የሳንሆዜ ሀገር ወዳዶች ግብረሃይል
እራሱን የአባይ ግድብ ካዉንስል ብሎ የሚጠራው የወያኔ ስርጎ ገቦች እና የባንዳወች ቡድን ለወራት ለወያኔ ቱባ ባለስልጣናት እጅ መንሻ የሚሆን ገንዘብ የማግኛ ዘዴ ላይ መዶለት እንደጀመረ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ወዲያውኑ ውጥኑን ስላወቅን በመሃከላቸው ሰርጎ በመግባት እያንዳንዶን እቅዳቸውን ስንከታተል ቆይተናል። የሴራው ዋንኛ የባንዳነት ሚና ተጫዋቾች ቀድሞውንም ለወራሪው የኢጣልያ ጦር እንቁላል አቀባይ ከነበሩ ቤተስብ የበቀሉ መሆናቸውን ስንረዳ ደግሞ ልባችን በሃዘን ደምቶል።በጣሊያን ወረራ ዘመን ድልድይና ህንጻ በመሰራቱ ወራሪው ጦር ይግዛን ያላለውን እና ነጻነቱን ያስቀዳመውን ህዝባችን ዛሬ የወያኔ ደናቁርት ካድሬዎች በህዝብ ጠኔ የትላልቅ ህንጻ ባለቤት እና የባለዘመናዊ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆናችው ያደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ፤ ላለፉት ሃያሶስት አመታት የህዝባችን ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ማምራቱ እየታወቀ ‘’ልማታዊ’’ የሚል ጭምብል ለብሰው ለማደናገር መሞከራቸውን ከጅምሩ በቁጭት ተከታትለናል።
ሴራው ወደ ተግባር የሚለወጥበት እለት እንደደረስም በከተማው የምንኖር ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖት፤ቋንቋ እና የብሄር ልዩነት ሳይከፋፍለን የእምነት እዳ የሆነውን እና በቃልኪዳን የወረስነውን ስንደቃችንን በማንገብ በቦታው ተገኝተን ካሃዲዎችን ተቃውመናል። ካአባይ በፈት ስብአዊ መብትን መገደብ ይገደብ ፤ ወያኔ ከፋፋይ ነው ፤ ወያኔ ህዝባዊ ውክልና የለውም፤ አላግባብ የታስሩ የሃይማኖት እና የፖለቲካ እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፤ ሌሎችንም መፈክሮች በማሰማት እና መዝሙሮችን በመዘመር የተነቃቃ እና የሚያስደንቅ ወኔ የተላበስ ጨዋነታችን አሳይተናል።
በሃገር ወዳዱ ተቃዋሚ ወኔ ልባቸው የራደው የወያኔ ጀሌዎች ባለ አራት ስኮድ የፖሊስ ሃይል እና ከአስር በላይ የግል ጸጥታ ስራተኞች በማስመጣት ግቢውን ለማጠር ቢሞክሩም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን የተላበሰው ተቃዋሚ ሃገር ወዳድ ለጸጥታ ሰራተኞች ህግ አክባረነቱን በማሳየት መብቱን ግን ሳይነጠቅ ድምጹን አሰምቶል። ተቃወሞውን ከሰአት በሆላ በስምንት ሰአት ግድም የጀመረው ሃገር ወዳድ እስክ ምሽቱ ሁለት ስአት በቦታው የተገኘ ሲሆን ጨለማን ተገን አድርገው ከገቡ ባንዳዎች በተጨማሪ በወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚነት የሚታወቁ ክሃዲወች ፤ ስለ ወያኔ አንጻራዊ ግልጽነት የሌላቸው ወይንም ከወያኔ ህልፈት በፊት ድርሻቸውን መውስድ የሚፈልጉ ባእዳን ተደምረው ከ40-50 ያልበለጡ ሰዎች ተገኝተውበታል።
አዳራሹ ባዶ የመኪና ማቆሚያው ባዶ ሆኖባቸው የተርበተበቱት የወያኔ ጀሌዎች ኑልን ኑልን እያሉ የተማጥኖ ስልክ ጥሪ ሰያደርጉም ተደምጠዋል። ማየት ማመን ነው እንዲሉ በቦታው የተገኙ ሃገር ዎዳዶች ለእማኝነት ያነሶቸው ፎቶግራፎች ይህን እውነታ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ። የወያኔው አይጋ ፎረም እና ትግራይ ኦን ላይን በፎቶሾፕ ኪሳራቸውን ለመደበቅ ቢሞክሩም እውነታው ፍጹም ሌላ ነው።
እንደሚታወቀው በወያኔ አገዛዝ ጋዜጠኞች አሸባሪ በመባል ዘብጥያ ወርደዋል፤ የሃይማኖት አባቶች ሞት እና ሰደት እጣ ፈንታቸው ሆኖል፤ ገዳማት ተደፍረዋል፤ዜጎቸ በራሳቸው ሃገር ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሃብት እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን ተነፍገዋል፡ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ እናቶቸ እና እህቶቸ የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዲቀንስ ተደርጉዋል። እስር ቤቶች በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በተለይም በኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ተጨናንቋል፤ የኑሮ ውድነቱ እማይቀመስ ሆኖል፤ በምርጫ የተሸነፈው ወያኔ በጠራራ ጸሃይ ያልታጠቁ ህጻናትን በአደስ አበባ እና በሌሎች ክተሞች በግፍ ፈጅቷል። የእስልምና ጉዳይ አፈላላጊ ወገኖችን በአሸባሪነት ከሱዋል፤ በመሃከለኛው ምስራቅ ወጣት ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ ባርነት በመዳረግ በታሪካችን ታይቶ እማይታወቅ ውርደት እና የሰነልቦና ጠባሳ ጥሎብናል። በጋምቤላ ዜጎችን በማፈናቀል እና የውጪ ጉቦ ሰጭዎች ለም ቦታ እንዲይዙ አድርጎል፤ በኦጋዴን ግድያው አስገድዶ መድፈሩ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንደቀጠለ ነው፤ አልፎ ተርፎም የሃገራችን ድንበር ለሱዳን በእጅ መንሻነት ተሰጥቷል። ዛሬ ታድያ ምኑ ተቀየረና ነው ይህ ጎጠኛ ቡድን ጋር መተቃቀፍ ያስፈለገው?
በመጨረሻም በዚህ የባንዳወች ሴራ ኢትዮጵያውያን ግራ እንዳይጋቡ እና ሰልፋችውን ከወገኖቻቸው ጋር እነዲያደርጉ የጥሪ ወረቀቶቻችን ላወጣችሁልን ድህረገጾች እና በቦታው ተገኝታችሁ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችን እየገለጽን ትግላችን ይቀጥላል ወያኔም ያለጥርጥር በህዝባዊ ትግል ይገረሰሳል እንላለን። ተቃዋሞችን ልማትን ሳይሆን በልማት ስም የሚደረገውን ሙስና እና ኢፍትሃዊ የሆነ የአስተዳደር በደል መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።
ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር!!!
የሳንሆዜ ሀገር ወዳዶች ግብረሃይል::
No comments:
Post a Comment