(EMF) በመጪው እሁድ መጋቢት 28 ቀን፣ 2006 ዓ.ም. መነሻውን፤ ቀበና የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ፤ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የአዲስ አበባ አስተዳደር በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል። ሆኖም የአንድነት ፓርቲ በሰላማዊ ሰልፉ የሚቀጥልበት መሆኑን በመግለጹ የአዲስ አበባ አስተዳደር የከንቲባው ጽ/ቤት ስብስባ አድርጎ ነበር። ከብዙ ውይይት በኋላ የአዲስ አበባ አስተዳደር፤ ሰላማዊ ሰልፉን ተቀብሎ ነገር ግን ቀኑ እና “ሰላማዊ ሰልፈኛው የሚሄድበት መንገድ ይቀየር” የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ – ለአንድነት ፓርቲ ልኳል።
በዚህ ደብዳቤ… ቀደም ሲል “በባቡር ስራው ምክንያት” የሚለው ቀርቶ፤ “በህዳሴውን ግድብ ምክንያት”፤ የሚል ማሳሳቻ ሃሳብ ቀርቧል። ቀኑ እሁድ መሆኑ እና ት/ቤት እና ስራ ዝግ በመሆኑ መንገዱ ጭር የሚል መሆኑ ቢታወቅም የአዲስ አበባ አስተዳደር ግን… “ትምህርት ቤቶች እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በመንገዱ ላይ ስላሉ” የሚል ሌላ ምክንያት በማቅረብ የሰላማዊ ሰልፉ ቀን እንዲራዘም እና ቦታው እንዲቀየር በደብዳቤ ጠይቋል። በአሁኑ ሰአት የአንድነት ፓርቲ አባላት በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ውይይት ላይ ናቸው። አዲስ ነገር ካለ ይዘን እንቀርባለን።
No comments:
Post a Comment