮጵያን ሊወር የመጣውን ጦር፣ አድዋ ላይ ገጥመው ወራሪውን ድባቅ መትተው አንፀባራቂ ድል ሲጎናፀፉ፣ ከሰሜን ሸዋ አብሮአቸው የዘመተው ስምንት ሺህ (8000) ፈረሰኛ የኦሮሞ ሚሊሽያ ሠራዊት በጦርነቱ ለተገኘው ድል ወሳኝ አስተዋፅዖ አድርጎ እንደነበረ በታሪክ የተመዘገበ የጀግንነት ሐቅ ነው። የአድዋው ድል የአውሮፓን ሀያላን መንግሥታትን አስደንግጦ ኢትዮጵያን እንደ አንድ ሉአላዊ ነፃ ሀገር እንዲያውቋት አስገድዷቸዋል። ይህ ታላቅ የጥቁር ሕዝብ ድል በዓለማችን ላይ ለሚገኙት ጭቁን ጥቁሮች ሁሉ ሕያው ተስፋ ሰጥቷል።
በሽንፈቷ ሀፍረት የተከናነበችው ኢጣልያ፣ 40 ዓመት ሙሉ በሚስጢር ስትዘጋጅ ቆይታ፦ ሀ) በሚሊሽያዎቻችን ላይ ከሰማይ በአውሮፕላን የቦምብ ናዳ በማዝነብና በዓለም ሕግ የተከለከለውን መርዝ በመርጨት፤ ለ) በምድር በታንክና በመትረየስ የታገዘ መጠነ ሠፊ የሰለጠነ እግረኛ ጦር በማዝመት፤ ሐ) ሕዝቡን በጎሳ ከፋፍላ እርስ በርሱ በማጫረስ፤ መ) አማሮችና ኦሮሞዎች የሥልጣኔ ተፃራሪዎች ስለሆኑ ሌሎች ጎሳዎች በጠላትነት እንዲፈርጇቸው በመስበክ፣ አዲስ አበባን (ሸገርን) እንደ አውሮፓ ዘመን አቆጣጠር በ1936 ዓ.ም ለመቆጣጠር ችላለች። ዋቢ፦ Habešská Odyssea (YeHabesha Jebdu) የሃበሻ ጀብዱ by Adolf Parlesak Translated by Techane Jobre Mekonnen
የፋሺስትን ወረራ ያልተቀበሉት የኢትዮጵያ አርበኞች (በአዲስ አባባና በአካባቢው የሚገኙትን ኦሮሞዎችን ጨምሮ)፣ አራዳ ጊዮርጊስ በዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት ዙሪያ ማታ ማታ እየተሰበሰቡ (ሬዲዮ አድማጭ መስለው) ይመካከሩ ነበር። ግራዚያኒ ይህን ሲሰማ ሐውልቱ እንዲነሳና በምሥጢር እንዲቀበር አዘዘ፤ በትእዛዙም መሠረት ሐውልቱ ተነስቶ ሌላ ጋ ተቀበረ። ፋሽስት ኢጣልያ ተሸንፎ ከሀገራችን ሲባረር፣ ሐውልቱ ከተቀበረበት ቦታ ተመልሶ እንደገና በቀድሞ ቦታው ላይ ሊተከል ቻለ።
ጠላት ተገዶ ያከበራቸውን እምዬ ምኒልክን ማክበር የምንኮራበት መብታችን ነው። እምዬ ምኒልክ ሲልቅ፣ የባንዳዎች ውላጅ ወያኔ ሲበሽቅ ሁሌ እደሰታለሁ። ምኒልክ አንድ ያደረጋትን ኢትዮጵያን ወያኔ ሲበታትናት አበክረን መቃወም የውዴታ ግዴታችን ነው። በዚህ ጉዳይ ለሚቃወሙን ተቺዎች መልሳችን ይሄው ነው።
ምኒልክ ከአንኮበር እስከ ሸገር
አፄ ምኒልክ ከአንኮበር ወደ ሸገር ሲመጡ ያጋጠማቸው ተፋላሚ ቱፋ ሙና የተባለ ሐይለኛ የኦሮሞ ገዢ ነበር። አፄው ብልሀተኛ ስለነበሩ አማላጅ ልከው ታረቁና ቱፋ ሙናን ክርስትና አንስተው አበልጅ ሆኑ። የቱፋ ሙና ሰፊ ዘሮች እነ አቶ ብሩ ጎሮንቶ ገፈርሳ ግድብ አካባቢ በስተ ምዕራብ-ደቡብ አንድ ትልቅ ግቢ ውስጥ ይኖሩ ነበር። አቶ ብሩን ባጋጣሚ ሱሉልታ አግኝቻቸው ከተዋወቅን በሗላ፣ ከባለቤቴ ጋር ገፈርሳ ድረስ እየሄድን እንጠይቃቸው ነበር። አቶ ብሩ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በተገኘበት በታላቅ ሥነሥርዓት ገፈርሳ በምትገኘው ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በተፈፀመው ቀብራቸውም ላይ ተገኝቻለሁ።
ምኒልክ ከአንኮበር እስከ ሸገር (አዲሰ አበባ) የመጡት በኦሮሞ ባላባቶች የሚታዳደሩትን ግዛቶች አቋርጠው ነው። ቱፋ ሙና ብቻ ነው በነውጥ የተፋለማቸውና ውጊያው በእርቅ የቆመው። በነገራችን ላይ፣ የ1966ቱ አብዮት ሲፈነዳ እኔ አሰከማቀው ድረስ በሸዋ ውስጥ ሰፍኖ የቆየው ባላባታዊ ሥርዓት አራማጆች በአብዛኛው አለጥርጥር የኦሮሞ ተወላጆች ነበሩ።
የተወለድኩት አዲሰ አበባ ቀጨኔ ጋላ ሰፈር በሚባላው መንደር ውስጥ ነው። የከተማውን ዙሪያ ደህና አድርጌ አውቃለሁ። ሸዋ ውስጥ በልጅነቴ በእግሬና በፈረስ ከዚያም ስጎረምስ በመኪና በብዙ አቅጣጫዎች ተዘዋውሪያለሁ። ለምሳሌ፣ ከአዲስ አበባ ተነስተን እስከ 130 ኪሎሜትር ርቀት ዙሪያውን በወፍ በረር ብንቃኝ፣ የክልሉን ባላባትነት የአንበሳውን ድርሻ የኦሮሞ ተወላጆች ይዘውት እንደነበር አያከራክርም ለማለት ይቻላል። አፄ ምኒልክ የመሬት ግብር አስከፈሉ እንጂ የባላባቶችን የመሬት ይዞታ አለምክንያት አልነኩም። ዘውዱንም መሬቱንም እኔ ይዤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ሊቀረው ነው ብለው የመሬት ባለቤትነት በግል የእያንዳንዱ ዜጋ ይዞታ መሆን እንዳለበት በችሎት ላይ ስለመፍረዳቸው በአድናቆት ይነገርላቸዋል።
ስለ ባላባታዊ ሥርዓት የወዝ ሊግና የመኤሶን ፖሊሲ
በዘውዳዊው ሥርዓት ከነበሩት 14 ጠቅላይ ግዛቶች ውስጥ፣ በአካል ተገኝቼ የማላውቃቸው ወለጋንና ኢሉባቦርን ብቻ ነው። ስለ ኢሉባቦር የዚያ ተወላጅ የነበረው ወዳጄ ዶክተር ሠናይ ልኬ ትንሽ አጫውቶኛል። ዶክተር ሠናይ በአፍቃሬ እስታሊንስትነቱ የታወቀ ምሁር ነበር። የባላባታዊ ሥርዓት ጭቆና ያልደረሰብት ብሔር ብሔረሰብ ስለሌለ፣ የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው በመደብ ትግል ነው የሚል የማያወላወል አቋም ነበረው። በዚያ ጊዜ ስለስታሊን ሥራዎች አንብቤ ባላውቅም፣ እኔም የባላባታዊውን ሥርዓት ጨቋኝነት ከምር እጠላ ስለነበር ከዶክተር ሠናይ ጋር ተቀራርበን ተወደጀን፤ ግን በምኒልክ ቤተ መንግሥት እነ ብ/ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ፣ ሻለቃ ዮሐንስ የተባለ የኢሕአፓ አባል ዶክተር ሠናይን (በ33 ዓመት እድሜው) ወዲያው ስለገደለው ከወዳጄ ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋረጠ። ምሁሩ ሠናይ በወጣትነት ሞተ፤ ኢትዮጵያም ጀግና ልጇን አጣች!
ዶክተር ሠናይ የጎሳ ፖለቲካ አጥብቆ ይቃወም ነበር። “በከልቻ ኦሮሞ” በሚል ስያሜ ይንቀሳቀስ የነበረውን የኦሮሞ ጎሳ ቡድን መሪዎችን ተከረክሮ ትግላቸውን ወደ መደብ ትግል እንዲቀይሩ ለማግባባት ያደረገው ብርቱ ጥረት ከሞላ ጎደል ተሳክቶለታል።
ወጣቱ ምሁር ዶክተር ሠናይ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሶሽያሊስት አብዮት ለማካሄድ ገና 30 ዓመት ያስፈልጋል ብሎ ይናገር ነበር። ስለዚህም ነበር ግራ-ዘመም ምሁራን የተሰባሰቡበት የሕዝብ ጉዳይ አደራጅ ጽ/ቤት፣ “አዲሱ ዴሞክራሲያዊ አብዮት” የተባለውን ፕሮግራም ከሰሜን ኮሪያ ተሞክሮ በመቅዳት በአማርኛ ቋንቋ አዘጋጅቶ በሥራ ላይ ለማዋል የሞከረው።
የልጅ እንዳልካቸው ካቢኔ የመሬት አዋጅ ቢያውጅ ኖሮ ለ30 ዓመት በሥልጣን ላይ እንደሚቆይ ዶክተር ሠናይ የነበረውን ግምት ተናግሮ ነበር። ዳሩ ግን ልጅ እንዳልካችው በሥልጣን ይቀናቀኑኛል ብሎ የፈራቸውን የነ አቶ ከተማ ይፍሩን ቡድን አባላት ሲያሳስር ቆይቶ በመጨረሻ እሱም የደርግ እስረኛ ሆኖ በደርግ ተረሸነ።
የወዝ ሊግ መሪ ሠናይ ልኬና የመላው ኢትዮጵያ ሶሽያሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) መሪ ሐይሌ ፊዳ፣ በመደብ ትግል ነፃነትና ፍትህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሰፍናል ብለው የታገሉ፣ በዙሪያቸውም እጅግ በጣም ተከታዮችን ያሰለፉ፣ የአሮሞ ተወላጆች ነበሩ። ሠናይ በኢሕአፓ አባል ሲገደል ሐይሌ በደርግ ተረሸነ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሁለቱም ምሁራን ተከታዎች፣ “ሰደድ” በተባለው እስከ አፍንጫው በታጠቀ የመንግሥቱ ሐይለማርያም ወታደራዊ ቡድን አዳኝነት ከያሉበት እየተለቀሙ ተገደሉ፤ የሁለቱም ምሁራን ድርጅቶች፣ ማለት የወዝ ሊግና መኢሶን፣ ከሰሙ።
ሀገራዊ አጀንዳ አራመጆቹ የወዝ ሊግና የመኢሶን ድርጅቶች ባይፈርሱ ኖሮ ዛሬ በአምቦ፣ በለቀምት፣ በኢሉባቦር፣ በጂማ፣ በዓለምማያ፣ በድሬዳዋ ወዘተ ዩኒቨረስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚማሩ የኦሮሞ ወጣቶችና በደጋፊዎቻው ላይ፣ በወያኔ መሪዎች ትእዛዝ የአግዓዚ ጦርና ፌዴራል ፖሊስ የፈፀሙት ምንጊዜም የማይረሳ ጭፍጨፋ እንኳን ሊደረግ ባልታሰበም ነበር።
ስለዚህ ታላቁ የኦሮም ሕዝብ ይህን የወያኔ ንቀትና እብሪት ከቶም እንደማይቀበለው በመገንዘብ ፣ አምባገነኑ የኢሐዴግ መንግሥት ጥፋቱን በማመን ይቅርታ ጠይቆ አጥፊዎቹን ለፍርድ እንዲያቀርብና በሀገራችን ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፈን የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ ሁሉን አቀፍ ጊዜያዊ የሸግግር መንግሥት አንዲቋቋም ሁኔታዎችን ማመቻችት አለበት።
አንድነት ሐይል ነው
በአድዋ ጦርነት የተገኘው ድል የአንድነትን ሀይል አስተምሮናል። በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ልዩነቶችን እያሰፋ ሲቪል ጦርነት ውስጥ ሊከተን ነው። ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ልዩነቶችን ተቋቁሞ ሰላምን ለማስፈን ብቸኛው ፍቱን መድሐኒት ዳያሎግ ስለሆነ ሁላችንም ተባብረን ወያኔን በቃህ ማለት ተገቢ ነው። ገዢው የወያኔ መንግሥት፣ በአምቦና በሌሎች የኦሮምያ ክፍሎች የተደረገውን ኢሰብአዊ ጭፍጨፋ ለማረሳሳት የሚያሰራጨው የማያዋጣ ከንቱ ፕሮፓጋንዳ፣ የተማሪዎችን የማሰብ ደረጃ ዝቅ ለማድረግ የታሰበ ትዝብት የሚያስከትል ምኞት ከመሆኑ በስተቀር ሌላ ፋይዳ የሌውም። ይልቁንስ ብጥቅጥቅ ያሉት ወያኔን የሚቃወሙ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ተስማምተው የጋራ ጠላታቸውን በአንድነት ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር ተሰልፈው መፋለም ይጠበቅባቸዋል።
