Tuesday, March 5, 2013

የካቲትን የምንዘክረው ከሀገር በቀል ወራሪው ህወሃት ጋር በመፋለም ነው!!

           ቀደምቶቻችንን የምናስታውስበት፣ ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ እና አንድነቷን ለማስጠበቅ ያደረጉትን ተጋድሎ ከምንዘክርበት እለት አንዱ የካቲት 12 ነው። በዚህ ግዜ ይህንን ታሪክ ገልብጦ ለማበላሸትና ለመጻፍ የሚጥረውን፣ የአሁኑን የግራዚያኒ ትንሽ ወንድም ሀገር በቀል ዘረኛ መንግስት የሆነውን ህወሃት/ኢህአዴግን ሀይማኖት፣ ዘርና ጾታ ሳይለየን የምንታገልበት ሁነኛ ወቅት ላይ እንገኛለን።
የቀድሞዋ የአፍሪካ ሀገራት የነጻነት ተምሳሌት የሆነችው እማማ ኢትዮጵያ፤ ዛሬ ሀገር በቀል በሆኑ የዘረኛ መዥገሮች ስብስብ ተጣብቃ የአበው መሰዋእትነት ከንቱ ይሆን ዘንድ ወያኔዎች እየሰሩ ነው። ጥንታዊ ታሪክን በመፋቅ፣ ባልተደረገና ባልተፈጸመ ታሪክ ለመተካት ወያኔ/ኢህአዴግ እያንዳንዱን የአበውን የታሪክ ማህደር በማጥፋት፣ እንደ አቡነ ጴጥሮስ የመሳሰሉ የጀግኖችን ሀውልት አሻራ በማፍራረስ ርካሽ የሆነ ግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ማስገኛ ስራ ላይ በመሰማራት ሀገራችንን ወደኋለዮሽ እድገት እየጎተቷት ይገኛሉ።
ሁለቱን ገዳዮች የሚያገናኛቸው፤ የግራዚያኒ ወታደር አበው ለነጻነታቸው ለአንድነታቸው ሲያደርጉት የነበረውን ተጋድሎ ለማስቆም፤ የህዝቡን የትግል ሞራል ለመግደል የአዲስ አበባን ነዋሪ ቁጥሩ 30ሺ የሚሆን ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ ፋሽስትነቱን ለማሳየት ያደረገው ያልተሳካ ሙከራ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያውያን ለነጻነታቸው የሚያደርጉትን ትግል ይህ አልገታቸውም። በተመሳሳይ ደግሞ ዘመን አመጣሹ የየካቲት አስራ አንዱ ወያኔም፤ እንደፋሽስቱ ሁሉ በንጹሃን ህዝባችን ላይ በጎንደር ስላሴ፣ በምርጫ 97፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ፣ በኦሮምያ፣ በአዋሳ፣ በሀረር አሁን ደግሞ በሙስሊሙ ወገናችን ያደረሰው ጭፍጨፋ፣ እስርና ግድያ ከግራዚያኒ ጋር ያመሳስለዋል። ልዩነታቸው ይሄኛው ሀገር በቀል ወራሪ መሆኑ ነው። ምን አልባትም ወያኔ ልደቴ ብሎ የሚጨፍርበት የካቲት 11 ለሱ የድል ቀን ሲሆን፤ ለእኛ ደግሞ አባቶቻችን የምናስታውስበት የመከራ ቀን ነው።
በየካቲት12 የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ፣ ለአንድነቱ፣ ለሀገሪቱ ከብር የፋሽስቱን ወራሪ ሃይል በመመከት፤ ልጅ አዋቂ ሳይለይ ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን በማስጨነቅ እየሞቱም አልበገርነታቸውን ያስመሰከሩበት ልዩ ቀን ነው። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት ሀገር እንድትሆንም በማድረግ፤ ወርሃ የካቲት ታሪካዊ ወርና በድል አጥቢያነት በሀገራችን እንዲሁም በአሁጉራችን አፍሪካ ዘለአለም እንዲታወስና እንዲዘከር አድርገው አበው አልፈዋል። ይህን የማስጠበቅ ታሪካዊ የሞራል ግዴታ የማን ነው?
አበው የፋሽስቱን የግራዚያኒ ወራሪ ጦር ድባቅ በመምታት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሀገራችንን ከጠላት ወራሪ አድነው አስረክበውናል። በዚህ ታሪካዊ ገድል በሆነው በወርሃ የካቲት የተሰዉት ጀግኖች፣ የኢትዮጵያ ልጆች አጥንትና ደም መሰዋእትነት ከቶ ከታሪክ ማህደር የማይጠፋ ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። ይህ ትውልድ ይህን የማስጠበቅ የታሪክ ባለተራ ነው እንላለን።
ግንቦት 7፣ የአባቶቻችንን ጀግንነትና ወደር የሌለውን የሀገር ፍቅር፣ የሀገር ክብር፣ የቁርጠኝነት መንፈስና የአደረጉት መሰዋእትነት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ይታገላል። በቁርጥ ቀን ልጆች በቁርጥ ቀን ሰዓትም ለመድረስ፤ እስከመጨረሻው በመታገል ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣትና ይህን ድል ለማስመለስ፤ አስመልሶ ለትውልድ ለማስረከብ፣ ለማስጠበቅ እያንዳንዷን ደቂቃ ሊጠቀምባት ቆርቶ ተነስቷል።እርሰዎስ?
የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡- የኢትዮጵያ ጀግኖች እነ አጼ ሚኒሊክ፣ የበላይ ዘለቀ፣ እነ አብዲሳጋ፣ እነ ዘራይደረስ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አፄ ዮሃንስ፣ እንደ ቋራው ካሳ እና ሌሎችም በበቀሉበት፣ በተፈጠሩበት በጥቁር አፈር ምድር፤ ፀረ-ኢትዮጵያ ሀገር በቀል ዘረኛ ሃይሎች መፈጠራቸው አሳዛኝ ታሪክ መሆኑን እኛም እንመሰክራልን። ይሁን እንጅ፣ ቅሉ ይህንን በሁለት ትውልድ መካከል የተፈጠረውን የሰማይና የምድር ልዩነት ቁጭ ብለን በማየት ከንፈራችንን እየመጠጥን የምንቀመጥበት ሰአት ላይ አይደለንም። ጥሪ ከወዲያ ማዶ እየተበራከተ ነው። የድረሱልን ጥሪ!
ስለዚህም መላው የሀገራችን ህዝብ ወያኔን ለማስገደድ አሊያም ለማስወገድ አቅሙ በፈቀደ ሁሉ በገንዘብ፣ በእውቀት በጊዜና ጉልበቱ በመርዳት ታግለን የካቲትን የመሰዋእትነት መንፈስ እያስታወስን፣ ግንቦት 7ን የህዝብ ድምጽ ለማስከበር ይህ ትውልድ ሞራላዊ ግዴታ አለበት እና እንነሳ! እንሂድ።
በአንጻሩ በወያኔ መንደር በአጋጣሚም ሆነ በጥቅም ምክንያት ያላችሁ፡- እንደ ጠዋት ጤዛ ብን ብለው ከሚጠፉ አምባገነኖች ጋር በመለጠፍ ህዝባችንና ሀገራችንን መበድልና ማሰቃየት ለታሪክ ተጠያቂነት ይደርጋል። በወንጀል ተባባሪነት ስለሚያስጠይቅ ከወዲሁ መንገድን በማስተካከል እምቢ ለህወሃት፣ በቃኝ ባርነት፤ በሚል የህዝብ አጋርነትና ድጋፍ ወደ አለው የነጻነት ትግል በመቀላቀል ከማይሻር፣ ከማይጠፋ የታሪክ ማህደር ውስጥ ራስዎትን ያስገቡ ዘንድ የካቲት ጥሩ አጋጣሚ ነው።
በተለይም ኢትዮጵያውያን አርበኞች በጠላት ላይ የወሰዱት የማያዳግም እርምጃ ለመድገም እና ኢትዮጵያን ከሀገር ውስጥ ጠላት ከሆነው ህወሃት ለመታደግ፤ ነፃነታችንን አሳልፎ ላለመስጠት፣ ብርቱ ክንዳቸውን በአኩሪ መሰዋእትነት ለማሳረፍ እና ሕያው ምስክር ለመሆን ከተነሱት ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ጋር ሆነን በጋራ በተባበረ ሃይል የምንታገልበት ጊዜ ዛሬ ነው።
                               ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!