Monday, March 3, 2014

ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ)


ከፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ
አንድ ጥናት ሳነብ፥ ምናልባት እናንተም አንብባችሁት ይሆናል፥ የተፈጥሮ ሀብት ባላት ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከተራቡ፥  የማሰብ ችሎታቸው ዝቅተኛ ቢሆን ነው ሲል አገኘሁት። “ጥልቀት የሌለው ረጋ-ሠራሽ ጥናት ነው” ብዬ ጣልኩት። የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ባለጠጋ መሆኗን እርግጥ ባለሞያዎች የመሰከሩት ነው። ማዳበሪያ የማያስፈልገው መሬት ታርሶ አያልቅም። የወንዞቿ ውሀ ለጎረቤት አገሮች ሳይቀር ይተርፋል። ይኸንን እውነታ በቀጥታ ከተመራማሪዎቹ  አፍ ለመስማት የፈለገ ፕሮፌሰር ስዩም ገላየን ማዳመጥ ይችላልProf Getachew Haile Ethiopia
እንዲህ ከሆነ፥ ትኩረቱ በኢትዮጵያውያን የማሰብ ችሎታ ላይ ሊሆን ነው። እውነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ተመጽዋች ሆኖ የቀረው የማሰብ ችሎታው ዝቅተኛ ሆኖ ነው? አይመስለኝም።  ሰውየው ጥናቱን ማስተካከል አለበት። አለዚያ፥ ከዚያ ቀጥሎ፥ “አንድ ሰው እሱቁ ውስጥ ከመስተዋቱ በስተኋላ ድፎ ዳቦ እያየ ከተራበ የአስተሳሰብ ችሎታው ዝቅተኛ ቢሆን ነው” ሊለን ነው። ምንም ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ ቢኖረው፥ ዳቦውን እንደማያገኘው ለማንም ግልጽ ነው።
እርግጥ ነው፥ በአስተሳሰብ ደከም የሚል ሰው ሊጎዳ ይችላል። ሌላው ቢቀር፥ የብልሁ ጓደኛውን ያህል አይደላውም።  ግን በከፍተኛ ደረጃ የማሰብ ችሎታ ያለው ሰውም ሊቸገር ይችላል።  ስንቶች ናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በችግር የሚኖሩ፥ መውጫ ቢያገኙ ግን ለሌላው ሳይቀር የሚተርፉ? በአፍሪካ፥ በአውሮፓ፥ በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በማስተማርና በምርምር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቊጥር ቀላል አይደለም። በንግዱ ዓለምም ቢሆን፥ “የሺ ብር ጌቶችን” ጓዳ ይቊጠራቸው።
የለም፥ የተፈጥሮ ሀብት ባለጠጋ የሆነች ኢትዮጵያ ብልሁ ሕዝቧ ለምን እንደሚራብ የተከበረ ጥናት መደረግ አለበት። ዋና ዋናዎቹን ምክንያቶች ፕሮፌሰር ስዩም ገላየ ደርድሯቸዋል። አንዱ፥ የመሬት ይዞታ መበላሸት ነው ይለናል። “የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬው የታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል። ሌላው፥ አገሪቱ በክልል መከፋፈል ነው። ማንም ሰው በገዛ ሀገሩ ከመሰለው ክፍለ ሀገር ሄዶ በሰፊው ማረስ አይችልም። ዛሬ ኢትዮጵያ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ሙሉ በሙሉ አገሩ አይደለችም። ኢትዮጵያ ለልጆቿ እናትነቷ በሙሉ ሰውነቷ እንዳይሆን ተከልክላለች።
የታሪክ ተመራማሮዎችም ያዩት ምክንያት ይኖራቸዋል። ክርስቲያኖችና እስላሞች፥ ኦሮሞዎችና ሌሎች መሆናችንን ዐውቀን በብልህነት አለማስተናገዳችን ጒዳት እንዳመጣብን ይናገራሉ። ሁላችንም የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች፥ አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብንሆን ኖሮ ከምሰሶ ጋር በእግር ብረት እንደተቈራኘ ሰው እጃችንን ብቻ ወደ እግዚአብሔር እያደረስን አንድ ዘመን ላይ ቆመን አንቀርም ነበር ይላሉ።
በሃይማኖት አንድ ባለመሆናችን ያስከተለውን ጕዳት ለማሳየት የአክሱምን ሥልጣኔ ያከሰመውን የጉዲትን አመፅና የአምሐራን (“የአማራን” ማለቴ አይደለም) ሥልጣኔ እሳት የለቀቀበትን የግራኝን ወረራ ይተርካሉ። እነዚህ ሁለት ሥልጣኔዎች ኢትዮጵያን በዚያ ዘመን ከገነኑ አገሮች እኩል አስሰልፈዋት ነበረ፤ ጠፉ፤ ባለንበት ቆመን ቀረን። ዛሬ ስለሁለቱ ሥልጣኔዎች የምናውቀው ከመጥፋታቸው በፊት ከተጻፈው ታሪካቸውና ከጥፋት ካመለጠው  ርዝራዣቸው ነው። ሀገሪቱ ከግራኝ ምች ልታንሰራራ አልቻለችም። የግራኝ ምች የምለው እስላሞች በዓሥራ ስድስተኛው ምእት ዓመት በክርስቲያኖች ላይ ያደረሱትን ጒዳት ነው። ታሪኩን ክርስቲያኖቹ በሐዘን፥ እስላሞቹ በደስታ መዝግበውታል፤ ዛሬም በዚያው ስሜት ያስታውሱታል። የደረሰው የሰውና የንብረት ጥፋት ሁሉ የሚያሳዝን ቢሆንም፥ ሁልጊዜ የሚታወሱኝ ቅጂ ያልተገኘላቸው ስማቸው ብቻ የቀረልን ብርቅ ድርሰቶች ናቸው።
እስላሞቹ ክርስቲያኖቹን ለማጥፋት ከጂሃድ በቀር ሌላ ምንም ምክንያት አልነበራቸውም። መንግሥቱን ተወደደም ተጠላ ያቋቋሙት ክርስቲያኖቹ  ነበሩ። ከሀገሪቱ ክፍል ሱማሌዎችና ይፋቴዎች እንደሚኖሩባቸው አንዳንድ ክፍሎች ሲሰልሙ፥ በኢትዮጵያ ስር ሆነው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ሙሉ ሥልጣን ተሰጥቷቸው ነበረ። በዛሬው ዓይናችን እንኳ ስናየው፥ የንጉሣዊው መንግሥት  ከዚህ የተሻለ ሌላ ምን አማራጭ አገዛዝ ነበረው? የጂሃዱ መንሥኤ ኦርቶዶክሱን ሕዝብ በሞላ አስልሞ በሸሪዓ ሕግ መግዛት  ነበር። እስላሞቹ፥ “መንግሥቱን ወስደን፥ ክርስቲያኖቹ ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እናደርጋለን” ቢሉ እንኳን ያባት ነበር።
ኦሮምኛ ተናጋሪዎችና ሌሎች መሆናችን ያስከተለውን ጕዳት ለማሳየት ደግሞ የኦሮምኛ ተናጋሪ ጎሳዎችን ወደማህል ኢትዮጵያ የመፍለስ ታሪክ ይተርካሉ። ለአባ ባሕርይና የዘመኑን ነገሥታት ታሪክ ለጻፉ፥ በተለይም ለተክለ ሥላሴ ጢኖና ለተክለ ኢየሱስ ዋቅጂራ ምስጋና ይድረሳቸውና የኦሮሞ ጎሳዎች ወደማህል ኢትዮጵያ ፍልሰት ያስከተለው የሥልጣኔ ውድመት ከብዙው በጥቂቱ ተመዝግቧል። ኦሮምኛ የሚናገሩ ጎሳዎች የእስላሞቹ አመፅ በተገታ ማግስት ፈልሰው፥ ከእስላሞቹ የተረፈውን የሥልጣኔ ምልክት ጠራረጉት። ጋዳ በሚሉት ሁሉን ለጦርነት በሚያሰልፍ የማፊያ ሥርዓት በውትድርና ተደራጅተው፥ በግብርና፥ በንግድ፥ በድብትርና (“በዕውቀትና በምርምር” ማለቴ ነው) የሚተዳደረውን ሰላማዊ ሕዝብ አረዱት፤ ንብረቱን አወደሙት። በእርሻው፥ በሰብሉ ላይ ከብታቸውን አስሠማሩበት። በባህላቸው መሠረት፥ ክርስቲያን ያልገደለ በቅማል ይሰቃያል እንጂ ራሱን አይላጭም ነበር። ሸዋን፥ ጎንደርን፥ ጎጃምን፥ አምሐራን (የዛሬውን ወሎ) ደመሰሷቸው።
እስላሞቹ የክርስቲያኖቹን ሥልጣኔ አጥፍተው በራሳቸው ሥነ ጽሑፋዊ ሥልጣኔ ሊተኩት አስበው ነበረ። ኦሮምኛ ተናጋሪዎቹ ግን እረኞች ስለነበሩ ሥልጣኔን በሥነ ጽሑፋዊ ሥልጣኔ የመተካት ግዴታ አልነበረባቸውም። ግን በባህል ረገድ ከወረሩት ሕዝብ አብዛኛውን እንደነሱ ኦሮምኛ ተናጋሪ፥ የቀረውን ገበር (አሽከር) አደረጉት። እስላሞቹና ኦሮምኛ ተናጋሪዎቹ ሰውና ቅርስ ባወደሙበት ቦታ ሁሉ ሐውልት ቢቆም ሀገሪቱ “ሀገረ ሐውልት” ትሆን ነበረ።
ከግድያቸው ሰለባቸው ይብስ ነበረ፤ ሴት ሳይቀር። የአዘዞ ባለቅኔው፥ “ጃዊ ቀደደ ሆድ ሆድሆዶሙ ወሰለቦሙ እስከ ሕምብርት” (ጃዊ ሆድ ሆዳቸውን ቀደደው፤ እምብርታቸው ድረስ ሰለባቸው) ያለው በጎንደር ዘመነ መንግሥት የደረሰውን መቅሠፍት አይቶ ነው። የወሎ እስላም ኦሮሞዎች በዘመነ መሳፍንት ስልጣን ሲይዙ ያወጁት እንዲህ ብለው ነበር፤
አልጋው ባይገባንም ረቢ ሰጠን፤ “ለጒግሣ ያልተገዛ  ወንዱን ቁላውን፥ ሴቱን ጡቱን ይሰለብ።”
የሆነውን በታሪክ ዓይን አይቶ በማለፍ ፈንታ፥ ዛሬ አቻው እንዲሆን ታስቦ ያልሆነ፥ ያልተደረገ የአረመኔነት ታሪክ ለራስ ጎበና ዳጨ ወታደር መፍጠር፥ ግፋ ቢል ሞኞችን በሞኝነታቸው እንዲኖሩ ከማድረግ የበለጠ አገልግሎት አይኖረውም። ውሸት ታሪክ አይሆንም።
