Tuesday, May 20, 2014

አማራውን በሁለንተናዊ መልኩ አዳክሞ መግዛት ወይም ማጥፋት


በጌታቸው ፏፏቴ
ራስ ስሁል(ራስ ስዑል) ሚካኤል መቀመጫውን በጐንደሩ ቤተ-መንግሥት በማድረግ በሥሩ ንጉሶችን በማንገስ ከላይ ሆኖ የሚቆጣጠራት በመሳፍንቶች የምትመራና አንድ ማዕከላዊ የሆነ ግዛቷ ለተወሰነ ጊዜ ተዳክሞ የነበረች ኢትዮጵያችን ይገዛ ነበር። በኋላ በመይሳው ካሣ(አፄ ቴዎድሮስ) የተገነባ ማዕከላዊ መንግሥት ተመስርቶ እነሆ እኛ እስካለንበት ዘመን ደርሷል። የኛው ሞራልና ኢትዮጵያዊነት ወኔ ደግሞ የት እንደሚያደርሰን እናየዋለን።ወደ ራስ ስሁል ልመለስና ራስ ስሁል ሚካኤል ጨካኝና ተንኮለኛ መሆናቸውን የሚያሳይ አንዱን ንጉሥ ከምግብ ጋር መርዝ በመጨመር አንደኛውን ንጉሥ በሻሽ አሳንቀው መግደላቸውን የሚገልጽ አንድ ጹሑፍ አንብቤ ስለነበር የህወሃት ድርጅታዊ ፕሮግራም ከዚህ የተቀዳ ይሆን ? በማለት አንዳንድ የቀደምት ጸሓፍትን መመልከት እንዳለብኝ የግድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ራስ እየተባሉ ንጉሶችን ይገዙ የነበሩት ራስ ስሁል ሚካኤልና ዛሬ ህወሃት ብዙ የክልል ንጉሶችን አንግሶ የክልል ንጉሶችን እየገዛ ሕዝባችን በጭቆና መዳፍ ሥር ወድቆ መተናፈሻ ተነፍጎት ሳይ ይህን ችግር ቶሎ ነቅለን ካልጣልን እስከ ወዲያኛው ትውልዳችን መክኖ እንደሚቀር ግልጽ ማሳያ መስሎ ይታየኛል።የዘመኑ የክልል ገዥዎች ወይም መሪዎች ከህወሃት መንገድ ትንሽ ሲያፈነግጡ ምን እንደሚከተላቸው ግልጽ ሲሆን ውክልናቸው ወይም ታማኝነታቸው ላሉበት ክልልና ህዝብ ሳይሆን ለህወሃት ብቻ እንደሆነ ማሳመኛ የሚያስፈልገው አይመስለኝም።በቅርብ ወራት የሞተውን የኦሮሞ ክልል ፕሬዘዳንት ዓለማየሁ አቶምሳን ህመም ምንጭ ምን እንደሆነ በተለያየ መንገድ ያፈተለኩት ወሬዎች እንደሚነግሩን ህወሃት የራስ ስሁልን ታሪክ እንደደገመ ነው።የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ከህወሃት የተቀሰረበትን ጣት ለማስነሳት ተገንጥየ ወደ ሶማሌ ሄጀ እቀላቀላለሁ ብሎ ለጊዜው ቢያስፈራራም ነገ የሚገጥመውን በጋራ የምናየው ይሆናል። እንግዲህ ይህን ያህል ካልኩ አቅሙና ጊዜው እንዲሁም መረጃው ያላችሁ ይህን መነሻ በማድረግ ጠንከር ያለ ጹሑፍ ታስነብቡን ይሆናል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

No comments:

Post a Comment