የዛሬዎቹን ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርጉንን ሁለት ምሳሌዎች ላንሳ፦
ሀ) አፄ ምኒልክ፣ የጦር ጄኔራሎቻቸውን እነ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴን፣ መኮንን ወልደሚካኤልን፤ ባልቻ አባነብሶን የመሳሰሉትን በጦር መሪነት መድበው፣ ከዝናኛው ከሰሜን ሸዋ አብሮአቸው የዘመተው ስምንት ሺህ (8000) ፈረሰኛ የኦሮሞ ሚሊሽያ ሠራዊት በጦርነቱ ለተገኘው ድል ወሳኝ አስተዋፅዖ አድርጎ እንደነበረ በታሪክ የተመዘገበ የጀግንነት ሐቅ ነው።
ለ) የወዝ ሊግ መሪ ሠናይ ልኬና የመኤሶን መሪ ሐይሌ ፊዳ፣ በመደብ ትግል ነፃነትና ፍትህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሰፍናል ብለው ታግለዋል። ለዚህም ያበቃቸው በአድዋው ድል በተገኘው ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ነፃነት፣ ቀጥሎም በማይጨው ጦርነት ወጣቶቹ እነ አብቹ ከሸዋ፣ ሀብቶም ከሃማሴን፣ ተስፋጽዮን ከትግራይ (መቐለ)፣ ጋሹ ከጎጃም(ዳሞት)፣ ወርቁ ከሰላሌ፣ የየራሳቸውን ጦር በአብቹ የበላይ አዛዥነት ስር አሰልፈው፣ የከምባታው ሚሊሽያ ጦር ለሰባት ወራት በእገሩ ተጉዞ ማይጨው በመድረስ በጀግንነት ተዋግተው የወራሪውን ፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት መግቢያ መውጫ በማሳጣት ባሳዩት የአልበገሬነት ጀግንነትና የከፈሉት መስዋዕተነት ነው። በማይጨው ጦርነት ጊዜም ቢሆን በጦርነቱ ላይ የተሰማራው ሚሊሽያ ለውጊያው ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጠው “በእምዬ ምኒልክ” ስም እየማለ እንደነበር የጦርነቱን ታሪክ የጻፈው ቼኮስሎቫኪው የጦር አማካሪ በጦርነት መስክ ያየውን ሐቅ መስክሯል። ዋቢ፦ Habešská Odyssea (YeHabesha Jebdu) የሃበሻ ጀብዱ by Adolf Parlesak Translated by Techane Jobre Mekonnen
ማጠቃለያ
ሰው በሀገሩ እስረኛ፣ ገበሬው የመንግሥት ጭሰኛ፣ ካድሬው የሕወሐት ፓርቲ ታማኝ ሠራተኛ፣ ተራው ሕዝብ የገዢው መደብ ጥገኛ የሆኑባት ሀገር በዓለማችን ላይ ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ለዚያውም በ21ኛው ክፍለ ዘመን!!! ይህ መቀጠል የለበትም።
ሁላችንም የሐም፣ የሴም የያፌት ልጆች ነን። ካም የሐም የመጀመሪያ ልጅ ነው። ስለዚህ ዛሬ የምንገኝባት ኢትዮጵያ የነዚህ ሶስቱ ጥንታውያን አባቶቻችን ፍጡር ናት። ተጋብተናል፤ ተዋልደናል፤ ለነፃነታችን አብረን ተሰውተናል፤ ወንዞቻችን አስተሳስረውናል። በሌሎችም ሀገር እንደታየው ሁሉ (ለምሳሌ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በቻይና) እርስበርስም ተዋግተናል። ስለዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚያዋጣን፣ የጎሳ ፖለቲካን አሽቀንጥረን በመጣል የግለሰብ ሰብዓዊ መብት የሚከበርባትን የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነው።
አንድ አዛውንት ከአምቦ ከተማ በ12/5/2014 ለኢሳት ራዲዮ ጣቢያ ባስተላለፉት መልዕክት ወያኔንን ተባብረን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በአንድነት እንድንታገለው ያቀረቡትን ልብ የሚነካ ጥሪ ተቀብለን በሥልጣን ላይ ያለውን አምባገነን መንግሥት ማንበርከክ ግድ ይላል።
ታዋቂው ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ታጋይ አበበ ገላው በኦሮምያ የተማሮዎች መጨፍጨፍ፣ የጎንደር ነዋሪዎች በጥይት መረሽን ከልክ በላይ አናዶት “ነፃነት ለኢትዮጵያ!” እያለ ደጋግሞ በመጮሁ ፕሬዚዳንት ኦባማ ያደርጉ የነበረውን ንግግር አቋርጠው ያዳመጡት መሆኑን በአድናቆት በዜና ብዙሃን አይተናል ወይም ሰምተናል። እግዚአብሔር የአርበኛውን የጋዜጠኛ አበበ ገላውን ወኔና የሀገር መውደድ መንፈስ ይስጠን።
እምዬ ምኒልክ እንደገና ሲመጥቅ፣ ወያኔ ሲወድቅ የምናይበት ጊዜ ስለተቃረበ የኢትዮጵያን ትንሣዔ ለማየት የምንጓጓ ልጆቿ ሁሉ ተባብረን እንነሳ።
የኢትዮጵያ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ የፈቱ!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
rababya@gmail.com

ዝክር ለግንቦት 7 1997 እና ለግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም


ዘንድሮ፣ የታሪካዊው ግንቦት 7 ቀን 1997 አገር ዓቀፍ ምርጫ ዘጠነኛ ዓመት እና ንቅናቄዓችን የተመሠረተበት ስድስተኛ ዓመት የምንዘክረው ከመችውም በላይ አገራችን አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ሁና ነው። ወያኔ የማይገዛትን አገር እንዳትኖር ለማድረግ እማትወጣው አረንቋ ውስጥ ከመክተት የማይመለስ ኃይል መሆኑን ዛሬ በአምቦ፣ በጉደር፣ በጊምቢ እና መሰል ቦታዎች በተግባር እያስመሰከረ ነው።Ginbot 7 logo
የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ፍላጎቱን የመግለጽ አንፃራዊ ነፃነት አግኝቶ የነበረበት የግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ምርጫን ስናስብ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ መመዘናችን አይቀርም። ያኔ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ እጁ መዳፍ ቀርባ ትታየው የነበረችው ድል እስከዛሬ አልጨበጣትም። ትግሉ ግን ቀጥሏል። የዛሬው ትግላችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከያኔው በበለጠ ከታሪክና ከራስዋ ጋር የታረቀች አገር የመመሥረትን ርዕይ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት መስጠትን የሚጠይቅ ሆኗል።
ወያኔ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለአለፉት አርባ ዓመታት ሲያብላላው የቆየው፤ በመንግሥት ሥልጣን በቆየባቸው ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ በፓሊሲ ደረጃ ሲያስፈጽመው የቆየውን የዘር ፓለቲካ አስከፊ ውጤት አሁን እየታየ ነው። ይህ የዘር ፓለቲካ ራሱ ወያኔን ያጠፋዋል። ችግሩ ግን የዘር ፓለቲካ ወያኔን ነጥሎ አያጠፋም፤ ከወያኔ ጋር አገራችንንም ሊያጠፋ ይችላል። ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ጉዳይ ደግሞ የዘር ፓለቲካ የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። በጎረቤት አገራት ውስጥ ያየነውን ዓይነት የእርስ በርስ እልቂት ወደ አገራችን ለማምጣት ህወሓትና ኦህዴድ ተግተው እየሠሩ ነው። ሌሎች የወያኔ ተቀጥላ ድርጅቶችም የዚህ ትልቅ የጥፋት ፕሮጀክት አካል ናቸው።
የግንቦት 7 1997ቱ ብሩህ ተስፋ በፋሺስቱ ወያኔ የግፍ አፈና ሲጨልም፤ ያ ተስፋ እንዲያንሠራራ በግንቦት 7 2000 ዓ.ም. የተቋቋመው ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ የኢትዮጵያን ተስፋ ለማጨለም ከተነሱ ኃይሎች በተፃራሪ በመቆም የሕዝብና የአገር አለኝታነቱ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
በዚህም ምክንያት፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች የሆንን ሁሉ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ ይኖርብናል። በግራም ይሁን በቀኝ ያለ ጽንፈኝነት አገራችን አይጠቅምም፤ የምንመኛትን ኢትዮጵያ አያመጣልንም። ሕዝባችንና አገራችንን ከዚህ አረንቋ ማውጣት የሚቻለው የአንድነትና የእኩልነት ፓለቲካን አሸናፊ ማድረግ ስንችል ነው።
በአሁኑ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ለሀገራችን የሚጠቅማትና ትክክለኛ ነው ብለን የምናምነው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚታገል፤ የተለያዩ የኅብረሰተሰብ ክፍሎች በመሰላቸው መንገድ ለመደራጀት መብታቸው እውቅና የሚሰጥ፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ ማኅበረሰቦች በሙሉ በእኩልነት የሚስተናገዱበት ሥርዓትን የሚያልም፤ መሰማማት፣ መቻቻል እና ከዚያም አልፎ መተጋገዝ ያለበት የኢኮኖሚና የፓለቲካ ሥርዓት እንዲኖር የሚታገል፤ የእምነቶች እኩልነትን የሚያከብር፤ በታሪክ ውስጥ የተፈፀሙ በደሎችን መርምሮ ማኅበራዊ እርቅ ለመፍጠር ፍላጎት ያለው ፓለቲካ ነው።
ይህ ዓይነቱ የአንድነትና የእኩልነት ፓለቲካ በአሸናፊነት እንዲወጣ ማድረግ ይቻላል ብሎ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያምናል። ይህ ለሁላችንም የሚበጀው ፓለቲካ አሸናፊ ለማድረግ የሚከተሉትን መፈፀም ይጠበቅብናል።
በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የሚደርስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፍጹም የማንታገስ መሆኑን ማመንና በተግባሮቻችንም ይህንኑ መግለጽ፤
ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር መውጫው መንገድ ወያኔን ማስወገድና በምትኩ የዜጎችን እኩልነት የሚያረጋግጥ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያስታርቅና የሚያስተሳስር መንግሥት መመሥረት መሆኑን ማመንና በተግባሮቻችን ማሳየት፤
የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላቶች ወያኔ እና ተቀጥላዎቹ፣ በተለይም ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደህዴድ መሆናቸውን በማመን ትኩረታችንን ነቀሎ ወደሌላ ከሚወስዱ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች መቆጠብ፤
በብሔር ከተደራጁ ኃይሎች ጋር በሚለያዩን ነገሮች ላይ ሳይሆን በሚያስተባብሩን ጉዳዮች ላይ በማተኮር የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ አጀንዳ ማክሸፍ፤
በስሜትከተሞሉ የአጭር ጊዜ እይታዎች ለእርስ በርስ ግጭቶች ከሚዳርጉ አስተሳሰቦችና ተግባራት መቆጠብ፤ እና
አርቆ አስተዋይነትና ታጋሽነት በተላበሰ መንገድ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለኢትዮጵያ ደህንነት፣ለፍትህና ለነፃነት በግንባር ቀደምትነት መቆም፤
የግንቦት 7 ንቅናቄ አባላትና ደጋፊዎች ከላይ የተዘረዘሩትን ለመፈጸም የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ ያለንን ዝግጁነት እየገለጽን፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔና ግብር አበሮቹ ከፊቱ የደቀኑበትን ከፍተኛ አደጋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተባብሮ እንዲያስወግድ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን ያቀርባል።
አስቸጋሪ ወቅት ላይ የምንገኝ ቢሆንም እንኳን በርትተን ከታገልን የተረጋጋች፣ ዲሞክራሲያዊ ሉዓላዊ አገር – ኢትዮጵያ – ይኖረናል። ለዚህ ውጤት በርትተን እንታገል።
ክብር የግንቦት 7 1997 ሀገራዊ ተስፋን እውን ለማድረግ ለወደቁ ሰማዕታት!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!