ማንም መጥቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሰፍር የኢትዮጵያ ነገሥታት አይከለክሉም ነበር። ሰው የሌለበት ሰፊ ቦታ ስለሞላ ማንም ከዚያ ቢሰፍር ማን ነህ የሚለው አልነበረም። ችግሩ፥ ኦሮምኛ  ተናጋሪ ጎሳዎች ከአንድ ቦታ ፈልሰው ከባዶ ቦታ በመስፈር ፈንታ፥ ሌሎች ያቀኑትን ቦታና ያተረፉትን ቅርስና ውርስ እንንጠቅ ማለታቸው ነበር። በዚያ ላይ፥ ማህል ኢትዮጵያን ከያዙ በኋላ፥ ለኢትዮጵያ መንግሥት አንገብርም ማለትን አመጡ። በዚህ ጊዜ የንጉሣዊው መንግሥት ምርጫ ምን መሆን ነበረበት?
ያምናው በሽታ፤
በዚህ እኛ ባለንበት ዘመን፥ እስላሞች ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ፥ አንዳንድ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሰላማዊውን ሰው በሕይወት ገደል ሲሰዱ፥ በ ዩቲዩብ (youtube) ሳይ፥ ሰውየው፥ “ኧረ እናንተ ሰዎች ሰው አይድንም ታሞ፤ ያምናው በሽታየ አገረሸ ደግሞ፡” ያለው ትዝ አለኝ። በሽታውን ማስገርሸት አንዱን ጠቅሞ ሌላውን አይጐዳም። ሁሉም ተጐጂ ነው የሚሆነው። ሁል ጊዜ ሳይሞቱ መግደል አይቻልም። ሌላውን የሚገድሉት እየሞቱ ነው።
በዚያ ላይ በማህል ቤት የሚሆነውን ማንም አያውቀውም። ለምሳሌ፥ የኦሮሞን አመፅ ይመሩ የነበሩ የወለጋ ፕሮቴስታንቶች እንደነበሩ ይታወሳል። አሁን አመፁን ከነሱ ተቀብለው በኦሮሞ ስም የሚያካሂዱት፥ “ከኦሮሞው ሕዝብ አርባ በመቶው እስላም ነው” የሚሉ የኦሮሞ እስላሞች ናቸው። ቊጥራቸውን ቢያጋንኑትም፥ እስላሞቹ ከፕሮቴስታንቶቹ መብለጣቸው አያጠራጥርም።  እንግዲህ፥ የፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መንግሥት  ላይ  ያካሄዱት ትግል በፍትሐ ነገሥት ቀርቶ በሸሪዓ ሕግ በሚያምኑ ወገኖች ለመተዳደር ሊሆን ነው።  የግብጽ ክርስቲያኖች የመለካውያን ክርስቲያኖችን የበላይነት በመጥላት አገሪቷን ዐረቦች እንዲወስዷት ረድተው፥ ዋጋ ከሌለው ጸጸት ላይ እንደወደቁ የምናየው ነው።
የመጀመሪያው እርምጃ፤
ከላይ እንደገለጥኩት፥ እስላሞችና ኦሮምኛ ተናጋሪ ጎሳዎች ኢትዮጵያን እንዴት እንዳቈረቈዟት ታሪኩ እንዳይፋቅ ሆኖ ተጽፏል፤ የሚፈለገው ግን ዕርቅና ሰላም እንዲወርድ ነው።  ዕርቅና ሰላም የሚወርድ ከሆነ፥ ታሪኩ ባይፋቅም ተከትቶ፥ ከድንቊርናና ከረኀብ የምንላቀቅበትንና ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ እንዳለን የምናስመሰክርበትን ብልሀት ልንፈልግ እንችላለን። ለዚህም መሆን ያለበት የመጀመሪያው እርምጃ አባቶቻችንን እንወክላለን የሚሉ እስላሞችና ኦሮሞዎች የአባቶቻቸውን ጥፋት ከመቀጠል አባቶቻችው በኢትዮጵያ ላይ ላደረሱት መጠን አልባ ጥፋት የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ ይሆናል።
የጥፋቱን ታሪክ ጸሐፊዎቹ ለወገኖቻቸው እያዳሉ ጽፈውታል  እንዳይሉ፥ የጻፉት ራሳቸው እስላሞቹ እነሽሀብ እዲን ዐረብ ፈቂህ፥ የአማራውና የኦሮሞ ተወላጆች እነ አባ ባሕርይ፥ እነ ተክለ ሥላሴ ጢኖ፥ እነ ተክለ ማርያም ዋቅጂራ ናቸው። ታሪካችንን ደብተራዎች አይጽፉትም የሚሉ ካሉ፥ የጸሐፊዎቹን ማንነት ባለማወቅ ሊሆን ይችላል። የሌሎችም ታሪክ ጸሐፊዎች ስማቸውና ሥራቸው “የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፤ ኦሮሞችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋራ” በተባለው መጽሐፌ ውስጥ ተዘርዝሯል።
ይህን መጽሐፍ ብዙ ሰው ስለሚፈልገው፥ ማንም ሰው  እያወረደና እያተመ  እንዲያነበው በማሰብ፥ www.ethiopiawinnet.net or www.ethiopiawinnet.org  ብለን ካቋቋምነው ድረ ገጽ ላይ ተለጥፏል። ኢትዮጵያን ለማገልገል ላቋቋምነው ድርጅት እርዳታ የሚሆን በፈቃድ ከሚሰጥ ገንዘብ በቀር የመጽሐፉን ዋጋ አንጠይቅም።
ሁለተኛው እርምጃ፤
ሁለተኛው እርምጃ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን የሚመለከት ነው፤ አፄ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጨ ስፍር ቊጥር በሌለው ጎሳ የተበታተኑትንና እርስ በርሳቸው አሁንም የሚባሉትን ኦሮምኛ ተናጋሪዎች አንድ ያደረጉበትን ቀን በየዓመቱ ማክበር አለባቸው። ግን ሁሉንም አንድ ያደረጉት በአንድ ቀን ድል ስላይደለ፥  የትኛውን ቀን እንደሚያከብሩ በጨፌያቸው ሊወስኑት ይችላሉ። ሆኖም በአፄ ምኒልክ ሐውልት ስር አበባ ማስቀመጥ የበዓሉ ክፍል መሆን አለበት። ራስ ጎበና ሐውልት ስለሌላቸው፥ ሳይውል ሳያድር ከተከበረ አደባባይ ላይ የጎላ ሐውልት እንዲተከልላቸው ባለውለታዎቹ መገፋፋት ይኖርባቸዋል።
ሶስተኛው እርምጃ
ሶስተኛው እርምጃ አስተሳሰብን ከሰብአ ትካት አስተሳሰብ ወደ ሰብአ ዘመን አስተሳስብ ማራመድ ነው። ‘”ሰብአ ትካት” በእንግሊዝኛ primitive people የሚባሉት ናቸው። አስተሳሰባቸው ከመንደራቸው ርቆ አይሄድም፤ የዚያኛው መንደር ሰው ጠላታቸው ነው፤ የዚያኛው ብሔረ ሰብ አባል ባለጋራቸው ነው። “ሰብአ ዘመን” modern man ነው። መንደሩ ጠቅላላዋ ሀገር ነች። በሰብአ ዘመን አስተሳሰብ የዚያ መንደር ወይም የዚህ መንደር ነባር መሆንና የዚያ ቋንቋ ወይም የዚህ ቋንቋ ተናጋሪ መሆን ዋጋ ሊሰጠው የማይገባ አጋጣሚ ነው። የሰብአ ዘመን አስተሳሰብ ከዚያም መጥቆ ሄዶ ዓለም አቀፍ ላይ ይደርሳል። በሰብአ ትካት አስተሳሰብ ያሉ ብሔርተኞችን በአንድ ጊዜ ወደዓለም አቀፍ አስተሳሰብ ይሸጋገራሉ ብለን አንገምትም፤ ለጊዜው ፍላጎታችንም አይደለም። ግን በሰላምና በብልጽግና ለመኖር ከብሔርተኛነትና ከሰብአ ትካት አስተሳሰብ ወጥቶ ዲሞክራት መሆን አማራጭ የሌለው እርምጃ ነው። በአካል የሰብአ ዘመን አባል ሆኖ በአስተሳሰብ ሰብአ ትካት መሆን፥ “የሚራቡት የማሰብ ችሎታቸው ዝቅተኛ ቢሆን ነው”  ለሚለው ጥናት ማስረጃ መሆን ነው።
እንደማየው፥ ብሔርተኞች ከዲሞክራሲ ጋር ያላቸው ግንኙነት በፍቅርና በጥላቻ የተሳሰረ ነው። የዲሞክራሲ ዋና መለዮ ሰብአዊ መብቶችን ማስከበር ነው። በአሁኑ ሰዓት ከገዢዎቹና ከደጋፊዎቻቸው በቀር ይኸንን የማይቀበል ያለ አይመስለኝም። እዚህ ላይ ብሔርተኞችና ዲሞክራሲ ፍቅረኞች ናቸው። ግን  ሰብአዊ መብቶች የሚባሉት የግለሰብ ብቻ ናቸው ወይስ ማኅበሮችና ብሔረ ሰቦችም ሰብአዊ መብቶች አሏቸው? የላቸውም ከተባለ፥ ብሔርተኞች ዲሞክራሲን አይቀበሉም።
መብት በመሠረቱ የግለሰብ ነው። ሆኖም ብሔረሰቦች በደፈናው መብት የላቸውም አይባልም። አቅም ካላቸው ቋንቋቸውንና ሌላ ሌላ ባህላቸውን ማዳበር መብታቸው ነው። ይኸንን በሥራ ላይ ለማዋል ሲሰበሰቡ ጸጥታቸውን መንግሥት ያስከብርላቸዋል። የአንድ ሀገር ሕዝብ ሆኖ ብሔረሰባዊ  ፓርቲ መመሥረት ግን ከሌላው ብሔረ ሰብ ጋር የጋራ ጥቅም የለንም ማለት ይሆናል። የፓርቲ መሠረቱ የግለሰብን ሕይወት በኢኮኖሚ እድገት ማሻሻል ነው። ለዚህ ዓላማ ፓርቲው ጉራጌ፥ አደሬ፥ ጉጂ፥ ወዘተ መሆን የለበትም።  ሆኖም፥ የብሔረሰብ አባላት በይፋ አድመው ድምጻቸውን ይጠቅመናል ለሚሉት ፓርቲ ሊሰጡ ይችላሉ። በዲሞክራሲ አስተዳደር ብሔርተኞች ብሔራቸውን የሚጠቅሙት በዚህ መንገድ ብቻ ነው።

የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮያ ዉስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳለ በዘንድሮዉ አመታዊ ሪፖርቱ ይፋ አደረገ


ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 20/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (State Department) ባወጣዉ የዘንድሮ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያከናዉናቸዋል ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመዘርዘር ሰፋ ባለ መልኩ አቅርቦታል።
ቀድም ሲል ኢትዮጵያ ዉስጥ በ2003 በተደረገዉ ምርጫ፤ በሟቹና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ይመራ የነበርዉ ኢ.ህ.አዴ.ግ ከ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ 545 መቀመጫዎች አሸንፏል መባሉን ሪፖርቱ እያመላከተ የምርጫ ጣቢያዎች በመንግስት ሐይላት ቁጥጥር ስር እንደነበሩና አለምአቀፍ ታዛቢዎች ስራቸዉን በተገቢዉ መልኩ እንዳያከናዉኑ ገደብ እንደነበረባቸዉ ይገፃል።John Forbes Kerry current United States Secretary of State.
በአገሪቱ ዉስጥ ባለዉ ከፍተኛ የመብት ረገጣ ሳቢያ ዜጎች የመሰብሰብ፣የመደራጀት፣የመናገር መብትን በገሃድ እንደሚነፈጉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ያስደረግቸዉን ጥናቶች ተመርኩዞ ያብራራል። እነዚህን የዲሞክራሲ እሴቶችን ለመተግበር የሚሞክሩም ይታሰራሉ፣ይንገላታሉ፣ይዋከባሉ፣ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ ክብራቸዉ ተነክቶ እንዲሸማቀቁምይደረጋሉ በማለት ሪፖርቱ ያትታል።እርዳታን የሚያስተባብሩ፣ እርዳታን ለጋሽ የሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበራዊና ትርፍ አልባ የሆኑ ተቋማት (NGO) የግብረ-ሰናይ ተልእኮ አቸዉን እንዳይፈጽሙ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚከለክል፤ በሰዎች ላይ ህገ ወጥ የሆነ ግድያ እንደሚፈጽም፣ዜጎች ግርፋት-ድብደባ እንደሚደርስባቸዉ፣ ወጥ የሆኑ የማሰቃያ ተግባራት በመንግስት ሐይላት እንደሚፈጽምና በአገሪቱ እስርቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን ህይወት ለአደጋ የሚያጋልጹ አሳቃቂ ተግባራትም እንዳሉም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።
ሰዎች በፍርድ ቤት ሳይበየንባቸዉ በጅምላ ተይዘድዉ ይታሰራሉ፤በፍርድ ቤት የአሰራር ዘይቤም ይሁን በፍትህ ሒደቱ ዉስጥ ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት አለበት፤ ፍርድ ቤቶችም ደካማ ናቸዉ! ሲል ሪፖርቱ ይደመድማል። መንግስት ሀሳብን በነጻነት ለመግለጽ የሚሞክሩ ያገሪቱ ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እንደሚወስድ በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን፤ በነሐሴ 2/2005 የኢድ-አልፈጥር በዓል በሚከበርበት ወቅት፤ በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሞ ያሰሙ ከነበሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን መካከል ከ 1000 በላይ የሚሆኑት በጅምላ ተግበስብሰዉ መታሰራቸዉና ከመካከላቸዉም የሞቱ መኖራቸዉ በሪፖርቱ ላይ አጽንኦት ተሰጥቶታል።የዜጎች ግላዊ መብትን በመግፈፍ፤ በሙስሊሙ ማህበረስብ ላይ ህገወጥ የሌሊት ፍተሻዎችም ተደርገዋል። ግልጽና ስልታዊ በሆነ መልኩም ከቦታ ወደ ቦታ ዜጎችን የማፈናቀል መርሃግብር በመንግስት መፈጸሙን የሚያስረዳዉ ሪፖርት ነጻ መሆን የሚገባዉ የመማርና የማስተማር ሒደት የመንግስት ጣልቃገብነት እንዳለበትም ይገልጻል።
ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸዉን ተጠቅመዉ በነጻነት መንግስትን የመቀየር አቅማቸዉ ሆን ተብሎ የተገደበ ነዉ!በፖሊስ፣በፍርድ ቤቶችና በመንግስት አመራር ዉስጥ በስልጣን መባለግ-ሙሰኝነት-ጉቦኝነት በገሃድ ይተገበራሉ። መንግስት በስልጣን የባለጉንና የህዝብን አደራ ያጎሳቆሉ ወንጀለኞች ችላ በማለት ፖለቲካዊ ዉለታን ይዉላል፤ ፖለቲካዊ ምህረትን ለምግባረ ብልሹ የመንግስት አካላት እንደሚያደርግ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ያጋልጻል።
በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የጾታ እኩልነት የተረጋገጠ ቢሆንም በመንግስታዊ የአሰራር መዋቅር ዉስጥ ሴቶች ይጨቆናሉ። ህገወጥ የሆነ የሰዉ ዝዉዉር ይፈሰማል፣ የአካል ጉዳተኞች (የተሳናቸዉ) ማህበራዊ ጭቆና ይደርስባቸዋል፣የ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህሙማን ማህበራዊ የሆነን በደል ይጋፈጣሉ፣የሰራተኖች መብት የተገደበ በመሆኑ ህፃናትን አስገድዶ የጉልበት ስራ ማሰራቱ የተለመደ መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተዘርዝሯል።
የመንግስት ሐይላት የሰዎችን ደብዛ ያጠፋሉ፤ የሰዎች መሰወር ይስተዋላል! በትግራይ ክልል በአላማጣ ከተማ መንግስት በልማት ስም ቤቶችን በሚያፈርስበት ወቅት አለመግባባት ተፈጥሮ የታሰሩ 12 የአካባዊ ተወላጆች የገቡበት እንደማይተዋቅ እና ተመሳሳይ በሆነ መልኩ በሶማሌ ክልል ያለዉ ልዩ የፖሊስ ሐይል በክልሉ ተወላጆች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ማንገላታት፣ማሰቃየት፤ ግድያ እደሚፈጽም መታወቁ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ህገመንግስት ቶርቸር (ግርፋት ድብደባ ማሰቃየት)ይከለክላል። ቶርቸርን የመሰሉ የሰዉ ልጅን ክብር ገፋፊ የሆኑ ጭካኔ የተሞላባቸዉ ተግባራት፤በመንግስት የደህነነትና የጥበቃ ሐይላት እንደሚፈጸሙ በማጋለፅ በጥር 9/2005 የተያዘዉ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሔት አምድኛ እና ማኔጂንግ ኢዲተር የነበረዉ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በማእከላዊ የምርመራ ማእከል ዉስጥ በተደጋጋሚ የዚሁ ህገወጥና አስከፊ ተግባር ሰለባ እንደነበር በዩናይትድ እስቴት የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ላይ በዋቢነት ተጠቅሷል።
በጥቅምት 8/2006 ሁማን ራይትስ ዎች ያወጣዉን ሪፖርት እንደ አብነት በመጥቀስ በመጥቀስ በማእከላዊ የምርመራ ማእከል ዉስጥ መርማሪዎች ታሳሪዎችን በማስገደድ የእምነት ቃል እንደሰጡ እንደሚያደርጉ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እየገለጸ፤ በማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ ቶርቸር (ግርፋት-ድብደባ-ማሰቃየትት)፣ ዛቻ፣ማስፈራራርት፣ እስረኞች ላይ ዉሃ መድፋት፣የእስረኞችን እጅ ጣራ ላይ አስሮ ለረጅም ሰዓታት ማቆም፣እሰረኞችን ነጥሎ ለብቻ ማሰርን የመሳሰሉ ኢሰብዓዊ ተግባራት እንደሚፈጽሙና ዲፕሎማቶች፣ኤንጂኦ (በጎ አድራጊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ትርፍ አልባ ድርጅቶች) እስረኞችን የመጎብኘት ፍቃድ እንደሚነፈጉ ተገልጿል።
በመስከረም 2005 በተገኘዉ መረጃ መሰረት ከ70,000 እስከ 80,000የሚድርሱ እስረኞች መኖራቸዉ ሲታወቅ፤ ከነዚህም መካከል 2500ሴቶች ሲሆኑ 600 ህጻናት ከእናቶቻቸዉ ጋር መታሰራቸዉ እና ታዳጊ ወጣቶች ከአዋቂዎች ጋር አብረዉ እንደሚታሰሩ ተዘግቧል። የአገሪቱ እስር ቤቶች በጣም የተጣበቡ ከመሆናቸዉም ባሻገር ወታደራዊ ተቋማትም እንደ እስር ቤት ማገልገላቸዉ ተዘግቧል። በርካታ እስረኞች ከመጣበብ፣ተነጥሎ ከመታሰር፣ የተማሏ የጤና ግልጋሎት ካለመኖሩ የተነሳ ለአእምሮ ህመም ይዳረጋሉ። ለአንድ እስረኛ የምግብ፣ የዉሃ አቅርቦትን ለመለገስ እና የጤና ግልጋሎት ለመስጠት በቀን ስምንት ብር ከአስር ሳንቲም ብቻ እንደተመደበ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አመታዊ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ይዘረዝራል።
ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ከ2004 ጀምሮ ሰላማዊ የሆነ ተቃዉሞን በአወሊያ የትምርት ተቋም ዉስጥ በመጀመር ከአርብ ስግደት (ከጁመዓ ሶላት) በሗላ በቀጣይነት የተቃዉሞ መርሃግብር እንደሚያከናዉኑና፤ ይህ የቅዋሜ ተግባር ምንም ሰላማዊ ቢሆንም የፖሊስ አካላት ሰዎችን በመያዝ አላስፈላጊ ሐይል እንደሚጠቀሙ ሪፖርቱ ያስረዳል። በሐምሌ 14/ 2004 በሙስሊሞች የተደረገዉን ሰላማዊ ተቃዉሞ ተከትሎ መንግስት “የደህንነት ሰጋት” የሚል ማመካኛን በመፍጠር 28 ሙስሊሞችን አስሮ በጥር 24/2005 ክስ ያቀረበባቸዉ ቢሆንም በታህሳስ 3/2006 አስሩን በነጻ አሰናብቶ በአስራ ስምንቱ ላይ ያቀረበዉን ክስ ዝቅ አድርጓል። መንግስት እነዚህን የሙስሊም ታሳሪዎች በአለማችን ላይ ከሚታወቁ አሽባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸዉ ብሎ በገሃድ ለመፈረጅ መሞከሩም በሪፖርቱ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት የመናገር-የመደራጀት-የመሰብሰብን መብት የሚተገብሩ ፖለቲከኞችናና ጋዜጠኞችን እንደሚያስር፣ እንደሚያሰቃይ፣ እንደሚያንገላታ፣ የሚገልጸዉ ሪፖርት ከፖለቲከኞች የመድረኩ አንዱአለም አራጌ ብሎም የኦሮሞን ማህበረስብ መብት በዲሞክራሲ ለማስከበር ከሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ተወላጆች በቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳ ታስረዉ እየተሰቃዩ መሆናቸዉን፤ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ከጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ሪዮት አለሙና ሰለሞን ከበደ በእስር ይማቅቃሉ ሲልም ሪፖርቱ ያስረዳል።
መንግስት ነጻ-ፕሬስ እንዲከስም በሚያደርገዉ ከፍተኛ ጫና ጋዜጠኞች የእስርና የስደት ሰለባ

ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ


ገለታው ዘለቀ
የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ።
በርግጥም ሁላችን  ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣  እንደገና መልሰን  የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው።
በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢተ ዳንዔል ላይ ኣንድ ናቡከደነጾር የተባለ ንጉስ ኣንድ ጊዜ ጠቢባንን  ጠርቶ የህልም ፍቺ ይጠይቃል። ጥበበኞቹም ህልሙን ንገረንና ፍቺውን እንነግርሃለን ሲሉት ህልሙ ጠፍቶብኛል ስለዚህ ህልሙንም ፍቺውንም ውለዱ ብሎ ጉድ እንዳፈላ እናነባለን።
እኛ ኢትዮጵያዊያን የዋናው ችግር ተጽእኖዎች የየእለት ኑሮኣችንን ሲያምሱት ብናይም ዋናውን የችግሩን ምንጭ መፈለጋችን ግን ኣሁንም ትክክል ነው።
የሃገራችንን ዋና ችግር የት ጋር ነው ብለን ኣጥብቀን ከጠየቅን በርግጥ የስርዓት ችግር ነው ወይ? ስርዓት በማጣታችን ነው ወይ የከፋ ችግር ላይ የወደቅነው? ብለን እንጠይቃለን።  በዚህ ኣገባብ ስርዓት ስንል የኣይዲዮሎጂውን ጉዳይ ሳይሆን ፍትህና ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና የህዝብ የበላይነት የሚንሸራሸርበት ሲስተም ተዘርግቷል ወይ ብሎ የመጠየቅ ያህል ነው።  ስለ ስርዓት ስናነሳ ደግሞ በዋናነት የሚታየው ህገ- መንግስታዊ ስርዓቱ ነው። ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ምን ያህል ለዜጎች ይጨነቃል፣ ምን ያህል ለፍትህና ለነጻነት ለህዝቦች ጥቅም መንሸራሸሪያ ይህናል? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። በዚህ ረገድ በርግጥ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም በዋናነት ግን ችግራችን የስርዓት ችግር ሆኖ ኣናይም። ለኣብነት የ1955ቱን ህገ መንግስት ስናይ የፕሬስ ነጻነትን ይሰጣል፣ እኩል የህግ ከለላ ይሰጣል፣ የመሰብሰብ፣ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሁሉ ይሰጣል። የደርጉም ቢሆን ለዜጎች የሚጨነቅ ኣይነት ነው። “ኢትዮጵያዊያን በህግ ፊት እኩል ናቸው” ይላል። ከሁሉ በላይ ደግሞ የ1995ቱን ስናይ “ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው” ብሎ እጅግ ኣጠንክሮ ለዜጎች መብት መቆሙን ይደነግጋል። በውነቱ ይህ ኣንቀጽ ብቻውን ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ዋስትና ይሆን ነበር። ይሁን እንጂ ተግባራዊው እውነት ደግሞ ለብቻው በተቃራኒው ተንሰራፍቶ ይታያል። ይህ ለምን ሆነ? እንዴት እንዲህ ሊሖን ይችላል? ብለን ነው መጠየቅ ያለብን። እንዲህ ስንጠይቅ የችግሩ ዋና ጉዳይም የስርዓት እጦት ሳይሆን ሌላ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። በርግጥ ለወደፊቱዋ ኢትዮጵያ የተሻለ ስርዓት ማምጣት ያስፈልጋል። በተለይም ብዙህነቱዋን ተንከባክቦ የሚይዝ ማህበራዊ የፖለቲካ ስርዓት ያሻናል። ያ ማለት ግን ከችግራችን እንድንወጣ ብቻውን ዋስትና ነው ማለት ኣይደለም። የቱንም ያህል ጥሩ ስርዓት ዘርግተን ከችግራችን ሳንወጣ ልንቆይ እንችላለን። ርግጥ ነው የማንነት ፖለቲካ ማህበራዊ ቀውስን ያመጣ ችግሮች የበለጠ እንዲነዱ የሚያደርግ ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ መንግስት ውድቀት በሁዋላ ከዚህ የፖለቲካ መዋቅር መውጣታችን ለመፍትሄ ትልቅ በር ኣለው። ይሁን እንጂ ኣሁንም ቢሆን የቱንም ያህል ቆንጆ ስርዓት እናምጣ ኢትዮጵያን ከመከራና ከርሃብ የሚያወጣት እሱ  ብቻውን ኣይደለም። ታዲያ ምንድነው? የሚል ጥያቄ መምጣት ኣለበት። ኣዎ፣ ዋናው የሃገራችን ችግር ያለው የፖለቲከኖች ስብእና ተክለሰውነት ወይም ፐርሰናሊቲ ጋር የተገናኘ ነው።
ሃገራችን ከችግር እንድትወጣ ከተፈለገ የፖለቲካ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። የችግሮቻችን ቁንጮም የፖለቲካ ቁርጠኝነት እጦት ነው ብሎ መደምደም ይቻላል።የፖለቲካ ቁርጠኝነት ስንል ኣንድ ፓርቲ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ የፍርድ ቤቱን ልጓም ለቀን መልሶ ከበላንም ይብላን፣  በራሳችን ላይ ይፍረድብን፣  ብሎ በራስ ላይ የመወሰን ኣቋም ነው። ወታደሩን ኣገርህን ጠብቅ የፓርቲ ጠባቂ ኣይደለህም ኣንተ ኣገር ጠባቂ ነህ ለማለት የፖለቲካ ሰዎችን ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ፖሊሱን፣ ባንኩን፣ ሚዲያውን ሁሉ ልጓሙን ለቆ በሙያህ ኣገልግል ብሎ መወሰን ሲቻል ነው ከገባንበት ኣረንቋ የምንወጣው። የናፈቀንን ዴሞክራሲ በህይወት የምናየው። ጥያቄው ይህ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንዴት ሊመጣ ይችላል ነው። የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከጥቂት የፖለቲካ መሪዎች ከራስ ጥቅምና ዝና በላይ የህብረተሰብን ዝናና ጥቅም በተጠሙ ሰዎች ሊነቃነቅ ይችላል። ኣንድ ቁርጠኛ መሪ ኣገር ሊለውጥ ይችላል። በታሪክ የታዩ ኣንዳንድ ቁርጠኛ መሪዎች በየሃገሩ ተነስተው ጥሩ መሰረት እየጣሉ ኣልፈዋል። በሃገራችንም የተጠማነው ይህንን ነው።
በኣሁኑ ጊዜ ተቃዋሚው ክፍል መንግስትን ኣጥብቆ ማውገዙ ትክክል ነው። የህዝቡም ልብ ነጸብራቅ ነው። ይሁን እንጂ ይህ መንግስት በማንኛውም መንገድ ሲወድቅ ስልጣን ይዞ ጥሩ ስርዓት መዘርጋቱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ቁርጠኝነት (political commitment) ያላቸውን ሰዎች ይዘዋል ወይ? ብለን እንድናስብ ያደርገናል። በዚህ ረገድ ተቃዋሚው ጥቃቅን በሆኑ ፖሊሲዎች ከመከፋፈል ይልቅ ወደ ጋራ እያመሩ ከሁሉ በላይ የፖለቲከኞችን ስብእና የመገንባቱ ላይ ማተኮር ለነገይቱ ኢትዮጵያ ዋስትና ይሆናል። ይህን ስብእና ወይም ተክለሰውነት የመገንባት ስራ ፓርቲዎችን ቢዚ የሚያደርግ ወቅታዊ ስራ መሆን ኣለበት። ኢትዮጵያ በኣሁኑ ደረጃዋ ጥቃቅን ፖሊሲዎችን በማነጻጸር የምታማርጥበት ጊዜ ላይ ኣይደለችም። መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ያጣች በመሆኑዋ የስካንዲኒቪያው ኣይነት ዴሞክራሲ ይሻልሻል የኣሜሪካው ኣይነት? ማለቱ ያልበላትን የማከክ ያህል ነው። ሁሉቱም ሆኖላትስ ነው?
ዋናው በኣሁኑ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጉዳይ ፓርቲዎች እኔ እሻላለሁ ለማለት ዋናው መመዘኛቸው የተሰባሰቡት በተለይም ኣመራር ላይ ያሉት ግለሰቦች የፖለቲካ ቁጠኝነት ኣላቸው ወይ? ቁርጠኝነት በሞላቸው ሰዎች ቁጥር የትኛው ፓርቲ ያይላል? የሚል ልብ ያለው ድጋፍ ነው በተግባር የሚታየው ወይም መታየት ያለብት።
በቲየሪ ደረጃ በኣሁኑዋ ኢትዮጵያ በፍርድ ቤት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ ኣይገባም። ይሁን እንጂ በተግባር ይገባል። ይገባል ብቻም ሳይሆን ፍርድ ቤት የፖለቲካ መሳሪያ ነው። ኣሁን እዚህ ጋር የጎዳን የስርዓቱ ወይም የኣሰራሩ ጉዳይ ሳይሆን መከራ ውስጥ የከተተን ጉዳይ የግለሰቦች ስብእና ጉዳይ ሆኖ ነው የምናየው። ለምን እነዚህ ግለሰቦች ስርዓቱን ይጥሳሉ፣ ህጉ ለምን ኣቅም ያጣል? ካልን የፖለቲከኞቹ ላእላይ ስብስብ በተለያየ የግል ጥቅማጥቅም የተተበተበ በመሆኑ ነው። ድህነታችንም ኣንዱ ኣስተዋጾ ያደረገ ይመስላል። የተሻለ ስራ ለማግኝነት፣ ከድህነት ለመላቀቅ፣ ፖለቲካን መሳሪያ ማድረጉ የተለመደ መሆኑና ወደዚያ ጠጋ ያሉ ሃላፊዎች በዚህ ሞቲቭ የተሞሉ  ስለበዙበት ስርዓቱ በቁሙ እንዲሞት ኣድርጎታል።
ባለፈው ጊዜ ኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ማቋቋም ያስፈልጋታል የሚል ኣንድ ኣርቲክል ጽፌ ነበር። በርግጥም በኣሁኑ የነጻነት ትግል ኣሰላለፍ በኩል ጎድሎ የታየው ይሄ ነውና ይህንን ማቋቋም ተገቢ ነው። ይህ ኮሚሽን ፓርቲዎችን እያበራታታ ይህን ተፈላጊ ስብእና በመገንባቱ ረገድ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ያደርጋል። ፓርቲዎችን በማቀራረብ ረገድ፣ የመፍትሄ ኣሳቦችን በማጠናቀር ረገድ፣ ለኣዲሲቱዋ ኢትዮጵያ የሚሆነውን ኣዲስ ሰውነት በመጠቆሙ ረገድ ከባድ ሚና ሊጫወት ይችላል። ከዚያ በተረፈ ደግሞ እኛ ተራ ዜጎች መሪዎቻችንን የማጎልበትና ወደ ህብረት የመግፋት እንዲሁም ስብእናቸውን የመገንባት ሃላፊነት ኣለብን።
የብዙ ኣፍሪካ ሃገሮች ችግር ይሄ ይመስለኛል። ታግለን በብዙ መስዋእትነት ኣንድ ኣምባገነን  ከጣልን በኋላ መልሰን በሌላ ኣምባ ገነን እንተካለን። ሌላው ኣለም እየተሻሻለ ሲሄድ ይሄኛው ክፍለ ኣለም ወደ ኋላ የቀረበት ትልቁ ምክንያት የነጻነት ታጋዮች ራሳቸው በሚገባ ለኣመራር የሚበቃ ስብእና ሳያዳብሩ ወደ ስልጣን ስለሚመጡ ነው።ደቡብ ሱዳን ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናት። ለብዙ ኣመታት የነጻነት ትግል ታግለው፣ ብዙ ደም በመፍሰሱ ዓለም ሁሉ  እነዚህ ሰዎች ቢገነጠሉ ይሻላል ብሎ ፈርዶላቸው ተገነጠሉ። የዳርፉሩን እልቂት የማያውቅ፣ ያልሰማ ያለም ክፍል የለም። ያ ሁሉ ሆኖ ኣዲስ ኣገር ከመሰረቱ በኋላ ገና ኣንድ ጊዜ እንኳን ምርጫ ሳያካሂዱ፣ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሳይመሰርቱ፣ ከሁለት ዓመት ያልዘለለ እድሜ ያላትን ኣገር በጎሳ ከፋፍለው ማመስ ጀመሩ።
ያለ መታደል ሆኖብን በኣንዳንድ ኣፍሪካ ሃገራት የሚነሱ መሪዎች ስልጣን ላይ ከመጡ በሁዋላ ሁለት ነገር በጣም ይወዳሉ። ኣንደኛው ዝና ሲሆን ሁለተኛው ገንዘብ ነው። ሁለቱም እጆቻቸው ይዘዋል። ባንዱ ስልጣን በሌላው ገንዘብ። ዝናውን ወደው ገንዘቡን ችላ የሚሉ ቢሆኑ ትንሽ ይሻል ነበር። ነገር ግን ሁለቱንም በሃይል ስለሚወዱና ለዚህ የተሰጠ ስብእናቸው በውስጣቸው ስላልሞተ ክብ በሆነ ችግር ውስጥ እንድንወድቅ ኣድርጎናል።ኢትዮጵያዊያን በዚህ ላይ ልንነቃ ይገባናል። በተለይ የፖለቲካ ሰው መሆን የፈለጉ ወገኖቻችን፣ መሪ መሆን የሚሹ ወገኖቻችን በየጊዜው የባህርይ ለውጥ እያሳዩ በኣመለካከትና በሃላፊነት ስሜት እያደጉልን እንዲሄዱ እንሻለን። ከፍ ሲል እንዳልኩት እኛ ተራ ዜጎች ከውጭ ሆነን መፍረድ ብቻ ሳይሆን መሪዎቻችንን መንከባከብና ፍቅርን ክብርን ማሳየት ለፖለቲካ ቁርጠኝነታቸው ሃይል ይሰጣል።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
geletawzeleke@gmail.com

A legacy reborn in Adwa: Ethnic Ethiopians of Ethiopia


by Teshome Borago
Former Ethiopian Minister of War Habte-Giyorgis Dinagde
Former Ethiopian Minister of War Habte-Giyorgis Dinagde
As we celebrate the anniversary of our proud military victory over the powerful Europeans in the 1890s, we should be reminded of the ongoing plight of mixed ethnic Ethiopians, one of the people reborn out of the womb of Adwa.
When we examine the existing condition of identity politics in Ethiopia, Post-1991 politics and the governing status quo in Ethiopia continue to impact our people’s narrow interpretations of identity. “I am Gurage”, “He is Oromo”, “she is Amhara” … such are the expressions we hear everyday in the streets. Most Ethiopian citizens are still forced and urged to self identify to one ethnic group; whether or not they actually descend from one, two or more ethnolinguistic ancestry. We even see this injustice during the national census and when obtaining identification cards in Ethiopia. This marginalization of millions of mixed “Ethnic Ethiopians” or the systematic restriction on our self identification continues to benefit the TPLF ruling party and its OPDO, OLF, AAPO, OFC, ODF, TPDM, SLF, ONLF, ANDM and other ideological partners. These one-ethnic organizations are still the most active in Ethiopia today and they define our current politics based on one-ethnic ideology.
So how deeply is their narrow one-ethnic ideology engrained in our minds? Sadly, it has influenced all aspects of our thought process. For example, when we look at multiculturalism and multinationalism in Ethiopia, we naively mention the list of ethnic groups individually but we rarely mention mixed Ethiopians who are the direct product of our multicultural society. Even when we look at the events of the Battle of Adwa, our politicians proudly declare how all heroic Ethiopians from Oromo, Amhara, Welayta to Gurage, Tigray etc came together united against the invading Italian army. But this statement in itself inherently ignores the fact that Ethiopians from multiple ancestry also fought and died for our country. The truth is Mixed Ethiopians born from Gurage fathers and Oromo mothers fought in Adwa. Mixed Ethiopians with Welayta fathers and Amhara mothers died in Adwa. And so many other mixed Ethiopians sacrificed their lives. Symbolic of that era, even the powerful Minister of Defense under Emperor Menelik II was Fitawrari Habte Giyorgis Dinagde, who was said to be mixed Ethiopian of both Gurage & Oromo ancestry. Unfortunately today, mixed ethnic Ethiopians are unrecognized in current Ethiopian politics and ignored by the government’s “ethnic federalism” because they are either passive themselves or they tend to choose only one of their lineage over the other.
But, it is time that mixed Ethiopians become proud of their ancestry and be heard. Interethnic mixings have occurred throughout our history in trade centers and thru migrations, including the mass Migration of semetic and Afan Oromo speakers over the last millennium. Then, the victory in Adwa exponentially increased the pace of inter-ethnic marriages in Ethiopia; especially in Shewa, Wollo regions and central Ethiopia. It is true that ethnic identities are, by nature, fluid throughout history. They might die, be reborn, expand and die again. For instance, the ethnic labels we see today (“Amhara”, “oromo”, “Gurage” etc) did not exist many decades ago and they might die or disappear as globalization penetrates more inside Ethiopia. Similarly, post-Adwa era saw the rebirth of mixed Ethiopians’ influence in politics of our country. But the extreme poverty and the pro-Amharic undemocratic policies of the Imperial regimes sparked rural grievances and it fed the grassroots support base for the rebirth of these one-ethnic organizations that exist today.
However, more than the Tigrayan, more than the Amhara and the Oromo, mixed Ethiopians have to rise up today and carry the country toward democracy because we identify and sympathize with all groups in Ethiopia. But to do this, First, we have to embrace our own complex identity. We have to declare our ethnicity as “Ethiopian.” Unlike some Amharas and other urban nationalists who claim to be defenders of the “Ethiopian” label, we mixed Ethiopians are born Ethiopian and we die Ethiopian: we have no other option. Unless we reject our true identity (unless we pick our father over or our mother or vice versa) we do not have the luxury of being from one-ethnic group because we can only be the broader Ethiopian. When we are asked “what is your ethnicity,” it is high time for those of us with multiple ethnic ancestry to be proud and loudly say, “i am ethnic Ethiopian. Period!”
Ethnic Ethiopians have been passive for too long and it is time that we unite and take action for the benefit of all people in the horn of Africa. Mixed Ethiopians living in Illubabor (where my maternal grandfather is from) share the same heritage, the same psychological attachment and the same destiny as mixed Ethiopians living in Arusi (where my paternal grandmother is from) or northern Gondar (where my maternal grandmother) and Welayta Sodo (my paternal grandfather are from). All mixed multiethnic Ethiopians have a common national experience and a shared ideology, one that does not favor one group over the other. Since mixed Ethnic Ethiopians should not attach their identity and political development with the Amhara, the Oromo or other groups; we must work to bridge these gaps. We should create our own unique political identity, preferably one that will promote more interethnic marriages and the empowerment of our mixed Ethiopian race. We should bring together the Oromo, the Tigrayan and the Amhara as well as promote peace between other smaller ethnic groups in Ethiopia. The triumphant Adwa legacy of multiethnic cooperation will be best illustrated in the 21st century reawakening of our rightful role in Ethiopian politics.

The Race to Save Ethiopians Damned by the Dam


by Alemayehu G. Mariam
People of Omo River Basin sold down the river
Exactly two years ago to the month, I wrote a commentary entitled, “The Dam and the Damned: Gilgel Gibe III Ethiopia” focusing on the impact of   “development” in the Omo River Basin (ORB) in southern Ethiopia. In that commentary, I echoed the deep concerns voiced by various international human rights and environmental organizations over the ecological impact and cost of that dam on the lives of indigenous populations.International rivers people, water and life
I also made it a special point to express gratitude and appreciation to “the great international human rights organization that have created so much international awareness on the precarious environmental situation in the Omo River Basin.” I am even more profoundly grateful to International Rivers, Human Rights Watch, the Oakland Institute, Survival International and the Africa Resources Working Group two years later for the extraordinary work they continue to do to save the environment and the indigenous people in the ORB. For years, these organizations have been in the forefront of the race to save Ethiopians damned by the Gilgel Gibe III hydroelectric dam. Ethiopia: Stop Using Anti-Terror Law to Stifle Peaceful Dissent
The various international organizations have done invaluable work by raising public awareness and undertaking advocacy campaigns to bring international attention to the ecological disaster taking place in the ORB. Over the years, they have all issued meticulously prepared field reports, research and policy analyses and other scientific and statistical reports documenting the effect of the “development programs” of the regime in power in Ethiopia on the lives and livelihoods of the people of the ORB. They have all sought to advocate and mobilize international public opinion to bring sanity to the madness of Gibe III dam, the flagitious leasing of tribal lands in the Basin for sugar and rice plantations for the export sector and to stop the forced resettlement (“villagization”) of indigenous communities.
In my 2012 commentary, I also publicly lamented the fact that Ethiopians, particularly those of us in the Diaspora, have been standing on the sidelines with arms folded as the various international human rights and environmental organizations groups were running a steep uphill race to save Ethiopians in the ORB. We haveThe Oakland Institute is a progressive think tank founded in 2004 been silently watching them doing all of the heavy lifting for us.  At the time, I pleaded with all Ethiopians to “join and help international human and environmental rights organizations help us, and engage in vigorous environmental activism of our own.” I appealed for the “creation of our own environmental civil society organizations, particularly in the Diaspora, to ensure that Ethiopia’s rich and diverse ecosystem is preserved and protected today and for future generations.” I also warned, “If we fail to do that, we will all find ourselves in the same position as the people of the Omo River Basin who are damned by the dam.”
It is painful for me (frankly, I am ashamed) to admit that two years after I wrote that commentary, we are still on the sidelines watching while the international human rights and environmental organizations are still doing all of the heavy lifting for us and keeping up the race to save our people. I find myself asking the same questions over and over, without answers: Is it fair to have the international human rights and environmental organizations do all of the heavy lifting for us in the ORB? When these organizations show so much care and concern for our people and our country, why are we so manifestly unconcerned? Why is that we do not join and support the organizations speaking up for our people? Why is it that we do not come to the aid of these organizations and defend themSurvival the movement for tribal peoples against the slings and arrows of a vicious regime which slanders them and scandalizes their good works?  Would we be as passive and silent if the same environmental crimes and crimes against humanity were being committed in the name of “development” in other parts of Ethiopia? Are we manifestly unconcerned about the people of the ORB because they are marginalized ethnic minorities? Could it be that we are ashamed of the people of the ORB because they do not look “modern” like the rest of us, or are a “backward civilization” as the late Meles Zenawi once called them? How can we justify to future generations that they owe their legacy of environmental conservation and protection of the indigenous peoples of the ORB to the tireless efforts of international organizations? I ask my readers to think about these questions.Africa Resources Working Group

I think it is only fair that we should at least financially help those organizations who are helping us. There is no reason why we cannot demonstrate our support to them as they fight for the rights of our people in the ORB. We should be standing with them and not standing on the sidelines watching them.
The clear and present danger posed by the Gilgel Gibe III dam to the people of the ORB
The Gibe III dam poses a clear and present danger to the lives of hundreds of thousands of Ethiopians in the ORB including the Bodi, Karo, Muguji, Mursi, Nyangatom and Dasanech , among others, who have survived for millennia practicing what is called “flood retreat agriculture”. At the end of the rainy season, the flooded land near the river banks provides rich silt for raising a variety of crops including sorghum, maize and beans. The very existence of these Ethiopians depends on the cyclical flooding season. The Gibe III dam will fundamentally disrupt the natural downstream flow by damming the river upstream for electricity production for export. Experts have convincingly argued that the water volume on the Omo River will be permanently reduced as a result of diversion of water for the dam reservoir and irrigation of sugar plantations. This will make flood retreat agriculture virtually impossible for the people living in the Basin. In August 2012, the world renowned conservationist and paleoanthropologist Dr. Richard Leakey challenged the self-serving Gibe III “scientific” studies minimizing the ecological effects of the dam and predicted, “the dam will produce a broad range of negative effects, some of which would be catastrophic to both the environment and the indigenous communities living downstream.”
“Developing” the Omo River Basin
In late January 2011, Meles Zenawi gave a speech in Jinka, South Omo. It was vintage Meles– bombastic, bitter and full of bluster. He promised the sun and moon to the people trapped in the “backward civilization” of the ORB. He pledged to take them out of the stone age and into the modern age by making the region “an example of rapid development.” He assured them that the “dam on the Omo River [will] eliminate flood, create a huge irrigation system and give pastoralists a sustainable income and a modern life.”
With a vengeance, Meles demonized and lashed out at the environmental and human rights organizations urging care and caution in the construction of the Gibe III dam and protection of the way of life of the indigenous people. He characterized them as naysayers and doomsayers “who want to block our freedom to use our rivers, and to save our people from poverty.” He called them malicious obstructionists. “They are creating huge propaganda… They are blocking us from getting financial loans from abroad to finish the project.” He ridiculed them as “best friends of backwardness and poverty… who don’t actually do anything tangible.” He virtually called them self-absorbed racists because “all they want is keep the pastoralists as a tourist attraction” and keep the people of the ORB “a case study of ancient living for scientists and researchers.”
Meles and his henchmen have gone to extraordinary lengths to conceal the environmental devastation that has occurred and continues to occur in the construction of the Gibe III dam and the “development” of the Basin. In July 2008, two years after construction began on the dam and international human rights and environmental organizations began sounding the alarm, Meles directed his “Environmental Protection Authority” to issue the Gibe III Environmental Social Impact Assessment. That report was a shameless whitewash which rubber-stamped Meles’ pigheaded decision to forge ahead with the project. It was full of boldfaced lies. It unabashedly concluded that the reservoir area for Gibe III is unfit for human habitation because it is infested by deadly mosquitoes and tsetse flies (which cause “sleeping sickness”). It claimed, “There is no settlement in the future reservoir area and settlements are concentrated on the highland in areas outside the valley…  There is very little farming activity around the Omo valley bottom lands. … The population living within the proposed dam and the reservoir areas are not in close proximity to the UNESCO designated heritage site. No visible archaeological remains, which have scientific, cultural, public, economic, ethnic and historic significances, have been observed in the area and dam sites.”
Meles’ way of “modernizing” the “backward” people of the ORB was to turn over the Basin to Saudi Arabian and other foreign investors and his buddies.  Meles announced in his speech that his “government is planning, and working hard to establish, a 150,000 hectare sugarcane development in this area starting this year.” Sure enough, according to IC Magazine, “A Saudi Arabian tycoon Al-Moudi, with close links to the top-level Ethiopian leadership [was] allotted 10,000 hectares for a rice plantation. His massive project has done considerable damage to the local environment, which includes a national park and wildlife habitat, and local communities that have lived in their homelands for many generations.”
Meles announced that five sugar factories will be built in the ORB by the Omo Kuraz Sugar Development project. According to “Ethiopian Radio and Television Agency”, “Mesfin Industrial Engineering (MIE) signed ETB 3 billion ($162.2 million) worth contracts with state-owned enterprises to deliver machineries for the Tana Beles Integrated Sugar Development Project and the Kuraz Sugar development projects in the Amhara region and the Omo Valley…” MIE is “also producing railroad tracks for the Dire Dawa-Addis Ababa railway project and finalizing preparations to deliver the same for the Djibouti through Afar to Northern Ethiopia railway line.”
In June 2011, UNESCO concluded that “GIBE III dam is likely to significantly alter Lake Turkana’s fragile hydrological regime, and threaten its aquatic species and associated biological systems” and “urged the State Party of Ethiopia to immediately halt all construction on the GIBE III dam [and not] damage directly or indirectly the cultural and natural heritage located on the territory of another State Party.”
In Meles “development” plans, the impoverished and defenseless people of the ORB get the shaft while his filthy rich friends became super-filthy rich. According to one environmental study published in January 2014, “Construction of the Kuraz Sugar plantations (projected to cover 161,285 hectares) and accompanying infrastructure, including sugar processing factories and resettlement villages, has started in advance of completion of the Gibe III. The Kuraz Sugar plantations, plus additional area identified as suitable for cultivation (47,370 hectares), could eventually require over 50% of the Omo River inflow, depending on irrigation efficiency.”
Meles Zenawi’s “modernization” of the ORB was a windfall for his buddies, but it literally left the people of the Omo River Basin high and dry. Meles’ vision for the ORB and its people was, “what’s good for the ‘Saudi Arabian tycoon Al-Moudi’ and ‘Mesfin Industrial Engineering’ is good enough for the people of the Omo River Basin.” That is how Ethiopians in the Omo River Basin got sold down the river!
The continuing race to save the Omo River and indigenous people
Last week, International Rivers released a video on the environmental risks to the Omo River valley and severe and irreversible damage that could result to the people and ecosystem of the valley if the dam and thoughtless “development” projects concocted by the regime in power in Ethiopia continue unrestrained. It is a video worth watching as it clearly explains the clear and present danger facing the ORB.
There is little scientific doubt that Gibe III dam and the irrigation diverting water on the Omo River poses a clear and present danger to the livelihoods of hundreds of thousands of indigenous people in Southern Ethiopia and Northern Kenya. Studies have shown that by ending the river’s natural flood cycle, harvests, grazing lands, river banks and fisheries extending to Lake Turkana, the world’s largest desert lake, would be destroyed. The dam will devastate the unique culture and ecosystems of the Lower Omo Valley and Lake Turkana, both recognized as UNESCO World Heritage Sites. Experts fear that “Gibe III could destroy the fragile ecosystem for an additional 300,000 people downstream in Lake Turkana, a UNESCO World Heritage Site  which gets up to 90% of its water from the Omo River.”
It is particularly important for Ethiopians to understand the scope of the environmental damage and the human cost of the dam in the ORB. I specially urge my Ethiopian readers to view the Amharic version of the International Rivers video by clicking  HERE or on the picture below.
USAID and Donors Assistance Group in Ethiopia (a/k/a those who “see no evil, hear no evil and speak no evil” in the race to save the people of the Omo River Basin)
The official position of the United States Agency for International Development (USAID) and the Development Assistance Group’s (DAG) (a consortium of 26 donors) in Ethiopia has been to stonewall any questions of human rights abuses in the ORB. Stated bluntly, their official response could best be characterized as: “We see no evil, hear no evil and say no evil about human rights violations in the Omo River Basin.”
In October 2010, a few days after Human Right Watch released its report on the abuses of aid in Ethiopia, USAID and DAG issued a statement denying the “widespread, systematic abuse of development aid in Ethiopia. Our study did not generate any evidence of systematic or widespread distortion.” In 2012, USAID reported that it “did not find evidence to support claims [of human right violations] during its visit to South Omo.” In a letter dated January 17, 2014, Dennis Weller USAID, current Mission Director in Ethiopia stated that his agency and “other donors have been monitoring the situation in South Omo” and that “the main finding from these trips is that there are no reports of widespread or systematic human rights abuses. Our observations do not support assertions… that the resettlement processes are accompanied by systematic and widespread human rights abuses.”
Interestingly, Weller’s comments brushing off human rights abuses in the ORB are in stark contrast to his predecessor Thomas Staal’s. In an interview Stall gave before his reassignment to Bagdad in October 2010, he made the stunning admission that “with respect to political participation, we have not done a good job. Specifically, with respect to the election that took place two years ago, we have not done much to promote democracy… This is a hard situation that causes us to despair.” No reason for Weller to “despair” over human rights abuses in the ORB!
The official position of  USAID and DAG with respect to human rights abuses in the ORB could be reduced to two basic propositions: 1) The reports by international human rights and environmental organizations concerning forced evictions, villagization, resettlement, denial of access to subsistence land, beatings, killings, rapes, imprisonment, intimidation, political coercion, and the denial of government assistance are all fabrications and lies. 2) Even if the reports are accurate, they document anecdotal and isolated incidents which do amount to “systematic and widespread human rights abuses”.
USAID’s denial of “systematic and widespread human rights abuses” in Ethiopia should not surprise anyone. For years, USAID has taken shelter behind the empty phrase “systematic and widespread human rights abuses”. When Meles Zenawi declared in 2010 that his party had won the parliamentary elections by 99.6 percent, USAID found no “systematic and widespread human rights abuses”. When the Meles regime was committing crimes against humanity in Gambella and Ogaden regions, USAID transformed itself into USA In Denial. When hundreds of top opposition political figures, activists, civil society leaders, journalists, dissidents, bloggers, human rights advocates were jailed, USAID’s response was, “No systematic and widespread human rights abuses”. Nope! Nyet! Nien!  Pray tell, what exactly is “massive and systematic human rights violations”? Does USAID mean, “A single death is a tragedy; a million deaths is a statistic”? Perhaps for USAID a single human rights violation in the ORB is a tragedy but the wholesale violation of the human rights of the people in the Omo River Basin is a statistic?!
The fact of the matter is that USAID and others who visited the Omo region in January 2012 were provided compelling “audio recordings of the interviews conducted in several Lower Omo communities.” These recording “leave no room for doubt that the donor agencies were given highly credible first-hand accounts of serious human rights violations during the field investigation [undertaken by USAID and the Development Assessment Group] and that they have chosen to steadfastly ignore these accounts.”
U.S. Congress joins the race to save the people of the Omo River Basin
In July 2013, Senator Patrick Leahy (D-Vermont) included language in Senate Bill 1372 imposing certain certification requirements in the administration of U.S. aid in Ethiopia. The Leahy language was adopted in the “Consolidated Appropriations Act, 2014” which passed both houses on January 3, 2014. Section 7042(d) of the Act requires the U.S. Secretary of State to “certify to the Committees on Appropriations that the Government of Ethiopia is implementing policies to — (i) protect judicial independence; freedom of expression, association, assembly, and religion; the right of political opposition parties, civil society organizations, and journalists to operate without harassment or interference; and due process of law; and (ii) permit access to human rights and humanitarian organizations to the Somali region of Ethiopia.” It further requires that U.S. ‘‘Development Assistance’ and ‘Economic Support Fund’ that are available for assistance in the lower Omo and Gambella regions of Ethiopia shall— (A) not be used to support activities that directly or indirectly involve forced evictions; (B) support initiatives of local communities to improve their livelihoods; and (C) be subject to prior consultation with affected populations.” The law requires the “Secretary of the Treasury to instruct the United States executive director of each international financial institution to oppose financing for any activities that directly or indirectly involve forced evictions in Ethiopia.” It seems the international human rights and environmental organizations that have been campaigning to protect the ORB and Gambella ecosystems and indigenous peoples have been right all along!!
Where are Ethiopians in the race to save the ORB and the indigenous people?
The titular prime minister of Ethiopia, Hailemariam Desalegn, is said to be knowledgeable about water development and sanitation. He reportedly held a “graduate assistantship” at Arba Minch Water Technology Institute. He is also said to come from “an Omotic community which forms the principal population group in Ethiopia’s Southern Nations, Nationalities, and People’s Region.” It is reasonable to suppose that Hailemariam would take both personal and professional interest in the environmental destruction and human cost of “development” in the ORB. Unfortunately, Hailemariam has repeatedly declared the he “will strive to carry on Meles’ vision to transform the country”, and by the same token oversee the destruction of the ORB ecosystem and the lives and livelihoods of hundreds of thousands of people in the Basin.
I admit it is a complete exercise in futility, but I urge Hailemariam and his regime to learn from the tragedy of Lake Oroumieh in Iran. That lake has shrunk by 80 percent in 10 years as a result of damning rivers and irrigation projects. The response of the Iran’s new president, Hassan Rouhani, to the environmental disaster was “to form a team and to invite scholars to help find solutions.”
I have no reason to believe that Hailemariam and his crew care much about Lake Turkana in which the Omo River empties or the environmental damage in the ORB. I know that a regime afflicted by the arrogance of ignorance will not invite scholars and experts in the field to seek long-term solutions. I expect the regime leaders will repeat like a broken record their Pollyannish rhetoric about the ORB and demonizing condemnation of all who urge caution and care. Regardless, I find it a historical imperative to register the fact that Hailemariam and Co., have a legal duty to mitigate the environmental disaster and human catastrophe in the ORB. After all, they must understand that “Truth will not remain forever on the scaffold, nor wrong forever remain on the throne.”
What about Diaspora Ethiopians? Will they join the race to save their fellow Ethiopians damned by the Gibe III dam? Will they stand up and speak up for the voiceless, defenseless, powerless and helpless people of the ORB? Will they stand up and be counted with the people of the ORB or abandon them because they are a “backward civilization” as Meles Zenawi called them? Will they join International River, Human Rights Watch, Survival International and the Africa Resources Working Group in the heavy lifting and uphill fighting to save the Omo River Basin and its indigenous people? I do not know the answer to these questions, but I will be doing what I always do: Carry water (though not from the Omo River) for those doing the heavy lifting and uphill fighting! 
“Indigenous peoples have the right to the full enjoyment, as a collective or as individuals, of all human rights and fundamental freedoms as recognized in the Charter of the United Nations, the Universal Declaration of Human Rights/3 and international human rights law.” United Nations Declaration on the Rights of Indigenous Peoples 61/295.
Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino and is a practicing defense lawyer.
Previous commentaries by the author are available at:
Amharic translations of recent commentaries by the author may be found at: