ክፍል አንድ
1. ሳይለወጥ መለወጥ?
2. የሁለት ድጂት ውዥምብርና የፊያል ወዲህ ቅዝምዝም…ተረት
1. ሳይለወጥ መለወጥ?
ድሮ በምትለው ቃል ላይ ‘ዘን’ን ከፊት ቀጠልንባት…ዘንድሮም ሆነ…ድሮም ክፉ ተባለ ከክፉም ክፉ!!! እኛ የሰለሞን ዘር ነን አሉት ህዝቡን…እናም የሰለሞን ዘር ደግሞ ስልጣን ይገበዋል አሉት!!! አፈታሪክ መሰረት ያደረገውን ቆጠራ ተከተሉና ለዘመናት ህዝቡን ተፈናጠጡት፡፡ አረ ስዩመ እግዝአብሔር ነን ያሉም ነበሩ፡፡ የሰለሞን ዘር ቅብርጥሶ እያሉ ህዝቡን በዘበዙ…በዘበዙ…በዘበዙ… ህዝቡ ስለመብቱ ጥያቄ እንዳያነሳ ‘ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ’ ብለው ...በዛ ላይ ከሰማይ የተቀቡ አስመስለው በመስበክ አጎንብሶ እንድሄድ አስገደዱት፡፡ የሀገሬ ሰው “እንደኣለመታደል ሆኖ ከሰለሞን ዘር አልተወለደምና” በቤቱ እራሱን በራሱ ማስተዳደር ቀርቶ ወደ እስራኤል የዘር ሀረጋቸውን በአፈታሪክ በሚመዙ ዘውድ በጫኑ ገዥ መደብ ጭቆና ተጭኖበት ስሰቃይ ሰነበተ፡፡
በጉልበት የመጣውን የጣሊያን ወራሪ ኀይልን አሻፈረኝ ያለው ህዝብ ሰለሞነዊያን ነን በሚሉ ሀገር በቀል ገዥ መደቦች ተረግጦ…ተረግጦ…መጨረሻ ላይ የሰለሞናዊያን ነን ባዮች ገመድ ልበጠስ ተቃረበ፡፡ የንጉሳዊያን የዘመናት ጉዞ በስተመጨረሻ በህዝባዊ አመፅ መንኮታኮት ጀመራ፡፡ የተስፋ ጭላንጭል ታየ፡፡…ህዝቡ ለዘመናት በላዩ ላይ ከተቀያየሩ በዝባዦች ነፃ የሚወጣበት ጊዜ ተቃረበ፡፡ ብዝበዛና ስቃይ ልያበቃ!!! ስልጣን ከሰማይ ነው የተቀባነው ከሚሉ የንጉሳዊያን በዝባዥ ስርዓት በህዝባዊ አመፅ ተላቆ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመግባት ህዝቡ ተቁነጠነጠ፡፡ ግን በመሃል ሌላ ያልተሰበ ነገር ተከሰተ፡፡ አብዮቱ ተቀለበሰ፡፡ የወታደሩ ቡድን ራሱን አደራጅቶ ወደ ስልጣን ከተፍ አለ፡፡ እራሱንም ደርግ ብሎ ሰየመና እኔ ነኝ የማውቅላችሁ ለማለት ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ በዕውቀት አልባ ደመነፍሳዊ ጉዞ ህዝቡን መተግተግ ተያያዘው፡፡ ህዝቡንና ሀገሪቷን የስልጣን ቤተሙከረና ቤተመከራ አደረገ፡፡ ድፍን 17 ዓመታት ሀገርን በሚያክል ትልቅ ነገር ላይ ሙከራ ስያደርግና ህዝቡን ስያሰቃይ፤ ህዝቡን ተፈናጦና ህዝቡም ተሸክሞት ኖረ፡፡ ህዝቡ ቀን እየጠበቀ ብሸከምም ድሮ የነበረው ትግል አልቆመመ፡፡ ከ17 ዓመታት በኋላ በሙከራና ፉከራ ላይ የሰነበተው ደርግ ተሽቀንጥሮ ተጣለ፡፡ “ግንቦት 20 ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሦስት…ብሶት የወለደው…ጀግና….ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል!!!”…ተባለና ታወጃ..የሀገሬ ሰውም ድሮን ትቶ ‘ዘን’ን ከፊትለፊት ጨምሮበት ዘንድሮን ተቀበለው፡፡
የዛሬ 20 ምናምን ዓመታት የዚያን ቀን ነው የአሁኑ የዘንድሮ የጀመረው፡፡ ህዝቡ በመታደራዊ አገዛዝ ስሳቀቅ ስለከረመ ሌላ ወታደር መምጣቱን በጥርጣሬ ማየት የጀመረው ውሎሳያድር ነበር፡፡ ደርግ ዕውቀት እንደቁምጣ አጥሮበት ስንት ጥፋት ስፈጽም የተመለከተ ህዝብ ነው፡፡ ከጫካና ከበረሃ ለመጡት ደግሞ ይቺን ሀገር ማስተዳደር ምንኛ እንደሚከብዳቸው መገመት ለህዝብ አያዳግትም፡፡ ይሄ ህዝብ ከዚህም ሌላ ብዙ ብዙ ጥርጣሬዎች ነበሩት፡፡ ለምን አይጠራጠርም!!! ባይጠራጠር ነው የሚገርመው….የነበሩት አጠቃላይ በዝባዥ፤ ጨካኝ፤ አምባገነን…ነበሩ፡፡ ታዲያ እንዴት አድርጎ ነው አዲስ መጪውን ኢህአዴግን የማይጠራጠረው?
2. የሁለት ድጂት ውዥምብርና የፊያል ወዲህ ቅዝምዝም…ተረት
ደርግ 17 ዓመታት በሙከራ ላይ…ሌላ የስልጣን ሙከራ ባለተረኞች ከጫካ መጡና የረዥም ጊዜ ሙከራቸውን ጀመሩ፡፡ በፖሊትካ፤ በኢኮኖሚ፤ ወዘተ ዘርፎች ስንትና ስንት ነገሮች ከውጭ ሀገር ተቀድተው የሀገሪቷንና ህዝቡን ነባራዊ ሁኔታን ባላገናዘበ ሁኔታ በህዝቡ ላይ ተሞከረበት…ተሞክሮበት ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡ አንዴ ወደ ሶሻልሽቱ፤ አንዴ ነጭ ካፒታልዝም፤ አንዴ ልማታዊ መንግስት እየተባለ እዚህና እዛ እየተረገጠ ጉዞ ቀጠለ፡፡ በቀን ሥስት ጊዜ እንድትበሉ እናደርጋለን ተብሎ ለህዝቡ ቃል ተገባ፡፡ ቃል ተገብቶ ብጠበቅ፤ ብጠበቅ ድንቄም ነገር ሆነ፡፡ የሀገሬ ሰው የነበረውን በቀን ሁለት ጊዜ መብላቱንም እንኳ ሳይችል ቀርቶ ወደ አንድ ማውረዱም ግድ እየሆነበት መጣ፡፡ እናም ህዝቡም የኢኮኖሚ ዕድገቱ ነው ብሎ “የካሮት ዕድገትም ዕድገት ነው!!!” በሚል እሳቤ ተጽናነ፡፡ እኔ ደግሞ የዘንድሮውን ነገር ሳልስና ሳድሱን ቀያይሬ ሌላ የእንግልዝኛ ቃልም Lessን ከፍት ጨምሬበት Less Thanድሮ አልኩት፡፡
የዋጋ ግሽበቱ ሰማይ ድረስ ተተኩሶ በወረቀት ላይ እንጂ በእውን ማን ያውርደው!!! ገቢ በስርንጅ ሆኖ ወጪው በቱቦ ሆኖ እንዴት ይሆናል!!!? በዚህ ላይ የውጪ ኢንቬስትመንት ለመሳብ ስባል የሀገሪቱን ብር ዋጋ Artificial Devalue በሚመስል ሁኔታ አፈር ድሜ ማስበላት!!!...አንዳንድ ምልክቶች ደግሞ ብር ያለአግባብ በገፍ ወደ ኢኮኖሚው የተረጫ የስመስላል፡፡ እንደዚህም ሆኖ ግን ትልቁ መጠን የተወሰነ አካባቢ ይሽከረከራል፡፡ የአብዛኛው ዜጎች ገቢ ደግሞ ዝቅተኛ ነው፡፡ ገቢ በወጉ ባይጨምርም ጨመረ እንኳ ቢባል ከወጪ ጋር ካልተጣጠመ፤ ለእለት ፊጆታ እንኳ መሆን ካቃተው፤ ዜጎች ከእለት ፊጆታ አልፈው ካልቆጠቡ እንዴት ተደርጎ ነው ዜጎች ማደግ የሚችሉት? የዋጋ ግሽበቱ ኢኮኖሚ ዕድገቱን ተከትሎ የተከሰተ ነው ሲባል ከመንግስት ተደጋግሞ ይሰማል፡፡ጥሩ!!! የዋጋ ግሽበት የኢኮኖሚ ዕድገቱን ተከትሎ ልከሰት እንደምችል የዘርፉ ባለሙያዎችም ይመሰክራሉ፡፡ ግን ፈሩን የለቀቀ ግሽበት የኢኮኖሚውን ጤነኝነት ያጠራጥራል፡፡ የዋጋ ግሽበት መቆጣጠሪያ መንገዶችንም የዘርፉ ባለሙያዎቹ ከMonetary Policyና Fiscal Policy እያጣቀሱ በስፋት ያስቀምጣሉ፡፡ ዘዴዎቹ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የማይሰራ ይመስላል!!!
የሥራ አጥነቱም ከዋጋ ግሽበቱ ልክ!!! ስንት በመቶ እንደሆነ በትክክል አንደደጉቱ ሀገራት ለማስቀመጥ ያለን የሰው ሀይል በዳታ የማስቀመጡ ልምድ ስለሌለን አንችልም፡፡ በግምት በግምት ብቻ…ስለዚህ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ማየቱ ተገቢ ይሆናል፡፡ ሥራ የሌለው በአስከፊ ሁኔታ በዘ!!! የሀገሪቷ የጀርባ አጥንት ለሆነ ወጣቱ ክፍል ትልቅ ፈተነ የሆነው ለዕለት ጉረስ እንኳ የምትሆን ሥራ ማግኘት ነው፡፡ ባለሁለት ድጂት የተባለው የኢኮኖሚ ዕድገት ወጣቱን ከሥራ አጥነት ልታደግ አልተቻለውም፡፡ መፍትሄ ተብሎ በትምህርት ስርዓት ውስጥ ሥራ ፈጠራን ሳያለማምዱ በስተመጨረሻ ሥራ ፍጠሩ…ሥራ ፍጠሩ..ሥራ ፍጠሩ…የነቶሎ ቶሎ ቤት ዓይነት!!! የሥራ አጥነት እንዲህ ተባብሶ ገሚሱ ለስደት እግሩን አንስቶ ሸመጠጠ፡፡ ገሚሱ ደግሞ በችግር ተቆርፍዶ ሲያበቃ ባለሁለት ዲጂቱን በባትሪ መፈለግ ተያያዝን፡፡ ብዙ ሰው ሥራ አጥ በሆነ ቁጥር በተለይ አምራቹ ሀይል ሥራ ከፈታ በዚህ ላይ የህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ካሻቀበ መጨረሻው ምን ይሁን?
ለነገሩ ሁለት ድጂትም ቢሆን የወረቀት ላይ ቁማር ነው፡፡ አንደኛው ነገር ብዙ ጊዜ ሀገራዊ የምርት መጠን መለኪያ GDP ብቻን ነጥለው ይጠቀሙና የአንዱን ለአንዱ ቆጥረው የአንተ ያልሆነው ለአንተ ተቆጥሮ ሀብታም ሳትሆን ሀብታም ብሎ ይሰይምሃል፡፡ እናም ተቆጥሮልን ነው ወይስ ተቆጥሮብን ነው የሚባለው? ይሄ መለኪያ አጠቃላይ የአንድን ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት በተወሰነ መልኩ ከማሳየት የዘለለ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ አያሳይም ተብሎ ትችት ስቀርብበት ቆይቶ ሌሎች መለኪያዎችን ሀገራት ከጎን መጠቀም የግድ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ እናም GDP ብቻ ይዞ ውዥምብር ከመፍጠር ወደ እውነቱ መምጣትና ሌሎች መለኪያዎችንም በመጠቀም የድሆችን የኑሮ ሁኔታ በነዚያ መነፅሮች ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ መንግስታችን ጎልተው የሚታዩትን ብቻ አጉልቶ በሚያሳይ መነፅር በGDP ብቻ ከማየት እንዲሁም የተሰሩ መንገዶች፤ ሕንፃዎችና ወዘተ በተናጠል እየቆጠራ ለማሳመን ከመጣር የድሆችን የኑሮ ሁኔታን በደምብ አይቶ የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ አንደነ Gini Coefficient, Human Development Indexና ሌሎች መሰል መነፅሮችን ለምን አይጠቀምም??? የራሱንም ብቃት ለመለከት ይረደዋል፡፡ ለነገሩ በGDP ብቻም ተለክቶም ቢሆን መንግስት ሁለት ድጂት ስያስቀምጥ እንደነ World Bankና International Monetary Fund ቁጥሩን ወደታች እየጨቆኑበት መንግስታችን እየተበሳጨ Neo-Liberalist ብሎ ስዘልፋቸው መስማት የተለመደ ነው፡፡ ህዝቡን ደግሞ መንገድ ተሰራልህ፤ ውሃ ተሰራልህ፤ ትምህርት ቤት ተሰራልህ…ወዘተ የዥጎደጉድና ለማሳመን ይጥራል፡፡ እነዚህ ሁሉ አልነበሩም ይላል፡፡ ከድሮዎቹ ስርዓት ጋር ከስንትና ስንት ዓመታት በኋለ እራሱን ለማነፃፀር መሞከርም ምን የሚሉት ኑው!!! መንገድም፤ ውሃም ወዘተ ብሆኑም በህዝብ ሀብትና በብድር የተሰሩ ናቸው፡፡ ማንም አካል ስልጣል ላይ ቢሆን ኖሮ ይሄኒኑ ነው የሚያደርገው፡፡ እናም መንገድ መስረት ወዘተ ተኣምር አይደለም፡፡ ይልቁንም ተኣምር ልሆን ሚችለው የድሆች ቁጥር በጥሩ ሁኔታ ቢቀንስና ዜጎች መሰረታዊ ነገሮች ማለትም ምግብ፤ ልብስና መጠለያ እንድያገኙ ቢያድርግ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment