ሕዝባዊ ተቋም ለመመስረት ሕዘባዊ መሆን ያስፈልጋል፡፡ የተቋሙን ሕዘባዊነት ለማረጋግጥ ሕዝባዊ አወቃቀር ሊኖረው ግድ ነው፡፡ የሕዝብን መሰረታዊ ጥያቄ ሊፈታ የሚችል ትልቅና ሁሉን አቀፍ አጀንዳ ወይም መርሃ-ግበር ሊኖሩት ይገባል፡፡
ተቋማት በተለይም የፖለቲካ ሕዝብን ማእከል አድርገው ካሉት ወይም በስልጣን ላይ ካለው የተሻለ እቅድና መርሃ-ግብር ነድፈው ሕዝብን ለለውጥ ማንቃት ሲችሉ እንዲሁም በሃገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እንዲሁም አስተዳደራዊ ችግሮች በመንቀስ የተሻለ አማራጭ ማቅረብ የሚችሉና የትኛውንም የህብረተሰብ ክፍል መድረስ የሚችሉ መሆን ይጥበቅባቸዋል፡፡
በሃገራችን ውስጥ ባለው የይስሙላ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በዘመነ ሕወሃት የተቋቋሙት ለቁጥር የሚታከቱ የብሔርም ሆነ የሕብረብሔር የፖለቲካ ድርጅቶች የረባ የስማቸውን ያህል ትጋት ሳይታይባቸው ሲያሻቸው በቡድን አለያም በተናጠል መግባባት አቅቷቸው የእመቧይ ካብ እየሆኑ ሕዝብን ሲያቆስሉ ሁለት አስርተ አመታት ተቆጥረዋል፡፡
አምባገነኑን ስርዓት ለማስገደድ በእቢተኝነት ከእስከ አሁኑ የተሻለ የሰላማዊ ትግል ተግባራትን ያከናወኑ የአዲሱ ትውልድ አዳዲስ ታጋዮች ትግልን እንደ ተቀላቀሉት ሁሉ ከፓርቲ ፓረቲ እየተከለሱ እየወጡና እየወረዱ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሳያመጡ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እርስት ያድረጉ አመራሮች ከአመት አመት መታየታቸው በትግሉ ላይ አሉታዊ ተፅኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡
ከዘረኛው የህውሃት ቡደን መሰሪ ተፈጥሮአዊ ባህሪ አንፃር በተናጠል ከሚደረግ ትግል ይልቅ በተደራጀ መልኩ ተቀራራቢ የፖለቲካ ፕሮግራም(መርሃ-ግብር) አላቸው ድርጅቶች ግንባር ፈጥረው እንዲታገሉና እንዲያታግሉ ከአንድነትና ከአብሮነት ጠላት ከሆነው ወያኔ በስተቀር የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጲያዊ ፍልጎት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ይሁንና በድርጅቶች በኩል ተራ ልዩነቶችን እየፈጠሩ ለውህደት መዘጋጀታቸውን ነግረውን ሳይጨርሱ ስለ መለያየታቸው በየፊናቸው ውሃ የማየቋጥር ምክንያት ሲደረድሩ መስማት ሕዝብ በድርጅቶቹ ላይ ያለውን አመኔታ አጠያያቂ ያደርገዋል፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባን በተቃዋሚው ጎራ በሚፈጠር ልዩነት ተጠቃሚው የሃገርና የሕዝብ ብቸኛ ጠላት የሆነው ዘረኛው የወያኔ ጉጅሌ ቡድን ነው፡፡ ለስርዓቱ እስኪከረፋ በሕዝብ ጫንቃ ላይ ለመንሰራፋት አሰተዋጾ ያደረጉት የሕዝብን ሃይል አስተባብረው በአንድነት ታግለው ማታገል ያልቻሉት ግለኛ የድርጅት መሪዎች መሆናቸው መዘንጋት የለበትም፡፡
ሕዝብና ሃገር በዘረኛው የህውሃት መዳፍ ከወደቀ ጀምሮ ይህ ነው የማይባል ግፍና በደል አሳልፏል እያሳለፈም ነው፡፡ በዚህ ግዜ ውስጥ የሕዝብ ጥያቄ ይዘው የተነሱ ቁርጠኛ የሕዝብ ልጆችን የኸው አመባገነን ዘረኛ ቡድን እንደ ኢሎሰ ቢንጥቀንም የነሱን እራእይ ለማሰቀጥል መሰራት ያለበትን ያህል ለመሰራቱ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ በአንፃሩ የጎላ እስቅስቃሴ ያደርጋሉ በስርዓቱም ላይ ተጽእኖ የፈጥራሉ የሚባሉት ድርጅቶች አንድም በስርዓቱ እኩይ ሴራ ሲፍተኑ አልያም በራሳቸው የውስጥ ችግር ከሃገርና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ በግለሰቦች ፍላጎት እይተዘወሩ የጋራ ጠላት የሆነውን ዘረኛውን ስርዓት ትተው እርሰ በእርሳቸው ሲላተሙ ማየትና መስማት የተልመደ ተግባር ሆኗል፡፡
ሕዝብ ድርሻውን በባለ ግዜዎች ተቀምቶ በርሃብና በእርዛት እንዲሁም የእንሰሳ ያህል ክብር ተነፍጎ ኢሰብአዊ ድርጊት እየተፈጸመበት እያለ፣ ሃገር በህውሃት ዘረኛ ቡድን ተበልታ በየአቅጣጫው ለባእዳን እጅ መንሻ በማትመተርበት በዚህ ወቅት ከመቼውም ግዜ በላይ አንድነታችንን አጠናክረን ልዩነታችንን አቻችለን ተከበራ የኖረች ሃገርን አስከብሮ ማቆየት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፡፡ በሰላማዊ ትግሉ ለውጥ መጣም አልመጣ ሕዝብ አደራጀቶና አንቅቶ ሃገር ለምትፈልገው ማንኛውም ጥሪ ማዘጋጀት አለን ከሚሉ ድርጅቶችና የድርጅት አመራሮች የሚጠበቅ ነው፡፡
መሪን ልዩ የሚያደርገው ሃገራችን እንዳለችበት ውስብስብ ጨለማ ዘመን ላይ ከሩቅ ተስፋን አሻግሮ አይቶ ማሳየት መቻሉ ነው፡፡ ሃገራችን አሁን ካለችበት ውስብስብ ጨለማ ዘመን የሚያስፈልጋት አሰተዋይና ጠንካራ ከራሱ ዝናና ክብር ይልቅ የሃገርና የሕዝብ ዘንን ክብር የሚያስቀድም መሪ ነው፡፡ አሁን ባለንበት አስቸጋሪ ወቅት ይህንን ክህሎት ተላበሰናል የምትሉ ሃገራችውን አስቀድሙ ሞክራችሁ ያልትሳካላችሁ ሳያስነውራችው አቅምና ብስለት ላለው አሳለፋችሁ ስጡ ሃገርና ሕዝብ መውደድ ማለት በእውር ድንብር ያለ ለውጥ መዳከር ሳይሆን ከራስ በላይ ለሃገርና ለሕዝብ ማሰብ ነው፡፡
ኢትዮጲያ በክብር ለዘላልም ትኑር!
No comments:
Post a Comment