Sunday, November 17, 2013

መድረክ ሳኡዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት፤ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርግ ተከለከለ

ኢ.ኤም.ኤፍ – የመድረክ ፓርቲ ዛሬ እሁድ ህዳር 8፣ 2006 ዓ.ም.፤ በሳኡዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረውን ግፍ እና በደል በመቃወም ከሳኡዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሊያደርግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ አስተዳደር መከልከሉ ታወቀ። የአዲስ አበባ መስተዳደር ለመድረክ በላከው ደብዳቤ ላይ፤ በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ጉባዔዎች እየተካሄዱ በመሆኑ በቂ የፖሊስ ጥበቃ ማድረግ እንደማይችል እና በዚህም ምክንያት ሰላማዊ ሰልፉ እንዲደረግ ያለመፈቀዱን ገልጿል።
medrek
በተመሳሳይ መልኩ ባለፈው አርብ እለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የወጡት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታስረው፤ ቁጣውን ለመግለጽ የወጣው ህዝብ ደግሞ በፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ የተደረገበት መሆኑ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment