ጉዳያችን ብሎግ
ፍርሃት የማያሰራው ነገር የለም።ኢህአዲግ በከፍተኛ የፍርሃት ማጥ ውስጥ ነው።ሁሉንም ይፈራል።አይዞህ አትፍራ ቢሉትም የሚችል አይመስልም።በሕዝብ ላይ የሰራቸው ሕዝብ የሚያውቃቸው እና የማያውቃቸው ብዙ ድብቅ ስራዎች ስላሉት የመፍራት ደረጃው ከዕለት ወደ ዕለት እየባሰበት እንጂ እየተሻለው አልሄደም። የሚደግፉትም ልያፅናኑት አልቻሉም።ከሚገባው በላይ ፍርሃት ሲያንቀጠቅጠው ሲመለከቱ እነርሱም ይብሱን ፈሩ።ብዙ የስርዓቱ ደጋፊዎች እና በሀብት የደለደሉቱ ሀገር ጥለው እየወጡ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።ይህ ደግሞ ሌላው የፍርሃት ገፅታ ነው።
የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሌሎች ሰሞኑን የተያዙት ጋዜጠኞች ምንም የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው ግን ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር ያሉ በእዚህም መስረት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ እየጠቀሱ የሃሳብ የመግለፅ መብታቸውን የተጠቀሙ፣የሚሰሩት በመንግስት መስርያቤቶች የሆነ፣የሚፅፉት አይደለም ምን በልተው ከማን ጋር ውለው እንዳደሩ መንግስት ብቻ ሳይሆን ሕዝብ የሚያውቃቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው።ከእዚህ በፊት በሃሳብ የሞገቱትን ሁሉ ”ህገ መንግስቱን እና ስርዓቱን ለመናድ የተንቀሳቀሱ” እያለ ሲያስራቸው የነበረው መንግስት ዛሬ እራሱ ህገ መንግስቱን አክብረው ሕግ እየጠቀሱ የፃፉትን በ20 ዎቹ እድሜዎች ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ”ሃገርን በውጭ ከሚኖር ድርጅት ጋር ተመሳጥረው ሊያሸብሩ” እያለ ፌዝ አይሉት ቀልድ መሰል ክስ አቅርቦ ማዕከላዊ እስር ቤት አስገባቸው።ምንም አይነት ወንጀል እንደሌለባቸው እራሱ ኢህአዲግ ያውቀዋል።ግፍ መስራት የማይሰለቸው እና በፍርሃት የተዋጠ መሆኑ ግን የእዚህ አይነቱን ተግባር እንዲቀጥልበት አድርጎታል።
”የፈሪ ዱላው አስር” እንዲሉ የኢህአዲግ አባላት ማታ ኢቲቪ ዜና ላይ የግብፅ፣የየመንን በቅርቡ ደግሞ የዩክረንን የህዝብ ንቅናቄ እያዩ በሰላም መተኛት አልቻሉም።ያ ቀፎው እንደተነካ ንብ የሚተመው ሕዝብ አንድ ቀን እኛም ላይ ይነሳል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።ለእዚህም ማስረጃው ኢቲቪ ባለፈው ሰሞን ያሳየው የዩክሬንን አመፅ የተመለከተ ፊልም መጥቀሱ ይበቃል።ፍርሃታቸውን ደግሞ እነ ሚሚ ስብሃቱ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ገብቶ እንደሚንዘፈዘፍ ሰው እየተንቀጠቀጡ ሲናገሩ ሕዝብ ታዝቦ ”ወይ ፍርሃት” ብሏል።ግንቦት 20 ስመጣ ጀግና እንደነበሩ ከሃያ ዓመት በፊት የነበሩ አሮጌ ታንኮች ያሳየናል።መለስ ብለው ደግሞ በፈስ ቡክ እና በጡመራ ፈራን ይላሉ።አጀብ ነው።
ኢህአዲግ ፈራሁ ብሎ ያሰራቸው ንፁሃን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እነማን ናቸው? የወጣቶቹን የስራ መስክ ግልፅነት እና ሙያ ተመልክታችሁ ፍረዱ።ለፈሪዎችም እዘኑላቸው።
1/ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ
ለተባበሩት መንግሥታት ዜና አገልግሎት ኢሪን ለረጅም ጊዜ የሰራ የእንግሊዝኛው ‘ፎርቹን’ ጋዜጣ አምደኛ እና ዘጋቢ
ለተባበሩት መንግሥታት ዜና አገልግሎት ኢሪን ለረጅም ጊዜ የሰራ የእንግሊዝኛው ‘ፎርቹን’ ጋዜጣ አምደኛ እና ዘጋቢ
2/ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ
አዲስ ጉዳይ መፅሄት ከፍተኛ ኤዲተር
አዲስ ጉዳይ መፅሄት ከፍተኛ ኤዲተር
3/ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ
በአካባቢ ጥበቃ የሰለጠነች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በቀድሞው ‘እንቢልታ’ ጋዜጣ ዘጋቢ
በአካባቢ ጥበቃ የሰለጠነች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በቀድሞው ‘እንቢልታ’ ጋዜጣ ዘጋቢ
4/ በፍቃዱ ኃይሉ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ፣ብሎገር እና ቅድስት ማርያም ዩንቨርስቲ በሙያው የሚሰራ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ፣ብሎገር እና ቅድስት ማርያም ዩንቨርስቲ በሙያው የሚሰራ
5/ አቤል ዋበላ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የአየር መንገዱ ‘ግራውንድ ቴክኒሻን’
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የአየር መንገዱ ‘ግራውንድ ቴክኒሻን’
6/ ማህሌት ፋንታሁን
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰራተኛ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰራተኛ
7/ አጥናፍ ብርሃኔ
የ25 ዓመት ወጣት በፌስ ቡክ ሃሳቡን የሚገልፅ በብሎጉ ላይ ሃሳቡን የገለፀ
የ25 ዓመት ወጣት በፌስ ቡክ ሃሳቡን የሚገልፅ በብሎጉ ላይ ሃሳቡን የገለፀ
8/ ናትናኤል
የ 26 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ባለሙያ፣’የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር’ አባል
የ 26 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ባለሙያ፣’የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር’ አባል
9/ ዘላለም ክብረት
የሕግ ባለሙያ፣ማስተርሱን ከሰራ ገና ሳምንታት የሆነው በአምቦ ዩንቨርስቲ የሕግ ትምህርት መምህር ናቸው።
የሕግ ባለሙያ፣ማስተርሱን ከሰራ ገና ሳምንታት የሆነው በአምቦ ዩንቨርስቲ የሕግ ትምህርት መምህር ናቸው።
ምንጭ – ከጦማርያኑ ውስጥ በውጭ ሀገር የሚገኙት እንዳልካቸው እና ሶልያና ለቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሚያዝያ 20/2006 ዓም ከሰጡት መግለጫ የተገኘ።
ጉዳያችን
ሚያዝያ 21/2006 ዓም
ሚያዝያ 21/2006 ዓም
No comments:
Post a Comment