Tuesday, January 14, 2014

አሳዛኙ የትውልድ ህይወት በሳውዲ አረቢያ «ጂዛን» ከተማ!

ጂዛን እየተባለ በሚጠራ የሳውዲ አረቢያ ግዛት ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌለውን ጨምሮ ከ50 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይነገራል። የጂዛን ከተማ ሳውዲ አረቢያን ከየመን የሚያዋስን ከተማ እንደመሆኗ በባህር የሚመጡ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ሪያድ እና ጅዳ ከተማ ለማቅናት በመሸጋገሪያነት እንደሚጠቀሙባት ይነገራል።
በዚች የድንበር ከተማ አያሌ ኢትዮጵያውያን ጉዳዩ በወል በማይታወቅ ምክንያት ያለ ፍርድ ለ 4 እና 5 አመታት ታስረው የሚሰቃዩባት ከተማ መሆኗን የሚነገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ወደ ሃገር ለመመለስ ጥያቄ ያቀርቡ አያሌ ወገኖቻችንም በሪያድ የኢትዮጵያን ኤንባሲ እና ለጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እስካሁንም ምላሽ ባለማግኘቱ ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መሆኑን ይናገራሉ ። ይህ በዚህ እንዳለ ከሁሉም በላይ እስከፊ አስከፊ በለው የሚገልጹት ምንጮች ከሶስት አመት በፊት በደረሰባት ከባድ የመኪና አደጋ ከወገቧ በታች በድን «ፓራላይዘድ» እንደሆነች የሚነገርላት ኢትዮጵያዊት እህት በዚህ ከተማ ውስጥ በተለምዶ «ኦድ ደርብ » እይተባለ በሚጠራ አካባቢ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ላለፉት ሶስት አመታት የአልጋ ቁራኛ ሆና ሃገር እና ወገን አልባ ሆና ሆስፒታል ውስጥ ለመኖር መገደዷ የአብዛኛውን ወገን ልብ የነካ መሆኑን ምንጮች አክለው ይገልጻሉ ።
በተለይ ስለጉዳዩ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እና ለጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት መረጃ እንዳላቸው የሚናገሩ ወገኖች የመንግስት ባለስልጣናቱ ዝምታን መምረጣቸው ለወገን ህይወት ደንታ የሌላቸው ሃላፊነት የጎደላቸው መሆናቸውን ያሳያል ብለዋል። የተጠቀሰችው ኢትዮጵያዊት ወጣት በአካሏ ላይ ለደረሰው አስከፊ የመኪና አደጋ «ኢንሹራስ» ካሳ ሳታገኝ ይቅርታ እንዳደረገች ተድረጎ ሆስፒታል ውስጥ እንዳስፈረሞት የሚገልጹት ምንጮች ወጣቷ አደጋው ከደረሰባት ግዜ ጀምሮ ወደ ሃገር ለመግባት ያደረገችው ጥረት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ የመግንስት ዲፕሎማቶች ድጋፍ እና ትብብር ማጣት ለበለጠ ስቃይ መዳረጓን ገልጸዋል። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ከ አራት አመት በፊት ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደገባች የሚነገርላት ወጣት ከዲጃ መሓመድ ሑሴን ትውልድ እና እድገቷ በአማራ ብ\ክ\መ\የኦሮሚያ ማህበረሰብ ዞን “ደዌ” ከሚባል አካባቢ በመሆኑ ከአረብኛ እና ከኦሮምኛ ቋንቋ ውጭ መናገር እንደማትችል የሚገልጹት ምንጮች ወጣቷ በአሁኑ ግዜ በተፈጠረው አጋጣሚ ህይወቴ ሳታልፍ ከቤተሰቦቼ ጋር እንድገናኝ እርዱኝ እያለች ብትማጸንም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘች ይናገራሉ።
ይህ በዚህ አንድ ወጣት ካሊዶ ኣሕመድ የተባለ ኢትዮጵያዊ በተመሳሳይ አደጋ በጂዛን ጀነራል ሆስፒታል ያልጋ ቁራኛ ከሆነ ድፍን ሁለት ኣመት ከስድስት ወራት እንዳስቋጠረ የሚናገሩ ምንጮች ወጣቱ ፓራላይዝ ከመሆኑም በላይ አይናገርም፣ አይሰማም፣ አያይም። እጅና እግሩ ከብረት አልጋው ጋር ተያይዞ እንድሚገኝ ገልጸዋል ። ወጣቱ ለረጅም ግዜ በመተኛት በሚፈጠር የሰውነት መቆሳሰል የተነሳ ወጣቱ በተጨማሪ በህክምናው አነጋገር \በድ ሶርስ\ በተባለ መጎሳቆሉን ይናገራሉ። ወጣቱን ሳይንሳዊው ህክምና አሳስሮ ወይም በቁሙ ገንዞ እንዳሰቀመጠው የሚናገሩ እነዚሁ የአይን እማኞች የጂዛን ትራፊክ ፅ\ቤት በተደጋጋሚ ለጅዳ እና ሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ቢያሳውቁም እስካሁን ወጣቱን ማንም ያየው እንደሌለ ይናገራሉ ።
በቀርቡ ጅዳ እና በጂዛን ከተማ የሚኖሩ ከስደት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እሮሮ አስመልክቶ በተከታታይ እየዘገበ በሚገኘው በጅዳ የጀርመን ራዲዮ ድምጽ «ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ» ዘገባ የተበሳጩ በጅዳ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ጋዜጠኛውን ህገወጥ በሆነ መንገድ ወገኑንን በነጻ ለማገልገል በጸሃፊነት ተመርጦ ሲሰራ ከነበረበት ወገን ለወገን ከሚል አንድ ግዜያዊ ኮሚቴ ማገዳቸው የሚታወስ ነው።
Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ ብፌስቡክ በኩል ለጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት
Ethiopian in Saudi

No comments:

Post a Comment