March 12, 2013
ገና ከጅምሩ ኢትዮጵያዊያንን ለማደናገርና የሃሳብ አቅጣጫቸውንም ለማስቀየር ታልሞ ለአንድ ሰሞን ህዝብን ሲያደነቁር የነበረው የትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ የኋልዮሽ ጉዞ መጀመሩን የዘረኛው አገዛዝ ባለስልጣናት በአደባባይ እየተናገሩና በቁጥጥራቸው ስር ያሉትም የመገናኛ ብዙሃን በይፋ እየዘገቡ መሆኑ ተዘገበ።የዘረኛው የወያኔ አገዛዝ አቀንቃኝ የሆነው ሪፖርተር ጋዜታ፣ የወያኔው ካድሬዎች ለትራንስፎርሜሽን እቅዱ ወደ ኋላ መጓዝ ጉልህ አስተዋሶ ማድረጋቸውን፣ በተለይም የግብርናው ዘርፍ እድገት ያሳያል ተብሎ ከታቀደለት ውስጥ በ 50 በመቶ የኋልዮሽ መጓዙን ዘግቧል።
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለጠው የመንግሥት ካድሬዎችና የበታች ቢሮክራቶች በውጭ ኢንቨስተሮች መስተንግዶ ላይ የሚያደርሱት መጉላላት ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር ኢንቨስት ከማድረግ እንዲታቀቡ እስከማድረስ የሚዘልቅ አስከፊ ሁኔታ እያሳዩ ነው ካለ በኋላ ይህ ድርጊትም ተቀባይነት እንዳለው የወያኔ ባለስልጣናት ማመናቸውን ገልጧል፡፡
በማያያዝም የወያኔው ዘረኛ አገዛዝ የግሉን ዘርፍ ብድር እንዳያገኝ እያደረገ በአንፃሩ ግን እንደ ኤፈርት ላሉት የህዋሃት የንግድ ድርጂቶች ሰፊ ፋይናንስ እያመቻቸ መሆኑን በዚህም ምክንያት እነኝሁ የንግድ ድርጂቶች እስከ 75 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ እየወሰዱ ነው ብሏል፡፡
ሃገር የማጥፋት አጀንዳን አነግቦ ኢትዮጵያን ለሃያ አንድ አመታት ያክል እየገዛ ያለው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ ሃገሪቱን ከፍላ ከማትወጣው እዳ ውስጥ እየዘፈቀና በጣት የሚቆጠሩ ወምበዴ ባለስልጣናትን በሃብት እያምበሸበሸ እንደሚገኝ፣ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment