March 26, 2013
የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡ የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በዘረኝነት ገመድ አስሮ እየረገጠ የሚገዛዉ ወያኔ ለዚህ የበቃዉ በዘረኝነትና በጥላቻ አነሳስቶ ያሰታጠቃቸዉ ገበሬዎች በከፈሉት መስዋዕትነት ነዉ ያለዉ ይሄዉ ህዝባዊ ኃይል ሠላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ከእነዚህ የቀን ጅቦች ለማላቀቅና አገራችንን የእኩሎች አገር ለማድረግ ማንኛዉንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት አለበት ብሏል። የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረዉ የፍትህ፤የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ግቡን እንዲመታ የመጀመሪያዉን እርምጃ የወሰደዉና ትግሉ የሚፈልገዉን የደም መስዋዕትነት ለመክፈል የትግሉ ግንባር የመጀመሪያዉ ደጃፍ ላይ የተሰለፈዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ካሁን በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔን ዘረኝነት፤ዝርፍያ፤ጥላቻና ንቀት ለማስቆም መፍትሄዉ ከአገር እየተሰደዱ በየባህሩና በየበረሀዉ መሞት ሳይሆን ለስደታችን፤ ለመዋረዳችንና ለመረገጣችን ቀንደኛ ምክንያት የሆነዉን የወያኔ ስርአት እዝያዉ አገር ቤት ዉስጥ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ብቻ ነዉ ብሏል።
የወያኔ እህአዴግ ዘመን አብቅቷል፤ከአሁን በኋላ ዘመኑ የኛ የኢትዮጵያዉያን ነዉ ያለዉ የግንቦት ሰባት ዝብባዊ ኃይሎች ቃል አቀባይ ይህንን የኛ የሆነዉን ዘመን እዉን የምናደርገዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ከዘረኝነት ነጻ የምናወጣዉ እንደአንድ ሰዉ ቆመን በጋራ ስንታገል ነዉ እንጂ የአገር ማዳኑንና የመስዋዕትነቱን አደራ ለተወሰኑ ወገኖች ብቻ በመተዉ አይደለም ብሏል። በመቀጠልም ወያኔን ፊት ለፊት ተፋልሞ ወንድሞቹንና እህቶቹን ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአባቶቹ በአደራ የተረከባትን ኢትዮጵያን ለልጆቹ ለማስተላለፍ የሚናፍቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከዛሬ በኋላ ዬት ሄጄ ወያኔን ልታገል የሚል ስጋት እንዳይሰማዉ አሳስቧል።ባለፈዉ ታህሳስ ወር እራሱን ለህዝብ ይፋ ይደረገዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ አያሌ ኢትዮጵያዉያን በየቀኑ እየተቀላቀሉት ሲሆን ይህንን የህዝብ ተገንና አለኝታ የሆነ ኃይል በመቀላቀል የአዲስቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ለመሆን የምትፈልጉ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገራት የምትገኙ ኢትዮጵያዉያን ህዝባዊ ኃይሉ በተከታታይ ለሚያወጣቸዉ መግለጫዎችና ህዝባዊ ጥሪዎች ምላሽ በመስጠት እንዲትተባበሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ጥሪዉን ያስተላልፋል።
No comments:
Post a Comment