Monday, January 27, 2014

አብረሃ ደስታ በአዲግራት ድብደባ ተፈጸመበት


Ethiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele
አብረሃ ደስታ
(ECADF) አብረሃ ደስታ ፌስቡክን በመጠቀም ከመቀሌ (ትግራይ) በሚያሰራጫቸው ወቅታዊ መረጃዎች፣ የፖለቲካ ትንታኔዎች እና ዜናዎች በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዘንድ አብዝቶ ይታወቃል። የአረና-ትግራይ ፖለቲካ ፓርቲ አባል እንደመሆኑ ደግሞ የፓርቲውን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ይዘግባል።
ሰሞኑን እንደተለመደው ዓረና እና መድረክ በዓጋመ (አዲግራት) ጥር 18 ስለሚያካሂዱት ህዝባዊ ስብሰባ እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር፣
ዓረና መድረክ ከዓጋመ (ዓዲግራት) ህዝብ ጋር በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለመወያየት ለእሁድ ጥር 18, 2006 ዓም በዓዲግራት ህዝባዊ አዳራሽ (ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ) ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል…
የአብረሃ ቀጣይ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ በተቃዋሚዎች ህዝባዊ ስብሰባ መጥራት የተሸበሩት ህወሀቶች የስብሰባው ቀን ከመድረሱ በፊት እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ነበር፣
ዓረና ፓርቲ በዓዲግራት ከተማ ለእሁድ ከጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ጋር በተያያዘ ዛሬ ዓርብ ሁለት የዓረና አመራር አባላት (አቶ ዓምዶምና መምህር ገብረጨርቆስ) በዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ፖሊስ ታስረዋል። የታሰሩበት ምክንያት ህዝብ በስብሰባ እንዲሳተፍ ቀስቅሳችኋል የሚል ነው። ህወሓቶች በተምቤን የፈሩትን ያህል በዓጋመ ፈርተዋል። በተምቤን ተመሳሳይ የእስር ሁኔታ አጋጥሞናል። ስብሰባ ፈቅደው ስለ ስብሰባው ህዝብ እንዳይሰማ ግን ከለከሉ። ይገርማል።
በማግስቱ አብረሃ ደስታ እና ታጋይ ጓደኞቹ በህወሀት ቅጥረኛ ወንጀለኞች፣ በፖሊሶች እና በከተማው አስተዳዳሪዎች ፊት ከፍተኛ ድብደባ ተካሄደባቸው። ሁኔታውን አብረሃ እንዲህ በማለት ገልጾታል፣
We are attacked by TPLF mercenary gangsters in front of administrators and police officers in Adigrat.
ሌሎች መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ አብረሃ ደስታን ጨምሮ አቶ አሰግድ ገብረስላሴ እና አቶ አምዶም ገብረስላሴም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፣ ከድብደባው በኋላ ሁሉም ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወስደው ምርመራ የተደረገባቸው ሲሆን አቶ አሰግድ እና አቶ አምዶም ህክምና ለማግኘት ወደ ሆስፒታል መሄዳቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment