March 21, 2013
ባለፉት ሃያ አንድ አመታት ጊዮን ሆቴል ለወልዱና ለልጁ ለብስራት ወልዱ እጅግ በጣም ከፍተኛ ትርፍ ሲያስገኝ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህ በሆነባቸዉ አመታት ሁሉ የባህርዳር ከተማ ህዝብ አንድ ኪዎስክ በ5 ሺ ብር እየተከራየ እንዴት ጊዮን ሆቴልን የሚያክል ትልቅና ዘመናዊ ሆቴል በ5 ሺ ብር ብቻ ይከራያል እያለ ተቃዉሞዉን ቢያሰማም የሚሰማዉ ጠፍቶ ሃያ አመታት አልፈዋል። ሆኖም በቅርቡ መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ የፌደራል የኪራይ ቤቶች ድርጅት የአማራ ክልል መንግስት ሆቴሉን እንዲረከብ ለአማራ ክልል የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ደብዲቤ በመጻፉ ጉዲዩ ከክልል አልፎ ገዢዉ ፓርቲ ጽ/ቤት መድረስ ችሏል። ሆቴሉን ለከልል መንግስት እንዲያስረክቡ ደብዲቤ የደረሳቸዉ ወሌደና ሌጁ ብስራት ጉዳዩን በቀጥታ ለበረከት ስምኦን፤ ለፌዳሩሽን ምክር ቤት ሰብሳቢው ካሳ ተክለብርሀንና ለአዲሱ ለገሰ የመለስ ዜናዊን ሞት ተክትል ሆቴሉን እንዱያስረክቡ መጠየቃቸውን በመናገራቸው፣ ባለስልጣኖቹ የክልሉ መንግስት የጻፈውን ደብዳቤ እንዱያነሳ ጠይቀዋል።
የክልሉ የመንግሰት ቤቶች ኤጀንሲ ጉዲዩ ከፍተኛ ዝርፊያ መሆኑን ገልጾ ዉሳኔዉን ለመለወጥ ፈቃደኛ አለመሆኑን ቢገልጽም የሆቴለ አስተዳዳሪ የሆነዉ ብስራት ወልዱ የክልሉን ባለስልጣናት በማስፈራራት እርምጃ እንደሚወስድ በመዛት ሆቴሉን ለማስረከብ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገልጿል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የዝግጅት ክፍላችን በስልክ ያናገረዉ አንድ የኪራይ ቤቶች ድርጅት ሰራተኛ የሆቴሉ አስተዳዳሪ ብስራት ወልዱ ሆቴሉን እንዲያስረክብ ደብዳቤ ሲጻፍለት “ዋጋህን ታገኛለህ” የሚል መልስ መስጠቱን ተናግሯል። የባህርዳር ከተማ ህዝብ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በአንድ ተራ የህወሀት አባል መደፈረቸዉን አስመልክቶ እያሾፈ ሲሆን እንደ ብዙ ታዛቢዎች እምነት የክልሉ መንግስት ከዚህ አይነቱ ህዝባዊ ትችት ነጻ መሆን የሚችለው ግለሰቡ ሆቴሉን እንዱያስረክቡ ሲያደርግና እንደማንኛውም ሰው ተጫርቶና ለጨረታዉ ተገቢውን ክፍያ ማስከፈል ሲችል ብቻ መሆኑ ታውቋል።
No comments:
Post a Comment