Friday, November 14, 2014

ልማታዊው ጭፍጨፋ በአፋር ክልል በ ግንቦት 2003 ዓ.ም

ምን ጊዜውም በአፋር ህዝብ ዘንድ የማይረሳ ቀን ነው!!
የተፈጸመው በአፋር ክልል በዱብቲ ወረዳ ነው።

police afar
በ2003 ዓ.ም አንድ አሊ ኡመር የተባለ የ10ኛ ክፊል ተማሪ የሆነው ወጣት ሌሊት በሱኳር ፋብሪካ ዘበኛ ሁኖ ሰለሚስራ ጧት ደግሞ የጦር መሰራውን እቤት አስቀምጦ ወደ ትምህርት ቤቱ የሄዳል።
እንደተለመደው ተማሪ አሊ ኡመር ከአንድ ጓደኛው ጋር የጦር መሳሪያውን ይዞ ከተኛበት የስራ ቦታ ወደ ቤቱ በመሄድ ላይ ሳለ ሁለት የፈደራል ፖሊሶች በመንገድ ላይ ያገኙዋቸዋል። መሳሪያውን አስረክብ አሉት!
ልጁ ደግሞ ማንነቱን በሚገባ ካስረዳቸው በኃላ መሳሪያውን ህጋዊ መሆኑንና እሱ በሱኳር ፋብሪካ ዘበኛ እንደሆነ ነገራቸው።
አሁንም መሳሪያውን አስረክብ አሉት እሱም እኔም ህጋዊ ዘበኛ ነኝ መሳሪዬም ህጋዊ ነው እንጂ አላሰረከብም አላቸው።
ከዛ ከፖሊሶቹ አንደኛው ለምን ብዙ ትከራከረዋለህ በማለት ጭንቅላቱን መቶ ገደለው አብሮት የነበረው ልጅም ወሰዱት እየደበደቡት ከዋሉ በኃላ ማታ ለቀቁት።
ይሁን እንጅ ችግሩ ተባብሶ ቀጠለ። የማቹ ቤተሰቦች ፖሊሱን ለህግ እንድቀርብ ደጋግሞው ቢጠይቁም ሰሚ አላገኙም።
ሁለት የማቹ ቤተሰብ የሆኑት ወጣቶች ልጁን ገድሎ ለህግ ያልቀረበ ፖሊሱን ፈለገው ገደሉት እነዚህ ሁለት ወጣቶች በጊዜው በአፋር ክልላዊ ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ወንጃለቻው ተጣርቶ ለፊርድ ቤት መቅረብ የነበረባቸው ቢሆንም በአቶ እስማእል አሊ ሲሮ የስልክ ትዕዛዝ መሰረት በሚሌ ካንፖ ለሚገኘው ፈደራል ፖሊስ አሳልፈው ሰጡዋቸው ፈዳራል ፖሊስም እነዚህ ወጣቶች ልክ ሚሌ እንደወሰዷቸው ገደሉዋቸው።
ይህን ተከትሎ የማቹ ጎሳ መሪን ጨምሮ ቤተሰቦቹ ሁሉም ታሰሩ።
ያለ ፊርድ ለ3 አመታት በሚሌ በፈደራል ፖሊሶች ከተሰቃዩ በኃላ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ተለቀዋል ከነዚህ ውስጥ በመጀመሪያ በፖሊስ የተገደለው አሊ ኡመር ወንድም አለ።
እነርሱም
1 ናስሪ አሊ ሀማድ
2 ሓቴ ዑመር ( የማቹ ወንድም )
3 ዳውድ ዑማር
4 ካዲር አስከር
5 አሊ ሓማድ ስሆኑ ከ3 አመታት በላይ በደብደባ፣ሙቀት፣ በረሃብ አንዲሁም በውኃ ጥም እያሰቃዩዋቸው እንደነበሩ ለምንጮችን ተናገሯል።
አሁንም ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ እስር ላይ የሚገኙ እንዳሉ ተጠቀመዋል።
1 ዑመር የተባለ ለጊዜው የአባቱ ስም አልታወቀም
2 አሊ ሩዔ
3 መሐመድ ማያባሄ እነዚህ ግለሰቦች እስካሁን በግፍ ታስረው በመሰቃየት ላይ መሆናቸው ተገልፇል።
ባለፈው ሳምንት በሰመራ ከተማ የፅጥታ ጉዳይን በተመለከተ ስብሰባ እንደነበረና አብዴፓዎች ስለዚህ ጉዳይ ከምረጫ በፊት በፍታ ቤሄር እንድጨርሱ ከህወሀት ትዕዛዝ መተላለፉን የሰመራ ምንጮች ለአኩ ኢብን አፋር ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment