Tuesday, July 15, 2014

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አደረጉ



ቅዳሜ ጁለይ 12/2014 በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አዘጋጅነት ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን በሚል አላማ በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የደንነት ሀይሎች መታፈንና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ታላልፈው መሰጠታቸውን በተመለከተ ወደ ፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ በኖርዌ ኦስሎ ለአምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል::
ሕዝባዊ ውይይቱ ከቀኑ 15: 00 ሰአት ላይ የተጀመረ ሲሆን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያኖች የአቶ እንዳርጋቸው ምስል ያለበትና ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን የሚል ጹሁፍ የተጻፉበትን ቲሸርት በመልበስ ለስብሰባው ድምቀት የሰጡት ሲሆን ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውንም የትግል አጋርነት አስማስክራዋል እነዚህን ቲሸርቶች የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ በራሳቸው አነሳሽነት የሰሩ ሲሆን የድጋፍ ድርጅታችን ወጪውን በመሸፈን ለተሰብሳቢው በነጻ ኣድሏል።
ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አቢ አማራ በሃያ ሶስት አመታት በወያኔ ጨካኝ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉትና በግፍ ለሚሰቃይዩ ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ አስጀምረውታል በመቀጠልም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር በስብሰባው ላይ የተገኛውን ሕዝብ እንኮን ደህና መጣችሁ በማለትና በማመስገን ፐሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ሲሆን አቶ ዮሀንስ በንግግራቸው የወያኔ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባደረሰው አፈና ግንቦት 7 የክተት አዋጅ ማስተላለፉን ጠቅሰው አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል እየታገሉ ባሉ ታጋዮች ላይ ሳይቀር እስር እያደረሰባቸው እንዳለ በማመልከት ሰሞንኑን እንኮን የሰመያዊ፣ የአንድነት፣ የአራና የፖለቲካ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ለስር ተዳርገዋል ብለዋል::
ስለሆነም ህዝባችንን ለእስር እያደረገ ያለውን አገዛዝ ለመቃወም ሁሉም በአንድነት መሰባሰብ እንዳለበት አጠንክረው በመናገር በአሁን ሰአት የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታፈንና መታሰር መላውን ኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር እያንቀሳቀሰውና ሕዝቡም እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በማለት በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቅሰው በአሁን ሰአት ትግሉ የግንቦት 7 ብቻ አይደለም ይህን ትግል በዚሁ አንድ ሆነን መቀጠል እለብን ብለዋል::
በመቀጠል አቶ ደባስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባል የአቶ አንዳርጋቸውን ከወጣት እድሜያቸው ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ አካሄድ አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ማን ነው ? በሚል ርእስ የአቶ አንዳርጋቸውን የትግል ጉዞ የሚዳስስ ዘገባ ሰፋ ባለ ትንታኔ በጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኢሀፓ ፣ የአርበኞች ግንባር፣ የሸንጎ ፣የስደተኛው ማህበር ተወካዮች እና ሌሎችም ሰዎች በየተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የየድርጅቷቹም ተወካዮች የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መታፈንና ለእስር መዳረግን በተመለከተ የድርጅታቸውን አቋም ለተሰብሳቤው ያስረዱ ሲሆን የሁሉም ፖርቲ ተወካይች በአቶ አንዳርጋቸው መታፈንና ለእስር መደረግ ማዘናቸውን ገልጸው ሁሉም በአንድነት በመተባበር በማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ የወያኔንን መንግስት ማስወገድ እንዳለባቸው አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል::
በየፕሮግራሞቹ መሀል ግጥሞችና ሌሏችም ፕሮግራሞች ቀርበው የመጀመሪያው ዞር ተጠናቋል::ከ30 ደቂቃ የእረፍት የሻይ እና የቡና ፕሮግራም በኋላ የሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ፕሮግራም በተያዘለት ጊዜ ተጀምሮ የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች ያሰተፈ ፕሮግራም በአቶ አብዱ የሱፍ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ ምክትል ሊቀመንበር ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪን ካብራሩ በኋላ ለተሰብሳቢው ለውይይት በማቅረብ በኖርዌ የምንኖር ኢትዮጵያኖች ይህን የትግል ጥሪ ለማስፈጸም ምን እናድርግ በማለት ለውይይት አቅርበው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በአቶ ዮሀንስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር አወያይ አማካኝነት በስፋት ተወያይተውበታል ::
ተሰብሳቢውም በብዙ ነገሮች ከተወያዩ በኋላ ይሄ ግንቦት 7 ያወጣውን የመጀመሪያ እንከን የትግል ጥሪ ተግባራዊ በየቦታው አለም አቀፍ ታክስ ፎርሶች እየተቋቋሙ እንዳለና በኖርዌይም ይህንኑ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቷች ያካተተ ታክስ ፎርስ እንዲቋቋም ተወስኖል:: በመቀጠልም በተሰብሰቢዎች በተመረጡ ሰዎች የተጻፋ ባለ ስድስት አሃዝ የተሰብሳቢው የአቋም መግለጫ ለጉባሄው በጹሁፍ ቀረቦል:: ተሰብሳቢው ያወጣው የአቋም መግለጫ
1. ሁላችንም አንዳርጋቸው ወይም አንድ አርጊያቸው ነን ስንል ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሐገራችን ኢትዮጵያ ለማስፈን የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ማለታችን ነው።
2. የተለያዩ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት የሚያደርጉትን መጠላለፍ እንዲቀርና በጋራ ወይም አንድ በመሆን እንዲሰሩ ግፊት እናደርጋለን።
3. ለሚቀርብልን ሐገርን የማዳን ጥሪ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።
4. የየመን መንግስት ከአለም አቀፍ ህግ ጋራ የሚፃረር ስራ በመስራት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት የሰራውን ወንጀል ለዓለም አቀፍ ህግ የማቅረብ ስራ በጋራ እንደምንሰራ።
5. የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ መታፈን ትግሉን የበለጠ እንደሚያጠናክረውና ወደ ውጤት እንዲያመራ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናደርጋለን።
6. ወያኔ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር ኢትዮጵያውያንን እስርቤት ማስገባቱን እንዲቀርና የታሰሩትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እንጠይቃለን በማለት የአቋም መግለጫ አውጥተዋል ።

በመጨረሻም አቶ ዳንሄል አበበ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ምክትል ሰብሳቢ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የአቋም መግለጫ ለተሰብሳቢው በጹሁፍ ያሰሙ ሲሆን በንግግራቸውም አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የቋሙ የነጻነት ታጋይ ናቸው እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ የምንል ሁሉ ለሃያ ሶስት አመታት ህዝብን በዘረኝነት የከፋፈለውን ወያኔን በቃ ልንለው ይገባል ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ አፈና፣ ግድያው፣ እስራቱ መጨመሩን በመናገር ይኼን ጨቋኝና አፋኝ ስርአት ለማስወገድ እንነሳ በማለት ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን በመጨረሻ እኔ እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ እናንተስ በማለት የፕሮግራሙን ተሳታፊ በመጠየቅ ፕሮግራሙ በተያዘለት ሰዓት ከምሽቱ 20:00 ተጠናቋል ::

እኛ ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!


ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

ሰበር ዜና - የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ) ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግ አዘዘ



ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይትዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባሰራጨው ዜና  የእንግሊዝከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ  ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ)ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ  መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራእንዲደረግ ያሳለፈውን ውሳኔ  ''ጠቃሚ እርምጃ'' በማለት አሞካሽቶታል።
ውሳኔው በተለይ በቅርቡ ከአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ መታገት በኃላ የእንግሊዝ መንግስት  ''የባህር ማዶ የልማት ትብብርድርጅት'' (UK Department for International Development (DFID) ) ለኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ድጎማሊያደርግ የነበረ ከመሆኑ አንፃር የዛሬው ውሳኔ ከፍተኛ መልዕክት ማስተላለፉ አይቀርም።በሌላ በኩል የዛሬው የፍርድቤቱውሳኔ ይሄው የልማት ድርጅት (DFID) በበቂ ሁኔታ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ ይዞታ ጉዳይ አለመመርመሩን ጠቁሞ በእዚሁአዲሱ የፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግበት ማዘዙን ያብራራል።

የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእርምጃውን ፋይዳ ሲያስረዳ  የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ተጠሪ የተናገሩትንበመጥቀስ ነው።እንዲህ ይነበባል -

''
የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድቤት ውሳኔ ለሌሎች መንግሥታት እና እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የማንቅያጥሪ ነው።ምክንያቱም ሀገራትም ሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡትን የልማት ፕሮግራም ሁሉ ቅድምያ ከሰብዓዊይዞታ አንፃር እንዲመለከቱ ያደርጋል''ይላል።

የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይትስለ እንግሊዙ ከፍተኛ ፍርድቤት የዛሬ ውሳኔ አስመልክቶያወጣውን ዘገባ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

Ethiopia: UK Aid Should Respect Rights
Ruling Permits Review of Development Agency’s Compliance
JULY 14, 2014
(London) – A UK High Court ruling allowing judicial review of the UK aid agency’s compliance with its own human rights policies in Ethiopia is an important step toward greater accountability in development assistance.

In its decision of July 14, 2014, the High Court ruled that allegations that the UK Department for International Development (DFID) did not adequately assess evidence of human rights violations in Ethiopia deserve a full judicial review.

“The UK high court ruling is just a first step, but it should be a wake-up call for the government and other donors that they need rigorous monitoring to make sure their development programs are upholding their commitments to human rights,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “UK development aid to Ethiopia can help reduce poverty, but serious rights abuses should never be ignored.”

The case involves Mr. O (not his real name), a farmer from Gambella in western Ethiopia, who alleges that DFID violated its own human rights policy by failing to properly investigate and respond to human rights violations linked to an Ethiopian government resettlement program known as “villagization.” Mr. O is now a refugee in a neighboring country.

Human Rights Watch has documented serious human rights violations in connection with the first year of the villagization program in Gambella in 2011 and in other regions of Ethiopia in recent years.

A January 2012 Human Rights Watch report based on more than 100 interviews with Gambella residents, including site visits to 16 villages, concluded that villagization had been marked by forced displacement, arbitrary detentions, mistreatment, and inadequate consultation, and that villagers had not been compensated for their losses in the relocation process.

People resettled in new villages often found the land infertile and frequently had to clear the land and build their own huts under military supervision. Services they had been promised, such as schools, clinics, and water pumps, were not in place when they arrived. In many cases villagers had to abandon their crops, and pledges of food aid in the new villages never materialized.

The UK, along with the World Bank and other donors, fund a nationwide development program in Ethiopia called the Promotion of Basic Services program (PBS). The program started after the UK and other donors cut direct budget support to Ethiopia after the country’s controversial 2005 elections.

The PBS program is intended to improve access to education, health care, and other services by providing block grants to regional governments. Donors do not directly fund the villagization program, but through PBS, donors pay a portion of the salaries of government officials who are carrying out the villagization policy.

The UK development agency’s monitoring systems and its response to these serious allegations of abuse have been inadequate and complacent, Human Rights Watch said. While the agency and other donors to the Promotion of Basic Services program have visited Gambella and conducted assessments, villagers told Human Rights Watch that government officials sometimes visited communities in Gambella in advance of donor visits to warn them not to voice complaints over villagization, or threatened them after the visits. The result has been that local people were reluctant to speak out for fear of reprisals.

The UK development agency has apparently made little or no effort to interview villagers from Gambella who have fled the abuses and are now refugees in neighboring countries, where they can speak about their experiences in a more secure environment. The Ethiopian government’s increasing repression of independent media and human rights reporting, and denials of any serious human rights violations, have had a profoundly chilling effect on freedom of speech among rural villagers.

“The UK is providing more than £300 million a year in aid to Ethiopia while the country’s human rights record is steadily deteriorating,” Lefkow said. “If DFID is serious about supporting rights-respecting development, it needs to overhaul its monitoring processes and use its influence and the UK’s to press for an end to serious rights abuses in the villagization program – and elsewhere.”

ምንጭ - http://www.hrw.org/news/2014/07/14/ethiopia-uk-aid-should-respect-rights