Friday, November 15, 2013

ብሄራዊ ውርደት፤ የምንመጻደቅበት ‘ሌጋሲ’

ክንፉ አሰፋ 
ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል[1]። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው። በስውር ሳይሆን በግልጽ። እንደ ኦሽዊትስ በታጠረ የማጎርያ ካምፕ ሳይሆን በአደባባይ።
ሰው ከሞተ በኋላ ለምን ሙት አካሉን ማሰቃየት አስፈለገ? ምን አይነት ጭካኔ ነው? ምን አይነትስ ጥላቻ ነው? ለሳውዲዎች ግማሽ ፈረንሳይን የሚያህል መሬት ሰጥተናቸው የለም እንዴ? ሀጥያታችን ምኑ ላይ ነው ታዲያ? አስከሬኑን ውሻ፣ ውሻ ሲሉ ሲሳለቁበት ከማየት በላይ የሚያም ነገር የለም።  በአደባባይ እንደዋዛ የተጣለው አስከሬን በእርግጥ የዉሻ አስከሬን ቢሆን ኖሮ የእንስሳ ተከራካሪዎች  አለምን ቀውጢ ባደረጓት ነበር።
መገናኛ ብዙሃን እና ማህበራዊ ድረ-ገጾች ይህንን ጉዳይ በስፋት ቢዘግቡትም፤ አለም አቀፉ ህብረተሰብ ግን ዝምታን መርጧል። በዚህ በሰለጠነ ዘመን፤ እንደ እንስሳ እየታደኑ ከሚያዙትና ከሚገደሉት ወገኖች ውስጥ አንድ አሜሪካዊ ዜጋ ቢገኝበት ኖሮ ትርምሱ ምን ደረጃ ላይ እንደሚደርስ እናይ ነበር። የኛስ ነብስ የሰብአዊ ፍጡር ነብስ አይደለችም እንዴ? ስንቀጠቀጥ፣ ስንታረድና ስንገደል የሚፈሰን ደም ከሌላው ዜጋ የተለየ ደም ነው? ግፉ ለምን በኛ ላይ ብቻ በረታ? ሌላ ዜጋ ሲገደል አላየን። እየተሳደዱ የሚታጎሩት ሁሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ይህ ሁሉ ግፍ እና መከራ ለምን በኢትዮጵያዊያን ላይ ብቻ? ድህነታች የዜግነት ክብራችንን አስነጥቆን ይሆን? እርግጥ ነው። የገንዘብ ድሆች ልንሆን እንችላለን። የአስተሳሰብና የስነ-ምግባር ድሆች ግን አይደለንም።
ችግሩ ያለው ሌላ ቦታ ነው። ብሄራውነት የሚሰማው መንግስት፤ ብሄራዊ ክብራችንንና ማንነታች የሚያስመልስ። በአለም አቀፍ መድረክ የሚያስከብረን ጠንካራ አካል ማጣታችን ነው የውርደታችን ምክንያቱ።
እንግዲህ ይህ ነው አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት ቅርስ እና ውርስ። ይኸው ነው ገዢው ፓርቲ የሚመጻደቅበት ‘ሌጋሲ’። በምእራብ አፍሪካ ኮሌጆች የኢትዮጵያ ታሪክ እንደኮርስ ይሰጣል። የአድዋ ገድል፣ የጸረ-ቅኝ ግዛት ተምሳሌት፣ የነ ማርክስ ጋርቤይ፣ የነ ክዋሜ ንክሩማ፣ የነ ጆሞ ኬንያታ ለነጻነት ትግል መነሳሳት ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ተቆራኝቶ በታሪክ ይዘከራል። ላለፉት 20 አመታት የተፈጠረው ክስተት ግን ይህንን ሁሉ መልካም ስም ድራሹን እያጠፋው ይገኛል። የተስፋይቱ ምድር እያሉ የሚጠሩዋት ራስ ተፈሪያን  የዛሬዩቱን ኢትዮጵያ የውርደት ታሪክ  እንዴት እንደሚያዩት እንጃ። ለአፍሪካ ነጻነት ተምሳሌት የሆንን ሰዎች ዛሬ ስደትን እንደመፍትሄ ለመውሰድ ተገደድን። በስደቱ ብቻ ሳያበቃ ሰብአዊነት በማይሰማቸው አካላት እነሆ ብሄራዊ ውርደትን እየተከናነብነው እንገኛለን።
እ.ኤ.አ. በ2004 የደች ንግስት ቢያትሪክስ ታይላንድ ተጉዛ ነበር። ቢያትሪክስ ወደ ታይላንድ የተጓዘችበት ዋነኛው ምክንያት በአደንዛዥ እጽ ዝውውር ታስረው የነበሩ ሁለት ሆላንዳውያንን ለማስፈታት ነው። አርባ እና ሃምሳ አመት ተፈርሮባቸው የነበረው እነዚህ ዜጎች በንግስቲቱ ጉብኝት ወቅት እንዲፈቱ ተደረገ።  የታይላንድና የሆላንድ የኢኮኖሚ ግንኙነት በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አረቢያ ካለው የንግድ ትስስር በልጦ አይደለም። ንግስቲቱ በባዶ እጅዋ ወንጀለኛ ዜጎችዋን ማስፈታት ቻለች። ለዜጎችዋ ክብር ስለነበራት። በርግጥ ወንጀል ሰርተዋል። ቅጣቱን እኛው እንስጣቸው ብላ ዜጎችዋን ይዛ ተመለሰች ንግስት ቢያትሪክስ። ሳውዲ አረቢያ የኔዘርላንድን ቆዳ ስፋት በእጥፍ የሚበልጥ መሬት ከኢትዮጵያ ተችራለች። በወንጀል ሳይሆን ይልቁንም በጉልበት ስራ የተሰማሩ ዜጎቻችን የሚፈጸምባቸውን ግፍ ለማስቆም አንድ ሄክታር መሬት ብቻ በቂ ነበር። ሳውዲ በኢትዮጵያ ከ200,000 በላይ ሄክታር ለም መሬት ይዛለች።  ለብሄራው ውድቀታችን እና ውርደታችን ዋነኛው ምክንያት የዜጎቹን ክብር የሚያስቀድም ብሄራዊ  መንግስት ስላጣን እንጂ በዚህ ብቻ ሳውዲን ማስፈራራት ይቻል ነበር።
በሳውዲ ያለው ኢትዮጵያዊ ከ30 ሺህ በላይ ይገመታል። በጉልበቱ ጥሮ እያደረ ያለን ዜጋ ህገወጥ እያሉ ያሳድዱታል። እነሱ ግን በሃገራችን ላይ  እንደአንደኛ ዜጋ በነጻነት የመኖር መብት ተሰጥቷቸዋል። ለሳውዲ ባለሃብቶች የተሰጠው ለም መሬት ለነዚህ ዜጎች ቢሰጥ ኖሮ፤ ወገኖቻችን ባልተሰደዱና ባልተዋረዱ ነበር። 
የኛ ትውልድ፤ ሀገር አልባ፣ ዜግነት አልባ ትውልድ። ከዚህ በላይ የሆነ ብሄራዊ ውርደት የለም።
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ በላከው ማስታወሻ እንዲህ ይላል፤…
…የእኛን መያዝ የተመለከቱ የሳውዲ ወጣቶች (ሸባቦች) ሚስት እህቶቻችን ይደፍራሉ፣ ንብረታችን ይዘርፋሉ!  ይህ ለሶስት ቀናት ሲቀጥል የደረሰልን የለም! ኢንባሲ ደወልን ምንም ማድረግ አንችልም ይሉናል፣ አንተም ድምጻችንን ታሰማናለህ ብለን ብንደውልልህ ፈራህ መሰል አታነሳልንም! የት እንድረስ? ምን እናድርግ?  ንብረታችን እየተዘረፍን ሴቶቻችን  እየተደፈሩ ዝም ብለን ማየት ነበረብን?  ይህን በመቃወም ሻንጣና ቤተሰቦቻችንን  ይዘን ወደ ሃገራችን ስደዱን ነው ያልናቸው“  የሚል እየተቆጣና ድምጹን ከፍ እያደረገ መልስ የሰጠኝን አንድ ወንድም መጨረሻችሁ ምን ሊሆን ይችላል ? አልኩት “… ወደ ሃገራችን ከነሚስት እህቶቻችን ይውሰዱን ነው የምንለው! ያለበለዚያ መንፉሃን እና ሚስት እህቶቻችን አንለቅም! ገድለው ያስለቅቁን” ሲል ክችም ያለ መልሱን ሰጥቶ ስልኩን ጀሮየ ላይ ዘጋው…

በሳዑዲ አረብያ የመከራ ማጥ ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን ሲባል ፈጥነን እንነሳ!


ዳኛቸው ቢያድግልኝ
እንደ ሰው አንድ የሚያደርገን ባሕርይ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት የማይነጣጥለው በደል በሳዑዲ አረብያ ግዛት እየተፈጸመ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። ይህ ዛሬ በሳዑዲ አረብያ የሚደረገው ጥቃትን ማስቆምና ቁጣችን መቆምያ እንደማይኖረው ማሳየት ለነርሱ ብቻ ሳይሆን ለራሳችን ደህንነትም ጭምር የምናደርገው ነው። ምክንያቱም ነገ ተመሳሳይ ጥቃትና በደል በመላው አለም ይስፋፋል። በአፍሪካ ሀገሮች የተበተኑ ኢትዮጵያን ከሶማሌና ኤርትራ ከሚሰደዱት በተለየ ይዘረፋሉ፣ ይደፈራሉ ይዋረዳሉ። እንደ አገር ልጅ አብረው እንዳይቆሙ በዘር በሀይማኖትና በፖለቲካ አቋም ምክንየት የተበተኑ ናቸው። ለሰላሳና አርባ አመት አምባገነኖች ያደረጉት ጭፈጨፋና በደል ፍርሃትን ሰማይ ጥግ አውጥቶታል። እናም ኢትዮጵያዊ በየተበተነበት ሁሉ ተኛ ሲሉት የሚተኛ አውልቅ ሲሉት እርቃኑን የሚቆም ፈሪ እንዲሆን ተደርጓል። ሲቸግረው የሚጮኸውን ያህል ሲመቸው ለወገን የሚደርሰው ጥቂቱ ነው። ይህ ሊቀጥል አይገባም!Protest at Saudi Arabia Mission to United Nations!
ቀደም ባለው ጊዜ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥቃት ቢደርስበት ባገኘው መሳርያ ዘነጣጥሎም ቢሆን ይገድል ስለነበር ማንም አይደፍረውም ነበር። በዘመነ ኮሎኒያሊዝም ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ሁሉ አንገት የማይደፉና ክብራቸውን የማያስነኩ ነበሩ። ዛሬ ጠቁመው የሚያስይዙ፣ ወገናቸውን የሚያሻሽጡና የሚሰልሉት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የዚህ ጽሁፍ መነሻም ሆነ መድረሻው የድሮውን አሁን እየሆነ ካለው ጋር ማወዳደር አይደለም። ለዚህ የሚሆን የቅንጦት ጊዜም የለንም። ዓላማው አሁን እየደረሰብን ያለውን በደል በቁርጠኛነት አንታገለው ነው። ይህ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ከዳር እስከዳር ማስነሳት ካልቻለና ቁጣቸውንም ለመላው አለም ማሳየት ካልቻለ እውነትም አገራችን እያበቃላት ነው ማለት ይቻላል።
የዱር አውሬ እንኳን ከዚህ የተሻለ ክብር አለው። እነዚህ አጅግ ሁዋላ ቀር የሆኑ አረመኔዎች ከእንስሳ እንኳን አንሰው አንዲት በፍርሃት ነብሷን የሳተችን ሴት አስር ሆነው የሚደፍሩትን እያየን የተደፈሩት ህጋዊ ናቸው ህገወጥ የሚል የሕግ አንቀጽ መረጣ ውስጥ ልንገባስ እንዴት ይቻለናል? በመላው አለም ያለ የሳዑዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ ሊደረግና የሳዑዲ ወሮበሎች በወጣት ሴቶች ላይ እያደረሱ ያለው ግፍ በመረጃም ተደገፎ በበራሪ ወረቀትም ተዘጋጅቶ ለአለም ሕዝብ ሊበተን ይገባዋል። ተፈጥሮ ዘይትን ስትቸራቸው አእምሮ ግን እንደነፈገቻቸው ከዚህ በላይ መረጃስ ከየት ይመጣል?
እንደ ትውስታ ከወሰድነው በኬንያ ያሉ ስደተኞች ላይ በደል ይደርስ በነበረበት ወቅት ያ በጨካኝነቱ የሚታወቀው መንግሥሰቱ ሀይለማርያም አንኳን “ኢትዮጵያውያኑ የተሰደዱት የምናራምደውን ፖለቲካ እንጂ ሀገራቸውን ጠልተው አይደለም…” በሚል ኬንያን ማስጠንቀቁን መስማቴ ትዝ ይለኛል። በየወሩ 40 ሺህ ሴቶችን እንልካለን እያለ እንደ እንቁላል በየአረብ ቤቱ ሲያከፋፍል የነበረው መንግስት ዛሬ ዜጎቹ እንዳይሆን መጫወቻ ሲሆኑ ዝም ብሎ መመልከቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ኢትዮጵያውያኑ ምናልባትም ኤምባሲውን ራሱን መቆጣጠር የሚገባቸው እስኪመስል ያስቆጣል።
በኢትዮጵያዊነት ላይ የተነጣጠረን ክፋት እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ካላስቆምነው በሳዑዲ የተጀመረው መረን የጥላቻ ሰደድ ሊቀጣጥል የሚችልና የየሀገሩ የፖለቲካ ኪሳራ ማስተንፈሻ የሚሆነው አገር አጥቶ የተሰደደው ኢትዮጵያዊው ላይ ሁሉ ይሆናል። ይህንን በአስቸኳይ ለመቃወም ያሉ የትግል መንገዶች ሁሉ ክፍት ሊሆኑ ይገባል። እኔ አዘጋጀሁ እኔ ጠራሁ የሚል ደካማ የፖለቲካ ትርፍ ፍለጋ መንቀሳቀስ ሳይሆን ለሰብዓዊ ክብርና የመከራ ማጥ ውስጥ ሆነው የወገን ያለህ ለሚሉት እህት ወንድሞቻችን የድረሱልን ጥሪ ምላሽ እንስጥ። በጣም የሚያሳዝነው አብዛኞቹ ለስራ የሚሄዱት ወጣቶች የትምህርት ደረጃቸው አነስተኛ የሆነና በድህነት ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት የሆነው ይሁን ብለው ከቤታቸው የወጡ ናቸው። አንዳንዶቹም ግሩም እድል አንደሚገጥማቸው በደላላዎች እየተነገራቸው ከቤት ወጥተው የቀሩ ናቸው። ለኒህ አጋር መሆን ለሀገር እንኳን ደንታ ባይኖረን ለነብስ የሚበጅ ስራ ነው። የኢትዮጵያ ኮሙኒቲዎች፣ በኢትዮጵያ ስም የተቋቋሙ የሀይማኖት ማዕከላት፣ ሲቪክ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ ለዚህ ዓላማ ቢቻል አደራጆች ካልተቻለም ዋንኛ ተሳታፊዎች ሊሆኑ ይገባል። ይህ በደል እጅ ለእጅ ሊያስተሳስረንና አንድ ላይ እንድንቆም ሊያደርገን የሚችል የጋራ ጉዳይ ነው። ዛሬ ነገ ሳንል በተደራጀና አለም አቀፍ ትኩረት ሊኖረው በሚያስችል አቅሙ እንነሳ ለወገንም አንድረስ።የመከራ ቀናችንን ለማሳጠር እንደ ሕዝብም ከአንገታችን ቀና እንድንል በያለንበት እንትጋ!
biyadegelgne@hotmail.com

አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሲየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።


0,,17229922_303,000,,17229927_404,000,,17229898_404,00
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት እርማጃና ተቃዉሞዉ
አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሲየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።
መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ፤ አስፋዉ ሚካኤል መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።
Thema: Äthiopien – Protest gegen Saudi Arabiens Aktion gegen Äthiopier Einwanderer Autor/Copyright: Yohannes Gebreegziabher (Addis Korri.) 15.11.2013
ዘገባዉ አክሎም ፖሊስ አንዳንድ ጋዜጠኞች ያነሱትን ፎቶግራፍ መደምሰሱንም አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይን አስተያየት ማግኘት እንዳልተቻለም ተገልጿል። ለተለያየ ሥራ ሳዑድ አረቢያ የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ እንዲያወጡ የተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ካለቀ ወዲህ እዚያ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት እየደረሰባቸዉ እንደሚገኝ እየገለፁ ነዉ።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሐገሩ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ላይ የሚያደርሠዉን በደል፥ በተለያዩ ሐገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአደባባይ ሠልፍ እያወገዙት ነዉ።ትናንት እዚሕ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ፍራንክፈርት ዉስጥ ባደረጉት ሠልፍ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያኑን፥ ማንገላታት፥ ማሠር፥ መደብደብ መግደሉን እንዲያቆም፥ የኢትዮጵያ መንግሥትም የዜጎቹን መብት እንዲያስከብር ጠይቀዉ ነበር።የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።
Thema: Äthiopien – Protest gegen Saudi Arabiens Aktion gegen Äthiopier Einwanderer Autor/Copyright: Yohannes Gebreegziabher (Addis Korri.) 15.11.2013
ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።ሠልፈኞቹ ተቃዉሟቸዉን ለማሰማት ገና ከመሠብሰባቸዉ ፖሊስ ደብድቦ አብዛኞቹን በተነ፥ የተቀሩትን አሠረ።ዮሐንስ አጭር ዘገባ ልኮልናል።
ዩናይትድ ስቴትስ ርዕሠ-ከተማ ዋሽግተን-ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንም የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚወስደዉን እርምጃ በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል። የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ ትናንት የተጀመረዉ የአደባባይ ሠልፍና ዉግዘት በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞችም ይቀጥላል።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ዜጎችን ከሐገሩ ማባረሩን ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ እንደነገረን በኢትዮጵያዉያንና በሳዑዲ አረቢያ ዜጎች መካካል ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉ ደም አፋሳሽ ግጭት ዛሬም ጋብ ብሏል።ከዚሕ ቀደም ኮንትራታቸዉ ተቋርጦ፥ ቀጣሪዎቻቸዉ ጠፍተዉ፥ ወይም ታመዉ ጂዳ ኢትዮጵያ ቆንስላ ዉስጥ ለወራት ተጠልለዉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ማቆያ ጣቢያ ገብተዋል። ነብዩን ከአንድ ሠዓት በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። የመጀመሪያዉ ጥያቄዬ ምን አዲስ ነገር —የሚል ነበር።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር/ አበበ ፈለቀ
ነብዩ ሲራክ/ ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ
http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_17230781_mediaId_17230761

“ይህ የኢትዮጵያውያን የውርደት ወር ነው” – ታማኝ በየነ በሳዑዲ ኢምባሲ ደጃፍ ላይ ያደረገው ንግግር (Video)

 

አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነን ዛሬ በስልክ ያወራው ሰው ካለ ድምፁ ተዘግቶ መጎርነኑን እንደኛ ሊረዳ ይችላል። ለ4 ሰዐታት በዋሽንግተን ዲሲ የሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲ ኢትዮጵያውያን ባዘጋጁት ሰልፍ ላይ ሲጮህ ነበር የዋለው። ታማኝ “የሳዑዲ የወገኖቼ ስቃይ አሞኛል” ይላል። አክቲቪስቱ በዋሽንግተን ዲሲ ከበርካታ ኢትዮጵውያን መካከል ሆኖ ባደረገው ንግግር “ይህ የያዝነው ወር የኢትዮጵያውያን የውርደት ወር ነው” ሲል በሳዑዲ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ስቃይ አስታውሷል። ሙሉ ንግግሩ ይኸው በቪድዮ፦

መቋጫ ያጠው የወገኖቻችን ስቃይ እና ሞት በሳውዲ አረቢያ ፡አሁንም ቀጥሏል !

ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፍሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የተጓዳ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አንድነን አንድነን … መብታችን ይከበር ….እኛም ሃገር አለን ወዘተ… በሚል መፈክር ታጅበው ብሷታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመብተን በከፈቱት ቶክስ ይሰማ በነብረው የጥይት ድምጽ አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን የገልጻሉ።

ይህንንም ተከትሎ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች ቦታው በመድረስ ተቃውሞውን መግታት ተችሎል ብለዋል ። እንዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሷ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መደሱን ገልጸዋል። ሰምኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ፡ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወስዱ ባሉት የተናጥል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመምለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በመንግስ በኩል ባለመኖሩ ከእልቂት ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ 20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እይተሰቃዩ እንደሚገኙ ተግልጾል።
በአንድ ማጎሪያ 4 ቀናቸውን እንዳስቆጠረ የሚነገርለትን ኢትዮጵያዊ እና ሪያድ መንፍሃ ጅዳ እና መካ እስከነ ልጆቻቸው በየመገዱ ፈሶ ቁም ስቅሉን እያየ ያለውን በመቶሺህ የሚቆጠር ወገን ብሷት ለማድመጥም ሆነ ለማየት የመጣ የመግስት ባለስልጣን አለመኖሩ ተገልጾል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ጅዳ በተለምዶ መስፈላ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች እና በኢትዮጵያውያን መሃከል በተነሳ ግጭጥ 76 ሰዎች መቁሰላቸውን የሚገልጹት ምንጮች በዛ ቀውጢ የቶክስ እሩምታ በጥይት ተደብድቦ የተገደለ ኢትዮጵያዊ ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ተቀማጭነታቸው ሪያድ እና ጃዳ ከተማ በሆኑት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር እና የቆንስላው ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች ላይ ተስፋ የቆረጠው ኢትዮጵያዊ ሰድተኛ እስካሁን በመግስት ወደ ሳውዲ አረቢያ ተጉዘዋል ያለው ለኡካን ቡድን ምንም አይነት የሚጨበጥ፡ነገር ባለምስራታቸው ኢትዮጵያውያኑ ለከፋ አልቂት በመዳረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል።ሰሞኑን የውጭ፡ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲናሞ ሙፍቲህ ኢትዮጵያውያኑ በሳውዲ አረቢያ እየተፈጸምባቸው ነው የሚባለው የጅምላ ግፍ እና በደል ይሄን ያህል የሚጋግነን እና ቦታ የሚሰጠው አለመሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት ምሽት መንፉአ አካባቢ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከ 17 በሚበልጥ አውቶብስ ተጭነው የተወሰዱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ህጻናት ሴቶች አረጋውያን ጨምሮ አያሌ ወገኖቻችን ከሪያድ የ6 ሰአታት ጉዞ በሃላ ያልታወቀ መድረ በዳ የሆነ አካባቢ እንዲወርዱ መገደዳቸውን እና የኢትዮጵያውያኑ እስካሁን ያሉበት ሁኔታ በውል እንደማይታወቅ ተገልጾል።

Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ

ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ እንዲሉ

 

ከዚህ በፊት በኢትዮጲያ ያለው የሳውዲአረቢያ ኤምባሲ ለአክራሪነት እርዳታዎችን ያደርጋል ለዚህም ደግሞ ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት አላቸው ያለውን በኦሮሚያ ክልል አክራሪነትን አስፋፍተዋል የተባሉት የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሐቢባ መሐመድ የእምነት ነፃነትን በመቃረን ከራሳቸው አክራሪ አስተሳሰብና አስተምህሮት ውጪ በኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ እምነትና ሃይማኖት መኖር የለበትም በሚል ሃይማኖታዊ መንግሥት ለማቋቋም ሲንቀሳቀሱና ሲያስተባብሩ ተይዘዋል  እያለ ወያኔ ሲከስ  ዛሬ ደግሞ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰያለውን ግፍ እና መከራ ያበቃ ብሎ  በኢትዮጲያ ባለው የሳውዲአረቢያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውን ህዝብ መደብደብ ማሰር ማገድ ምን ማለት ነው? ስለ ወገኖቹ መቆርቆር ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ምኑ ላይ ነው ክፋቱ? እኔ ያልኩት ብቻ ማለት ካልሆነ በስተቀር ይህ ምን የሚሉት ነው?ለዛውም ለአፍሪቃ  ዲሞክራሲን ያሳየን እኛ ነን  ለኢትዮጲያ የማውቀው እኔ ነኝ ከሚለው ወያኔ ስራ በዛብኝ የተቃዋሚዎችን ስራ ሁሉ ደርቤ እየሰራሁ ነው የሚል የሃገር መሪ ነኝ ያለን ዛሬ ግን ምን ነካው ተቃዋሚዎች ናቸው ለህዝብ ሲቆረቆሩ ሲጮሁ ሲሰሩ የሚታዩት ለዛውም መሰራት ያለበትን ትንሹን ስራ አትሰሩም እየተባሉ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ እንዲሉ ሆነ ሁሉም ነገር ግዜ ይወስዳል እንጂ ወደ ፍርድ መመጣቱ አይቀርምና ለዛውም በህዝባቸው ግፍ የሚያደርጉ በአለም አቀፍ ፍርድቤት ቀርበው በሚፈረድባቸው ዘመን ቀኑ አሁንም አልመሸም ከዚህም የከፋ እንዳይመጣ አይምሮአችንን ለበጎ ብንጠቀምበት እና ለኢትዮጲያ ህዝብ ሁሉ የሚበጀውን ብንሰራ ጥሩ ነው
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ
እግዚአብሄር ኢትዮጲያን ይባርክ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ጐን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን በዛሬው እለት አስመስክሯል!

    
999410_10201428110199302_1866404023_n
November 15/2013
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና ስቃይ መጠኑ ከመጨመር አልፎ ሕይወትን እስከማሳጣት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን በደል እና ስቃይ ለመቃወም እና ሀዘናችንን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ማለትም ህድር 6 ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራ ቢሆንም በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ በአሰቃቂ እርምጃ ሰልፉ ሊካሄድ አልቻለም፡፡
እኛ ኢትዮጵያን በውጭ በሚገኙ ዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲቆም፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት ለሕግ እንዲቀርቡና የተጐዱ ዜጐች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዜጐቹ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በአስቸኳይ በማቆም ተገቢ የሆነውን የመንግሥት ኃላፊነት እንዲወጣ ቢጠየቅም፤ ሰልፉ በተቃራኒው በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ ተጠናቋል፡፡
በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ቢሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራችን ድምፃችንን እንኳን እንዳናሰማ ታፍነናል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡
የመንግሥት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል፡፡
ይህ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገነን መንግሥት ሕዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ ወደ ጐን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድም አያቶቹን በማስታወስ ያስረከቡትን ክብር ከማስመለስ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
ፓርቲያችን እንዲህ አይነቱን የለየለት የመንግሥት ሕገ ወጥ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ የሚመለከተው መሆኑን እየገለፅን፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐናችን እንዲቆም በአፅንኦት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም