አዘጋጅ ናትናኤል አባተ
By Nathnael Abate (Norway)
በሰዉ ልጅ ታርክ ዉስጥ ነጻነት ከመንግስታት ወይንም ከገዥዎች ለተገዥዎ ች የሚቸር ስጦታ ሳይሆን ተጨቋኝ ተገዥዎች በደም ጠብታቸዉና
ጩሄታቸዉ ከብዙ ትግል በሁዋላ የሚቀዳጁት የመስዋእትነት ፍሬ ነዉ፣፣
ስለዝህ የነጻነት ታርክ ህዝባዊ እምቢተኝነትና የመስዋእትነት ታርክ
ነዉ፣፣የነጻነት ትግል በሚደረግበት ወቅት አንዳንድ ትግሉን የሚመሩና ለነጻነት የሚታገሉ የነጻነት ጀግናዎች ይሞታሉ፣ ይታሰራሉ፣ይሰቃያሉ፣፣
ከእነዝህ የነጻነት አርበኞች የሚፈሰዉ የደም ጠብታዎ ች ትልቁ የነጻነት ዛፍ ሆኖ ያድጋል፣፣ ለነጻነት ብለዉ በአምባገነኖች እጅ ስሰቃዩ የነበሩ የሞት ጥላ ሸለቆ አልፎ በመጨረሻ አምባገነኖችን አሸንፈዉ የነጻነት ተራራ አናት ይደርሳሉ፣፣ ይህ ሁሉ መስዋእትነት
የተከፈለበት ነጻነት፣ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ በደም የማይተላለፍ በመሆኑ ፣ካልተንከባከቡትና የነጻነትን ባህል ካልተከሉ፣ አንድ ትዉልድ
ሲያልፍ ወይንም ያንድ ገዥ ዘመን ሲያልቅ ሊከስም ይችላል፣፣ ስለዝህም
አንድነትና ነጻነትን በህይወት እንድቀጥል ለነጻነት የተጋደለዉ ትዉልድ
ለተተኪዉ ትዉልድ ስለነጻነት ማስተማር እንድሁም የነጻነት ባህልን ማስረከብ አለበት፣፣ ባሃገራችን ለነጻነትና ፍትህ በተለያዪ ዘመናት
የተለያዪ አይነት ትግሎ ች ተደርጉዋሉ፣፣ በንጉሱ ዘመን የጎጃም፣የባለ፣የወሎ፣የተማሪዎ
ች መሬት ላራሹ ጥያቄ ትግሎችና ሌሎች ዘዉዳዊ አገዛዝን ለመገርሰስ የተደረጉ ትግሎች ይጠቀሳሉ፣፣ ንጉሳዊዉ ስርአት ተገርስሶ ወታደራዊዉ ስርአት በተተካ ጊዜም ቢሆ ን የተለያዩ ግለሰቦች ድርድችና ቡድኖ
ች ለነጻነት ታግሉዋሉ፣ ተጋድለዋሉ ታስረዋሉ፣የተለያዩ አይነት ስቃዮች
ደርሶባቸዋል፣፣ ከላይ ያስቀመጥኳቸዉ ሁለቱም ትግሎ ች ባሃገራዊ
ማንነትና ብሄራዊ አንድነት ላይ ተመርኩዘው የሚደረጉ ስለሆኑ ወጠታቸዉ አመርቂ ነበር፣፣ወታደራዊዉ አገዛዝ ብሄራዊ አንድነትን የስርአቱ
መሰረት ቢያደርም በህዝቦች ላይ የሚያደርሰዉ ግፍና ጭቆና በስልጣን
እንዳይቆይ እንዳደረገዉ የአደባባይ ምስጥር ነዉ፣፣ ወታደራዊዉን ስርአት የተካዉና አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ ከጫካ የመጣ
የትግራይ ነጻ አዉጨ ቡድን ሲሆ ን ይህ የወበዴዎች ቡድን ሃገርቱን ለመዝረፍ በአክስዮን የተደራጀ እንድሁም ሃገር ለማፍረስና ህዝብ
ለማጥፋት የታጠቀ ነዉ፣፣ይህ የወንጀለኞች ቡድን በአስተዳደራዊ መዋቅሩ፣በሃገሪቱ
ማህበራዊ ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ጉዳዮችም ከዘዉዳዊዉ አገዛዝና ወታደራዊዉ ስርአት ይልቅ እጅግ የከፋ ነዉ፣፣ ባለፉት በሁለቱም ስርዓቶች
የነጻነት ጉድለት ብኖርም የብሄራዊ ማንነት ዉድቀትና የሃገር ሃብት ዝርፍያ አልተፈጸመብንም፣፣ ህወሃት መራሹ መንግስት ህዝብን ከመጨቆን፣ ከማዋረድ፣ከማሰር ፣ሃብት ንብረታቸዉን
ቀን በጠራራ ጸሃይ ከመዝረፍ አልፎ ይህንን እኩይ ተግባራቸዉን የሚቃወምና የሚያጋልጥ ሰዉ እያሳደዱ መግደል ማሰርና ማፈን ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፣፣ በወያኔ መንግስት እጅ የታሰሩ ፣የታፈኑና ሽብርተኛ የተባሉ ሁሉ
የስርዓቱን እኩይ ተግባር ያወገዙ፣ ሃገር ለምን ታፈርሳላችሁ ያሉዋቸዉ፣ያገር ሃብት መዘረፍን የተቃወሙ፣ፍትህ ነጻነት፣እኩልነት
ስጐድል አይቶ ዝም ያላሉና ለሆ ዳቸዉ አናድርም ብለዉ ለእዉነት የቆሙ ናቸዉ ፣፣ የወያነ መንግስት የሃገርቱን፣ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት፣የደህንነት ሃይሎችን ለራሳቸዉ
በሚያመች መልኩ የቀረጹዋቸዉ በመሆኑ የነጻነትን የሚጠይቁንና እነሱን
የሚቃወሙትን ለማፈንና ለአሳድዶ ለመያዝ ሁነታዎችን ቀላል
አድርጎላቸዋል ፣፣ ሆኖም የወያነ የነጻነት አፈና ሃይሎች ቁጭትና ቢሶት የወለደዉን ህዝባዊ ትግል ለማምከን አንዳችም አቅም የላቸዉም፣፣
ጭቆናና ግፍ የፈጠረዉ ህዝባዊ ብሶት ባሃገራችን ዉስጥ ከመቼዉም ጊዜ
በላይ ባሁኑ ወቅት እጅግ የጎላ በመሆኑ ከላይ የቆመ የሚመስል ግን ከስሩ የበሰበሰ አራዊታዊን ስርአት ባስቸኳይ ለመጣል ትልቅ አጋጣሚ
ይሆናል፣፣ በርግጥ እንድህ ሲባል የትግል ጉዞዉ ቀላል ነው ማለት አይደለም፣፣ምክንያቱም ወያነ ስርአት ለስልጣኑ ያሰጋኛል ብሎ ያሰበዉን
ሁሉ እንደተራበ ጅብ ከመብላት፣ የፈራቸዉን ደሞ እንዳበደ ዉሻ ከመናከስና ከማጥፋት ወደኋላ የማይሉ በመሆናቸዉ እያንዳንዱ ትግላችን በጥንቃቀ የተሞላና ዉጤት ተኮር መሆን አለበት፣፣ ዛሬ እዝህ የተሰበሰብን የነጻነት ሰባኪያኒና
የአንድነት ሃዋሪያት የሃገራችን ጉዳይ ስለሚያሳስበንና ለዉጥ ስለምንፈልግ ነዉ፣፣ ባሃገራችን የፍትህ የነጻነት፣የእኩልነትና
አንድነት ክስረት ከደረሰብን ፣ የንጹሃን ደም በየአደባባዩ እንደጎርፍ መፍሰስ ከጀመረ፣ ብሄራዊ ማንነታችን ከተዋረደ 23 አመታት አለፉ፣፣ 24 አመታት፣ ፣ ለዝሁ ክስረታችንና ለወያነ ባርነታችን
ትልቁ መንስኤ የአንድነታችን መናጋት መሆኑ ገሃድ ነዉ፣፣ አንድነት ከለለ፣ ሰላም የለም፣፣ ሰላም ከለለ ቤተሰብና ማህበረሰብ አይኖም፣፣
ማህበረሰብ ከለለ ደግሞ ሃገር አይኖርም ፣፣ ምክያቱም ቤተሰብ ማህበረሰብን ይገነባል፣ማህበረሰብ ደግሞ ሃገር ይገነባል፣፣ ሃገር ማለት በአንድ አከባቢ የሚኖር የማህበረሰብ ድምር
ነዉ፣፣ ስለዝህ ለሃገራዊ ህሊዉና ብቻ ሳይሆን ለቤተሰባዊ ህልዉናና ደህንነት ሃገራዊ አንድነት መሰረት ነዉ ማለት ነዉ፣፣ ነጻነት፣ እኩልነት፣
ዲሞክራሲ፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግናዎች ሁሉ ከአንድነት በኋላ የሚመጡ በመሆናቸዉ ከሁሉም አስቀድመን አንድነት
እንድጎ ለብት መታገል አለብን፣፣ ከልዩ ነታችን ይልቅ አንድነታችንን ማጎልበትት አለብን ምክንያቱም ሁላችንም በአንደነት መኖር ካልቻልን
ባንድነት እንጠፋለን፣፣ አንዳችን ከለላዉ ተለይተን ወደፍት መንቀሳቀስኧንችልም፣፣ ሁላችንም ወደፍት መሄድ የሚንችለዉ ባንድነታችን
ብቻ ነው፣፣ ለዚህም ምክንያቱ ማንነታችን አንድነታችን ሲሆን አንድነታችንም ኢትዮጵያዊነችን
ነዉ፣፣ ስለዚህ ማንነታችን አትዮጵያዊነታች ነው፣፣ ስለዝህም
የአማራ ኢትዮጵያ የለም፣ የኦሮም ኢትዮጵያ የለም ፣የወላይታ ፣የትግረ፣ የስዳማ ፣የአርጎባ፣የሃረር የለሎችም ኢትዮጵያ የለም፣፣ ያለዉ አንድ ኢትዮጵያ ሲሆን እኛም ኢትዮጵያዉያን ነን፣፣ ኢትዮጵያዊያንን
በመሆናችን ሁላችንም አንድ አካሎች ነን፣፣ አንድ አካሎች ነን ስንል ከስጋዊ አካላዊነት ያለፈ መንፈሳዊ አካላዊነትንና ማንነትን
አንድነት እያወራን ስለሆነ እጅግ ረቂቅ ነዉ፣፣ ያ መንፈሳዊ አንድነት
ነበር ባአባቶቻችን ዉስጥ የነበረዉ፣፣ ያ መንፈሳዊነት ነበር ጠላቶቻቸዉን አንከትክተዉ ከመረት ስር እንድቀብሩ የረዳቸዉ፣፣ እንግድህ
የአባቶ ቻችን ታርክ የሚያስተምረን ልይነቶቻችንን አጥፍተን አንድነታችንን
ማጎልበት እንዳለብን የሚያሳይ ሲሆን ይህም ዛሬ የጋራ ጠላታችን የሆነ ወያነ ከሚያደርስብን ሃገራዊ፣ህዝባዊ፣ማህበረሰባዊ፣ቤተሰባዊና ከግለሰባዊ ጥፋቶች ያድነናል፣፣ በገዛ ሃገራችን እንደሁለተኛ ዜጋ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና
ኢኮኖሚያዊ በደሎች እየፈጸሙብን፣ ስያሻቸዉ የሚያስሩን ፣የሚገርፉን፣ከቦታችን የሚያፈናቅሉንና ሃገር ጥለን እንድጠፋ የሚያደርጉን ሃገር አልባ ሰዎ ች አድርገዉናል፣፣፣በወያኔ መንግስትና በአጫፋሪዎቹ ያልተበደለ፣ግፍ
ያልደረሰበት ኢትዮጵያዊ የለም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣፣
ለነጻነት ስታገሉ ብዙ ወንድሞቻችንና፣እህቶቻችን በወያነ ዲያብሎሳዊ
ወጥመድ ስር ወድቋሉ፣፣ ለለሎች ነጻነት ብለዉ የራሳቸዉን ነጻነት ካጡ ከብዙዋች መሃከል መሪያችንና የነጻነት አባት የሆነዉ አንዳርጋቸው
ጽጌ፣ በብእራቸዉ ጫፍ የወያነን ዙፋን ያናጉ፣ ርእዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ እና ጦማሪያንና፣እነ በቀለ ገርባ ዉብሸት ታየና ለሎች ጠቅሰን የማንጨርሳቸዉ ይገኛሉ፣፣
እነዝህ እንቁ የሃገራችን ልጆች በዲያቢሎሱና ጨቋኙ ወያነ ማጎርያ
ጣቢያዎች ከቀን ወደ ቀን የተለያዩ ስቃዮ ች እየደረሱባቸዉ ይገኛል፣፣ እነዚህ ሰዎች እንደለሎች ለሆዳቸዉ አናድርም ብለዉ፣ ለለሎች
ነጻና እኩል ካልሆኑ እኛም ነጻ አይደለንም በማለት የነጻነት ተምሳለት ሆነዉ ታስሩዋሉ፣፣ እነዚህ ታላቅ የነጻነትታጋዮች
በአምባገነን ሃይል የታሰሩ ቢሆንም ስራቸዉና ለነጻነት ትግል የጣሉት መሰረትን ከሰማይ በታች ባለዉ በማንም እጅ መታሰር
ባለመቻሉ በሁላችንም ዉስጥ አለ፣፣ይህንን መሰረት የተጣለለትን የነጻነት ትግል ከዳር የማድረስ ግደታ እያንዳንዳችን ላይ ተጥሉዋል፣፣ ትግላችን፣ በስሜት የታከለ ጊዚያዊ ሳይሆ
ን ከዉስጣችን የመነጨና በፍጹም ሃይላችን የሚናከናዉነዉ እንደሁም የወያነን ዙፋን ለዘላለም የሚያፈርስ መሆ ን አለበት፣፣ ትግላችን፣የነጻነት
የፍትህ የእኩልነትንና የአንደነት ክስረት የሚመልስና ብሄራዊ አንድነትን
የሚያለመልም መሆን አለበት፣፣ ትግላችን የአንዳርጋቸው ጽጌ፣የርእዮ ት አለሙ፣የእስክንደር ነጋ ለሎ ችም ለሃገር አንደነትና ነጻነት
ስታገሉ የነበሩትን ህልም የሚያሰምር መሆን አለበት፣፣ ትግላችን የሃገርና
የህዝብ የዉርደት ጠባሳ የሚሽርና የነጻነትነት ሰባኪያኒና የአንድነት ሃዋሪያት መሆናችንን የሚያስመሰክር መሆን ፣፣በሃገራችን
ነጻነት እንደተራራ ጎልቶ እስከሚታይ ፣ እንድሁም ፍትህም፣ነጻነት፣እኩልነት እንደ ጅረት ሞልቶ እስከሚፈስ ትግላችንና መስዋእትነታችን ይቀጥላል፣፣
ነጻነትን ማንም አይሰጥህም፣ ጀግና ከሆንክ ነጻነትን በራስህ ተቀዳጅ
Facebook Nathnael
Abate
Twitter @nathysaint
http://www.ethiolion.com/Pdf/09272014seqayena-yemesewaete-ferie.pdf
http://www.assimba.org/Articles/Yetagaupc_Sikayna_Meswatenet.pdf
http://wwwfreedomstar.blogspot.no/2014/09/blog-post_29.html
http://www.ethiolion.com/Pdf/09272014seqayena-yemesewaete-ferie.pdf
http://www.assimba.org/Articles/Yetagaupc_Sikayna_Meswatenet.pdf
http://wwwfreedomstar.blogspot.no/2014/09/blog-post_29.html
No comments:
Post a Comment